cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ኩሉ ነፍሲ ዛኢቀተል መዉት

አንተ ወጣት ሆይ ተዉሂድ ህይወትህ ነዉ ኑርለት!!!!! ስጋህ ነው ጠብቀዉ ፣ደምህ ነው virus እንዳይቀላቀልበት ጠብቀው ብቸኛ ሀብትህ ነው ለሰዎች ሼር አድርገው ቀጥ በል በተውሂድ ከሽር ክ ቦታ እራቅ የሽርክና የሙሽሪኮች የቢድአ ና የሙብተዲኦች ጠበቃ ና አማካሪ አትሁን ለዲን መስዋት ሁን @Yarsululahhh @rahu_bot የሚለቀቀው Islamic ነገሮች @Yarsululahhh

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
155
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

As wr wb
Mostrar todo...
የማይፋቅ ስህተት ክፍል 26 አምሪ ኮስተር እንደማለት እያለች "ከዚህ በኋላ ሌላ ሴት አያለሁ ብትል ግን ሟች ነህ!" አለችኝ። እየሳቅኩ "ያዉ እሱማ መች ይቀራል?" አልኳት። አምሪ እየተነጫነጨች "ሞክረዉ እና ታየኛለህ!" አለችኝ። አሁን በህይወቴ ዉስጥ ሰላም ለማግኘት የፌቨን ህይወት ተስተካክሎ ማየት አለብኝ። ማበላሸት ቀላል ነዉ። ያፈረሱትን ለመገንባት መሞከሩ ግን በጣም ይከብዳል ። አንዳንዱን ብልሺት ደግሞ መጠገን የማይችል ነው። አምሪ ሁሉንም ጉዴን ማወቋ ትንሽ እረፍት ሰጠኝ። ይቅርታዋ ልቤን አረጋጋዉ። በነጋታዉ ፌቨንን ከአምሪ ጋር አገናኘኋት። አምሪ እኔን እንደገና መስራት ችላለችና ፌቪን መስራት አይከብዳትም ብዬ አስቤያለሁ። ሀጂ ትምህርት ቤታችን ዉስጥ ልዩ ዝግጅት አዘጋጅተዉ ሊድሩን እየተሯሯጡ ነዉ። አምሪን ከፌቪ ጋር ካስተዋወቅኳት ሳምንት አለፈ። አምሪ ከሷ ጋር ከተግባባች በኋላ የፌቪን ቤተሰቦች አናገረች። ቤተሰቦቿ መፀፀቷን ሲሰሙ በጣም ደስ ብሏቸዉ ተቀበሏት። እኔም እረፍት አገኘሁ። . የኔና የአምሪ ጋብቻ ጥቅምት መጨረሻ ላይ እንዲደረግ ቀኑ ተቆረጠ። ጥቅምት 26 ሀሙስ ቀን ትምህርት ቤታችን ዉስጥ በጣም ደስ የሚል ድግስ ተዘጋጀ። የመርከዙ ተማሪዎች የተለያዩ ዝግጅቶችን አቀረቡ። በኋላ ላይ ምስክሮች ባሉበት የኒካህ ስነ ስርዓቱ ተፈፀመ። አምሪ ሚስቴ ሆነች። አምሪ የኔ ዉድ! ጋብቻችን ቢፈፀምም አብረን መኖር ለመጀመር ያሰብነዉ ግን ከአራት ወራት በኋላ ነዉ። እነሰሚራ የኛን ቤት ለቀዉ ሌላ ቤት ለመቀየር የሚያስፈልጋቸዉን ጊዜ ለመስጠትና እኛም የሚያስፈልጉንን ነገሮች ለማዘገጃጀት እንዲረዳን አስበን ነዉ። የኒካህ ስነ ስርዓቱ ሲያልቅ ሀጂ ብድግ አሉና "ያዉ ዛሬ ሁለት ልጆቼን ድሬያለሁ። ሽኩሪያ የሰጠችኝን አደራ ተወጣሁ ማለት እችል ይሆን? አላዉቅም! ለማንኛዉም ሀቢብ አሁን ትምህርት ቤቱ ዉስጥ ከማስተማር እና ከመማር በዘለለ የተቋሙን ስራ በምክትል ስራ አስኪያጅነት ታስተዳድረዋለህ። እዉቀቱ ስላለህና ጠንካራም ስለሆንክ ትልቅ ደረጃ እንደምታደርሰዉ ተስፋ አለኝ።" አሉ። እንባ እየተናነቀኝ አቀፍኳቸዉ። ከዝቅጠቴ የነፃሁበትን ተቋም ታላቅ ደረጃ በማድረስ ብዙዎችን ለመጥቀም ለራሴ ቃል ገባሁ። . አምሪያን ካገባሁ ከአንድ ወር በኋላ ዉጪ ሀገር ያሉ ሴቶች ገንዘባቸዉን እንደነሚኪ ባሉ ሰዎች እንዴት እንደሚገፈፉ በዝርዝር የሚያስረዳ ቪዲዮ አዘጋጅቼ የፌስቡክ ገፄ ላይ ለቀቅኩ። እንደ ተሚማ ያሉ ሴቶች ይማሩበት ይሆናል። ቪዲዮዉ በጣም ብዙ ተመልካች አገኘ። አንዳንዶች የደረሰባቸዉን በሙሉ ይፅፉልኝ ጀመር። ሰው በስንቱ እንደሚበዘበዝ ሳስብ ሴቶቹ አሳዘኑኝ። ከአምሪ ጋር ባልናሚስት ከተባልን ወር ከአስራአምስት ቀን ሆነዉ። ሀሙስ ነበር። መርከዝ ቤተ መፅሀፍ ተቀምጬ እያነበብኩ ነዉ። አምሪ ደወለችልኝ። ስልኩን አንስቼ "ወዬ የኔ ዉድ!" አልኳት። "ሆዴ ኸበር አለ! ፌቨን ወለደች።" አለችኝ። ኸበር ማለት ዜና ማለት ነዉ። የሆነ የደስታ ስሜት እየተናነቀኝ "መች ወለደች?" አልኳት። "ከትናንት ወዲያ ነዉ አሉ! ዛሬ መስማቴ ነዉ!" አለችኝ። ወደ ማታ ተገናኝተን አራስ ለመጠየቅ ለመሄድ ተቀጣጠርን። አስራአንድ ሰዓት አካባቢ ከአምሪ ጋር ሆነን ፌቪን ለመጠየቅ ወደ ቤታቸዉ ሄድን። ቤታቸዉ ባለ ሶስት ፎቅ ነዉ። በጣም ያምራል! ከዚህ የመሰለ ቤት አዉጥቼ እንዳሰቃየኋት ሳስብ በጣም አመመኝ። ቤቱ ዉስጥ ስንገባ ሰራተኛቸዉ ፌቨን ወዳለችበት ክፍል እየመራች ወሰደችን። ፌቪ ልጇን አቅፋ ተጋድማለች። እኛ እዛዉ እንዳለን ሚኪ፣ከሪሜ እና ኤልዳና ሊጠይቋት መጡ። "ሀቢቤ!" አለ ሚኪ እያቀፈኝ። በጣም ከሳስተዋል። በአትኩሮት እያየኋቸዉ "እንዴት ናችሁ?" አልኩ። ሚኪ "ያዉ እንዳንተ ባንሆንም ደህና ነን!" አለ። ከነሚኪ ጋር ብዙ ነገሮችን ተጨዋወትን። ሚኪ ባጃጅ ገዝቶ ከኤልዳና ጋር አብሮ መኖር ጀምሯል። ያዉ የፈረደባቸዉን ግጦ እንደገዛዉ አልጠፋኝም። ከሪሜ ትምህርቱን ቀጥሏል። አብነት ግን ክፍለሀገር ከሄደ በኋላ ደዉሎላቸዉ እንደማያዉቅ ነገሩኝ።ከነሚኪ ጋር ተጨዋዉተን ፌቪንም ትንሽ አጫዉተናት ተሰናብተን ወጣን። ቤተሰቦቿ በደንብ የሚንከባከቧት ይመስለኛል። . ጊዜዉ መቁጠሩን ቀጥሎ እነሰሚራም ቤቱን ለቀዉልን ታች ሰፈር ሌላ ቤት ተከራዩ። ሀጂም ለአንዳንድ ነገር እንዲሆነኝ ብለዉ የቤት ኪራዩን ገንዘብ ወደ ባንክ አካዉንቴ አስገቡልኝ። አጠቃላይ ሁለት መቶ ሺህ ብር አካባቢ ይሆናል። ቤቱን ካሳደስነዉ በኋላ የቤት እቃዎችን ገዝተን አሟላን። ያዉ ሴት ያለበት ቤት መድመቁ የግድ ነዉና ቤታችን በአምሪ እቅድ ተኳለ። ቤታችንን አስተካክለን ከጨረስን በኋላ በተጋባን በአምስተኛዉ ወር አብረን መኖር ጀመርን። እኔ ሀጂ የሰጡኝን ሀላፊነት ከትምህርቴ ጋር ደርቤ እያስኬድኩ ነዉ። አምሪ የህክምና ትምህርቷን እየተከታተለች ነዉ። የሶስተኛ ዓመት ተማሪ ናት። ማታ ማታ ማጥናት ስትፈልግ ወተትእናቡና እያፈላሁ ማኪያቶ እሰራላታለሁ። እሷ አምሽታ የምታጠና ቀን እኔም ስፅፍ አመሻለሁ። አሁን ፌስቡክ ላይ መቶ ሺህ ተከታይ አፍርቼያለሁ። ብዙ ቦታዎች እየዞርኩ አስተምራለሁ። አንዳንዴ አምሪ ሳሎን ተቀምጣ እያነበበች እንቅልፍ ይዟት እብስ ይላል። እንደህፃን ልጅ እቅፍ አድርጌ ወደ አልጋዉ እወስዳትና አስተኛታለሁ። ከዛም ረዥም ሰዓት ቆሜ አያታለሁ። ይህቺን የመሰለች ሴት አገባለሁ ብዬ በህልሜ እንኳ አስቤ አላዉቅም። የክፍተቴ ሁሉ መሙያ! የኔ ውብ! ትዳር ግን ምን የሚሉት ዉብ ጥምረት ነዉ? በተጋባንባቸዉ ቀናት ዉስጥ ያጣጣምኳቸዉን ደስታዎች ቆጥሬ አልዘልቃቸዉም። ሀጂ እና ልጆቻቸዉ በኛ ትዳር በጣም ደስተኛዎች ናቸዉ። . ከአምሪ ጋር መኖር ከጀመርን አንድ ወር ሞላን። ዛሬ ማታ ሶስት ሰዓት ሲል ቤት ገባሁ። አምሪ ነገ ፈተና ስላላት እያጠናች ነዉ። እራት አቀራርባ ስለነበር እጃችንን ታጥበን በላን። አምሪን ማጉረስ በራሱ ትልቅ ደስታ አለዉ። የኔ ሁሉነገር! የሁልጊዜ ንግስቴ! የንግስናዬ መሟላት ምክንያት! ምግቡን እየተጎራረስን በልተን እንደጨረስን ወደ ማዕድቤት ሄድኩ። ይዤ የመጣሁትን ወተት ላፈላ ማንቆርቆሪያዉ ዉስጥ ስገለብጥ አምሪ መጥታ "ሁቢ ተወዉ እኔ አፈላለሁ።" አለችኝ። አይሆንም ብዬ ወደ ጥናቷ መለስኳት። ተመልሳ ንባቧን ቀጠለች። ወተቱን አፍልቼ ስጨርስ ወደ ሳሎን ወስጄ አቅርቤላት እኔም ማንበብ ጀመርኩ። በመሀል የአምሪ ስልክ ብልጭ ብሎ ጠፋ። የፅሁፍ መልዕክት ገብቶላት ነዉ። ከፈተችዉና ካነበበችዉ በኋላ ወደኔ አዙራ አሳየችኝ። "ታንክስ ፎር ኦል አምሪ! በት ፎር ሚ ኢትስ ሶ ሀርድ ቱ ሊቭ ኢን ዲስ ዎርልድ! ፋር ዌል ቱ ዩ ሲስ!" ይላል። ግራ እየተጋባሁ "ከማን ነዉ?" አልኳት። አምሪ እንባዋ ከአይኗ እየወረደ "ሀቢቤ ፌቨን ናት!" አለችኝ። የሆነ ነገር ሰዉነቴን ነዘረኝ። ግራ እየተጋባሁ "ማለት ምን ልታደርግ ነዉ?" አልኳት። አምሪ እንባዋን ለመጥረግ እየሞከረች "ሀቢቤ መልዕክቷ እኮ እዚህ ምድር ላይ መኖር ከብዶኛል ደህና ሁኚ ነዉ የሚለዉ!" አለችኝ። "እና ይሄ ምድር ከከበዳት የት ልትሄድ ነዉ?" ካልኩ በኋላ ሳስበዉ የመልዕክቱ ትርጉም ገባኝ። ክፍል 27 ይቀጥላል... SHARE👇 @Yarsululahhh @Yarsululahhh @Yarsululahhh 👌👌👌👌
Mostrar todo...
Join Join Join 🙏🙏🙏🙏
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.