es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Ir al canal en Telegram
1 474
Suscriptores
Sin datos24 horas
-37 días
-2130 días
Archivo de publicaciones
photo content
+3

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እሕመድ እና ልዑካቸው ዛሬ ከቀትር በኋላ አንካራ ቱርክ ገብተዋል። ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በጽሕፈት ቤታቸው አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን ሁለቱ መሪዎች ከልዑካን ቡድናቸው ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል:: #PMOEthiopia

የካዛንቺስ ልማት ተነሺዎች በገላን ጉራ!

ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ

photo content
+1

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ሁለት ወራት ከ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የ"ፋይዳ" ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ አከናውነዋል: በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ሁለት ወራት ከ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የ"ፋይዳ" ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ማከናወናቸውን የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡ የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የቴክኖሎጂ ዘርፍ ኃላፊ በረከት በቀለ እንደገለፁት "ፋይዳ" ዲጂታል መታወቂያ ያለውን ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ በተመለከተ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ በመፍጠር ተደራሽ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሁሉም ወረዳዎች በሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት ጽህፈት ቤት አገልግሎቱ እየተሰጠ መሆኑን የገለጹት አቶ በረከት በተጨማሪም በትምህርት ቤቶች እና በመኖሪያ አካባቢዎች አገልግሎቱ ተደራሽ እየሆነ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በዚህም የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም እና ሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ በጋራ በሰሩት ስራ በመዲናዋ ባለፉት ሁለት ወራት ከ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የ"ፋይዳ" ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ማከናወናቸውን ገልፀዋል፡፡ በተለየ ሁኔታ በተደረጉ የንቅናቄ ስራዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ የህብረተሰቡ ግንዛቤ እየጨመረ በመምጣቱ አመርቂ ውጤት ማምጣት መቻሉንም አንስተዋል፡፡ በቀጣይም ዜጎች በተለያዩ ተቋማት አገልግሎት ለማግኘት ሲፈልጉ "ፋይዳ" ዲጂታል መታወቂያን መያዝ ቅድመ ሁኔታ እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡ የምዝገባ ስርዓቱን ለመከታተል እንዲሁም የ"ፋይዳ" ዲጂታል መታወቂያ ቁጥር በሚጠፋበት ጊዜ በፋይዳ ዌብሳይት (ID.et) ስልክ ቁጥር በማስገባት ብቻ የጠፋውን ቁጥር መልሶ ማግኘት እንደሚቻል ተመላክቷል፡፡ ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

photo content
+7

ወጣቶችን ያማከለ የጸረ ሙስና ትግል የነገ ስብዕናን ይገነባል!" በሚል መሪ ቃል በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ21ኛ ጊዜ ፤በሀገራችን ደግሞ ለ20ኛ ጊዜ የሚከበረውን የጸረ ሙስና ቀን ምክንያት በማድረግ ለሁሉም የምትመች እና ከሙስና ስጋት ነፃ የሆነች ከተማን መገንባት በምንችልባቸው መንገዶች ዙሪያ ከከተማችን ነዋሪዎች ጋር ውይይት አድርገናል:: ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

photo content
+8

የተረፈ ምርትና ተያያዥ አዋኪ ድርጊቶች ላይ እርምጀ መውሰድ መጀመሩ ተገለፀ፡፡ የክፍለ ከተማው ስራ አስኪያጅና ደንብ ማስከበር ፅህፈት ቤት በጋራ በመሆን በክፍለ ከተማው ሁሉም ወረዳዎች በተረፈ ምርትና ለመንገድ ደህንነት፣የአካባቢ ውበትንና ፅዳትና አዋኪ በሆኑ ድርጊቶች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን የሁለቱ ፅህፈት ቤት ኃላፊዎች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡ የክፍለ ከተማው ስራ አስኪያጅ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዳኛቸው አበበ በክፍለ ከተማው ሁሉም ወረዳዎች ከደንብ ማስከበር ፅህፈት ቤት ጋር በመሆን የግንባታ ተረፈ ምርቶች፤ያለ አግባብ ቆሻሻ በሚጥሉ ግለሰቦችና ተቋማት፣ፍሻስ በመንገድ ላይ የሚለቁ ድርጅቶች እንዲሁም ባልተፈቀደ ቦታ ለረጅም ጊዜ ከቆሙ መኪኖች ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የማስተካከያ እርምጃ በመውሰድ ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ ኃላፊው አያይዘውም ተግባራቱ ከመደበኛ ስራዎች ጎን ለጎን እየተከናወኑ እንደሚገኙ አስታውቀው አዲስ አበባ እንደ ስሟ አዲስ፣ ውብና ፅዱ ለማድረግ የሚሰራውን ንቅናቄ ታሳቢ በማድረግ እንዲሁም በቀጣይ በመዲናችን የሚካሄደውን የአፍሪካ ህብረት ስብሰባዎችን አካባያችንን ፅዱ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡ የክፍለ ከተማው የደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሙልጌታ ጎንፋ በበኩላቸው ቅንጅታዊ አሰራርን ከማጠናከር አኳያ ከፍተኛ ስራዎች እየተሰሩ እንዳሉ ገልፀው የመንገድ ድህንነት ስራዎች ማስጠበቅ፤ህገ-ወጥ ማስታወቂያና መደበኛ የደንብ መተላለፍና ተያያዝ ህገወጥ ተግባራትን ላይ አርምጃዎች እየተወሰዱ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ኃላፊው በመግለጫቸው ህግን የማስከበርና ክፍለ ከተማዋን ውብና ማራኪ ለማድረግ በተሰሩ ስራዎች ላይ የሚያውኩ ተግባራትን ለመከላከል ህግን የማስከበር ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉና ለዚህም ህብረተሰቡ ተባባሪ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል። ህዳር 30 /2017 Kolfe Keranio Communication /ኮልፌ ቀራኒዮ

photo content
+8

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የኡራኤልና የፒኮክ አካባቢ የግል ባለይዞታ የወንዝ ዳር ልማት ተነሺዎች የካሳ ክፍያ መርሐ ግብር እንደቀጠለ ነው። ተነሺዎቹ በግል ይዞታ የሚኖሩ ሲሆን ከዚህ በፊት የልማት ተነሺዎች ግልፅና ይፋዊ በሆነ መልኩ እጣ ምትክ ቦታ እጣ ማውጣታቸው ይታወቃል። በዛሬው እለትም የግል ባለይዞታዎች በቦታና ቤት ግምታቸው መሰረት የካሳ ክፍያ እየወሰዱ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን ነገን ጨምሮ የካሳ ክፍያው የሚቀጥል መሆኑም ተገልጿል። የከተማ አስተዳደሩ በኮሪደር ልማት ከተማዋን ከማስዋብ ባሻገር የህዝቡን አኗኗር ባህል እየቀየረ ስለመሆኑ የልማት ተነሺዎቹ እጣ አወጣጥና የካሳ ክፍያ አንዱ ማሳያ መሆኑን በመርሐ ግብሩ ላይ ተገልጿል።

photo content
+2

photo content
+9

ዛሬ የገላን ጉራ የመኖሪያ እና የተቀናጀ የልማት መንደርን መርቀን ከካዛንቺስ በልማት ለተነሱ ነዋሪዎቻችን አስረክበናል። የኢትዮጵያ መልክ የሆነችው አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ አበባ ለማድረግ በገባነው ቃል መሰረት፣ መሰረተ ልማት ከማሟላት በተጨማሪ የሰው ህይወትን ለማሻሻል እና የነዋሪዎቻችንን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትልቅ ትኩረት ሰጥተን በመስራት ላይ እንገኛለን። ነዋሪዎቻችንን ካረጀ እና ለመኖር ምቹ ካልሆነ የካዛንቺስ አካባቢ እንዲወጡ አድርገን ለኑሮ ምቹ የሆነ ቤት እና አካባቢ እንዲገቡ ያደረግን ሲሆን በዚህም የሰው ህይወትን የመቀየር ስራን ሰርተናል። ከካዛንቺስ አካባቢ ለልማት በፈቃደኝነት የተነሳችሁ እና ከጎናችን የቆማችሁ ነዋሪዎችን ስለ ትዕግስታችሁ እና ድጋፋችሁ እያመሰገንኩ፣ ይህ ስራ እንዲሳካ ህግ እና አሰራሩን በመቀበል ቦታውን በፈቃደኝነት ለልማት የለቀቃችሁ የአካባቢው አርሶ አደሮችንም ላመሰግናቸው እወዳለሁ። ይህን ታላቅ ስራ በአጭር ጊዜ ውስጥ ገንብታችሁ ያጠናቀቃችሁ ኮንትራክተሮችን፣ አማካሪ ድርጅቶችን፣ ድጋፍ ያደረጋችሁ አካላትን፣ ያስተባበራችሁ አመራሮችን እንዲሁም የክፍለከተማው አመራሮችን በራሴ እና በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የረዳን ፈጣሪ ይመስገን! “አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ አበባ እናደርጋታለን” ስንል የነዋሪዎቿን ህይወት እና አኗኗር ማሳመርንም የሚያካትት ነው። ለዚህ አንዱ ማሳያ የሆነው ለካሳንችስ ልማት ተነሺዎች በገላን ጉራ የገነባነዉን ማዕከል ነዉ። ዛሬ አገልግሎት የምናስጀምረው የገላን ጉራ የመኖሪያ እና የተቀናጀ የልማት መንደር በውስጡ:- 👉በ1200 መኖሪያ ቤቶች 6500 ነዎሪዎችን የያዘ መኖሪያ መንደር ነው። 👉1.6 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለዉ የአስፋልት መንገድ አለው። 👉ከ20 በላይ አውቶቡሶችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚያስችል ተርሚናል አለው። 👉በ2 ወር ጊዜ ዉስጥ የተገነቡ ከቅድም አንደኛ ደረጃ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ያሉ ትምህርት ቤቶች ከነምገባ ማዕከሉ ይዟል። 👉በ3 ሺፍት ለ270 እናቶች የስራ እድል የፈጠረ የእንጀራ መጋገርያ ፋብሪካ አለው። 👉500 አረጋዉያን እና አቅመ ደካሞችን በቀን አንድ ጊዜ መመገብ የሚያስችል የምገባ ማዕከል አለው። 👉በቀን 60 ሺህ ዳቦ የማምረት አቅም ያለው የዳቦ ፋብሪካ እና የዕህል ወፍጮዎችን ይዟል። 👉ደረጃውን የጠበቀ የህጻናት መጫወቻ እና የህጻናት ማቆያ አለው። 👉ሁለት የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እንዲሁም አረንጓዴ ቦታዎችና መናፈሻዎች ተገንብተዋል። 👉በቋሚ እና በጊዜያዊነት ለ1646 ነዋሪዎች የስራ እድል መፍጠር ተችሏል። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ