cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Tsegaye R Ararssa

TA

Mostrar más
Finlandia314El idioma no está especificadoPolítica3 596
Publicaciones publicitarias
16 523
Suscriptores
-224 horas
-517 días
-23130 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

በብሔራዊ ውይይት ኮሚሽን ውስጥ የተቀመጡት ኮሚሽነሮች፣ አንዳንዶቹን ከፍ አድርገን የያዝናቸው፣ እነዚህን እውነታዎች ማጤን አለባቸው። በጠ/ሚንስትር አብይ እንደተቋቋሙት ኮሚሽኖች በጥቂት ወራት ውስጥ ካልተበተነ ኮሚሽናቸው፦ ሀ) አገዛዙ ሊጋፈጣቸው የማይፈልጋቸው ጥያቄዎች ሁሉ የማያልቁ እና ቆራጥ ውሳኔ የማይሰጡበት የወሬ መደብር (talking shop) አይነት የውይይት መድረክ መሆን ወይም፣ (ለ) ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የስልጣን ማጠናከሪያ (power consolidation) መሳሪያ ይሆናል። በዚህ ሂደት ውስጥ ምንም አይነት ውጤት ቢመጣ፣ የናንተ ትሩፋት ግን በስልጣን ላይ ያለው አካል ስልጣኑን ለማጠናከር እንዲረዳው እና በሂደቱም ወደ ሰላምና ዲሞክራሲ ለሚደረገው ሽግግር ዉድቀት ትልቅ አስተዋፅኦ ማድረግ ብቻ ይሆናል። ኮሚሽነሮቹ ለትጥቅ ትግል ተሳታፊዎች በቅርቡ ባደረጉት ጥሪ ደህንነት ዋስትና ሲሰጡም በመገረም ተመልክተናል። ከአክብሮት ጋር፣ የገለልተኛነት ምልክት ካሳዩ ኮሚሽነሮቹ የሌላዉን ይቅርና የራሳቸውን ደህንነት ማረጋገጥ አይችሉም። ለዚህ ደግሞ በቅርቡ ሃሳባቸውን ለመግለፅ የሞከሩት የአገዛዙ ባለስልጣናት እጣ ፈንታ የመጨረሻው የማንቂያ ደወል መሆን ነበረበት። በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የብልፅግና ዋና ስልታዊ ጥቅም ከBretton Woods እና ሰፊው ምዕራብ ሐገራት ጦርነቱን ለማስቀጠል እርዳታ ማግኘት ነዉ። ብዙ ጊዜ ውድ የሆኑ የግብይት ስምምነቶችን ከተባበሩት አረብ ኤሚሬት፣ ቻይና፣ ቱርክ እና ኢራን ጋር የሚያደርገው አገዛዙ ፈጣን የጦር መሳሪያ ግዢ ለማድረግ እና ጊዜያዊ ችግሩን ለመቅረፍ ስለሚረዳው ይሆናል። አገዛዙ ግን በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ የተንሰራፋውን መዋቅራዊ ችግር ያለ ምዕራባውያን የዋስትና ገንዘብ መቅረፍ እንደማይቻል ተገንዝቧል። ውጤታማ በሆነ መንገድ ጥቅም ላይ ከዋለ፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ትርጉም ያለው ተፅእኖ አለው። ለአጭር ጊዜ ስልታዊ የፖለቲካ ጥቅም ሲባል አስፈላጊ የፖለቲካ መግባባት እና ተገቢ ተጠያቂነትን መተው የለበትም። ይህ ከሆነ፣ ከምዕራባውያን የተገኘው ገንዘብ የእርስ በርስ ጦርነቶችን ለመደገፍ የሚያስችል ኢኮኖሚ ለመደገፍ ይጠቅማል። የምዕራባውያኑ ዋስትና መድህን ገንዘብ በአብይ ከንቱ ፓርክ ፕሮጀክቶች የህዝብን (ከተማ ነዋሪዎችን) ትኩረት ለመቀየር የሚረዱትን ምግባሮች ለመግዛት ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ። ነገር ግን በወሳኝ ሁኔታ ፖለቲካውን መድረሻ ወደሌለው ገደል የሚያስገቡና ለዘር ማጥፋት ጀብዱዎች የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋሉ። ምዕራባውያን አቅማቸውን በብቃት ካልተጠቀሙበት እና በዋናነት በዩክሬን እና በጋዛ መዋዕለ ንዋያቸውን ማፍሰሳቸው ከቀጠለ፣ በተመሳሳይ ችግር ውስጥ በሚገኙት የአፍሪካ ቀንድ እና ቀይ ባህር ኮሪደር ውስጥ እጅግ በጣም ብዙ ህዝብ ያላት ሀገር ቀስ በቀስ ትፈርሳለች። የኦነግ-ኦነሰ ከፍተኛ እዝ ግንቦት 7፣ 2024
Mostrar todo...
የጠ/ሚኒስትር አብይ የግጭት አፈታት ፍኖተ ካርታ፤ ብሔራዊ ውይይት፣ የሽግግር ፍትህ ምክክር እና ትጥቅ አስፈትቶ ወደ ህብረተሰቡ መመለስ እንዲሁም መልሶ ማቋቋም (DDR) – የኦነግ-ኦነሰ መግለጫ ** በኦሮሚያ ላይ አምስት አመታትን ካስቆጠረዉ ጦርነት በኋላ፣ ከፕሪቶሪያው ድርድር አስራ ስምንት ወራት በኋላ እናም ለአንድ አመት ከዘለቀዉ የአማራ ክልል ግጭት በኋላ፣ ቀስ በቀስ ብሔራዊ ውይይት፣ የሽግግር ፍትሕ እና ትጥቅ ማስፈታት፣ ወደ ህብረተሰቡ መመለስና መልሶ ማቋቋም (DDR) የብልጽግና ፓርቲ ሶስትዮሽ የግጭት አፈታት ንድፍ ሆኖ ብቅ ብሏል። ከ2021 መገባደጃ ጀምሮ ውይይትን የሚያመቻች እና የሚጠራ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተቋቁሟል። የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ በፍትህ ሚኒስቴር ተዘጋጅቷል። የ‘ትጥቅ ማስፈታት፣ ወደ ህብረተሰቡ መመለስና መልሶ ማቋቋም ሂደቶችን የሚከታተል የብሔራዊ መልሶ ማቋቋም ኮሚሽን ተቋቁሟል። ይህን የብልጽግና የግጭት አፈታት ንድፍ በጨረፍታ ብቻ በማየት የምንረዳው የብሔራዊ ዉይይቱ ግጭቶችን ለመፍታት ሳይሆን አፈታታቸዉን አድበስብሶ ለማለፍ መሆኑን ፣ የሽግግር ፍትህ ተብዬው ያለ የሽግግር ስርዓት በሁሉም የሰብአዊ መብት ተሟጋች አካላት ከሞላ ጎደል እንደተዘገበው በአብዛኛዎቹ የፖለቲካ ወንጀሎች ዋና ወንጀለኛ ለሆነዉ ቡድን ያለመከሰስ መብትን ለማረጋገጥ የቀረበ ገፀበረከት ብቻ መሆኑን እና በመጀመሪያ ለጠመንጃ ማንሳት ምክንያት የሆኑ የፖለቲካ ጥያቄዎችን ለመፍታት ምንም ፍንጭ በሌለበት ትጥቅ ማስፈታት፣ ወደ ህብረተሰቡ መመለስና መልሶ ማቋቋም ፍቱን መድሃኒት ተደርጎ እየተወደሰ መሆኑን ነው። ውይይትን እና ፍትህን የሚያሞካሹ በቀለማት ያሸበረቁ ባዶ ቃላትን የያዘው የአብይን ፍኖተ ካርታ ሃገሪቱ እና እውነተኛ ወዳጆቿ በአንክሮት ሊያዩት ይገባቸዋል። ሆኖም አንዳንድ የሐገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ተዋናዮች በግርግር እና/ወይም በግዴለሽነት ደመና የተሸፈኑ ይመስላሉ፣ ይህም ብዥታ ምናልባትም በአገዛዙ የውይይት እና የፍትህ ንግግሮች ውስጥ ለሚፈጠሩት ተቃርኖዎች እና ውጤታቸው ግድየለሾች ስለሆኑ ሊሆን ይችላል። በእርግጠኝነት፣ ሁሉም አይነት ተቃርኖዎች በብልፅግና ኢትዮጵያ የአገዛዝ ዘመን የተለዩ አይደሉም፣ ቋሚ ደንብም ናቸው። እነዚህም ደንቦች አገዛዙን በከፊል አጽንተው አቆይተውታል። በሃሳብ አቀራረቡም ሆነ በአተገባበሩ በብሔራዊ ውይይቱ ላይ ሁለት ተቃራኒ ሃሳቦች እየተነሱ ነው። በአንድ በኩል ገዢው አካል በመሰረታዊ ጥያቄዎች ላይ ማለትም በመንግስታዊ ተቋማት፣ በመንግስታዊ መዋቅር፣ እና በፖለቲካውም ዙሪያ ስላለፈው እና ስለ ወደፊቱ ሐገራዊ ውይይት እንደሚያስፈልግ ይደግፋል። አጠያያቂ የሆነዉ ጉዳይ ግን ገዢው ፓርቲ ለስልጣን የተመረጥኩት በህጋዊ የመንግስት ተቋማት በተደራጀና ህጋዊ የአሰራር ሂደትን ተከትሎም ነው ይላል። የኋለኛው ካለ፣ ቀድም ብሎ ያስፈልጋል የተባለው አግባብነት የለውም። የነባር ተቋማትን ህጋዊነት ካልተጠራጠርክ እንደገና ህጋዊ ተቋማትን ለመፍጠር ለምን ሀገራዊ ውይይት ላይ ኢንቨስት ማድረግ አስፈለገ? ወጥነት ስለሌለው፣ ውይይቱ መሠረታዊ የመንግስት ተቋማትን ያጠቃልላል፥ ብሔራዊ ውይይቱም ያሉትን ተቋማት ያጠናክራል የሚለውን አባባል አገዛዙ ሊክድ ይችላል። ነገር ግን ውይይቱ ወሳኝ የሆኑ መንግስታዊ ተቋማትን ምርጫን ህጋዊ የሚያደርጉትን ጨምሮ እንደገና ማጤንን እንደሚያጠቃልል የሚያከራክር ከሆነ ውይይቱ በፍፁም ተራ ጉዳዮች ዙሪያ ላይ ይሆናል ማለት ነው። እንዲሁም ቢያንስ በመርህ ደረጃ፣ ለብሔራዊ ውይይት የሚቀርቡ ጉዳዮችን መወሰን ያለበት የገዢው አካልም አይደለም። ከዚህም በላይ፣ እንዲሁ ሕጋዊ የመንግሥት ተቋማት መኖራቸውንና የ2021 ምርጫን በበላይነት መምራታቸውን ብንቀበል እንኳን መንግሥት የፌዴሬሽኑ አካል በሆኑት ሶስት ክልሎች ውስጥ በሚያካሂደዉ ጦርነቶች ምክንያት ህጋዊነቱ ከፍተኛ ጥያቄ ውስጥ ያስገባዋል። እራሱ በሚያቀርባቸው ተፃራሪ ሃሳቦች፣ ገዢው አካል ሚዛኑን እየለቀቀም ለሽግግር አስተዳደር የታቀዱ ፅንሰሀሳቦችን እና ሂደቶችን እያሰናከለም ይገኛል። ብሄራዊ ውይይት እና የሽግግር ፍትህ በቲዎሪም ሆነ በተግባር የሚሠሩት ከሽግግር አስተዳደር አደረጃጀት አንፃር እንጂ ህዝባዊ ንቅናቄን በጠለፈና የአንድ ፓርቲ አገዛዝን ብቻ የሚያቀነቅንና የሚያራምድ አገዛዝ ውስጥ አይደለም። እነዚህ ጽንሰ-ሀሳቦች እና ሂደቶች የሽግግር አስተዳደር በሌለበት ጊዜ ገዢው አካል ስልጣኑን ለማጠናከር ብቻ ጥቅም ላይ ይውላሉ። እንደዚያም ሆኖ የብልፅግና ብሔራዊ ውይይት ቁልፍ የሆኑ ባለድርሻ አካላት መካከል አስፈላጊውን የፖለቲካ ድርድር ሳይደረግ የተነደፈም ነው። አገራዊ ውይይቶች ማለት ከተለመደዉ የፖለቲካ እና የወታደራዊ ልሂቃንም በላይ ተሳትፎን ለማስፋት እንጂ መሳተፍ የሚገባቸውን ልሂቃን ወደ ጎን ለመግፋት አይደለም። የውይይት ኮሚሽኑም ሆነ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲዉ የተቀረጸዉ ከሽግግር አስተዳደር ውጭ በአንድ የፖለቲካ ፓርቲና ሁሉንም ቁልፍ ባለድርሻ አካላት ያገለለ ሂደት ነዉ። ከታች ወደ ላይ ያለዉን ተሳትፎም የሚቆጣጠረዉ አንድ ፓርቲ ማለትም ገዢው ፓርቲ ነዉ። ምናልባት ውይይቱ ውጤት ቢያፈራም ይኸውም አሁን ባለው ሂደት ላይ የተመርኮዘና በቅድሚያ የተወሰኑ ውሳኔዎች በመሆናቸው የኮሚሽኑ ምክሮች ተግባራዊ ለማድረግም ሆነ ላለማድረግ ለራሱ ለብልፅግና ፓርቲ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ገለልተኛ ለማስመሰል እንኳን ኮሚሽኑ አፈጻጸምን ለማረጋገጥ ሕጋዊ ሥልጣን አልተሰጠውም፣ የአፈጻጸም ጉዳዮችን በሚመለከት ኮሚሽኑ ከመጣበት ሂደት አንፃር አስፈላጊም አይደሉም። ቁልፍ የሆኑ ባለድርሻ አካላት ሂደቱ ዉስጥ አለመካተታቸውም ኮሚሽኑ ከህግ ማዕቀፍ ውጭ የሆኑ ተጨማሪ ዘዴዎችም የሉትም ማለት ነው። በምድሪቱ ውስጥ ካሉት አስጨናቂ የፀጥታ እና የፖለቲካ ፈተናዎች አንፃር አሁን ያለው ንድፍ በቀላሉ መንደርደሪያ እንኳን ሊሆን የማይችል ነዉ። የግጭት አፈታትን በትክክል ለመተግበር ተፈልጎ ቢሆን ኖሮ፣ ውይይቱ የመጀመሪያው አጀንዳ በተፋላሚ ወገኖች እና ቁልፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ሆኖ፣ ከዚያ በኋላ የሕዝብን ተሳትፎ ለማረጋገጥ ሰፋ በማድረግ ህዝብን ማሳተፍም በተቻለ ነበር። የህዝባችንን የወደፊት ተስፋ ለመንደፍ ዝርዝር ውይይቶች ቢቀጥሉም፣ ቢያንስ ቢያንስ ትርጉም ያለው ሐገራዊ ውይይት ለማድረግና የሽግግርን ፍትህ ለማስፈን በሚከተለሉት ነጥቦች መጀመር ይገባዋል። 1. የተዘጋውን የፖለቲካ ምህዳር መክፈት ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልን የመረጡ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች በትንሽ እና ትልቅ ከተማዎች በጥይት ሲገደሉ፣ በአገራዊ ውይይት ታሳቢ በሆኑት በትውልዶች መካከል ያሉ ጉዳዮች ይቅርና በየትኛውም ጉዳይ ላይ መነጋገር ሊኖር እንደማይችል ግልጽ ነው። እንደውም ስልጣን በያዘ ጥቂት ወራት ዉስጥ ልክ የሀገሪቱን የደህንነት እና የስለላ መዋቅር በአንፃራዊነት መቆጣጠር በጀመረበት ግዜ ነበር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቄሮ እንቅስቃሴ፣ በኦሮሞ ነጻነት ግንባር፣ በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አባላት እና የኦሮሞ ህዝብ ዋና ዋና ጥያቄዎችን የተገነዘቡ አካላት የፓርቲያቸው አባላት ላይ ጭምር ከባድ እርምጃ መውሰድ የጀመረው። እርምጃው ከዛ በኋላ ወደ ትግራይ እና አማራ ክልሎች በተከታታይ ተስፋፍቷል።
Mostrar todo...
በኦሮሚያ ብቻ ባለፉት አምስት አመታት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞች በተለያዩ ማጎሪያ (ማሰቃያ) ካምፖች እና ጊዜያዊ እስር ቤቶች ታስረዋል። ከኦነግ እና ኦፌኮ አመራር ጋር እነዚህ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞች አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ። ይኼ ለእነሱ አይገባም ነበር። በነፃ መፈታት አለባቸው። የሕግ ማሻሻያዎቹ የፖለቲካ ምህዳሩን ከመክፈት ሂደት አካል መሆን አለበት፣ ከእነዚህም መካከል የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ። ማንኛውም ነጻ የሆነ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ታዛቢ በኢትዮጵያ ውስጥ የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጎች ስለ ሽብርተኝነት ወይም ሁከት ፈፅሞ እንደዳልነበረ ይገነዘባል። ሕጉ ሁሌም የተደራጁ ተቃዋሚዎችን እና የተቃውሞ ድምፆችን ዝም ለማሰኘት የሚያገለግል የአፈና መሳሪያ ነው። የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማጥበብ በቀጥታ የተዘጋጀ ነው። ግንቦት 2021 ብልፅግና የእርስ በርስ ጦርነቱ በድርድር እንዲቆም አለማቀፋዊ ጫና እንዳይፈጠር በማሰብ ህወሓትን እና ኦነግ-ኦነሰን በሽብርተኝነት ለመፈረጅ በፍጥነት ወደ ፓርላማ አቅርቧል። አዋጁ የታወጀዉ እውነተኛ ውይይትን ለማጨለም ነበር። 2. በመላ ሐገሪቱ እውነተኛ ፖለቲካዊ መግባባት ላይ መድረስ ዋናው የግዛቲቱ የፖለቲካ ፉክክር መድረክ የጦር አውድማ በሆነበት ወቅት በሐገሪቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ዉስጥ ምን አይነት ውይይት ነዉ የሚደረገው? ወጣትና በእድሜ የገፉ ለሰላማዊ ትግል ፍላጎት የነበራቸው ፍትህን እንዳያገኙና ውይይትም እንዳይደረግ አውቆ በማሳጣቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽን ትተው ወደ ጫካ ትግል እየተመሙ ባለበት ግዜ ምን አይነት የፖለቲካ ውይይት ነው ኢትዮጵያ የምታካሂደው? አሰቃቂና ጭካኔን የተካኑ ወንጀሎችን በመፈልፈል የምታወቁትን የእርስ በርስ ጦርነቶችን እያባባሱ የሽግግር ፍትህ ሂደቱ የሚዘጋው የትኛውን የጭካኔ እና የወንጀል ምዕራፍን ነው? የነዚህ ሁሉ ጥያቄዎች መልስ የጠ/ሚ አብይን ኢትዮጵያ ወለፈንዲ መራር ቀልዶች እያስጋተ ቀጥሏል። በቅርብ ጊዜ ዉስጥ በትግራይ ክልል አንፃራዊ እፎይታ የታየ ቢሆንም ሀገሪቱ በዉስብስብ እና ስር የሰደደ ግጭቶችን እያስተናገደችም፣ የአየር ላይ ጥቃቶች በምዕራብ (ወለጋ አከባቢዎች)፣ በደቡብ (ጉጂ አካባቢ)፣ በማዕከላዊ (ሰሜን እና ምዕራብ ሸዋ) እና በሰሜን (የአማራ ክልል አራት ዞኖች) እየማቀቀች ትገኛለች። በኦሮሚያ ላይ በኦሮሞ ህዝብ ልብ እና አእምሮ ላይ የከፈተዉን ጦርነት ማሸነፍ ባለመቻሉ አገዛዙ እቅዴን ያሳኩልኛል ብሎ ያሰበውን የተለያዩ ስልቶችን እንደ ሚድያ ላይ ፕሮፓጋንዳ፣ በሰው አልባ አውሮፕላኖች ሕዝብ ላይ ቦምብ በማዝነብ እና የሰው ማዕበል እየተጠቀመ ይገኛል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ወታደሮቹን እና የአካባቢውን ካድሬዎች በማስተባበር የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የቤተሰብ አባላት፣ አባቶች እና እናቶች፣ እና የተቃውሞ እንቅስቃሴ ደጋፊዎች ናቸው ብሎ የጠረጠራቸዉን ወገኖች የጤና ጥበቃ ተቋማትን፣ ሆስፒታሎችን፣ ት/ቤቶችን ፣ ፍርድ ቤቶችን፣ እና ማናቸዉም የማህበረሰባዊ አገልግሎቶችን የመቃብር ቦታዎችን ጨምሮ ለሞቱ የቤተሰብ አባላት እንዳይጠቀሙ እየከለከለ ይገኛል። መሬት ላይ ያለው እውነታ የፌደራል መንግስት እና የክልል ልዩ ሃይል አዳዲስ ወታደሮችን እየመለመለ እና እያሰለጠነ ይገኛል። ይህ መቀየር አለበት። በመላ አገሪቱ ትርጉም ያለው ፖለቲካዊ መግባባት ላይ መድረስ ለማንኛውም ውይይት ወይም ፍትህ (የሽግግር ፍትህ) አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ ነው። እዉነተኛ ፖለቲካዊ መግባባቶች በመላው ሐገሪቱ መስፈን አለባቸው። እውነተኛ የፖለቲካ ድርድር ማለት ትጥቅ ማስፈታት፣ ወደ ህብረተሰቡ መመለስና መልሶ ማቋቋም (DDR) አይደለም። በተለይ ትጥቅ ማስፈታት፣ ወደ ህብረተሰቡ መመለስና መልሶ ማቋቋም ላይ ብቻ በማተኮር ነገር ግን ስለ መሰረታዊ የፖለቲካ ጥያቄዎች ሳያነሳ መቆየቱ አገዛዙ ከግጭት በኋላ ህይወትና ሰላማዊ ኑሮ የሚያብብበት ማህበረሰብ ለመፍጠር ፍፁም ፍላጎት እንደሌለው ማሳያ ነው። ይልቁንም አቋሙ ሐገሪቱን ከራሷ ጋር በማጋጨት የሐገሪቱን የተበታተነ ሃብት በማሰባሰብ ስልጣኑን ማጠናከር ነው። የፖለቲካ መግባባቱም አገሪቷን በሙሉ ያቀፉ መሆን አለባቸው። በእኛ እምነት ትግራይም የፖለቲካ መግባባት ያስፈልገዋል። በጥይት መግደልን ማስቆም የተቻለውን ያህል፣ CoHA የጦርነት ማቋረጥ ስምምነት ብቻ እንጂ አጠቃላይ የሰላም ስምምነት አልነበረም። ሆኖም በአሁኑ ወቅት፣ ሁሉም መረጃዎች እንደሚያሳዩት የኢትዮጵያ መንግሥት እውነተኛ የፖለቲካ መግባባት ፍላጎት እንዳለው ያሳያል። ይህም ማለት የተቃውሞው ትግል፣ ትውልድ አምባገነንነትን መታገል እና የሀገሪቱን እና የአከባቢውን የወደፊት እጣ ፈንታ የመቅረጽ ከባድ ሃላፊነት አለበት። 3. ሁሉን አቀፍ ሂደት ገለልተኛ ኮሚሽን (ኮሚሽኖች) መመስረት- ተቀባይነቱ በሁሉም ዋና ባለድርሻ እካላት መሆን ውይይት ሰብሳቢዎችና አስተባባሪዎች በሂደት ወደ ፊት መምጣት አለባቸው፣ ይህም ዋና ባለድርሻ አካላትን በማያገል ሂደት መሆን አለበት። ከላይ የተጠቀሱት በሌሉበት፣ የጠ/ሚኒስትር አብይ ሐገራዊ ውይይት እና የሽግግር ፍትሃዊነት ወገንተኛ አላማዎችን ብቻ ያሳካል። በአገር ውስጥ ውይይቱ ለአማራ እና ኢትዮጵያዊነት ካምፕ ሕገ-መንግሥት ለማሻሻል ነዉ በሚል መልኩ ይንጸባረቃል። በብልጽግና ፓርቲ ውስጥ የተከሰተው የውስጥ ልዩነቶች እና ቅራኔዎች ወደ ደጋፊዎቻቸውም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ መጥቷል። በርካታ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ደጋፊዎች የነበሩ ወደ መረረ ጠላትነት ተቀይረዋል። ጠ/ሚኒስትሩ ለዚህ ካምፕ የብሔራዊ ውይይቱ ሲጠናቀቅ ከዓላማቸው ጋር እንደሚጣጣሙ ቃል በመግባት ፓርቲያቸውን እና የድጋፍ መሰረታቸዉን ለጊዜውም ቢሆን አንድ ለማድረግ ይፈልጋሉ። ያለፉት ስድስት ዓመታት ትምህርት ከሆነ፣ መንግሥት ለሌሎቹ የፖለቲካ ካምፖች ደግሞ ፍጹም ተቃራኒ የሆነውን ቃል እንደሚገባ እንጠብቃለን። ሐገራዊው ውይይቱ አገዛዙ በየፖለቲካ ካምፑ ውስጥ ያሉ ለዘብተኛና ወላዋይ ሃይሎች ብሎ የፈረጃቸውን ለመቆጣጠር የሚሞክርበትን እድል መፍጠር ነው። አገዛዙ በኦሮሞ፣ በአማራ እና በትግራይ መካከል አለመግባባት ለመፍጠር ሲጥር ቆይቷል። አገዛዙ ለዘብተኛና ወላዋይ የሚላቸውን የፖለቲካ ቡድኖችን በማበረታታት እና ብሄራዊ ውይይቱን በተሳትፎ በማስጌጥ በየፖለቲካ ካምፑ ውስጥ አዲስ አለመግባባት ለመፍጠር ተስፋ አድርጓል። አብይ በግጭትና በኢኮኖሚ ችግር ለሚማቅቀው ህዝብ የተሳሳተ የተስፋ እና የዕድገት ስሜት ለመፍጠርም ተስፋ ያደርጋል። በመጨረሻም ከዚህ ሂደት ውስጥ አንዳች ነገር ቢመጣ ያዉ አብይ ስልጣኑን ለማጠናከር መንገድ የሚከፍትለት ህገ-መንግስታዊ ተንኮል ብቻ ነው። በሂደትም በድህረ 1991 የስርዓት ለውጥ ላይ የተደረሰውን ስስ የፖለቲካ እልባት ሊያናጋ ይችላል።
Mostrar todo...
Repost from KMN
Mostrar todo...
ታይታ ሰልፍ በምርጫ ምትክ

#KMN #KUSH

Repost from KMN
Hayilee fidaa har’a jiru kaan hidhanii itti roorrisaa kaan ajjeesat Hayilee Fidaa kaleessa sirni biroo ajjeesef akka waan quuqamaniitti maqaa isaanitiin daldalu. Hayilee Fidaa kaleessaatiif quuqamuuf imaltoota daandii Hayilee Fidaa Battee Urgeessaa fa’iif kabaja laatuu fi yoo dadhabdan lubbuudhan akka jiraataniif heyyamtu ture. Hayilee Fidaa kaleessaa kabajjanii du’a isaaniitiif quuqamuuf har’a Gadaa Gabbisaa fi Jaallan isaatif bilisummaadhan akka socho’aniif hidhaadhaa baaftu ture. Hayilee Fidaa waan lubbuudhan hin jirreef faarsitu malee waan Mangistuu Hayila Maariyaam irratti raawwate caala isa gootu ture. Mee haa ta’u yookaa nutu dhumee isin gaafachuu dhiisa, ykn isintuu of baree fafakkeesuu dhiisa diddus… https://www.facebook.com/share/A8fyW5FxUER7Dyo3/?mibextid=WC7FNe
Mostrar todo...
Repost from KMN
Mostrar todo...
የወለጋዉ ጉዞ, የኢሰመኮ እና OLA መግለጫ

#kmn #kush

Repost from KMN
Oromo for Justice, Security, and Truth (O-JUST), media release!
Mostrar todo...