es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete 👈

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Ir al canal en Telegram
1 474
Suscriptores
Sin datos24 horas
-37 días
-2130 días
Archivo de publicaciones
photo content
+5

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው የ4ኛ ዓመት 6ኛ መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል ። በዚሁም መሰረት ካቢኔው የሃገራችንን ዲፕሎማሲ ታሳቢ ያደረገ የኤምባሲዎች የመሬት ጥያቄን እና የከተማዋን የኢኮኖሚ እንቅቃሴ ለሚያጎለብቱ፣ ሰፊ የስራ እድል እየፈጠሩ ላሉ፣ የዉጪ ምንዛሬ እያስገኙ ላሉ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረቻ ማስፋፊያ ቦታ ጥያቄዎችን መርምሮ ውሳኔ አሳልፏል።

ዜና ሹመት ኮማንደር አህመድ መሀመድ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነዉ ተሹመዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ሆነው ለተሾሙት ለኮማንደር አህመድ መሀመድ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ይመኛል። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ መደበኛ የሰራተኛ ደንብ ልብስ ማልበስ ስነ- ስርዓት እና ሁለተኛውን የእውቅና መርሃ ግብር -(በምስል)

photo content
+3

photo content
+9

ከህጻንነታቸዉ ጀምሮ በኮልፌ የወንዶች ልጆች ማሳደጊያ እና በቀጨኔ የሴቶች ማሳደጊያ ማዕከል ካሳደግናቸው ልጆቻችን መካከል ሰባቱን ለወግ ለማዕረግ አብቅተን የጋብቻ ስነ ስርዓታቸውን ለመፈጸም ያበቃን ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን:: ሙሽሮች እንኳን ደስ ያላችሁ! እንኳን ፈጣሪ በህይወት ውጣ ውረድ ውስጥ ረድቷችሁ ለዚህ ለተባረከ እና ለተቀደሰ የህይወታችሁ ምዕራፍ ቀን እንኳን አደረሳችሁ:: መልካም ጋብቻ ይሁንላችሁ! የከተማ አስተዳደራችን ወላጅ ለሌላቸዉ ወላጅ እና ቤተሰብ በመሆን አሳድጎ፣ ለወግ ለማዕረግ እንዲበቁ ከማድረግ በተጨማሪ በቀጣይ የህይወታቸው ምዕራፍ የስራ እድል በመፍጠር ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ዉጤታማ ህይወት እንዲኖራቸው እየተመኘን በዚህ በተቀደሰ ስራ የተሳተፉትን ሁሉ ላመሰግናቸው እወዳለሁ። በድጋሚ መልካም ጋብቻ ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

photo content
+9

photo content
+6

በሲቪል ምዝገባ እና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የሚሰሩ የሪፎርም ስራዎች መዲናዋን ስማርት ለማድረግ ከፍተኛ ድርሻ አንዳላቸው በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ አመለከቱ። በሲቪል ምዝገባ እና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የሚሰሩ የሪፎርም ስራዎች አዲስ አበባ ከተማን ስማርት ከተማ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ ረገድ ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ተናግረዋል። የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ መደበኛ የሰራተኛ ደንብ ልብስ ማልበስ ስነ- ስርዓት እና ሁለተኛውን የእውቅና መርሃ ግብር አካሂዷል። 81 አመታትን ያስቆጠረው ተቋሙ ከአገልግሎት አሰጣጡ ጋር በተያያዘ በርካታ ቅሬታዎች ሲቀርቡበት እንደነበረ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ተናግረው ባለፉት ሁለት አመታት ተኩል በተሰራው የሪፎርም ስራ በርካታ መሻሻሎች መምጣታቸውን ገልጸዋል። በቴክኖሎጂ ፣ በአሰራር ፣ በሰው ሀብት፣ በአደረጃጀት እና የስራ ከባቢን ምቹ በማድረግ ላይ ያተኮረው የተቋሙ ሪፎርም ቀልጣፋና ከብልሹ አሰራር የጸዳ አገልግሎትን ለመስጠት መሰረት እንደጣለ ነዋና ዳይሬክተሩ ተናግረው በዚህ አመት ሪፎርሙን ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ ወደ ተሟላ ትግበራ እንደሚገባም አስታውቀዋል። አክለውም የተቋሙ ሰራተኞች መደበኛ የደንብ ልብስ እንዲኖራቸው እና በየአመቱ የተሻለ አፈጻጸም ያላቸውን ሰራተኞች እውቅና መስጠትም የሪፎርሙ አካል መሆኑን ገልፀዋል። ከወረዳ እስከ ማዕከል ባለው የኤጀንሲው ተቋማት የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ሰራተኞች እውቅና የሰጡት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ የከተማ አስተዳደሩ የጀመራቸው የሪፎርም ስራዎች እንዲሳኩ እያደረጉ ከሚገኙ ተቋማት አንዱ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ነው ብለዋል። የተቋሙ አገልግሎት የከተማ አስተዳደሩ ለሚያከናውኗቸው ማናቸውም ስራዎች መሠረት ነው ያሉት ኢንጅነር ወንድሙ በተቋሙ የሚሰሩ የሪፎርም ስራዎች አዲስ አበባ ከተማን ስማርት ከተማ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ ረገድ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለውም ተናግረዋል ። የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች የተጀመረውን ሪፎርም ውጤታማ በማድረግ የተቀላጠፈ እና የተገልጋዩን እርካታ የሚያሳድግ አገልግሎትን በቀጣይነት እንዲሰጡም አሳስበዋል። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

በበጀት ዓመቱ 6 ወራት በየሳምንቱ ቅዳሜ በሚከናወነው ሁሉን አቀፍ የፅዳት ንቅናቄ ላይ 668 ሺህ 591 የሚሆኑ የመዲናዋ ነዋሪዎችን እንዲሳተፉ ለማድረግ ታቅዶ 668 ሺህ 571 ያህል ነዋሪዎችን በንቅናቄው ማሳተፍ ተችሏል።

የፅዳት ንቅናቄ ስራው ትሩፋቶች በከፊል... በየሳምንቱ ዓርብ በትምህርት ቤቶች በተካሄደ የፅዳት ንቅናቄ 99 ት/ቤቶችን ተምሳሌት ማድረግ ተችሏል በየሳምንቱ ዓርብ በሀይማኖት ተቋማት ላይ በተካሄደ ንቅናቄ ስራ 19 ተቋማት በፅዳታቸው ሞዴል ማድረግ ተችሏል በየሳምንቱ ዓርብ በወረዳዎች ላይ በተካሄደ ንቅናቄ 22 ወረዳዎችን በፅዳታቸው ሞዴል ማድረግ ተችሏል። በየሳምንቱ ቅዳሜ በብሎኮች ላይ በተካሄደ ፅዳት ንቅናቄ 340 ብሎኮችን ተምሳሌት ማድረግ ተችሏል። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

‟ከተማዋ አምራና ተውባ ከምትታይበት ደረጃ እንድትደርስ ከሆነችበት ተግባራት መካከል ፅዳት ላይ ትኩረት መደረጉ ነው” አቶ ጌታሁን አበራ - የአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ የአራዳ ክ/ከተማ ፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ሳምንታዊ የፅዳት ንቅናቄውን በአንድ ማዕከል ወረዳ ሁለት አራት መንታ የክ/ከተማው ከፍተኛ አመራሮች ፣ የፅዳት አምባሰደሮች እና ነዋሪዎች በተገኙበት ዛሬ ማለዳ አካሂዷል። የአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጌታሁን አበራ ከተማዋ አምራና ተውባ ከምትታይበት ደረጃ እንድትደርስ ከሆነችበት መካከል ፅዳት ላይ ትኩረት መደረጉ ነው ብለዋል። ፅዳት አካባቢን ውብና ፅዱ ያደርጋል፣ ወደ ሀብትነት ይቀየራል፣ ጤናችንን ያስጠበቃል ያሉት አቶ ጌታሁን አበራ ሁልጊዜ ፅዳትን አዕምሯችን ላይ በማኖር ባህልነቱን ማዳበር ይገባል ሲሉ ተናግረዋል። አቶ ጌታሁን አበራ አክለውም ፅዳት አስተሳሰብ ነው የሚጀምረው ጥሩ በማሰብ በፅዳትም እና በሁለንተናዊ ስራዎች ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ጠቁመዋል። የፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እንየው ዘላለም በበኩላቸው ፅዳት በማህበረሰቡ ዘንድ ባህል እየሆነ መምጣቱን ገልፀው ተጠናክሮ የእለት ከእለት ተግባር ሆኖ እንዲቀጥል የድርሻችንን እንወጣ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወጣው ደንብ ቁጥር 167/2016 መሠረት ቆሻሻን አግባብ ባልሆነ ስፍራ የሚጥሉ አካላት ላይ ቅጣት መጣሉ እንደሚቀጥል መልዕክት ተላልፏል። የክፍለ ከተማ አስተዳደሩ ከተማዋን ውብ፣ ፅዱና ለኑሮ ምቹ እንድትሆን ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል የፅዳት ዘርፍ ስራ አንዱ ነው። የክ/ከተማዋ ነዋሪዎችናጵተቋማት ፅዳትን ልማድ እንዲያደርጉም የንቅናቄና መደበኛ የፅዳት ስራዎች በማካሄድ ለውጥ በማምጣት ላይ እንደሚገኝ ተመላክቷል። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ያየነውን ለማሳየት እንተጋለን። ያየነውን ለማሳየት እንተጋለን።