1 474
Suscriptores
Sin datos24 horas
-37 días
-2130 días
Archivo de publicaciones
መዲናችን አዲስ አበባን ዘመናዊ ከተማ በማድረግ ሂደት ወሳኝ የሆኑ የመሠረተ ልማት ዝርጋታዎች መካከል ከመንገድ መብራት ዝርጋታ ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮችን ለመቅ…
See more
የኮሪደር ልማት በርካታ ትችቶችን አልፎ እምርታ ማሳየቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ
የኮሪደር ልማት ገና በአዲስ አበባ ከተማ ሲጀመር፣ በርካታ ትችቶች እና ነቀፌታዎች ሲሰነዘሩበት እንደነበርና ያንን ሁሉ አልፎ ትልቅ እምርታ ማስመዝገቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመደመር ሀሳብ ላይ የጻፉት አራተኛውንና "የመደመር መንግሥት" የተሰኘውን አዲስ መጽሐፍ በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ ከኮሪደር ልማቱ ጋር በተያያዘ የተገኘውን ስኬት አንስተዋል።
የመዲናዋን ገፅታ በብዙ መልኩ እየቀየረ የሚገኝው የኮሪደር ልማት፣ ከመዲናዋ አልፎ በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች ጭምር እየተተገበረ እና ትልቅ ለውጥ እያመጣ እንደሚገኝ አመላክተዋል፡፡
የኮሪደር ልማት ሥራው ከኢትዮጵያ ባለፈ ለአፍሪካ ከተሞችም ተምሳሌት እየሆነና ልምድ እየተቀሰመበት እንደሚገኝም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማት ሥራ አርቆ በማሰብ እና አልቆ በመስራት የመጣ ሀገርን የሚያኮራ ተግባር የተሰራበት እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
ብዙዎች በሩቅ በሌሎች ሀገራት እያዩት ሲመኙት የነበረው ልማት፣ በሀገር ውስጥ እውን መሆኑ፣ ዜጎች በሀገራቸው ለመኖር፣ ለመሥራት እና በሀገራቸው እንዲኮሩ ከማድረጉም ባሻገር፣ የሌላ ሀገር ዜጎች ኢትዮጵያን ለመጎብኘት እንዲነሳሱ ያደረገ ልማት መሆኑንም አመላክተዋል፡፡
AMN-Addis Media Network
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት፣ የህብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፈቃድ ስራዎቾ የ90 ቀናት ልዩ የንቅናቄ እቅድ የ70 ቀናት የስራ አፈፃፀም የመስክ ምልከታ እና ሱፐርቪዥን ተካሄደ።
በቢሮ ሃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ዋ/ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ የተመራው የሱፐርቪዥን ቡድን በ90 ቀናት በልዩ የንቅናቄ አጀንዳ እቅድ ተይዘው ባለፉት 70 ቀናት የተከናወኑ የፅዳትና የዉበት፣የአደጋ መከላከልና ቅነሳ ፣ የፋይዳ ምዝገባ ስራዎች እና ከህብረተሰብ ተሳትፎ አንፃር የተቀናጀ የሞዴል ብሎክ ስራዎች በተቀመጠዉ መስፈርት መሠረት ስለመከናወኑ በተመረጡ ክፍለ ከተሞች እና ወረዳዎች የመስክ ምልከታ ተከናውኗል።
በተካሄደው የመስክ ምልከታም በየክፍለ ከተሞች በተከናወኑት ተግባራት አበረታች ዉጤቶች መገኘቱን አቶ ተፈራ ሞላ ገልፀዋል።
አክለዉም በሁሉም ዘርፎች የተከናወኑ ተግባራት ዘርፈ ብዙ መሆናቸዉን ገልፀው ሞዴል ብሎኮችን ለመፍጠር በተደረገው ርብርብ ልክ ሞዴል ወረዳዎችን የመፍጠር ስራ በ24/7 በልዩ ትኩረት የተጠናክረ ርብርብ ሊደረግበት እንደሚገባም አመልክተዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ እሴቶቻችን የኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን ማሳያ ናቸው።
ብዝኃነት እና ኅብረ ብሔራዊ አንድነት መገለጫዋ የኾነችው ኢትዮጵያ የክረምቱን መገባደድ የሚያበስሩ ትውፊቶች ባለቤት ናት።
ከነሐሴ አጋማሽ ጀምሮ ልጃገረዶች ወደ ዐደባባይ በመውጣት የሚያሰሟቸዉ ኅብረ ዝማሬዎች በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የክረምቱን መገባደድ፤ በየጋራ ሸንተረሩ የአበቦችን መፍካት፣ የምንጮችን መጥራት እና የቡቃያዎችን ማፍራት ያበስራሉ።
ከእነዚህ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ ክዋኔዎች መካከል ከነሐሴ አጋማሽ ጀምሮ ለቀናት በድምቀት የሚከበረው እና በተለያዩ አካባቢዎች በተቀራራቢ ሻደይ፣ አሸንዳ፣ አሸንድዬ እና ሶለል በሚሉ መጠሪያዎች የሚታወቀው በዓል ተጠቃሽ ነው።
በዓሉ በተለያዩ አካባቢዎች በተለያዩ ትውፊታዊ ዳራዎች በተቀራራቢ ዓውድ፣ በተመሳሳይ ጊዜ፣ በተለያዩ ባህላዊ ኅብረ ዝማሬዎች በሴቶች የሚከበር የነፃነት የዐደባባይ በዓል ነው።
ይህን በዓል የአጎራባች ሕዝቦች ግንኙነትና ትስስርን በሚያጎለብት መልኩ ማክበር፣ መጠበቅ እና ለትውልድ ማስተላለፍ ያስፈልጋል።
ይህ በዓል ከትውልድ ትውልድ እየተወራረሰ ቢመጣም በአግባቡ ተዋውቆ አንድ የመስሕብ ሀብት እንዲኾን ተጨማሪ ሥራ ይፈልጋል። ከዚህም ባሻገር ከነሐሴ አጋማሽ ጀምሮ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የሚከበሩ የተለያዩ በዓላት ጋር በማስተሳሰር ኅብረ ብሔራዊነትን በሚገነባ መልኩ መሥራት ይጠይቃል።
የጳጕሜን ቀናት፣ የኢትዮጵያ ዐዲስ ዓመት፣ የተለያዩ ብሔሮች እና ብሔረሰቦች የዘመን መለወጫ በዓላት፣ የመስቀል በዓል እንዲሁም የኢሬቻ በዓልን በቅርብ ርቀት የሚያስከትሉ በመኾናቸው የበለጠ ለጎብኝዎች ቆይታ መራዘም ጉልህ ሚና ሊጫወቱ የሚችሉ ናቸው።
በመሆኑም በተለመደ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ እሴታቸዉ መሠረት በድምቀት እየተከበሩ ለቱሪዝም ዘርፉ መነቃቃት የበኩላቸዉን ሚና እንዲጫወቱ መንግሥት አስፈላጊዉን ኹሉ ድጋፍ ያደርጋል።
እንኳን ለሻደይ/አሸንዳ/አሸንድዬ/ሶለል በዓል አደረሳችሁ!
የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ነሐሴ 16 ቀን 2017 ዓ.ም
የመንገድ መብራቱ መጠገን ማህበረሰቡ በተደጋጋሚ ያነሳ የነበረውን የረጅም ጊዜ ቅሬታ እንዲፈታ አስችሏል
ከመንገድ መሰረተ ልማቱ ጋር አብረው የለሙና ለማህበረሰቡ አገልግሎት ባለመዋላቸው ተደጋጋሚ ቅሬታ ሲነሳባቸው የነበሩ የመንገድ መብራቶችን በመለየትና በመጠገን የትራፊኩን እንቅስቃሴ ምቹ፣ ጤናማና አስተማማኝ ማድረግ መቻሉን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ገለፁ፡፡
ይህን የገለፁት ከመገናኛ ደራርቱ ህንፃ - ውሃ ልማት 40/60 ኮንደሚኒየም - ሃያ አራት በሚወስደው መንገድ ላይ ተጠግኖ ወደ አገልግሎት የገባውን የመንገድ መብራት የደረሰበትን አፈፃፀም ከሚመለከታቸው የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በጋራ የመስክ ምልከታ ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡
በምልከታቸውም ከመንገድ መሰረተ ልማቱ ጋር አብሮ ለምቶ ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች ከፕሮጀክቱ ጋር ባለመጠናቀቃቸው ለነዋሪው ተደጋጋሚ የቅሬታ ምንጭና የመልካም አስተዳደር ችግር ሆነው የቆዩትን በመለየት ዘላቂ መፍትሄ በመስጠት በኩል በመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን በኩል እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል፡፡ አክለውም የጥገና ስራው የከተማውን ውበትና ገፅታ ከመለወጥ ባለፈ በምሽት ላለው እንቅስቃሴ ምቹ፣ አስተማማኝና ደህንነቱ የተጠበቀ እንደሚያደርግ ኢንጂነር ወንድሙ ተናግረዋል፡፡
በጉብኝቱ ላይ የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን አዲስ አበባ ያላትን ገቢ የመሰብሰብ አቅምን በማሳደግና ለሚከናወኑው የልማት ስራዎች አብዛኛውን በጀቷን ለካፒታል ፕሮጀክቶች በመመደብ የተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ በዛሬው እለትም በተካሄደው የመንገድ መብራት ጥገና ስራ ከመንገዱ ጋር አብሮ አገልግሎት ሳይሰጥ ሲንከባለል የነበረውን የረጅም ጊዜ የማህበረሰብ ጥያቄ መመለስ መቻሉን ገልጸዋል፡፡ በዚህም መንገዱ ብርሀን በመሆኑ ሰው በነፃነት እንዲንቀሳቀስ አድርጓል ያሉ ሲሆን ይህ በመሆኑ ንግዱን በማዳበር ከዛው የሚገኘውን ገቢ መልሶ ለከተማው ልማት ይውላል ብለዋል፡፡
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰብስብ ሁሴን የከተማውን የመንገድ ዳር መብራት መጠገን፤ ህብረተሰቡ ለሚያነሳው የረጅም ጊዜ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሙሉ በሙሉ ምላሽ የሚሰጥ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ለዚህም ይህ ፕሮጀክት አንዱ ማሳያ መሆኑን ያነሳት ዋና ዳይሬክተሩ ህብረተሰቡ ለረጅም ዓመታት በጭለማ ያደርግ የነበረውን እንቅስቃሴ በብርሀን በመለወጥ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ ከማድረግ ባለፈ መንገዱን ተከትሎ ለሚገኙ የንግድ ቦታዎችና ከመንገዱ ጋር አብሮ ለምቶ ነዋሪዎች ለሚኖሩበት የ40/60 ኮንደሚኒየም ምቹና ሰላማዊ እንቅስቃሴ ፈጥሯል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
አያይዘውም ባለስልጣኑ በከተማዋ የተለያዩ መንገዶች ላይ ያሉትን መብራቶች አስፈላጊውን ጥናት በማድረግ ያጋጠመ ብልሽትና ያልተሟሉ መሰረተ-ልማቶችን በማሟላት ህብረተሰቡ በምሽት ምቹና ሰላማዊ እቅስቃሴ እንዲያደርግ የሚሰራውን ስራ በከተማው መንገዶች ላይ ሁሉ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖር ይጠበቃል
****************
በሚቀጥሉት 11 ቀናት በመካከለኛው፣ በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ እና ሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ቅፅበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖር የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ገልጿል።
ከባለፉት የክረምት ወራት ጀምሮ መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ ባገኙት በእነዚህ አካባቢዎች በሚቀጥሉት ቀናትም ከመደበኛ በላይ የዝናብ መጠንና ስርጭት የሚኖር መሆኑን በኢንስቲትዩቱ የሚቲዎሮሎጂ ትንበያ ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ምርምር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አሳምነው ተሾመ (ዶ/ር) ለኢቢሲ ዶትስትሪም ገልጸዋል።
ይህ ሁኔታ በተለይ የጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ተጽዕኖ እንዳያደርስ አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄና ዝግጅት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ዶ/ር አሳምነው አሳስበዋል።
በሌላ በኩል በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ እና ደቡብ የሀገሪቱ ክፍሎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
#ኢቢሲዶትስትሪም #ሚቲዎሮሎጂ #የአየርሁኔታ
"ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እናረጋግጣለን!
ስማርት አዲስ አበባን እንገነባለን" በሚል ተግባራዊ ከተደረጉት መሠረታዊ ጉዳዮች አንዱ የፋይዳ ምዝገባ እንደመሆኑ በተጠናቀቀው በጀት አመት 3 ነጥብ 1 ሚሊዮን ነዋሪዎችን መመዝገብ መቻሉን በም/ ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አስታውቀዋል።
ቀጣዩን ቪዲዮ ይከታተሉ👉👉
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን ፈጣን፣ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ ከተከናወኑ ስራዎች በጥቂቱ.. በምስል ሲቃኝ:-…
See more
