1 474
Suscriptores
Sin datos24 horas
-37 días
-2130 días
Archivo de publicaciones
አዲስ አበባ በመዲናዋ እየተካሄደ ባለው አለምዓቀፍ ጉባኤ በሲቪል ምዝገባ እና የፋይዳ ስርዓት ላይ እየሰራች ያለውን ስራ ልምድ አቅርባለች
አዲስ አበባ እያስተናገደች ባለችው ዓለም ዓቀፉ የID4 Africa 11ኛ ጉባኤ በወሳኝ ኩነት እና በፋይዳ ምዝገባ ቅንጅታዊ ትግበራ ላይ የቅንጅት ልምዷን አቅርባለች።
የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ የሲቪል ምገባ ሽፋንን በማጠናከር ዘርፉን ለመለወጥ የተወሰደውን የከተማ አስተዳደሩ እርምጃ፣ ከፋይዳ ስርዓት ጋር ቅንጅት ለመፍጠር እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ፣ የከተማ አስተዳደሩ ቁርጠኝነት እንዲሁም የተገኘውን ውጤት በመድረኩ አካፍለዋል።
በጉባኤው ላይ ከ105 ሃገራት እንዲሁም ከ2300 በላይ ተሳታፊዎች በመታደም ላይ ይገኛሉ።
ግንቦት 12/2017ዓ.ም
Addis Ababa Showcases Civil Registration and Identity Management Experience at IDAfrica 2025
As Addis Ababa begins hosting the 2025 IDAfrica Conference under the theme “Unlocking Identity for Development”, the city has proudly presented its achievements and ongoing efforts in Civil Registration and Identity Management.
Mr. Yonas Alemayehu, Director General of the Addis Ababa City Administration Civil Registration and Residency Service Agency (CRRSA), shared the city’s experience and strategic direction in building a robust and inclusive identity system rooted in comprehensive civil registration.
In his remarks, Mr. Yonas emphasized that the Addis Ababa Smart City Initiative has positioned civil registration as a key pillar for addressing governance challenges and advancing digital service delivery for residents. He further highlighted that the national digital ID initiative “Fayda”, led by the Prime Minister of Ethiopia, is becoming a foundational component of the city’s digital transformation journey.
Mr. Yonas also noted that the ongoing Fayda enrollment, being carried out by CRRSA in collaboration with the National ID Program, has seen a significant and rapid increase in registration rates—demonstrating strong public engagement and institutional momentum.
On this international conference more than 105 countries and 2300+ participants are participating.
"ፋይዳ ማለት በአገርኛ ቋንቋችን እሴት፣ዋጋ የተሰጠው፣ ጠቃሚ ማለት ነው።ፋይዳ ካርድ ብቻ አይደለም።
የአንድ ዜጋ የግላዊ መረጃዎቹ ሚስጥራዊነቱ በተጠበቀ መልኩ ተይዞ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች ብቻ የሚጋሩበት እና ማንነቱ የሚረጋገጥበት ልዩ የመለያ ቁጥር ነው።ፋይዳ በኢትዮጵያ ተግባራዊ መሆን ከጀመረበት እስካሁን ባለው ጊዜ 50 ሚሊዮን ያህል ዜጎችን ደርሷል።"
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ
AMN-Addis Media Network
"ፋይዳ ማለት በአገርኛ ቋንቋችን እሴት፣ዋጋ የተሰጠው፣ ጠቃሚ ማለት ነው።ፋይዳ ካርድ ብቻ አይደለም።
የአንድ ዜጋ የግላዊ መረጃዎቹ ሚስጥራዊነቱ በተጠበቀ መልኩ ተይዞ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች ብቻ የሚጋሩበት እና ማንነቱ የሚረጋገጥበት ልዩ የመለያ ቁጥር ነው።ፋይዳ በኢትዮጵያ ተግባራዊ መሆን ከጀመረበት እስካሁን ባለው ጊዜ 50 ሚሊዮን ያህል ዜጎችን ደርሷል።"
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ
ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የ 9 ወራት ስራ አፈጻጸሙን ከተጠሪ ተቋማት ጋር ገመገመ።
የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በስሩ ከሚገኙ የክ/ከተማና የወረዳ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት፣ የጽዳት አስተዳደርና የየሲቪል ምዝገባና የነዋሪውች አገልግሎት ጽ/ቤት ባለሙያዎች ጋር የ2017 ዓ.ም የ 9 ወራት ስራ አፈጻጸሙን ገምግሞ የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችንም አስቀምጧል።
በመድረኩ ከሪፎርም፣ ከልደት ሞትና ጋብቻ፣ ከተማሪዎች የብሔራዊ መታወቂያ ፋይዳ ምዝገባ፣ ከዘላቂ ማረፊያ/ የመቃብር ስፍራ/ ማመቻቸት ከመሳሰሉ ከሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት ጋር በተያያዘ እንዲሁም ከቆሸሻሻ ቅብብሎሽ ጣቢያና ከብሎክ ጽዳት ሁኔታዎች፣ከሞደል ብሎክ መፍጠርና ከመሳሰሉ ጉዳዮች እንዲሁም ከእቅድና ሪፖርት አቀራረብ፣ከመንገድ ዳር መብራቶች ጋር ግንኙነት ያላቸው አሰራሮች ተነስተው ምላሽና የቀጣይ የስራ አቅጣጫ ተሰጥቶባቸዋል።
መድረኩን የመሩት የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወንድማገኝ ታደሰ ከአገልግሎት አሰጣጥ አንጻር ያሉ ችግሮች በፍጥነት ማስተካከልና ስታንዳርድን ጠብቆ መስራት እንደሚገባ በማውሳት አገልግሎትን የህብረተሰቡን ርካታ ሊጨምር በሚችል መልኩ መሰጠትና ከምንም ነገር አስቀድሞ ምቹ የስራ ቦታ መፍጠር እንደሚያስፈልግ ጠቁመው ተቋማዊ የስራ ሪፎርም በማድረግ፣ ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከርና ስራን ቆጥሮ በመቀበልና በማስረከብ መርህ ላይ በልዩ ትኩረት መስራት እንዳለበት ብሎም ከክረምት የጎርፍ አደጋ ስጋት ጋር በንቃት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
ግንቦት 12/2017 ዓ.ም
በጉለሌ ክፍለ ከተማ የህብረተሰቡ የረጅም ጊዜ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ የነበረው የመብራት አገልግሎት ምላሽ አገኘ።
በክፍለ ከተማው ወረዳ 2 አስተዳደር ከግብፅ ኢምባሲ እስከ ሀምሌ 19 መናፈሻ ያለ የመንገድ መብራት አገልግሎት ሳይሰጥ ረጅም አመት የቆየ መንገድ መብራት ጥገና ተደርጎለት አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ነጋሽ እንደገለፁት ለረጅም አመት ተሰርቶ አገልግሎት ሳይሰጥ የቆየ ከመሆኑ ባሻገር ለደረቅ ወንጀል መንስኤ ሆኗል ብለዋል ስለሆነም የህብረተሰቡን ጥያቄ ከአዲስ አበባ መብራት አገልግሎት ባለስልጣን ጋር በመቀናጀት ጥገና በማድረግ አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጓል።
ኃላፊው አያይዘው ማህበረሰቡ የኔነት ስሜት ተሰምቶት በመሰረተ ልማት ላይ የሚፈፀሙ ስርቆቶችን በንቃት ሊከላከልና ሊጠብቅ ይገባል ብለዋል።
በቅርብ ዓመታት ውስጥ፣ ዲጂታል ማንነት ተስፋ ሰጪ ከሆነው ፈጠራ ወደ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን መሠረታዊ ምሦሶ ተሻሽሏል። ከአሁን በኋላ አማራጭ ሳይሆን ሰዎችን ከአገልግሎቶች፣ ከማኅበረሰቦች፣ ከተቋማት እና ከመንግሥታት ጋር የሚያገናኝ አስፈላጊ መሠረተ ልማት ነው።
ከአምስት ዓመት በፊት በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ራዕይ እየተመራን እጅግ አስፈላጊ ውሳኔ ወስነናል። ይህም ዘመናዊ፣ አካታች፣ መሠረት ያለው እና ሊሰፋ የሚችል ዲጂታል የማንነት ሥርዓት መገንባት ነው። ይሄንንም ለእያንዳንዱ ነዋሪ ተደራሽ እንዲሆን ማድረግ ነበር። ይሄንን ሥርዓት ‘ፋይዳ’ ብለን እንጠራዋለን። ፋይዳ ካርድ ብቻ አይደለም። የግለሰቦችን ግላዊ መረጃዎች ምሥጢራዊነት በመጠበቅ እና አስፈላጊ የሆነውን ብቻ በማጋራት ማንነትዎን የሚያረጋግጥ ልዩ መለያ ቁጥር ነው!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ
In recent years, digital identity has evolved from a promising innovation into a foundational pillar of digital transformation. It is no longer an optional layer, it is an essential infrastructure that connects people to services, communities to institutions, and governments to the aspirations of their citizens.
Five years ago, guided by the vision of Digital Ethiopia 2025, we made a bold and necessary choice: to build a modern, inclusive, foundational and scalable digital identity system accessible to every resident regardless of location, income, or background. We call this system Fayda, meaning “value” in our local language. Fayda is not merely a card. It is a unique identification number that proves who you are, while protecting your privacy and sharing only what is necessary!
Prime Minister Abiy Ahmed Ali ( PHD)
ሁለንተናዊ ጤና ለሃገር ብልፅግና!!
በቦሌና አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በተለያዩ ጤና ተቋማት የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች እና የዘርፉ ባለድርሻ አካላት 'ሁለንተናዊ ጤና ለሀገር ብልፅግና!' በሚል መሪ ሀሳብ ዉይይት ማካሄድ ጀምረዋል፡፡
ከለውጡ ማግሥት በተገኙ ስኬቶችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እንዲሁም ከጤና ባለሙያዎች በሚጠበቀው ሚና ዙሪያ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዮሐንስ ጫላ የቪዲዮ ገለፃ ቀርቦ ውይይት በመደረግ ላይ እንደሚገኝ ተመላክቷል።
በመዲናዋ ደረቅ ቆሻሻን ወደ ኃይል የሚቀይርና መልሶ ጥቅም ላይ የሚያውል የ500 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ስራ ላይ ሊውል ነው።የኢዜአን ዘገባ በቀጣዩ ቪዲዮ ይከታተሉ👉👉
ዛሬ የኬንያ የሞምባሳ ግዛት አስተዳዳሪ አብዱልስዋማድ ሸሪፍ ናስርን እና የልዑካን ቡድናቸውን ወደ አዲስ አበባ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለን ተቀብለናቸዋል።
በቆይታችንም አዲስ አበባን ህጻናትን ለማሳደግ ምቹ አፍሪካዊት ከተማ ለማድረግ በቀዳማይ ልጅነት መርሃ ግብር ያገኘናቸው ስኬቶችን እንዲሁም ሌሎች እንደ ልምድ ሊወሰዱ የሚገባቸው የከተማ ልማት ስራዎችን ለልዑካን ቡድኑ አቅርበናል።
የሞምባሳ ግዛት አስተዳዳሪ አብዱልስዋማድ ሸሪፍ ናስር ከተማችን አዲስ አበባ የስበት ማዕከል እና የተቀናጀ ከተማ ተምሳሌት ሆና የምትጠቀስ መሆኗን ገልጸውልናል።
የልዑካን ቡድኑ አባላት በአራት ቀናት የአዲስ አበባ ቆይታቸው በከተማችን የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም፣ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና ፍሳሽ አስተዳደር፣ የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ስርዓታችንን እንዲሁም ኮሪደር ልማት ተኮር እና ሌሎች የከተማ ትራንስፎርሜሽን ስኬቶቻችንን በመጎብኘት ከከተማችን ጋር የልምድ ልውውጥ የሚያደርጉ ይሆናል።
