cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Woldia University/ወልድያ ዩኒቨርሲቲ

ይህ ትክከለኛዉ የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የቴሌግራም ቻናል ነዉ፡፡ This is Woldia University official Telegeram channel.

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
11 550
Suscriptores
+124 horas
-67 días
-3930 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና መሰጠት ተጀመረ። (ሰኔ14/2016 ዓ.ም (የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት) የ2016 ዓ.ም የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) በዛሬው እለት መሰጠት ተጀምሯል። በትምህርት ሚኒስቴር በኩል የትምህርት ጥራትን ለማምጣት እየተሰሩ ካሉ ጉልህ ስራዎች መካከል የተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና አንዱ ነዉ። ይህን ተከትሎ የዘንድሮውም የመውጫ ፈተና ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መርሐ-ግብር መሰረት ከሰኔ 14-21/2016 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ3ኛ ጊዜ እየተሰጠ ይገኛል። ወልድያ ዩኒቨርሲቲም በዩኒቨርሲቲው ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ እጩ ምሩቃን ተማሪዎቹንና ከተለያዩ ኮሌጆች የተውጣጡትን ጨምሮ 2365 ተማሪዎችን ለማስፈተን የቅድመ ዝግጅት ስራዎቹን ማጠናቁን ከፈተና አስፈጻሚ አካላት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። የዛሬው የፈተና መርሀ-ግብርም የማኔጅመንት ተማሪዎችን በማስፈተን ተጀምሯል። ---------------------------------------------------------------------------------------------- አእምሮ ሲከፈት አይኖች ማየት ይችላሉ / Open Mind. Open Eyes! የተቋሙን ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፤ Web site: https://www.wldu.edu.et/ Facebook = https://www.facebook.com/WoldiaUniversity Telegram Channel = https://t.me/Woldia_University YouTube = https://www.youtube.com/channel/UCHt88As5v2BmynWine1Oexw P.O.Box = 400 Woldia Town, Amhara Region, Ethiopia.
Mostrar todo...
ለ2016 ዓ.ም ክረምት በጎ ፍቃደኛ ተማሪዎች ስልጠና መስጠት ተጀመረ:: ሰኔ 11/2016 ዓ.ም (ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት) የሰላም ሚኒስቴር ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር “ብዝሀነት ለአብሮነት” በሚል መሪ ቃል ለወልድያ ዩኒቨርሲቲ በጎ ፍቃደኛ ተማሪዎች ስልጠና መስጠት ተጀመረ። ስልጠናውን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አበበ ግርማ ኢትዮጵያ በርካታ ሀብት፣ ባህልና ቋንቋ ያላት ባለታሪክ ሀገር በመሆኗ ተማሪዎች ይህንን በማወቅና በመገንዘብ ሁላችንም በጋራ ለሃገር ዕድገት አስተዋጽኦ ለማድረግ መስራት ይኖርብናል ብለዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ አክለውም ተማሪዎች ከትምህርት ጊዜ በኋላ በትርፍ ጊዜያችሁ በክረምት በጎ ፍቃደኝነት በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉ ችግሮችን በመፍታት እንዲሁም በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉ ባህሎችን ለማሳደግ የምታዩበት ፕሮግራም በመሆኑ ሁላችሁም በአገልጋይነት መንፈስ እንድትወጡ ሲሉ አሳስበዋል፡፡ በሰላም ሚኒስቴር በፌደራሊዝምና መንግስታት ግንኙነት ዘርፍ የፌደራሊዝምና ዲሞክራሲ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ጌታቸው በለጠ እንደተናገሩት በዋናነት ስልጠናው ከበጎ ፍቃደኝነት ገለጻ ጀምሮ የእዉቀት ክህሎት ፣ ተወዳዳሪ ዜጋ ከመሆን አንጻር እና ሀገር ግንባታ ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልጸዋል። (Soft Skills, Competent citizen and nation building) አቶ ጌታቸው አክለውም በጎ ፍቃደኞቹ ከአምስት የስልጠና ቀናት በኋላ የስራ ስምሪት ይዘው ወደተመረጡ አካባቢዎች በመሄድና የማህበረሰቡን ችግሮች በመለየት በተለይም የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ፣ የፍሳሽ ማስወገጃ ትቦዎችን የማጽዳት፣ የጎዳና ተዳዳሪዎችን በተለያዩ ነገሮች የመደገፍ፣ የክረምት የማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠትም ሆነ ተያያዥ ጉዳዮች እንደየሙያ መስካቸውና እንደየአካባቢው ሁኔታ ለተከታታይ 25 ቀናት በበጎ ፍቃደኝነት እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡ በ2016 ዓ.ም በሃገር አቀፍ ደረጃ በ32 ዩኒቨርሲቲዎች ከ20‚000 በላይ ተማሪዎችን አሰልጥኖ በክረምት በጎ ፍቃድ ስራ ለማሰማራት እየተሰራ እንደሚገኝ የገለጹት ባለሙያው በተለያዩ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ተማሪዎችና በአካባቢው ማህበረሰብ መካከል አንድነትን ለማጎልበት፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ በጎ ፍቃደኞች ከትውልድ ቀያቸው ውጭ ያለውን ማህበረሰብ ባህልና ቋንቋን ማስተዋወቅ እንዲሁም ለማህበረሰቡ አገልግሎት የመስጠት ባህልን በማሳደግ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ከፍ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ስልጠናው ከዛሬ ሰኔ 11/2016ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት ይቆያልም ተብሏል። ስልጠናውን ከሰላም ሚኒስቴር በመጡ ባለሚያዎች አቶ ጌታቸው በለጠ እና አቶ ስምረት ተፈራ አማካኝነት እንደሚሰጥና 465 የሚሆኑ የክረምት በጎ ፍቃደኛ ተማሪዎች በስልጠናው ላይ እንደሚሳተፉም ከስልጠናው አስተባባሪዎች ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። ---------------------------------------------------------------------------------------------- አእምሮ ሲከፈት አይኖች ማየት ይችላሉ / Open Mind. Open Eyes! የተቋሙን ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፤ Web site: https://www.wldu.edu.et/ Facebook = https://www.facebook.com/WoldiaUniversity Telegram Channel = https://t.me/Woldia_University YouTube = https://www.youtube.com/channel/UCHt88As5v2BmynWine1Oexw P.O.Box = 400 Woldia Town, Amhara Region, Ethiopia.
Mostrar todo...

የዩኒቨርሲቲዉ የሴኔት አባላት ኢድ-አል -አድሀ (አረፋ) በአልን ከተማሪዎች ጋር በደማቅ ሁኔታ አከበሩ! ሰኔ 10፣ 2016 ዓ.ም (የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት) በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በደማቅ ሁኔታ የሚከበረዉን የኢድ-አል አድሀ (አረፋ) በአልን ምክንያት በማድረግ በትናንትናዉ እለት በወልድያ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች መመገቢያ ካፌ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፡፡ በበአሉም የዩኒቨርሲቲዉን ፕሬዝደንት ዶ/ር አበበ ግርማን ጨምሮ ሁለቱ ምክትል ፕሬዝደንቶች፣ የተማሪዎች ዲን እና ሌሎችም የሴኔት አባላት በተማሪዎች ካፌ ተገኝተዉ ከተማሪዎች ጋር ማእድ በመጋራት እና ተማሪዎችን እንኳን አደረሳች በማለት አሳልፈዋል፡፡ ለዉድ የዩኒቨርሲቲያችን የሙስሊም ማህበረሰቦች በሙሉ በድጋሜ እንኳን ለኢድ-አል-አድሀ (አረፋ) በአል አደረሳችሁ! ኢድ ሙባረክ ማለት እንወዳለን! ---------------------------------------------------------------------------------------------- አእምሮ ሲከፈት አይኖች ማየት ይችላሉ / Open Mind. Open Eyes! የተቋሙን ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፤ Web site: https://www.wldu.edu.et/ Facebook = https://www.facebook.com/WoldiaUniversity Telegram Channel = https://t.me/Woldia_University YouTube = https://www.youtube.com/channel/UCHt88As5v2BmynWine1Oexw P.O.Box = 400 Woldia Town, Amhara Region, Ethiopia.
Mostrar todo...
የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ወልድያ ከተማን ‹ወደ ዲጂታላይዜሽን› እያዘመናት ይገኛል! ሰኔ 07/2016ዓ.ም (የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት) በወልድያ የኒቨርሲቲ ባለቤትነት የወልድያ ከተማ የመሰረተ ልማት መምሪያ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን የተሰራዉ ሶፍትዌር ስራ የማስጀመር መርሀ-ግብር ሰኔ 06 2016ዓ.ም የከተማዉን ከንቲቫ ጨምሮ የከተማዉ አፈ-ጉባኤ፣ የከተማ መሰረተ-ልማት መምሪያ ሀላፊዎችና ባለሙያዎችች፣ የኒቨርሲቲዉ አመራሮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸዉ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የማስጀመር መርሀ ግብሩ ተከናዉኗል፡፡ ሶፍትዌሩን ስራ በማስጀመር መርሀ-ግብሩ ላይ ተገልጋይ አገልግሎት ለማግኘት ይዞት የመጣዉን ጉዳይ ከተለየ በኋላ የሚጠይቀዉን አገልግሎት በሙሉ ወደ ሲስተሙ በማስገባት- ወደ ሚመለከተዉ ባለሙያ ሰነዱን በሲስተም ይልካል፣ ባለሙያዉ አዲስ የተገልጋይ ፋይል እንደመጣለት ‹በአላርም› ያሳዉቀዋል፣ የተገልጋይ ፋይል ከባለሙያዉ ከደረሰ ጀምሮ ሰአትና ቀን በመቁጠር ተገልጋዩ እንዳይንገላታ ለቁጥትርና ለቀጠሮ አሰጣጥም ምቹ የሆነ እንደሆነ በማስጀመሪያ መርሀ-ግብሩ ከባለሙያዎች በተደረገዉ ገለጻና በተግባርም ጭምር ለማየት ተችሏል፡፡ ሶፍትዌሩን በጋራ ካበለጸጉት ባለሙያዎች አንዱ የሆነዉ መ/ር ተሾመ ጌታቸዉ በማብራሪያቸዉ የከተማ መሰረተ-ልማት መምሪያ (በተለምዶ ማዘጋጃ ቤት) የሚባለዉ ጽ/ቤት የከተማዋ ዋና የአገልግሎት ማእከል ነዉ፡፡ የልማት ቋት ነዉ፡፡ በመሆኑም የዚህን መምሪያ አገልግሎት አሰጣጥ ማዘመን ታሳቢ ያደረገ የሶፍትዌር መተግበሪያ ነዉ የሰራነዉ ብለዋል፡፡ የመተግመሪያ ሶፍትዌሩን ከሰሩት ባለሙዎች አንዱ የሆነዉ መ/ር ደመቀ ጌታነህ በበኩላቸዉ የበለጸገዉ ሶፍትዌር አመታትን የፈጀና የብዙ ባለሙያዎች ትብብር የታየበት የተለያዩ ከተሞችን ልምድ እና መመሪያ በመቀመር በሀገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና የተሻለ ሆኖ የተሰራ ሲሆን፤ በወልድያ ከተማ በሚታየዉ ዉጤት ወደ ሌሌች ከተሞችም የማስፋት እቅድ እዳላቸዉ ገልጸዋል፡፡ ሶፍትዌሩ ማንኛዉም አገልግሎት ፈልጎ የሚመጣ ተገልጋይ ካሁን በፊት በልማዳዊ አሰራር ሲያገኛቸዉ የነበሩትን የአገልግሎት አይነቶችን እና አዳዲስ አሰራሮችን በመጨመር ጊዜን፣ ሀብትን፣ እንግልትን፣ ብልሹ አሰራርን፣ ስርቆትንና የመረጃ መጥፋትን ለመከላከል እንዲያስችል ታስቦ የተሰራ ነዉ፡፡ የወልድያ ከተማ አቶ ዱባለ አብራሬ ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ከመቸዉም ጊዜ በላይ ከተማችንን ሊያዘምኑ የሚችሉ በርካታ ስራዎችን እየሰራ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲዉን አመስግነዋል፡፡ አክለዉም ይህን መተግበሪያ ዉጤታማ እንዲሆን ከዛሬ ጀምሮ በየቀኑ ከምከታተላቸዉ ተግባራት አንዱ ነዉ ብለዉ፤ የከተማ አገልግሎት መምሪያን ማዘመን የበርካታ ዜጎቸችን እንግልትና ሮሮ የሚቀርፍ በመሆኑ ካሁን በኋላ ወደ ኋላ የምንመለስበት አሰራር የለም በማለት ለመምሪያዉ ሀላፊዎችና ባሙያዎችም ማሳሰቢያ ሰተዋል፡፡ ሶፍትዌሩን በማስጀመሪያ መርሀ-ግብሩ ከእንግዶችና ከባለሙያዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ ተሰቶባቸዋ፡፡ የወልድያ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ለዚህ ሶፍትዌር መበልጸግ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የዩኒቨርሲቲዉ መምራኖች የምስጋና ምስክር ወረቀትና ማበረታቻ ሽልማት በመምሪያዉ ተበርክቶላቸዋል፡፡ ይህ ሶፍትዌር የወልድያ ዩኒቨርሲቲ በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ እየተገበራቸዉ ካሉ ስራዎች በተለይም በአይሲቲ እና በዲጅታላይዜሽን የትኩረት አቅጣጫ አንዱ ሲሆን ሶፍትዌሩን ከማበልጸግ ጀምሮ የባለሙያዎችን ክፍያ በመክፈል፣ የኮምፒዉተርና የሰርቨር መሰረተ ልማቶችን አሟልቶ ለከተማ አገልግሎቱ ያስረከበ ሲሆን፤ በቀጣይ ይህን ሶፍትዌር የሚጠቀሙ አገልግሎት ሰጭ ባለሙያዎችን ማሰልጠን እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን እንደሚሰራ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ---------------------------------------------------------------------------------------------- አእምሮ ሲከፈት አይኖች ማየት ይችላሉ / Open Mind. open Eyes! የተቋሙን ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፤ Web site: https://www.wldu.edu.et/ Facebook = https://www.facebook.com/WoldiaUniversity Telegram Channel = https://t.me/Woldia_University YouTube = https://www.youtube.com/channel/UCHt88As5v2BmynWine1Oexw P.O.Box = 400 Woldia Town, Amhara Region, Ethiopia.
Mostrar todo...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

Graduation is approaching... so here is Woldia University Graduation song
Mostrar todo...
Woldia University Mezmur.mp34.42 MB
Archivo de publicaciones
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.