cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ደህንነት

"ከውኃና ከመንፈስ ዳግመኛ መወለድ" ማለት ምን ማለት ነው? ኃጢአትን እንዴት ማሸነፍ ይቻላል? የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ለመሆን ምን ማድረግ አለብን? እውነተኛውን ወንጌልና የእንክርዳዱን ወንጌል እንዴት መለየት እንችላለን? አስተያየትና ጥያቄ ካላችሁ በሚከተለውን አድራሻ መጻፍ ይቻላል። @Johnnlm 0910555190

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
1 801
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ጌታን ተቀብሎ ነገር ግን ዳግመኛ ላልተወለደ ሰው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ስመሰክር የተቀዳ ንግግር። ይህን መልዕከት ያዳመጠ ሰው እውነኛውን ወንጌልና እንክርዳዱን ወንጌል ይለያል። @dehnenet @dehnenet @dehnenet
Mostrar todo...
የወንጌል ምስክርነት.m4a32.96 MB
ራሳችንን አናስትም
Mostrar todo...
1 ከውኃና ከመንፈስ ዳግም መወለድ.pdf2.35 MB
2 ወደ ውኃውና መንፈሱ ወንጌል ተመለሱ.pdf2.10 MB
3 መንፈስ ቅዱስ እንዴት ይገኛል.pdf2.09 MB
5 (1) በሮሜ መልዕክት ስብከት.pdf1.91 MB
6 (2) በሮሜ መልዕክት ስብከት.pdf2.12 MB
7_1የፀረ_ክርስቶስ_የሰማዕትነት_የንጥቀት_ዘመን_.pdf1.90 MB
9_የመገናኛ_ድንኳን፡የኢየሱስ_ክርስቶስ_ስዕላዊ_መግለጫ_1.pdf2.35 MB
52 የአቤልና የቃየን እምነት ልዩነት.pdf2.48 MB
51 ውጥንቅጥ ባዶነት ጨለማ የለም .pdf2.60 MB
Watch "ለምን የዘመኑ ክርስትና ዘቀጠ?" on YouTube https://youtu.be/IwJqx4mMyfc
Mostrar todo...
ለምን የዘመኑ ክርስትና ዘቀጠ?

#nlmethiopia #bjnewlife.org #ደህንነት #የውሃውናየመንፈሱወንጌል

Watch "ከመጎምጀት እንጠንቀቅ" on YouTube https://youtu.be/xQAjVB2HSdg
Mostrar todo...

Photo unavailableShow in Telegram
በእያንዳን ቀን እርስ በርስ መመካከር ~~ መጽሐፍ ቅዱስ ደጋግሞ ከሚነግረን ነገሮች ውስጥ አንዱ የጻድቃን ኀብረት ነው። እግዚአብሔር በተናጥል በሚናደርገው ነገር ፈጽሞ አይደሰትም። እግዚአብሔር አንድ አካል ነው ማየት የሚሻው። በእርግጥ የተለያዩ ብልቶች ነን ግን አንድ አካል ነን። እያንዳንዱ ብልቶች በጅማት የተጋጠሙ፣ በጥብቅ የተቆራኙ ናቸው። አንድ ብልት ከአካል ቢቆርጥ፣ በራሱ ሕይወት ሊኖሮው አይችልም። functional አይደለም። እጃችን ከአካላችን ቢቆረጥ፣ ብቻውን መስራት አይችልም። እግራችን ከሰውነታችን ተቆሮጦ ቢወጣ፣ በራሱ መሮጥ አይችልም። መሮጥ የሚችለው ከአካል ጋር ሲቆራኝ ብቻ ነው። ጠንካራ፣ ብርቱ፣ ቆራጥ ብንሆንም፣ ከአካል ከተገነጠልን፣ ምንም ማድረግ አንችልም። ለጊዜው ልንፍጨረጨር እንችላለን። ነገር ግን በጊዜ ሂደት እንሞታለን። ዶሮ ሲታረድ አይታችሁ ታውቃላችሁ? አባቴ ቤት ከሌለ፣ ዶሮ የማርደው እኔ ነኝ። አንገቱን በቢላዋ እቆርጥና ቅርጫት ወይም ሳፋ እደፋበታለሁ። ከዚያም አንዱን እግሬን አሳርፍበታለሁ። ዶሮው ቢታረድም ወዲያውኑ አይሞትም። ይፈጨረጨራል። ተነስቶ ለመሮጥም ይሞክራል። መፍጨርጨሩ ሲበዛ አንዳንዴ በደምብ ጉሮሮውን አልቆርጥክም አባላለሁ። የዶሮው መፍጨርጨር ግን ጊዝያዊ ነው። ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ይሞታል። ከአካል ከተገነጠልን፣ ለጊዜው ልንፍጨረጨር እንችላለን። አልሞቱኩም አለው አለው ልንል እንችላለን። የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ በሂደት መሞታችን አይቀሬ ነው። የአካላችን ማዘዣ ጣቢያ ጭንቅላታችን ነው። አካላችን ማንኛውንም ትዕዛዝ የሚቀበለው ከጭንቅላታችን ነው። አንድ ብልት ከአካል ከተገነጠለ፣ ከጭንቅላት የሚላከውን ትዕዛዝ መቀበል አይችልም። ቤተክርስቲያን የክርስቶስ አካል ናት። ኢየሱስ ክርስቶስ የቤተክርስቲያን ራስ ነው። ቤተክርስቲያንን ዓለም ላይ እንዳሉ ተራ ተቋማት ማየት የለብንም። ቤተክርስቲያን የክርስቶስ አካል ናት። ለዚያ ነው መጽሐፍ ቅዱስ ከቤተክርስቲያን መጣበቅ እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ የሚነግረን። ይህን ቀለል አድርጎ ማየት አያስፈልግም። ስለዚህ እኛ በውኃውና በመንፈሱ ወንጌል የምናምን ጻድቃን ሁልጊዜ መሰባሰብ፣ እርስ በርስ መመካከር፣ በሕብረት የእግዚአብሔርን ሥራ መስራት ያስፈልጋል። ይህን ስናደርግ ከቤተክርስቲያን ጋር እንቆራኛለን። ከቤተክርስቲያን ያልተቆራኘ፣ ከዓለም ጋር መቆራኘቱ አይቀርም። ከቤተክርስቲያን ጋር ያለው ቁርኝት ሲላላ፣ ልቡ ይደነድናል። መንፈሱም ይበከላል። በመጨረሻም ይሞታል። የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ይላል፦ 📌“ነገር ግን ከእናንተ ማንም በኃጢአት መታለል እልከኛ እንዳይሆን፥ ዛሬ ተብሎ ሲጠራ ሳለ፥ በእያንዳንዱ ቀን እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ፤” (ዕብራውያን 3፥13) 📌“በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደ ሆነው፥ መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ።” (ዕብራውያን 10፥25) 📌"ቃሉንም የተቀበሉ ተጠመቁ፥ በዚያም ቀን ሦስት ሺህ የሚያህል ነፍስ ተጨመሩ፤ በሐዋርያትም ትምህርትና በኅብረት እንጀራውንም በመቍረስ በየጸሎቱም ይተጉ ነበር።" (ሐዋርያት 2:41-42) ጸጋ ይብዛችሁ! (ወንድም ዮሐንስ) ሐምሌ 23-2014
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
ለመነቃቂያ ጉባኤው ዝግጅት ላይ ነን
Mostrar todo...
በእምነት ተወልደናል፤በእምነት እንኖራለን፤ በእምነት እንሞታለን። ~~ የዕብራውያን መልዕክት ጻሐፊው መጀመሪያ እምነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ዕብራውያን ምዕራፍ 11 ላይ ያብራራልናል። ከዚያም በእምነት የኖሩ አባቶቻችንን ይዘረዝርልናል። የእነሱን ፈለግ እንድንከተልም ይመከረናል። የእምነት ቀድምቶችን ሽማግሌዎች (elders) ብሎ ይጠራቸዋል። እነሱ እንዴት በእምነት እንደኖሩና የደረሰባቸውን ማንኛውንም መከራ እንዴት በእምነት ድል እንደነሱ ይናገራል። 📌"እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው። ለሽማግሌዎች የተመሰከረላቸው በዚህ ነውና" (ዕብራውያን 11:1-2) ከአቤል ይጀምራል። አቤል በምንድን ነው የኖረው? በእምነት። ቀጥሎ ሄኖክን ያነሳል። ሄኖክ በምንድን ነው የኖረው? በእምነት። ከዚያም ኖኀን ያነሳል።ኖኅ በምንድን ነው የኖረው? በእምነት። 📌"አቤል ከቃየል ይልቅ የሚበልጥን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር በእምነት አቀረበ፥ በዚህም፥ እግዚአብሔር ስለ ስጦታው ሲመሰክር፥ እርሱ ጻድቅ እንደ ሆነ ተመሰከረለት፤ ሞቶም ሳለ በመሥዋዕቱ እስከ አሁን ይናገራል። ሄኖክ ሞትን እንዳያይ በእምነት ተወሰደ፥ እግዚአብሔርም ስለ ወሰደው አልተገኘም። ሳይወሰድ እግዚአብሔርን ደስ እንዳሰኘ ተመስክሮለታልና፤ ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና" (ዕብራውያን 11፡4-6)። አብርሃምን ያነሳል። ሣራን ያነሳል። ይስሐቅን ያነሳል። ያዕቆብን ያነሳል። ዮሴፍን ያነሳል። ሙሴን ያነሳል። ጋለሞታይቱ ረዓብን ያነሳል። ጌዴዎንን፣ ሶምሶንን፣ ባርቅን፣ ዮፍታሔን፣ ዳዊትን፣ ሳሙኤልን፣ ነቢያትን ያነሳል። አብርሃም በምንድን ነው የኖረው? ሣራ በምንድን ነው የኖረችው? ይስሐቅ፣ያዕቆብ፣ዮሴፍ፣ ሙሴ፣ ጋለሞታይቱ ረዓብ፣ ጌዴዎን፣ ሶምሶን፣ ባርቅ፣ዮፍታሔ፣ዳዊት፣ ሳሙኤል፣ነቢያት....በምንድን ነው የኖሩት? በእምነት። መንግስታትን ድል የነሱት በእምነት ነው። ጽድቅን ያደረጉት በእምነት ነው። የተሰጣቸውን የተሰፋ ቃል ያገኙት በእምነት ነው።የአንበሶችን አፍ የዘጉት በእምነት ነው። የእሳትን ኃይል ያጠፉት በእምነት ነው።ከሰይፍ ስለት ያመለጡት፣ከድካማቸው የበረቱት፣በጦርነት ኃይለኞች የሆኑት፣ የባዕድ ጭፍሮችን ያባረሩት በእምነት ነው።..........ሁሉንም ነገር በእምነት ነው ያደረጉት። በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ከእምነት ውጭ የሆነ ነገር አይሰራም። ዳግም የተወለድነው በእምነት ነው። የምንኖረው በእምነት ነው። የምንሞተውም በእምነት ነው። የተወደደው ወንድማችን ጳውሎስ እንዲህ ብሏል፦ 📌“ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና።” (ፊልጵስዩስ 1፥21) ያለ እምነት ምንም ነገር ብናደርግ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት የለውም። እግዚአብሔርን ደስ ልናሰኝ አንችልም። የውሃውና የመንፈሱን ወንጌል ከልባችን እንዳመንን ሁሉ፣ እያንዳንዱን የተጻፈውን የእግዚአብሔርን ቃል በልባችን ማመን ያስፈልጋል። ልባችንን የእግዚአብሔር ቃል የተከማቸበት ግምጃ ቤት ማድረግ ያስፈልጋል። እያንዳንዱ የእግዚአብሔር ቃል የተጻፈው ገጽ ለመሙላት ሳይሆን እንድናመነው ነው። እግዚአብሔር አምላክ በእምነት ድል ነሺ ሕይወት እንድንኖር ይርዳን! አብረን እንደ ሐዋርያት ይህን ጸሎት እንጸልይ፦ "ጌታ ሆይ እምነትን ጨምርልን!" 📌“ሐዋርያትም ጌታን፦ እምነት ጨምርልን አሉት።”(ሉቃስ 17፥5) (ወንድም ዮሐንስ) ሐምሌ 22፣ 2014
Mostrar todo...
📌"በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ ማለት ምን ማለት ነው❓" በመደመራያ እነዚህን ሁለቱን የወንድማችን ሐዋርያው ጴጥሮስ መልዕክቶች እናንበብ። ✍ “ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ።” (1ጴጥሮስ 2፥24) ✍ “ይህም ውኃ ደግሞ ማለት ጥምቀት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል፥ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም፥ ለእግዚአብሔር የበጎ ሕሊና ልመና ነው እንጂ፥ ይህም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ነው፤” (1ጴጥሮስ 3፥21) እግዚአብሔር በቅዱስ መንፈሱ አማካኝነት አዕምሯችን ካልከፈተ በስተቀር መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት እጅግ ከባድ ነው። ሰው በራሱ መረዳት መጽሐፍ ቅዱስን ሊተነትን ቢሞክር፣ ለተሳሳተ መረዳት ይጋለጣል። ለዚያ ነው ጳውሎስ ለጢሞትዎስ እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ማስተዋልን ይስጥህ ያለው (2ጢሞ 2:7)። ኢየሱስ ክርስቶስም ሰዱቃውያንን መጽሐፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ትስታላችሁ ብሏቸዋል (ማቴ 22:29)። ሰዱቃውያንና ፈሪሳውያንን ቅዱሳን መጽሐፍትን እያነበቡ ለምን ይሳትሉ? በራሳቸው አሳብ ላይ ተመርኩዞ ስለሚረዱ። ስለዚህ ማስተዋል የላቸውም። ይስታሉ። በዓለም ላይ እጅግ በጣም የተነበበ መጽሐፍ ቢኖር፣ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። የዚያን ያህል እጅግ ብዙ ሰዎች በተሳሳተ መንገድ የተረዱት መጽሐፍ ቢኖር፣ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። ለዚያ ነው በክርስቲና ስም ብዙ የስህተት ትምህርቶች የተንሰራፉት። ከላይ ያነበብነው ጥቅስም ብዙ ክርስቲያኖች በተሳሳተ መንገድ ከሚረዱት ጥቅሶች ውስጥ አንዱ ነው። ሐዋርያው ጴጥሮስ ኢየሱስ ራሱ በሥጋው ኃጢአቶቻችንን በእንጨት ላይ እንደተሸከመና በመገረፉ ቁስል እንደፈወሰን ይናገራል። በሌላ ሥፍራ ደግሞ ራሱ ጴጥሮስ ይህ ውኃ አሁን ጥምቀት ምሳሌ ሆኖ ያድነናል ብሎ ይመሰክራል። እግዚአብሔር በሚሰጠን ማስታዋል ካልተረዳን በስተቀር፣ ሐዋርያው ጴጥሮስ የተናገረው ነገር እርስ በርስ የሚጣረስ ይመስላል። በአንድ በኩል ውሃው (የክርስቶስ ጥምቀት) ያድነናል ይላል፣ በሌላ በኩል ደግሞ ኃጢአቶቻችን በሥጋው በእንጨት ላይ ተሸከመ ይላል። ኢየሱስ የዓለምን ኃጢአት የተሸከመው በብሉይ ኪዳን የመስዋዕት ስርዓት መሠረት ከአሮን ዘር በመጣው በሊቀ ካህኑ በዮሐንስ አማካኝነት እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ቢናገርም፣ ብዙ ክርስቲያኖች ይህ የእውነት እውቀት የላቸውም። ስለሆነም ኢየስሱ በሥጋው ኃጢአቶቻችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ የሚለውን የሐዋርያው ጴጥሮስን መልዕክት በትክክል አይረዱም (1ጴጥሮስ 2: 24)። ኃጢአት ወደ ኢየሱስ የተላለፈው በእንጨት ላይ ሲሰቀል ነው ብሎ ያስባሉ። ይህ ትክክለኛ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረዳት አይደለም። የዓለም ኃጢአት ወደ ኢየሱስ የተላለፈው ሲሰቀል አይደልም። ኢየሱስ በእንጨት ላይ የተሰቀለው የዓለምን ኃጢአት ሊሸከም አይደለም። ኢየሱስ በመስቀል የተሰቀለው ኃጢአትን ስለ ተሸከመ ነው። እደግመዋለሁ ሊሸከም ሳይሆን ስለ ተሸከመ ነው። በኦሪት ኪዳን ለኃጢአት የሚቀርብ መስዋዕት ከመታረዱ በፊት፣ እጅ ተጭኖ መስዋዕቱ ላይ ኃጢአት መተላለፍ ነበረበት። መስዋዕቱ የሚታረደው ኃጢአት ከተላለፈበት በኋላ ነው እንጂ ሲታረድ አይደለም ኃጢአት የሚተላለፍበት። ልክ እንደዚያው ኢየሱስ በእንጨት ላይ ከመስቀሉ በፊት የዓለምን ኃጢአት በጥምቀቱ አስቀድሞ መሸከም ነበረበት። ሳይሸከም ቢሰቀል ኖሮ፣ ሞቱ ከንቱ ይሆን ነበር። የመስዋት በግ ኃጢአት ሳይተላለፍበት ቢታረድ ፣ ደሙ ኃጢአተኛውን አያነፃም። በከንቱ የፈሰሰ ደም ይሆናል። ምክንያቱም ኃጢአት አልተላለፈበትማ። ስለዚህ ሐዋርያው ጴጥሮስ ኢየሱስ በሥጋው ኃጢአቶቻችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ ሲል ምን ማለቱ ነው? ኢየሱስ በእንጨት ሲሰቀል የዓለም ኃጢአት ወደ ኢየሱስ ተላልፏል እያለ አይደለም። እንደዛ ቢሆንማ፣ ይህ ውሃ አሁን ጥምቀት ምሳሌ ሆኖ ያድነናል ብሎ ባልተናገረ ነበር። ስለዚህ ኢየሱስ በስጋው ኃጢአቶቻችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ ማለት ኢየሱስ በጥምቀቱ የተላለፈበትን ኃጢአት በእንጨት እስኪ ሰቀል ድረስ በሥጋው ተሸክሞት ነበር ማለት ነው። ለዚያ ነው በመገረፉ ቁስል ከኃጢአት ዴዌ ተፈውሰን ጻድቅ የሆንነው!!! ኃጢአቶቻችንን በጥምቀቱ ተሸክሞ፣ እስከ መስቀል ሞት ድረስ በመታዘዝ የኃጢአታችንን ዕዳ ክፍሎ ለዋጀን ለአዳኛችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ምስጋና ይግባው! ሰኔ 09- 2014 ወንድም ዮሐንስ (Brother John)
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.