1 474
Suscriptores
Sin datos24 horas
-37 días
-2130 días
Archivo de publicaciones
የኢሬቻ በዓልን ለመታደም የሚመጡ እንግዶችን ለማስተናገድ ዝግጅት አድርገናል- የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አባ ገዳዎች፣ሃደ ሲንቄዎች፣ የክፍለ ከተማው ነዋሪዎችና የስራ ኃላፊዎች የተገኙበት የኢሬቻ ፌስቲቫል ተካሄዷል፡፡
በመርሐግብሩ ላይ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ አይዳ አወል፣በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ዋ/ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ ፣የአዲስ አበባ ከተማ የውሀና ፍሳሽ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ዘሪሁን አባተ እና ሌሎች የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
የኦሮሞ ህዝብ የጥንታዊ ስልጣኔ መገለጫዎችን በማስተዋወቅ ትልቅ አስተዋፅኦ ያደረገ ማህበረሰብ ነው ያሉት የአዲስ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ አይዳ የኢሬቻ በዓልም በኦሮሞ ማህበረሰብ ብቻ ሳይሆን ህብርና ብዝሀነትን በሚያሳይ መልኩ በሁሉም ኢትዮጵያውያን ዘንድ እንደሚከበር ተናግረዋል።
ኢሬቻ ከሚያንፀባርቀው ባህላዊ ቀለም በተጨማሪ ሰላም፣ፍቅር፣ አንድነትና ፍትህን የሚሰብክ በዓልም ነው ብለዋል።
የከተማዋ ነዋሪ በኢትዮጵያዊ የእንግዳ አቀባበል እንግዶችን በፍፁም ጨዋነት እንዲቀበልም ስራ አስፈፃሚዋ ጥሪ አቅርበዋል።
በፌስቲቫሉ የተገኙ የክፍለ ከተማው ነዋሪዎችም የኢሬቻ በዓልን ለመታደም ከተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚመጡ እንግዶችን ለማስተናገድ ዝግጅት ስለማድረጋቸው አንስተዋል።
በፌስቲቫሉ ላይ የኦሮሞ ባህላዊ ምግቦች፣ባህላዊ አልባሳትና ባህላዊ ጭፈራዎች በተሳታፊዎች ቀርበዋል።
ኢሬቻ ሰላም በመሆኑ በዓሉን ስናከብር ለሰላምና ለአብሮነት ያለንን ቁርጠኝነት ማሳየታችን ነው - በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ
በአዲስ አበባ ከተማ የኢሬቻ በዓል የሚከበርበት አካባቢ የማፅዳት መርሀ ግብር በዛሬው እለት መስከረም 23 ቀን 2017 አ.ም ተካሄዷል።
የፅዳት መርሐ ግብሩ በኦሮሞ ባህል መሰረት በአባገዳዎችና በሀደሲንቄዎች ምረቃ ተጀምሯል።
በኢሬቻ ፓርክ የተካሄደው ጽዳት ላይ በም/ ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ የበርካታ ብሔር ብሔረሰቦች መገኛ የሆነችው ኢትዮጵያ የህዝቦቿን ባህልና እሴት አክብራ የምትንቀሳቀስ መሆኗን አመልክተው በዛሬው እለት የምንካሂደው የፅዳት ንቅናቄ ቦታውን ከማፅዳት ባለፈ የጋራ አብሮነታችንን የምናሳይበት ተምሳሌትም ነው ብለዋል።
እሬቻ የጋራ ሃብታችን፣ የሁላችንም ኩራት፣ የአብሮነታችን መድመቂያና ዘመናትን በህብር የተሻገረው የአብሮ መኖራችን ሚስጥር ነው" ያሉት ደግሞ የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከፍያለው ተፈራ ናቸው።
አቶ ከፍያለው አክለውም የኢሬቻ በዓል የሰላም የአብሮነት፤ የተለያየ የሚገናኝበት፤ ከሁሉ በላይ ፈጣሪ የሚመሰገንበት በመሆኑ ሁላችንም ተቀራርበን አብሮነታችንን ከፍ እያደረግን አንድነታችንን እያፀናን ልናከብር ይገባል ብለዋል ፡፡
አያይዘውም በዓሎቻችን የጋራ ሃብቶቻችን፣ የሁላችንም ኩራት፣ የአብሮነታችን መድመቂያና ዘመናትን በህብር የተሻገረው የአብሮ መኖራችን ሚስጥር ናቸውም ብለዋል፡፡
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሙባረክ ከማል በበኩላቸው እሬቻ የገዳ ስርዓት ካጎናፀፈን እሴቶች አንዱና ዋናው ነው። እሬቻ ሲከበር ጎላ ብሎ ከሚከወኑ ጉዳዮች አንዱና ዋናው ምስጋና ነው። ስለዚህ ይህ የምስጋና በዓል በክፍለ ከተማችን በመከበሩ ለእኛ ለቂርቆስ ነዋሪዎች ትልቅ አጋጣሚ ነው ብለዋል።
በፅዳት መርሐ ግብሩ ላይ የከተማ አስተዳደሩ እና የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም አባገዳዎችና ሀደሲንቄዎች፣ የተለያዩ የሀገር ሽማግሌዎች፤ ታዋቂ ሰዎችና የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል፡፡
ከጽዳቱ መርሃግብሩ ጎን ለጎን በአሉ የሚከበርበት ቦታ በአባገዳዎች፣ በአመራሮችና በተሳታፊ እንግዶች ተጎብኝቷል።
ሰላማችን ለሁለንተናዊ ብልፅግናችን!!
በአዲስ አበባ 11 ሺ የሰላም ሰራዊት አባላት ተመረቁ
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በ2017 ዓ.ም በመጀመሪያ ዙር ያሰለጠናቸውን 11 ሺ የሰላም ሰራዊት አባላት አስመርቋል።
አባላቱ በንድፈ ሃሳብና በተግባር የተደገፈ የአካል ብቃትና ወታደራዊ ስልጠና እንደተሰጣቸው ተጠቁሟል።
በከተማዋ የሰላም ሰራዊት አባላት ስራ ከጀመሩበት ጊዜ ወዲህ የወንጀል ክስተት ምጣኔ መቀነሱን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሊዲያ ግርማ ተናግረዋል።
ከተማዋ የአስተማማኝ ሰላም ባለቤት የሆነችው በሰላም ሰራዊቱ ፣ በፀጥታ ተቋማትና በነዋሪዎች ቅንጅት መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ናቸው።
ተመራቂዎቹ የከተዋን ሰላም ዘላቂ የማድረግ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡም ኮሚሽነር ጌቱ አደራ ብለዋል።
በበጀት ዓመቱ በአምስት ዙር በሁሉም ክፍለ ከተሞች በርካታ የሰላም ሰራዊት አባላት እንደሚሰለጥኑ ተጠቁሟል።
በም/ ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ የረጲ ደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ስፍራና ከደረቅ ቆሻሻ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ጣቢያ አሁናዊ የስራ እንቅስቃሴን ጎበኙ።
ኢንጅነር ወንድሙ ከአፍሪካ የመጀመሪያው የሆነውን የረጲ ደረቅ ቆሻሻ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ጣቢያ (Waste to Energy) እና የቆሻሻ ማስወገጃ ስፍራ ላይ የስራ ጉብኝት ያካሄዱት ከጽ/ ቤቱ አመራሮች፣ ከኤጀንሲው አመራሮች እና ባለሙያዎች ጋር በመሆን ነው።
በዚሁ ወቅት በረጲ የሃይል ማመንጫ ጣቢያ በከተማው በአሁኑ ወቅት ከሚመነጨው ደረቅ ቆሻሻ በየቀኑ በአማካይ 1280 ያህል ቶን ወደ ኤሌክትሪክ ሃይል እንደሚቀይር በባለሙያዎቹ ተገልፆላቸዋል።
የረጲ ከደረቅ ቆሻሻ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ጣቢያ ተገቢነቱና ጥራቱ ከተረጋገጠ የከተማው ደረቅ ቆሻሻ የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት የቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓቱን በማዘመን ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝም በገለጻው ተመልክቷል።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ የሃይል ማመንጫ ጣቢያውን እና የማስወገጃ ስፍራውን ከጎበኙ በሁዋላ እንደተናገሩት የከተማችንን የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት በይበልጥ ለማዘመን ስራ ላይ እየዋሉ ካሉ ቴክኖሎጅዎች በተጨማሪ ቆሻሻን መልሶ የመጠቀምን (Recycle) የማስፋት ፣ በእያንዳንዱ ነዋሪ ቤት የቆሻሻ መለዬትን (Sorting) የመተግበር ጉዳይ አንገብጋቢ በመሆኑ ይህንን ተግባር በይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ለማ በበኩላቸው በከተማው በየቀኑ ከተለያየ ቦታ የሚመረተዉ ቆሻሻ እየጨመረ መምጣቱን ገልፀዉ የቆሻሻ አወጋገድ ስርአቱን በአግባቡ ለማስተዳደር ተጨማሪ የቆሻሻ ማስወገጃ ስፍራ ( land fill) ማመቻቸት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል::
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
መስከረም 21 ቀን 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
39ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 39ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡
1. በቅድሚያ ምክር ቤቱ የተወያየው ብሔራዊ የመካከለኛ ዘመን 2017-2020 የገቢ ስትራቴጂ ላይ ነው፡፡ ስትራቴጂው የታክስ ሥርዓቱን ለማዘመን እና ለግል ኢንቨስትመንቱ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር የታለመ ሲሆን አጠቃላይ የታክስ ፖሊሲዎችን እና አስተዳደራዊ ሪፎርሞችን እንዲሁም ማሻሻያዎችን ለመተግበር የሚያስችል ነው፡፡ ሰትራቴጂው ከ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድ ጋር የተጣጣመ እንዲሆን ተደርጎ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በስትራቴጂው ላይ በዝርዝር ከተወያየበት በኋላ በምክር ቤቱ ውሳኔ ካገኘበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
2. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ከማልታ ሪፐብሊክ መንግስት እና ከቻድ ሪፐብሊክ መንግስት ጋር የተፈረማቸውን የአየር አገልግሎት ስምምነቶችን ለማጽደቅ የቀረቡ 2 ረቂቅ አዋጆች ላይ ነው፡፡ ስምምነቶቹ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ማንኛውም የማልታ ከተማ እና ወደ እንጃሜና ከተማ በ3ኛና 4ኛ ትራፊክ መብት የመንገደኛ እና የጭነት የበረራ ምልልስ ለማድረግ፣ ተወካይ አየር መንገዶችን በሽርክና ለማሰራት፣ በ5ኛ ትራፊክ መብት ወደ ተመረጡ መዳረሻዎች በረራ ለማድረግ የሚያስችል እና አገራችን ከሁለቱ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር፣ ለንግድና ኢንቨስትመንት፣ ለወጪ ንግድ፣ ለቱሪዝም፣ ለስራ እድል ፈጠራ እና ለውጭ ምንዛሪ ግኝት ትልቅ አስተዋጽኦ ያላቸው ስምምነቶች ናቸው፡፡ ምክር ቤቱ በረቂቅ አዋጆቹ ላይ ከተወያየ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ ወስኗል፡፡
3. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የፓሪስ ኢንዱስትሪያዊ ንብረት ኮንቬንሽን ለማጽደቅ በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ የፓሪስ ኢንዱስትሪያዊ ንብረት ኮንቬንሽን በአባል አገራት መካከል ሕብረት በመፍጠር የኢንዱስትሪ ንብረትን ለመጠበቅ፣ የፈጠራ ባለቤትነት፣ የግልጋሎት ሞዴሎች፣ የኢንዱስትሪ ንድፎች፣ የንግድ ምልክቶች፣ የአገልግሎት ምልክቶች፣ የንግድ ስሞች፣ የምርቶች ምንጭ አመልካች ምልክቶች ለመጠበቅ እንዲሁም ተገቢ ያልሆነ ውድድር ለመከላከል እና ለግብርና እና ሁሉንም የተመረቱ ወይም ተፈጥሯዊ ምርቶች የሚያካትት ነው፡፡ የኮንቬንሽኑ መጽደቅ ሀገራችን ለምታደርገው የአለም ንግድ ድርጅት አባልነት ጥያቄ ድጋፍ የሚሆን ሲሆን ከአባል ሀገራቱ ለሚነሱ የኢንዱስትሪያዊ ንብረት ጥበቃን ለሚመለከቱ ጥያቄዎች አዎንታዊ መልስ ለመስጠት ያስችላል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
4. ሌላው ምክር ቤቱ የተወያየው የዓለም አቀፍ ምልክቶችን ከሚመለከተው የማድሪድ ስምምነት ጋር የተዛመደውን ፕሮቶኮል ለማጽደቅ በወጣ ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ ፕሮቶኮሉ የንግድ እና የአገልግሎት ምልክቶች በአገር ውስጥ ሕግ ከሚደረግላቸው ጥበቃ አልፈው በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥበቃ እንዲኖራቸው ለማድረግ የሚያስችል ከመሆኑም በተጨማሪ ምርቶች እና አገልግሎቶች ያላግባብ ለሌሎች ጥቅም እንዳይውሉ በቂ ጥበቃ የሚደረግበትን ሁኔታ የሚፈጥር፣ ጥራታቸውን የጠበቁ ምርቶችና አገልግሎቶች እንዲኖሩና የሀብት ምንጭ እንዲሆኑ ትልቅ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ ምክር ቤቱ በፕሮቶኮሉ ላይ ከተወያየ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል፡፡
5. በመጨረሻም ምክር ቤቱ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ደንብ እና የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ሰራተኞች ደንብ ላይ ነው፡፡ አገልግሎት መስሪያ ቤቱ በአዋጅ የተሰጠውን ተግባር እና ሀላፊነት ለመወጣት፤ የተቀላጠፈ አገልግሎት ለደንበኞች ለመስጠት እንዲሁም ከፓስፖርት የቆይታ ጊዜ ጋር በተያያዘ ያሉ ጥቄዎችን መፍታት እንዲችል የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ረቂቅ ደንቡ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ በተጨማሪም የጀመረውን ሪፎርም ውጤታማ ለማድረግ፣ ሪፎርሙ በተሟላ ሁኔታ እንዲተገበር ለማስቻል የአገልግሎቱን ልዩ ባህሪይ ከግምት ውስጥ ያስገባ ሰራተኞች መተዳደሪያ ደንብ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቦቹ ላይ በዝርዝር ከተወያየባቸው በኋላ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው ከወጡበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረጉ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
ባለፉት ሁለት ቀናት በኮሪደር ልማት ስራችን የጀመርናቸውን የታክሲ እና ባስ ተርሚናሎች፣ የመኪና ማቆሚያ ፓርኪንጎች እንዲሁም የፒያሳ መልሶ ማልማት ስራዎች ያሉበትን ሁኔታ ተዘዋውረን ገምግመናል::
በመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት ስራችን ሰርተን ለህዝብ ክፍት ካደረግናቸው ስራዎች በተጨማሪ በከተማችን ያለውን የትራፊክ ስርዓት እንዲያሳልጡ ከጀመርናቸው 48 የመኪና ማቆሚያ እና የታክሲ/ባስ መጫኛና ማውረጃዎች ውስጥ 11 የሚሆኑት ከ 2 እስከ 3 ወለል ከመሬት በታች እና ከመሬት በላይ እየተገነቡ መሆኑን መግለፃችን ይታወሳል::
በመሆኑም በአራት ኪሎ፣ ፒያሳ ጊዮርጊስ አካባቢ፣ ቸርችል መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ፣ ባሻ ወልዴ አካባቢ፣ ደጎል አደባባይ አካባቢ፣ ቦሌ ድልድይ አካባቢ፣ ቦሌ መንገድ ደንበል አካባቢ፣ ሳር ቤት፣ ቀበና አካባቢ፣ መገናኛ እና ሲኤምሲ አካባቢ ከመሬት በታች ከ 2 እስከ 3 ወለል ከመሬት በታች እና ከመሬት በላይ የሆኑ የታክሲና የባስ ተርሚናሎች የግንባታ ሁኔታ በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ ሲሆን በታቀደው ጊዜ ውስጥ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት የሚደረግ ይሆናል::
በተጨማሪም በኮሪደር ልማት ስራችን የዋና መንገድ አካባቢ ብቻ ሳይሆን የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን ጨምሮ ከተማችንን ለመኖር ምቹ እና አለምአቀፍ ደረጃዋን የጠበቀች ለማድረግ የጀመርናቸው ልዩ ልዩ መሰረተ ልማቶችንም የሚያካትት ሲሆን እነዚህ ስራዎች ለከተማችን ነዋሪዎችም ሰፊ የስራ እድል እየፈጠሩ ናቸው::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በ2ኛው ዙር የኮሪደር ልማት የልደታ እና ነፋስ ስልክ ክፍለ ከተሞችን የሚያካልለው ከሳር ቤት አደባባይ እስከ ፉሪ አደባባይ ለሚካሄደው የኮሪደር ልማት በፕላንና ልማት ቢሮ ተዘጋጅቶ በቀረበ የዲዛይን ስራ ላይ በዛሬው እለት ውይይት ተካሂዶበታል።
በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አስተባባሪነት እየተከናወነ ያለው ይህ የኮሪደር ልማት 14. 65 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና 544 ሄክታር ስፋት የሚሸፍን ነው።
ይህ የኮሪደር ልማት አለም ዓቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የተሽከርካሪ መንገድ እና ተያያዥ መሠረተ ልማቶች፣ የእግረኛና የብስክሌት መንገዶች፣ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡን የሚያሳልጡ የአውቶቡስ እና የታክሲ ተርሚናሎች፣ መጫኛ ማውረጃ ስፍራዎች፣ የህዝብ መናፈሻ ስፍራዎች፣ ፋውንቴይኖችና የአረንጓዴ ስፍራዎች እንዲሁም የልጆች መጫዎቻ፣ የህዝብ ፕላዛዎችን እና የመሳሰሉትን ያካተተ ነው።
በቢሮው የቀረበውን ዲዛይን አስመልክቶ በመድረኩ የተገኙት የመሠረተ ልማት ተቋማት ባለሙያዎች ጠቃሚና ገንቢ አስተያዬቶችን ሰጥተዋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ በዲዛይኑ ላይ የመሠረተ ልማት ባለሙያዎች የሰጡት ግብአት ታክሎበት የተሟላ ዲዛይን እንዲቀርብ አሳስበው የመሠረተ ልማት ተቋማትም የቀረበውን ዲዛይን መነሻ በማድረግና እቅዳቸውን በማዘጋጀት በፍጥነት ወደ ተግባራዊ ስራ እንዲገቡ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
