cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegaciĂłn. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Ayuti Islamic Post 🕌📿

🌜 <<ጌታችን ሆይ! አንተ በርሱ(ለመምጣቱ) ጥርጥር የሌለበት በሆነ ቀን ሰውን ሁሉ ሰብሳቢ ነህ። ምንጊዜም አላህ ቀጠሮውን አያፈርስምና።>>🌛 [ ሱረቱል-ኢምራን=9] አላምችን የምናውቀውን ማካፈል ነው ። ሀሳብ እና ለአስተያየት ካሎት በ👉 @Halaltube_bot Leave ከማለቶ በፊት ስህተቴን ያሳውቁኝ🙏🙏🙏

Mostrar mĂĄs
El paĂ­s no estĂĄ especificadoEl idioma no estĂĄ especificadoLa categorĂ­a no estĂĄ especificada
Publicaciones publicitarias
1 193
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 dĂ­as
Sin datos30 dĂ­as

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ይህ ቻናል በእጅ የተሰሩ የቤት ውስጥ ዲኮሮች የስልክ ከቨሮች ለ ኪችን ለሳሎን ለመኝታ የሚሆኑ ምርጥ በእጅ የተሰሩ እቃዎችን በጣም በተመጣጣኝ ዋጋ በትእዛዝ ይሰራል https://t.me/hafsa_decore
Mostrar todo...
Hafi design 🎒👗

ይህ ቻናል በእጅ የተሰሩ የቤት ውስጥ ዲኮሮች የ ሴት እና የወንድ ቦርሳ ለ ኪችን ለሳሎን ለመኝታ የሚሆኑ ምርጥ በእጅ የተሰሩ እቃዎችን በጣም በተመጣጣኝ ዋጋ በትእዛዝ ይሰራል Contact me @Hafsa_decore_and_collection_bot

💧〰〰〰አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰💧   የታሪኩ ርዕስ 💁‍♂ #SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )       #ክፍል ☞ #የመጨረሻ_ክፍል ✍ ፀሀፊ ☞ #ዘቢባ_ሱልጣን አመቱ አለቀ 12ተኛ ክፍል ገባን።ትምህርት በጀመርንበት 15 ቀን ሰአዳን የትምህርት ቤታችን በር ጋር ነጠላ ለብሳ ቆማ እኔኑ ስትጠብቀኝ አየኋት። በድርጊትዋ በጣም ስለተናደድኩ ላናግራት አልፈለኩም ዝም ብያት ባላየ ሸምጥቻት አለፍኩ።ዘይባ ዘቦ አናግሪኝ አንዴ ዘይባ እያለች ስትከተለኝ አላስችል ብሎኝ ዞሬ ምነው ችግር አለ?? አልኳት አይኗን ማየት አስጠልቶኝ መሬት መሬቱን እያየሁ። .....እሷም አፉ በይኝ በአላህ አፉ በይኝ እያለች አንገቴ ሾር ተወሸቀች። .....እኔም መስቀል ገድግዶ ነጠላ ለብሶ ሂጃብ አውልቆ አፉ በይኝ አይከብድም? አልኳት። .....ሰአዳም እባክሽ አሁን አትውቀሺኝ ይቅርታ ልጠይቅሽ ነው ብሩክን ቤተክርስትያን ነኝ ብዬው የወጣሁት አለችኝ። እኔ ይቅርታ ባደርግልሽም ባላደርግልሽም ችግር የለውም ችግሩ አላህ ጋር ነው ይቅርታ መጠየቅ ያለብሽ አላህን ነው አልኳት። ....ልጄስ?? አለችኝ .....ልጅሽ ምን ሆነ ስል ጠየኳት? ......ብሩክን ከተውኩት ልጄ ማን ያሳድግልኛል?? አለች። .....እኔም አንቺ ወደ እስልምና የመመለስ ፍላጎት ካለሽ አንጥፈን እየለመንም ቢሆን ሊላህ ወረሱል በሉን እያልንም ቢሆን ልጁን እናሳድገዋለን አያትሽም አሉ አብሽሪ አንቺ ብቻ ወስኚ አልኳት። ....ያለምንም ማቅማማት ተስማማች።እዛችው ቦታ ላይ ድንጋይ ላይ ቁጭ ብለን ስላሳለፈቸው ታሪክ ሁሉንም ነገር አጫወተችኝ። ብሩክ ውጪ በወጣች ቁጥር ሌላ ወንድ ጋር ሄደሽ ነው እያለ እንደሚጠረጥራት እና እንደሚደበድባት ነገረችኝ። ነገር ግን እስዋ ከዛ ሹሾ ሙሉ ለሙሉ ወጥታለች ማጨስም መቃምም ብሩክን ፍራቻ አቁማለች።እሱ ግን እዛ ቤት ይመላለሳል።ከሌላ ሴት ጋር ተኝቶ እጅ ከፍንጅ እንደያዘችውም ነገረችኝ። .....ለምን እዚህ ምን ትሰራለህ?? እንዴት ይሄን ታደርጋለህ ??ባለችው ጊዜም ..... አንቺን ያገኘሁሽ ይሄን ስትሰሪ አይደለም ወይ ምን እራስሽን እንደ ጨዋ ታያለሽ ብሎ እንዳሸማቀቃት እያነባች እያለቀሰች ነገረችኝ።አንዳንዴም አድሮ እንደሚገባ ሴት ይዞ መቶ አልጋዋ ላይም እንደሚተኛ ስትነግረኝ አብሬያት አለቀስኩ። ከዚህ ሰውዬ እንደማድናት ለልሴ ቃል ገባሁ። ንግግራችንን በመቋጨት ላይ እንዳለን ብሩክ መጣ። ......ቤተክርስትያን ነኝ ያልሽኝ ከዚች ጋር ለማውራት ነው ብሎ መደብደብ ጀመረ። .....ሰአዳ እመቤቴን ቤተክርስትያን ነበርኩ አሁን ነው ያገኘኋት እያለች እያለቀሰች ትማፀነው ጀመር። .....እሱ ምክንያትዋን አይሰማም ዝም ብሎ ይደበድባታል ይጎትታታል።እስከዛሬ ድረስ ያሳለፈችውን ሂወት ሳስብ ይበልጥ አሳዘነችኝ። ከነ ሀዩ ጋር እና ዘቦንም ጨምረን ሂወቷን ለመታደግ ቆርጠን ተነሳን ሀያትዋ ጋር ሄደን ስልክ ቁጥርዋን እና የመኖርያ አድራሻዋን ተቀበልን።ወደ ቤትዋም ሄደን ልብስዋን እና ልጅዋን ይዘን አያትዋ ቤት ወሰድናት።አያትዋም በደስታ ተቀበሉን .....ትግስት አልፎ አልፎ እየደወለች ትጠይቀኛለች። ሾል እንዳላገኘች እና ቤት መዋል እንደሰለቻት ታጫውተኛለች። እኔ ለልብስ መግዣ ተብሎ የተሰጠኝን 1000 ብር ሀዩ ቦርሳ መግዣ ብላ ያስቀመጠችውን 500 ብር ዚነት ከትምህርት በኋላ ሾል ስለምትሰራ ያገኘችውን 1000 ብር ሌላኛዋም ሀዩ ለቤተሰብዋ ታሪኩን ተናግራ የተቀበለችውን 2000 ብር በድምሩ 4500 ብር ለ ሰአዳ ለጊዜው ማቋቋሚያ እንዲሆናት ብለን ሰጠናት። ....እንደዛ እያልን ያለንን እያካፈልናት ብዙ ጊዜ ካሳለፍን በኋላ የራስዋ ሾል መስራት ጀመረች የኛንም እርዳታ እንደማትፈልግ ከምስጋና ጋር ነገረችን። አንድ ቀን በማላውቀው ስልክ ተደወለልኝ ሄሎ! ሄሎ! አሰላሙ አለይኩም! ....... ወአለይኩም ሰላም ማን ልበል? ሴት ናት ድምፅዋ አዲስ አልሆነብኝም። .....ፍርዶስ ነኝ ዘቦ አለችኝ። ......ፍርዶስ? አላወኩሽም አልኳት ........ውይ ይቅርታ ትግስት ማለቴ ነው አለችኝ።ግራ ተጋባሁ ትግስቴ እንዴት ነሽ ብዬ ሞቅ ያለ ሰላምታ ከሰጠኋት በኋላ ቅድም ግን ምንድነው ፊርዶስ ምናምን ያልሽኝ አልኳት ...... እስዋም ስሜ ፍርዶስ ሁኗል ሙስሊም ሆኛለሁ የጠፋሁብሽ ቁርአን ለመቅራት አዳሪ መርከዝ ስለገባሁ ነው።ኢንሻ አላህ ካሁን በኋላ አልጠፍብሽም እያለች በደስታ እየተፍለቀለቀች ነገረችኝ። ኢስላም ማለት ሰላም ነው ኢስላም ማለት ደስታ ነው።ይሄንን ደሞ ከትግስት(ከፊርዶስ) ተገንዝቤያለው።አልሀምዱሊላህ ትግስት እስልምናን ተቀበለች። ብሩክ ሰአዳን ይዘናት ወደ ሀያትዋ ቤት የወሰድናት ቀን እዛ ማጨሻው እና መቃሚያው ቤት በመጣው ፀብ ምክንያት በሺሻ እቃ አንዱን ልጅ ጭንቅላቱን መቶት ለሞት ስለዳረገው ለእስር ተዳርጓል። አላህ አሟሟታችንን ያሳምርልን። ፍርዶስም ጊዜ ሳትፈጅ ፍቅረኛ ምናምን ብላ ሳትጃጃል ወንድምዋ ያመጣላትን ባል አገባች ከነ ሀዩ ጋ ከተዋወቅን 4 አመት አስቆጠርን።ከ preparatory school ጀምሮ እስከ ዩኒቨርስትይ ድረስ አልተለያየንም።ዘንድሮ የሁለተኛ አመት ተማሪዎች ነን። አላህ ኒያችንን በሀላል መንገድ እንዲያሳካልን ዱአቹ አይለየን። አደራ አደራ!!! የተሳሳቱ ሰዎችን መመለሾ ባንችል እንኳን የተስተካከሉ ሰዎችን መበላሸት ምክንያት አንሁን ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ መጋቢት 10/07/2012 #ተ.......... #ፈ.......... #ፀ......... #መ ዉድና የተከበራችሁ ቤተሶች ሾለ ታሪኩ ያላችሁን አስተያየት በዚህ ላኩልኝ👇👇👇 @Halaltube_bot @Halal_tube_official
Mostrar todo...
💧〰〰〰አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰💧   የታሪኩ ርዕስ 💁‍♂ #SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )       #ክፍል ☞ ሀያ ሁለት 2⃣2⃣ ✍ ፀሀፊ ☞ #ዘቢባ_ሱልጣን አከራዮቹም ለብዙ ወራት ባለመክፈልዋ አባረዋት ጎዳና ወጥታለች። ጀመአችንም እውቀት ያለው አስተዳደር በማጣቱ ምክንያት ፈረሰ እኔም 11ኛ ክፍል በተዋወኳቸው ሁለት ሀያት ሀያት ከሚባሉ እና ዚነት ከምትባል ልጅ ጋር ጋደኝነት መስርቻለው። ሶላት የምንሰግደውም ከትምህርት ቤታችን ፊት ለፊት ካለው ኮንዶሚኒየም ቤቶች መካከል አንዱ በሆነው በማዘር ቤት ነው. ማዘር የእውነት እናት ናቸው ውሀ ሲጠማን እና ሲርበን ፊታችንን አይተው ይረዳሉ። ልንሰግድ ቤታቸው ስንሄድ እንክብካቤያቸው አይለየንም። ጉዳይ ገጥሟቸው ሌላ ቦታ መሄድ ቢኖርባቸው እንኳን በራቸውን አይዘጉትም ልጆቼ ይመጣሉ አስተናግዱአቸው ብለው ለጎረቤት መልክት ያስቀምጣሉ። አብዛኛው የጊቢው ተማሪም የሚሰግደው ማዘር ጋር እየሄደ ነው።እነ ሀዩ ልክ እንደ ዘቦ የምወዳቸው ልዩ ጋደኞቼ ናቸው በምሳሳት ጊዜ ይመልሱኛል በየአንዳንዱ እንቅስቃሴዬም ይደግፉኛል።ጀመአችን በኛ ምክንያት ፈረሰ። እኛ እውቀት ቢኖረን ባንሰለች ግልምጫቸውን እና ስድባቸውን መቋቋም ብንችል ምናልባትም ባልፈረሰ ነበር። ስልጣን ትልቅ አደራ ነው። ሰው ስልጣን ለመያዝ ይፍጃል ይገዳደላል ይተራረዳል። ሰው ስልጣን ለመያዝ አፈር ድሜ ይበላል ነገር ግን ስልጣን ትልቅ አደራ ነው ስልጣን ትልቅ ሸክም ነው። ስልጣንህን በአግባቡ ካልተጠቀምክ ትጠፋለህ አልያም ሌሎችን ታጠፍለህ። ያለ እውቀታችን ያለ ቦታችን የማይገባንን ስልጣን ተረክበን ከ 14 አመት በላይ የቆየውን ጀመአ አፈረስን።እኛ ያፈረስነው አንዲት ትንሽዬ የተማሪዎች ጀመአ ነው ነገር ግን ሌሎች ያለ ቦታቸው ስልጣን እየያዙ ሀገር እያፈረሱ ነው። ለስልጣኑ ብቁ ካልሆንክ ስልጣን አትያዝ ምክንያቱም ትጠየቅበታለህ!!! 11 ክፍል ልንጨርስ አካባቢ ሰአዳ ልጅ አቅፋ አንገትዋ ላይ መስቀል አድርጋ አየኋት። ያየሁት ህልም እንዲሆን ተመኘሁ ቀርቤ ላናግራት ስሞክር ዞር በይልኝ እያለች ሸሸችኝ።በጣም ተናደድኩ ጅልባብ ለብሳ ያየኋት ልጅ መስቀል አርጋ ሳያት በሸቅኩ። በሌላ ቀን ቤትዋ ሄድኩ።ያረጁት አያትዋ ይንደፋደፋሉ። .....አሰላሙ አለይኩም ማዘር ብዬ ገባሁ። ........ወአለይኩም ሰላም እንኳን ሳይሉኝ የጠፋ ልጃቸው የተገኘ በሚመስል ሁኔታ በደስታ ሰከሩ።አለሽ ልጄ ምነው ጠፍሽ? ወይ ዘይባ!! ሰአዳ እኮ ስላንቺ አውርታ አጠግብም ምነው ተቆራረጣቹሳ? አሉኝ በሀዘኔታ። .....እኔም የትምህርቱ ጉዳይ እኮነው ማዘር አሁን የት ሄዳለች ??ብዬ ወደሄድኩበት አላማ አመራሁ። ....ማዘርም አሁንማ እኔጋር ምን ትሰራለች ባልዋ ጋር ናታ አሉኝ በቁጭት። .....አገባች እንዴ? ብዬ ስጠይቃቸው ......አንቺም አታውቂም ልጄ?ጉድ አረገችኝ እኮ ጉድ ሰራችኝ።አሳድጌ አሳድጌ ረግጣኝ ሄደች። ከፍራ አገባች እኮ።እንደሌላው ሰው በወጉ እንኳን ብታገባ ጥሩ ነበር ነገር ግን ሳትነግረኝ ወንድጋ ኮበለለች አሉኝ። በጣም አሳዘኑኝ። .....ኮበለለች ማለት ለምን አልነገረቾትም? ብዬ ጥያቄዬን ቀጠልኩ።ማወቁንስ አውቄያለው ከረፈደ ሆነ እንጂ። በጅልባብ ደልላኝ ራስዋን ደብቃ 6 ወር ከሆናት በኋላ ነው ማርገዟን ያወከት አሉኝ። ለካ ጅልባብ ለብሳ የነበረው እርግዝናዋን ለመደበቅ ነበር።የሰው አስተሳሰብ ይገርማል። እኔ እኮ ጅልባል ያለበስኩት ለልብሱ ካለኝ ክብር የተነሳ ልብሱን ለብሼ እብድ እብድ ስል ያዩኝ ሰዎች እስልምናን በኔ እንዳይገምቱት እምነቴን በኔ እንዳይመስሉት ካለኝ ፍራቻ አንፃር ነው።እስዋ ያለምንም ማፈር ለእርግዝናዋ መሸፈኛ ስትል አንስታ ለብሳዋለች ሱብሀን አላህ። ......ማዘር ቀጠሉ ከዛም ልደግስልሽ ብላትም አልፈልግም ብላ ልብስዋን ይዛ ቤቱ ድረስ ሄደችለት አሁን ልጅ ወልደው እየኖሩ ነው እየመጣች ትዘይረኛለች።ውድዋ ልጄ ተጎሳቁላለች እኮ። ልጁም ያሰቃያታል መሰለኝ ብቻ አላውቅም አሉ በንዴት። ትንሽ ካቀረቀሩ በኋላም።ፍቺው እኔ አሳድገዋለው ብላትም አሻፈረኝ አለች ከልጅነትዋም ጀምሮ ደረቅ ግትር ናት።ግን ስላንቺ ሳታወራ አልፍ አታውቅም እስዋን ብሰማት ኖሮ ጓደኝነቴን ባጠናክር ኖሮ እዚህ ባልደረስኩ ነበር ትላለች አሉ ማዘር። ብስጭታቸው እየጠነከረ ሲመጣ ንግግሬን አቁሜ እየመጣሁ እዘይራቹሀለሁ በሉ ቻው ወሰላሙ አለይኩም ብያቸው ወጣሁ።እስከ አስፓልቱ ጫፍ እስክደርስ ድረስ አትጥፊ እራስሽን ጠብቂ እንደስዋ እንዳትሆኚ እያሉ እየሸኙ አስጠነቀቁኝ። አመቱ አለቀ 12ተኛ ክፍል ገባን።ትምህርት በጀመርንበት 15 ቀን ሰአዳን የትምህርት ቤታችን በር ጋር ነጠላ ለብሳ ቆማ እኔኑ ስትጠብቀኝ አየኋት። #የመጨረሻዉ_ክፍል_ ይ.........ቀ....... ........ጥ.......ላ........ል @Halal_tube_official
Mostrar todo...
💧〰〰〰〰አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰💧   የታሪኩ ርዕስ 💁‍♂ #SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )       #ክፍል ☞ ሀያ አንድ 2⃣1⃣ ✍ ፀሀፊ ☞ #ዘቢባ_ሱልጣን በሌላኛው ቀን ደሞ ትምህርት ቤታችን ላይ ሌላ አስደንጋጭ ዜና ተሰማ 128 የድላችን ተማሪ ሺም ቤት እንደተያዘ ተሰማ። ከምንም በላይ የሚገርመው ከ 128ቱ 85ቱ ሙስሊም ተማሪዎች መሆናቸው ነው።ከ85ቱ ደግሞ 50ው ሴቶች ናቸው። ከተያዙት መካከል መርየም አንዋር እና ሰአዳ እንዲሁም ብሩክ እንዲሆኑ ምኞቴ ነበር።ነገር ግን እነሱ የዛን ቀን ሌላ ቤት እንቀይር ብለው ወተው ስለነበር አልተያዙም። ወላሂ በሙስሊሙ ተማሪ ብዛት ከልቤ አዘንኩ። የተማሪው ወላጆች እያነቡ የኔ ልጅ እንዲህ አያደርግም ልጄ ከሳምንት ሳምንት ትምህርት ቤት ነው(ናት) ቅዳሜና እሁድም ላይብረሪ ነው ሚያሳልፈው(ምታሳልፈው) እያሉ ወገባቸውን ይዘው ይከራከራሉ። አንዳንዱ ወላጅም በውንጀላ እንከስሀለን እያሉ ዳይሬክተራችን ላይ ይደነፋሉ። ጁመአ ሳይደርስ አስቸኳይ ሚል አደረግን ሁሉም አነባ መፍትሄው ምን እንደሆነ ተወያየን ግን የተሻለ ሀሳብ አላመጣንም። ሁሉም አሚር የጥሪ ሾል እንዲሰራ ተወሰነ ግን ለውጥ አልተገኘም። ትውልዱ ቀልቡ ደርቋል መሰለኝ በአንዱ ጆሮው ሰምቶ በአንዱ ጆሮው ያፈሰዋል። መርየምም ከ አንዋር ጋር የፍቅር ጨዋታዋን ቀጥላለች። አንዋር የሀብታም ልጅ ነው በእድሜውም ከኛ ተለቅ ይላል። ዲነኛ ቤተሰብ አለው እሱ ግን እንደምናውቀው። ማጨስ መጠጣት መቃም ስራው ነው ሁኔታው ያላማራቸው ቤተሰቦቹም ማግባት አለብህ ብለው ወስነው ማትሪክ ሳይፈተን ያንተ መማር ትርጉም የለውም ብለው ትምህርት አስትተውታል። መርየምን እኔ ለማግባት ዝግጁ ነኝ እንጋባ ብትለውም ማግባት የምፈልገው ከነክብርዋ የተቀመጠችን ሴት ነው ንፁህ የሆነች ጋጠወጥ ያልሆነች ቤተሰቦቼ የመረጡልኝን ነው ማገባው ብሎ ቅስሟን ሰባብሮ ጢባጢቤ ተጫውቶ እንደ ሸንኮራ መጦ ቱቱቱ ብሎ ተፍቷቷል። እስዋም በብስጭት ካገኘችው ወንድ ጋር እየተኛች እየተጃጃለች ትምህርቷን አቋረጠች። ሰአዳም እንደመርየም እንዳትሆን በመስጋት ግልምጫዋን ተጋፍቼ ልመክራት ወሰንኩ። ብሩክ ነገ ይተውሻል አላህ ግን መቼም አይተውሽም ተይ ተመለሺ ስል ተማፀንኳት። ሌላው ቢቀር እኮ እሱ ክርስትያን ነው ስላት... እሰልምልሻለሁ ብሎኛል ብላ አፍ አፌን አለችኝ። የፈለገውን እስኪያገኝ ነው እንደዛ ሚልሽ እንጂ እሱ አይሰልምልሽም ብላትም ልትሰማኝ አልቻለችም። ማትሪክ ተፈተንን ስልጣንም አስረከብን። ውጤት መጠባበቅ ጀመርን ትግስት፤ ሰአዳ፣ አሚራ፣ብሩክ፣እየሩስ.......ሁሉም ጓደኞቼ ወደቁ እኔና ዘቦ ግን አለፍን ትግስት ውጤት ባይመጣላትም ቀድሞውኑ እናቴን ማስደሰት አለብኝ የምትፈልገውን ማድረግ አለብኝ ወደ ከሚሴ እሄዳለው ብላ ወስና ስለነበር ውጤቱን እንደሰማች ከእናትዋ ጋር ወደ ከሚሴ ወደ ታላቅ ወንድምዋ አማር ቤት ተጓዙ። ከሚሴ እንደደረሱም ደውላ በእግዚአብሄር ፍቃድ በሰላም ገብተናል አትጨነቂ አለችኝ። ትምህርት ቤታችን የሚመድበው አዲስ ከተማ የተባለ ትምህርት ቤት ቢሆንም በኛ ጊዜ እራሱ ትምህርት ቤቱ ወደ preparatory school ስለተቀየረ እዛው እንድንቀጥል ሆነ።እናም እኔ መሆን የምፈልገው አዋላጅ ዶክተር ስለነበር naturale science ገባሁ ዘቦ ጠበቃ መሆን ስለምትፈልግ social science ገባች። ሰአዳ ጅልባብ ለብሳ አይቻታለው በዚህም ተደስቻለው መርየም በ አንዋር በደል ተጎሳቁላ እራስዋን መጠበቅ ባለመቻልዋ አብረዋት እያደሩ ብር የሚሰጡአት ወንዶችም ርቀዋት የቤት ኪራይ መክፈል አቅቷቷል ።አከራዮቹም ለብዙ ወራት ባለመክፈልዋ አባረዋት ጎዳና ወጥታለች። Part 2⃣2⃣ ይ.........ቀ....... ........ጥ.......ላ........ል @Halal_tube_official
Mostrar todo...
🎉 አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ🤗 እንዴት ናችሁልኝ ውዶች?? ሁሉ አማን? አልሀምዱሊላህ እዚ ሁሉ ሰላም ነው 😊😊😊 🎉 ዛሬ አንድ ለየት ያለ ውድድር ይዤላችሁ መጥቻለው...ውድድሩ በጣም ቀላልና ጠቀም ያለ ሽልማት የሚያስገኝ ነው 😳😳😳 🎉 ውድድሩ በIslamic picture ሲሆን ማንኛውንም ኢስላማዊ ፎቶ በመጠቀም መወዳደር ትችላላችሁ...ለምሳሌ ያክል ከላይ በፎቶ እንዳስቀመጥኩላችሁ ማለት ነው 👆👆👆👆 🎉 ውድድሩ አንድ ዙር ብቻ ነው ያለው ሲሆን ለውድድሩ ዳኝነት የሚሰጠው ሙሉ በሙሉ በ Vote ድምፅ ወይም በlike ብዛት ነው ...ለውድድሩ አሸናፊዎችም 👇👇👇 🥇 1GB 🎁🎁🎁🎁🎁 🥈 500 Mb 🎁🎁🎁🎁 🥉 250Mb 🎁🎁🎁 4 150Mb 🎁🎁 5 70Mb 🎁 🎉 የመወዳደሪያ ፎቶ ለመላክ 👇👇👇👇 @SofiaAhmed_Bot @SofiaAhmed_Bot 🎉 ውድድሩ የሚካሄድበትን ቻናል ለማግኘት 👇👇👇 💝 https://t.me/joinchat/AAAAAFTY7U25epJIYBLuIA 💝 🥳 ከአሁን ሰአት ጀምሮ የመወዳደሪያ ፎቶአችሁን መላክ ትችላላችሁ 🌃 🥳 ፎቶውን ስትልኩ ከፎቶው ጋር አያይዛችሁ ስማችሁንና አድራሻችሁን መላክ እንዳትረሱ ✍ ይወዳደሩ!! ያሸንፉ!!! ይሸለሙ!!! 🏆🏆🏆 ምን ይጠብቃሉ ሳይሞላ ቶሎ ይመዝገቡ እንጂ 😳😳😳😍😍😍😍 @SofiaAhmed_Bot 👇👇👇👇 Join https://t.me/joinchat/AAAAAFTY7U25epJIYBLuIA
Mostrar todo...
💧〰〰〰አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰💧   የታሪኩ ርዕስ 💁‍♂ #SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )       #ክፍል ☞ 2⃣0⃣ ✍ ፀሀፊ ☞ #ዘቢባ_ሱልጣን ብዙ ወላጆችም ልጆቻቸውን ከዛ ትምህርት ቤት አስወጥተው ወደ ሌላ ትምህርት ቤት አዘዋውረዋል... የመርየም እና ሰአዳ ጉዳይ አይምሮዬን አላሳርፍ ሲለው ዘቦን ለምን ከነሱጋር ተመሳስለን ቀስ በቀስ አንመልሳቸውም?? ስል ጠየኳት። .....ዘቦም በፍፁም አላህ ከሀዲዎችን አትምሰሏቸው ብሏል እኮ አለች፡፡ እኔ ግን ሀሳቤን አልቀየርኩም ሰአዲን እና መርየምን የምትቅሙበት ቤት ማየት እፈልጋለሁ አልኳቸው ያለምንም ማቅማማት እሺ ብለው ወሰዱኝ። ቤቱ በተማሪ ተሞልቷል ግን ከመርየም እና ከሰአዳ ውጪ ምንም ሙስሊም ተማሪ አላየሁም። ሄሄሄ.....ጨቅጫቃዋ መጣችችችች እያሉ ጮሁ።ይሄ ስም የተሰጠኝ እየዞርኩ አሰላሙ አለይኩም እያልኩ ሰላት እንዲሰግዱ በመጨቃጨቄ ነው።ሙስሊም ተማሪ ባለማየቴ ተደሰትኩ። ወደ ክፍሉ ከገባሁ 30 ደቂቃ ያክል አስቆጠርኩ እኔ ግን አንድ አመት ያክል የቆየሁ ነበር የመሰለኝ በጣም ይጨንቃል ሽታው ያቅለሸልሻል።ሁሉም እየመጣ እንቺ ንከሺ እያለ ጫት ይሰጠኛል።ተቀብዬ እግሬ ሾር አስቀምጠዋለው። አንዳንዱ ሺም ይስባል።አንዳንዱ ደሞ ሀሺሽ ይስባል። ተማሪው አንድ አንድ እያለ ይመጣል። ክፍሉ ከገባሁ 1 ሰአት አካባቢ ሆነኝ። አንዲት ጅልባቢስት መጣች።እጅዋ ላይ ጓንት አጥልቃለች እግርዋም እስከላይ ካልሲ (ስቶኪንግ) ስላደረገች አይታይም።አለባበስዋ ትክክለኛ ሙስሊምን ይገልፃል። ምን ልትሰራ መጥታ ነው? እንደኔ ለማየት ነው ብዬ እራሴን አሳመንኩ።ወደውስጥ ዘለቀች ሀይ ጋይስ...! ብላ ሰላምታዋን ሰጠቻቸው።አይኔ ከእሷ ጋር ይንከራተታል ስትቀመጥ ዝቅ ይላል ስትቆም ወደላይ ያፈጣል። ቅድምያ ቦርሳዋን አስቀመጠችው።ቀጥላም ጅልባብዋን አወለቀች ግራ ተጋባሁ።አሁንም ቀጥላ ሂጃብዋን አውልቃ ቁጭ አለች። ለካ ሙስሊም ተማሪ የሌለ የመሰለኝ ሁሉም ሂጃቡን አውልቆ ስለሚቅም ነው። እንባዬ መጣ ስሜቴን መቆጣጠር አቃተኝ።እራሴን አመመኝ።የሺሻው እና የሀሺሹ ሽታ ሆዴን አገለባበጠው።ተዝለፍልፌ ወደቅኩ እራሴን ሳትኩ። ወንዶቹም ይሄንን ተጠቅመው ሊጫወቱብኝ ሲሉ መርየም ጓደኛዬን አሳልፌ አልሰጥም ብላ ታደገችኝ። እዛ ቦታ የሚታየው ነገር ይዘገንናል።ሁሉም ወንድ እና ሴት ጥንድ እና ጥንድ ሆነው ነው የሚቀመጡት።ሌላው የገረመኝ ወንዶቹ በአንድ እጃቸው የሺሻ ገመድ ይዘው በአንድ እጃቸው ደሞ እሴቱቹ አካል ላይ ነዉ.....። ሴቶቹም ዩኒፎርማችን ሸሚዝ እና ሹራብ ስለሆነ ሹራቡን አውልቀው ሸሚዙን ጡታቸው አካባቢ ከፍተው ያቀብሏቸዋል። ስሜት መቆጣጠር ሲያቅታቸው ለዚህ ጉዳይ መፈፀምያ ተብሎ ወደተዘጋጀው ክፍል ያመራሉ። አንዱም መልከመልካም ወጣት ነይ እንመቻች አዲስ ትመስሊያለሽ ሲለኝ --------በእድሜ ዘመኔ ያጠራቀምኩትን ስድብ ሁላ አወረድኩበት።መርየምም አዲስ ስለሆበች ነው ሌላ ቀን ስትለምደው ብላ ጠቀሰችው።እዛች መባለጊያ ክፍል አንዱ ተረኛ ፈፅሞ ሲወጣ ሌላኛው ይቀጥላል።ስሜቱን መቆጣጠር ያልቻለም ተራውን ሳይጠብቅ ተደርቦ ይገባል። በጣም የገረመኝ ያሻቸውን ፈፅመው ስሜታቸውን ካበረዱ በኋላ ሴቶቹም ወንዶቹም ሌላ ወንድ ጋር ወይም ሌላ ሴት ጋር ሄደው የሚቀመጡት ነገር ነው በሄዱበት ቦታም ከሌላ ሰው ጋር ልክ እንደዛው ስሜት ቀስቅልሽ አስነዋሪ ነገር ካደረጉ በኋላ ስሜታቸው ሲመጣ በድጋሚ ተያይዘው ወደዛች ክፍል ይገባሉ።በቀን ውስጥ አንዲት ሴት ከተለያዩ ወንዶች ጋር ስትወጣ አይቻለው። ታዳ እነዚህ ተማሪዎች ለHIV ኤድስ ተጋላጭ አይደሉ እንዴ??? የማየዉ ነገር ዘገነነኝ ከዚህ በላይ እዛ መቆየት አልፈለኩም። ሙስሊሙንም ክርስትያኑንም የሚመለከት ንግግር ተናገርኩ።ከተቀመጥኩበት ተነስቼ እኔ መፅሀፍ ቅዱስንም ቁርአንንም አንብቤያለው የትኛውም ሀይማኖት ይሄን ተግባር አይደግፍም ፈጣሪያቹን ፍሩ ከዚህ ዘግናኝ ሹሾ እራሳቹን አርቁ ይሄ እኮ በቁም መሞት ነው። ለነጋቹ አስቡ......................ብዙ ነገር ተናገርኩ ግን አንድም የሰማኝ የለም። ቀልድ ያወራሁ ይመስል ክትክት ብለው ሳቁ። በስተመጨረሻም መርየምንን እና ሰአዳን ቻው ብዬ ወጣሁ።ልብሴ ይሸታል መንገደኛው ሁሉ ያጨስኩ ይመስለዋል ብዬ ፈራሁ።አላህዬ ወደዚህ ቦታ በመምጣቴ ምህረትህን ለግሰኝ እያልኩ ተማፀንኩት። በማግስቱም ለዘቦ እያንዳንዱን ነገር ነገርኳት።መጀመርያም አትሂጂ ብዬሽ ነበር ጥፋቱ የአንቺ ነዉ ብላ ወቀሰችኝ። ከመሄዴ በላይ ያበሳጨኝ የጅልባቢስይዋ ጉዳይ ነው። ከኛ በፊት ከነበሩት አሚሮች መካከል አንድዋ እንደነበረች ሳውቅ ደግሞ ይበልጥ ተበሳጨሁ። ሰው እንዴት ለስሜቱ ይገዛል? እንዴት በስሜት ይነዳል? ራስን መቆጣጠር እንዴት ያቅታል? የእየሩስ አብሮ አደጌ ወንድም ዳግም ትዳር መሰረተ።ከመሰረተም በኋላ ቤቱ እንድትለቅለት አላስቀምጥ ሲላት ቤቱን ለቃለት ከጎረቤቶቿ ጋር መኖር ጀመረች። ጎረቤቶችዋም ይሄን የማድረግ መብት የለውም አንቺም ሀቅ አለሽ ብለው በፍርድ ቤት ተከራክረው ቤቱን እንድትካፈል አድርገውላታል። በሌላኛው ቀን ደሞ ሌላ አስደንጋጭ ዜና ተሰማ Part 2⃣1⃣ ይ.........ቀ....... ........ጥ.......ላ........ል Join👇👇 @Halal_tube_official
Mostrar todo...
💧〰〰〰አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰💧   የታሪኩ ርዕስ 💁‍♂ #SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )       #ክፍል ☞ አስራ ዘጠኝ 1⃣9⃣ ✍ ፀሀፊ ☞ #ዘቢባ_ሱልጣን መፅሀፉንም ከቦርሳዬ አውጥቼ በእጄ እንደያዝኩ የሆነ ድምፅ ተሰማኝ እእእእእእእ እእእእእ ቀስ.....ቀስ.... እእእእእእ የሚል የሴት ድምፅ።ፅው ፅው ፅው የሚለው ትቦ ውስጥ የሚኖሩት አይጦች ልፍያ ድምፅም መሰለኝ። ከክፍላችን ጣራ ላይ ያለው ክፍል ተማሪዎች እርግጫም መሰለኝ ብቻ አላወኩትም ወደ ኋላ ለመዞር አንገቴ አልዞር አለኝ ፈራሁ። አንዳች ነገር በ ፊልም እንደምናየው ሆረር የሚሉት ነገር የመጣብኝ መሰለኝ። አንገቴን ሸርተት ባደረኩ ቁጥር ገና ከመዘሮ በጥፊ የሚደረግምብኝ ሰው ያለም መሰለኝ ብቻ እንደምንም ዞርኩ ዴስኩ ላይ ምንም አይታይም የሰው ዘር የለም።ሶስት ጊዜ አኡዙቢላህ አኡዙ ቢላህ አልኩ።ድምፁ ግን አሁንም አለ። የጥግ ወንበር ሾር ወደ መሬት ስመለከት እንደ እንስሳ የሚንከባለሉ አንድ ወንድ እና አንድ ሴት ተማሪ ተመለከትኩ። ሰአዳ እና ብሩክ ...ያየሁትን ማመን አቃተኝ እውነት መሆኑን ላለማመን አይኔን ውሸት ነው ቅዠት ነው እያልኩ ልደልለው ሞከርኩ ግን አልቻልኩም እውነትን መደበቅ አይቻልማ!!! የእግሬ ኮቴን እንኳን መስማት እስኪሳናቸው በር ሰው ይመጣ ይሆናል ብለው እንኳን ማሰብ እስኪሳናቸው ድረስ በስሜት ጦዘዋል እንባዬ ከጎንጬ ተንቆረቆረ እያዞረኝ ከክፍሉ ድምፅ ሳላሰማ ወጣሁ። በማግስቱም ለማንም ሳልናገር ሰአዳን ልመክራት ወሰንኩ እናም እፈልግሻለሁ ብያት ትናንት ስለሰራችዉ ሾል አናገርኳት .... እስዋም ግን ምነው አንቺ ድንግል ነኝ ማለትሽ ነው? አታስቂኝ የኛ ገሀድ ስለወጣ ነው እንዴ ሁልሽም እናቅሻለን አንገት ደፊ ሀገር አጥፊ የናንተንስ ማን አየላቹ? ስንቱን የቤት ልጅ የተባሉ አይደል እንዴ እዛ ምናየው ብላኝ ሄደች የሰአዲ እንዲህ መበላሸት በጣም ነው የገረመኝ አሳዝኖኛልም ጭምር። የስዋ ብቻ አይደለም የሁሉም ሙስሊም ተማሪዎች መበላሸትም እረፍት ነስቶኛል። አንድ ቀን ለት ጥዋት ሰልፍ ላይ ዳይሬክተራችን አጭር መልእክት አስተላለፈ እያንዳንዱን ጥጋበኛ ለቅመን እናባርራለን ሲል ፎከረ።ንግግሩ ከተማረ ሰው አይጠበቅም። ሁሌም ጋጠወጥ ንግግር ይናገራል። ሳዲቅ የሚባል ልጅ ያለ ጥፍቱ አባሮታል።ምን ሆነ መሰላችሁ ሳዲቅ ሁሉም ተማሪ እንደሚያደርገው አስተማሪ እስኪመጣ ድረስ በርጋ ቆሞ እንዳለ ዳይሬክተራችን ደረሰበት ከዛም ዳይሬክተሩ፦ አስተማሪ የለም? ሳዲቅ፦-... አው ዳይሬክተሩ፦...እና እንደሸሌ(ሴተኛ አዳሪ) በር ጋር ምን ትሰራለህ? ሳዲቅ፦...ምነው ሄደህ ታውቃለህ እንዴ? በማለቱ ነበር የተባረረው።ለ3 አመት የትኛውም ትምህርት ባት እንዳይማርም ታግዷል። በእርግጥ ሳዲቅም ጥፋት አለበት የዳይሬክተሩ ግን ይብሳል። አንዲት ተማሪም ተኳኩላ ሊፒስቲክዋን ተቀብታ ሽቶዋን ነስንሳ ሲያያት ምነው ከሽርሙጥናው ቤት ነግቶብሽ ነው እንዴ የመጣሽው ብሎ አባሯት እናትዋ መታ ልጄን እንዴት እንዲ ትናገራታለህ?? ባለችው ጊዜ ሽርሙጥና እንድትሰራ መንገድ የከፈትሽላት አንቺ ነሽ ማለት ነው ብሎ ተናግሯት አገር ጉድ ብሏል። ነገሩ የገባን በኋላ ላይ ነበር።ለካ የሴቶች ሽንት ቤት ኮርኒስ ውስጥ ተደብቀው የሚያጨሱት ተማሪዎች ተይዘው ተባረው ነው ሲደነፋ የነበረው። የተያዙት ተማሪዎች ደግመው ድላችን ትምህርት ቤት መማር እንዳይችሉ ታግደው ተባረሩ። የሽንት ቤቱ ኮርኒስ እና የወንዶች እና የሴቶች ሽንት ቤት ማገናኛ ያደረጉት ያፈረሱት ግንብም እድሳት ተደረገለት። እኛም በጣም ቁጥጥር በዛብን። ለጥቂት ወራት እስኪረጋጋ ድረስ ምሳ ሰአታችንን ወደቤት ወይም ወደ መስጊድ እንዳንሄድ ተደረግን ሁሉም ተማሪ ትምህርት ቤት መዋል ጀመረ።በነዚህ ተማሪዎች ምክንያት ለብዙ ወራት ትምህርት ቤቱ መነጋገሪያ ርእስ ሆኖ ነበር። በየተኬደበት የሚወራው ድላችን የሚባለው ትምህርት ቤት እኮ አሺሽ ሲያጨሱ ተማሪዎችን ያዘ የሚል ወሬ ነበር የሚሰማው።ብዙ ወላጆችም ልጆቻቸውን ከዛ ትምህርት ቤት አስወጥተው ወደ ሌላ ትምህርት ቤት አዘዋውረዋል... #Part 2⃣0⃣ ይ.........ቀ....... ........ጥ.......ላ........ል Join👇👇 @Halal_tube_official
Mostrar todo...
💧〰〰〰አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰💧   የታሪኩ ርዕስ 💁‍♂ #SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )       #ክፍል ☞ #አስራ_ስምንት 1⃣8⃣ ✍ ፀሀፊ ☞ #ዘቢባ_ሱልጣን ተማሪዎቹ ከአቅማችን በላይ ሁነዋል። ፈቱዲን ያለው ንግግር ትዝ አለኝ። ጀመአው ፈርሷል ማለት ይቻላል ብሎ ነበር አምና።አሁን ግን የምር ፈርሷል ማለት ይቻላል። ሰአዳ እና መርየም ብዙ ጊዜ አንዋር እና ብሩክ ከሚባሉ ልጆች ጋር አብረው ሲንቀሳቀሱ እመለከታለው። እኔና ዘቦ ሰአዳን እና መርየምን ለማስተካከል በጣም እየጣርን ነው። ግን ሊሳካልን አልቻለም። እንዳውም እየሸሹን መተዋል። ዛሬ ፓርቲ አለ ብለው እቅድ ሲያወጡ መስማት የተለመደ ነው። ሰአዳ ግልምጫዋ አያስቀርብም መርየም ግን ገር ናት ፈገግታዋ በራሱ ይስባል። አሰላሙ አለይኩም ስንላት ወአለይኩም ሰላም ሳትለን አታልፍም። ከዚህ ሹሾ እንድትወጣ በምንጠይቃት ጊዜም በኔ አልተጀመረም እኮ ደሞም እንዴትም ብዬ መውጣት አልችልም ሞክሬ ያቃጠኝ ነገር ነው ትለናለች ፡፡ ሰይጣኗ የተነሳ ቀን ደሞ ምናገባቹ አቦ ፍቱኝ ቀኔን አታበላሹ ትለናለች። እንደተለመደው የአሚሮች ሚል ላይ ሾለ ተማሪዎቹ መበላሸት አወራን እናም ቀጣይ የዳእዋ ፕሮግራም በዚህ ጉዳይ ላይ እንዲሆን እና የንግግር ችሎታ ያለው ኡስታዝ እድዲጠራ ወሰንን። የኡስታዝ ምርጫ ላይም ትንሽ ከተከራከርን እና ከተመካከርን በኋላ ኡስታዝ ሙሀመድ ፈረጅ(አይ ዱንያ!) በሚለው ትምህርቱ አፍሪካ ቲቪ ላይ የምናውቀው ኡስታዝ እንዲጠራ ወሰንን እና ተለያየን ።ቀኑ ደረሰ ተማሪዎችም እንዳይቀሩ ብዙ እንቅስቃሴ ከልመና ጋር አደረግን። አልሀምዱሊላህ ፕሮግራሙ ላይ ሰአዳን እና መርየምንም ጨምሮ በርካታ ተማሪዎች ተገኝተዋል። ኡስታዝ ሙሀመድ ፈረጅ ንግግሩ ድንቅ ነው ቀልብ ይስባል ሲናገር ቁጣ እና እልህ በተሞላበት ስለሆነ እንድናዳምጠው ያስገድዳል። ሾለ ተማሪዎች አለባበስ እና ሁኔታንም ጨምሮ ሾለ ሰላት አለመስገድ ብዙ ነገር አስተማረ። ግማሹ ተክዟል ግማሹም ያለቅሳል ሳናውቀው ሰአቱ ሄደ 10 ደቂቃ የቆየን ሳይመስለን በንግግሩ እንደተመሰጥን ፕሮግራሙ አለቀ።ተማሪዎቹ ሄዱ እኛ የተበላበትን ሰሀን ማጠብ እና ቦታውን ማፀዳዳት ጀመርን። ኡስታዝ ሙሀመድ ፈረጅም በርቱ በዚሁ ቀጥሎ ለትውልድ አሻራ ጣሉ እኔም በፈለጋችሁ ጊዜ እገኝላችሆለሁ ብሎን ሄደ። ከዛን ቀን የዳእዋ ፕሮግራም በኋላ ብዙ ተማሪዎች እንደ አዲስ መስገጃ ቤታችን መጉረፍ ጀመሩ። ትግስትም ስራዬ ብላ የጀመአችን ፕሮግራም ከኛ እኩል ትከታተላለች።ሰአዳ እና መርየም ግን የባሰ ስራቹ ላይ በርቱ የተባሉ ይመስል ብሶባቸዋል። የጀመአው ፕሮግራም ላይም መገኘት አቆሙ።መርየም ከአንዋር ጋር ሰአዳ ደሞ ከብሩክ ጋር የፍቅር ግንኙነት ጀምረዋል።ሰአዳ የምትኖረው ከአያትዋ ጋር ስለሆነ አያትዋን አታላ ለፓርቲ እና ለመጠጥ መውጣት ለስዋ ቀላል ነው። ዘይባ ጋር ላድር ነው ብላ በእኔ አሳባ ወጥታ ከ ብሩክ ጋር ታድራለች። መርየም የምትኖረው ብቻዋን ስለሆነ ቁጥጥር የለባትም። ቤተሰቦችዋ ያሉት ገጠር ሲሆን ያሳደገቻት አክስትዋ ናት።ሆኖም ዘጠነኛ ክፍል መጨረሻ አካባቢ በዚህ ባህሪዋ ከ አክስትዋ ጋር ስለተጣላች ከቤት ተባራ ሌላ ቤት ለብቻዋ ተከራይታ ነው የምትኖረው። ለዛም ነው 10 ኛ ክፍል እኛ ትምህርት ቤት የመጣችው። የቤት ክራይ የምትከፍለው አብራቸው ከምታድራቸው የተለያዩ ወንዶች ብር እየተቀበለች ነው። ጀመአችን ተዳክሞአል ብር የሚያዋጣ ሰው እና እስፖንሰር በማጣታችን ምክንያት የምንረዳቸው የቲሞች ቁጥር 10 ደርሷል። አመቱ እየተገባደደ ነው። አንድ ቀን ለታ It (informastion tecnology) ትምህርት ልንማር ኮንፒተር ወዳለበት ክፍል አመራን። የ አይቲ ላብራቶሪያችን ካለንበት ፎቅ ወርደን ሌላኛው ፎቅ ገብተን ስለሆነ የምንማረው ርቀት አለው። አይቲ ላብ ገብተን ወንበራችንን ይዘን እንደተቀመጥን ነበር መፅሀፍ መርሳቴን ያስታወስኩት። አስተማርያችንን እስማኢልን አስፈቅጄ መፅሀፌን ላመጣ ወደ ክፍላችን አመራሁ። ክፍላችን 2ተኛ ፎቅ ላይ ነው ሚገኘው። በሩ አልተዘጋም ገርበብ እንዳለ ነው። ክፍት አድርጌው ወደ ቦታዬ አመራሁ።መፅሀፉንም ከቦርሳዬ አውጥቼ በእጄ እንደያዝኩ የሆነ ድምፅ ተሰማኝ። #Part 1⃣9⃣ ይ.........ቀ....... ........ጥ.......ላ........ል Join👇👇 t.me/Halal_tube_official
Mostrar todo...
Ayuti Islamic Post 🕌📿

🌜 <<ጌታችን ሆይ! አንተ በርሱ(ለመምጣቱ) ጥርጥር የሌለበት በሆነ ቀን ሰውን ሁሉ ሰብሳቢ ነህ። ምንጊዜም አላህ ቀጠሮውን አያፈርስምና።>>🌛 [ ሱረቱል-ኢምራን=9] አላምችን የምናውቀውን ማካፈል ነው ። ሀሳብ እና ለአስተያየት ካሎት በ👉 @Halaltube_bot Leave ከማለቶ በፊት ስህተቴን ያሳውቁኝ🙏🙏🙏

"በሰለዋት የደመቀ የፍቅር ጁምዐ ይሁንልን❣ ❤️የታመሙት የሚድኑበት የታሰሩት የሚፈቱበት ያፈቀሩ የሚዘወጁበት ሀጃ ያለበት ሁሉ የሚሳካለት 🤲 ጁምዓ ይሁንልን 🤲 አሚንን
Mostrar todo...
🤲 368
💧〰〰〰አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰💧   የታሪኩ ርዕስ 💁‍♂ #SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )       #ክፍል ☞ አስራ ሰባት 1⃣7⃣ ✍ ፀሀፊ ☞ #ዘቢባ_ሱልጣን በነገራችን ላይ 10ኛ ክፍል ከገባሁ በኋላ አንዲት አዲስ ልጅ ክፍላችን ገብታለች።መርየም ትባላለች ሲበዛ እብድ ናት እንደስሟም ቆንጆ ልእልት ናት። ውሎዋ ከወንዶች ጋር ነው ደስ ሲላት ክፍል ትገባለች ደስ ሲላት ደግሞ ትቀራለች ሂወቷ ላይ የሆነ አለመረጋጋት እንዳለ ስለተረዳሁ እስዋን ለመምከር የግድ ጓደኛዋ ሆኜ ስለስዋ በደንብ ማወቅ እንዳለብኝ ወሰንኩ እናም ከዘቦጋ ተመካክረን አቀረብናት። መስገጃው ቤታችን እንድትሄድ ብዙ ጊዜ ብንጠይቃትም እናንተ ስለተመላለሳቹ ምን አገኛችሁ?? እያለች ታላግጥብናለች። መርየም ሲበዛ የዋህ እና እንደመሩዋት ምትመራ ሰው ናት ሞኝ ናት።እንዲህ እንድትሆን ያደረጉዋትም ሱሶችን ያስተማርዋት የሰፈርዋ ልጆች ናቸው። ትምህርት ብዙ ጊዜ የምትቀረው መቃሚያ ቤት እየሄደች እንደሆነ አረጋግጫለው። ሰአዳም ቀስ በቀስ ከኛ ጋር መሆን ሙሉ በሙሉ አቁማለች።ጓደኛዋ መርየም ሆናለች።ጭራሽ እንደ አዲስ ገቢ ተማሪዎቹ አሰላሙ አለይኩም ስንላት ትገላመጠን ጀምራለች ሰላትም አቁማለች።ከመርየም ጋር መውጫ እና መግቢያ ሰአታቸው እኩል ሆኖዋል። ሲቀሩ አብረው ይቀራሉ ሲመጡ አብረው ይመጣሉ። የ እየሩስ አሳዳጊ በሽታውን መቋቋም ስላልቻለች ለሞት ተዳርጋለች። እንደ ነገሩ hiv ገደላት ይባላል እንጂ አላህ ከፃፈው ቀን ፍንክች የሚል የለም። ታመመም አልታመመም መሞቱ የማይቀር ነው።እየሩስም በአሳዳጊዋ ሞት በጣም አዝናለች።ያለስዋ ዘመድ አዝማድ ስለማታውቅ ኑሮ ሁሉ አስጠልቶአታል። ይባስ ብሎ ዳግም ያሉበትን ቤት ውርስ እንዳትካፈለው ብሎ ከቤት እንድትወጣለት ማያደርገው ጥረት የለም። የትግስት እናት ዘይነባ ከልጅዋ አማር ጋር ወደ ከሚሴ የመሄድ ፍላጎት ቢኖራትም ትግስትን ትታ መሄድ አልፈለገችም ስለሆነም አማር ለብቻው ወደ ከሚሴ ተመልሷል። መርየም እና ሰአዳ በተለይ የማትሪክ መፈተኛ ፎርም ከሞላን በኋላ ጭራሽኑ መግባት አቁመዋል።ፈተና ሲኖር ለመርየም ቴክስት ስለምናረግላት ይመጣሉ። የሚውሉት ሺም እና ጫት ቤት ነው አሽሽም ያጨሳሉ። በሱስ ተዘፍቀው ካገኙት ወንድ ጋር ይተኛሉ። ትምህርት ቤትም በሚመጡበት ጊዜ ሹሹ አላስቀምጥ ሲላቸው ሽንት ቤት እየሄዱ አጭሰው ይመለሳሉ። የሴቶች ሽንት ቤት ጣራ ውስጥ ምሽግ ሰርተው ከክፍል ፎርፈው ቁጭ ብለው የሚያጨሱ ተማሪዎች አሉ እዛው ቦታም ዚና የሚፈፅም ሞልተዋል። የሴቶች ሽንት ቤት ኮርኒስ ውስጥ የሚሰሩትን ሾል ለመጀመርያ ጊዜ ያየሁት እኔና ዘቦ በ history ክፍለ ጊዜ ስናወራ አስተማሪያችን አይቶን አስወጥቶን አንበርክኮን እጅ ወደላይ አስብሎን የቀጣን ቀን ነው። ሾለ አድዋ ጦርነት እየተማርን ነበር ከተንበረከክንም በኋላ አስተማሪው ለ ዘቦ አንድ ጥያቄ ጠየቃት፦ ጣልያን ኢትዮጵያን ብትገዛት ኖሮ አባቶቻችን ታግለው ባያድኑን ኖሮ ምን ይፈጠር ነበር ሲል ጠየቃት ዘቦም ፦ ጣልያን ብትገዛንማ ኖሮ የካቲት 23 (የአድዋ ቀን) ትምርት አይዘጋልንም ነበር ስትል መለሰች። . .....አስተማሪያችን በመልስዋ በጣም ስለተናደደ ሁለተኛ በኔ ክፍለ ጊዜ እንዳትገቢ ከክፍሉ ውጪ ብሎ አባረራት።እንዴት ታፌዝብኛለች ብሎ ተበሳጨ። እኔን ደሞ ከተንበረከኩበት ተነሽና ወንበርሽ ላይ ተቀመጪ ብሎ ምህረት ቢያደርግልኝም ጓደኛዬን ትቼ አልገባም ያወራነው አብረን ነው ከተባረርንም አብረን ነው ብዬ መለስኩለት ያኔ አንቺም በኔ ክፍለ ጊዜ እንዳትገቢ ብሎ ከክፍሉ አስወጣኝ። እውነት ለመናገር በዘቦ ንግግር እኔም ተናድጃለሁ። ክፍላችን ያለበት ፎቅ እየወረድን እንዴት እንዴ ትይዋለሽ ብዬ ጮህኩባት።ለነገሩ ሸር አስባ ወይም ለማላገጥ ብላ አልነበረም የእውነት ስሜትዋን ነው የተናገረችው። ትምህርት የለም ከተባለ ደስታዋን አትችለውም።ብዙውን ጊዜም ትቀራለች። ፎቁን ከወረድን በኋላ ዳይሬክተራችን እንዳያየን እየሮጥን ወደ ሽንትቤት ሄድን ክፍለ ጊዜው አልቆ እስኪደወል ድረስ እዛው ለመቆየት አሰብን። እኔ በአርፋጅ ዘቦ ደግሞ በመቅረት ሪከርድ ስላለብን ዳይሬክተሩ ካየን መባረራችን የማይቀር ነው። ሽንት ቤት ደረስን።ለሴቶች ከተዘጋጀው 6 ሽንትቤት መካከል 6ተኛው ከወንዶች ሽንትቤት ጋር የተያያዘ ነው።እዛ ክፍል ውስጥ አንዳች ድምፅ ሰማን የሚንገጫገጭ ድምፅ። በሩን ከፍተን ምን እንደሆነ ለማየት ገባን።ለካ ክፍሉን መወጣጫ አድርገው ወደ ኮርኒሱ እየገቡ ነበር። የዛን ቀን ነው ኮርኒስ ውስጥ አሽሽ እንደሚያጨሱ ያወቅነው። በጣም የሚገርመው ደግሞ ያ ስድስተኛው ሽንት ቤት ከወንዶቹ ሽንትቤት ጋር የሚያገናኘውን ግድግዳ አፍርሰው ከወንዶች ጋር መገናኛ አድርገውታል። ውስጥ ለውስጥ ሳይታወቅባቸው ወንዱ በወንዶች በኩል ሴትዋ በሴቶች በኩል ገብተው ያሻቸውን ያደርጋሉ ዚና ይሰራሉ።ትምህርት ቤት ውስጥ(የሴቶች ሽንት ቤት) ማጨስ ሳይችሉ ሲቀር የግንቡን አጥር በድብቅ ዘለው አምልጠው ወደ ማጨሻ ቤታቸው ያመራሉ።... Part 1⃣8⃣ ይ.........ቀ....... ........ጥ.......ላ........ል Join👇👇 @Halal_tube_official
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sĂłlo permite el anĂĄlisis de 5 canales. Para obtener mĂĄs, elige otro plan.