cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

@ለሚያነብ ትውልድ

@tare idea this group are emotional intelligence group

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
215
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ወዳጄ ሁለት ጆሮ አንድ ምላስ የተፈጠረ ብዙ እንድንሠማ ጥቅት እንድናወራ ነዉ የምጠቅመንን በሁለት ጆሮችን ሰምተን እያጣራን በአንድ ምላስ እንናገር በአንድ ልብ እንበል፤በአንድ አዕምሮ እናስብ፤ማጣሪያዉን እንጠቀምበት በዉስጣችን ፍቅር፤ሰላም፤በጎነት፤ደስታ፤ትጋት፤ ስኬት፤ቸርነት፤ትግስት፤ራስን መግዛት፤መልካምነት እናምርትበት።
Mostrar todo...
ግብህን ካላወክ የትኛውም መንገድ ይወስድሃል የዛሬዋ የአመቱ የመጀመሪያ ቀን ሳታልፍ አንድ ነገር ላሳስብ፡- በዚህ አመት የምትሄድበትን አቅጣጫ ወይም ግብህን ጠንቅቀህ ካላወክ በፊትህ ያለው ሁሉም መንገድ ይወስድሃል፡፡ “ቁም ነገሩ ከየት እንደመጣህ አይደለም፣ ዋናው ቁም ነገር ወደ የት እንደምትሄድ ማወቅህ ነው” – Brian Tracy አንድ መንገደኛ ሰው ረጅምና አድካሚ የሆነ ጎዳናን ካለፈ በኋላ መንትያ መንገዶች ላይ ደረሰ፡፡ በዚያ የቆመን አንድ ሌላ የሀሃገሩን ሰው አየና፣ “ከእነዚህ ሁለት መንገዶች ትክክለኛው መንገድ የቱ ነው?” ብሎ ጠየቀው፡፡ ይህ የሃገሩ ሰው፣ “መሄድ የምትፈልገው ወደ የት ነው?” ብሎ ለመንገደኛው ጥያቄውን በጥያቄ መለሰለት፡፡ መንገደኛውም፣ “ወደ የት መሄድ እንደፈለኩ ገና አላወኩም” አለው፡፡ የቆመውም ሰው፣ “እንግዲያውስ፣ ሁለቱም ትክክለኛ መንገዶች ናቸው” በማለት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መለሰለት፡፡ መንገደኛው፣ “የምትሄድበትን ካላወቅህ የትኛውም መንገድ ይወስድሃል” የሚልን መልእክት ተቀብሎ፣ “መልእክቱ ገብቶኛል” በሚል ዝምታ ተዋጠ፡፡ ብዙ ሰዎች በደመ-ነፍስ ነው የሚኖሩት፡፡ ከየት ተነስተው ወደ የት መሄድ እንዳለባቸው በቅጡ አያውቁትም፡፡ ወደ የት እንደሚሄዱ ማወቅ በሕይወት ላይ ያለውን ተጽእኖ በፍጹም አስበውት አያውቁም፡፡ የግብ ጉዞ የምርጫ ጉዞ ነው - “የትኛውን ጎዳና ብመርጥ ወደ ዋናው የሕይወቴ አላማና ራእይ ያደርሰኛል” የሚል ምርጫ! ግቡን በቅጡ ያላወቀ ሰው የመጣውን ያስተናግዳል፣ ወደተከፈተለት ይገባል፣ ጊዜአዊ ደስታን በሰጠው ነገር ላይ ጊዜውን ያባክናል፡፡ ሕይወት በምርጫ የተሞላች ነች፡፡ ጠዋት በስንት ሰአት ከመኝታዬ መነሳት እንዳለብኝ ከምወስነው ውሳኔ አንስቶ ማታ በስንት ሰአት ወደመኝታዬ መሄድ አለብኝ እስከሚለው ድረስ የምንመርጠው ምርጫና የምንወስነው ውሳኔ በአላማችን ላይ ጣልቃ ይገባል፡፡ “ብዙ ሰዎች የሚያስፈልጋቸው አሳ እንዳልሆነ ሳይገባቸው እድሜ ልካቸውን አሳ ሲያጠምዱ ይኖራሉ” –Henry David Thoreau “የምትፈልገውን ነገር ካልተከታተልከው አትጨብጠውም፡፡ ካልጠየክ መልሱ ሁልጊዜ የእምቢታ ነው፡፡ ወደፊት ካልተራመድክ ዘወትር ራስህን ባለህበት ታገኘዋለህ” – Nora Roberts “ግቡ አልደረስ ያለ ሲመስልህ መቀየር ያለብህ ግቡን አይደለም አደራረግህን እንጂ” Source Dr_MehretDebebe
Mostrar todo...
ከሰማሁት ላካፍላችሁ በድሮ ጊዜ የእንቁራሪቶች ውድድር ነበረ አሉ እና ሁሉም ተወዳዳሪዎች የሚሸነፋበት ነገር ነበረ መሀል ላይ ሲደርሱ" ከዚህ በላይ የተጓዘ ሰው ማለፍ አይችልም ከባድ ነው "ስለሚሏቸው ነበር ነገር ግን ሁሉም እየወደቁ ሲመጡ አንዷ ግን ቀጥ ብላ መውጣት ጀመረች "ለምን"ብለው ሲጠይቁ ጆሮዋ መስማትም አይችልም ነበር አሉ እና አንተስ ጆሮው ምን እየሰማ ነው በምን ወደ ኃላ እየተመለስክ ነው ማን ምን ብሎ ወደ ኃላ እየመለሰህ ነው በዛ ላይስ ምን እየመለስክበት ነው መቶ ብርን ብታጨማድደው ጭቃ ውስጥ ብትከተው ያው ብርነቱን አይቀይረውም ስለዚህ አንተ ውስጥ ያለውን ምንም ነገር ውስጥ ብትገባ ማንም ሊቀይርህ አይገባም ምክንያቱም አንተ ውስጥህ ያለው ሀይል በጣም ትልቅ ነህ ሁሉን ነገር ማድረግ የምትችል ብቸኛው እንቁ ሠው ነህ ለትውልድ ታስፈልጋለህ ከሚሉህ ይልቅ የሆንከው ይበልጣል።። እወድሀለሁ ምክንያቱም አንተ ምርጡ ሰው ነህ
Mostrar todo...
ጀባ ጀባ አንብቡልኝ ።።ቀና በል።። መንገድ ሁሉ እንቅፋት በሆነበት አለም መነሳት ነው እንጂ መውደቅ ብርቅ አይደለም ሰው ብታጣ ዛሬ አትዘን ወንድሜ አግኝቶ ማጣትን ያስተምራል እድሜ ሲኖርህ የኖረህ ስታጣ ብታጣው አለኝ ያልከው ወዳጅ ከፊት ባታገኘው የዛሬው ውድቀትህ መማሪያ ነውና ባጣሀው ሳይጨንቅህ ባለህ ላይ ተፅናና መሙላት ቢቸግርህ ቀን እየጎደለ አታቀርቅር ተነስ ቀና በል ቀን አለ። @menesat....... @menesat @menesat....... @menesat @menesat....... @menesat.. join
Mostrar todo...
ሰላም ሰላም "በህይወት ውስጥ አንዴ ከሄዱ ማይመለሱ ነገሮች : #ጊዜ #ቃል እና #አጋጣሚ በህይወት ውስጥ ልታጣቸው የማይገቡ ሶስት ነገሮች #ሰላም #ተስፋ እና #ታማኝነት በህይወትህ ውስጥ እጅግ ዋጋ ያላቸው ሶስት ነገሮች #ፍቅር #እምነት እና ባለእንጀሮች አንድን ሰው ሰው የሚያደርጉ ሶስት ነገሮች #ጠንክሮ መስራት #ቅንነት እና #ፅናት @menesat........ @menesat @menesat......... @menesat @menesat. ...... . @menesat @menesat.......... @menesat..... join
Mostrar todo...
ጀባ ጀባ በጥዋቷ 👇👇👇👇👇👇 " አንተ ጥዋት ተነስተህ ፊትህን ስትጣጠብ ሌላኛው ደግሞ ጥዋት ተነስቶ ኩላሊቱን የሚያሳጥብ አለና ምንም ባይኖርህም ጤናን አሟልቶ የሰጥህን ጌታ አመስግን"። @menesat......... @menesat @menesat........ @menesat @menesat....... @menesat
Mostrar todo...
#ትራምፕ እና #አል-ሲስ ።።።።። ገጣሚ ታሬ #አል-ሲሲ እንዴት ነው ጌታዬ.. የግድቡ ነገር ኢትዮጵያን ለማስቆም.. እርዱኝ ብዬ ነበር #ትራምፕ በቃሌ መሰረት.. ልረዳህ ወስኜ የሚሳካ መስሎኝ.. በራስ ተማምኜ ኑ ፈርሙ ብዬ.. ላስገድድ ብጠራ እምቢ ብለው ቀሩ ሰረዙ በረራ #አል-ሲሲ ታዲያ ምን ወሰኑ.. እንዲህ ሲዳፈሩ የእርሶ መቺ ሀይል.. አልሰማም ወይ ጦሩ #ትራምፕ ቀላል አይምሰልህ ኢትዮጵያ ላይ መዝመት ፈጣሪም ጭምር ነው አብሮ ሚዋጋላት የአሜርካን ጥቅም.. እስካልነኩ ድረስ ዓለም ይወቅሰኛል.. መብታቸውን ብጥስ #አል-ሲሲ እኔ ግን አልተውም.. እስከ መጨረሻ ጦሬን አዘምታለው..ግድቡን ማፍረሻ #ትራምፕ አትሞክር ወዳጄ.. ይከፋል መዘዙ አይለቁም ሀበሾች..ጦር ከተማዘዙ አስዋን ግድብን..በአየር ከመቱ ካይሮን ያጠፋል.. የውሃ ሙላቱ #አል-ሲሲ ታዲያ ምን ይሻላል..ምን ላድርግ አለቃ እጄን አጣጥፌ.. መቀመጥ ነው በቃ??? #ትራምፕ ተናዳፊ ንቦች..ከሚያሳጡ ፋታ ሳትዋረድ አቁም..ይሻላል ዝምታ የአድዋን ታሪክ..አስታውስና ዛሬ ሚበጅህን ምረጥ..ብስሉን ከጥሬ። @menesat....... @menesat @menesat........@menesat @menesat........ @menesat @menesat......... @menesat.... join
Mostrar todo...
🙏🙏🙏🙏🙏🙏 ዛሬም ጀባ ጀባ 🙏🙏🙏🙏🙏🙏 "የገበሬው ጉብዝናው ዘርን በአንድ ቀን ዛፍ የማድረግ ብቃቱ ሳይሆን የዘራው ዘር ሂደቱን ጠብቆ እስከ ፍሬ እንዲደርስ መስራቱ ነው። ይህ መንገዱም በመጨረሻ ፍሬውን በጣዕም ፣ በጥቅም ፣በይዘት እንዲውም በዋጋ ውድ ያደርገዋል።የዘሩ ደግሞ ውድነቱ ለማፍራት የወሰደው ተፈጥሮአዊ መንገድ ነወ። ትጉህ ገበሬ ከመልካም ዘር ጋር ሲገናኝ ፍርያማነት እና ብልፅግና ተያያዥ መዘዙ ነው። በህይወታችን ለህይወታችን መልካም ገበሬ ካልሆንን፣ የምንዘራውን ዘር መልካም የሆነውን ካልመረጥ፣ በህይወታችን ትክክለኛ መንገድ ላይ አይደለንም ማለት ነው። @menesat @menesat @menesat....... join
Mostrar todo...
💔የድሀ ፍቅር ❣️ 🌺ክፍል 8 👉በእውነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ👈 የአንደኛ እመት የኢንጂነሪንግ ተማሪ ሆኜ ትምህርቴን ጀመርኩ ,ከቤተሰብ ተለይቻለው ሜላቴንም በቀን ሰወስት ጊዜ በስልክ ሰለማወራት እንጂ ናፍቃኛለች ,ለወንድሜ ትንሽዬ ስልክ ገዝታ ሜላት ሰጥታው በሷ ይደውልልኛ በርታ እሽ እኔ ለእናታችን አለውላት ይለኛል የእናቴንም ድምፀ ስስማ ሰላም ይሰማኛል., ትምህርቴን በሚገባ እየተከታታተልኩ ነው ምክንያቱም የእናቴን የወንድሜን የሜላትን ህልም ማሳካት እንዳለብኝና በተራዬ እነሱን ማስደሰት እንዳለብኝ አምናለው ለዛም ነበር በርትቼ የማጠናውና የምማረው.ሜላት አባቷ መስሪያ ቤት እየሰራች ነው በየ ወሩ ትንሽ ብር በባንክ ታስገባልኛለች በቃ የምታደርግልኝ ነገር ከአይምሮዬ በላይ ነው ,እሷ ለኔ የተሰጠች ልዬ ስጦታ ናት,. በዮኒቨርሲቲው ውስጥ ብዙም ጋደኛ አላፈራሁም ምክንያቱም አንዳንዶቹ ልጆች የከተማ ልጅ መሆኔን ይጠራጠራሉ,በዛ ላይ ለነሱ ስልጣኔ ማለት መጠጣት መቃም ማጨስ ነው ያንን ካላደርግሁ ለነሱ ፋራ ነኝ ስለዚህ ማንንም መቅርብ አልፈልግም .አንዳንዴ ከዶርም ከወጣሁ እንኳን ቤተክርስቲያን እንጂ ሌላ ቦታ የትም አልሄድም መሄድም አልፈልግም,. በዚህ ሁኔታ ግማሽ አመት ሆኖ ለእርፍት ወደ አዲስ አበባ መጣሁ ሜላት ልምጣና ልጠይቅህ ስትለኝ እምቢ ያልኳት እንድትንገላታ ስላልፈለግሁ እንጂ ሳትናፍቀኝ ቀርታ አልነበርም ሁሉም ተሰብስበው አገኝኃቸው ሜላት መኪና ተገዝቶላታል ከከተማ ውጪ ግን አይፈቀድላትም ,ሳገኛቸው ደስ አለኝ አብረን ወደ እኛ ቤት ሄድን ቤት ቀይረዋል ነገሮች ሁሉ ተስተካክለዋል ደስ አለኝ እናቴም በቋሚነት የጉልት ስራ እየሰራች ነው,. የእረፍት ጊዜዬን ከቤትሰቤና ከሜላት ጋ በደንብ አሳለፍኩ ቀኑ አልቆ ወደ ዮኒቨርስቲ አመራሁ በቃ ትምህርቴን በደንብ እየተማርኩ ነው በማህል ሜላት መጣች አብረን ዘና አልን ሁለት ቀን ተቀምጣ ወደ አዲስ አበባ ተመለሰች ,እኔም ወደ ጥናቴ ተመለስኩ የ አንደኛ አመት በደረጃ ደስ በምይል ውጤት ተጠናቀቀ,እኔም ቤተሰቤም ተደሰትን,. ወደ ቤተሰብ ተመለስኩኝ ሁለት ወር ክረምትን በፍቅር አሳለፍን ሜላቴም አብራኝ ነች ከስራ መልስ መኪናዋን ታቆምና በታክሲ እኛ ቤት ትመጣለች አብረን አምሽተን እሸኛታለው ,በእኔና በሜላት መሀከል ምንም አይነት መጋጨትም ሆነ መኮራረፍ ተፈጥሮ አያውቅም በድህነቴ እወዳታለው ከእነ ድህነቴ ትወደኛለች በቃ ፍቅራችን እዚህ ድረስ ነው,. የሁለት ወር ከርምት አልፎ ወደ ዮኒቨርሲቲ ተመለስኩኝ ትምህርቴን በሚገባ መከታተል ጀመርኩ ,በቃ ሜላት እየመጣች እየጠየቀችኝ እኔም በእረፍት ጊዜ እየሄድኩ እያየኃቸው አመቱ ተጠናቀቀ ክረምት ሆኖ ወደ ቤተሰብ ተመለስኩ ሜላትን ግን አላገኝኃትም ነበር ,. እቤት ሄጄ ሜላቴጋ ደወልኩ እመጣለው እቤት ቅድም ስብስባ ሰለነበረ ነው አለችኝ ልቤ ፈራ ማታ ደርሶ እስከምትመጣ ስጠቃት አመሸሁ መጣች ተጠምጥማብኝ አለቀሰች ይሄን ያክል ናፍቄሻለው ብዬ ቀለድኩባት አይ አይደለም አለችኝ ልትነግርርኝ የፈለገችው ነገር እንዳለ ከአይኗ እነበብኩ እንባዋ በጉንጮቿ ላይ መውረድ ጀመሩ ግራ ገባኝ,........ ✍✍✍ይቀጥላል✍✍✍..... ❤️ከወደዱት ሼር እና ላይክ👍 ያድርጉ :*:*:*:*:*🌺:*:*🌹:*:🌺*:*:*:*:*:*: ••●◉Join us share @yefeker_kemist ┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹✿🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄ ...📩 @yefeker_kemist
Mostrar todo...
💔የድሀ ፍቅር 🌺#ክፍል 7 👉በእውነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ👈 ... የማትሪክ ፈተና መጥቶ እኔና ሜላት ውጤት ለመቀበል ትምህርት ቤት ተገናኝን። የማትሪክ ውጤት ቅድሚያ የኔ ወጣ ደስ የሚል ውጤት አምጥቼ አለፍኩ በጣም ደስ እለኝ ሜላትም ደስ አላት። ከቆይታ በሁዋላ የሜላትም ውጤት መጣ.. በሚያሳዝን ሁኔታ ሜላት ግን አላለፈችም ነበር... በጣም ያሳዝናል! አዘንኩ! አብረን እንደምንቀጥል ነበር የማስበው በቃ ግን አልሆነም፤ ሜላት በውጤቷ ብዙም አልተበሳጨችም ይልቅስ የኔ ማለፍ አስደስቷታል። እኔ ግን አዝኛለው። ውዴ አለችኝ እንደከፋኝ አውቃ ወዬ አልኳት.. አየህ የእኔ መውደቅ አሪፍ ነው ምንክያቱም ባልፍ እንኳን አንድ ዮኒቨርሲቲ ላይደርሰን ይችል ነበር... እኔ እዚህ ከሆንኩ ግን ቢያንስ አንተጋ እየመጣሁ እጠይቅሀለው የፈረደበት የአባቴ ድርጅት አለ እዛ መቀጠር እችላለው ለእናትህና ለወንድምህም እኔ ቅርብ ሆኜ እንከባከባቸዋለው አለችኝ። ከሜላት ያልጠበኩትን ነገር ስሰማ በጣም ደነገጥኩ ይከፋታል ብዬ አስቤ ነበር በተቃራኒው ግን አልከፋትም። እሽ! ብያት ተያይዘን እኛ ቤት ሄድን ለእናቴ የኔ ማለፍ አስደሰታት ሜላት እንዳላለፈች ስታውቅ አዘነች ግን ሁሉም ለበጎ ነው። እናቴ እንደተለመደው ነጠላዋን አንጠልጥላ ወደ ቤተክርስቲያን ሄደች። እኔና ሜላትም ያበጠው ይፈንዳ ብለን ተያይዘን ዘና ለማለት ሄድን። ያን ጊዜ ግን ብር ስለነበረኝ እኔ ልክፍል አልኩ ሜላት አልፈቀደችልኝም! እኔና ሜላት ስንዝናና ውለን መሽቶ ልንለያይ ስንል የባንክ አካወንት መክፈት እንዳለብኝና አንዳንድ ነገሮችን ማስተካከል መጀመር እንዳለብኝ ነገረችኝ። ብዙም ሳይቆይ በሜላት ሀሳብ አመንጪነት ተያይዘን ለመዝናናት ከከተማ ወጣን። በሕይወቴ የማልረሳቸዉ ሁለት ድንቅ ቀናት ካሳለፍን በኧላ ወደ አዲስ አበባ ተመለስን። ነገ ማታ እቤት እመጣለው ብላኝ ተለያየን... በማግስቱ ማታ ሜላት እቤት መጣች በእጆቿ ፊስታል አንጠልጥላለች ተቀብያት ገብታ ተቀመጠች ገና ከመቀመጧ ምንም እንዳትለኝ አለችኝ በፍረሀት ምንድነው አልኳት። ፌስታሉን ፈትታ ለቢጃማ የሚሆን ቱታ የውጪ ቲሽርት ጅንስ ሱሪ ጫማ ቦርሳ ስልክ ሳይቀራት ገዝታ ነበር የመጣችው ምን ልበል ምንም እንዳትል ብላ አስጠንቅቃኛለች ዝም አልኩ አመስግናለው! ከማለት ውጪ... ሜላት ለኔ ከምንም በላይ ነች! በርትተህ ተማር እኔም እየመጣሁ እጠይቅሀለው እነ ማዘር ከናፈቁህ አንተም በእረፍት ጊዜ መጥተህ ታያቸዋለህ ብቻ ትኩረትህ ትምህርትህ ላይ ይሁን አለችኝ። እሽ ማሬ አልኳት! እናቴም ተባረኪ ልጄ አለቻት በርታ እሽ ልጄ አለችኝ በስስት እያየች የእናት እንጀት ሆኖባታል። ወንድሜም ስማ ለኛ እንዳታስብ እሽ እኔ እንዳንተ ጎበዝ እሆናለው አለኝ። እሽ እልኳቸው ሁላችንም እንባ ተናንቆናል! ትንሽ አምሽተን ሜላትን ሸኘኃት። የተለመደውን ግንባሯን አንገቷን ከንፈሯን ስሜ ተለየኃት። ዝግጅቴን አጠናቅቄ የዮኒቨርሲቲ መግቢያ ጊዜ ስለነበር ለመሄድ ወሰንኩ። ሜላትም እናቴና ወንድሜ ሆነው ሸኙኝ። እንደምወዳቸው! ነገርኳቸው ሜላቴ አፈቅርሻለው! አልኳት በቃ ቻው ብዬ ተለየኃቸው። የሚያስፈልገኝን ሁሉ ይዤ ጉዞ ጀመርኩ የብቸኝነት ህይወት አንድ ተብሎ ተጀመረ። እኔና ሜላት እንደዋወላለን ሜላቴ እዛው አባቷ መስሪያ ቤት መስራት ጀምራለች። እኔም ትምህርቴን የመጀመርያ አመት የኢንጅነሪንግ ተማሪ ሆኜ ጀምርያለው። ነገር ግን አሁንም አንድ ነገር አስባለው........ ✍✍✍ይቀጥላል✍✍✍..... ከወደዱት ሼር እና ላይክ👍 ያድርጉ :*:*:*:*:*🌺:*:*🌹:*:🌺*:*:*:*:*:*: ••●◉@yefeker_kemist ┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹✿🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄ ...📩 @yefeker_kemist
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.