cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Info Health Service (አይ ኤች ኤስ የጤና ማዕከል, IHS Health and Wellness Consultation Center )

አገልግሎታችን በአካል ቀርበው ለማግኘት፤ ለማማከር፥ ቀጠሮ_ለማስያዝ በ 0913744598 ላይ ይደውሉ። #ጎተራ_ንፋስ_ስልክ_ማሞ_ራሚ_ህንፃ_4ኛ_ፎቅ_ ላይ ያገኙናል።

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
11 353
Suscriptores
-724 horas
-517 días
-19830 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

   #CPD_Training_ነገ_ማክሰኞ_ይጀምራል ETHIO_MEDICAL_TRAINING_CENTER            #ሚያዚያ_29_ጀምሮ #Pain_Management ስልጠና እንጀምራለን። #15CEU ይይዛል። #ሰልጣኞች፦ ➯ ሀኪሞች ➩ የጥርስ ሀኪም ➯አነስቴዥያ ባለሙያ ➯ ነርሶች ➯ ፋርማሲዎች ➯ ለላብ ባለሙያዎች እና ለሌሎችም የሚሆን https://t.me/ethiomedicaltrainingplc ባሉበት ሁነው ይደውሉ!!! ይመዝገቡ። 0921785903 አድራሻ፦ ጎተራ ንፋስ ስልክ ማሞ ባቡር  ፌርማታ ሲደርሱ ንግድ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Mostrar todo...
የበዓላት ሰሞን ምግቦችን ከጤና አንፃር 🌲በበዓላት ሰሞን ጤነኛ ባልሆነ የምግብ ስርአትና በሚፈጠር የምግብ ለውጥ ምክንያት ብዙ ሰው አዳዲስ የህመም ስሜት ሲሰማው ወይም ነባር ህመሙ ሲባባስበት ማየት የተለመደ ነው 🍜በበዓላት ሰሞን በአብዛኛው ማህበረሰባችን ዘንድ የተለመዱና ቤት ውስጥ ከማይጠፉ የምግብ አይነቶች ውስጥ ዶሮ ወጥ ፣ ቁርጥ (ጥሬ ስጋ)፣ ክትፎ ፣ ጥብስ ፣ እና የመሳሰሉትን መጥቀስ ይቻላል 🍲ከነዚህ የምግብ አይነቶች ውስጥ ዶሮ ወጥ (በዶሮ ወጥ መንገድ የሚዘጋጁ) ምግቦችን አንስተን ከጤና አንፃር የሚያስከትሉትን ችግር ለማየት እንሞክር:- 🍅ዶሮ ወጥን ለመስራት ከምንጠቀምባቸው ግብአቶች ውስጥ ሽንኩርት ፣ ቲማቲም ፣ በርበሬ ፣ ዘይት (ቅቤ) እና ሌሎች ቅመማቅመሞችን መጥቀስ ይቻላል 🍜የዶሮ ወጥ ዝግጅት ሂደት በከፍተኛ ሙቀት ዘይትን በማጋል ሽንኩርት እና ሌሎች ግብአቶችን ለረጅም ጊዜ ማቁላላት (ማብሰልን) ይጠይቃል በዚህ ሂደት:- 🍅በሽንኩርትና ሌሎች ግብአቶች ውስጥ የሚገኙ ሙቀት መቋቋም የማይችሉ ለጤና እጅግ በጣም ጠቃሚ የሆኑ ቫይታሚኖችና ውህዶች ሊጠፋ (ሊቀንሱ) ስለሚችሉ ከምግቡ ተገቢውን ጥቅም አናገኝም 🍟በተጨማሪም የምንጠቀመው ፈሳሽ ዘይት ውስጥ የሚገኘው ሲስ (cis) ተብሎ የሚጠራው ጤነኛ እና ተፈጥሯዊ የዘይቱ ክፍል ትራንስ (trans fat) ወደሚባል እጅግ መርዛማ ቅባት ይቀየራል 🍟ከዶሮ ወጥ በተጨማሪ ይህ መርዛማ ቅባት በተጠበሰ ስጋ ወይም አሳ፣ ችፕስ ፣ ሳንቡሳ ፣ ቦንቦሊኖ እና በመሳሰሉት ምግቦች ውስጥ ይገኛል 🥫ሌላኛው እና ዋነኛው የትራንስ ቅባት (trans fat) መገኛ ሰው ሰራሽ የአትክልት ቅቤ ነው 🥫አንዳንድ የዘይት አምራቾች በተለያየ ምክንያት በከፍተኛ ሙቀትና ግፊት hydrogenation የሚባል ሂደትን በመተግበር ፈሳሽ የአትክልት ዘይትን ወደ ጠጣር ሰው ሰራሽ የአትክልት ቅቤ ይቀይራሉ 🥫በዚህ ሂደትም ከፍተኛ መጠን ያለው ትራንስ (trans) እና ሳቹሬትድ ቅባት (saturated fat) ይፈጠራል 🥫እነዚህ የቅባት አይነቶች  "partially hydrogenated oil" በመባል የሚታወቁ ሲሆን ጤና ላይ በሚፈጥሩት ከፍተኛ ችግር ምክንያት በብዙ ሀገራት እገዳ (ክልከላ) የተደረገባቸው (FDA, 2020) ቢሆንም በእኛ ሀገር ግን በሰፊው እየተመረቱና ለተጠቃሚ እየቀረቡ ይገኛሉ 🥫በብዙ ጥናቶች እንደተረጋገጠው ትራንስ ቅባት (trans fat) LDL ተብሎ የሚጠራውን መጥፎ ኮሌስትሮል (bad cholesterol) እና TAG የሚባለውን የቅባት አይነት በመጨመር፣ HDL ተብሎ የሚጠራውን ጠቃሚ የኮሌስትሮል አይነት በመቀነስና የኢንሱሊን መጠን በመጨመር:- 🥫የደም የኮሌስትሮል መጠን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር ያደርጋል 🥫የደም ግፊት ፣ የልብ ፣ የስትሮክ እና የስኳር በሽታ ተጋላጭነትን ይጨምራል ወይም ችግሮቹ እንዲባባሱ ያደርጋል 🥫ትራንስ ቅባት ለሰውነታችን ምንም አይነት ጥቅም የሌለው እና በአንፃሩ ጤና ላይ እጅግ ከፍተኛ ችግር ስለሚያስከትል እንዳትጠቀሟቸው  እንመክራለን 🍚ሌላኛው ለጤና ጎጂ ናቸው ከሚባሉ የቅባት አይነቶች ውስጥ አንዱ ሳቹሬትድ ቅባት (saturated fat) ነው 🍚እነዚህ የቅባት (የዘይት) አይነቶች በመደበኛ አከባቢያዊ ሙቀት የመርጋት ባህሪ ያላቸውን እንደ ቅቤ፣ ጮማ ስጋ ፣ የሚረጋ ዘይትና የመሳሰሉትን ያጠቃልላሉ 🍚ሳቹሬትድ ቅባት  የትራንስ ቅባትን ያክል ባይሆንም በብዛት የሚወሰድ ከሆነ LDL ተብሎ የሚጠራውን ኮሌስትሮል በመጨመር የልብ ጤናን ያውካል 🦴ስለዚህ የኮሌስትሮል የስኳር፣ የኮሌስተሮል፣ የግፊት፣ የስትሮክ፣ የልብና ተያያዥ የጤና ችግሮች ያሉባችሁ ከሆነ በምግብ ከሚገኘው ጊዚያዊ ደስታና እርካታ ይልቅ ከላይ የዘረዘርናቸው ምግቦች የሚያስከትሉት አሉታዊ ተፅዕኖን በመረዳት አለመመገብና በምትኩ በውሃ የተቀቀሉና ለጤና ጠቃሚ የሆኑ ቅመማ ቅመሞች የተጨመሩባቸው እንደ አሳ፣ የዶሮ የደረት ስጋና እንቁላል መመገብ የሚመረጥ ሲሆን የተቀነባበሩ ዘይቶችንና ሰው ሰራሽ የአትክልት ቅቤ ከመጠቀም ይልቅ  ተፈጥሯዊና ጤነኛ የቅባት ምንጭ የሆኑ እንደ ተልባ፣ ሱፍ፣ ሰሊጥ፣ አቮካዶ፣ ኦቾሎኒና የመሳሰሉትን መጠቀም ይመከራል 🥦ምግብ መድኀኒትም መርዝም  ነው! ለይቶ መጠቀሙ ደግሞ የኛ ፋንታ ነው! እያንዳንዱ ጉርሻ ጤና ላይ በኈ ወይም አሉታዊ ተፅዕኖ ይፈጥራል ሙሉቀን ፈቃዴ (የሜዲካል ባዬኬሚስትሪና ስነ ምግብ ረ/ፕሮፌሰር) https://t.me/jossiale2022
Mostrar todo...
Info Health Service (አይ ኤች ኤስ የጤና ማዕከል, IHS Health and Wellness Consultation Center )

አገልግሎታችን በአካል ቀርበው ለማግኘት፤ ለማማከር፥ ቀጠሮ_ለማስያዝ በ 0913744598 ላይ ይደውሉ። #ጎተራ_ንፋስ_ስልክ_ማሞ_ራሚ_ህንፃ_4ኛ_ፎቅ_ ላይ ያገኙናል።

ለመላው የክርስቶስ ትንሳኤ በዓል ለምታከብሩ ወገኖች መልካም የፋሲካ (Passover) በዓል ይሁንላችሁ!! መልካም የፋሲካ በዓል!!
Mostrar todo...
👍 1
   #CPD_Training_ከበዓል_ማግስት_ማክሰኞ_ይጀምራል ETHIO_MEDICAL_TRAINING_CENTER            #ሚያዚያ_29_ጀምሮ #Pain_Management ስልጠና እንጀምራለን። #15CEU ይይዛል። #ሰልጣኞች፦ ➯ ሀኪሞች ➩ የጥርስ ሀኪም ➯አነስቴዥያ ባለሙያ ➯ ነርሶች ➯ ፋርማሲዎች ➯ ለላብ ባለሙያዎች እና ለሌሎችም የሚሆን https://t.me/ethiomedicaltrainingplc ባሉበት ሁነው ይደውሉ!!! ይመዝገቡ። 0921785903 አድራሻ፦ ጎተራ ንፋስ ስልክ ማሞ ባቡር  ፌርማታ ሲደርሱ ንግድ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Mostrar todo...
👍 1
   #CPD_Training_ከበዓል_ማግስት_ማክሰኞ_ይጀምራል ETHIO_MEDICAL_TRAINING_CENTER            #ሚያዚያ_29_ጀምሮ #Pain_Management ስልጠና እንጀምራለን። #15CEU ይይዛል። #ሰልጣኞች፦ ➯ ሀኪሞች ➩ የጥርስ ሀኪም ➯አነስቴዥያ ባለሙያ ➯ ነርሶች ➯ ፋርማሲዎች ➯ ለላብ ባለሙያዎች እና ለሌሎችም የሚሆን https://t.me/ethiomedicaltrainingplc ባሉበት ሁነው ይደውሉ!!! ይመዝገቡ። 0921785903 አድራሻ፦ ጎተራ ንፋስ ስልክ ማሞ ባቡር  ፌርማታ ሲደርሱ ንግድ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Mostrar todo...
👍 2 1
#የኪንታሮት_መንስኤና_መፍትሄዎች (ህክምና) ይህ መረጃ ለብዙ ሰዎች ይደርስ ዘንድ በቅድሚያ ሼር ብታደርጉትና ወደ ንባብ ብትገቡ ደስ ይለናል፡፡ መልካም ንባብ… የቂጥ ኪንታሮት ሠገራን በምናስወገድ ጊዜ ከማማጥ ወይንም በእርግዝና ጊዜ በሚከሰት የደም ስሮች ላይ የሚገኝ ግፊት ምክንያት የሚመጣ ሲሆን በሁለት መልኩ ይከፈላል፡፡ 1) ውስጣዊ ኪንታሮት (internal hemorrhoid) በፊንጢጣ ውስጥ የሚገኝ 2) ውጫዊ ኪንታሮት (external hemorrhoid) በላይኛው ቆዳ ላይ የሚገኝ ኪንታሮት በአብዛኛው የሚከሰት ሲሆን በተለይ ዕድሜያቸው 50 ዓመት የሞላቸው ሰዎች ላይ በስፋት (ግማሽ በሚሆን ደረጃ) የኪንታሮት ምልክቶች እንደሚያዩ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ነገር ግን አብዛኞቹ በቤት ውስጥ ሕክምና እና የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ በማድረግ ይድናሉ፡፡ ኪንታሮትን የሚያስከትሉ ምክንያቶች • ሠገራን ሲያስወግዱ ለረጅም ጊዜ ማማጥ • ለረጅም ሰዓታት በመፀዳጃ ቤት መቀመጥ • የሆድ ድርቀት (ለረጅም ጊዜ የቆየ) • ከመጠን ያለፈ ውፍረት • ዕርግዝና • የፋይበር መጠኑ የቀነሰ ምግብ መመገብ ናቸው • በዕድሜ መጨመር ቬይኖችን የሚደግፉ የሰውንት ክፍሎች እንዲደክሙ ስለሚያደርግ ለሄሞሮይድ ያጋልጣል፡፡ የኪንታሮት ምልክቶች • ሕመም የሌለው ከፊንጢጣ የሚፈስ ደም • በሰገራ መውጫ አካባቢ ማሳከክ • ሕመም ወይንም አለመመቸት • በፊንጢጣ አካባቢ እብጠት ናቸዉ፡፡ ሃኪምዎን ማማከር የሚገባዎ መቼ ነው? • በፊንጢጣ የሚወጣ ደም የኪንታሮት የተለመደ ምልክት ነው፡፡ ነገር ግን ከሌሎች የሕመም ዓይነቶች እንደ ኮሎሬክታል ካንሰር እና ሌሎች የህመም አይነቶች ጋር ተመሳሳይ ምልክት ሊኖረው ስለሚችል ሄሞሮይድ ነው በሚል ግምት ችላ ሊባል አይገባም፡፡ ስለዚህም ወደ ሐኪም በመሄድ መመርመር ያስፈልጋል፡፡ • ከፍተኛ ሕመም የሚሰማዎ ከሆነ እና በቤት ውስጥ የሕክምናዎች ለውጥ የማያገኙ ከሆነ ወደ ሕክምና ቦታ መሄድ ይገባዎታል፡፡ • ከፍተኛ መጠን ያለው ደም መፍሰስ ካጋጠምዎ እና እንዲሁም ራስ የማዞር የመሳሰሉት ስሜት ከተሰማዎ ወደ ሐኪም እንዲሄዱ ይመከራል፡፡ ኪንታሮት የሚያስከትለው ተያያዥ ጉዳቶች ምንድን ናቸዉ? • አኒሚያ (የደም ማነስ) ከፍተኛ የሆነ ደም በሚፈስ ጊዜ በሰውነታችን ውስጥ ኦክስጂን ተሸካሚ ቀይ የደም ሴሎች መጠን ስለሚቀንስ የድካምና ራስ የመሳት ሁኔታዎችን ያስከትላል፡፡ • ለውስጣዊ ሄሞሮይድ የሚደርሰው የደም ፍሰት መጠን ሲቀንስ ከፍተኛ የሆነ ሕመምን ያስከትላል፡፡ ይህም ለሴሎች መሞት እና ለጋንግሪን ይዳርጋል፡፡ በቤት ውስጥ የሚደረጉ ሕክምናዎችና የአኗኗር ዘይቤ ለውጦች • ለብ ባለ ውሃ ከ10 – 15 ደቂቃ በቀን በቀን ሁለትና ሶስት ጊዜ መዘፍዘፍ • ሁሌም ከተፀዳዱ በኋላ በሚገባ በንፁህ ለብ ባለ ውሃ መታጠብ • ደረቅ የሆነ የመፀዳጃ ወረቀትን አለመጠቀም • እብጠት እንዲቀንስ በረዶን መጠቀም • ሕመም ማስታገሻ መድኃኒቶችን መጠቀም ከላይ የተጠቀሙትን በመጠቀም በአጭር ጊዜ ውስጥ ሄሞሮይድን ማጥፋት የሚቻል ሲሆን ሕመም የሚያብስ ከሆነ እና ምንም ዓይነት ለውጥ በሳምንት ውስጥ ካላገኙ ወደ ሕክምና ቦታ እንዲሄዱ ይመከራል፡፡ ሄሞሮይድን ለመከላከል ምን ማድረግ ይገባል? • በፋይበር የበለፀጉ ምግቦችን ማዘውተር - አትክልት፣ፍራፍሬዎችን መመገብ ሠገራን በማለስለስ ማስማጥ እንዳይኖር ያድርጋል፡፡ • ፈሳሽ በብዛት ይውሰዱ - በቀን ከስድስት እስከ ስምንት ብርጭቆ ውሃን ወይም ጭማቂን መውሰድ • ማስማጥን ማስወገድ - ሠገራን ለማስወጣት በምናምጥ ጊዜ በደም ስሮቻችን ላይ ከፍተኛ የሆነ ግፊትን ስለምንፈጥር ለሄሞሮይድ/ለኪንታሮት/ ተጋላጭንት ይጨምራል፡፡ • ሠገራ በሚመጣ ጊዜ ጊዜውን ሳያልፉ ወደ መፀዳጃ ቤት በመሄድ ያስወግዱ፡፡ አለዚያ ሠገራዎ ስለሚደርቅ ለማስወገድ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ • የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያዘውትሩ - የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ ጤናማ እንድንሆን ያደርጋል፣ • ለረጅም ሰዓታት መቀመጥን ያስወግዱ፡፡ በተለይም በመፀዳጃ ቤት ለረጅም ሰዓት መቀመጥ ለሄሞሮይድ መከሰት ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ ለበለጠ መረጃ 👇👇 https://t.me/jossiale2022
Mostrar todo...
Info Health Service (አይ ኤች ኤስ የጤና ማዕከል, IHS Health and Wellness Consultation Center )

አገልግሎታችን በአካል ቀርበው ለማግኘት፤ ለማማከር፥ ቀጠሮ_ለማስያዝ በ 0913744598 ላይ ይደውሉ። #ጎተራ_ንፋስ_ስልክ_ማሞ_ራሚ_ህንፃ_4ኛ_ፎቅ_ ላይ ያገኙናል።

3👍 1👎 1
" የተጠየቀው የህክምና ወጪው በመንግሥት የሀኪም ደመወዝ እና በቤተሰቦቼ አቅም የሚቻል አይደለም " - ዶ/ር ሳምሶን ይስሀቅ ዶ/ር ሳምሶን ይስሀቅ ላጋጠመው የጤና እክል መታከሚያ ደጋግ ኢትዮጵያውያን እንዲተባበሩት ጠየቀ። ዶክተሩ 2015 ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በህክምና ሙያ ትምህርት ነው የተመረቀው። ከተመረቀ በኃላም ለ6 ወራት በጠቅላላ ሀኪምነት ወገኑን ሲያገለግል ቆይቷል። በድንገት ግን ሚዛኑን ስቶ መውደቅ እና ሌሎችም ምልክቶችን በማሳየቱ ወደ ጤና ተቋም ሄዶ ምርመራ ካደረገ በኋላ ' የጭንቅላት እጢ ' እንዳለበት ተነግሮታል። የናሙና ምርመራ ተደርጎ ' GradeIII Astrocytoma ' እንዳለበት ተገልጾለታል። " ትልቅ ቦታ ደርሼ ማየት ለሚመኙት ቤተሰቦቼና ከኔ በታች ላሉት እህት ወንድሞቼ ዜናው በጣም ትልቅ ዱብዳ ነው የሆነባቸው " ያለው ዶክተር ይስሃቅ " የጥቁር አንበሳ የጭንቅላት ቀዶ ጥገና ሀኪሞች ወደ ውጪ ሀገር ሄጄ ህክምና ማድረግ እንዳለብኝ ወስነዋል " ሲል ገልጿል። ለህክምናው ወጪው እስከ 👉 2.3 ሚሊዮን ብር  እንደሚያስፈልግም እንደተነገረው አስረድቷል። ይህን ከፍተኛ ወጪ በመንግስት ሰራተኛ የሀኪም ደሞዝም ሆነ በቤተሰቦቹ አቅም የሚቻል ባለመሆኑ ሁላችሁም የቻላችሁትን እንድትረዱት ተማጽኗል። ዶ/ር ይስሃቅ " በየሃይማኖታችሁ ፈጣሪ በመንገዴ ሁሉ እንዲረዳኝ በጸሎታችሁ አስቡኝ " ሲልም ጠይቋል። ከዶክተሩ የተላከ የህክምና ማስረጃን መመልከት የቻልን ሲሆን  ወላጅ እናቱን ብርሃኔ በየነን በስልክ ቁጥ ር +251911353752 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል። እገዛ ለማድረግ የምትፈልጉ ፦ ዶክተር ሳምሶን ይስሃቅ በየነ ንግድ ባንክ ፦ 1000139965691 አዋሽ ባንክ ፦ 013201172039000 ብርሃኔ በየነ ሚደቅሳ (እናት) ንግድ ባንክ ፦ 1000549927681 አዋሽ ባንክ ፦ 01347903970500 GoFundMe👇 https://gofund.me/618fc8ee
Mostrar todo...
Help save the doctor, organized by Abigia Aschalew

Hello my name is Abigia and I'm fundraising to help my brother Dr.Samson Yishak Beyene a 28 year … Abigia Aschalew needs your support for Help save the doctor

👍 4
#ከሩካቤ_ስጋ_ጋር_የሚከሰቱ_የጤና_ጠንቆች 👫ጤነኛ ሩካቤ ስጋ ዘርፈ ብዙ የጤና ጥቅሞች ያሉት ሲሆን ጤነኛ ያልሆነ ወሲብ ደግሞ የተለያዪ የአካል እና የስነልቦና ጠንቆችን ያመጣል። ጤነኛ ያልሆነ ሩካቤ ስጋ (ወሲብ) ሊያመጣቸው የሚችሉ የጤና ችግሮች እጅግ ብዙ ናቸው። ከእነዚህ መካከል 1. 🧖‍♂️ለተላላፊ በሽታዎች መጋለጥ ኤችአይቪ ኤድስ፣ የጉበት ቫይረሶች፣ ጨብጥ ፣ቂጥኝ፣ ባንቡሌ፣ ከርክር  ፣የብልት ተባይ እንዲሁም ሌሎች ያልተጠቀሱ ተላላፊ ህመሞች ባልተቆጠበ ሩካቤ ስጋ ምክነያት ይፈጠራሉ። 🧖‍♀️2. ያልተፈለገ እርግዝና ያልተፈለገ እርግዝና አካላዊ ፣ አይምሮአዊእና ማህበራዊ የጤና ቀውስ የሚያስከትል ሲሆን ለውርጃ፣ ለከፍተኛ መድማትና ለሞት አደጋ ያጋልጣል። 👥3.የወሲብ ሱስ ወሲብን እንደ መደበኛ ስራ በማድረግ የእለት ተእለት እንቅስቃሴን በማሰናከል ለአይምሮ ጤና መቃወስ ያጋልጣል። 👀4. የአይምሮ ጭንቀት እና ድባቴ ከወሲብ በኋላ የወሲብ መዘዞችን በማሰብ መጨነቅ ድብርትና የአይምሮ ውጥረትን ይጨምራል። 🕴5.ከመጠን በላይ ክብደት መቀነስ ወሲብ ላይ በማተኮር የምግ ፍላጎት መቀነስ ፣ የሰውነት ፈሳሽ ከመጠን በላይ ማጣት እንዲሁም የጭንቀት ሆርሞኖች በመጨመር ከመጠን በላይ ክብደት እንዲቀንስና ለምግብ እጥረት(malnutrition)ያጋልጣል። 👫6. የስራ ትኩረት ማጣት እና ውጤት መቀነስ ለስራ ሞራል ማጣት፣ ትኩረት ማጣት እና ጊዜን በወሲብ ማሳለፍ ለስራ ውጤት መቀነስ አስተዋፅኦ ያደርጋል። 🤞7. የመራቢያ አካላት ጉዳት አግባብ የሌለው ወሲብ በሁለቱም ፆታ ላይ የሚከሰቱ መፋፋቅ፣  መሰንጠቅ እንዲሁም መተርተርንና የወንድ ብልት መሰበር ሊያስከትል ይችላል። 🤺8.ግንኙነት መፍራት የመጀመሪያ ግንኙነት ጤነኛ ካልሆነ መልሶ ግንኙነት ማድረግን መፍራት እንዲሁም የተቃራኒ ፆታ ጥላቻን ያሳድራል። 🤹‍♂️9.ከልክ ያለፈ ድካም በስራ ላይ ጫና የሚያሳድር  ድካም እና የቀን እንቅልፍን እና ከልክ ያለፈ ድካም ያስከትላል። 🎠10. የወገብ እና የዳሌ አካባቢ ህመም ለአጭር ጊዜ ወይም ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የወገብ የዳሌ አካባቢ ህመም ሊያመጣ ይችላል። በተለይ ስነልቦና ጋር ጉዳት ካስከተለ የማይታይ አካላዊ ህመምን ይፈጥራል። 🧬11. ካንሰር የማህፀን በር ካንሰር(cervical ca) ፣ የፊንጢጣና የብልት ካንሰር የሚያመጣውን HPV ቯይረስ መተላለፊያው ልቅ የግብረስጋ ግንኙነት ነው። 📈12. አንዳንድ ህመሞችን ያባብሳል ከፍተኛ የልብ ህመም እና የጭንቅላት የደም ስር ችግር(Aneurysm) መባባስ እንዲሁም በወሲብ ወቅት መቸገር  ሊያስከትል ይችላል። 🚫🚫🚫🚫🚫🚫🚫🚫🚫🚫🚫 ጤነኛ የሆነ ሩካቤ ለመልካም ጤና! ጤና ተመኘንልዎ። በቀናነት ሸር ያድርጉ!!!! ዶ/ር ነጋልኝ መቻል https://t.me/venasia https://t.me/jossiale2022 #በአካል_ቀርበው_ቢያገኙን_በአገልግሎታችን_ይረካሉ። ለቀጠሮ ማስያዣ ስልክ ቁጥር = 0921785903 ➮በፅሁፍ መልዕክት ቢያስቀምጡ ይመረጣል። ➯አድራሻ #ከጎተራ_ከፍ_ብሎ_ማሞ_ባቡር_ጣቢያ_ራሚ_ህንፃ_4ኛ_ፎቅ_ቢሮ_ቁጥር_402 ያገኙናል። 1. የዩቲዩብ አድራሻ = https://youtube.com/channel/UCM2HMbAuepuSrLQGVvhLUHw?sub_confirmation=1 2. የቴሌግራም አድራሻ = https://t.me/jossiale2022 3. የቲክቶክ አድራሻ = tiktok.com/@infohealthcenter 4. የፌስቡክ አድራሻ = https://www.facebook.com/yosef.alebachew.9 5. የፌስቡክ ፔጅ =https://www.facebook.com/profile.php?id=100064131361093
Mostrar todo...
👍 9
   #CPD_Training_ማክሰኞ_ይጀምራል ETHIO_MEDICAL_TRAINING_CENTER            #የፊታችን_ማክሰኞ_ሚያዚያ_22_ጀምሮ #BASIC_lIFE_SUPPORT (BLS) ስልጠና እንጀምራለን። #15CEU ይይዛል። ስልጠናው ለማንኛውም የጤና ባለሙያዎች  የሚሰጥ ስለሆነ በ 0921785903 ደውለው ይመዝገቡ። #ሰልጣኞች፦ ➯ ሀኪሞች ➯ ነርሶች ➯ ፋርማሲዎች ➯ ለላብ ባለሙያዎች እና ለሌሎችም የሚሆን https://t.me/ethiomedicaltrainingplc ባሉበት ሁነው ይደውሉ!!! ይመዝገቡ። 0921785903 አድራሻ፦ ጎተራ ንፋስ ስልክ ማሞ ባቡር  ፌርማታ ሲደርሱ ንግድ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Mostrar todo...
👍 1 1
   #CPD_Training_ነገ_ጧት_ይጀምራል ETHIO_MEDICAL_TRAINING_CENTER            #የፊታችን_ቅዳሜ_ሚያዚያ_19_ጀምሮ #Pain_management ስልጠና እንጀምራለን። #15CEU ይይዛል። ስልጠናው ለማንኛውም የጤና ባለሙያዎች  የሚሰጥ ስለሆነ በ 0921785903 ደውለው ይመዝገቡ። #ሰልጣኞች፦ ➯ ሀኪሞች ➯ ነርሶች ➯ ፋርማሲዎች ➯ ለላብ ባለሙያዎች እና ለሌሎችም የሚሆን https://t.me/ethiomedicaltrainingplc ባሉበት ሁነው ይደውሉ!!! ይመዝገቡ። 0921785903 አድራሻ፦ ጎተራ ንፋስ ስልክ ማሞ ባቡር  ፌርማታ ሲደርሱ ንግድ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Mostrar todo...
👍 3