cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

አርሰናል daily fans page🇪🇹

🔻|| ወቅቱ የዝውውር ነው ይህንንም አስመልክቶ የትም መሄድ ሳይጠበቅብዎት ካሻዎት በፌስ ቡክ ፔጅ ወይም በመወያያ ግሩፓችን ለቴሌግራም ተጠቃሚዎች ደሞ በቴሌራም ቻናላችን ሥለ ተወዳጁ ክለባችን አርሠናል 👇👇👇👇👇👇👇👇 ➡️|| ዜናዎች ➡️|| የዝውውር ጭምጭምታዎች ➡️|| የተረጋገጡ ዝውውሮችን ➡️|| ሰበር ዜናዎችን [Breaking news] ➡️|| ትንታኔዎችን እና ➡️|| ቀጥታ ሥርጭት

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
2 356
Suscriptores
+124 horas
-17 días
-2330 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Photo unavailableShow in Telegram
✊በዩሮ 2024 አንዳንድ ቁጥራዊ መረጃ ... ☑️ ብዙ ሙከራ ያደረገ = ካይ ሀቨርት 🥇 ☑️ ብዙ ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ = ካይ ሀቨርት 🥇 ☑️ በተቃራኒ የግብ ሳጥን ውስጥ ብዙ ኳስ የነካ = ካይ ሀቨርት 🥇 ☑️ ከፍተኛ xG ያለው = ካይ ሀቨርት 🥇 ✅👉  የኛዋ ተወካይ 👉 ከይ ሉካስ ሀቨርትዝ በዚ የውድድር አመት ለክለቡ እና ለሀገሩ በአጠቃላይ 19 ጎል አስቆጥሯል 👉በአጠቃላይ ለሀገሩ ጀርመን ያለው እስታት                         ✅ 38 Starts                         🛑 30 G/A                         ⚽️18 Goals                         ✍️12 Assists 💪     The    king strikes again 🎯 👑 kai is on 🔥
Mostrar todo...
👍 5🔥 1
👑
Photo unavailableShow in Telegram
"ቡካዮ ሳካ ከኮል ፓልመር የተሻለ ፈጣን እና ልምድ ያለው ተጫዋች ነው።" 🇬🇬󐁿😃             🗣 ይህንን የተናገረው የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን አሠልጣኝ ጋሬዝ ሳውዝጌት ነው 🗣️ ጋሬዝ ሳውዝጌት ለምን ከፓልመር ይልቅ ሳካን በቋሚ አሰላለፍ  እንደሚመርጥ ተናግሯል፡- 🗣“ሰካ እና ኮል ፓልመር ትንሽ የተለያዩ ተጫዋቾች ናቸው ፣ ነገር ግን ሁለቱም የግራ እግር ተጫዋቾች ናቸው  የግራ እግር ተጫዋች በመሆናቸው ሚናቸው አንድ አይነት ቢሆንም  ሁለቱም ከመስመር እየተነሱ ወደ ሳጥን ውስጥ እየገቡ የቀኝ ክንፍ መሥመሩን ይጠቀሙበታል የሁለቱም ሚና አንድ ቢሆንም የተወሰነ ጥቂት ልዩነት አላቸው።" 🗣" ቡካዮ ሳካ ምናልባት ከፓልመር የበለጠ ቀጥተኛ ፣ የበለጠ ፍጥነት ያለው ከኳስ ጋርም ያለ ኳስም የበለጠ ፍጥነት ያለው  እና ከእሡ [ፓልመር] የበለጠ ልምድ ያለው ተጫዋች መሆኑ ግልጽ ነው።" 🗣"ኮል ፓልመር በዚህ የውድድር ዘመን የመጀመሪያ የውድድር አመቱ ከፕሪሚየር ሊጉ ጋር በጥሩ ሁኔታ እየተላመደ ነው እና ከእኛ ጋርም  ህይወትን ይሰጣል። ስለዚህ በሁለቱም ተጫዋቾች በቡድናችን በመኖራቸው በጣም ደስተኞች ነን።" 🗣"ሁለቱም ጥሩ ለቡድናችን ጥሩ አስተዋፅዖ አበርክተዋል እያበረከቱም ይገኛሉ እናም ቡድናችን ላይ ያላቸውን ብቃት ሠጥተው ቡድኑ ላይ የተለየ ለውጦችን ማምጣት ይፈልጋሉ።" 👉 እሥኪ እናንተም ሀሳብ ስጡ ከደጋፊነት መንፈስ ውጡና ለእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን በቋሚነት መጀመር ያለበት ማን ነው ? ✨ ቡካዮ ሳካ 😘 ✨ ኮል ፓልመር ❤️
Mostrar todo...
🥰 3 1
😘
❤️
👍 4 1
🚨 ሰበር ዜና ✍🇹🇷ፈርዲ ካዶዮግሉ ወደ አርሰናል? ↘️አርሰናል ለቱርኩ ኮከብ  20 ሚሊዮን ይሮ ይፋዊ ጥያቄ ለፌነርባቼ አቅርቧል !🇹🇷 🔥ፌነርባቼ ለተርካዊ ጥበበኛ 35 ሚሊዮን ይሮ ይፈልጋል! ✍Aygun Ozipek ( ታማኛ የቱርክ ዘጋቢ ) ስለ ቱርካዊው 🇹🇷ፈርዲ ካዶዮግሉ ሌላው መረጃ ደሞ 👇 🚨 ታዋቂው ቱርካዊው ጋዜጠኛ ሳቻ ታቮሊሪ እንዳለው ቱርካዊው የፊነርባቼ የግራ ፉልባክ ተከላካይ እና ሁለ ገብ ተጫዋች ወደ አርሰናል ሊቀላቀል መቃረቡን የፈርዲ ካዲኦግሉ የቅርብ ምንጮች ሹክ ብለውኛል በማለት ታዋቂው ጋዜጠኛ  ሳቻ  ታቮሊሪ አረጋግጠዋል። 🔸️አርሰናል ቱርካዊውን የ24 አመት ሁለገብ ተጫዋች ወደ ኤምሬትስ ለማዘዋወር ከተጫዋቹ ጋር በሁለቱ ወገኖች መካከል ረዥም ግዜን የፈጀ ውይይት ማድረጋቸውን እና በግል ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ ለመድረስ በሁለቱም ወገኖች መካከል የተካሄደው ውይይት ሥኬታማ እንደነበረ የዘገበ ሲሆን ። ዘገባው አክሎም  አርሠናል ከተጫዋቹ እና ከወኪሉ ጋር ሥምምነት ላይ መድረሳቸውን ነገር ግን ከክለቡ ከፌነርባቼ ክለብ ጋር ምንም አይነት ቀጥተኛ ውይይት እንዳልተደረገ ዘግቧል። 🔸️ከአንድ ወር በፊት ሥለዚህ ዝውውር ያልተረጋገጠ ምንጭ ከወደ ቱርክ 🇹🇷  የአገሪቷ ከፍተኛ ተነባቢ እና የፊነርባቼ የቅርብ መገናኛ አውታሮች መረጃው የተሰራጨ ሲሆን በተጨማሪም የካዲኦግሉ አባት ልጁ መድፈኞቹን በክረምቱ ዝውውር እንደሚቀላቀል ተናግሯል። ከዚህ ቀደም አርሰናል ይህን ተከላካይ እንደሚያነጋግረው ብዙ ወሬዎች ነበሩ። 🔸️ፌርዲ ካዲዮግሉ የ24 አመቱ ወጣት ሲሆን በዋናነት የሚጫወተው በግራ ተከላካይነት ነው ነገርግን በቀኝ በኩል እና በመሀል አማካዩ ጥሩ መጫወት ይችላል። 🔸️ይህ በቴክኒክ ላይ የተመሰረተ በማጥቃት ላይ ያተኮረ ተከላካይ ነው ኳስን የመቆጣጠር እና የማዞር ዝንባሌ ያለው እና በጥሩ ሁኔታ መጨረስ ይችላል። 🔸️ፌርዲ ካዲኦግሉ በቱርክ ብሄራዊ ብሄራዊ  ሻምፒዮና ሊግ ውሥጥ ከክለቡ ጋር የተሳካ የውድድር አመት ማሳለፍ የቻለ ሲሆን ይህ ቱርካዊ ሁለገብ ኮከብ በቱርክ ሊግ ውሥጥ በርካታ የተሳኩ ፓሶች በማድረግ እና ኳስ ለጎል አመቻችቶ በማቀበል የሚቀድመው አንድም ተጫዋች የሌለ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ የኋላ መሥመር ተከላካዮችን በማገዝ እና ኳሥ በማሠራጨት ኳሥ ከቡድን አጋሮቹ ተቀብሎ በማቀበል ይመራል በተጨማሪም የመልሶ ማጥቃትን በማቋረጥ  እና የተሳኩ ታክል በመውረድ እግር ኳስ ላይ የተመሰረተ ብቃት ያለው በሁሉም ቁጥሮች ይህ ኮከብ በሊጉ አናት ላይ ይገኛል። ↪️ይህን ልጅ አይቶ ለአርሰናል አለመመኘት ሀጥያት ነው.... ↪️እውነት ለመናገር ስለዚህ ልጅ የሰማውት እና መከታተል የጀመርኩት ፕሪሚየር ሊጉ የመጨረሻ ሳምንት አካባቢ ነበር...ትክክለኛ የአርሰናል ተጫዋች ቀለም ያለው ፤ ቴክኒካሊ ጊፍትድ የሆነ ፤ ድሪብል በደምብ ማድረግ እሚችል፤ ከሳጥን ውጪ ሹት አርጎ የሚያገባ  ፤ በሁለቱም እግሩ መጫዋት ሚችል ፤ የተለያየ ቦታ መጫወት የሚችል ፋልባክ መሀል ክንፍ ፤ ገና ወጣት ሁሉም ነገር ያለው ድንቅ ተጫዋች ነው። ለማንኛውም ዝውውሩ የሚሳካ ከሆነ ብዙ ትንታና ሠርተን እናጋራችኋለን  ለጊዜው ግን የልጁን ድንቅ ብቃት አጭር ቪዲዮ ኮሜንት ላይ  ከስር ችሎታውን በቪዲዮ ተመልከቱት ✊
Mostrar todo...
👍 5👏 2😁 1
😳ስፐርስ በትናት ምሽቱ ጨዋታ በቼልሲ ከተሸነፈ በኋላ የዋንጫ ተፎካካሪዎቹ በተለይም የማንችስተር ሲቲ ደጋፊዎች ከትናንቱ የቶትንሃም ሽፈት በኋላ "ይህ ቶትንሃምን ነው የአርሰናል ደጋፊዎች ሲቲን እንዲያሸንፍ  የሚጠብቁት ከወዲሁ እርማችሁን አውጡ ተስፋ ያረጋችሁት በዚህ ቶተንሃም ከሆነ፣ እንግዲያውስ ማንችስተር ሲቲ የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ አሸንፈናል እያሉ ነው  😁🙌" 😳የሲቲ እና አንድ አንድ አርሰናል ጠል ለሆኑ ክለቦች የተወሠነ ነገር ላስታውሳቸው ወደድኩኝ በትናንቱ የቶትንሃም ሽንፈት ሲቲ በቃ ዋንጫውን በላው ለሚሉ የረሡትን ነገር ላሥታውሳቸው ተከተሉኝማ 👀👇 ↪️ባለፈው የውድድር ዘመን ኒውካስል ቶተንሃምን 6-1 በሆነ ሠፊ ውጤት ከጨዋታ ብልጫ ጋር አሸንፎት ቶትንሃም ከዚህ መራራ ሽንፈት ለማገገም ግዜ ሳይወሥድበት በሜዳው ማንችተር ሲቲን አሥተናግዶ ስፐርስ ማን ሲቲን 1-0 ማሸነፉን የሲቲ ደጋፊዎች እና አንድ አንድ አርሰናል ጠል የክለብ ደጋፊዎች ያለፈውን አመት ቢረሡትም ፔፔ ጋርዲዮላ እና የሲቲ ተጫዋቾች ግን መቼም አይረሡትም ↪️በዚህ ሲዝን  ኒውካስትል ቶተንሃምን 4-0 አሸንፏል ?????? 😳ባለፈው የውድድር አመት አርሰናል ቶተንሃምን 2-0 አሸንፎታል  ነገር ግን ስፐርስ አሁንም በአርሰናል ሽንፈት ሳይደናበር  ማን ሲቲ አሸንፏል 💁🏾‍♂️ 🤞በዚህ ሲዝን; አርሰናል ስፐርስን 3-2 አሸነፈ ?????? ✊ቼልሲ እና ሊቨርፑል ሁሌም የቶተንሃም ቅዠት እንደሆኑ ሁላችንም እናውቃለን መለስ ብላችሁ የቸልሲ እና የቶትንሃምን ያለፉ ጨዋታ ውጤቶችን መመልከት በቂ ነው ሊቨርፑልም ስፐርን በገጠመበት ጨዋታ ያን ያህል ሲቸገር አንመለከተውም ስለዚህ ቶተንሃም በቸልሲ አልያም በአርሰናል በተከታታይ መሸነፍ ከሲቲ ውጤት ጋር ምንም አይገናኝም በቸልሲ እና አርሠናል መሸነፍ ለእነሱ ትልቅ ነገር አይደለም። 😳ይህ ሲዝንም ካለፉት ሲዝኖች  ያን ያህል የተለየ አይደለም ቶትንሃም በአርሰናል ተሸነፈ በቸልሲ ተደገመ ስፐርሶች ሁሌም ለፔፔ ጋርዲዮላው ማንችስተር ሲቲ ቅዠት የሆነ ቡድን ስፐርስ ነው ቀልድ ሊመስላችሁ ይችላል አርሰናል ቀሪውን ጨዋታ የራሱን የቤት ሥራ በአግባቡ ይወጣ እንጂ ማንችስተር ሲቲ ነጥብ መጣሉ አይቀርም ሌላው ቢቀር  ማን ሲቲ በቶተንሃም ሆትስፐር ስታዲየም ሶን-ሄንግ-ሚን  በአንድ እግሩ ቢጫወት እንኳን ቶትንሃም ስታድየም ላይ ሲቲ ይሸነፋል 😂 🤳
Mostrar todo...
👍 13🔥 1
🇬🇬ቤን ዋይት - 26 ዓመቱ 🇩🇪Kai Havertz - 24 ዓመት 🇬🇬Declan Rice - 25 ዓመት 🇳🇴ካፒቴን ማርቲን Ødegaard - 25 አመቱ 🇧🇷ገብርኤል ማርቲኔሊ - 22 ዓመቱ 🇹🇯Jakub Kiwior - 24 Ars 🇬🇬ቡካዮ ሳካ - 22 ዓመት 🇫🇷ዊሊያም ሳሊባ - 22 ዓመቱ 🇧🇷Gabriel Magalhaes - 26 ዓመቱ 🇳🇱Jurrien Timber - 22 ዓመቱ 🇵🇹ፋቢዮ ቪዬራ - 23 ዓመቱ 🇬🇬ሪስ ኔልሰን - 24 ዓመቱ 🇬🇬ኤዲ ንከቲያ - 24 አመቱ 🇪🇸ዴቪድ ራያ (ከፈረመ) - 28 አመቱ 🇬🇬ስሚዝ ሮው 22 አመቱ 🇯🇵Takehiro Tomiyasu - 25 ዓመት 🇬🇬አሮን ራምስዴል (ከቆየ) - 25 ዓመቱ ✊ልምድ ጠገቦቹ 🇮🇪ጆርጂኒሆ 🇧🇷ገብርኤል ጂሰስ 🇹🇩ሊዮ ትሮሳርድ 🇬🇭 ቶማስ ፓርቴ 🇺🇦 ዚንቼንኮ ✊ልምድ ጠገቦቹን ትተን ከላይ ያሉት የአርሰናል የመጪው ዘመን የስኬት ቁልፎች እነዚህ ተጫዋቾች አሁንም በአርሰናል ቤት ቢያንስ 3 አመት የሚያቆያቸው ኮንትራት አላቸው።✍ ↪️ከዴቪድ ራያ በስተቀር እሡም ቢሆን ለበረኛ 28 አመት ገና ወጣር እንደሆነ ይቆጠራል ከዛ ውጪ ሁሉም ከ22-26 አመት እድሜ ክልል የሚገኙ ሮጠው ያልጠገቡ በክህሎት የዳበሩ እርሥ በእእሥ የሚተሳሰቡ እና የሚዋደዱ ተጫዋቾች ናቸው። ✍በዚህ በመጪው ክረምት ወጣቱ አለቃ ለሚመራቸው ወጣት ክዋክብቶቹ ከፊት መሥመር ላይ ሻርፕ የሆነ አጥቂ የዴክላን ራይስ አጣማሪ እና የሳካ ሁነኛ ቤንች የምናሥፈርም ከሆነ እዚህ እምቅ ሃይል እና ባለክህሎት ወጣት ሥብሥብ ላይ ጥቂት አዲስ ተጨማሪ ተጫዋች ብናመጣ ፣ 💪አርሰናል በቅርብ በእርግጠኝነት ፕሪሚየር ሊጉን (እና አውሮፓ ሻምፒዮንሥ ሊግን ) ለመቆጣጠር ማንም ሃይል አያግደውም ↪️አርሰናል በዚህ ስብሥብም ዘንድሮ ለሊጉ ዋንጫ እየተፋለመ ይገኛል ለዚህ ሥብሥብ ከፍተኛ ክብር እና ፍቅር ይገባቸዋል ❕ 💯 T R U S T T H E P R O C E S S💯
Mostrar todo...
10👍 5👏 2
🇧🇷ብራዚላዊው ኮከብ ጋብርኤል ጄሱስ ከአርሰናል ኦፊሻል ቲቪ ጋር አጭር ቆይታ አድርጎ ነበር ጋቢ በዛሬው ቃለመጠይቅ የተናገራቸው ዋና ዋና ነጥቦችን እናጋራችሁ 🗣ጋብሪኤል ጄሱስ በአርሰናል ቤት ደስተኛ ነው ፤ እናም ጄሱስ ለቦታው መፋለም እና በአርሰናል ቤት ተጨማሪ አመታትን መቆየት እንደሚፈልግ ተናግሯል ። 🗣ጋብሪኤል ጄሱስ ለአርሰናል ደጋፊዎች መልዕክት አስተላልፏል ! " እባካችሁ ደጋፊዎቻችን እኛን መደገፍ እና በእኛ ማመናችሁን ቀጥሉ ፤ አንዳንድ ጊዜ ነገሮች ባይሳካ እንኳን መደገፋችሁን ቀጥሉ ፤ ምክንያቱም እግርኳስ ውስጥ ማሸነፍ እና መሸነፍ ያጋጥማል። " እኛ እናንተን ለማስደሰት ጠንክረን እየሰራን ነው ፤ ዋንጫውን ለማሸነፍ እየታገልን እንገኛለን ፤ ያለፈው አመት አሳዛኝ ነበር ፤ በዚህ አመት ዋንጫውን ለማሸነፍ እንፋለማለን ፤ ዘንድሮ ባይሳካ እንኳን የሚቀጥለው አመት ለማሳካት እንሰራለን ፤ በጣም አስፈላጊው ነገር የናንተ ድጋፍ ከእኛ አለመለየቱ ነው።" ሲል ተናግሯል ። 🗣ጋብሪኤል ጄሰስ ስለ ካይ ሃቨርትዝ፡ “እዚህ ሁሉም ሰው ብቃት እና መጫወት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ያውቃል፣ እና ካይ ብቃት ያለው እና ጥሩ እየተጫወተ ሲሆን ጎሎችንም አስቆጥሯል። አሰልጣኙ በእሱ ያምናል እና ይህ ለተጫዋቹ  በጣም አስፈላጊ ነው መጀመሪያ ላይ ለእሱ ቀላል አልነበረም ነገር ግን ደግፈነዋል እና አሁን ፊቱ ላይ በፈገግታ እየተጫወተ ነው። 🗣ጋብሪኤል ጄሱስ ስለ ማርቲኔሊ 🗣“ጋቢ [ማርቲኔሊ] ገና 22 ዓመቱ ላይ የሚገኝ ተጫዋች ቢሆንም እድገቱ አሥገራሚ ነው ጋቢ በዚህ እድሜው አገሩን ወክሎ በአለም ዋንጫው በትልልቅ ደረጃዎች ተጫውቷል እናም ጠንክሮ እየሰራ እና አሁን ካለው ብቃት እየተሻለ እንደሚያሳይ  ተስፋ አደርጋለሁ። እሱ ማሽን ብለው ይቀላል ከኳስ ጋርም ያለ ኳስም ፈጣን ነው ከቡድን ጓደኞቹ ጋር ተናቦ መጫወት ተክኖበታል አሁን ያለበትን መንገድ እንደማይለውጥ ተስፋ አደርጋለሁ።" 🗣ገብርኤል ጄሱስ ስለ ሚኬል አርቴታ፡ 🗣“እሱ የትለየ ሰው ነው ኦህ ከቦስ ብዙ ነገር  ተምሬአለሁ ከእሱ ጋር ላለፉት ሰባት ዓመታት በላይ አውቀዋለሁ። ማንቸስተር ሲቲን ለቆ ከእኔ በፊት ወደ አርሰናል ሲመጣ ሶስት አመት የተለያየን ቢሆንም በእሱ ትልቅ እምነት ስላለኝ ዳግም አብረን አርሰናል ቤት አብረን እንገኛለን ከማይክል ብዙ ተወርተው የማያልቁ ጥሩ ትምህርቶችን ተምሬያለው።" 🗣“ከእሱ ጋር በሲቲ ቤት ለሶስት ሲዝኖች አብረን ነበርን  ከእኔ ጋር ብዙ ስራዎችን ሰርቷል፣ ከዚያም እዚህ መጣሁ። እሱ ያውቀኛል እኔም በደንብ አውቀዋለሁ። ከዚህ በፊት ብዙ ረድቶኛል እና አሁን እየረዳኝ ነው።" 🗣ገብርኤል ጄሱስ በአርሰናል ቤት ከሳካ ማርቲኔሊ ጋር ሥላለው ጥምረት 🗣 በራሱ፣ ቡካዮ ሳካ እና ገብርኤል ማርቲኔሊ መካከል ስላለው ኬሚስትሪ፡ 🗣“እንደ እድል ሆኖ በዚህ የውድድር ዘመን አንድ ላይ ብዙ ጨዋታዎች ላይ አልተጫወትንም፣  በዋናነት እኔ ያጋጠመኝ የተወሰነ የጉዳት ችግሮች እንዲሁም በተወሰነ መልኩ  ጋቢ አንዳንዴም እንዲሁ በጉዳት ምክንያት እንደ እንድል ሆኖ ብዙ ጨዋታዎች ላይ አልተጫወትንም።" 🗣"ያለፈው የውድድር ዘመን አብረን በርካታ ጨዋታዎች ላይ አንድ ላይ ተጫውተናል የሶስታችን ጥምረት እና ግንኙነቱ በጣም ጥሩ ነበር ያለፈው ሲዝን ብዙ ነገር ማሳካት ነበረብን እውነት ለዚህ ደጋፊ ብዙ ክብሮች ይገባቸዋል ይህንን  ባለማሳካታችን ሁሌም ይጸጽተኛል።" 🗣" አንድ ላይ ሥንሠለፍ በብዙ ነፃነት እና እንቅስቃሴ ተጫውተናል፤ ይህ ጥምረት ተመልሰን አብረን መጫወት እንደምንችል ተስፋ አደርጋለሁ ምክንያቱም ሜዳው ላይ ሶስታችንም በተለየ መልኩ እንግባባለን እንረዳዳለን ወደ ፊት ዳግም  የምንጣመርበት በርካታ ጨዋታዎች ይኖሩናል።"
Mostrar todo...
👏 4 3👍 2
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.