cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

የደጉ ሳምራዊ መልካምነት®

ይህ ትክክለኛ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት የቴሌግራም ቻናል ነው:: (በመ/ር ሲራክ ሰሎሞን) በዚህ የቴሌግራም ቻናል:- ➮አስተማሪ እና መንፈሳዊ ፅሁፎችን ➮የቅዱሳን ገድላት ➮ መዝሙሮችን ➮መንፈሳዊ ትምህሮቶችን ያገኛሉ። የመወያያ ግሩፕ: https://t.me/+QKiTJYGJvYpmNWM0 የዚህ ግሩፕ ዓላማ ለበጎ ምግባር ቃለ እግዚአብሔርን መማማር ነዉ::

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
721
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
+230 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

+ ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል + ንጉሥ ሕዝቅያስ በጠና ታምሞ ተኝቶአል::  ነቢዩ ኢሳይያስ ሊጠይቀው መጣ:: ሆኖም እንደ ልማዱ እግዚአብሔር ይማርህ አላለውም:: ለጆሮ የሚከብድ  ቃል ጥሎበት ወጣ:: "ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል!" ነቢዩ ይህንን ብሎት ከወጣ በኁላ ሕዝቅያስ ወደ ግድግዳው ዞሮ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ:: አምላኩ በንግግር ብዛት የሚሰማ አምላክ አይደለምና ፊቱን ወደ መቅደሱ አቅጣጫ አዙሮ አለቀሰ::  ከጥቂት ደቂቃ በኁዋላ ነቢዩ ኢሳይያስ ሌላ መልእክት ይዞ ተመለሰ:: እግዚአብሔር እንዲህ ይላል :- ጸሎትህን ሰምቻለሁ ዕንባህን አይቻለሁ በዕድሜህ ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እጨምራለሁ" (ኢሳ 38:5) ሕዝቅያስ ቤትህን አስተካክል ከተባለ በኁዋላ ፊቱን አዙሮ ከማልቀስ በቀር ምንም አላደረገም:: ሕዝቅያስ ሆይ ከአልጋህ ሳትወርድ ያስተካከልከው ቤት ምን ዓይነት ቤት ነው? ለባሪያዎችህ መመሪያ ሳትሠጥ የምታስተካክለው ቤትስ እንዴት ያለ ነው? በደቂቃዎች ውስጥ ትሞታለህ ከተባልክ በኁዋላ ዐሥራ አምስት ዓመት ያስጨመረልህ ምን ዓይነት ማስተካከያ አድርገህ ነው? ለእኛም ንገረንና ዕድሜ እናስጨምር:: ሕዝቅያስ ከአልጋው ሳይነሣ ያስተካከለው ቤቱ ልቡ ነበር:: ልብህን ካስተካከልህ ቤትህ ይስተካከላል:: እግዚአብሔር እንደሆን ትሞታለህ ቢልህም መሞትህን አይፈልግም:: እርሱ ካንተ ጋር ጸብ የለውም:: "በውኑ ኃጢአተኛ ይሞት ዘንድ እፈቅዳለሁን? ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ከመንገዱስ ይመለስና በሕይወት ይኖር ዘንድ አይደለምን?" ይላል መሐሪው (ሕዝ 18:23) እርሱ ትሞታለህ የሚልህ መኖርህን ፈልጎ ነው:: አንዴ ብያለሁ ብሎ አይጨክንብህም:: በንስሓ ተመለስ እንጂ ምሬሃለሁ ለማለት ይቸኩላል:: አሁን ትሞታለህ ብዬው አሁን ትድናለህ ብለው ይንቀኛል ሳይል ተመልሶ ይምርሃል:: ኃጢአትህንም ወደ ጥልቁ ይጥለዋል:: በጎ እንድትሠራም ዕድሜ ይጨምርልሃል:: አንተ ብቻ ተመለስና አሁኑኑ ንስሓ ግባ:: ከበደል አልጋ ጋር ያጣበቀህን ፈተናም ድል መንሻው ጊዜ አሁን ነው:: ሕዝቅያስ በደቂቃ ዕንባ ምሕረት አግኝቶ ዕድሜ ካስጨመረ በዐቢይ ጾም ሙሉ የሚያለቅስ ምን ያህል ዕድሜ ያገኝ ይሆን? ወዳጄ አንተም ተነሣና በዚህ ወር ቤትህን አስተካክል:: እንደ ሕዝቅያስ ፈጣሪህ ይጠብቅሃል:: የተቀየምከውን ይቅር በል  የበደልከውን ካስ የሚበቀልህን የማይተኛ ጠላትህን ዲያቢሎስ ተበቀለው:: የዐቢይ ጾም የወንጌል ምንባብ ስለ ዲያቢሎስ ፈተና ሦስቱ ወንጌላት የተናገሩትን ስናስተውል ሦስት ዓይነት ጥቅሶች እናገኛለን:: አርባ ቀን ከዲያብሎስ ተፈተነ። (ሉቃ 4:2) በምድረ በዳም ከሰይጣን እየተፈተነ አርባ ቀን ሰነበተ (ማር 1:13) የሚሉት ቃላት ጌታችን ዐርባውንም ቀን መፈተኑን ያሳያሉ:: አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ በኋላ ተራበ። ፈታኝም ቀርቦ እንዲህ አለው (ማቴ 4:2) የሚለው ደግሞ ከጾሙ በኁዋላ የቀረቡለትን ሦስት ፈተናዎች የሚያሳይ ነው:: ሦስተኛው ጥቅስ ደግሞ ከተፈተነ በኁዋላ ያለው ሲሆን ዲያቢሎስም ፈተናውን ሁሉ ከጨረሰ በኋላ እስከ ጊዜው ከእርሱ ተለየ። (ሉቃ 4:13) ይላል:: ዲያቢሎስ ፈተናውን ቢጨርስም የሚተወው ለጊዜው እንጂ መፈተኑን አያቆምም::  የዲያቢሎስ ፈተና ስልቱ ይቀያየራል እንጂ ይቀጥላል:: ዐቢይ ጾም ዲያቢሎስ ድል የተደረገበት የጦር ዐውድማ ነው:: በዚህ ወራት ድል ያላደረግነውን ፈተና በሌላ ጊዜ አናደርገውም:: ሰነፍ ገበሬ በሰኔ ይሞታል እንደሚባለው በዐቢይ ጾም የተኛ ክርስቲያን መቼም አይነቃም:: ከነስሙ ሁዳዴ (ሰፊ እርሻዬ) የምንለው ይህ ጾም ለነፍሳችን ብዙ ዘር የምንዘራበት አጋንንት መድረሻ የሚያጡበት ጾም ነው:: በዐቢይ ጾም ያልተገራ አንደበት መቼም አይገራም:: በዐቢይ ጾም ያልተፈወሰ ቂም መቼም አይፈወስም:: ጌታችን በወንጌል አንዴ ወደ እሳት አንዴ ወደ ውኃ የሚጥል ጋኔን ያለበትን ልጅ ሲፈውስ "ይህ ዓይነቱ ጋኔን ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም" ብሎ ነበር:: ሀገራችንን አንዴ ወደ እሳት አንዴ ወደ ውኃ የሚጥላት የጥላቻ ጋኔንም ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም:: ወዳጄ ከቁስልህ የምትፈወስበት ወር እንደደረሰ ዕወቅ:: አንተስ ብትሆን ልትላቀቀው እየፈለግህ ያቃተህ ክፉ ልማድ የለብህም:: እንደ ቅዱስ ጳውሎስ "የምፈልገውን መልካም ነገር አላደርግም የማልፈልገውን ክፉ ነገር ግን አደርጋለሁ:: ምንኛ ጎስቋላ ለዚህ ለሞት ከተሠጠ ሰውነት ማን ያድነኛል?" ብለህ ምርር እንድትል ያደረገህ ኃጢአት የለም? እንግዲያውስ እወቀው:: ይህ ዓይነቱ ወገን ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም:: ይህ ጾም ቁስል የሚሽርበት ጾም ነው:: ይህ ጾም ሸክም ማራገፊያ ጾም ነው:: እንደ ሕዝቅያስ በዚህ ወር ቤትህን በንስሓ አስተካክል:: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
Mostrar todo...
✞አድርገኽልኛልና✞ አድርገህልኛልና በቸርነትህ አመሰግንሃለሁ እልል ለዓለም/2/ አማኑኤል እገዛልሃለሁ ለዘላለም ቀኑ ጨልሞብኝ ዙሪያው ገደል ሆኖ ይችግር አረንቋ ፊቴ ተደቅኖ እረዳት ያጣሁኝ በመሰለኝ ጊዜ ፈፅሞ አራክልኝ የልቤን ትካዘዜ       አዝ= = = = = አምላኬ ጉልበቴ ኃይሌ መመኪያዬ ጠላት ማሳፈሪያ የእምነት ጋሻዬ እንደማትተወኝ አሁን አውቄአለሁ ካለኝ ነገር ሁሉ ባንተ ታምኛለሁ       አዝ= = = = = ጥቂቷን አብዝተህ ለምትመግብ ጌታ የምመልስልህ በላገኝ ስጦታ በቀንም በለሊት ሁሌ የሚያበራ መንክር ለባህሪ እፁብ ያንተ ሥራ       አዝ= = = = = አምላክ ሆይ ምስጋና ላንተ ይገባሃል ለምስኪኗ ጎጆ በረከት ሰጥተሃል ድሃ ነኝ አልልም ሐብቴ አንተ ነህና ማሰሮዬ ሞልቷል ላይጎል እንደና
Mostrar todo...
"#የትናንት ሊቃውንት አባቶቻችን ጦም እያደሩ  የጠበቋትን ቤተ ክርስቲያን እኛ እየበላን አሳልፈን መስጠት አይገባም"  ብፁዕ አቡነ አብርሃም ከ200 በላይ የአብነት መምህራን የተሳተፉበት የምክክር ጉባኤ በመንበረ ፓትርያርክ ጽርሐ ተዋሕዶ እየተካሔደ ይገኛል። ግንቦት ፲፭/፳፻፲፮ ዓ/ም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ በመንበረ ፓትርያርክ ትምህርትና ማሰልጠኛ መምሪያ ከሊቃውንት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው  ሀገር አቀፍ የምክክርና የውይይት ጉባኤ ማካሔዱን ጀምሯል። በመርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ የበላይ ሊቀ ጳጳስ፣የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያ ሐላፊዎች  ከየ አህጉረ ስብከቱ የመጡ ከ200 በላይ ሊቃውንት ቤተ ክርስቲያንና የጉባኤ መምህራን  ተገኝተዋል። ጉባኤው በጸሎተ ወንጌል የተጀመረ ሲሆን በማስከተልም የደብረ ምሕረት ሰአሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያምና ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል ሊቃውንት "ያሬድ ካህኑ ለእግዚአብሔር ትርድአነ ነዐ በህየ መካኑ ያሬድ ነዐ ትርድአነ" የሚለውን ወረብ አቅርበዋል። የመምሪያው ሐላፊ  መልአከ መዊዕ ሳሙኤል እሸቱ ሊቃውንቱ ከየጉባኤ ቤቱ የመጡትን ሊቃውንት አስተዋውቀዋል። በዚህም የድጓ፣ የዝማሬ መዋስዕት ፣ የቅኔ ፣የአቋቋም ፣ የሐዲሳትና የብሉያት  መጻሕፍት ትርጓሜ መምህራን መሆናቸው ተገልጿል። መልአከ መዊዕ ሳሙኤል እሸቱ ለጉባኤ መሳካት የበኩሉን ድርሻ የተወጡትን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የትምህርትና ስልጠና ዋና ክፍልንና ሌሎችን አመስግነዋል። አክለውም ጉባኤ  ሁልጊዜ በየዓመቱ ከግንቦቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት ከመጀመሩ በፊት ጉባኤ እንዲዘጋጅና እውቅና እንዲሰጠው ጥያቄ አቅርበዋል። የእንኳን ደህና መጣችሁ አባታዊ መልእክት ያስተላለፉት ብፁዕ አቡነ አብርሃም  ብዙ ኪሎ ሜትሮችን አልፈው ወቅታዊ የሀገሪቱ ሁኔታ ተቋቁመው   የተገኙትን ሊቃውንት እንኳን ደህና መጣችሁ ያሉ ሲሆን የምክክር ጉባኤውን  ያሰናደውን የትምህርት ማሰልጠኛ መምሪያ  አመስግነዋል። ብፁዕነታቸው  አክለውም ለዘመናት የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አባቶች ቤተ ክርስቲያናችንን በበላይነት በሚመሩበት ጊዜ  "አማኙን ከሀገሩ" "እምነቱን ከታሪኩ" ጠብቀው ያቆዩ ሊቃውንት መሆናቸውን በማስታወስ አሁንም የበኩላችሁን የሊቅነት ድርሻችሁን በመወጣት ቤተ ክርስቲያናችንን ልታስከብሩ ይገባል ብለዋል። በዚህ ዘመን በሕይወት የሚያገለግሉትን ሊቃውንት በኑሯቸውም ልናስባቸውና የት አሉ ልንል ይገባልም ብለዋል። "የትናንት ሊቃውንት አባቶቻችን ጦም እያደሩ  የጠበቋትን ቤተ ክርስቲያን እኛ እየበላን አሳልፈን መስጠት አይገባም" ሲሉ ገልጸዋል። ስለሆነም ሊቅነትን ከቤተ ክርስቲያን ተልእኮ ውጤት ጋር በማጣመር ዘመኑን የዋጀና ትውልዱን የሚያተርፍ  አገልግሎት እንድታገለግሉ ወደፊት መምጣት ይገባችኋል ብለዋል።   ጉባኤው ለሁለት ቀናት የሚቆይ እንደሆነ ከወጣው መርሐ ግብር ለማወቅ ተችሏል። #ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን በአማን ተንሥአ እሙታን ምንጭ:- የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ
Mostrar todo...
#ከ60 ዓመታት በላይ ወንበር ዘርግተው ደቀ መዛሙርትን ያፈሩት ታላቁ ሊቅ የኔታ #ኅሩይ ዓለማየሁ ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፉ። በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት በደብረ ማርቆስ ከተማ የጽርሐ ጽዮን አብማ ማርያም ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን የድጓ መምህርና ለ65 ዓመታት ወንበር ዘርግተው በርካታ ደቀ መዛሙርትን ያፈሩት የኔታ ኅሩይ ዓለማየሁ ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፉ። ሊቀ የኔታ ኅሩይ ዓለማየሁ ከ፲፱፻፶፩ ዓ.ም እስከ ፳፻፲፮ ዓ.ም ድረስ ጉባኤ ዘርግተውና አስፍተው ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን በርካታ ደቀ መዛሙርትን ያፈሩና ማኅሌታዊው የድጓ፣ የምዕራፍና ዝማሬ እንዲሁም የቅኔ ሊቅ እንደነበሩ ተገልጿል። የኔታ ኅሩይ ዓለማየሁ በተወለዱ በ፹፰ ዓመታቸው ግንቦት ፲፬/፳፻፲፮ ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉ ሲሆን ጸሎተ ፍሕታታቸውም በብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ የሀ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ መሪነት በርካታ ሊቃውንተ ጎጃምና ምዕመናን በተገኙበት በጽ/ጽ አብማ ማርያም ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተከናውኗል። ብፁዕነታቸውም በቃለ ምዕዳን ትምህርታቸው ለሊቃውንቱና ቤተሰቦቻቸው እንደገለፁት እጅግ የትህትና አባትና መምህር ለሁላቸንም አርአያ የሚሆኑ በመንፈስ ብዙዎቻችን የወለዱ መምህር ናቸውና መጽናናትን ለሁላችን ያድለን ሲሉ በመንፈስና በሥጋ ለወለዷቸው ልጆቻቸው የማጽናኛ መልዕክት አስተላልፈዋል ሲል የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሕዝብ ግንኙነት ዘግቧል። የሊቁን ነፍሳቸውን በአብርሃም በይስሐቅ በያዕቆብ ዕቅፍ ያኑርልን። #ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን በአማን ተንሥአ እሙታን #ቻናሉን_ይቀላቀሉ? https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv
Mostrar todo...
የደጉ ሳምራዊ መልካምነት®

ይህ ትክክለኛ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት የቴሌግራም ቻናል ነው:: (በመ/ር ሲራክ ሰሎሞን) በዚህ የቴሌግራም ቻናል:- ➮አስተማሪ እና መንፈሳዊ ፅሁፎችን ➮የቅዱሳን ገድላት ➮ መዝሙሮችን ➮መንፈሳዊ ትምህሮቶችን ያገኛሉ። የመወያያ ግሩፕ:

https://t.me/+QKiTJYGJvYpmNWM0

የዚህ ግሩፕ ዓላማ ለበጎ ምግባር ቃለ እግዚአብሔርን መማማር ነዉ::

Photo unavailableShow in Telegram
#ከ60 ዓመታት በላይ ወንበር ዘርግተው ደቀ መዛሙርትን ያፈሩት ታላቁ ሊቅ የኔታ #ኅሩይ ዓለማየሁ ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፉ።
Mostrar todo...
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ_ከቅዱሳን_ባሕታውያ_ጋር በአንድ ወቅት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ፡-ከዕለታት አንድ ቀን በሀገረ ስብከቴ ሥር በነበሩ በሜዲትራኒያን ባሕር በሚገኙ ደሴቶች ውስጥ የሚኖሩ ምእመናንን ለመጎብኘት አሰብሁ፡፡ ከእኔ ጋር ቀሳውስትንና ዲያቆናትን አስከትዬ በጀልባ ተሳፍሬ ወደ ቆጵሮስ ደሴት ተጓዝሁ፡፡ በደሴቱ ውስጥ ስንዘዋወር የሰው ዱካ ብንመለከትም ምንም ሰው ማየት አልቻልንም ነበር፡፡ በአሸዋው ላይ ታትሞ የነበረውን የሰው ዱካ ተከትለን ስንጓዝ ካልተፈለፈሉ ዐለቶች የተሠራ ቤተ ክርስቲያን የሚመስል ዋሻ ላይ ደረስን፡፡ ዋሻው በርም ሆነ መስኮት የለውም፡፡ ወደ ውስጥ ስንገባ ልክ እንደ ሰባቱ ደማቅ ከዋክብት እጅግ በጣም አንጸባራቂ ብርሃን ቆመው ከሚጸልዩ ሰባት አባቶች ዘንድ ሲወጣ ተመለከትን፡፡ እኛም ከእነርሱ ጋር ለመጸለይ ባለንበት ቆምን። አባቶች ጸሎታቸውን ከጨረሱ በኋላ ወደ እኛ ዞሩና በፊቴ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ሰገዱ። በመቀጠልም ሰላምታ ሰጡን፡፡ እኔ ዮሐንስም ‘እኔ አባታችሁና ፓትርያርካችሁ ዮሐንስ ነኝ’ አልኳቸው፡፡ ቅዱሳኑ እንደገና ራሳቸውን ዝቅ አድርገው በፊቴ ሰገዱ እና እኔን ደካማውን እንዲህ አሉኝ፡- “የምንወደው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንድትባርከንና እኛም አንተን በማየት እንድንበረታ ወደዚህ አመጣህ” አሉ። እኔም “እባካችሁ ታሪካችሁን ንገሩኝ” አልኋቸው፡፡ ሰባቱ አባቶችም “ከብዙ ዓመታት በፊት ሰባታችንም ከቍስጥንጥንያ ወጥተን በአንድነት ተሰባስበን ሕይወታችንን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምና በአምልኮ ብቻ ለማሳለፍ ወደዚህ ደሴት መጣን፡፡ ከዚህ ደሴት በደረስንበት ዕለት ከባሕሩ ከሚመጣው አስቸጋሪ ነፋስ ራሳችንን ለመከላከል ዋሻዎችን ለመገንባት ዐለቶችን ሰበሰብን፤ በሁለተኛው ቀን ደግሞ ይህን ቤተ ክርስቲያን መሥራት ጀመርን፡፡ በዐለቶች መካከል ከሚበቅለው ሣር እንበላለን፤ ውኃም ከባሕሩ እንጠጣለን፡፡ ቤተ ክርስቲያኑን የከበቡትን እነዚህን የአሸዋ ክምሮች ለማስወገድ ፈልገን ነበር፤ ግን አእምሯችንና አሳባችን ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ስለተያዘ ጊዜ አጣን” በማለት ታሪካቸውን ነገሩኝ። እኔም “መንፈሳዊ አባታችሁ የት ነው?” ብዬ ጠየቅኋቸው፡፡ ይህን ጥያቄ ከመጠየቄ ወዲያውኑ አንድ ሽማግሌ በትሩን ተደግፎ ወደ እኔ ቀረብ አለና “እኔ የአንተ አገልጋይ ነኝ” አለኝ፡፡ አረጋዊው ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል ሁኔታ ራቁቱን ነበረና “ሰውነትህን የምትሸፍንበት ትንሽ ልብስ ትፈልጋለህ?” ስለው እሱም “ጌታ ከክረምቱ ቅዝቃዜ፣ ከበጋው ሙቀት ይከላከልልናል፤ ይጠብቀናልም” በማለት መለሰልኝ፡፡ “ምግብ ያስፈልጋችኋል?” ብዬ ስጠይቀው እርሱም “የሚበቃንን ያህል ከእነዚህ ዕፅዋት እንመገባለን ከዓለም የሆነ ምንም ነገር አያስፈልገንም” በማለት መለሰልኝ፡፡ እኔም “አባቶቼ እባካችሁ ለእኔ እና ስለቤተ ክርስቲያን ደኅንነት ጸልዩ” አልሁት። የእነዚያን ቅዱሳን ባሕታውያን አባቶች በረከት ከተቀበልን በኋላ ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለም ምሥጋና የሚገባውን የምንወደውን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እያመሰገንን ወደ መጣንበት ተመለስን” ይለናል ቅዱሱ አባታችን ዮሐንስ አፈ ወርቅ። #ቻናሉን_ይቀላቀሉ? https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv
Mostrar todo...
የደጉ ሳምራዊ መልካምነት®

ይህ ትክክለኛ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት የቴሌግራም ቻናል ነው:: (በመ/ር ሲራክ ሰሎሞን) በዚህ የቴሌግራም ቻናል:- ➮አስተማሪ እና መንፈሳዊ ፅሁፎችን ➮የቅዱሳን ገድላት ➮ መዝሙሮችን ➮መንፈሳዊ ትምህሮቶችን ያገኛሉ። የመወያያ ግሩፕ:

https://t.me/+QKiTJYGJvYpmNWM0

የዚህ ግሩፕ ዓላማ ለበጎ ምግባር ቃለ እግዚአብሔርን መማማር ነዉ::

👍 3
👉ክርስቶስ ተንስአ እም ሙታን                  ✝️በዐቢይ ሀይል ወስልጣን 👉አሰሮ ለሰይጣን                   ✝️አግአዞ ለአዳም 👉ሰላም                  ✝️እምይዝኤሰ 👉ኮነ                  ✝️ፍሰሃ ወሰላም #ወደ_አባቴ_አላረኩምና_አትንኪኝ ✍🏾 ማርያም መቅደላዊት ግን ሽቱ ይዛ ጎህ ሳይቀድ ሄደች ሌሎችም ተከትለዋት ከመቃብር በደረሱ ጊዜ የጌታችንን ቅዱስ ሥጋ አጡት ‹‹ወስደውታል›› እያሉ ሲያለቅሱ መልአክ ‹‹ ሕያውን ከሙታን መካከል ለምን ትፈልጉታላችሁ ተነስቷል። ከዚህ የለም ይልቁኑስ ገና በገሊላ ሳለ ለእናንተ እንደተናገረ አስቡ ቃሉንም አስቡ ለደቀመዛሙርቱ ንገሯቸው አላቸው ፡፡ ሉቃ 24፡1 👉ሌሎች ሲሔዱ ማርያም መቅደላዊት ግን የደረሰበትን ሳላውቅ አልሄድም ብላ ቆማ ታለቅስ ነበር ጌታችንም ከወደኋላዋ መጥቶ ‹‹ ምን ሆነሽ ታለቅሺያለሽ ›› አላት የአትክልት ጠባቂ መስሏት ‹‹ ጌታዬን አንተ ወስደኸው እንደሆነ ሽቱ እንድቀባው ያደረክበትን አሳየኝ ›› አለቸው ‹‹ ማርያም ›› ብሎ ስሟን ሲጠራት ጌታ መሆኑን አውቃ ‹‹መምህር ሆይ›› ብላ እጅ ልትነሳው ስትቀርብ ‹‹ገና ወደ አባቴ አላረኩምና አትንኪኝ ሄደሽ ለደቀመዛሙርቴ ተነሣ ብለሽ ንገሪያቸው ›› አላት። ዮሐ20፡17 ሄዳ አብስራቸዋለች ጴጥሮስና ዮሐንስ እየሮጡ መጥው መግነዙን እንጂ እሱን አላገኙትም ‹‹ በእውነት ተነስቷል ›› እያሉ ተመለሱ፡፡ 👉ሰውን ወዳጅ ኢየሱስ ክርስቶስ መቅደላዊት ማርያምን አትንኪኝ ያላት ጠልቷት ወይም ተጸይፏት አይደለም፡፡ 👉ትንሣኤውን ከሰው ልጆች ቀድማ እንድታይ የፈቀደላት ስለወደዳት ነው፡፡ #ታዲያ_ለምን_አትንኪኝ_አላት? * 3 መዓልት 3 ሌሊት በከርሰ መቃብር አድሬ እነሳለው ብሎ የተናገረውን ስለረሳች ስለ እምነቷ ማነስ ሊገስጻት ፈልጎ ነው። ለመላእክት ስለምን ታለቅሺያለሽ ሲላት ጌታዬን ወስደውታል አለች እንጂ ‹‹እንደተናገረው ተነስቷል›› አላለችም። ዮሐ 20፡11-13 👉 #አንድምበዛው ወደ ባህሪ አባቱ የሚያርግ መስሏት እግሩን ስማ ልትሰናበተው ነበር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን። የማርግበት ጊዜ ገናነውና ለመሰናበት ብለሽ አትንኪኝ ሲላት ነው። 👉#አንድምሥርዓተ ክህነትን ሲመሰርት ሴቶች ካህን መሆን ሥጋወ ደሙን መፈተት እንደማይችሉ ሥርዓት ሲሰራልን ነው። ለዚህም ማረጋገጫ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስን ግን እንዲዳስሰው የፈቀደለት ሲሆን መግደላዊት ማርያምን ግን አትንኪኝ ነው ያላት። ዮሐ 20፡26 ወዲያው ጌታ በተዘጋ ቤት እንዳሉ በማይመረመር ጥበብ በመሐከላቸው ቆሞ ‹‹ ሰላም ለክሙ ›› ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው፡፡ ምትሃት መስሏቸው ታወኩ በጦር የተወጋ ጎኑን በችንካር የተቸነከሩ እጆቹን እሮቹን አሳይቷቸው አውቀውታል። 👉መቃብሩን ሲጠብቁ የነበሩ ወታደሮች በክብር ብርሃን ተጎናጽፎ ሲነሣ አይተው ደንግጠው ወደ አይሁድ ዘንድ ሔዱና መነሳቱን የሆነውን ሁሉ ነገሯቸው፡፡ አይሁድም ‹‹ ብዙ ገንዘብ እንሰጣችኋለን ተኝተን ሳለ ደቀመዛሙርቱ ሰረቁት በሉ አሏቸው፡፡ በነግ አይሁድ ጲላጦስ ዘንድ መጥተው ‹‹ ሥጋው ተሰርቋል ጠባቂዎቹን አስጠርተህ መርምርልን ›› አሉት። 👉 ለየብቻ ከፋፍሎ ሲመረምራቸው ግማሹ ጴጥሮስና ዮሐንስ ሰረቁት ሲሉ ሌሎች ደግሞ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ሰረቁት አሉ። 👉አስራ አንዱም መጥተው ሰረቁት ያሉም ነበሩ፡፡ ጲላጦስም ወደ መቃብሩ ሄዶ ሲያይ መግነዙን አገኘው ‹‹ ደቀመዛሙርቱ ከወሰዱትማ መግነዙንም አብረው ይወስዱት ነበር ›› አለ። 👉በእነዚህ ምክንያቶች ደቀመዛሙርቱ እንዳልወሰዱት አወቀ። ‹‹ ሞትን ያጠፋ ሞትን ድል የነሣ ጌታችን ኢየሱስ ግን አይሁድን ይህን ቀን አነሣዋለሁ እንዳላቸው፡፡ በእውነት በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፡፡ 👉አንበሳ ከተኛበት ፈጥኖ እንዲነሣ ወይን ጠጥቶ የሰከረ ኃይለኛ ፈጥኖ እንዲነሣ፡፡ በመንፈስ ቅዱስና በባቱ ኃይል በራሱም ሥልጣን ፈጥኖ ተነሣ የሞት ቁራኝነትንም አጠፋ፤ ሞት ሊያዘው አይችልምና፡፡ 👉የተገነዘበትንም ልብስ ትቶ ልብሰ መንግሥቱን ለብሶ ተነሣ፡፡ በተወለደም ጊዜ የናቱን ማኅተመ ድንግልና እንዳለወጠ፡፡ 👉በትንሣኤውም የመቃብሩን ቁልፍ አልከፈተም፡፡ በተገነዘበትም ልብስ የመቶ አለቃውን ዐይን አዳነ፡፡ የሞተውንም ሰው አስነሣ፡፡ በመቃብርም ጲላጦስ በውስጡ በቀበረው ጊዜ ፊያታዊ ዘየማንን አስነሳው፡፡ 👉እሁድ ማታም ጌታችን ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ አይሁድን ስለፈሩ ተሰብስበው ወዳሉበት ከዝግ ቤት ገባ ያረጋጋቸውና ደስም ያሰኛቸው ዘንድ፡፡ 👉ጌታችን ኢየሱስም ቸር አላቸውን አትፍሩ አትደንግጡ እኔ ነኝ አላቸው፡፡ እነሱ ግን ምትሐት የታያቸው መስሏቸው ፈጽመው ፈሩ፡፡ 👉ጌታችን ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱን ምን ያስደነግጣችኋል እንደዚህ ያለ ሐሳብ በልቡናችሁ ለምን ያድራል አላቸው፡፡ እጄንም እግሬንም ዳሳችሁ እዩ፡፡ 👉ለምትሐት በኔ እንደምታዩት ሥጋ ዐጥንት የለውምና፡፡ ይህን ብሎ የተወጋ ጎኑን የተቸነከሩ እጆቹንና እግሮቹ አሳያቸው ደቀመዛሙርቱም ጌታችንን ባዩት ጊዜ ደስ አላቸው፡፡›› #ቻናሉን_ይቀላቀሉ? https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv
Mostrar todo...
የደጉ ሳምራዊ መልካምነት®

ይህ ትክክለኛ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት የቴሌግራም ቻናል ነው:: (በመ/ር ሲራክ ሰሎሞን) በዚህ የቴሌግራም ቻናል:- ➮አስተማሪ እና መንፈሳዊ ፅሁፎችን ➮የቅዱሳን ገድላት ➮ መዝሙሮችን ➮መንፈሳዊ ትምህሮቶችን ያገኛሉ። የመወያያ ግሩፕ:

https://t.me/+QKiTJYGJvYpmNWM0

የዚህ ግሩፕ ዓላማ ለበጎ ምግባር ቃለ እግዚአብሔርን መማማር ነዉ::

Photo unavailableShow in Telegram
👉ክርስቶስ ተንስአ እም ሙታን                  ✝️በዐቢይ ሀይል ወስልጣን 👉አሰሮ ለሰይጣን                   ✝️አግአዞ ለአዳም 👉ሰላም                  ✝️እምይዝኤሰ 👉ኮነ                  ✝️ፍሰሃ ወሰላም #ወደ_አባቴ_አላረኩምና_አትንኪኝ ጌታችንም ‹‹ ማርያም ›› ብሎ ስሟን ሲጠራት ጌታ መሆኑን አውቃ ‹‹መምህር ሆይ›› ብላ እጅ ልትነሳው ስትቀርብ ‹‹ገና ወደ አባቴ አላረኩምና አትንኪኝ ሄደሽ ለደቀመዛሙርቴ ተነሣ ብለሽ ንገሪያቸው ›› አላት። ዮሐ20፡17 #ቻናሉን_ይቀላቀሉ? https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv
Mostrar todo...
ወደ ኖኅ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ የገባችው እንስሳ የኖኅ መርከብ ጉዳይ በጣም አስገራሚ ከሚሆኑብኝ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች አንዱ ነው:: በዓለማችን አሁን ያሉ እንስሳት ሁሉ "ከነ ባለቤትዎ" እንዲገኙልን እንደሚባልበት ሰርግ ጥንድ ጥንድ ሆነው የገቡባት ትልቅ መርከብ ታሪክ : ዳግም ለሰው ልጆች ወላጆች ለመሆን የተመረጡ አራት ወንዶችና አራት ሴቶች ብቻ የተሳፈሩባት ትልቅ መርከብ ሁኔታ ትኩር ብሎ ላየው አስገራሚ እውነቶችን ያዘለ ነው:: ከሁሉም በላይ ግን መርከቢቱ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ መሆንዋ ብዙ ነገር እንድናስብ ያግዘናል:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ወደ ኖኅ መርከብ ተኩላ ገብቶ ሲወጣም ተኩላ ሆኖ ይወጣል:: ወደ ቤተክርስቲያን ግን ተኩላ ሆነው ገብተው በግ ሆነው የወጡ ብዙዎች ናቸው" ብሎአል:: እውነትም ቤተ ክርስቲያን ወደ እርስዋ የገቡትን መለወጥ የምትችል መርከብ ናት:: ወደ ቤተ ክርስቲያን እንደ ጅብ ሆዳም ሆነው ገብተው ጾመኞች ሆነው የወጡ አሉ:: እንደ የሌሊት ወፍ በቀን መኖር አቅቶአቸው ሌሊቱን የልባቸው ዓይን ታውሮ በኃጢአት ጨለማ ሲደናበሩ የኖሩ ሰዎች ወደ መርከቢቱ ገብተው እንደ ንስር አርቀው አጥርተው ቀኑን የሚያዩ ሆነዋል:: ቤተ ክርስቲያን ወደ እርስዋ የገቡትን የምትለውጥ መርከብ ናት:: ውኃ ወደ እርስዋ ሲገባ ጠበል ይሆናል:: አፈር ወደ እርስዋ ሲገባ እምነት (እመት) ይሆናል:: ዘይት ወደ እርስዋ ሲገባ ቅዱስ ቅባት ይሆናል:: ኅብስትና ወይን ወደ እርስዋ ሲገባ ወደ ቅዱስ ቁርባን ይለወጣል:: ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ያልተለወጠ ሰው ግን ሲገባም ጅብ ሲወጣም ጅብ ሆኖአል:: ኖኅ ከመርከብ መልእክት ልኮት የቀረው የቁራ ነገርስ? ከቤተ ክርስቲያን ወጥተው ስንቶች በዚያው ቀርተዋል? ለዓለም ጨው እንዲሆኑ ተልከው በዚያው ሟሙተው የቀሩ ስንት አሉ:: ርግብ ግን ማረፊያ ስታጣ ተመልሳ ነበር:: ከመርከቢቱ የራቅን ሁላችን "ልባችን በእግዚአብሔር እስካላረፈ ድረስ ዕረፍት የለውም" እንዳለ ሊቁ ወደ መርከቢቱ ፈጥነን መመለስ አለብን:: ሰሞኑን ደግሞ አንድ ጥያቄ በአእምሮዬ ተመላለሰብኝ:: "ወደ ኖኅ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ የገባው እንስሳ ማን ሊሆን ይችላል?" የሚል:: ይህን ጥያቄ በግልም በጉባኤ ላይም ሰዎችን ጠይቄ ነበር:: መቼም ለዚህ ጥቅስ አያስፈልገውም:: ኖኅ ቆሞ እንስሳቱ እስኪገቡ ድረስ እንደጠበቀና ማንንም እንስሳ ጥሎ እንዳልገባ የታወቀ ነው:: በዚህ ምክንያት እንስሳቱ ወደ መርከቢቱ የሚገቡት እንደደረሱበት ቅደም ተከተል ነው:: ክንፍ ያላቸው በርረው ቀድመው ይገባሉ:: እንደ ጥንቸል እንደ ካንጋሮ እንደ ሚዳቁዋ ያሉትም እየዘለሉ ፈጥነው ይገባሉ:: ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ነፍሳቸውን ለማዳን ፈጥነው በርረው የገቡ እንደ ሚዳቋ ዘልለው የደረሱ ብርቱዎች አሉ:: እንደ ፒኮክ ያሉ ባለ ውብ ክንፎች : እንደ ቀጭኔ ያሉ ባለ ረዥም አንገቶች እንደ ጃርት ያሉ ሌላው ላይ የሚሰኩት እሾኽ የለበሱ እንስሳት ወደ መርከብዋ ገብተዋል:: በቤተክርስቲያን እንደ ፒኮክ አምሮ መታየት መዘባነን የሚወዱ ለታይታ የሚገዙ ብዙዎች ገብተዋል:: እንደ ቀጭኔ አንገታቸውን ከፍ አድርገው ሰውን ቁልቁል የሚመለከቱና "አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ የዕብራውያን ሴቶች" ዓይነት ሕይወት ያላቸውም ገብተዋል:: እንደ ጃርት በክፉ ንግግር የሰው ልብ ላይ የሚሰኩት ጥላቻ የተላበሱ ሰዎችም ገብተዋል:: የኖኅ መርከብ ያልያዘችው እንስሳ እንደሌለ ቤተ ክርስቲያንም ያልተሸከመችው ዓይነት ሰው የለም:: ወደ ጥያቄው ስመለስ በእኔ ግምት ወደ መርከቡ በጣም ዘግይታ የገባችው ኤሊ ነበረች:: በላይዋ ድንጋይ የተጫናት እጅግ ቀርፋፋዋ ኤሊን የማይቀድም እንስሳ መቼም አይኖርም:: ምንም ብትዘገይም ኖኅ እስከመጨረሻው ጠብቆ አስገብቶ ለዘር አትርፎአታል:: የኤሊ ዘሮችም "ኖኅ ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ዳይኖሰር በጠፋን ነበር" ብለው ኖኅን ማመስገናቸው አይቀርም:: እግዚአብሔር ምንም ብትዘገይ ኤሊ ሳትገባ መርከቡን አልዘጋውም:: የኤሊ በመርከቡ መትረፍ በቤተ ክርስቲያን ልንተርፍ ተስፋ ለምናደርግ ለእኛ ትልቅ መጽናኛችን ነው:: ወዳጄ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመምጣት እንደ ወፍ ትበርራለህ? እንደ ሚዳቋ ትዘልላለህ? ወይንስ እንደ ኤሊ ትጎተታለህ? እግሮችህ ለመንፈሳዊ ነገር ሲሆን አቅም እያጡ አልተቸገርህም? ልብህ ቢፈልግም እንደ ኤሊዋ የተጫነህ የኃጢአት ድንጋይ አላንቀሳቅስ ብሎህ አልዘገየህም? እንዲህ ከሆነ አትጨነቅ መርከብዋ ቤተ ክርስቲያን አንተን ሳትይዝ ጥላህ ወዴትም አትሔድም:: ጉዞህን እስካላቆምህ ድረስ ትጠብቅሃለች:: እየተጎተትህም እየተሳብህም ቢሆን አንተ ብቻ ወደ ደጁ ገስግስ:: አንተ ብቻ መንገድ ጀምር እንጂ ፈጣሪ በሩን የሚዘጋው አንተ እስክትገባ ጠብቆ ነው:: ከቅዱስ ኤፍሬም ጋር እንዲህ ብለህ ለምነው :- "ብበድልህም እንኳን አሁንም በርህን እያንኳኳሁ ነው:: እየተጎተትሁም ቢሆን አሁንም የምጉዋዘው ወደ አንተ ለመምጣት ነው" የቴሌግራም #ቻናሉን_ይቀላቀሉ ቤተሰብ ይሁኑን! 👇 Telegram: https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv
Mostrar todo...
የደጉ ሳምራዊ መልካምነት®

ይህ ትክክለኛ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት የቴሌግራም ቻናል ነው:: (በመ/ር ሲራክ ሰሎሞን) በዚህ የቴሌግራም ቻናል:- ➮አስተማሪ እና መንፈሳዊ ፅሁፎችን ➮የቅዱሳን ገድላት ➮ መዝሙሮችን ➮መንፈሳዊ ትምህሮቶችን ያገኛሉ። የመወያያ ግሩፕ:

https://t.me/+QKiTJYGJvYpmNWM0

የዚህ ግሩፕ ዓላማ ለበጎ ምግባር ቃለ እግዚአብሔርን መማማር ነዉ::

Photo unavailableShow in Telegram
የሶርያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ሞር አግናጥዮስ ኤፍሬም ዳግማዊ በካይሮ የሚገኘውን የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ የባሕል ማዕከል ጎበኙ ! የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ሞር አግናጥዮስ ኤፍሬም ዳግማዊ በግብፅ ካይሮ የሚገኘውን የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ የባሕል ማዕከል ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ወቅት ከቅዱስነታቸው በተጨማሪ ብፁዓን ሊቃነ የተገኙ ሲሆን ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የኮፕቲክ ባሕል ማዕከል እና የሚ ሳት ቴቪ የበላይ ጠባቂ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስነታቸውንና ልዑካቸውን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት በማዕከሉ ቅጥር ግቢ በመገኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል። የቴሌግራም #ቻናሉን_ይቀላቀሉ ቤተሰብ ይሁኑን! 👇 Telegram: https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv
Mostrar todo...