1 474
Suscriptores
Sin datos24 horas
-37 días
-2130 días
Archivo de publicaciones
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሁለተኛ ምዕራፍ ኮሪደር የስራ አፍፃፀም ግምገማ ::
ዛሬ ምሽት ይጠብቁን
ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ ማዋልን- ከጃፓን
ከ10 ዓመት በኋላ በአዲስ አበባ ደረቅ ቆሻሻን ሙሉ በሙሉ ወደ መልሶ መጠቀም ዑደት ውስጥ ለማስገባት እየተሰራ ነው…
ዛሬ ከሰዓት በኋላ ከኩባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቡሩኖ ሮድሪጌዝ ፓሪላ ጋር ተገናኝተን በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
መዲናችን አዲስ አበባ በፅዳቷ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያመጣች ያለችውን ለውጥና በአህጉሩና በአለም ዓቀፍ ደረጃ ለዘርፉ እየተሰጡ ያሉ እውቅናዎችን በዘላቂነት ለማስቀጠል በየደረጃው ያለው አመራር በላቀ ቁርጠኝነት መስራት እንዳለበት በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አስገነዘቡ።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ይህን ያስገነዘቡት የአለም ዓቀፍ የፅዱ ከተሞች ተሞክሮ ለዘመናዊ እና ስማርት አዲስ አበባ ያለውን ፋይዳ አስመልክቶ 250 ለሚሆኑ የሁሉም ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች ስራ አስኪያጅና ጽዳት ጽ/ ቤት አመራሮች ባቀረቡት ገለፃ ነው።
አያይዘውም መዲናችን አዳስ አበባ ከለውጡ ወዲህ ጽዱ፣ውብ ማራኪ፣ሳቢና ለኑሮ የምትመች በማድረግ ረገድ በተሰሩ ስራዎች እምርታዊ ለውጥ ማምጣቷ በሁሉም ዘንድ እውቅና እየተሰጠው እንዳለ በመጥቀስ በቅርቡም በጃፓን ዮካሃማ በተካሄደ መድረክ ላይ በመዲናችን ፅዳት ረገድ የመጣው ለውጥ አድናቆት እንደተቸረው አውስተው በመድረኩ ከቀረቡ የፅዱ ከተሞች ልምድ ከጃፓን ተሞክሮ መዲናችን አዲስ አበባ የምትቀሰመውን ልምድ አቅርበዋል።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ከጃፓን የጽዳት ልምድ ለዘመናዊ እና ስማርት አዲስ አበባ የሚወሰደው ተሞክሮ ህጻናት ጽዳትን ባህል እንዲያደርጉ ለዘላቂነቱ ያለው አስተዋፅኦና ፅዳት የህዝብ ባህል እንዲሆን በቁርጠኝነትና በልዩ መሰጠት ያከናወኑት ተግባር ተሞክሮ የሚቀሰምበት ነው ብለዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎችም የከተማችንን የጽዳት ተምሳሌትነት ቀጣይነትን ለማረጋገጥ የቀረቡ ተሞክሮዎች እንደ ከተማችን መተግበር ያለባቸውና በትጋት ሊፈፀሙና ሊተገበሩ የሚገባቸው ናቸው ሲሉ ገልፀዋል።
በመጨረሻም እንጅነር ወንድሙ ሴታ ሁሉም አመራር የመደበኛና የንቅናቄን ስራዎች አመጋግቦ የአመራር ሀላፊነቱንና ተግባራትን በአግባቡ መወጣት እንዳለበት አሳስበው የማዘጋጃቤታዊ አገልግሎት ስራዎችን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመከወን የባለድርሻ አካላትንና የህብረተሰቡን ተሳትፎ ማጠናከር እንደሚገባም በአጽንኦት ገልፀዋል።
አክለውም ፅዱ ሞዴል ቀጠና እና ፅዱ ሞዴል ወረዳ ፈጠራ ላይ በ7/24 በልዩ ሁኔታና ትኩረት መሠራት አለበት ብለዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ላለፉት ሁለት ቀናት ከሁሉም የኮሪደር ልማት አስተባባሪዎች ጋር በመሆን በ2ኛ ምዕራፍ በከተማችን እየለሙ የሚገኙ ስምንት ኮሪደሮችን የስራ አፈጻጸም ተዘዋውረን ገምግመናል።
የ 2ኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ስራ 135 ኪ.ሜ ርዝማኔ ያለው የመንገድ ግንባታ፣ 42 ኪ.ሜ የሚረዝም የወንዝ ዳርቻ ልማት ስራ፣ 431 ሄክታር የሚሸፍን የአረንጏዴ ልማት ስራ፣ በከተማችን ያለውን የትራንስፖርት ስርዓት ለማዘመን ከምንሰራው ስራ በተጨማሪ 23,320 በላይ መኪኖችን የማስቆም አቅም ያለው የፓርኪንግና ተርሚናሎች ግንባታ፣ 112 የህዝብ የመጸዳጃ ቦታዎች ግንባታ፣ 2669 ህንጻዎች እድሳት፣ የህጻናት መጫወቻ ሜዳዎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ የህዝብ መዝናኛ ፕላዛዎች፣ የእግረኛ እና የብስክሌት መንገዶችን ያካተተ ሲሆን ከ 62 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ የከተማችን ነዋሪዎች ደግሞ የስራ እድልን የፈጠረ ሰፊ ስራ ነው::
ከተማውን በመበከል የህዝቡን ጤና በመጉዳት ከፍተኛ አሉታዊ ጉዳት ሲያደርሱ የነበሩትን ህግ እና ስርዓት አዉጥተን የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓት በከፍተኛ ደረጃ እየተገበርን ነዉ። የወንዞችን ብክለት በመከላከል በኩል ጽዱ አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ለመፍጠር የብክለት መከላከል ህግ ህብረተሰባችን መቀበሉን እና የየተገበረዉ መሆኑን በጉብኝታችን ወቅት ተመልክተናል::
በተሰጣቸው ጊዜ ገደብ ውስጥ ያልገነቡ እና የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓታቸውን ያላስተካከሉትን በመቅጣት ላይ የምንገኝ ሲሆን ከቅጣቱ በላይ የምንፈልገው ህዝባችን በዋናነት ለራሱ ጤና ሲል የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓቱን እና ብክለት መከላከልን እንዲተገብር በመሆኑ ሁላችንም ለዚህ ርብርብ እንድናደርግ ጥሪ አቀርባለሁ::
ያቀረብንላቸውን ጥሪ በመቀበል ህንጻዎችን በማደስ፣ ቀለም በመቀየር እና በከተማዋ ስታንዳርድ መሰረት መብራት በመዘርጋት እያገዙን የሚገኙ የከተማችን ነዋሪዎች፣ ባለሀብቶች እንዲሁም የመንግስትና የግል ተቋማትን ጨምሮ ሙያዊ እና ቁሳዊ ድጋፍ እያደረጉልን የሚገኙ ነዋሪዎቻችንን በራሴ እና በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ::
በቀሪ ጊዜያት ልዩ ክትትል በማድረግ ቶሎ መጠናቅ ያለባቸውን ስራዎች መጨረስ፣ መደገፍ የሚገባቸውን ደግሞ እየደገፍን ህዝባችንን በታማኝነት ለማገልገል በገባነው ቃል መሰረት 2ኛውን ምዕራፍ የኮሪደር ልማት አጠናቅቀን ለግልጋሎት ክፍት የምናደርግ ይሆናል::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የሐረር አቅጣጫና ተስፋ
በሐረር ከተማ የተጀመረውን የኮሪደር ልማትና አካባቢውን ለኑሮና ለቱሪዝም ምቹ የማድረግ እንቅስቃሴ ተመልክቻለሁ። በከተማዋ የተጀመረው ሥራ ዕምቅ ዐቅምን ማወቅ፤ አካባቢያዊ ጸጋዎችን ለብልጽግና መጠቀም፤ ማኅበረሰብን ማስተባበር እና የአመራር ቁርጠኝነት ሲደመሩ - ለውጥ እንዴት እንደሚመጣ ማሳያ ነው።
ሐረርን እንደ ተምሳሌት በመውሰድ አካባቢዎቻችን ለመቀየር የሚያስችሉ ሰባት ልምዶች እና አቅጣጫዎች ቀጥለው ቀርበዋል።
1. የአመራር ቁርጠኝነት፦ ሐረርን በዋናነት የቀየራት የአመራር ቁርጠኝነት ነው። ዓመታዊ ገቢያቸው ከሌሎች ያነሰ ነው። ለሥራው ያዋሉት በጀትም ዝቅተኛ ነው። ቀሪውን ያሟሉት አመራሩ ቁርጠኛ ሆኖ ቀን ከሌት በመሥራት እና ዐቅሙን አሟጥጦ በመጠቀም ነው። ሌሎች ከዚህ መማር አለብን።
2. ታሪካዊ ሀብትን ዐውቆ ማልማት፦ ሐረር እና አካባቢዋ ከሺ ዓመታት የዘለለ ታሪካዊ ሀብት አላቸው። ይሄንን ሀብት በማወቅ እና በመለየት ለጉብኝት ምቹ አድርገውታል። መንገድ ተሠርቷል፤ ሙዝየም ተገንብቷል። የአካባቢውን ንጽሕና የመጠበቅ ሥራም እየተሠራ ነው። ይሄ ለሌሎችም ትምህርት የሚሆን ነው።
3. ጥንታዊ አካባቢን አናብቦ ማዘመን፦ የሺ እና የመቶ ዓመታት ታሪክ ያላቸው የኢትዮጵያ ከተሞች እንዴት መቀየር እንዳለባቸው ሐረር ተምሳሌት ናት። ጀጎል ተለውጧል። የውስጥ ለውስጥ መንገዱ ተዘርግቷል። ግንቡን ለመጠገን የተሠራው ሥራ፣ የመብራት ሥራው፤ ጥንታዊው ከተማ የወዳደቁ ቤቶች መከማቻ እንዳይሆን እየተሠራ ያለው ሥራ፣ ጀጎልን ሁሌ አዲስ እንድትሆን አድርጓታል። ያረጁና ያፈጁ ከተሞች እንዴት እንደሚቀየሩ መማሪያ ነው።
4. አካባቢያዊ ልዩ ጸጋን ለቱሪዝም መጠቀም፦ ሐረር ሰዎችና የዱር እንስሳት ተግባብተው የሚኖሩባት ከተማ ናት። ለዚህ አንዱ ማሳያ የጅብ ትርዒት ነው። ከመቶ ዓመታት በፊት ጀምሮ ሐረርን የጎበኙ ጸሐፍት ይሄንን ትርዒት አድንቀው ጽፈዋል። ይሄንን ትርዒት ወደ ዘመናዊ የቱሪስት መዳረሻነት ለመቀየር በመደመር ትውልድ መጽሐፍ ሽያጭ መነሻነት የጅብ ትርዒት ማሳያ አምፊ ቴአትር በሐረር ተገንብቷል። በየአካባቢያችን ያሉትን ልዩ ጸጋዎች በዚህ መንገድ ነው ዐውቀን ማልማት ያለብን።
5. ለኮሪደር ሥራ አካባቢያዊ ዕውቀትን መጠቀማቸው፦ በአንዳንድ ከተሞች የኮሪደር ልማት በውድ ዋጋ የሚገኙትን የመንገድ መብራቶች ሐረሮች በአካባቢያቸው በማምረት በርካሽ አግኝተዋቸዋል። የመንገድ መብራትን ለመጠገን ያለውን ችግር በሚፈታ መልኩ ሐረሮች የመንገዶቻቸውን መብራቶች በርካሽና በተሻለ መንገድ ሠርተዋል። ሥራን ውድ የሚያደርገው ሀብትን እና ዕውቀትን በሚገባ አለመጠቀም ነው።
6. በአካባቢ ጸጋ አካባቢን ማስዋብ፦ ሐረር ላይ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች የተሠሩት በሐረር ድንጋይ ተጠርበው ነው። ይሄ ተግባር አዱሱ ግንባታ ከነባሩ ጋር እንዲጣጣም አድርጓል። ለአካባቢው ወጣቶችም የሥራ ዕድል ፈጥሯል፤ በጥቂት ወጪ ብዙ ሥራ ለመሥራትም አስችሏል፤ የዕውቀት ሽግግር እንዲኖር አድርጓል። ዘወር ዘወር ብለን መሬቱን እንየው። ለልማት የሚውል ብዙ ሀብት አለው።
7. አስፍቶ ማሰብ፦ ሐረር በቆዳ ስፋት ከብዙ ክልሎች ያነሰች ናት። ታሪካዊ ከተማ በመሆኗም የነዋሪዎች መጨናነቅ እና የቦታ ጥበት አለ። ጠባብን ቦታን የሚያሰፋው ሰፊ አመለካከት ነው። ሩቅን የሚያቀርበው አርቆ ተመልካችነት ነው። የሐረር የኮሪደር ልማት ሰፊ የሆነው በዚህ ዕይታ ነው። በዚህ ዕይታ የተሠሩት የእግረኛ መንገዶች፣ ፓርኮች፣ አምፊ ቴአትሮች፣ አረንጓዴ ሥፍራዎች፣ ወዘተ. አስደናቂ ናቸው። አስፍቶ ማሰብ ጥቁቱን ያበዛል፣ ሩቁን ያቀርባል።
እነዚህ ሁሉ ሥራዎች ሀብት እንዲያመነጩ ምቹ ሆቴሎች ያስፈልጋሉ። ኢንቨስተሮችን ስቦና አበረታትቶ ንግዱን ማቀላጠፍ ይገባል።
በከተማ የተሠሩ ሥራዎች ዘላቂ እንዲሆኑ በገጠሩ የሌማት ትሩፋት ይበልጥ መስፋፋት አለበት። ዘመናዊ ግብርናና የግብርና ተዋጽዖ ማቀነባበሪያዎች እንዲፈጠሩ እንትጋ። የአካባቢያችንን ገበያዎች እናነቃቃቸው።
ከዚህ ጎን ለጎን የሕዝቡን የመለወጥ ፍላጎት፣ የሰላም ፍላጎት እና ታታሪነት እንደ ሀብት በመውሰድ ሕዝብ የሚያረካ አገልግሎት እንስጥ።
ሐረሮች በርቱ። ግን ገና ብዙ ይቀረናልና ረክታችሁ እንዳትቆሙ። ሕዝብን እያወያያችሁና እያስተባበራችሁ ሐረርን ከዓለም ጋር ለማወዳደር እስክትችሉ ትጉ።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ (ዶ/ር)
ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ ማዋልን- ከጃፓን
ከ10 ዓመት በኋላ በአዲስ አበባ ደረቅ ቆሻሻን ሙሉ በሙሉ ወደ መልሶ መጠቀም ዑደት ውስጥ ለማስገባት እየተሰራ ነው…
ዛሬ ከሰዓት በኋላ ከኩባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቡሩኖ ሮድሪጌዝ ፓሪላ ጋር ተገናኝተን በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
መዲናችን አዲስ አበባ በፅዳቷ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያመጣች ያለችውን ለውጥና በአህጉሩና በአለም ዓቀፍ ደረጃ ለዘርፉ እየተሰጡ ያሉ እውቅናዎችን በዘላቂነት ለማስቀጠል በየደረጃው ያለው አመራር በላቀ ቁርጠኝነት መስራት እንዳለበት በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አስገነዘቡ።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ይህን ያስገነዘቡት የአለም ዓቀፍ የፅዱ ከተሞች ተሞክሮ ለዘመናዊ እና ስማርት አዲስ አበባ ያለውን ፋይዳ አስመልክቶ 250 ለሚሆኑ የሁሉም ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች ስራ አስኪያጅና ጽዳት ጽ/ ቤት አመራሮች ባቀረቡት ገለፃ ነው።
አያይዘውም መዲናችን አዳስ አበባ ከለውጡ ወዲህ ጽዱ፣ውብ ማራኪ፣ሳቢና ለኑሮ የምትመች በማድረግ ረገድ በተሰሩ ስራዎች እምርታዊ ለውጥ ማምጣቷ በሁሉም ዘንድ እውቅና እየተሰጠው እንዳለ በመጥ… See more