cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

የ ኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር

ማንኛውም ከ ተማሪዎች ጋር የተያያዙ እንዲሁም ስለ ስኮላርሽፕ ጉዳዮችን በፍጥነት እንዲደርሳቹ join በማለት ቤተሰብ ይሁኑ። ለ ተፈታኞች፡ - ቻናሉን ጆይን በማለት ከ ፈተናው ጋር የተገናኘ ማንኛውም መረጃ በፍጥነት ይደርሳቹዋል!! የ ኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስትር

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
3 514
Suscriptores
+124 horas
-47 días
-1430 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

የቴክኒክና ሙያ የመግቢያ ነጥብ ይፋ ተደረገ። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም ወደ ቲክኒክና ሙያ መግቢያ ነጥብ ይፋ አድርጓል። ሚኒስቴሩ የመግቢያ ነጥቡን ይፋ ያደረገው ረቡዕ ኅዳር 5 ቀን 2016 ዓ.ም ላምበረት በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው። መግለጫውን የሰጡት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ፤ የተፈጥሮ ሳይንስ ደረጃ 5 የመቁረጫ ነጥብ ወንድ ከ218፣ ሴት 199 በላይ፣ የታዳጊ ክልል (የአርብቶ አደር አካባቢዎች) ወንድ ከ192፣ ሴት 187 በላይ፣ በተፈጥሮ ሳይንስ አካል ጉዳተኞች 147ና ከዚያ በላይ (ሁሉንም ክልሎች ታሳቢ ያደረገ ነው)  ብለዋል። ደረጃ 3 እና 4 ወንድ ከ173፣ ሴት 163 በላይ፣ ታዳጊ ክልሎች ወንድ ከ157፣ ሴት 156 በላይ፣ አካል ጉዳተኞች 130ና ከዚያ በላይ ነው ተብሏል። ተፈጥሮ ሳይንስ ደረጃ 1 እና 2 ወንድ 172፣ ሴት 162ና ከዚያ በላይ፣ ታዳጊ ክልሎች ወንድ 156፣ ሴት 155ና ከዚያ በላይ ነው። ማኅበራዊ ሳይንስ ደረጃ 5 ወንድ 179፣ ሴት 170ና ከዚያ በላይ፣ ታዳጊ ክልሎች ወንድ 166፣ ሴት 162፣ አካል ጉዳተኞች 147ና ከዚያ በላይ ነው። ደረጃ 3 እና 4 በማኅበራዊ ሳንይንስ ወንድ 149፣ ሴት 147፣ ታዳጊ ክልል ወንድ 138፣ ሴት 137ና ከዚያ በላይ፣ አካል ጉዳተኞች 130ና ከዚያ በላይ ሆኗል። ደረጃ 1 እና 2 በማኅበራዊ ሳይንስ ወንድ 148፣ 146፣ ታዳጊ ክልል ወንድ 137፣ ሴት 136፣ አካል ጉዳተኞች 129ና ከዚያ በላይ መሆኑን አስረድተዋል። ሚኒስትሯ አክለውም፣ "በ2016 ዓ.ም 844 ሺሕ 384 የሚሆኑ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ወስደዋል። ከእነዚህ ውስጥ በእኛ ምልከታ 632 ሺሕ 587 የሚሆኑት ወደ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ይመጣሉ የሚል ግምት አለን" ነው ያሉት። የሰው ሃይል ለመቀበል የተሻለ ዝግጁነት አላቸው ያልናቸውኝ የመንግሥትና የግል የቴኪኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማትን ፈትሸናል ያሉት ሚኒስትሯ፣ እስካሁን ባለው ከ28 ሺህ በላይ የሚሆኑ አሰልጣኞች፣ ወደ 1ሺሕ 400 ገደማ የተሻለ ብቃት ያላቸው ማሰልጠኛ ኮሌጆች አሉ ብለዋል። መረጃው በአ/አ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው። @Ethiopian_national_educationa
Mostrar todo...
" የሬሜዲያል ተማሪዎች ምደባ በቀጣይ ይካሄዳል” ትላንት ይፋ በተደረገው የማካካሻ ትምህርት / ሬሜዲያል መቁረጫ ነጥብ መሰረት ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ገብተው ለሚማሩ ተማሪዎች በቀጣይ የዩኒቨርሲቲ ምደባ እንደሚካሄድ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። የመቁረጫ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ከተደረገላቸው በኃላ ለ4 ወራት የማካካሻ ትምህርት የሚወስዱ ሲሆን ይህንን ተከታትለው በተቋማቸው እና በማዕከል የሚሰጣቸውን ፈተና ማለፍ ሲችሉ በቀጣይ መደበኛ ተማሪ ሆነው ወደ ፌሽማን ይቀላቀላሉ። ትምህርት ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው የመቁረጫ ነጥብ በሁሉም አማራጮች ማለትም #በግል እና #በመንግስት ተቋማት የሬሜዲያል ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል፤ ይህም ማለት 210 ከ700፣ 180 ከ600 እና 150 ከ500 ማስመዝገብ አለባቸው። በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) በዩኒቨርሲቲ ተመድበው የሬሜዲያል ፕሮግራም የሚከታተሉ በ #ተፈጥሮ_ሳይንስ የመደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች መቁረጫው 255 ከ700 ነው። የሴት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች መቁረጫው ደግሞ 234 ከ700 ነው። በዩኒቨርሲቲ ተመድበው ለሚማሩ የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥቡ 218 ከ600 ሲሆን ፤ የሴት ተማሪዎች መቁረጫው 200 ከ600 ነው። እንደ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ከሆነ ዘንድሮ 164,242 የሬሜዲያል ተማሪዎች በግል እና በመንግሥት ተቋማት ገብተው ይማራሉ። #ማስታወሻ ፦ የሬሜዲያል መቁረጫ ነጥብ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል። በሌላ በኩል ፤ በ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈትነው የማለፊያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ምደባ ከትላንት ጀምሮ ይፋ የተደረገ ሲሆን የምደባ መመልከቻው ፦በድረገፅ https://result.ethernet.edu.et/ የቴሌግራም ቦት @moestudentbot መሆኑን ለማስታወስ እንወዳለን። @Ethiopian_national_educationa
Mostrar todo...
👍 11 10
የሬሜዲያል መቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ። የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የሚያስችል የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደርጓል፡፡ በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያላስመዘገቡ ነገር ግን ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣቸውን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተማሪዎች የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የሚያስችላቸው የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደርጓል፡፡ በዚህም መሰረት በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማለትም (210 ከ 700፣ 180 ከ 600 እና 150 ከ500) የተቆረጠ መሆኑ ተመላክቷል። ከላይ በተራ የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የRemedial ፕሮግራም የሚከታተሉት የሚከተሉትን መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ ብቻ እንደሚሆኑ ተጠቁሟል፡፡ ☑️ የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች 255 ከ700 ያመጡ ☑️ የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች 234 ከ700 ያመጡ ☑️ የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች 218 ከ600 ያመጡ ☑️ የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች 200 ከ600 ያመጡ ☑️ ታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 224 ከ700 ያመጡ ☑️ ታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 210 ከ700 ያመጡ ☑️ ታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 192 ከ600 ያመጡ ☑️ ታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 180 ከ600 ያመጡ ☑️ አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 210 ከ700 ያመጡ ☑️ አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 210 ከ700 ያመጡ ☑️ አርብቶ አደር አካባቢ የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 180 ከ600 ያመጡ ☑️ አርብቶ አደር አካባቢ የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 180 ከ600 ያመጡ ☑️ ዓይነ ስውራን ማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 150 ከ500 ያመጡ ☑️ ዓይነ ስውራን ማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 150 ከ500 ያመጡ መሆን አለባቸው ተብሏል። @Ethiopian_national_educationa
Mostrar todo...
10👍 6👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ምደባ ትምህርት ሚኒስቴር በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ወስደው ያለፉ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ አሰራርን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥቷል። ማብራሪያ ፦ - የምደባ ስርዓቱ በተፈጥሮም ሆነ በማህበራዊ ሳይንስ መስኮች 1000 ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን በመጀመሪያ የዩኒቨርስቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫቸው ምደባ የሚካሄድ ይሆናል ተብሏል። - የምደባ ስርዓቱ እያንዳንዱ ተማሪ ያስመዘገበውን አጠቃላይ ውጤት በምደባ ስርዓት ሂደት ውስጥ መለያ አድርጎ ይጠቀማል፡፡ የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ሌሎች ተፈጻሚ የሚሆኑ ህግና ደንቦችን ባልጣሰ መልኩ ምርጫቸውን በመጠበቅ ረገድ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል። - የምደባ ስርዓቱ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሚመደቡ ተማሪዎችን ተዋጽኦ በጠበቀ መልኩ እንዲሆን እንደሚያግፅ ተነላክቷል። ይህም ከአንድ ት/ቤት የወጡ ተማሪዎች በአንድ ዩኒቨርሲቲ ወይም ፕሮግራም ውስጥ እንዳይታጨቁ ይደርጋል። -  በምደባ ወቅት የጤና ችግር ኖሮባቸው ትክክለኛ የሕክምና ማስረጃ ላላቸው ተማሪዎች ምደባው በተለየ መልኩ ሊታይ ይችላል። - በተማሪዎቹ መካከል ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትዮች ካሉ የምደባ ስርዓቱ ከፍተኛ ነጥብ ያገኘው/ችው ተማሪ ከተመደበበት/ችበት የትምህርት ተቋም ቀሪው መንትያ ደግሞ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በቀጥታ ይመድባል። - የምደባ ሲስተሙ የአካል ችግር ላለባቸው ተማሪዎች እኩል እድሎችን የሚሰጥ ሲሆን ልዩ ፍላጎቶቻቸውን እና ለምደባ መስፈርቶቻቸውን ግምት ውስጥ በማስገባት የሚሰራ ይሆናል። ትምህርት ሚኒስቴር ሀሰተኛ የህክምና ማስረጃ  የሚያቀርብ ተማሪ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከምደባ ውጭ የሚሆን መሆኑን አሳስቧል።
Mostrar todo...
👍 7 5😢 2🥰 1
Photo unavailableShow in Telegram
የትምህርት ሚኒስቴር ፤ በአካዳሚክ ጉዳዮች ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ኤባ ሚጄና አማካኝነት ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በላከው ደብዳቤ በ2016 ዓ.ም አጋማሽ ላይ ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ዝግጅት ለማድረግ እንዲቻል ለፈተናው የሚቀመጡ ተማሪዎች መረጃ በአስቸኳይ እንዲላክለት ጠይቋል። ሚኒስቴሩ ፤ ተቋማት መረጃው እጅግ ቢዘገይ እስከ ጥቅምት 16 ቀን 2016 ዓ.ም እንዲልኩ ያሳሰበ ሲሆን የማያሳውቅ ዩኒቨርሲቲ " ተፈታኝ ተማሪ የለውም " በሚል ተይዞ የሚታቀድ መሆኑን በጥብቅ አስገንዝቧል። በ2015 ዓ/ም ለመጀመሪያ ጊዜ በተሰጠው የመውጫ ፈተና በመንግስት ተቋማት ለፈተናው ከተቀመጡት 77,981 ተማሪዎች ውስጥ 50 እና ከዚያ በላይ በማምጣት ያለፉት 48,632 ተማሪዎች ወይም 62.37 በመቶ መሆናቸው አይዘነጋም። በግል ተቋማት ደግሞ ለፈተና ከተቀመጡት 72,203 ተማሪዎች ውስጥ 50 እና ከዚያ በላይ ውጤት አምጥተው ያለፉት 12,422 ተማሪዎች ወይም 17.2 በመቶ ብቻ ነበሩ። በድምሩ ከአጠቃላይ 150,184 የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ፈተናውን ያለፉት 61,054 ብቻ ወይም 40.65 በመቶ ናቸው። የመጀመሪያውን የመውጫ ፈተና ያላለፉ ተማሪዎች በዚህ አመት አጋማሽ ላይ በሚዘጋጀው ሌላ ፈተና መፈተን የሚችሉ ሲሆን ከዚህ ቀደም ትምህርት ሚኒስቴር  ተፈታኞች ዳግም ፈተና ለመውሰድ መጀመሪያ ሲማሩበት ወደነበረበት ተቋም መሄድ ሳይጠበቅባቸው ባሉበት አካባቢ ባሉ ተቋማት ፈተናውን እንደሚወስዱ የሚደረግበት ስርዓት እንደሚዘረጋ መግለፁ አይዘነጋም (በዚህ ጉዳይ ወደፊት የሚወጣ መረጃ ካለ ተከታትለን እናሳውቃለን)። @Ethiopian_national_educationa
Mostrar todo...
👍 7 4👎 2
Photo unavailableShow in Telegram
#ሀናን_ናጂ_አህመድ👏 በኢትዮጵያ 🇪🇹 ደረጃ የ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበችው የክሩዝ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ ናት። ተማሪ ሀናን ናጂ አህመድ በተፈጥሮ ሳይንስ 649 ውጤት በማስመዝገብ ከዘንድሮ ተፈታኞች በቀዳሚነት ተቀምጣለች፡፡ ተማሪ ሀናን ናጂ ባስመዘገበችው ውጤት በጣም ደስተኛ መሆኗን ገልጻለች። በቀጣይም ለበለጠ ውጤት እንደመትተጋ ተናግራለች፡፡ የክሩዝ ሁተኛ ደረጃ ት/ቤት በአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማ የሚገኝ የግል ትምህርት ቤት ነው፡፡ @Ethiopian_national_educationa
Mostrar todo...
👏 28👍 18 9🤯 4
" ምንም አይነት የሲስተም / ቴክኒካል ችግር የለም " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዛሬ ይፋ ሆኗል። ውጤት በዌብሳይት eaes.et ላይ ፣ በአጭር የፅሁፍ መልዕክት በ6284 ፣ በቴሌግራም ቦት @eaesbot ላይ " ሬጅስትሬሽን ቁጥር " በማስገባት ማየት እንደሚቻል ተገልጿል። ነገር ግን በርካታ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ውጤት ለማየት መቸገራቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ጠቁመዋል። ይህ በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎትን አነጋግሯል። አገልግሎቱ ፤ በውጤት መመልከቻ አማራጮቹ ላይ ምንም አይነት ቴክኒካል / የሲስተም ችግር እንደሌለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል። " በአንድ ግዜ ተማሪዎችና ወላጆችን ጨምሮ ከ1 ሚሊዮን በላይ ሰው ውጤት ለማየት እየሞከረ ስለሆነ መጨናነቅ መፈጠሩን " ከፍተኛ የአገልግሎቱ አመራር ለቲክቫህ ተናግረዋል፡፡ ተማሪዎች በትዕግስት በመሞከር ውጤታቸውን እንዲያዩ ኃላፊው መክረዋል፡፡ @Ethiopian_national_educationa
Mostrar todo...
👍 9 4🔥 3👏 3🥰 1🎉 1
ውጤት እንዴት መመልከት ይቻላል ? የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች መገ መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በሚከተሉት አማራጮች ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ። በዌብ ሳይት 👉 https://eaes.edu.et/ በአጭር የጽሑፍ መልዕክት 👉 6284 በቴሌግራም 👉 https://t.me/eaesbot @Ethiopian_national_educationa
Mostrar todo...
👍 39 15😁 6👎 1
ሚኒስትሩን ያስደናገጣቸው ቁጥር ? ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፦ " ከዚህ ፈተና አንድ #ሊያስደነግጠን የሚገባ ነገር ከተፈተኑት ጠቅላላ ተማሪዎች ውስጥ 50 ከመቶ የሚሆኑት እና ከዛ በላይ 26 ከመቶ ነው ያገኙት። ከ845 ሺህ ፤ 422,500 ሺህ ተማሪ ከ26 በታች ነው ያገኘው። እንደው ዝም ብሎ አንድ ተማሪ ፈተናውን በግምት ቢሞላ እንኳን ሊያገኘው የሚችለው ውጤት ነው። ለዚህ ነው ከታች ጀምሮ በደንብ አጥርተን መስራት አለብን የምንለው። " ስለ 2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ቁጥሮች ምን ይላሉ ? - በ2015 የተፈተኑ ተማሪዎች ብዛት 845,099 ፤ 50 በመቶና በላይ ያመጡ 27,267 ተማሪዎች (3.2%) ብቻ ናቸው። ከነዚህ ውስጥ ፦ • ከተፈጥሮ ሳይንስ ያለፉ 19,017 ተማሪዎች • ከማህበራዊ ሳይንስ ያለፉ 8,250 ተማሪዎች - በማታ የተፈተኑ 16,541 ያለፉ 12 ተማሪዎች ብቻ - በግል የተፈተኑ 169,502 ያለፉ 498 ተማሪዎች ብቻ - በመደበኛ የተፈተኑ 659,056 ያለፉ 26,757 ተማሪዎች ብቻ - የ12ኛ ክፍል ፈተና ካስፈተኑ 3,106 ት/ቤቶች፤ 1,328 ትምህርት ቤቶች #አንድም_ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም / ምንም ተማሪ አላሳለፉም። - በሀገሪቱ ካሉትና የ12ኛ ክፍል ፈተና ካስፈተኑት ትምህርት ቤቶች 42.8 በመቶ የሚሆኑት አንድም እንኳን ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም። - 27 ሺህ 267 ተማሪዎች በቀጥታ ፍሬሽ ማን ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ 160 ሺህ ገደማ ተማሪ በሬሜዲያል ይገባሉ። @Ethiopian_national_educationa
Mostrar todo...
👍 9😱 6😁 4👎 2🔥 1