es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Ir al canal en Telegram
1 474
Suscriptores
Sin datos24 horas
-37 días
-2130 días
Archivo de publicaciones
“የሀሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልጽግና!” በሚል መሪ ቃል የብልጽግና ፓርቲ አምስተኛ ዓመት የምስረታ በዓል በዓድዋ ድል መታሰቢያ የፓን አፍሪካ አዳራሽ በመከበር ላይ ይገኛል::

ዛሬ ህዳር 15 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ ከተማ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 11 ሎሚ ሜዳ እየተባለ በሚጠራዉ ኢንደስትሪ መንደር ከረፋዱ 5:57 ሰዓት ላይ ተከስቶ የነበረዉ የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ተችሏል። የእሳት አደጋዉ ያጋጠመዉ የእንጨትና የብረታ ብረት ዉጤቶች ማምረቻ ሼድ ላይ ሲሆን በእሳት አደጋዉ በአንድ መለስተኛ ሼድ ላይ ጉዳት ደርሷል። በዚህ ኢንደስትሪ መንደር በርካታ የእንጨትና የብረታ ብረት ማምረቻ ሼዶች የሚገኙበት ሲሆን የእሳት አደጋዉ ወደሌሎች ሼዶች ተዛምቶ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር ተችሏል። የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር የአደጋ መቆጣጠር ሰባት የአደጋ ጊዜ መቆጣጠር ተሽከርካሪዎችና 45 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር የተሰማሩ ሲሆን በአደጋዉ በሰዉ ላይ የደረሰ ጉዳት የለም። ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ! ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ዛሬ ማለዳ የብልጽግና ፓርቲ አምስተኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከ300 መቶ ሺሕ በላይ የከተማችን ነዋሪዎች የተሳተፉበት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አከናውነናል። ባለፉት አምስት ዓመታት ብልጽግና ፓርቲ ከተማችንን በተግባር ውብ አበባ ከማድረግ ስራው በተጨማሪ፣ በአዕምሮ እና በአካል ብቃት የዳበረ ትውልድ ለመፍጠር ነዋሪዎቻችን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚያደርጉባቸው ከ1300 በላይ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን አዘጋጅቶ ለአገልግሎት አብቅቷል። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

"የሀሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልጽግና!!" የብልጽግና 5ኛ ዓመት የምሥረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በአድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ይገኛል። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የአዲስ አበባ ከተማ የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በስነምግባር እና መልካም አስተዳደር ዙሪያ ያተኮረ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና በዛሬው እለት ሲሰጥ ውሏል። ስልጠናው በነገው እለት ህዳር 15 መሰጠቱ የሚቀጥል ሲሆን ለተቋሙ ሁሉም ባለሙያዎች ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጋር በተያያዘ የከተማውን ነዋሪዎች እርካታ ለማረጋገጥ የሚያግዝ የአገልጋይ ስነ ምግባርን ከመላበስና የተቋም ባህል ከማድረግ አንፃር መርሆዎችና ፅንሰ ሀሳቦቹ ላይ እንዲሁም ተግባራዊነቱ በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በቀረበ ሰነድ ላይ ውይይት ተካሂዶበታል። ስልጠናውን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የዋና ስራ አስኪያጅ አማካሪ አቶ ይብሬ ኢስማኤል ጽ/ ቤቱ በራሱና በአጠቃላይ ከማእከል እስከ ወረዳ ባለው መዋቅሩ የሚሰጡ አገልግሎቶች፣ ፈጣን፣ ፍትሃዊና ግልፅነትን የተላበሱ ለማድረግ እንዲህ አይነት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች ወሳኝ ናቸው ብለዋል። የስራ አስኪያጅ የፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ወሰን መግራ ባቀረቡት ሰነድ ላይ የተቋሙ አመራሮችም ሆነ ባለሙያዎች ከብልሹ አሰራር የጸዳ፣ ተጠያቂነት የሰፈነበት እና ሁሉንም ዜጎች በእኩልነት የሚያስተናግድ ምስጉን እና ታማኝ የህዝብ አገልጋይነት ስነምግባርን በመላበስ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የግንባር ቀደም አርአያነት ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል። በጽ/ ቤቱ የአገልግሎት አሰጣጥና ክትትልና ድጋፍ ባለሙያ አቶ ወርጃሞ ብሩ የስነ ምግባር ፅንሰ ሀሳቦች እና ምንነት፣የመልካም አስተዳደር አስፈላጊነት እና መርሆዎች ላይ ባቀረቡት ሰነድም ላይ አሳታፊ የሆነ ውይይት ተካሂዷል። የጽ/ቤቱ የስነ ምግባርና የፀረ ሙስና መከላከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ምህረቴ ሙሉ ሰው በበኩላቸው የጽ/ ቤቱ የማዘጋጃ ቤታዊ ዘርፍ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ሰፊ ስራዎችን የሚከወንበት እና የመልካም አስተዳደርን የማስፈን ጉዳይ ትልቅ ትኩረት የተሰጠው በመሆኑ ይህን መሠል የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ሲሉ አስገንዝበዋል። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ባለስልጣኑ የግንባታ መሠረተ ልማት ያበላሹ ግለሰቦችን ተጠያቂ አደረገ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ራስ መኮነን ድልድይ ከፍ ብሎ ኦቪድ ኮነስትራክሽን እየገነባ ያለው የግንባታ መሠረተ ልማት ያበላሹ ግለሰቦችች ተጠያቂ አደረገ። ባለስልጣኑ በአካባቢው የመንገድ መሠረተ ልማትበማበላሸት፣የአረንጓዴ ቦታዎች በመርገጥና የተሠጠውን ቅጣት ባለመቀበል በአራዳ ክ/ከ ራስ ደስታ ፖሊስ ጣቢያ በፈፀሙት ጥፋት በተሻሻለው የደንብ ቁጥር 167/16 መሠረት ክስ ተመስርቶባቸዋል። ባለስልጣኑ ክስ የመሠረተባቸው 1ኛ-አቶ ናሆም ብርሃነ ስላሴ አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት 2ኛ -አቶ ፍቅሩ ፅጌ ሰርቪስ 3ኛ- አረጋይ በርሄ ፕሮጀክት ማናጀር ናቸው። ባለስልጣኑ በከተማችን ውስጥ የሚገኙ በግንባታ ስራ ላይ የተሠማራችሁ ሁሉ ህግና አሰራርን በመከተል በተሠጣችሁ ፈቃድ እና በመንግስትና በህዝብ ሀብት የተገነቡ መሠረተ ልማቶችን በመጠበቅና በመንከባከብ እና የከተማ አስተዳደሩ ያወጣቸውን ደንቦች ተግባራዊ በማድረግ ስራቹን እንዲሠሩ በጥብቅ ያሳውቃል። ባለስልጣኑ በደንብ ተላላፊዎች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑ አሳውቋል።

የትንሳኤው ዐሻራ ዛሬ ምሽት ይጠብቁን

ህገ-ወጥ እርድ በማካሄድ ላይ በነበረ ድርጅትና ግለሰቦች ላይ እርምጃ ተወሰደ በአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወሪዳ 7 ውስጥ በህገ ወጥ መንገድ ጤንነቱን ያልተረጋገጠ እንስሳት በማረድ ለህብረተሰቡ ሊያቀርብ የነበረው ድርጅትና ግለሰብ ከሌሊቱ 7:00 ሰዓት ላይ በደረሰው የህብረተሰቡ ጥቆማ ከታረደው በሬ እና ለእርድ ከተዘጋጁት በሬዎች ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል ። ድርጅቱና ግለሰቦቹ የደንብ ማስከበር አባላት ከፀጥታ ጥምር ግብረ ሀይል ጋር በቦታው የተገኙ የታረደ የአንድ በሬ ስጋ ለቄራዎች ድርጅት እንዲወገድ ያስረከቡ ሲሆን በተጨማሪም ለእርድ ተዘጋጅተው የነበረ አምስት በሬዎች ለቄራዎች ድርጅት በማስረከብ ለመንግስት ገቢ እንዲሆን አድርገዋል። ድርጊቱ ሲፈፅም የነበረ ድርጅት እንዲታሸግ በማድረግ 15000/አስራ አምስት ሺህ/ ብር የተቀጣ ሲሆን በቦታው የተገኙ በሬ አራጅ ግለሰቦች እያንዳንዳቸው ሦስት ሦስት መቶ ብር ተቀጥተዋል። ባለስልጣኑ ጥቆማ ለሰጡ የማህበረሰብ ክፍሎች ምስጋና እያቀረበ በሌሎች አካባቢዎችም ለህብረተሰቡ ጤንነቱን ያልተረጋገጠ ስጋ በማቅረብ የህብረተሰቡን ጤና ችግር ውስጥ የሚጥሉ ግለሰቦችን መረጃ በመስጠት ማህበራዊ ሀላፊነቱን እንዲወጣ መልዕክት አስተላልፏል። ለማንኛውም የደንብ መተላለፍ ጥቆማዎች ነፃ የስልክ መስመር 9995 ይጠቀሙ! የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የ’ጥራት መንደር’ን ዛሬ በይፋ ከመመረቃችን ቀደም ብሎ የገነባነውን ብሔራዊ የጥራት መሠረተ ልማታችንን ትናንት የመጎብኘት እድል ነበረኝ። ይኽ ወሳኝ ተቋም የሀገር ውስጥ ምርቶቻችን በአለም ገበያ የሚኖራቸውን ተወዳዳሪነት በማላቅ በአለም የእሴት ሰንሰለት የሚኖራቸውን ተሳትፎ የሚያጎለብት ነው። ከሀገራችን መሪ ተቋማት አንዱ በመሆን የውጭ ንግድ አቅሞቻችንን በማጠናከር በአለምአቀፍ መድረክ ተወዳዳሪ ሆነን እንድንዘልቅ የሚያስችለንም ይሆናል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ Before officially inaugurating ‘Quality Village ‘today, I had the opportunity yesterday to visit and review the National Quality Infrastructure we have developed. This critical institution is designed to catalyze the competitiveness of our local products in global markets and enhance our participation in global value chains. As one of our leading national institutions, it will play a vital role in strengthening our export capabilities and ensuring we remain competitive in the international arena.

photo content
+9