es
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Ir al canal en Telegram
1 474
Suscriptores
Sin datos24 horas
-37 días
-2130 días
Archivo de publicaciones
በአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት ተጠሪ በሆኑ ተቋማት ለሚሰጡ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች የሚከተሉትን አድራሻዎች ይጠቀሙ! 1.የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ቢሮ አድራሻ፡- በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 1 በተለምዶ ፒያሳ እሪ በከንቱ ዮናታን ቢቲ ህንጻ ከ7ኛ ፎቅ ጀምሮ ነጻ የስልክ መስመር - 6199 ቴሌግራም፡- https://t.me/CGAACMA ዩቲዩብ ፡- https://www.youtube.com/@aacma-bu4zt ዌብሳይት፡- www.aacma.gov.et ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/profile.php?id=100064800963883 2.የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ቢሮ አድራሻ :- አዲሱ ገበያ ቱኒዝያ መንገድ ሸገር መናፈሻ ግቢ ውስጥ ነጻ የስልክ መስመር - 7533 ዌብ ሳይት (website): https://www.aacrrsa.gov.et የፌስቡክ (facebook): https://www.facebook.com/profile.php?id=100064083391686 ቴሌግራም (telegram): https://t.me/addisvaitalpress ፖስታ ሳ.ቁ (Box No)፡ 20320 3. የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ዋና ቢሮ አድራሻ ;-አራዳ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 10 አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ፊትለፊት ነጻ የስልክ መስመር :- 939 fdrmc1926@addisfire.gov.et ፌስቡክ - https://www.facebook.com/AADRMC1 4. የአዲስ አበባ ከተማ መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን የቢሮ አድራሻ:- አራዳ ክ/ ከተማ ወረዳ 1 በተለምዶ ፒያሳ እሪ በከንቱ አካባቢ ኤንሪኮ ኬክ ቤት ዝቅ ብሎ ዋስትና ንግድ ማዕከል 17ኛ ፎቅ ስ.ቁ 0111127775 ፌስቡክ ገፅ:-https://www.facebook.com/profile.php?id=61565439308107 EMail; AAESAA@aaca.gov.et Website:-https://aaesa.gov.et ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager?is_from_webapp=1&sender_device=pc Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et https://www.facebook.com/EEUOfficial

photo content
+5

ከለውጡ ወዲህ በተሰሩ በርካታ ስራዎች በአካባቢ ፅዳት ላይ ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡ ተገለፀ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ወረዳ 4 አያት አራት ኮንዶሚኒየም ግቢ አመራሮች፣ የፅዳት አምባሳደሮችና የተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት ሳምንታዊ የፅዳት ንቅናቄ ተካሂዷል ። በፕሮግራሙ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙላት ተገኝ እንደተናገሩት በከተማችን ከለውጡ ወዲህ በተሰሩ ስራዎች በፅዳት ላይ ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን ገልፀው የኮሪደር ልማት ስራዎች ለፅዳቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ተናግረዋል ። አክለውም ከከተማው ከሚመነጨው ቆሻሻ መልሶ የመጠቀም 12% መድረሱንና ለዜጎች ስራ ዕድል በመፍጠር ሀብት እንዲያፈሩ እድል ፈጥሯል ብለዋል። የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ባህር አሜ በበኩላቸው ህብረተሰቡ የራሱን የሚኖሩበትን ግቢ እና አካባቢያቸውን በማፅዳት ፅዱና ማራኪ በማድረግ ለነዋሪዎቿ ምቹ የሆነች ለሚ ኩራን ለመፍጠር ሁላችንም የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል ። Lemi Kura Communication ለሚ ኩራ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

photo content
+1

photo content
+9

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ ሚኒስትር አለሙ ስሜ(ዶ/ር) ጋር በመሆን የቃሊቲ የሀገር አቋራጭ እና የመካከለኛ ትራንስፖርት መናኻሪያ ግንባታን ጎብኝተዋል:: በ3 ነጥብ 9 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው የቃሊቲ የሀገር አቋራጭ እና የመካከለኛ ትራንስፖርት መናኻሪያ ለዋናው መንገድ ቅርብ ሲሆን በሰዓት 120 አውቶቢሶችንና 7ሺ 200 ተሳፋሪዎችን የሚያስተናግድ፣ 4ሺ800 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ሁለገብ ህንጻ፣ 13 የትኬት መቁረጫ ቢሮዎች፣ ካፍቴሪያዎች፣ ሱቆች፣ የስብሰባ አዳራሾች፣ የመመገቢያ ስፍራዎች፣ ከ1ሺ 130 በላይ የማረፊያ ወንበሮች፣ ከ8ሺ ካሬ ሜትር በላይ የአረንጓዴ ስፍራ እንዲሁም ከጎኑ የታክሲ ተርሚናል የተዘጋጀለት ማዕከል ነው:: የህዝብ ትራንስፖርት ስርዓትን ለማዘመን እየተከናወነ ባለው ተግባር ተሳፋሪዎች በጸሀይ እና በዝናብ ሳይንገላቱ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማስቻል መናኻሪያዎችን ለማዘመን በሚሰራው ስራ የአቃቂ መናኻሪያ የኤሌክትሮኒክስ የትኬት መቁረጫ ስርዓትን ተግባራዊ ያደረገ ሲሆን ለሌሎች ሞዴል በሚሆን ደረጃ የተገነባ ነው::

photo content
+5

የኮሪደር ልማት የእሳትና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀንስ አድርጓል በመዲናዋ የኮሪደር ልማት በተሰራባቸው አካባቢዎች የእሳትና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች የመከሰት ምጣኔ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና ድንገተኛ አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ኮማንደር አሕመድ መሐመድ ገለጹ፡፡ ኮሚሽነር ኮማንደር አሕመድ መሐመድ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት፤ በመዲናዋ እየለሙ የሚገኙ የኮሪደርና የወንዝ ዳር ልማቶች የአዲስ አበባን ገጽታ ከመቀየር ባሻገር በርካታ ጠቀሜታዎች እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ የኮሪደር ልማቱ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎችን በመከላከል እና ፈጥኖ ምላሽ በመስጠት ረገድ አዎንታዊ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝም አንስተዋል፡፡ ከዚህ ቀደም የመዲናዋ በርካታ ስፍራዎች ለእሳትና ጎርፍ አደጋ ተጋላጭ የነበሩ ስፍራዎች የኮሪደር ልማትን ተከትሎ ከዚህ ስጋት ነጻ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ በተደጋጋሚ ለሚከሰቱ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች የቤቶች ማርጀትና ተጠጋግቶ መሰራት፣የኤሌክትሪክ መስመሮች ዝርጋታ መደራረብ እና በወንዞች ዳርቻ የመኖሪያ ቤቶችን መገንባት በቀዳሚነት የሚነሱ ምክንያት መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ እነዚህ ለአደጋ አጋላጭ የሆኑ መሰረተ ልማቶች በአዲስ መልክ መሰራታቸውን ተከትሎ በከተማዋ የአደጋ ምጣኔ በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ መቻሉን ነው የተናገሩት፡፡ የብስክሌተኛ፣ የሰው እና የመኪና መንገዶች ተለይተው መሰራታቸው የኮሪደር ልማቱ ባልደረሰባቸው አካባቢዎች አደጋዎች ሲያጋጥሙ ፈጣን መተላለፊያ ሆነው በማገልገል አደጋውን በመቀነስ በኩል ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሆነ አንስተዋል፡፡ አያይዘውም ከዚህ በፊት በተለይ የእሳት አደጋ በሚከሰትበት ወቅት ተሽከርካሪዎች ውሃ ተመላልሰው ለመቅዳት ረዥም ርቀት መጓዝ ይጠበቅባቸው እንደነበር ያስታወሱት ኮሚሽነሩ፥ የኮሪደር ልማቱን ተከትሎ በርካታ የውሃ መቅጃ ሐይድራንቶች በአካባቢው መሰራተቻውን ተናግረዋል፡፡ በከተማዋ ረዥም ርቀት መጓዝ ሳይጠበቅባቸው በአቅራቢያ ውሃ ተመላልሰው በመቅዳት ፈጣን ምላሽ እንዲሰጡ እንዳስቻለ አስታውቀዋል፡፡ የኮሪደር ልማቱ ተደራሽ በሆነበት አካባቢ የሚኖሩት አቶ ጌታቸው ረጋሳ በበኩቸው፥ከዚህ በፊት የቤቶች ግንባታ እጅግ የተጠጋጋና ለአደጋ አጋላጭ ስለነበር ተደጋጋሚ አደጋዎች ይከሰቱ እንደነበር አውስተዋል፡፡ የእሳት አደጋ ተሽከርካሪዎች አደጋውን ለመቆጣጠር በትራፊክ መጨናነቅ ምክንያት ተሽከርካሪዎች ይዘገዩ እንደነበር አስታውሰው፥ የኮሪደር ልማቱ በመሰራቱ የእሳት አደጋ ተሽከርካሪዎች ፈጣን አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን መታዘባቸውን ገልጸዋል። መንገዶች ደረጃቸውን ጠብቀው በመሰራታቸው፤ከዚህ ቀደም የሚደርሱ አደጋች መቀነሳቸውን የተናገሩት ደግሞ ሌላዋ አስተያየት ሰጪ ወይዘሮ ስሜነሽ ቤልጅግ ናቸው፡፡ ማሾ አየለ በበኩላቸው፥ የኮሪደር ልማቱ አዲስ አበባ እንደ ስሟ አዲስ ያደረገ እኛንም ከተለያዩ አደጋዎች የታደገ ነው ብለዋል፡፡ ሚያዝያ 2/ 2017 #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #ኮሪደርልማት #ውበት #ገጽታ

ስማርት እየሆነች ለመጣችው መዲናችን አዲስ አበባ የሚመጥን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው የስማርት መሠረተ ልማት ዝርጋታ አካል የሆኑ ዘመናዊ የመብራት ፖሎችን አስመልክቶ በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ከአዲስ ሚዲያ ኔት ወርክ ጋር ያደረጉትን ቃለምልልስ በቀጣዪ ቪዲዮ ይከታተሉ 👉👉 ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተሰጠ ማሳሰቢያ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ዛሬ ሐሙስ ሚያዝያ 2 ቀን 2017 ዓ.ም ከስምንት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ለአንድ ሰዓት የሚቆይ የድንገተኛ አደጋ ምላሽ አሰጣጥ የሙሉ አቅም ልምምድ በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ ይህ ልምምድ የድንገተኛ አደጋ ምላሽ አሰጣጥ እና የእርዳታ መስጫ ቁሳቁሶች ብቁነትን፣ በአደጋ ጊዜ የሚኖር የመልዕክት ልውውጥ ፍሰትን እንዲሁም በእርዳታ ሰጪዎች መካከል የሚኖረውን ቅንጅት እና ጥምረት ለመፈተሸ ይረዳል፡፡ በተጨማሪም ልምምዱ ከአውሮፕላን ማረፊያው ውጪ የሚገኙ እርዳታ ሰጪዎች በአውሮፕላን ማረፊያው አቀማመጥ እና በውስጡ ከሚገኙ የእርዳታ መስጫ ቁሳቁሶች ጋር እንዲተዋወቁ በማድረግ በእውነተኛ ድንገተኛ አደጋ ወቅት የእርዳታ አሰጣጥ ሂደቱ የተፋጠነ እንዲሆን በማስቻል ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡ ይህንንም ለመፈተሽ በወቅቱ በከተማው ሆስፒታሎች እና በአውሮፕላን ማረፊያው መካከል የእርዳታ መስጫ ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ይኖራል፡፡ ስለሆነም ይህ እንቅስቃሴ የልምምዱ አካል መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች እንዲረዱልን በታላቅ አክብሮት እንገልፃለን። አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መሰል ልምምዶችን በየሁለት ዓመት አንድ ጊዜ ያከናውናል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

መዲናችን አዲስ አበባ ከመቼውም ጊዜ በላይ ፅዱ፣ሳቢ እና ማራኪ እየሆነች ትገኛለች! በውቧ ከተማችን ታታሪ ልጆቿ ፅዳትን ባህላቸው ያደርጋሉ! የመብራት እና ሌሎች መሠረተ ልማቶቿንም ከስርቆትና ከውድመት ይታደጋሉ! "ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዳሉት አበው ስንተባበር ሁሉን እንችላለን! ማህበረሰባችንን ለበጎ ስራ ለማንቀሳቀስ ደግሞ የተፅእኖ ፈጣሪዎች ድርሻ የጎላ ነው!

photo content
+4

የድህረ እውነት ዘመንን በእውቀት እና በእውነት ! በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት የህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ በከተማዋ ከሚገኙ የተለያዩ ተቋማት ለተውጣጡ የሚዲያ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም በጎ የማህበረሰብ አንቂዎች "የድህረ እውነት ዘመንን በእውቀት እና በእውነት" በሚል ርዕስ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀምሯል። በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በስልጠናው መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ዘመኑ መረጃዎች በቴክኖሎጂ ተቀምመው እውነቱንና ሀሰቱን ለመለየት አስቸጋሪ በሚሆን አግባብ የሚሰራጩበት የድህረ እውነት ዘመን መሆኑን በአግባቡ በመረዳት ይሄን የሚመጥን ዝግጁነትን መላበስ ይገባል ብለዋል ። ብልፅግና ፓርቲ ሀገር በቀል በሆነ የመደመር እሳቤ የሀገራችን ትርክት በቅጡ ተረድቶ ፣ ለሀገራችን የሚበጀውን የብሔራዊነት አሰባሳቢ ትርክት ለመገንባት እየተረባረበ እንደሚገኝ ያወሱት አቶ ሞገስ ይህንን ሀቅ በእውቀት እና በክህሎት ማሳወቅ እንደሚገባ ገልፀዋል። የሚዲያና ህዝብ ግንኙነት አመራሩና ባለሙያው ሁሌም ለአዳዲስ እውቀቶች እራስን ክፍት ማድረግ እንደሚገባ ያስረዱት ኃላፊው በዛሬው ዕለት መሰጠት የጀመረው ስልጠናም ተጨማሪ አቅም እንደሚፈጥር አስረድተዋል። በውጤታማ ኮሙኒኬሽን የሀሰት መረጃን በእውነትና በእውቀት ማሸነፍ መቻል ለሀገራችን ስኬታማ የለውጥ ጉዞ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ያመላከቱት አቶ ሞገስ አዲስ አበባን የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ ለምናደርገው ጥረትም ጉልህ አስተዋፅዖ እንደሚያበረክት አስረድተዋል። የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት የህዝብና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ በስልጠናው ላይ እንደተናገሩት የሀገራችንን የለውጥ ጉዞ ለማጠናከር እና የህዝባችንን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ዘመኑን የዋጀ ፣ የድህረ እውነት ዘመንን የሚመጥን እውቀትና ክህሎት በመያዝ ሀሰተኛ መረጃዎችን መመከትና እውነተኛ መረጃዎችን ተደራሽ ማድረግ ይገባል ብለዋል። ዘመኑ ሀሰተኛና ስሜት ቀስቃሽ መረጃዎች የሚለቀቁበት የመረጃ ፣ የውሳኔ እንዲሁም የእውቀት ግራ መጋባት የሚስተዋልበት የድህረ እውነት ዘመን መሆኑንም አስገንዝበዋል። ፊታችን ብሩህ ፣ መንገዳችን ቀናህ ነው ያሉት ኃላፊው ስራዎችን በስኬታማ ኮሙኒኬሽን በመደገፍ ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በእውቀትና በክህሎት ብቁ አመራሮችን እና ባለሙያዎችን ለማፍራት አበረታች ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ የጀመረውን ስልጠና ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚሰጥ ሲሆን በሌሎችም ክልሎች እንደሚሰጥ ተመላክቷል። በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ/ቤት #aa_prosperity

አዲስ አበባን ፅዱ፣ውብ፣ምቹ ማራኪና በአለምዓቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነቷን ለማሳደግ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ውጤት እያመጡ መሆናቸው ተገለፀ።… See more

photo content
+3

photo content
+9

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 4 አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ ****************** የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በዛሬዉ እለት በ4ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ስብሰባው አራት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አስተላልፏል። በዚህም መሰረት፤- 1ኛ. በፕላንና ልማት ቢሮ እና በትምህርት ሚኒስቴር በጋራ ተጠንቶ የቀረበዉን ከአራት ኪሎ እስከ ሽሮ ሜዳ ያለዉ አካባቢ የዩኒቨርሲቲ መንደር በመሆን በአካባቢዉ ያሉትን አገልግሎቶች አካቶ የትምህርት፣ የምርምር፣ የእውቀት እና የባህል ልህቀትን በከተማዋ ለማሳደግ በሚያስችል አግባብ የቀረበ በመሆኑ፤ ካቢኔዉ ተወያይቶ የመንደር ምስረታውን ዉሳኔ አፅድቋል፡፡ 2ኛ. የምግብ ስርዓትና ኒዉትሪሽን ምክር ቤት ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ ዉሳኔ አስተላልፏል:: 3ኛ. የአደጋ ስጋት አመራር ምክር ቤትና የአደጋ ዝግጁነት ፈንድ ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ላይ ካቢኔዉ ተወያይቶ ዉሳኔ አስተላልፏል፡፡ 4ኛ. በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቀረበዉን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸዉ ፕሮጀክቶች፤ የመሬት ምደባ ጥያቄዎች አስመልክቶ ካቢኔዉ ተወያይቶ ዉሳኔ አስተላልፏል፡፡