cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ሁሌ መረጃ.com/hule merja

የሰው ልጅ መረጃ የማግኘት መብቱ መገደብ የለበትም...እኛም ይህንን ፍላጎት ለመሙላት እዚ አለን፡፡ሁሌ መረጃ ሁሌ እውነት

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
660
Suscriptores
+124 horas
+37 días
+1330 días
Distribuciones de tiempo de publicación

Carga de datos en curso...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Análisis de publicación
MensajesVistas
Acciones
Ver dinámicas
01
Media files
230Loading...
02
ኢትዮጵያ የራሷ የኮሙዩኒኬሽን ሳተላይት ባለቤት እንድትሆን የአዋጭነት ጥናት ተጠናቋል፡- የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት ኢትዮጵያ የራሷ የኮሙዩኒኬሽን ሳተላይት ባለቤት እንድትሆን የአዋጭነት ጥናቱ ተጠናቆ ለሚመለከተው የመንግስት አካል ለውሳኔ መላኩን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት ገለፀ፡፡ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር ቤተልሔም ንጉሴ፤ ኢትዮጵያ የራሷ ኮሙዩኒኬሽን ሳተላይት ስለሌላት በአሁኑ ወቅት ከሉግዘመበርግ ኢ ኤስ ኢ ኩባንያ ኢትዮ ሳትን  በመጠቀም ላይ ትገኛለች ብለዋል፡፡ ኢትዮ ሳት ኢትዮጵያ ለሳተላይት የምታወጣውን ከፍተኛ ወጪ ከመቀነስ፣ የባህል ወረራን ከመከላከል እንዲሁም ሀገራዊ እሴትን ከማስጠበቅ አንጻር ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ኃላፊዋ አንስተዋል፡፡ በኢትዮጵያ ከ2014 ዓ.ም በአዲስ መልክ የተደራጀው የስፔስ ሳይንስና ጂኢስፓሻል ኢንስቲቲዩ፤ በቀጣይ ኢትዮጵያ የራሷ የኮሙዩኒኬሽን ሳተላይት ባለቤት እንድትሆን የአዋጭነት ጥናት ተጠናቆ ለፕላንና ልማት ሚኒስቴር  መላኩንና ውሳኔ እየተጠበቀ መሆኑን ገልጸዋል። Via EBC
510Loading...
03
ቦይንግ የ346 ሰዎችን ህይወት በቀጠፈው የ737 ማክስ አውሮፕላን አደጋ ክስ ሊመሰርትበት እንደሚችል ተገለፀ በኢትዮጵያው አየር መንገድ እና የኢንዶኔዥያው የ737 ማክስ 9 አውሮፕላን አደጋዎች የ346  ሰዎችን ህይወት በቀጠፈው አደሳ ምክንያት ቦይንግ ላይ ክስ ለመመስረት እያጤነ እንደሆነ የአሜሪካ የፍትህ መስሪያ ቤት አስታወቀ። ቦይንግ የሚያመርታቸውን አውሮፕላን ምርቶች ደኅንነት እና ጥራት ለማስጠበቅ ከ3 ዓመት በፊት ከአሜሪካ የፍትህ ሚኒስቴር ጋር የገባውን የቁጥጥር መርሃ ግብር ስምምነት መጣሱንም መስሪያ ቤቱ ስለመግለፁ ቢቢሲ በዘገባው አመልክቷል። ቦይንግ ስምምነት ጥሷል የተባለውን ክስ አስተባብሏል። ይህ አስከፊ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን አደጋ በኢትዮጵያው 157 እንዲሁም በኢንዶኔዥያው አየር መንገድ 189 ሰዎች ህይወት መቅጠፉ ይታወሳል።
940Loading...
04
በሀገሪቱ ያለው የፀጥታ ችግር የማዕድን ዘርፉን እየጎዳው ነው ። የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን  የሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን ሀላፊ  ካሳሁን ለምለሙ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በሀገሪቱ ያለው የፀጥታ ሁኔታም ያለንን ሀብት በተገቢው መልኩ እንዳንጠቀም አድርጎናል ብለዋል ፡፡ በሀገራችን በሚገኙ በርካታ ክልሎች ከፍተኛ የሆነ የማዕድን ክምችት እንደሚገኝ ጠቅሰዋል፡፡ ባለ ሀብቶች ወደ ማዕድን ኢንዱስትሪ ከገቡ ሀገሪቱ ከዘርፉ ከፍተኛ ጥቅም ታገኛለች ተብሎ እንደሚጠበቅም አስረድተዋል፡፡ ማዕድን ለማውጣት የሚያግዙ ከውጪ የሚገቡ ማሽነሪዎች ለማስገባት የሚያስፈልገው ወጪ ከፍተኛ መሆን እና  የመሰረተ ልማት ችግር  ሌላኛው በዘርፉ የሚነሳ እንቅፋት መሆኑን አቶ ካሳሁን ጠቅሰዋል፡፡ ተቋሙ በዘርፉ ያለውን ክፍተት ለማስተካከልም በማምረት ፣በፍለጋ፣በጥናት እና በማዕድን ሽያጭም ከፍተኛ ስራ ለመስራት የቅድመዝግጅት ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡ አሁን ካሉት በተጨማሪ በተለያዮ አካባቢዎች ላይ አዳዲስ ሳይቶች እየከፈቱ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል። የወርቅ ምርቶችን ፣ኢንዱስትሪ ማዕድናትና የከበሩ ድንጋዮችን ለደንበኞቹ በመላክ ለሀገራችን የውጪ ምንዛሬ ለማስገባት ከፍተኛ ስራ እየሰራን እንገኛለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡
1090Loading...
05
የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ሰዉ ሰራሽ የነዳጅ እጥረት እንዲፈጠር በሚያደርጉ ነዳጅ ማደያዎች ላይ ከማሸግ የዘለለ እርምጃ መዉሰድ የሚያስችለውን አዋጅ ማዘጋጀቱ ተነገረ! ባለስልጣኑ ባዘጋጀው በዚህ አዋጅ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሰው ሰራሽ የነዳጅ እጥረት በሚፈጥሩ ሕገ ወጦች ላይ እስራትና የገንዘብ ቅጣት እርምጃ መውሰድ የሚያስችሉ አንቀጾች መካተታቸውን ተጠቁመዋል። አዋጁ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መቅረቡን ተከትሎ በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ ወደ ስራ እንደሚገባ የተነገረ ሲሆን በነዳጅ ማደያዎች ነዳጅ እያለ እንደሌለ ማስመሰል፣ የነዳጅ ግብይትን በጥሬ ገንዘብ መሸጥ፣ ነዳጅን በተለያዩ ስፍራዎች ደብቆ ማስቀመጥና የመሳሰሉትን ህገወጥ አሰራሮችን ሊያስቀር እንደሚችልከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።
1060Loading...
06
በጂንካ የ8 ዓመት ታዳጊን  አስገድዶ ግብረ ሶዶም  ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ  ጽኑ እስራት ተቀጣ በጂንካ ከተማ በ8 ዓመት ታዳጊ ልጅ ላይ የአስገድዶ ግብረ ሶዶም   መድፈር ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በጽኑ እስራት እንደተቀጣ የጂንካ ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት አስታዉቋል፡፡ የጂንካ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ግንቦት 2 ቀን 2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት ውሳኔዉን በተከሳሹ ላይ አስላልፎበታል፡፡ተከሳሽ ወጣት ማንያዘዋል አዳሙ  የካቲት 15 ቀን 2016 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 2:00 ሰዓት አከባቢ ድርጊቱን መፈፀሙን በማመኑ ባመነው መሰረት ማስረጃ መስማት ሳያስፈልግ  ውሳኔ እንደተሰጠ የጂንካ ከተማ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት  አቶ በቃሃኝ ጥላሁን  በተለይም  ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል  ። ተከሳሽ የግል ተበዳይን እኔ ጋር  አሳድራለው በማለት ከቤተሰቦቹ  በመውሰድ ህፃኑን አስገድዶ  ግብረ ሶዶም ወንጀል  መፈፀሙ አረጋግጧል ። አሰገድዶ የመድፈር ወንጀል የደረሰበትን ህፃን ለጤናም ሆነ ለስነ-ልቦና ጉዳት የሚዳርግ ተግባር ከመሆኑ አንጻር በጂንካ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠው  ውሳኔ ተከሳሽንና ሌሎችንም  መሠል ወንጀል አድራጊዎችን የሚያስተምር ውሳኔ አስተላልፎበታል፡ በመሆኑም  ግንቦት 2 ቀን 2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት አስገድዶ ግብረ ሶዶም መፈፀሙን ሙሉ በሙሉ በችሎት ቀርቦ በማመኑ የጂንካ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት  በ15 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ  መወሰኑን አቶ በቃኀኝ ጥላሁን ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል  ፡፡ በኤደን ሽመልስ #ዳጉ_ጆርናል
1310Loading...
07
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሁለት ወረዳዎች የድሮን ጥቃት መፈጸሙን ነዋሪዎች ገለጹ። በቀወት ወረዳ ተሬ ቀበሌ በሚገኘው ጉሎ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ በተፈጸመው የድሮን ጥቃት ንጹሃን ህይወታቸው ማለፉንና መቁሰላቸውን የአይን እማኞች ለአል አይን አማርኛ ተናግረዋል። በጣርማበር ወረዳ በሚገኘው የመዘዞ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይም የድሮን ጥቃት መፈሙን የገለጹ ነዋሪዎች በሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ነው ያብራሩት። ዘገባው የ AL AIN ነው
1300Loading...
08
ከሐዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረዉ አዉሮፕላን ዉስጥ ታይቷል የተባለዉ ጭስ በዉስጡ ያለዉ ዘይት በመቃጠሉ የተነሳ መሆኑ ተገለፀ! የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰሞኑ በአዉሮፕላኑ ላይ የተከሰተው ጉዳይን አስመለክቶ እንዳስታወቀው ከእሳት ወይም ከሌላ ነገር ጋር የተያያዘ ሳይሆን አዉሮፕላን ዉስጥ ያለዉ ዘይት ተቃጥሎ ነዉ በወቅቱ የተከሰተው ጭስ ሊፈጠር የቻለዉ ይህም አልፎ አልፎ የሚያጋጥም ችግር ነዉ ብሏል። የአየር መንገዱ ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰዉ በተለይ ለካፒታል እንደተናገሩት " በአዉሮፕላኑ ዉስጥ ያለዉ ዘይት መጋጠሉ እና ከእርሱ ጋር ተያይዞ የተፈጠረ ጭስ ነዉ ይህ ደግሞ የተለመደ ነዉ ብለዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET154 ሚያዝያ 29፣ 2016 ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያለ በአውሮፕላን ውስጥ ጭስ መታየቱን አስታዉቆ እንደነበር ይታወቃል ። [Capital]
1350Loading...
09
Media files
1490Loading...
10
Media files
1750Loading...
11
የ10 ዓመት ታዳጊን ዋና ካልዋኘህ በማለት ውሃ ውስጥ ገብቶ ህይወቱ እንዲያልፍ ምክንያት ሆኗል የተባለ ግለሰብ በእስራት ተቀጣ በምስራቅ ሀረርጌ ዞን  ጃርቱ ወረዳ ሙለታ  ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የ10 ዓመት ታዳጊ ውሃ ውስጥ ዘሎ ለመዋኘት ሲገባ ህይወቱ ማለፉን  የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት  ገልጿል፡፡ ተከሳሽ አንሴ አህመድ የተባለው የ20 ዓመት ወጣት  10 ዓመት ከሆነው  ሙዓዝ  ጋር እየተጫወቱ  በነበረበት  ሰዓት ለምን አትዋኝም የሚል ጥያቄ ሲያቀርብለት መዋኘት አልችልም  የሚል ምላሽ ሲሰጠው  እንዴት ትፈራለህ ወንድ አደለህ ወይ  ግባ  በማለት ወደ ውሃ ዘሎ  እንዲገባ ገፋፍቶት ለሞት ምክንያት እንደሆነ የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የኮሙኒኬሽን ክፍል ሃላፊ ካሚል ቱጅሃን በተለይም  ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡ በሰዓቱም የ10 ዓመት ታዳጊው ለመዋኘት  ተንደርድሮ ሲገባ  ውሃው ውስጥ ያለው ድንጋይ ላያጭንቅለቱ ላይ ያርፋል በዚህም አደጋ ወዲያውኑ ህይወቱ አልፏል።  በሁኔታው የተደናገጠው  አንሴ  ልጁን ለማውጣት ይሞክራል። በአካባቢው የነበሩ ነዋሪዎች ደርሰው ተጋግዘው ያወጡታል ይሁን እና ልጁ ጭንቅላቱ ላይ ከባድ ግጭት አጋጥሞት ከውሃ ውስጥ ሳይወጣ  ህይወቱ ማለፉን ይረዳሉ ስለሆነም አደጋውን ለፖሊስ ያሳውቃሉ :: ፖሊስም  አስከሬኑን  ወደ ሆስፒታል ወድያውኑ በመላክ   ምርመራውን ማጣራት ይጀምራል  ተከሳሽም ልጁ ውሃ ውስጥ ሲገባ ልረዳው ነው የገባሁት እንጂ ምንም የማውቀው  ነገር የለም የሚል ምላሽ ቢሰጥም  በአካባቢው የነበሩ የሁለቱን ንግግር ያዳመጡ ምስክሮች ቃላቸውን ይሰጣሉ ፖሊስም በህክምና እና በሰው ማስረጃ መዝገቡን በማደራጀት  ለዓቃቢህግ ይልካል፡፡ የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ  ቤት  ዓቃቢ ህግ ባቀረበው መሰረት ተከሳሸ ሆን  ብሎ ለአደጋ በሚጥል መንገድ ሰውን  በመገፋፋት የግድያ ወንጀል በመፈጸም የተመሰረተበት ክስ  በመመልከት  በተከሳሽ አንሴ አህመድ  ላይ  በ7 ዓመት ከ8 ወር እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ  የተላለፈበት መሆኑን የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የኮሙኒኬሽን ክፍል ሃላፊ ካሚል ቱጅሃን ጨምረውም ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡ በኤደን ሽመልስ #ዳጉ_ጆርናል
1810Loading...
12
በደቡብ ኢትዮጵያ 148 ቀበሌዎች ከ75 ሺህ በላይ የቤተሰብ አስተዳዳሪዎች ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ መሆናቸው ተነገረ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እየጣለ ያለውን የበልግ ዝናብ ተከትሎ 148 ቀበሌዎች ከ75 ሺህ በላይ የቤተሰብ አስተዳዳሪዎች ለጎርፍና ለአፈር ናዳ አደጋ ተጋላጭ መሆናቸው የክልሉ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ገለፀ። የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ጋንታ ጋምአ ለኢዜአ እንደገለጹት መደበኛና ከመደበኛ በላይ የሆነ የበልግ ዝናብ ስርጭት በክልሉ የጎርፍና የአፈር ናዳ አደጋዎችን ሊያስከትል ይችላል። በተለይ ጎፋ፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ አሌ እና አሪ ዞኖች ለጎርፍና ለናዳ እንዲሁም ደቡብ ኦሞ፣ ኮንሶና ጌዴኦ ዞኖች ለጎርፍ አደጋ የመጋላጥ ስጋት ያለባቸው መሆናቸውን ጠቅሰዋል። በመሆኑም በክልሉ የአደጋ ተጋላጭ አካባቢዎችን በመለየት ህዝብን ባሳተፈ መልኩ የቅድመ መከላከል ሥራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።
1950Loading...
13
Media files
1740Loading...
14
በአዲስ አበባ ከተማ በትላንትናው እለት ባጋጠመ የእሳት አደጋ የአንድ ሰዉ ህይወት አለፈ በአዲስ አበባ ከተማ ግንቦት 1ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 5:17 ሰዓት ላይ በቦሌ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 2 ጃፓን ኤንባሲ አካባቢ ባጋጠመ የእሳት አደጋ የአንድ ሰዉ ህይወት ማለፉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል። የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ እንደተናገሩት የእሳት አደጋዉ ያጋጠመዉ በአንድ መጋዘን ላይ ሲሆን ህይወታቸዉ ያለፈዉ ግለሰብ የመጋዘኑ የጥበቃ ሰራተኛ ናቸዉ። የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ቦታዉ ላይ ፈጥነዉ ቢደረሱም የጥበቃ ሰራተኛዉ ህይወት አስቀድሞ ያለፈ በመሆኑ የእሳት አደጋዉ ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር ችለዋል። መጋዘኑ ለመጋዘን አገልግሎት ስራ መዋል የማይገባዉ የመኖሪያ ቤት ቢሆንም ባለንብረቶቹ ቤቱን ለመጋዘን አገልግሎት ይጠቀሙት እንደነበር ኮሚሽኑ አስታውቋል። ማናቸዉም ዕቃዎች የሚቀሙጡባቸዉ መጋዘኖች እሳትን ሊቋቋሙ ከሚችሉ ግብዓቶች የተገነቡና ለዚሁ ዓላማ ብቻ የተገነቡ መሆን ይኖርባቸዋል ሲል ኮሚሽኑ አሳስቧል።
1760Loading...
15
Media files
1880Loading...
16
50 አመታት በሕጻናት መንደሮች የመክፈቻ መርሐግብር ኤስ ኦ ኤስ የሕጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ ላለፉት ሃምሳ ዓመታት የቤተሰባቸውን እንክብካቤ ያጡ እና የቤተሰባቸውን እንክብካቤ ለማጣት በአደጋ ላይ ያሉ ሕጻናት የቤተሰብ እንክብካቤና ጥበቃ አግኝተው እንዲያድጉ ለሁለንተናዊ እድገታቸው  የሚያስፈልገውን  በማሟላት እንክብካቤ ሲሰጥ እንደቆየ አስታውቀዋል። ኤስ ኦኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ለሚገኙ ሕጻናት ያጡትን ቤትና ቤተሰብ በመተካት  ያላቸውን አቅም ችሎታ ለማውጣት እንዲረዳቸው አቅማቸውን ለማጎልበት የሚረዷቸውን የተለያዩ እድሎችን በመፍጠር አስፈላጊውን ትምህርትም እንዲያገኙ በማድረግ ላለፉት ሃምሳ አመታት ሕጻናቱን ሲያገለግል እንደቆየ ገልጸዋል ። የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ስራውን የጀመረው በ1966 ዓ.ም በተከሰተው ድርቅ በትግራይ ከተማ በእርዳታ ሰጪነት (emergency program )እንደነበርና በጊዜ ሂደትም ዘጠኝ ክልሎች ላይ ተደራሽነታቸውን እንዲስፋፉና በአለም አቀፍ ደረጃ ሰባ አምስት አመታትን እንዳስቆጠሩ በመቶ ሰላሳ ሰባት ሀገራትም   እየሰሩ እንደሚገኙ አሳውቀዋል ።   ይህ የ50ኛ አመት በዓል የሃምሳ አመታት ጉዟችንን የምናስታውቅበት ብቻም ሳይሆን ልንሰራ ያቀድነውንም በይፋ የምንገልጽበት ነው የሚሆን እንደሆነ ገልጸዋል። የሴቶች ማህበራዊ ጉዳይ መሪ ስራ አስፈጻሚ ክብርት ዶክተር ትፍስህት ሰሎሞን"በዚህ አጋጣሚ ይንን እድል ለሕጻናቱ ሳላመቻቻቹ በድርጅቱ እና በእኔ ስም ምስጋናዬን እያቀረብኩ የሀገር ፍቅር አለኝ የሚል የአንድ ዜጋ መገለጫ እነዚህን የነገ ሀገር ተረካቢ ሕጻናትን የበኩላችንን ድጋፍ  ማድረግ ስንችል ነውና ሁላችንም ድርሻችንን እንወጣ እላለሁ"። እንዲሁም ድርጅታቸው ለኤስ ኦ ኤስ ተገቢውን ድጋፍ  እንደሚያደርግ በመስሪያ ቤታቸውን ለሰራተኞቻቸው የልጆች ማቆያ በመክፈትን ለሴቶች ልዩ ድጋፍ በማድረግ ከጎኑ እንደሚቆሙ ገልጸዋል። የሲቪል ማህበረሰቦች ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር አቶ ፋሲካ ሞላው "የበጎ አድራጎት ድርጅቶች መብዛት እንደ ሀገር የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ትልቅ ነው ተቋማችንም አስፈላጊውን ክትትል ቁጥጥርና ድጋፍ  እያደረገ ይቀጥላል "ብለዋል። በአጠቃላይም በአማራጭ የቤተሰብ እንክብካቤ፣ በቤተሰብ እና ማህበረሰብ አቅም ግንባታ፣ በአስቸኳይ ጊዜ ሰብዓዊ ድጋፍ ፣በትምህርት ፣በጤናና በወጣቶች ማብቂያ መርሐግብሮቻችን ከ8,100,000 በላይ የሚሆኑ ዜጎችን ለማድረስ እንደቻሉ ገልጸዋል።
2070Loading...
17
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በኢንዱስትሪ ፓርኮች ዉስጥ የሚሰሩ ኩባንያዎች 50 በመቶ ምርታቸውን ለሀገር ዉስጥ ገበያ እንዲያቀርቡ መፍቀዱን ገልጿል። የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) እንደተናገሩት በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ኩባንያዎች ምርታቸውን ሙሉ በሙሉ ለውጭ ገበያ እንጂ ለሀገር ውስጥ ማቅረብ ሳይፈቀድላቸው ቆይተዋል። ይሁን እንጂ በተለያዩ ምክንያቶች ተጽዕኖ ሥር የነበሩ ባለሃብቶችን ለማበረታታት በፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ኩባንያዎች 50 በመቶ ምርታቸውን ለሀገር ውስጥ ገበያ እንዲያቀርቡ በአዋጅ መፈቀዱን ኢዜአ ዘግቧል። ይህ እርምጃ ኩባንያዎች ምርታማነትን ለማሳደግ ብቻ ሳይሆን ለሸማቹ ማኅበረሰብም የገበያ ዋጋን በማረጋጋት ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል ተብሏል።
1940Loading...
18
በ55 የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሰራተኞች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተነገረ ከደንበኞች የደረሰው ቅሬታ መሰረት በማድረግ እንዲሁም አገልግሎቱ ባከናወነው የስራ ክትትል ከጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እስከ ስራ ማሰናበት የሚደርስ እርምጃ  በሰራተኞች ላይ መውሰዱን የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡ በአገልግሎቱ 13 ሰራኞች ላይ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ፣ በ35 ሰራተኞች ላይ ከ7 እስከ 90 ቀን የሚቆይ የደሞዝ ቅጣት እንዲሁም በ5ቱ ላይ ከስራ የማሰናት እርምጃ እንደተወሰደ የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሚኒኬሽን ኃላፊ ዩሃንስ ገብሬ ተናግረዋል፡፡ በዋናነት ሙስና እንደ አንድ ምክንያት የሚጠቀስ መሆኑን እና እሚጠበቅባቸውን አገልግሎት በወቅቱ ባለማከናወን እርምጃ እንደተወሰደ ተመላክቷል፡፡ በተደጋጋሚ የጽሁፍ እና የቃል ማስጠንቀቂያ ተሰቷቸው ባልታረሙ የአገልግሎቱ ሰራተኞች ላይ በማስረጃ በቀረቡ የስራ ስህተቶች እርምጃ እንደወሰደ ተነግሯል፡፡
2201Loading...
19
በኢትዮጲያ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ወስጥ የነበሩ ሱዳናዉያን በጥቃት ምክንያት መሰደዳቸዉ ሰተማ በሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን ስደተኞች በሰሜን ኢትዮጵያ በሚገኙ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ካምፖች ዉስጥ የሚገኙ ሲሆን የጥቃት ሰለባ ሆነዋል፡፡ሶስት ስደተኞች ለቢቢሲ እንደተናገሩት ከኮሜር እና ኦላላ ካምፖች የተሰደዱት ሰዎች ቁጥር 7,000 ሊደርስ ይችላል። ሆኖም ግን ከካምፑ ተሰሰደዱ ስለተባሉት ሰዎች በገለልተኛ አካል አሃዙን ማረጋገጥ አልተቻለም፡፡የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ ስለ ክስተተ መግለጫ አልሰጠም። ነገር ግን በጸጥታ እጦት ቅሬታ ሳቢያ ካምፑን ለቀው የወጡ ስደተኞችን መኖራቸዉን እንደሚያውቅ አስቀድሞ መናገሩ ይታወሳል፡›፡ካምፑ ካለፈው አመት ነሃሴ ወር ጀምሮ በአካባቢው ሚሊሻዎች ከሰራዊቱ ጋር እየተፋለሙ ባለበት የኢትዮጵያ ሰሜን ምዕራብ የአማራ ክልል ዉስጥ ይገኛል። ክልሉ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር በመሆኑ የበይነመረብ ግንኙነት ተቋርጧል።ስደተኞቹ እንዳሉት ካምፖች ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በታጣቂዎች ጥቃት እየተፈጸመባቸው ሲሆን እገታ እየተለመደ መጥቷል።ከባለሥልጣናት ጥበቃ እጦት የተነሳ በዋናው መንገድ እና በአቅራቢያው ባለ ትንሽ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ አጠገብ እንዳደሩ አንድ ስደተኛ ተናግሯል። “በድንኳኔ ብቆይ ምናልባት መጥተው በጥይት ሊመቱን ይችላሉ። በአደጋ ላይ እንዳለዉ ስለተሰማኝ ጥሩ እንቅልፍ መተኛት አልቻልኩም” ፣ “በሌሊት በጣም አደገኛ ስለሆነ በዚያ ቦታ መቆየት አትችልም” ሲል አክሏል፡፡በሱዳን ጦር እና ተቀናቃኝ የፈጣን ደጋፊ ሃይሎች (RSF) ጦርነት ከጀመረበት ካለፈው ሚያዚያ ጀምሮ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ የሱዳን ዜጎች ከሀገር ተሰደዋል። ወደ 33,000 የሚጠጉት ወደ ኢትዮጵያ መሰደዳቸዉን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታዉቋል፡፡
1840Loading...
20
በአስመራ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ከ7 ዓመታት በኋላ የቪዛ አገልግሎት መስጠት ሊጀምር ነው በአስመራ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ከሚቀጥለው ሳምንት ማክሰኞ ግንቦት 6፤ 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለሰባት ዓመታት አቋርጦት የነበረውን የቪዛ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ኤምባሲው አስታወቀ። ነገር ግን በኢሚግሬሽን እና ዜግነት ህጉ ክፍል 243(መ) ስር ባሉት ኦፊሴላዊ የኤርትራ ዜጎች ላይ ያለው የቪዛ እገዳ ባለበት እንደሚቀጥል ቢቢሲ አማርኛ በዘገባው አመልክቷል። የቪዛ እገዳው ከዋና ዳይሬክተርነት ማዕረግ በላይ ላሉ የኤርትራ መንግሥት ባለስልጣናት፣ በገዢው ፓርቲ ህዝባዊ ግንባር ለዴሞክራሲ እና ፍትህ (ህግደፍ) ውስጥ በአመራርነት ላይ ያሉ የፓርቲ ኃላፊዎችን ይመለከታልም ተብሏል። በተጨማሪም እነዚህ የመንግሥት እና የፓርቲ ኃላፊዎች በትዳር አጋሮቻቸው እና ከ21 ዓመት በታች ባሉ ልጆቻቸው ላይ እገዳው ተፈጻሚ እንደሚሆን ተገልጿል። ከእነዚህ ግለሰቦች ውጭ የሆኑ ኤርትራውያን እና በኤርትራ ነዋሪ የሆኑ ዜጎች የቪዛ አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ ተጠቁሟል።
1950Loading...
21
Media files
2040Loading...
22
ታግታ የተወሰደችውን የ2 ዓመት ከ8 ወር ህፃን  በሦስት ቀናት ውስጥ መገኘቷን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።          የ2 ዓመት ከ8 ወር ዕድሜ ያላት አቢጊያ ዳንኤል የተባለችው ህፃን የታገተችው በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሳርቤት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ተወስዳ ነው። ቸርነት ጥላሁን የተባለው ግለሰብ ከቤሰተቡ ጋር በነበረው ቅርበት  ህፃን አቢጊያን በተለያዩ ቦታዎች እየወሰደ በማዝናናት እንደ ቤተሰቡ አባል ያጫውታት እንደነበረ እና ከአምስት ወር በላይ ከቤተሰቡ ጋር  በትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪነት የነበረው ቅርርብ ወንጀሉን በቀላሉ ለመፈፀም ምቹ ሁኔታን እንደፈጠረለት ፖሊስ ገልጿል። ግለሰቡ ሚያዚያ 25 ቀን 2016 ዓ/ም ከምሽቱ 12 ስዓት ተኩል ገደማ ወደ ህፃኗ ወላጆች መኖሪያ ቤት በመሄድና "እናቷ አምጣት ብላኛለች "ብሎ ለቤት ሰራተኛዋ ከነገረ በሗላ ህፃን አቢጊያ ዳንኤልን ወስዶ በማገት ገንዘብ እንዲሰጠው ከወላጆቿ ጋር ሲደራደር መቆየቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል። ተጠርጣሪው 150ሺህ የአሜሪካን ዶላር እንዲሰጠው   በመጠየቅ ገንዘቡን ማግኘት ካልቻለ ህፃኗን በህይወት እንደማያገኟት ሲዝት እንደነበረ የህፃን አቢጊያ ወላጅ እናት ለፖሊስ በሰጠችው ቃል አስረድታለች ።የአዲስ አበባ ፖሊስ፤ ህፃኗን ለማስመለስና ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመቀናጀት ቀንና ለሊት ክትትል ሲያደርግ ቆይቶ በተደረገው ክትትልም ዛሬ ሚያዚያ 28 ቀን 2016  ዓ/ም በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 አለም ሰላም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተጠርጣሪው ተከራይቶ በሚኖርበት መኖሪያ ቤት ውስጥ ለሶስት ቀናት ያህል ታግታ የቆየችው ህፃን አቢጊያ ዳንኤል  ልትገኝ መቻሏን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል። ህፃናት ልጆች ለእንደዚህ አይነት ወንጀል ተጋላጭ እንዳይሆኑ እንዲጠብቋቸው አደራ የተሰጣቸው ግለሰቦችም ሆኑ ሞግዚቶችና ወላጆች  ነገሮችን በጥርጣሬ በማጤንና የማረጋገጥ ሃላፊነታቸውን በመወጣት አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱ አስተላልፏል።
2260Loading...
23
በሀላባ : በጎርፍ አደጋ የ5 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀላባ ዞን ነፋስና በረዶ ቀላቅሎ በጣለዉ ከባድ ዝናብ ባስከተለዉ ጎርፍ 5 ሰዎች ተወስደዉ ህይወታቸዉ ማለፉ የዞኑ ፖሊስ ገለጧል። በዞኑ በዌራ ዲጆ ወረዳ በሁሉም ቀበሌያት ከባድ ዝናብ በመጣሉ አካባቢዉ በጎርፍ መጥለቅለቁ ነዉ የተገለፀዉ። በወረዳዉ በአጠቃለይ ( 5)ሰዎች በጎርፍ የተወሰዱ ሲሆን፣ የሶስት ሰዎች አስክሬን በፍለጋ ሲገኝ የሁለት ሰዎች አስክሬን ያልተገኘ በመሆኑ ፖሊስ ከአካባቢዉ መሀበረሰብ ጋር በመሆን የሟቾችን አስክሬን በማፈላለግ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል። ሀይለኛ ወጀብና በረዶ የተቀላቀለበት ዝናብ በመጣሉ ምክንያት 5 ሰዎች ህይወታቸዉን በጎርፍ አደጋ ምክንያት በማጣታቸዉ በእጅጉ ማዘናቸዉ የገለፁት የሀላባ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ ሙህድን ሁሴን፣ ለሟች ቤተሰቦች መፅናናትን ተመኝተዋል። ዋና አስተዳዳሪዉ አክለዉም ሀገራዊና ክልላዊ የዝናብ ትንበያ መረጃዎችን ከመከታተል ባለፈ፣ በዞኑ የተለያዩ መዋቅሮች ሊኖር የሚችለውን የዝናብ/አየር ሁኔታዎች በመገናዘብ ተጨማሪ አደጋ እንዳይከሰት ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።
2050Loading...
24
Media files
2030Loading...
25
Media files
1890Loading...
26
Media files
2320Loading...
27
Media files
2460Loading...
28
Media files
2060Loading...
29
ትላንት ማታ በአቃቂ የገበያ ማዕከል በደረሰው ድንገተኛ የእሳት አደጋ 16 ሱቆች ሙሉ በሙሉ ተቃጥለዋል። ሚያዚያ  24 ቀን2016   ዓ.ም ምሽት 3:10 ሰዓት ላይ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ  ወረዳ 03 አቃቂ የገበያ  መዕከል በተነሳ የእሳት አደጋ 16 ንግድ  ሱቆች  ሙሉ በሙሉና በከፊል ተቃጥለዋል። የእሳት አደጋዉን  ለመቆጣጠር አምስት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪ ሁለት የዉሀ  ቦቴ  ከ44 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር የተሰማራ ሲሆን እሳቱ ወደገበያ ማዕከሉ ተስፋፍቶ በሰዉና በንብረት ላይ የከፋ ጉዳት ሳይደርስ መቆጣጠር የተቻለ ሲሆን አደጋዉን ለመቆጣጠር ሁለት ሰዓት ፈጅቷአል። በአደጋ መቆጣጠሩ ሂደት የፌደራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ከፍተኛ ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን በሰው  ላይ የደረሰ ጉዳት  የለም ። አቃቂ የገበያ ማዕከል ትንሹ መርካቶ እየተባለ የሚጠራ የገበያ ማዕከል ሲሆን ገበያ ማዕከሉ በከተማ ደረጃ ለእሳት አደጋ ተጋላጭ ተብለዉ ከተለዩ አንዱ ሲሆን በገበያ ማዕከሉ በተደጋጋሚ የእሳት አደጋ እያጋጠመ በንብረት ላይ ጉዳት ሲደርስ ቆይቷል። ኮሚሽን መ/ቤቱ ገበያ ማዕከሉ ለአደጋ የተጋለጠባቸዉን ዝርዝር ጉዳዮችን የመፍትሄ ሀሳቦችን አካቶ ለገበያ ማዕከሉ ማህበራትና ለሚመለከታቸዉ አካላት ያቀረበ ቢሆንም የማስተካከያ ዕርምጃዎች አልተወሰዱም። በመሆኑም በቀጣይ መሰል አደጋዎች እንዳያጋጥሙ መፍትሄ እንዲሰጥ ኮሚሽኑ አሳስቧል።
2340Loading...
30
በአዲስ አበባ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ መፀዳጃ  ቤት ውስጥ እርድ ሲከናወን ተገኘ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ እና መድኃኒት ባለስልጣን በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ ከወረዳ እስከ ማዕከል የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በማከናወን ከ805 በላይ የሚሆኑ ተቋማት ላይ የቁጥጥር ስር መስራቱን አስታውቋል።በዚህም ባለስልጣኑ ባከናወነው የቁጥጥር ስራ ለ251 ተቋማት የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ሲሰጥ ሶስት ድርጅቶችን ማሸጉን አስታውቋል። ከታሸጉት  ተቋማት ውስጥ አንዱ  በፆም ወቅት አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ህግ እና ደንብ በማይፈቅድ መልኩ መፀዳጃ ቤት ውስጥ በግ እና ፍየል እርድ ሲያከናውን መያዙ ተገልፆል፡፡ በተጨማሪም የባለስልጣኑ የብቃት ማረጋገጫ ሳይኖራቸው ፅዳቱን ያልጠበቀ ዶሮዎች ለሱፐርማኬት ሲያከፋፍሉ የተገኙ የስጋ ማቀናባበሪያ እና ሱፐር ማርኬት መታሸጋቸው ተገልፆል፡፡ በፍተሻው የተገኙት ምርቶች በአጠቃላይ የተወገዱ ሲሆን በኮልፌ፣በለሚ ኩራ እና በአራዳ ክፍለ ከተሞች ናቸው፡፡ በቀጣይ ቀናቶች የበዓል ወቅት በመሆኑ  ህብረተሰቡ ህገ ወጥ እርድ የሚያከናውኑ ተቆማቶች በሚመለከትበት ጊዜ በነፃ የስልክ መስመር 8864 ላይ በመደወል ለባለስልጣኑ ማሳወቅ እንዳለበት የባለስልጣኑ የምግብና የጤና ነክ ተቋማት ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ እስጢፋኖስ ጌታቸው  ተናግረዋል።
2011Loading...
31
Media files
2120Loading...
32
Media files
2290Loading...
33
ጦርነቱን ተከትሎ በአማራ ክልል ስር የተቋቋሙ አስተዳደሮች እስከ ሰኔ 30 መፍትሔ እንደሚያገኙ ጄነራል ታደሰ ተናገሩ የትግራይን ጦርነት ተከትሎ በአማራ ክልል ስር ተጠቅለው የተቋቋሙ አስተዳደራዊ መዋቅሮች እስከ ሰኔ 30/ 2016 ዓ.ም መፍትሔ እንደሚያገኙ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት ጄነራል ታደሰ ወረደ ተናግረዋል። ጄነራል ታደሰ ባለፉት ሁለት ቀናት የፕሪቶሪያ ግጭትን በዘላቂነት የማቆም ስምምነት አተገባበር በተመለከተ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከመከላከያ እና ከፌደራል መንግሥት ባለስልጣናት ጋር ያደረጉትን ውይይት መሰረት በማድረግ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ነው ይህንን የተናገሩት። የአማራ ክልል ይገባኛል በሚላቸው እና የትግራይን ጦርነት ተከትሎ ክልሉ ጠቅልሎ እንደ አዲስ ያዋቀራቸው የደቡብ ትግራይ እና ጸለምቲ ወረዳዎች መፍትሄ ለማበጀት እስከ ግንቦት 30/2016 ዓ.ም የጊዜ ሰሌዳ ስምምነት ላይ መደረሱን ጄነራል ታደሰ ገልጸዋል። በተጨማሪም በአማራ ክልል በኩል ወልቃይት ተብሎ በሚጠራው ምዕራብ ትግራይ እንደ አዲስ የተቋቋመው አስተዳደር እስከ ሰኔ 30 ባለው ጊዜ መፍትሔ ይበጅለታል ብለዋል። በዚህም ውይይት ላይ ትጥቅ መፍታትን አስመልክቶ የትኞቹ አስተዳዳራዊ መዋቅሮች መፍረስ እንዳለባቸው እና የተፈናቀሉ ዜጎች እንደሚመለሱ ዝርዝር እቅድ የወጣ ሲሆን ይህንንም የሚቆጣጠረው እና የሚያረጋግጠው የአፍሪካ ኅብረት የስምምነት ክትትል አረጋጋጭ እና አስከባሪ ኮሚቴ እንደሚሆን ተገልጿል። ኮሚቴው መቀለ ላይ ቢሮ እንዳለው ከዚህ ቀደም ጄነራል ታደሰ መናገራቸው ይታወሳል።
2080Loading...
34
በ3 ዓመታት ዉስጥ ይጠናቀቃል የተባለዉ የመገጭ የግንባታ ፕሮጀክት ሳይጠናቀቅ 11 ዓመታት ከማስቆጠሩ በላይ ለ 4 ቢሊዮን ብር  ተጨማሪ ወጪ ተዳርጓል ተባለ ከ 5.6 ቢሊዮን ብር በላይ አጠቃላይ ወጪ የኮንትራት ዋጋ የተጀመረዉና በአማራ ክልል በጎንደር ከተማ ዙሪያ በተለምዶ መገጭ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የሚገኘዉ የመገጭ የመስኖ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ሳይጠናቀቅ ለተጨማሪ 4 ቢሊዮን ብር ወጪ መዳረጉ ተነግሯል ። በ2001 ዓ.ም. እንደተጀመረ የሚነገረዉ ይህ ፕሮጀክት የከተማዋን የንፁህ ዉኃ ችግር ለመፍታት እና በጎንደር ከተማ ዙሪያ የሚገኙ አርሶአደሮችን በመስኖ ልማት ተጠቃሚ ለማድረግ ታሳቢ ተደርጎ ነበር ። የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጪዉ 5.6 ቢሊዮን ብር እንደሚሆን ከዚህ ቀደም ተገምቶ የነበረ ቢሆንም አሁን ግንታዉ ሳይጠናቀቅ 11 ዓመታትን ከማሳለፉ በላይ ለተጨማሪ 4 ቢሊዮን ብር ወጪ መዳሩን ነዉ ካፒታል ያገኘዉ መረጃ የሚያመላክተዉ። የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ዛሬ ባካሄደው 23ኛዉ መደበኛዉ ስብሰባው የመስኖና ቆላማ አከባቢ ሚኒስትርን የ 2016 በጀት ዓመት የ 9 ወራት የዕቅድ አፈፃፀምን ገምግሟል ። ምክርቤቱ በዚህ ወቅት እንደገለፀው በ3 አመት ማለቅ የነበረበት እንደመገጭ ያለ የግንባታ ፕሮጀክት 6 ጊዜ የዲዛይን ጥናት የተደረገበት ቢሆንም ሳይጠናቀቅ 11 አመት በማስቆጠሩ ለ4 ቢሊየን ተጨማሪ የገንዘብ ወጪ ተዳርጓል ብሏል። Capital NP
1950Loading...
35
Media files
2100Loading...
36
Media files
2520Loading...
37
በአማራ ክልል ከ4.1 ሚልየን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ውጪ ሆነዋል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት የኢትዮጵያ ቢሮ በአማራ ክልል ከ 4.1 ሚልየን በላይ ተማሪዎች በግጭት ሳቢያ ትምህርት አቋርጠዋል ብሏል። በክልሉ 4 ሺህ 178 ትምህርት ቤቶች አሁንም በቀጠለው የጸጥታ ችግር እና በሰሜን ኢትዮጵያ ለሁለት ዓመታት ምክንያት ተዘግተው እንደሚገኙ ጽህፈት ቤቱ ገልጿል። በተጨማሪም 300 ትምህርት ቤቶች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን 350 ትምህርት ቤቶች ከአገልግሎት ውጪ ናቸውም ብሏል። እንደ መንግስታቱ ድርጅት መስሪያ ቤት መረጃ ከሆነ በአማራ ክልል ከ1.5 ሚልየን የሚበልጡ ልጆች የትምህርት ቤት ምገባ አገልግሎት ያስፈልጋቸዋልም ብሏል።
2120Loading...
38
ከሰሜኑ ጦርነት ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋሉ የትግራይ ተወላጅ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እንዲፈቱ ተጠየቀ። ከሰሜኑ ጦርነት ጋር በተያያዘ አሁን ድረስ 154 የሚሆኑ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በእስር ላይ እንደሚገኙ ቅድሚያ ለሰብዓዊ መብቶች በኢትዮጵያ አስታወቀ። በኢፌዴሪ መከላከያ ሲያገለግሉ በነበሩ የትግራይ ተወላጆች እስርን አስመልክቶ ቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች ባወጣው ሪፖርት ነው ይህን ያስታወቀው ። ድርጅቱ ባወጣዉ ሪፖርት ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም  ጀምሮ በኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት ለዓመታት ሲያገለግሉ የነበሩ የትግራይ ተወላጆች በወቅቱ በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት በማንነታቸው ተለይተው ወደ ተለያዩ ወታደራዊ ካምፖች መላካቸዉን በሪፖርቱ ገልጿል። አሁንም ድረስ በአገሪቱ 16 የተለያዩ እስር ቤቶች ያልተፈቱ የሰራዊቱ አባላት እንደሚገኙ ድርጅታችን ለማረጋገጥ ችሏል ሲል በሪፖርተመቱ ተመላክቷል፡፡ ታሳሪዎች ጉዳያቸው በወታደራዊ ፍርድ ቤት የታየ እና እየታየ ያለ መሆኑን የተረዳን ቢሆንም  አብዛኞቹ ይግባኝ እንዳይጠይቁ የውሳኔ ግልባጭ ተከልክለው ይገኛሉ ሲል ሁኔታውን አስታውቋል። በአሁኑ ሰዓት ክስ ቀርቦባቸው በፍርድ ሂደት የሚገኙ እና የተፈረደባቸው የትግራይ ተወላጅ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ቁጥርም በአጠቃላይ 154 መሆኑ ተጠቅሷል። ከዚሁ መካከል ቁጥራቸው 37 የሚሆኑት ታሳሪዎች ከፍተኛ የፀጥታ ስጋት ባለባቸውና በ 8 ቱ የአማራ ክልል ከተሞች ታስረው የሚገኙ ሲሆን በክልሉ ባጋጠመው ጦርነት ምክንያት ታሳሪዎቹ በከፍተኛ የደህንነት ስጋት ውስጥ ይገኛሉ ብሏል፡፡ ድርጅቱ በምርመራው እነዚህ የጦር ሰራዊት አባል የነበሩ ግለሰቦች በሃዋሳ፣ቃሊቲ፣እንጅባራ፣ደብረ ታቦር፣ደብረ ማርቆስ፣ሸዋ ሮቢት የመሳሰሉ የተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ታስረዉ ይገኛሉ ብሏል። በመሆኑም ድርጅቱ የፕሪቶሪያዉ የሰላም ስምምነት እንዲከበር፣ሰራዊቶቹ በጦርነት ያልተሳተፉ ከጦርነቱ ቀድመዉ የታሰሩ በመሆናቸው የሚመለከተዉ አካል መፍትሄ እንዲሰጣቸዉ እንዲሁም የሚመለከታቸዉ የሀገር ዉስጥ እና የዉጭ ተቋማት የመከላከያ አባላቱ እንዲፈቱ ጫና እንዲያደርጉ ሲል ጠይቋል ።
1950Loading...
39
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 30 - ሐምሌ 11 በተለያዩ ፕሮግራሞች ይሰጣል ተባለ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ አድርጓል። በዚህም መሰረት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 5 ለማህበራዊ ሳይንስ ፤ ከሐምሌ  9 እስከ ሐምሌ 11/2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል ተብሏል። እንዲሁም በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ከሰኔ 30 እስከ ሐምሌ 01/2016 ዓ/ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ከሐምሌ 6 እስከ 7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ይሆናል። 
1920Loading...
40
Media files
2130Loading...
Photo unavailableShow in Telegram
ኢትዮጵያ የራሷ የኮሙዩኒኬሽን ሳተላይት ባለቤት እንድትሆን የአዋጭነት ጥናት ተጠናቋል፡- የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት ኢትዮጵያ የራሷ የኮሙዩኒኬሽን ሳተላይት ባለቤት እንድትሆን የአዋጭነት ጥናቱ ተጠናቆ ለሚመለከተው የመንግስት አካል ለውሳኔ መላኩን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት ገለፀ፡፡ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር ቤተልሔም ንጉሴ፤ ኢትዮጵያ የራሷ ኮሙዩኒኬሽን ሳተላይት ስለሌላት በአሁኑ ወቅት ከሉግዘመበርግ ኢ ኤስ ኢ ኩባንያ ኢትዮ ሳትን  በመጠቀም ላይ ትገኛለች ብለዋል፡፡ ኢትዮ ሳት ኢትዮጵያ ለሳተላይት የምታወጣውን ከፍተኛ ወጪ ከመቀነስ፣ የባህል ወረራን ከመከላከል እንዲሁም ሀገራዊ እሴትን ከማስጠበቅ አንጻር ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ኃላፊዋ አንስተዋል፡፡ በኢትዮጵያ ከ2014 ዓ.ም በአዲስ መልክ የተደራጀው የስፔስ ሳይንስና ጂኢስፓሻል ኢንስቲቲዩ፤ በቀጣይ ኢትዮጵያ የራሷ የኮሙዩኒኬሽን ሳተላይት ባለቤት እንድትሆን የአዋጭነት ጥናት ተጠናቆ ለፕላንና ልማት ሚኒስቴር  መላኩንና ውሳኔ እየተጠበቀ መሆኑን ገልጸዋል። Via EBC
Mostrar todo...
ቦይንግ የ346 ሰዎችን ህይወት በቀጠፈው የ737 ማክስ አውሮፕላን አደጋ ክስ ሊመሰርትበት እንደሚችል ተገለፀ በኢትዮጵያው አየር መንገድ እና የኢንዶኔዥያው የ737 ማክስ 9 አውሮፕላን አደጋዎች የ346  ሰዎችን ህይወት በቀጠፈው አደሳ ምክንያት ቦይንግ ላይ ክስ ለመመስረት እያጤነ እንደሆነ የአሜሪካ የፍትህ መስሪያ ቤት አስታወቀ። ቦይንግ የሚያመርታቸውን አውሮፕላን ምርቶች ደኅንነት እና ጥራት ለማስጠበቅ ከ3 ዓመት በፊት ከአሜሪካ የፍትህ ሚኒስቴር ጋር የገባውን የቁጥጥር መርሃ ግብር ስምምነት መጣሱንም መስሪያ ቤቱ ስለመግለፁ ቢቢሲ በዘገባው አመልክቷል። ቦይንግ ስምምነት ጥሷል የተባለውን ክስ አስተባብሏል። ይህ አስከፊ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን አደጋ በኢትዮጵያው 157 እንዲሁም በኢንዶኔዥያው አየር መንገድ 189 ሰዎች ህይወት መቅጠፉ ይታወሳል።
Mostrar todo...
በሀገሪቱ ያለው የፀጥታ ችግር የማዕድን ዘርፉን እየጎዳው ነው ። የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን  የሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን ሀላፊ  ካሳሁን ለምለሙ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በሀገሪቱ ያለው የፀጥታ ሁኔታም ያለንን ሀብት በተገቢው መልኩ እንዳንጠቀም አድርጎናል ብለዋል ፡፡ በሀገራችን በሚገኙ በርካታ ክልሎች ከፍተኛ የሆነ የማዕድን ክምችት እንደሚገኝ ጠቅሰዋል፡፡ ባለ ሀብቶች ወደ ማዕድን ኢንዱስትሪ ከገቡ ሀገሪቱ ከዘርፉ ከፍተኛ ጥቅም ታገኛለች ተብሎ እንደሚጠበቅም አስረድተዋል፡፡ ማዕድን ለማውጣት የሚያግዙ ከውጪ የሚገቡ ማሽነሪዎች ለማስገባት የሚያስፈልገው ወጪ ከፍተኛ መሆን እና  የመሰረተ ልማት ችግር  ሌላኛው በዘርፉ የሚነሳ እንቅፋት መሆኑን አቶ ካሳሁን ጠቅሰዋል፡፡ ተቋሙ በዘርፉ ያለውን ክፍተት ለማስተካከልም በማምረት ፣በፍለጋ፣በጥናት እና በማዕድን ሽያጭም ከፍተኛ ስራ ለመስራት የቅድመዝግጅት ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡ አሁን ካሉት በተጨማሪ በተለያዮ አካባቢዎች ላይ አዳዲስ ሳይቶች እየከፈቱ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል። የወርቅ ምርቶችን ፣ኢንዱስትሪ ማዕድናትና የከበሩ ድንጋዮችን ለደንበኞቹ በመላክ ለሀገራችን የውጪ ምንዛሬ ለማስገባት ከፍተኛ ስራ እየሰራን እንገኛለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡
Mostrar todo...
የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ሰዉ ሰራሽ የነዳጅ እጥረት እንዲፈጠር በሚያደርጉ ነዳጅ ማደያዎች ላይ ከማሸግ የዘለለ እርምጃ መዉሰድ የሚያስችለውን አዋጅ ማዘጋጀቱ ተነገረ! ባለስልጣኑ ባዘጋጀው በዚህ አዋጅ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሰው ሰራሽ የነዳጅ እጥረት በሚፈጥሩ ሕገ ወጦች ላይ እስራትና የገንዘብ ቅጣት እርምጃ መውሰድ የሚያስችሉ አንቀጾች መካተታቸውን ተጠቁመዋል። አዋጁ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መቅረቡን ተከትሎ በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ ወደ ስራ እንደሚገባ የተነገረ ሲሆን በነዳጅ ማደያዎች ነዳጅ እያለ እንደሌለ ማስመሰል፣ የነዳጅ ግብይትን በጥሬ ገንዘብ መሸጥ፣ ነዳጅን በተለያዩ ስፍራዎች ደብቆ ማስቀመጥና የመሳሰሉትን ህገወጥ አሰራሮችን ሊያስቀር እንደሚችልከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
በጂንካ የ8 ዓመት ታዳጊን  አስገድዶ ግብረ ሶዶም  ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ  ጽኑ እስራት ተቀጣ በጂንካ ከተማ በ8 ዓመት ታዳጊ ልጅ ላይ የአስገድዶ ግብረ ሶዶም   መድፈር ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በጽኑ እስራት እንደተቀጣ የጂንካ ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት አስታዉቋል፡፡ የጂንካ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ግንቦት 2 ቀን 2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት ውሳኔዉን በተከሳሹ ላይ አስላልፎበታል፡፡ተከሳሽ ወጣት ማንያዘዋል አዳሙ  የካቲት 15 ቀን 2016 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 2:00 ሰዓት አከባቢ ድርጊቱን መፈፀሙን በማመኑ ባመነው መሰረት ማስረጃ መስማት ሳያስፈልግ  ውሳኔ እንደተሰጠ የጂንካ ከተማ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት  አቶ በቃሃኝ ጥላሁን  በተለይም  ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል  ። ተከሳሽ የግል ተበዳይን እኔ ጋር  አሳድራለው በማለት ከቤተሰቦቹ  በመውሰድ ህፃኑን አስገድዶ  ግብረ ሶዶም ወንጀል  መፈፀሙ አረጋግጧል ። አሰገድዶ የመድፈር ወንጀል የደረሰበትን ህፃን ለጤናም ሆነ ለስነ-ልቦና ጉዳት የሚዳርግ ተግባር ከመሆኑ አንጻር በጂንካ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠው  ውሳኔ ተከሳሽንና ሌሎችንም  መሠል ወንጀል አድራጊዎችን የሚያስተምር ውሳኔ አስተላልፎበታል፡ በመሆኑም  ግንቦት 2 ቀን 2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት አስገድዶ ግብረ ሶዶም መፈፀሙን ሙሉ በሙሉ በችሎት ቀርቦ በማመኑ የጂንካ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት  በ15 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ  መወሰኑን አቶ በቃኀኝ ጥላሁን ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል  ፡፡ በኤደን ሽመልስ #ዳጉ_ጆርናል
Mostrar todo...
👍 1