1 474
Suscriptores
Sin datos24 horas
-37 días
-2130 días
Archivo de publicaciones
እንኳን ለ1500ኛው የመውሊድ በዓል አደረሳችሁ፡፡
የታላላቆቻችንን በዓል የምናከብረው የእነርሱን አርአያ ለመከተል ምክንያት እንዲሆነን ነው፡፡ ምን እንደሠሩ? ምን እንዳስተማሩ? ምን እንደገጠማቸው? ፈተናዎችን እንዴት እንዳለፉ? ታሪካቸውን እያነሣን እንማርበታለን፡፡ የመውሊድንም በዓል ስናከብር የነቢዩ መሐመድን(ሰዐወ) ፈለግ እናጠናለን፣ ከሕይወታቸው እንማራለን፤ ፈተናን የተሻገሩበት መንገድ ለእኛ ብርታት ይሆነናል፡፡ አስተምህሯቸውን እያስታወስን ራሳችንን እንመዝንበታለን፡፡
የዘንድሮው በዓል የሚከበረው 2017ን በምናሰናብትበት ዋዜማ ላይ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ “ከትዕግሥት እና ከዕውቀት በተሻለ ሊጣመሩ የሚገባቸው ነገሮች የሉም” ያሉትን የነቢዩን ቃል እናስታውሳለን፡፡ ያለንበት ጊዜ የኢትዮጵያ ማንሠራራት እውን የሆነበት ጊዜ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ፈጣሪ የደከምንበትን ባርኮ የለመንነውን ሰጥቶናል፡፡ የኢትዮጵያ ብልጽግና የበለጠ እውን እንዲሆን ደግሞ ነቢዩ እንዳሉት ዕውቀትና ትዕግሥትን አጣምረን እንጓዛለን፡፡ ዕውቀት ብርሃን ሆኖ ይመራል፡፡ ትዕግሥት ደግሞ ፈተናዎችን በጽናት እንድንሻገር ያደርጋል፡፡ ይሄንንም ከነቢዩ መሐመድ(ሰዐወ) ተምረናል፡፡
“ዛፍ እየተከልክ የፍርድ ቀን ቢደርስ፣ ሳታቋርጥ ዛፍ መትከልህን ቀጥል” እንዳሉት፣ ፈተናዎች ቢበዙም፣ መሰናክሎች ቢደረደሩም እስከ ሕቅታ ድረስ ለሀገራችን እና ለሕዝባችን መልካም መሥራትን እንቀጥላለን፡፡ ከመልካም ሥራ የተሻለ በምድርና በሰማይ ሰውን የሚያስከብር ሕዝን የሚጠቅም ነገር ስለሌለ፡፡
ይሄንን የመውሊድ በዓል የሚያከብሩ ሙስሊም ወገኖቼ ሁሉ፣ መጪውን ዓመት በአላህ ዘንድ እጅግ ተወዳጅ በሆነው መልካም ሥራ እንዴት እንደምናሳልፈው በመዘጋጀት እንደሚያከብሩት ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ 2018 የኢትዮጵያን ማንሠራራት በሁሉም ዘርፎች ይበልጥ የምናጸናበት ዓመት በመሆኑ፡፡
መልካም የመውሊድ በዓል ይሁን፡፡
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ነሐሴ 28 ቀን 2017 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
#ከተማና #ከተሜነት
አዲስ አበባ ከዬት ወዴት? ለአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማቱ ይዟቸው የመጣቸው ትሩፋቶችና መልካም እድሎች ምንድናቸው?
በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ እና የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ኪነ ህንፃ መምህር አርክቴክት ዮሃንስ መኮንን በኢቢሲ ዳጉ ያካሄዱትን ውይይት በቀጣዩ ቪዲዮ ይከታተሉ።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
See less
የመሰረተ ልማትና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከአስፈጻሚ አካላት ጋር የእቅድ ውይይት አደረገ።
በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመሰረተ ልማትና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተጠሪ ከሆኑ አስፈጻሚ አካላት ጋር የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት አድርጓል።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር ግዛቸው አይካ መድረኩ ለምክር ቤቱም ለአስፈጻሚ አካላትም 2018 በጀት ዓመትን ቀድሞ ለመመልከት የሚያስችል መሆኑን ገልጸው፤ ከተማዋ በ2023 ለመድረስ ያስቀመጠችውን ግብ ለማሳካት ይቻል ዘንድ በተቋማት እቅድ ውስጥ የተካተቱ ጉዳዮችን ለመመልከት እንደሚያስችል ጠቁመዋል።
በዚህም የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት፣ ትራንስፓርት ቢሮ፣ ኤሌትሪክ አገልግሎት፣ መንገዶች እና የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በሀላፊዎቻቸው አማካኝነት በ2018 በጀት ዓመት ሊሰሯቸው በእቅድ የያዟቸውን አበይት ተግባራት ለቋሚ ኮሚቴው አቅርበዋል።
በመድረኩ የቋሚ ኮሚቴው አባላትን ጨምሮ ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን ፤ በከተማ ፣ክፍለ ከተማ እንዲሁም በወረዳ ደረጃ በዘርፉ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰሩ በታቀዱ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።
አስፈጻሚ አካላትም ቋሚ ኮሚቴዎች ቢደግፈን ያሏቸውን ጉዳዮች በዝርዝር ያስረዱ ሲሆን ከባለፈው ዓመት የተሻለ አፈጻጸም እንዲኖርም ከሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩም ገልፀዋል።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር ግዛቸው አይካም በሰጡት ማጠቃለያ መድረኩ በቀጣይ እንደ ከተማ መታየት ያለበት የመሰረተ ልማት እድገት ምን ሊመስል እንደሚችል ያሳየ መሆኑን ገልጸው ፤ አክለውም ተቋማት እቅዳቸውን መሠረት በማድረግ የታለመውን ውጤት ማምጣት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት Addis Ababa City Council l
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
መጪዎቹ የጳጉሜን ቀናት…
በተገባደደው ዓመት የተከናወኑ ስኬታማ ተግባራትና የቀጣይ ሀገራዊ እቅዶች የሚተዋወቁባቸው መጪዎቹ የጳጉሜን ቀናት የተለያዩ ስያሜ ተሰጥቷቸዋል፡፡
ጳጉሜን-1 የጽናት ቀን
የጽናት ቀን “ጽኑ መሰረት ብርቱ ሃገር” በሚል መሪ ሀሳብ ለኢትዮጵያ ብልጽግና የሚተጉና ዋጋ የከፈሉ ኢትዮጵያውያንን በመዘከርና በማመስገን ይከበራል፡፡
ጳጉሜን-2 የህብር ቀን
የህብር ቀን “ብዝሃነት የኢትዮጵያ ጌጥ” በሚል ሀሳብ የኢትዮጵያን የብዝሃነትና የአንድነት ውበት እንዲሁም የአብሮነት እሴት በሚያጎሉ ዝግጅቶች ተከብሮ ይውላል፡፡
በዕለቱ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የቁሳቁስ፣ የማዕድ ማጋራት፣ የመማሪያ ቁሳቁስና መሰል ድጋፎችን በማድረግ አብሮነትን የሚያሳዩ የበጎ አድራጎት ተግባራት ይከናወናሉ፡፡
ጳጉሜን-3 የእመርታ ቀን
የእመርታ ቀን “እመርታ ለዘላቂ ከፍታ” በሚል መሪ ሀሳብ ባለፉት አመታት የተመዘገቡ ስኬቶችንና ለቀጣዩ አመት የተሻለ ስራዎች እንዲሰሩ በማሰብ ይከበራል፡፡
በግብርናው ዘርፍ የምግብ ሉአላዊነትን ለማረጋገጥ፣ በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር፣ በኢንዱስትሪ፣ በማዕድንና ሌሎች ዘርፎች የተመዘገቡ ስኬቶች ይወሱበታል፡፡
ጳጉሜን-4 የማንሰራራት ቀን
የማንሰራራት ቀን “ዘላቂ ልማት ለሀገራዊ ማንሰራራት” በሚል መሪ ሀሳብ ኢትዮጵያ በለውጥ የማንሰራራት ጅማሮ ላይ መሆኗን በሚያሳዩ ሁነቶች ይከበራል፡፡
ጳጉሜን-5 የነገው ቀን
የነገው ቀን “ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ” በሚል መሪ ሀሳብ የነገዋን ኢትዮጵያ በዲጂታል ለመገንባት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማውሳት የሚከበር ይሆናል፡፡
መዲናችን አዲስ አበባ በጽዳት ዘርፍ የተመዘገበው እምርታዊ ለውጥ ከተማችን የአፍሪካ ሞዴል እንድትሆን እንዳስቻላት በም/ ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አመለከቱ።
መዲናችን በፅዳቱ ዘርፍ ያስመዘገበችው ስኬት የከተማ አስተዳደሩ የሚመለከታቸውን ሁሉም ባለድርሻ አካላትና መላው የከተማችንን ነዋሪዎች ስትራቴጂካሊ በመምራት በማስተባበርና በሂደቱ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን በማስቻሉ እንደሆነ ገልፀው ይህንን ለውጥ ሁላችንም አጠናክረን ልናስቀጥል ይገባል ሲሉም ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ጥሪ አቅርበዋል።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ይህን መልእክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ በ2017 በጀት ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ላበረከቱ አካላትና ተቋማት እውቅናና ሽልማት በሰጠበት ወቅት ነው።
በዚሁ ወቅት የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ደሲሳ እንደገለፁት ከተማችን አዲስ አበባም በተለይ ከለውጡ ወዲህ ውብ፣ፅዱ እና ለኑሮ ምቹ ለማድረግ በተከናወነው ዘርፈ ብዙ ሰራዎች አስደማሚ ለውጥ ማምጣት መቻሏን ጠቅሰው ይህም በአለምዓቀፍ ደረጃ ጭምር የተመሰከረላት ሲሆን በዚህም የቱሪስት መዳረሻ ለመሆን በቅታለች ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አክለውም ይህን ውጤት በያዝነው የ2018 በጀት አመት አጠናክረን በህብረተሰብ ተሳትፎ በማስቀጠል በመዲናችንን ፅዳቱን ባህል ያደረገ ህብረተሰብ በመፍጠር ከተማችን የብልጽግና ማዕከል ማድረግ አለብን ብለዋል፡፡
በዚሁ መድረክ የ2017 በጀት ዕቅድ አፈጻጸምንና የ2018 በጀት ዓመት ቀጣይ አቅጣጫን ያቀረቡት የኤጀንሲው ም/ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳዲቅ ሽኩር ናቸው።
በመቀጠል በበጀት ዓመቱ የተሻለ አፈጻጻም ለነበራቸው ተቋማት፣ የጽዳት አምባሳደሮች፣ እንዲሁም ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
በዚህ መሠረት በ2017 በጀት አመት የላቀ አፈፃፀም እና ከፍተኛ
ውጤት ያስመዘገቡ ክፍለ ከተሞች :-
1ኛ ) - ቦሌ ክፍለ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ፅ/ ቤት
2ኛ)- የካ ክፍለ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ፅ/ ቤት
3ኛ )- ለሚኩራ ክፍለ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት
ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ በመውጣት እውቅናና ሽልማት ከኤጀንሲውና ከስራ አስኪያጅ ፅ/ ቤት ተሸላሚ ሆነዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
“ግድቡ በተሟላ ደረጃ ተጠናቆ ስራ ከጀመረበት እለት ጀምሮ የኢትዮጵያ የጂኦ-ፖለቲካ ኩስመና ታሪክ አበቃ ማለት ነው። የኢትዮጵያ የጂኦ-ፖለቲካ ቁመና ተሻሻለ ማለት ነው። ይህ የተሰመረበት ሃቅ ነው!” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) … See more
“ዓባይን ጨርሶ በኢትዮጵያ ውስጥ የታሪክ እጥፋትን ማረጋገጥ የመጨረሻው ጸሎቴ፤ የመጨረሻው ምኞቴ ነበር” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
"የኩስመና ታሪክ ማብቂያ
በስራ አስኪያጅ ልዩ ወረዳ የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የማጠቃለያ ኮንፈረንስ ተካሄደ።
በኮንፈረንሱ በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ ዋ/ስራ አስኪያጅና የስራ አስኪያጅ ልዩ ወረዳ ሰብሳቢ አቶ ተፈራ ሞላ ፓርቲያችን ብልፅግና ትልቅ ህልም አንግቦ፣ አገራችንን ወደ ሚጨበጥ ተስፋ ማሸጋገር እና ሁለንተናዊ ብልፅግና ማረጋገጥ የቻለ ግዙፍ አፍሪካዊ ፓርቲ ነው ሲሉ አስገንዝበዋል።
አሁን የምናካሂደው ኮንፈረንስ የመላው ኢትዮጵያውያን የጋራ ጥረት ውጤት የተረጋገጠበት የታላቁ የህዳሴ ግድባችን ተመርቆ ለአገልግሎት ለመብቃት ዝግጁ በሆነበት ታሪካዊ ወቅት ላይ የምንገኝ መሆኑ እለቱን ልዩ ያደርገዋል ሲሉ ገልፀው ከዚህ ጎን ለጎንም እንደ ሀገር ያጋጠሙንን ተግዳሮቶችን በድልና በጥበብ በመሻገር የተፈጥሮ ፀጋዎቻችን በመጠቀም ቀይ ባህርን በአለም አቀፍ ደረጃ አጀንዳ ማድረጋችንም ሌላው ስኬታችን ነው ሲሉ ተናግረዋል።
አክለውም በስራ አስኪያጅ ልዩ ወረዳ ያሉ ተቋማት አብዛኞቹ አገልግሎት ሰጪ እንደመሆናቸው የአባላት አቅም ግንባታን በማሳደግ፣ሌብነትና ብልሹ አሰራርን መታገል፣የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት በቴክኖሎጅ የታገዘ ቀልጣፋና ፈጣን አገልጎሎት መስጠት በ2018 በጀት አመት በልዩ ትኩረት የሚሰራበት እንደሆነ ገልፀዋል።
በኮንፈረንሱ የ2018 ዓ.ም የፖለቲካ እና የድርጅት ስራዎች ዕቅድ፤ ባለፉት ሁለት ወራት የተከናወኑት የፖለቲካና የድርጅት ስራዎች የተገመገሙ ሲሆን ጎን ለጎን የተጓደሉ የህብረት አመራሮችን የማሟላት፤ አዳዲስ አባላትን የማፀደቅ ስራዎች እና የ2018 ኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ዕቅድ ቀርቦ የማፀደቅ ስራ ተከናውኗል ፡፡
በስተመጨረሻም በስራ አስኪያጅ ልዩ ወረዳ በሁሉም ህብረቶች ባለ 7 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ኮንፍረንሱ ተጠናቋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የአዲስ አበባ ሪጅን አገልግሎት መስጫ ማእከላት የተገልጋይ እንግልትን የሚቀንስ ምቹ የስራ አካባቢን እየፈጠሩ መሆናቸውን በም/…
See more
