EECSF
Ir al canal en Telegram
ይህ በ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ ህንፃ ኮሌጅ ወንጌል አማኞች ክርስቲያን ህብረት ነው:: #ተቀዳሚ_ዐላማ፤የምንኖርለት:- •ተማሪዎችን በማገልገል የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋት #በዚህ_ቻናል:- ☞ የክርስቶስን አካል የ ሚያንፁ ልዩ ልዩ መልዕክቶች ይቀርባሉ:: ☞ከ ህብረቱ መሪዎችና ከ [ኢቫሱ] የ ሚተላለፉ መልዕክቶችን ያገኛሉ::
Mostrar más508
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días
Archivo de publicaciones
508
እሺ....ጌታ ይመስገን!!
ዛሬ ቀለል ያሉ የ 100 MB ሽልማት የሚያስገኙ ጥያቄዎች አሉ። ቀድሞ ለመለሰ ብቻ😊!!!
እንሂድ...................
508
ማስታወቂያ
📌 በጌታ ፊት እየተጋችሁ እንደሆነ ተስፋ እናደርጋለን አሁንም ለእኛ ደስታችን እርሱ ነውና ሳንታክት ወደ ፀጋው ዙፋን በዕምነት እንቅረብ
📌 እባካችሁ ማገልገል የምትፈልጉ በጌታ እንለምናችኃለን አሳውቁን!!!!!!!!!!
ተባረኩ
508
ስለ ቃሉ ጊዜ ጌታችን የተመሰገነ ይሁን!!
ቃሉ የሚለንን ሰምተን የምናደርግ እንድንሆን ጌታ ይርዳን፤ አሜን። መልዕክቱን ያካፈለንን ወንድም አቤል እግዚአብሔር ይባርክልን፣ያሳድግልን!!
508
"በመከራችን ደግሞ እንመካለን"🙏
ወንድም አቤል ታረቀኝ
👋 እንደምን ናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች እና እህቶች ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
ዛሬ ሰሞኑን በውስጤ ይመላለስ ያለውን ቃል አካፋላችኋለሁ።💥
📖" በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው፤ ከተፈተነ በኋላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን የሕይወትን አክሊል ይቀበላልና።"
(የያዕቆብ መልእክት 1:12)
📌 የሰው ልጅ በሚኖርባት በዚች በዘላለም ቅፅበት በሆነች የምድር ቆይታው ላይ አልፈተንም ማለት አይችልም።
📌ይብዛም ይነስም ሁሉም ሰው በህይወቱ መከራ ይደርስበታል።🤷♂
📌ስራ ማጣት, በህመም ምክንያት አልጋ ላይ መቆየት, በከፍተኛ ጭንቀት እና ድብርት ውስጥ መውደቅ, በሱስ እስራት ውስጥ መዘፈቅ, በሚያምኑት ሰው መከዳት, ረሀብ, ገንዘብ ማጣት, ጦርነት, እስራት እና የመሳሰሉት የመከራ ናዳዎች በእያንዳንዱ ሰው ህይወት ውስጥ በር አንኳኩተው የሚገቡ ችግሮች ናቸው።
📌በመከራ እና በፈተና መሀከል ልዩነት አለ።👌
📌ፈተና ችግር ውስጥ ሳንገባ ችግሩን የምናልፍበት ጥበብ ሲሆን መከራ ግን ችግር ውስጥ ከገባን በኅላ ችግሩን ለማለፍ የምናሳየው ትዕግስት ነው።
✅ ፈተናን ለማለፍ እውቀት ያስፈልጋል።
✅ መከራን ለማለፍ ግን ፅናት ያስፈልጋል።
✅ መከራን ማለፍ የሚቻለው በመፅናት ነው።
📖" ሴት በምትወልድበት ጊዜ ወራትዋ ስለ ደረሰ ታዝናለች፤ ነገር ግን ሕፃን ከወለደች በኋላ፥ ሰው በዓለም ተወልዶአልና ስለ ደስታዋ መከራዋን ኋላ አታስበውም።"
(የዮሐንስ ወንጌል 16:21)
📌ፈተናን ማለፍ የሚቻለው ግን በእግዚአብሔር ቃል ሙላት እና በፀሎት ነው።
📖" ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤ መንፈስስ ተዘጋጅታለች ሥጋ ግን ደካማ ነው አለው።"
(የማቴዎስ ወንጌል 26:41)
📖(የሉቃስ ወንጌል ምዕ. 4)
----------
3፤ ዲያብሎስም። የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ ይህን ድንጋይ። እንጀራ ሁን ብለህ እዘዝ አለው።
4፤ ኢየሱስም። ሰው በእግዚአብሔር ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል ብሎ መለሰለት።
📌መከራም ሆነ ፈተና የሚያልፋ ጉዳዮች ናቸው ግን ማንም ሲፈተን በእግዚአብሔር እፈተናለሁ አይበል ምክንያቱም እግዚአብሔር በክፋ አይፈትንምና።
📖(የያዕቆብ መልእክት ምዕ. 1)
----------
13፤ ማንም ሲፈተን። በእግዚአብሔር እፈተናለሁ አይበል፤ እግዚአብሔር በክፉ አይፈተንምና፤ እርሱ ራሱስ ማንንም አይፈትንም።
14፤ ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል።
📌እና በፈተና ውስጥ የሚያልፍ ሰው ሁሉ የሱ ፈተና ከሌላው ቢለያይም ግን እስከ ዛሬ ያሉ ክርስቲያኖች ተፈትነው ያለፉበት መንገድ ስለሆነ በእግዚአብሔር ይታመን።
✅ ሁሉም ሰዉ እንደየአቅሙ ሊፈተን ግድ ነውና
✅ በመከራ አለመፅናትም ዋጋው ከባድ ነው
✅ ግን እኛ ይሄን እናምናለን እግዚአብሔር መውጫውን ያዘጋጅልናል።
📖" ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል።"
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10:13)
📌ደግሞም
📖 " ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን መከራ ትዕግሥትን እንዲያደርግ፥ ትዕግሥትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን፥ በመከራችን ደግሞ እንመካለን፤"
(ወደ ሮሜ ሰዎች 5:3-4)
📖" በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።
"
(የዮሐንስ ወንጌል 16:33)
🛑 ሀሌሉያ ዓለምን ያሸነፈ አምላክ አለን ሁሌም በአምላካችን ላይ እምነታችን የፀና ይሁን።
❓ ታዲያ መከራን እና ፈተናን ለማለፍ ምን ማድረግ አለብን??🤔
🛑 አጥብቀን በእግዚአብሔር ፊት መፀለይ እና ፊቱን መፈለግ እለት እለት በቃሉ ሙላት መሞላት እና በመፅናት አጥብቀን ክርስትናችንን መያዝ ወይ እኛ እስከምንሄድ ወይ ደግሞ ክርስቶስ እስኪመጣ
🙏አሜን ማራናታ ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ ና!!!!!
ተባረኩ።🖐
508
ሰላም የክርስቶስ ኢየሱስ ለሆናችሁ ለእናንተ ይሁን!! ፕሮግራማችንን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንጀምራለን፡፡ እንግዲህ እግዚአብሔር አምላክ በምህረቱ ጠብቆን ለዛሬ ደርሰናልና ክብር ሁሉ ለእርሱ ይሁን፡፡ ዛሬም የምንተናነፅበትን እና የምናድግበትን መልካም ፍሬ አብረን እንካፈላለን
አብራችሁን ቆዩ።
508
📌 2ዜና 31:20-21 (አ.መ.ት)
ሕዝቅያስ በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት መልካም፣ ቅንና ታማኝ ሆኖ በመገኘት በመላው ይሁዳ የፈጸመው ተግባር ይህ ነው።
የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በማገልገልም ሆነ፣ ለእግዚአብሔር ሕግና ትእዛዝ በመገዛት አንጻር ያደረገውን ሁሉ በፍጹም ልቡ አምላኩን በመፈለግ አከናወነ፤ ተሳካለትም።"
📌 የምናደርገውን ነገር ሁሉ እግዚአብሔር አምላካችንን #በፍጹም ልባችን ከመፈለግ የመነጨ እና በፊቱ በመልካምነት፣ በቅንነት እና በታማኝነት እንፈጽም ዘንድ ፀጋ ይብዛልን!
👤ወንድም እዮሲ
(ከ ኢቫሱ)
Join now:
@EvaSUE58
@EECSF
