cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Sunniyoch dawa group

﴿ هذا مِن فَضلِ رَبّي لِيَبلُوَني أَأَشكُرُ أَم أَكفُرُ ﴾ Welcome to Sunniy channale This is your channale from chiro to expand tawahid & sunnah انشاء اللہ we are selfiy For any comments @UmmiHubi

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
148
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

"እናት አንድ ሆና ለሰው አስቸገረች፤ ምነው እንደ ዘመድ ሶስት አራት በሆነች!" በህመም ላይ ያሉ እናቶቻችንን አላህ አፊያ ያድርግልን! የሞቱብንንም ማረፊያቸውን በጀነት ያድርግልን!
Mostrar todo...
ኢብኑ ባዝ ቁርኣን ሲቀሩ… t.me/sultan_54
Mostrar todo...
1.36 MB
ይህን የሺዓዎችን "እርግማን" ኣሚን እላለሁ‼ =============================== ✍ ሺዓዎች አቡበከረን፣ ዑመርን፣ ዑሥማንን፣ እናታችን ዓኢሻንና ሌሎችንም ታላላቅ ሶሐባዎች ከመሳደብና ከመራገም ባሻገር የእሳት ናቸው ብለው ያምናሉ። እናም ሱን'ኒዩን ማህበረሰብ ለመራገም ሲፈልጉ እንዲህ ይላሉ፦ «اللهم بحقك احشرهم مع أبي بكر وعمر وعثمان‼» «አላህ ሆይ! በሐቅህ ይሁንብህ ፥ ከአቡበከር፣ ከዑመርና ከዑሥማን ጋር ቀስቅሳቸው።» ኣሚን አትሉም ታዲያ⁉️ ከነዚህ ከዋክብቶች ጋር አብሮ ከመቀስቀስ የበለጠ ምን የሚያስደስት ነገር አለ‼ شرف لنا ان يحشرناالله مع صحابة رسوله الكريم عليه الصلاة والسلام‼ በእውነቱ ይህ እርግማን ሳይሆን ዱዓእ ነው። من أجمل أدعية #الشيعة على أهل #السنة والجماعة‼ || t.me/MuradTadesse
Mostrar todo...
Murad Tadesse (Official Channel)✅☪🇪🇹

ትክክለኛው ኢስላማዊ አስተምህሮ፦ 1) ከቁርኣን፣ 2) ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ] 3) ከታማኝ ዑለማዎችና 4) ከትክክለኛ ቂያስ ተጠናቅሮ ይቀርብበታል። √ አዳዲስና ወቅታዊ ኢስላማዊ የሆኑ ጉዳዮችም ይዳሰሳሉ። √ አላማዬ በዲኔ ላይ ያለውን የመረጃ ክፍተት መሙላት ነው። ማንኛውም አስተያዬት ሲኖራችሁ @Murad_Tadesse ላይ አስፍሩልኝ። ስህተትም ባያችሁ ጊዜ አርሙኝ። ጀዛኩሙል`ሏህ ኸይራ!

እንደ ንስር ሁኑ‼ =========== ✍ ንስር አሞራን ለማጥቃት የሚደፍረው ብቸኛ ወፍ "ቁራ" ነው። The only bird that dares to attack an eagle is the crow. ከታች በፎቶው ላይ እንደምትመለከቱት ከጀርባዋ ላይ ይሆንና አንገቷን በመንከስ ያጠቃታል። It sits on its back and bites into the eagles neck. ነገር ግን ንስሯ ለቁራው አጸፋ አትመልስም፣ አትታገለውም። አቅም አጥታ እንዳይመስላችሁ። ይልቁንም ለእርሱ ምላሽ በመስጠት ጊዜዋንና ጉልበቷን አታባክንም። However, the eagle does not respond nor fight with the crow;it spends no time or energy on the crow. እና ምን ታደርጋለች?! ክንፏን ትከፍትና ወደ ሰማይ ከፍታ መብረር ትጀምራለች። It just opens it wings and starts to soar higher into the heavens. ከዚያስ? ከዚያማ የንስሯ የከፍታ ጉዞ በጨመረ ቁጥር፤ ቁራው የመተንፈስ አቅሙ እየቀነሰ ይመጣል። በመጨረሻም ኦክስጂን ስለሚያንሰው ኃይል ያጣና ይወድቃል። The higher the flight, the tougher it is for the crow to breathe and then the crow falls down from lack of energy. ታዲያ ምን ለማለት ነው? ወደ ግብህ በተጠጋህ ቁጥር፤ መሰናክሎችና ተግዳሮቶች ይበዙብሀል። ነገር ግን ተቋቁመህ ጉዞህን ወደፊት ከገፋኸው፤ አላስፈላጊ የሆኑ መሰናክሎች ሁሉ ሳትዋጋቸው በራሳቸው ጊዜ ይከስማሉ። It simply means that once you move closer to your goals, you'll be faced with obstacles and challenges but when you keep pushing yourself forward every other unnecessary obstacle will fall by itself. አንዳንድ ሰው አጋጣሚዎችን እየጠበቀ ሊያጠቃህ ይሞክራል! የርሱ ስኬት በአንተ መቃብር ላይ ይመስለዋል። የርሱ እድገት አንተ ካልወደቅክ የሚሳካ አይመስለውም። የሚገርመው እኮ አንተ ያለህን ነገር እርሱ ቢይዘው አጠቃቀሙን እንኳ ላያውቅበት ይችላል። ታዲያ ካልተጠቀመበት ምን አለበት ቢተውህ? ነገሩ McGowan እንደሚለው ነው። "This would be kind of like a dog chasing a car and jumping up on it, Dogs always want to catch the car, but they never know what they'd do if they get it." «ውሾች መኪና ሲያልፍ ይጮኻሉ። አንዳዶች ከላዩም ላይ ዘለው ይወጣሉ። ነገር ግን መኪናውን ቢያገኙት እንኳ ምን መሥራት እንዳለባቸው አያውቁም።» አንዳንዱ ሰው ለምን እንደሚተችህ እንኳ አያውቅም‼ እናማ ወንድሜ! You don't have to respond to all fights. You don't have to respond to all arguments or critics. ለሁሉም ትግል፣ ክርክርና ትችት መልስ መስጠት የለብህም። በሚሰነዘርብህ ትችትና አሉባልታም ልታዝንና ልትከፋ አይገባም። Raise a standard, they'll fall‼ መርህ ይኑርህ፣ ዝም ብለህ ወደላይ ከፍታህን ቀጥል!፤ አልቻል ስትላቸው እነርሱ የሆነ ቀን ተስፋ ቆርጠው ይወድቃሉ። Stop wasting time with the 'crow'! ከ"ቁራዎች" ጋር ጊዜህን አታባክን‼ እንደ ንስር ሁን! ከፍ በል‼ (ደግሞ «አላህ የሰው ልጅ አድርጎ ፈጥሮን፣ የሰውን ልጅ በእርግጥም አክብሬዋለሁ! ብሎን፤ እንደት "እንደ ንስር አሞራ ሁኑ!" ይለናል⁉️ ብላችሁ ረድ እንዳትሰጡብኝ። እኔ እንደ ንስር ሁኑ ማለቴ ከቁራ ጋር ላላት ትግል የተጠቀመችውን ስልት ተጠቀሙ ለማለት እንጅ ሰውነታችሁን ትታችሁ እንደ እርሷ ክንፍና እግር ያላችሁ ሁኑ ማለቴ አይደለም¡) ለማንኛውም ይመቻችሁ‼ ሃሳቡን ከአንድ የእንግሊዝኛ ጽሑፍ የወሰድኩት ነው! || ወንድማችሁ፦ ሙራድ ታደሰ ========= ጥር 29, 2013 E.C February 06, 2021 G.C || t.me/MuradTadesse
Mostrar todo...
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷 አጂጂጂብ የሆነ ልብ የሚነካ የነብዩ(ሠዐወ)......... 🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷 ልቦና ያለውን ሰው ሁሉ የምታስለቅስ ቆንጆ ታሪክ ከረሱል (ሰዐወ) የህይወት ማህደር! መነበብ እና ለሌሎች መተላለፍ የሚገባው ! ነብዩ (ሰዐወ) ጠዋፍ እያደረጉ ሳለ አንድ ዓእራብይ /የአረብ ገጠሬ/ …‘ያ ከሪም!’ /ቸሩ ፈጣሪ ሆይ እንደማለት/… እያለ ሲጣራ ሰሙት። እርሳቸውም ከኋላው ሆነው …’ያ ከሪም!’… አሉ። ዓእራብዩም አቅጣጫ በመቀየር …’ያ ከሪም!’… እያለ መጣራቱን ቀጠለ ነብዩም (ሰዐወ) ከኋላው ተከትለው …’ያ ከሪም!’… አሉ። ዓእራብዩም ፊቱን ወደ እርሳቸው በማዞር:- “አንተ ባለግርማ እና በሻሻ ፊት ሆይ!… ዓእራብይ ስለሆንኩ ነው የምታሾፍብኝ?… በአላህ እምላለሁ! የፊትህ ሞገስ እና በሻሻነት ባልነበረ ወዳጄ ሙሐመድ (ሰዐወ) ዘንድ ወስጄ እከስህ ነበር!” አላቸው። ነብዩም (ሰዐወ) ፈገግ ብለው:- “አንተ አረብ ወንድሜ ሆይ! ነብይህን አታውቀውም ማለት ነው?” አሉት ዓእራብዩም “አዎን!” ሲል መለሰላቸው። “ለመሆኑ በእርሱ ላይ ያለህ እምነት ምንድነው?” ሲሉ ጠየቁት ዓእራብዩም:- “በነብይነቱ አመንኩኝ! አይቼው ግን አላውቅም፣ ረሱልነቱን ተቀበልኩኝ! አግኝቼው ግን አላውቅም።” ሲል መለሰላቸው። ነብዩም (ሰዐወ):- “አንተ ዓእራብይ ሆይ! የዱንያው ነብይህ እና የአሄራ አማላጅህ እኔ መሆኔን እወቅ!” አሉት። ዓእራብዩም የነብዩን(ሰዐወ) እጅ በፍጥነት መሳም ያዘ ነብዩም (ሰዐወ):- “አንተ አረብ ወንድሜ ሆይ! ሌሎች ህዝቦች ንጉሶቻቸውን እንደሚያደርጓቸው አታድርገኝ፤ አላህ (ሱወ) ኩራተኛ እና አጉራዘለል አድርጎ አላከኝም፤ ይልቁንም አብሳሪ እና አስጠንቃቂ አድርጎ በእውነት ልኮኛል።” አሉት በዚህን ጊዜ .. ጅብሪል ወደ ነብዩ መጣና:- “ሙሐመድ ሆይ አላህ (ሱወ) ሰላምታን ያቀርብልሀል! በክብር እና ልቅናም ከሌሎች አስበልጦሀል፤ ለዚህ ለዓእራብይ:- የአላህ ቸርነት እና ቻይነት እንዳያዘናጋው!፣ ነገ በትንሹም ይሁን በትልቁ፣ በልምጩ ይሁን በቅሉ እንደሚተሳሰበው ንገረው”… አላቸው። ዓእራብዩም:- “አንቱ የአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) ሆይ! ጌታዬ ይተሳሰበኛል ማለት ነው?” ብሎ ጠየቃቸው “አዎን ከፈለገ ይተሳሰብሀል!” አሉት “እንግዲያውስ በአሸናፊነቱ እና በልቅናው ይሁንብኝ! የሚተሳሰበኝ ከሆነ እኔም እተሳሰበዋለሁ!” አለ። ነብዩም (ሰዐወ):- “አንተ አረብ ወንድሜ ሆይ! ጌታህን በምን ትተሳሰበዋለህ?” አሉት። “ጌታዬ በወንጀሌ ከተሳሰበኝ እኔ በምሕረቱ እተሳሰበዋለሁ፣ በጥፋቴ ከተሳሰበኝ እኔ በይቅር ባይነቱ እተሳሰበዋለሁ፣ በስስታምነቴ ከተሳሰበኝ እኔ በቸርነቱ እተሳሰበዋለሁ!”… አለ። ~~ ነብዩ (ሰዐወ) ፂማቸው እስኪረጥብ ድረስ አለቀሱ። ጅብሪል ወደ ነብዩ ወርዶ:- “ሙሐመድ ሆይ! አላህ ሰላምታን ያቀርብልሀል። ለቅሶህንም ቀንስ! የአርሽ ተሸካሚ መላኢካዎችን ተስቢህ ከማድረግ አዘግይታቸዋለችና ይልሀል። ለዓእራብዩ ወንድምህ ደግሞ:- እንዳይተሳሰበን ንገረው! እኛም አንተሳሰበውም! እርሱ የጀነት ጎረቤትህ ነው!።”… አላቸው። አላህ በታላቋ ጀነተል ፊርደውስ ውስጥ የነብዩን (ሰዐወ) ጉርብትና ከሚያገኙት እንዲያደርገን እንለምነዋለን። ያ አላህ ይህንን መልእክት አንብበው ለሚያስተላልፉ ሁሉ ከነቤተሰቦቻቸው ምሕረትህን ለግስ መመንዳትንም አትንፈጋቸው …ያ ከሪም!። ከአላህ ውጭ በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም! ሀይልም ሆነ ብልሀት በርሱ ቢሆን እንጂ አይገኝም!። ~~ ‘አላሁመ ሰሊ አላ ሙሐመድ ወ አላ አሊ ሙሐመድ’ …ጌታዬ ሆይ ምሕረትህን እለምንሀለሁ ወዳንተም ንሰሀ እገባለሁ!። ከመካከላችን ሰደቀተል ጃሪያን የሚፈልግ ማነው? ከሞትን በኋላ እንኳ በቀብራችን ውስጥ ሆንነን አጅር የምንቋደስበትን!። እንግዲያውስ ይህንን መልካም ስራ በነፍሳችን ላይ አናስመልጥ! 👇👇👇👇ለመቀላቀል ይህ ምልክት ይጫኑ @ahihnananaa
Mostrar todo...
አለም አቀፉ የጤና ድርጅት(WHO) መዲና ከተማን የአለማችን ጤናማዋ ከተማ ሲል መድቧታል!! የነቢ ሀገር ይገባታል ©ከመከቱል-ሙከረማህ ፔጅ የተገኘ ወቅታዊ መረጃ እንዲደርሶ የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ https://t.me/joinchat/AAAAAFACld9qu1NhysxDHw
Mostrar todo...
አንድ ነኝ ከልጁ!! አንገቱን ከሚሰጥ ቋሚ ለመንሀጁ፤ የማያስቆርጠው ሞፈሩን ከደጁ፤ አንድ ነን ከልጁ መንሀጅ ያዋደደን፤ በኑሁ መርከብ ላይ ሱናው ያዋሀደን፤ ደምግባቱን ሳየው የሱናውን ለዛ፤ ሰለፍይ ነኝ ይላል የአንደበቱ መአዛ፤ አሏሁ ተአላ እንዲህ አለ ይላል፤ ሊመክረኝ ሲፈልግ ድክመቴን ሲያስተውል፤ የአሏህ መልእክተኛ ይሄን ከልክለዋል፤ ከፈሳዱ ቦታ በፍፁም አትዋል፤ ይሉኝታን ሳይፈራ ይከለክለኛል። ===================== ቂርአትም ቅራ በፍፁም አትስነፍ፤ ጧት ማታ ተጥደህ እውቀትን አነፍንፍ፤ ጌታህን እወቀው በደሊል ቡርሀን፤ ጅህልናን አስወግድ ግፈፍ ጨለማውን፤ ይለኛል ወንድሜ ያሰለፍይ ጀግና፤ አሏህ ያዋደደን ነውና በተውሂድ በሱና፤ እናማ አንድ ነኝ ከዚህ ብርቅዬ ልጅ፤ ሁሌም አይለየኝ ይሁንልኝ ወዳጅ። ===================== ይለኛል ወንድሜ በአስተዋይ አንደበት፤ ከቂርአት ስቀር ከጀመአም ሶላት፤ ሁሌ ያሳስበዋል ከርሱ የኔ መጥፋት፤ ምንም ቢጎሳቃል ሰውነት ቢርቀው፤ ኑሮው ባይመቻች አዱኒያ ባትደላው፤ ከአፉ የሚወጣው አልሀምዱሊላህ ነው። ==================== እናማ የኔውማ ሚዛን የማይንሻፈፈው፤ ስወደው በምክንያት እንዲሁም ስጠላው፤ ወላእ እና በራእ የምንመሰርተው፤ በሸሪአ ሚዛን በቁርአን ሀዲስ ነው፤ ጉሙዝ ስለሆን ኦሮሞ አማራ፤ ሀረሪ ጉራጌ መሆኑ ከአስመራ፤ ጋምቤላ መሆኑ ከአገው ሲዳም፤ ከወሎ ከጎጃም ከጎንደር መተማ፤ አንድ አያደርገንም ዘርም አንቆጥርም፤ ጥንቧን ዘረኝነት ለድርድር ሚዛን ፍፁም አናቀርብም። =================== የመደመር ሚስጥር አንድ የመሆኑ፤ ተውሂድና ሱና ከሆነ ሚዛኑ፤ ካወቀ መሆኑን ቢድአ ዶላላ፤ የቆሸሸ ተግባር እጅግ የሚያስጠላ፤ ጠንቅቆ ካወቀ ወድቆ እንደሚሰበር፤ ተውሂድ ከለቀቀ ከዋለ ሽርክ ስር፤ ቢድአን ሰንቆ ሱናውን ከረሳ፤ መሆኑን ካወቀ ወድቆ የማይነሳ፤ አንድ ነኝ ከልጁ ከሰለፍይ ጀግናው፤ በደማቁም ብእር ከልቤ ምፅፈው፤ አንድ ነኝ ለማለት ሁሌ ማላፍርበት፤ ይህ ነው የኔ ወንድም ሁሌ ምኮራበት። https://t.me/AbuSarahh
Mostrar todo...
አቡ ሳራህ

قال تعلى: ولا تكونوا من المشركين ➊➌ من الذين فرقو دينهم وكانوا شيعا كل حزب بمالديهم فرحون ➋➌ وقال صلى الله عليه وسلم: من مات وهو يدعو من دون الله ندا دخل النار. አቡ ሳራህ ቦት ⤵⤵⤵ @Abusarrah_bot

➪ታላቅ ምክር !! _ 𒊹︎︎︎የረመዳንን መድረስ አስመልክቶ ታላቁ የዘመናችን ሼይኽ ዶ/ር ሷሊሕ ኢብኑ ፈውዛን አል ፈውዛን ሐፊዘሁሏሁ ወረዓሁ የሰጡት ልባዊ ምክር!! ☞︎︎︎ተጠየቁ:- __ “የረመዳን ወር በመቃረቡ ምክንያት ምን ትመክራላችሁ? ما نصيحتكم بمناسبة اقتراب شهر رمضان؟ الشيخ صالح الفوزان حفظه الله السؤال : ما نصيحتكم للمسلمين بمناسبة اقتراب شهر رمضان؟ “𒊹︎︎︎የረመዳን ወር በመቃረቡ ምክንያት ምን ትመክራላችሁ?” الجواب: الواجب علىالمسلم يسأل الله أن يبلغه رمضان وأن يعينه على صيامه وقيامه، والعمل فيه، ☞︎︎︎"አንድ ሙስሊም አላህ ለረመዳን ወር እንዲያደርሰው እና አድርሶትም ፆሙ ላይ፣ ስግደቱ ላይ እና ሌሎች አምልኮዎች ላይ አላህ እንዲያግዘው አላህን መለመን አለበት። لأنه فرصة في حياة المسلم: مَنْ صَامَ رَمَضَانَ إِيمَانًا وَاحْتِسَابًا غُفِرَ لَهُ مَا تَقَدَّمَ مِنْ ذَنْبِهِ ، مَنْ قَامَ رَمَضَانَ إِيمَانًا وَاحْتِسَابًا غُفِرَ لَهُ مَا تَقَدَّمَ مِنْ ذَنْبِهِ ، 𒊹︎︎︎ምክንያቱም ይህ ወር በአንድ ሙስሊም ህይወት ዕድል ነው። ረሱል ﷺ እንዲህ አሉ:- 𒊹︎︎︎‹‹ረመዳንን አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ ከጅሎ የፆመ ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል። ‹‹ረመዳንን አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ ከጅሎ የሰገደ ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል›› فهو فرصة في حياة المسلم قد لا يعود عليه مرة ثانية. ☞︎︎︎ስለዚህ ይህ ወር ላይመለስ የሚችል ዕድል ነው። فالمسلم يفرح بقدوم رمضان ويستبشر به، ويستقبله بالفرح والسرور، ويستغله في طاعة الله ليله قيام، ونهاره صيام وتلاوة للقرآن والذكر فهو مغنم للمسلم، ➪ሙስሊም የሆነ ሰው ረመዳን ሲመጣ ይደሰታል፣ ተስፋም ያደርጋል፣ በደስታ እና ነው የሚቀበለው፣ እድሉን በደንብ በአላህ ትዕዛዝ ላይ ነው ሚያሳልፈው። ሌቱን በመቆም፣ ቀኑን በመፆም፣ ቁርዓን በመቅራት እና አላህን በማስታወስ ነው የሚያሳልፈው። ትልቅ ዕድል ነው። أما الذين إذا أقبل رمضان يعدون البرامج الفاسدة والملهية والمسلسلات والخزعبلات والمسابقات ليشغلوا المسلمين فهؤلاء جند الشيطان، الشيطان جندهم لهذا، 𒊹︎︎︎ነገር ግን አንዳንዶቹ ግን ረመዳን ሲደርስ አዘናጊ ፕሮግራሞችን፣ ፊልሞችን፣ ዝባዝንኬዎችን፣ ውድድሮችን የሚያዘጋጁ አሉ።እነዚህ የሸይጣን ወታደሮች ናቸው። ሸይጣን ነው ለዚህ ተግባር ያዘጋጃቸው። فعلى المسلم أن يحذر من هؤلاء ويحذر منهم، ➪አንድ ሙስሊም የሆነ ሰው ደግሞ ከነዚህ ሰዎች እና ከተግባሮቻቸው መጠንቀቅ አለበት። رمضان ما هو وقت لهو ولعب ومسلسلات وجوائز ومسابقات وضياع للوقت. 𒊹︎︎︎ረመዳን የፍንጥዝያ፣የጨዋታ፣ የፊልም፣ የውድድር ወር አይደለም።" 🤲አላህ የረመዳን ወር በሰላም አድርሰን፣ደርሶም ከሚጠቀሙበት አድርገን የሸይኹን ነሲሓ ቀጥታ ካንደበታቸው ለመስማት ሊንኩን ይከተሉ⤵ http://alfawzan.af.org.sa/sites/default/files/29_7.mp3 ☞︎︎︎ሼር በማድረግ ሌሎችንም የምክሩ ተካፋይ እናድርግ። ጠቃሚ ፅሑፎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ ☟︎︎︎☟︎︎︎☟︎︎︎☟︎︎︎ 𝐓𝐞:https://t.me/dawatulanbiya
Mostrar todo...

▪️ጁሙዓ ነው ፤ ሰለዋት እናብዛ 🔻የአላህ መልእክተኛ - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦ [ በኔ ላይ አንድ ሰለዋትን ያወረደ ሰው ፤ አላህ በሱ ላይ አስር ሰለዋትን ያወርድበታል። ] (ሙስሊም ዘግቦታል). ____ اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد، اللهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد. ___ 📣https://t.me/ibnyahya7
Mostrar todo...
5.03 KB
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.