cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegaciĂłn. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

𝗔𝗽𝗼sɪᴛᴏʟɪᴄ.𝗼F 𝗪ᴀʏ

#መዝሙር 40 ÷ 3 ¹.አዲስ ዝማሬ ለአምላካችን ፤ ምስጋና በአፌ ጨመረ ብዙዎች ያያሉ ይፈሩማል በእግዚአብሔርም ይታመናሉ #መዝሙር 33 ÷ 3 ³.አዲስ ቅኔም ተቀኙለት፤ በእልልታም መልካም ዝማሬ ዘምሩ.🗣️ ENY COMMENT.contact.this BØT. t.me/YE_HAWARIYAT & @Ame5_Apo

Mostrar mĂĄs
Publicaciones publicitarias
2 818
Suscriptores
+1424 horas
+397 dĂ­as
+14730 dĂ­as

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

#Apostolic_Way #የሰባኪው_አባባሎች
• ተስለህ የማትፈፅም ብትሆን ባትሳል ይሻላል • ህልም በስራ ብዛት ይታያል ፣ እንዲሁም የሰነፍ ድምፅ በቃሉ ብዛት ይሰማል • እጅግ ወይም ጥቂት ቢበላ የሰራተኛ እንቅልፍ ጣፉጭ ነው፤ የባለጠጋ ጥጋብ ግን እንቅልፍን ይከለክለዋል • ብርን የሚወድ ብርን አይጠግብም ፤ ባለጠግነትንም የሚወድድ ትርፋን አይጠግብም • በአይን ማየት በነፍስ ከመቅበዝበዝ ይሻላል • በጥበብ መብዛት ትካዜን ያበዛል ፤ እውቀትንም የሚጨምር ሃዘንን ይጨምራል • የሰው ድካም ሁሉ ለአፉ ነው ነፍሱ ግን አትጠግብም • ሰው የሰነፎቹን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሳፅ መስማት  ይሻለዋል • ሁልጊዜ ልብስህ ነጭ ይሁን ቅባትም ከስራህ አይታጣ 📖| መፅሐፈ መክብብ....|        JOIN US @Apostolic_way @Apostolic_way
Mostrar todo...
❤ 1🥰 1
#ድንቅ_መዝሙር ዘገየብኝ ብዬ የጌታዬ መምጣት ቆየብኝ ብዬ የኢየሱስ መገለጥ እስከመጨረሻው መፅናት አቅቶኝ እንቅልፌ እንቅልፍ ብሎኝ ተኝቼ እያለሁኝ አይሆንብኝ ያንተ መምጫ ሳላስብ አይድረስብኝ ያ ቀን በድንገት *2 … … … @MARANATHAWOCH @MARANATHAWOCH
Mostrar todo...
Track 5.mp36.19 MB
❤ 10👍 8🥰 4😢 2🤔 1
| < ሁል ጊዜ ሊኖሩን የሚገቡ መልካም ፍሬዎች [ ⭐️|>1ኛ ቃሉን የማስተዋል ፍሬ   .| የመንግሥትን ቃል ሰምቶ በማያስተውል ሁሉ፥ ክፉው ይመጣል በልቡ የተዘራውንም ይነጥቃል በመንገድ ዳር የተዘራው ይህ ነው። ማቴዎስ 13:19 ብዙእንሰማለን ብዙ እናቃለን ግን ካላስተዋልን በሕይወታችን ካልተገበርን የሰማነው ቃል እራሱ ይፈርድብናል። እኔ የተናገርሁት ቃል እርሱ በመጨረሻው ቀን ይፈርድበታል። ዮሐ12:48 የምለውን ተመልከት ጌታም በነገር ሁሉ ማስተዋልን ይስጥህ። 2ኛጢሞ 2:7 ለትግሥተኛ ሰው ብዙ ማስተዋል አለው ቍጡ ግን ስንፍናውን ከፍ ከፍ ያደርጋል። ምሳሌ 14:29 እነሆ ባሪያዬ በማስተዋል ያደርጋል ይከብራል ከፍ ከፍም ይላል እጅግ ታላቅም ይሆናል። ኢሳይያስ 52:13      ይቀጥላል ...... @Apostolic_Way @Apostolic_Way
Mostrar todo...
❤ 5🥰 2
THEY THAT WAIT
Wait on, wait on, wait on the Lord /3* They that wait upon the Lord Shall renew their strength They shall mount up with wings as an eagle They shall run and not grow weary They shall walk and not faint They that wait, they that wait, they that wait I’m waiting for my blessing /2* I’m waiting Lord They that wait they that wait …. Let us not grow weary in well doing I know that my season is going to come Let us not grow tired in the running I know my rewards is coming soon I will wait on you (Said I will wait on you lord) I will trust in you (I’ll trust in you with all my heart) I will wait on you (I’ll wait on you, I will) I will trust in you (Trust in you Lord with all my heart) I will wait on you (The name of the lord is a strong tower) I will trust in you (I will trust in the lord) I’m waiting for my blessing /2* I’m waiting Lord They that wait they that wait
ďťżApostolic--Media @YE_HAWARIYAT
Mostrar todo...
❤ 3🥰 2
✿TO PI C _ ራስን መግዛት     |Part two 2| በመጽሐፍ ቅዱስ እይታ ራስን መግዛት ማለት ከስጋ ሀሳብ ጋር ትግል ማድረግ ማለት ነው፡፡ እስኪ የስጋ ፍሬ የምንላቸውን እንይ፦ ዝሙት ፣ ርኩሰት፣ መዳራት ፣ ጣኦትን ማምለክ ፣ ምዋርት ፣ ጥል ፣ ክርክር ፣ ቁጣ ፣ አድመኝነት ፣ መለያየት ፣ መናፍቅነት ፣ ምቀኝነት ፣ መግደል ፣ ስካር ፣ ዘፋኝነት እነዚህ ሁሉ አንድ በአንድ ብናያቸው ራስን ባለመግዛት የሚመጡ የስጋ ፍሬዎች ናቸው፡፡ በመንፈስ ፍሬዎች ፈታኙ የትዕግል  ምዕራፍ እና ፊት ለፊት ወደ ግብግብ ከስጋ ጋር ምንገጥመው ራስን የመግዛት ወቅት ነው፡፡ ይህ ግዜ አስቸጋሪው የመንፈስ ፍሬዎች ሁሉ መለኪያነው፡፡ ለዛም ነው ራስን መግዛት ለመንፈስ ፍሬዎች መጨረሻ የሆነው፡፡ የአገልግሎታችንን ልክ የትዕግስታችንን መጠን የፍቅራችንን እና የመዋደዳችን መለኪያው ራስን መግዛት ነው፡፡ በተለይም ክርስቲያን በነገሮች ራሱን ካልገዛ አደጋ ላይ ነው፡፡ ለምሳሌ በቤተክርስቲያን ውስጥ ከወንድም ከእህቶች ጋር ባለን የአገልግሎት ግኑኝነቶች ላይ በመክሊት ፣ በተለያዩ አገልግሎቶች አለመግባባቶች ቢፈጠሩ የሃሳብ ግጭት ቢፈጠር በራሳችን ችግር ከቤተክርስቲያን ብንገፀፅ ሾለ ወንድሞች መጥፎ ወሬ ብንሰማ የዘር ልዩነት ቢኖር ፀባይን ከፀባይ ጋር እንዴት አድርገን በሰላም ማዋሃድ እንችላለን? በአለም ላይ የሚሰጠን ስፍራ በቤተክርስቲያን ባይሰጠንስ? በነዚህ እና በተለያዩ ነገሮች ራሳችንን እንደ ክርስቲያን ለመምራት #ራስን መግዛት ወሳኙ ነገር ነው፡፡ በተጨማሪ በቤተክርስቲያን ከአገልግሎታችን ትጋት የተነሳ በሚሰጠን አድናቆት ሙገሳ ከተለያዩ ሰዎች በምንሰማው ትችት ባላጠፋነው ጥፋት ብንኮነን አሁንም መለኪያችን ራስን መግዛት ነው አደራ!!!! ምን አልባት ከሰማነው ነገር እንዳንወሰድ ለእርሱ አብልጠን ልንጠነቀቅ ያስፈልጋል እንደ ቃሉ፡፡ ራስን መግዛት የክርስትናችን ህልውና ነው!! በተለይ ለአገልጋይ ህግ አለው ለዛውም ጥብቅ ሕግ ኤጲስ ቆጲስነት ለቄሶች ብቻ ነው ካልን ተሳስተናል መንግስተ ሰማይ አንድ ነች ፡፡ ምን አልባት እነሱ በብዙ ሰዎች ሊታዩ ይችሉ ይሆናል ቅድስናቸውን መጠበቃቸው እኛስ በነገስታት ንጉስ በኢየሱስ ፊት እንታያለን ስለዚህ የተፃፈው ለትምህርታችን ተፃፈ፡፡፡ 1ጢሞ 3:1
Mostrar todo...
👍 2❤ 1🥰 1
ኤጲስ ቆጲስ አገልጋይ ወይም ቢሾፕ ቄስ ማለት ሲሆን ለመሆን የሚያስፈልግ መስፈርት፦ መልካም ስራ ይመኛል ፣ የማይነቀፍ ፣ የአንዲት ምስት ባል ፣ ልከኛ ፣ #ራሱን #የሚገዛ ፣ እንደሚገባው የሚሰራ ፣ እንግዳ ተቀባይ ፣ ለማስተማር የሚበቃ ፣ የማይሰክር ፣ የማይጨቃጨቅ ነገር ግን ገር የሆነ ፣ የማይከራከር ፣ ገንዘብን የማይወድ ፣ ልጆቹን በጭምትነት ሁሉ አየገዙ የራሱን ቤት በመልካም የሚያስተዳድር፥ ራስን መግዛት ለአገልጋይ ከላይ የተዘረዘሩትን በሙሉ ለመተግበር ወሳኝ ነው፡፡ ✿ በንግግራችን..... የተለያዩ ሀጢያት በማይመስሉ ቀልዶች(ፌዝ) በአካሄዳችን ✿ በአለባበስ ✿ እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንደ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ፤ ኤፌ 5:15 ምን እንድትሰሙ ተጠበቁ ማር 4:24 አንደበትን እና ሰውነትን በሙሉ እንደ እግ/ር ቃል መምራት፡፡ ራስን መግዛት ይበጃል እንደ ክርስቲያን ስጀምር ራስን መግዛት ከስጋ ጋር ትግል እንደሆነ አውርተን ነበረ። ለምሳሌ ከቃሉ ብናይ፦ ሥጋዬን እየጓሰምኩ አስገዛለሁ                         1ቆሮ 9:27 አደብ አስይዛለሁ ማለቱ ነው ስጋዬን በጥርሴ እይዛለሁ ፣ ሕይወቴን በእጄ አኖራታለሁ። ዕዮ 13:14 ራስን መግዛት ውስጥ ፈረ እግዛብሔር አለ እግ/ርን መፍራት ጥበብ ነው ከሀጢያት መራቅ ማስተዋል ነው፡፡    እዮ 28:28 ፨መጓምጀት የሰው ሕይወት በገንዘብ ብዛት አይደለምና ተጠንቀቁ ከመጓምጀት ሁሉ ተጠበቁ አላቸው፡፡ ሉቃ 12:15 👉ራስን መግዛት ማለት    ✍ አለም ወይም የስጋ ሀሳብ ከሚያመጣቸው ነፍስን ከሚጎዱ ነገሮች መቆጠብ ማለት ነው፡፡ ✍ ከአንደበት የሚወጣውን ቃል በሙሉ በእግዚአብሔር ቃል ቀምሞ የምያንፅ ንግግር ማውራት ማለት ነው፡፡ ✍ ወንድሞችን ከሚያሰናክል ነገር የራስን ጥቅም መተው ማለት ነው፡፡ ስሜታችን ወደ ድፍረት ድፍረት ደግሞ ወደ ትዕቢት ከዛ ራሳችንን ወደማንገዛበት ከፍታ እንወጣለን፡፡ በትንሹ ያልተቀጨ አጉል ስሜት ከፍ ብሎ ከእግዚአብሔር መምሰል ይጥለናል ስለዚህ አስተዋይ ጠቢብ ሆነን እግ/ርን መፍራት ተምረን ራሳችንን እንግዛ፡፡ ኢየሱስ ሀይሉን ይስጠን !!   አሜን!!!🙏
Mostrar todo...
👍 4🥰 3❤ 2👏 2
በተለይ ለጓረምሶች ዋ !! ራሳችሁን ግዙ በወጣትነት ውስጥ ራስን መግዛት ትልቅ ሚና ይጫወታል በተለይ ለክርስቲያን ወጣት፡፡ ቀጣዩን ህይወታችንን መልክ ማስያዝ የምንችለው ራሳችንን ስንገዛ ብቻ ነው፡፡ እኔ ራሴን ባለመግዛቴ የተጓዳሁባቸው አጋጣሚዎች አሉ፡፡ እናንተስ? በሰራችሁት ስህተት ቁጭት ተሰምቷቹ ያውቃል? ብቻ ጠንቀቅ!! ራስን መግዛት ብልህነት ነው፡፡ ከጓደኞቻችን ጋር በምናወራው ወሬ በጣም ወሬ ካበዛን ምስጢራችንን እና የሰውንም ምስጢር እናወጣለን። መጎምጀት መመኘት 👉ራስን መግዛት ከሌለ በአይን የሚገባው ራሱ ያረክሰናል፡፡ 👉በአጭሩ ራስን አደብ ማስገዛት 👉ገደብ መስጠት 👉እስከዚህ ብቻ እሄዳለሁ ከዛ በቃ 👉ራስሽን ጊዢ ራስህን ግዛ!! አትሰናከል!! አታሰናክል!! ጌታ ኢየሱስ በረዳን መጠን የሱን ሕይወት ብንኖር ይሻላል፡፡ ይሁዳ እንኳ እንደሚሸጠው እያወቀም ራሱ ጥሎት እስኪሄድ እኮ፡አልነካውም፡፡ ስንቶቻችን ነን ከከሳሻችን ጋር በአንድ ማዕድ የምንቀመጥ? ስንቶቻችን ነን ስተፉብን ዝም የምንል? በድንጋይ የምንወገር? በጥፊ የምንመታ? ትህትናን እንደልብስ የለበስን ስንቶቻችን ነን? መልሱን ለእያንዳዳችን ትቼዋለው፡፡ ኢደሱስ ይርዳን !!!🙏🙏🙏
Mostrar todo...
👍 2❤ 1🥰 1
TO PI C _ ራስን መግዛት     |Part one 1| ✏️በደፈናው ራስን መግዛት ማለት ምን ማለት ነው? ✏️እርሶ ራስዎን ከምን ከምን ገዝተው ያውቃሉ? ✏️ራስን በመግዛት ምን ምን ተጠቀምክ/ሽ? ፨ራስን መግዛት የሚለውን ሀሳብ ከመጀመሬ በፊት መንፈሳዊ ባይሆንም ለትምህርታችን እንደ መንደርደሪያ ይሆነን ዘንድ አንድ ታሪክ ካነበብኩት ላካፍላቹ፤ ታሪኩ ትንሽ ያዝናናችኀል ብዬ አስባለው፡፡ ወደ ታሪኩ👇👇 አንድ በጣም የሚዋደዱ ባል እና ሚስት ነበሩ እናም ከዕለታት አንድ ቀን በጣም በትንሽ ምክንያት ይጣላሉ፡፡ የመጣላታቸው ምክንያት የማይሆን ቅነአት እና ትዕግስት ማጣት ነበረ፡፡ተጣልተውም አልቀሩም አብረው እየኖሩ አያወሩም ነበረ ማለት ተኮራርፈው ነበረ፡፡ ጥንዶቹ የተለያየ ሾል ነበራቸው፡፡ ባል በስራ ምክንያት በጣም ብዙ አገራትን ይዞራል፡፡ እና እንደተለመደው ወደ ሌላ አገር  አገር ለመሄድ ከመስሪያ ቤቱ ጋር እና ከባልደረቦቹ ጋር ለሊት ለመነሳት እና ሰሪቪስ መኪና መነሻ ሰአት ተነጋግሮ ወደ ቤቱ ይመለሳል፡፡ ሁሌ ባል ሾል ስለሚበዛበት ዕረፍት ስለሚያጣ ከተኛ ቶሎ አይነቃም ነበርና ሁል ጊዜ ከእንቅልፉ የምትቀሰቅሰው ሚስቱ ነበረች፡፡ እና እሄኛው ፊልድ እሱ መቅረት የሌለበት በዋናነት እሱን የሚመለከት ነበረና ማርፈድ እንደሌለበት ከመስሪያ ቤቱ ባልደረቦች በጥብቅ ተነግሮታል፡፡ ነገር ግን ቀስቃሹ እና እሱ ተጣልተው ግራ ገብቶታል፡፡ ሆኖም አንድ ነገር ትዝ ይለዋል እሱም ለሚስቱ ደብዳቤ ወረቀት ላይ በፅሁፍ ለማስቀመጥ፤ አስቦ ብቻ አልቀረም በምትተኛበት አልጋ አጠገብ "ጠዋት 12 ሰአት መኪና እንዳያመልጠኝ ቀስቂሺኝ" ብሎ ፅፎ እሷ በምታይበት ቦታ ያስቀምጥላትና ይተኛል፡፡ እርሷ ለመተኛት ወደ አልጋዋ ስትመጣ ወረቀቱን ታገኝና አንብባ ትተኛለች እናም ልክ 12 ሰአት ላይ ተነስታ እንዳትቀሰቅሰው ጨንቋታል ተኮራርፈዋል፡፡ እሷም እንደ እሱ ወረቀት አውጥታ በሚነሳበት ቦታ በፅሁፍ ፅፋ አስቀምጣ ትተኛለች፡፡ ባል ቆይቶ ከእንቅልፉ ሲነቃ ነግቷል፡፡ በሚስቱ በጣም ተናዶ ሲነሳ ወረቀት እፊቱ ተቀምጧል ስያየው "ተነስ ሰአት ደርሷል" የሚል ነበር፡፡ ነገር ግን ወደ ጉዞው እንዳይሄድ ሚጠቀመው መኪና አልነበረም ረጅም መንገድ ስለነበረ በቀን አንድ ጊዜ ብቻ ነበረ መኪና የሚገኘው፡፡ ከዚህ ታሪክ በጣም ብዙ ነገር እንረዳለን ብዬ ተስፋ አደርጋለው፡፡ ፨ራስን የመግዛት ችግር ፨ትእግስት የማጣት ችግር ፨ይቅርታ የማጣት ችግር ብዙ ማለት ይቻላል፡፡ነገር ግን ራስን መግዛት አላማው ከፊት ያለ ነገር በጎ እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡ ትዕግስት በማጣት የምናጣውን ጊዜ ገንዘብ ሰው እና ብዙ ነገር ራሳችንን ገዝተን ብሆን ከዛች ቀላል ወይም ለስጋ ከባድ ከሚመስል ስሜት እራሳችንን ገዝተን ከወጣን እና ካመለጥን የምናጣቸውን ነገሮች ልናተርፍ ልንታደግ እንችላለን፡፡ የራስ ሰላም ከምንም በላይ ይመስለኛል ራሳችንን ባለመግዛታችን ምክንያት በተለያዩ ነገሮች የራሳችንን ሰላም እናጣለን፡፡ ፨ለምሳሌ በምንወስናቸው ውሳኔዎች ራሳችንን ባለመቆጣጠር ውስጥ ባለ ጥል ከብዙ ሰዎች እና ከራስ ከተፈጥሮም ጋር መጋጨት ፤ የሚገርመው ራስን አለመግዛት ኃላ ኃላው ቁጭት ያስከትላል
Mostrar todo...
👍 2🥰 2❤ 1
Mostrar todo...
Apostolic | ይህሄማ ለአንተ |Church of Kenya ACIFK

ለማንኛው Comment| ለመስጠጥ እኛ ደግሞ Accepted ነን ደግሞ የታላግራም ቻናሊችንን Join &Sher forward እንድታደርጉ.!! በእግዚአብሔር ፍቅር ልንጠይቃቹሁ ወደድን አሁን link Telegram Chennal @YE_HAWARIYAT

🥰 5❤ 2👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
Apostolic | Church of Kenya +ACIFK 🎙️ይሄማ ለአንተ ! ስያንስህ በዚህ Link 👇🏾 See https://www.youtube.com/@ANDI_AMLAK
Mostrar todo...
🥰 3👍 2❤ 2
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sĂłlo permite el anĂĄlisis de 5 canales. Para obtener mĂĄs, elige otro plan.