cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Heni Drawing &...

For any comment , suggestion & advice @withchrist

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
327
Suscriptores
Sin datos24 horas
-57 días
-930 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ደህና ነኝ! ሰላምታ ሲጠየቅ በተለምዶ ሁሉም ሰው መልሱ ደህና ነኝ ነው! እየከፋው፣ እያዘነ፣ ውስጡ ተጎድቶ፣ ለህይወት ትርጉም አጥቶ፣ ዲፕሬሽን ውስጥ ሆኖ፣ 'ደህና ነህ?' ስንለው ወግ ነውና 'ደህና ነኝ!' ይላል! እያለቀሰ ብታገኘው 'ደህና ነኝ' ይልሀል! ቆዝሞ ብታገኘው 'ደህና ነኝ!' ይልሀል... ስንት የምናቃቸው ወጣቶች ዛሬ ሰላምታ ስንሰጣቸው 'ደህና ነኝ!' ብለውን.. በንጋታው ራሳቸውን አጥፍተዋል! ስንቱ ለቅሶ ላይ ተገኝተን... ትላንትኮ፣ የዛሬ ሳምንትኮ፣ የዛሬ ወር ኮ አጊኝቼው... 'ደህና ነኝ!' ብሎኝ ነበር... ምነው ለዚህ ውሳኔ ያበቃውን ባማከረኝ ብለን አልቅሰናል ስንቱ ጠዋት 'ደህና ነኝ!' ብሎን ከሰዓት ራሱን አጠፋ ተብለናል! ምክንያቱም እንዴት ነህ? ለሚለው የለመድነው፣ ያደግነው፣ 'ደህና ነኝ!' እያልን ነው! መርምሮ፣ ቀርቦ፣ ያለንበትን ሁኔታ ተረድቶ፣ አጥብቆ ካልጠየቀን 'ደህና ነህ?' ለሚለው መልሱ የቱን ያህል ቢከፋን፣ ብናዝን፣ መልሱ ደህና ነኝ ነው! እስኪ ራሳችንን እንጠይቅ?! ስንቱ ደህና አለመሆኑን እያወቅን.. 'ደህና ነኝ!' ስላለ ብቻ አልፈነዋል ስንቱ ራሱን ሊያጠፋ በኪሱ መርዝ፣ ገመድ ይዞ 'ደህና ነኝ!' የሚል ቃል እያወጣ ደህና አለመሆኑ ሁኔታው እያሳበቀ አልፈነው የሞቱን ዜና ሰምተናል? ደህና ነኝ! ያለ ሁሉ ደህና ነው? ደህና ነኝ! የሚል ቃልስ ደህንነትን ይገልፃል? ስለዚህ ምናልባት ደህና ነኝ! ከሚለው ቃል ጀርባ ያለውን ህመም ተረድተን ወይም ገምተን ደህና መሆኑን አጥበቀን ብንጠይቀው..... ደህና አለመሆኑን ነግሮን... ምናልባት ላለበት ችግር መፍትሔ ማስቀመጥ ችለን ካለበት ዲፕሬሽን ወይም ራስ የማጥፋት ስሜት እንታደገው ይሆናል ኮ! እስኪ እንጠይቅ ስንቱ ሀሳቡን፣ ጭንቀቱን፣ የሚያካፍለው አቶ ደህና ነኝ! እያለ አተነዋል? ምናልባት ቤታችን ውስጥ አንድ ጣሪያ ስር እየኖርን ቀርቦ ባለመጠየቁ፣ አይዞህ ያልፋል ባለመባሉ ከባድ ጊዜን ብቻውን እያሳለፈ ነው? ከጊዜ በኋላ ወይ በሽታ ላይ ወይ ሞት ወስዶብናል? ብዙ ባለማውራታችን፣ ባለመወያየታችን፣ ባለመጠየቃችን፣ ባለመረዳታችን በአከባቢያችን ያለን ሰው እያጣን ነው? አሁን እየተበራከተ የመጣው የወጣቶች ሱሳይድ ቀርቦ የሚጠይቃቸው አተው፣ ችግራቸው የሚያዋዩት አተው 'ደህና ነህ?' 'ደህና ነኝ!' በሚል ቃል እያለፍናቸው በጣም ከተጎዱ በኋላ ያኔ ባወራሁት ብለናል! በተለይ ጉዳታቸውን፣ ስሜታቸውን፣ ስብራታቸውን ለሰው ማዋየት ልምድ እንደሌላቸው የምናውቃቸው ምናልባት የቤተሰባችን አካልም ሊሆን ይችላል እሱ/ሷ እንደዛ ነው! እንደዛ ናት! ማውራት አትወድም፣ አይወድም ብለን አንለፋቸው! የሰው ልጅ በተፈጥሮ መፍትሔ ማግኘት ባይችል እንኳ ችግሩን በአፅኖት የሚያዳምጠው ካገኘ ይቀለዋል ማውራት በራሱ የመፍትሔው 50% ነውና! Via: Rediet Aseffa እናም ወዳጆቼ... 😭 እስቲ እንፈላለግ ፣ እንቀራረብ ፣ እንጠያየቅ ፣ እንነጋገር ፣ እንደማመጥ ፣ እንወያይ ፣ አለሁልህ ፤ አለሁልሽ ፣ አይዞህ እንባባል... ከሁሉ አጥብቀን ደግሞ ስለ ሌላው እንንበርከክ ፤ እንፀልይ ። “ሰው ከሞት ወጥመድ ያመልጥ ዘንድ የጠቢብ ሰው ትምህርት የሕይወት ምንጭ ነው።”   — ምሳሌ 13፥14 😭let's talk @withchrist @henokdrawing
Mostrar todo...
1
ደህና ነኝ! ሰላምታ ሲጠየቅ በተለምዶ ሁሉም ሰው መልሱ ደህና ነኝ ነው! እየከፋው፣ እያዘነ፣ ውስጡ ተጎድቶ፣ ለህይወት ትርጉም አጥቶ፣ ዲፕሬሽን ውስጥ ሆኖ፣ 'ደህና ነህ?' ስንለው ወግ ነውና 'ደህና ነኝ!' ይላል! እያለቀሰ ብታገኘው 'ደህና ነኝ' ይልሀል! ቆዝሞ ብታገኘው 'ደህና ነኝ!' ይልሀል... ስንት የምናቃቸው ወጣቶች ዛሬ ሰላምታ ስንሰጣቸው 'ደህና ነኝ!' ብለውን.. በንጋታው ራሳቸውን አጥፍተዋል! ስንቱ ለቅሶ ላይ ተገኝተን... ትላንትኮ፣ የዛሬ ሳምንትኮ፣ የዛሬ ወር ኮ አጊኝቼው... 'ደህና ነኝ!' ብሎኝ ነበር... ምነው ለዚህ ውሳኔ ያበቃውን ባማከረኝ ብለን አልቅሰናል ስንቱ ጠዋት 'ደህና ነኝ!' ብሎን ከሰዓት ራሱን አጠፋ ተብለናል! ምክንያቱም እንዴት ነህ? ለሚለው የለመድነው፣ ያደግነው፣ 'ደህና ነኝ!' እያልን ነው! መርምሮ፣ ቀርቦ፣ ያለንበትን ሁኔታ ተረድቶ፣ አጥብቆ ካልጠየቀን 'ደህና ነህ?' ለሚለው መልሱ የቱን ያህል ቢከፋን፣ ብናዝን፣ መልሱ ደህና ነኝ ነው! እስኪ ራሳችንን እንጠይቅ?! ስንቱ ደህና አለመሆኑን እያወቅን.. 'ደህና ነኝ!' ስላለ ብቻ አልፈነዋል ስንቱ ራሱን ሊያጠፋ በኪሱ መርዝ፣ ገመድ ይዞ 'ደህና ነኝ!' የሚል ቃል እያወጣ ደህና አለመሆኑ ሁኔታው እያሳበቀ አልፈነው የሞቱን ዜና ሰምተናል? ደህና ነኝ! ያለ ሁሉ ደህና ነው? ደህና ነኝ! የሚል ቃልስ ደህንነትን ይገልፃል? ስለዚህ ምናልባት ደህና ነኝ! ከሚለው ቃል ጀርባ ያለውን ህመም ተረድተን ወይም ገምተን ደህና መሆኑን አጥበቀን ብንጠይቀው..... ደህና አለመሆኑን ነግሮን... ምናልባት ላለበት ችግር መፍትሔ ማስቀመጥ ችለን ካለበት ዲፕሬሽን ወይም ራስ የማጥፋት ስሜት እንታደገው ይሆናል ኮ! እስኪ እንጠይቅ ስንቱ ሀሳቡን፣ ጭንቀቱን፣ የሚያካፍለው አቶ ደህና ነኝ! እያለ አተነዋል? ምናልባት ቤታችን ውስጥ አንድ ጣሪያ ስር እየኖርን ቀርቦ ባለመጠየቁ፣ አይዞህ ያልፋል ባለመባሉ ከባድ ጊዜን ብቻውን እያሳለፈ ነው? ከጊዜ በኋላ ወይ በሽታ ላይ ወይ ሞት ወስዶብናል? ብዙ ባለማውራታችን፣ ባለመወያየታችን፣ ባለመጠየቃችን፣ ባለመረዳታችን በአከባቢያችን ያለን ሰው እያጣን ነው? አሁን እየተበራከተ የመጣው የወጣቶች ሱሳይድ ቀርቦ የሚጠይቃቸው አተው፣ ችግራቸው የሚያዋዩት አተው 'ደህና ነህ?' 'ደህና ነኝ!' በሚል ቃል እያለፍናቸው በጣም ከተጎዱ በኋላ ያኔ ባወራሁት ብለናል! በተለይ ጉዳታቸውን፣ ስሜታቸውን፣ ስብራታቸውን ለሰው ማዋየት ልምድ እንደሌላቸው የምናውቃቸው ምናልባት የቤተሰባችን አካልም ሊሆን ይችላል እሱ/ሷ እንደዛ ነው! እንደዛ ናት! ማውራት አትወድም፣ አይወድም ብለን አንለፋቸው! የሰው ልጅ በተፈጥሮ መፍትሔ ማግኘት ባይችል እንኳ ችግሩን በአፅኖት የሚያዳምጠው ካገኘ ይቀለዋል ማውራት በራሱ የመፍትሔው 50% ነውና! Via: Rediet Aseffa እናም ወዳጆቼ... 😭 እስቲ እንፈላለግ ፣ እንቀራረብ ፣ እንጠያየቅ ፣ እንነጋገር ፣ እንደማመጥ ፣ እንወያይ ፣ አለሁልህ ፤ አለሁልሽ ፣ አይዞህ እንባባል... ከሁሉ አጥብቀን ደግሞ ስለ ሌላው እንንበርከክ ፤ እንፀልይ ። 😭let's talk @withchrist @henokdrawing
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
New drawing of Michael B. Jordan😎🔥 @habteshsketch @habteshsketch
Mostrar todo...
3
00:24
Video unavailableShow in Telegram
Mostrar todo...
8.51 MB
2
Photo unavailableShow in Telegram
Mostrar todo...
2
Photo unavailableShow in Telegram
The final result...🤌 Commissioned work Order yours... @withchrist @henokdrawing
Mostrar todo...
5👍 2
Progress of new ordered drawing... A4 size Order yours @withchrist @henokdrawing
Mostrar todo...
👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
The cock😁 አውራ ዶሮው🐓 Happy new year.🌻 2016 Ethiopian calendar “እስካረጅም እስክሸመግልም ድረስ፥ ለሚመጣ ትውልድም ሁሉ ክንድህን ኃይልህንም ጽድቅህንም እስክነግር ድረስ፥ አቤቱ፥ አትተወኝ።”   — መዝሙር 71፥18 “Now also when I am old and grayheaded, O God, forsake me not; until I have shewed thy strength unto this generation, and thy power to every one that is to come.”   — Psalms 71:18 (KJV) ከኖርን ፤ በህይወታችን አዲስ ዓመት ከተጨመረ አይቀር...ለተፈጠርንበት ዓላማ መኖር ይሁንልን።🙌 @withchrist 📷 @henokdrawing
Mostrar todo...
3👍 1
Someone asked me if it is possible to draw a photo with a filter without the filter... And here is the final result🤌 Order yours... @withchrist @henokdrawing
Mostrar todo...
👏 9 2
Photo unavailableShow in Telegram
Hey family... Sorry for disappearing... i was on my final exam but now I'm back... So you can order drawings for you , for your family , friends ...and for your beloved one... And also if it is your will...follow me on Instagram(@henok_tesfaye20) and tiktok(@henok.tesfaye) @withchrist @henokdrawing
Mostrar todo...
👍 1
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.