es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Ir al canal en Telegram
1 474
Suscriptores
Sin datos24 horas
-37 días
-2130 días
Archivo de publicaciones
ዛሬ ከንግድ ማህበረሰብ አባላት እና ከከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ጋር የፋይናንስ ሚኒስትር ዲኤታ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በተገኙበት መንግስት በቅርቡ ተግባራዊ ባደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ማሻሻያ ዙሪያ ውይይት አድርገናል። ሪፎርሙ ለሀገራችን በርካታ ጥቅም የሚያስገኝ ሲሆን በዋነኛነት ዘላቂ ልማትንና አካታችነትን ለማረጋገጥ፣ ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል ተጠቃሚ የሚያደርግ የኢኮኖሚ ስርዓት ለመገንባት፣ የመንግስትን የእዳ ጫና ለመቀነስ፣ የተረጋጋ ተወዳዳሪ እና የዋጋ ግሽበትን መቀነስ የሚያስችል የገበያ ሁኔታን ለመፍጠር፣ ተኪ ምርቶችን በማምረትና ለውጪ ገበያ የምንልከውን ምርት በማሳድግ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ እንዲሁም ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታ በመፍጠር የውጪ ምንዛሬ ገቢን ለማሳደግ እድል የሚፈጥር ይሆናል። ወቅታዊ ተግዳሮቶችን ለመቆጣጠር ደሃው እና ዝቅተኛ ገቢ ያለው ማህበረሰብ እንዳይጎዳ የመንግስት ሰራተኞችን ደሞዝ መጨመር፣ ደሃውን መደጎም ፣ በተለይም በሴፍቲኔት የታቀፉ የማህበረሰብ ክፍሎችን ገቢ በሚያስገኝና ተረጂነትን በሚቀንስ መንገድ መደገፍ እንዲሁም የስራ እድልን በስፋት መፍጠርን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የሚተገበር ሲሆን በቀጣይም ከአምራቾች እና አስመጪዎች ጋር በቅርበት በመስራት እንዲሁም ገበያውን የሚያዛቡ፣ በተለይም ምንም ከውጪ ምንዛሪ ጋር ግንኙነት የሌላቸው ምርቶች ላይ አላግባብ ዋጋ በሚጨምሩ እና ምርት በሚሰውሩ አካላት ላይ ጠንካራ የሆነ ቁጥጥር እና ህግ የማስከበር ስራ የምንሰራ ይሆናል። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ዛሬ ከንግድ ማህበረሰብ አባላት እና ከከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ጋር የፋይናንስ ሚኒስትር ዲኤታ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በተገኙበት መንግስት በቅርቡ ተግባራዊ ባደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ማሻሻያ ዙሪያ ውይይት አድርገናል። ሪፎርሙ ለሀገራችን በርካታ ጥቅም የሚያስገኝ ሲሆን በዋነኛነት ዘላቂ ልማትንና አካታችነትን ለማረጋገጥ፣ ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል ተጠቃሚ የሚያደርግ የኢኮኖሚ ስርዓት ለመገንባት፣ የመንግስትን የእዳ ጫና ለመቀነስ፣ የተረጋጋ ተወዳዳሪ እና የዋጋ ግሽበትን መቀነስ የሚያስችል የገበያ ሁኔታን ለመፍጠር፣ ተኪ ምርቶችን በማምረትና ለውጪ ገበያ የምንልከውን ምርት በማሳድግ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ እንዲሁም ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታ በመፍጠር የውጪ ምንዛሬ ገቢን ለማሳደግ እድል የሚፈጥር ይሆናል። ወቅታዊ ተግዳሮቶችን ለመቆጣጠር ደሃው እና ዝቅተኛ ገቢ ያለው ማህበረሰብ እንዳይጎዳ የመንግስት ሰራተኞችን ደሞዝ መጨመር፣ ደሃውን መደጎም ፣ በተለይም በሴፍቲኔት የታቀፉ የማህበረሰብ ክፍሎችን ገቢ በሚያስገኝና ተረጂነትን በሚቀንስ መንገድ መደገፍ እንዲሁም የስራ እድልን በስፋት መፍጠርን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የሚተገበር ሲሆን በቀጣይም ከአምራቾች እና አስመጪዎች ጋር በቅርበት በመስራት እንዲሁም ገበያውን የሚያዛቡ፣ በተለይም ምንም ከውጪ ምንዛሪ ጋር ግንኙነት የሌላቸው ምርቶች ላይ አላግባብ ዋጋ በሚጨምሩ እና ምርት በሚሰውሩ አካላት ላይ ጠንካራ የሆነ ቁጥጥር እና ህግ የማስከበር ስራ የምንሰራ ይሆናል። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

photo content
+2

photo content
+9

አዲስ የአገልግሎት ምዕራፍ በአዲስ ጅማሮ !" በሚል መርህ-ቃል የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የሪፎርም እቅድ ይፋ ሆነ ኤጀንሲው በበጀት ዓመቱ አቅዶ ያከናወናቸውን ዋና ዋና ተግባራት አፈፃፀም ከክ/ከተማ እና ወረዳ ሃላፊዎች ጋር በዛሬው እለት ነሐሴ 27/ 2016 በጋራ ገምግሟል። በእቅድ ግምገማው ላይ የክ/ከተሞች እና የዋና መስርያ ቤት የተለያዩ አጀንዳዎች ቀርበው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን የ2017ዓ.ም የትኩረት መስኮች ላይ በኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ አቅጣጫ ተሰጥቶበታል። ዋና ዳይሬክተሩ የሶስተኛ ዓመት የሪፎርም እቅድን ይፋ ያደረጉ ሲሆን እቅዶቹ ተግባራዊ ተደርገው ተቋሙ ወደ ኦንላይን የዲጂታል አገልግሎት እንደሚሸጋገር ገልፀዋል። የዓምቱ የሪፎርም እቅድ የሰራተኛ አቅምን፣ እውቀት እንዲሁም የአገልጋይነት ስሜትን መሰረት ያደረገ የምዘና ስርዓት ላይ ያተኮረ ሪፎርም እንሚሆን በሃላፊው የተገለፀ ሲሆን ስር-ነቀል በሆነ መልኩ አገልግሎትን ለማሻሻል አዲስ የቴክኖሎጂ ስርዓት እንደሚዘረጋ አቶ ዮናስ ተናግረዋል። ኤጀንሲው በ2016ዓ.ም በተመዘገቡ ውጤቶች ላይ ምዘና በማድረግ በሁለት ዘርፎች እውቅና ሰጥቷል: 1ኛ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ 2ኛ. የካ ክ/ከተማ እንዲሁም 3ኛ. ቂርቆስ ክ/ከተማ ባጠቃለይ የKPI ምዘና በደረጃ ተሸላሚ የሆኑ ሲሆን በወቅታዊ የኩነት ምዝገባ 1ኛ. ቂርቆስ ክ/ከተማ 2ኛ. ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ እንዲሁም 3ኛ. ለሚ ኩራ ክ/ከተማ እውቅና ተሰጥቷቸዋል። ቀሪ ክ/ከተሞች ለሰሯቸው ስራዎች የመልካም አፈፃፀም እውቅና የተሰጣቸው ሲሆን በቀጣይ ሳምንታት የተቋም ግንባታ ላይ ያተኮረ ምዘና እና እውቅና እንደሚዘጋጅ በዚህም ምርጥ የዓምቱ ሶስት ወረዳዎች እንዲሁም ክ/ከተሞች እውቅና እንደሚሰጣቸው ተነግሯል። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ከመስቀል አደባባይ እስከ ቦሌ መንገድ የኮሪደር ልማት ድባብ https://linktr.ee/AddisMediaNetwork AMN - ሐምሌ 27/2016 ዓ.ም

photo content
+2

photo content
+9

በተለምዶ ቆሼ" ተብሎ በሚጠራው የረጲ ቆሻሻ ማስወገጃ ስፍራ የ2ኛው ዙር 2ኛው ምእራፍ አረንጓዴ አሻራ የማሳረፍ አካል የሆነ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ተካሄደ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት አመራሮች፣የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም ከማእከል እስከ ወረዳ መዋቅር ያለው የዘርፉ አመራሮችና ሠራተኞች በረጲ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ስፍራ በዛሬው እለት ሐምሌ 27 ቀን 2016 አ.ም አረንጓዴ አሻራቸውን በጋራ አኑረዋል። በችግኝ ተከላው መርሀግብር ላይ በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ቆንጅት ደበላን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ለማ ፣ የክ/ከተማና የወረዳ የዘርፉ አመራሮችና ሰራተኞች ፣ የፅዳት አምባሳደሮች ፣ አርቲስቶች ፣ እና አጠቃላይ የኤጀንሲው ሰራተኞች ተሳትፈዋል። መርሐ ግብሩ የተካሄደው "የምትተክል ሀገር፤ የሚያፀና ትውልድ" በሚል መሪ ሀሳብ ነው። በዘንድሮው አረንጓዴ አሻራ 7 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል እቅድ የተያዘ ሲሆን በዛሬው ዕለት 30ሺህ የተለያዩ አይነት ያላቸው ችግኞች በረጲ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ ተተክለዋል። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

እንኳን ደስ አለን! በፈረንሳይ ፓሪስ በመካሄድ ላይ በሚገኘው 33ኛው የኦሎምፒክ ውድድር ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የብር ሜዳሊያ በአትሌት በሪሁ አረጋዊ በ10 ሺ ሜትር ወንዶች የፍፃሜ ውድድር አግኝታለ
+2
እንኳን ደስ አለን! በፈረንሳይ ፓሪስ በመካሄድ ላይ በሚገኘው 33ኛው የኦሎምፒክ ውድድር ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የብር ሜዳሊያ በአትሌት በሪሁ አረጋዊ በ10 ሺ ሜትር ወንዶች የፍፃሜ ውድድር አግኝታለች፡፡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በተለምዶ "ቆሼ" ተብሎ በሚጠራው የረጲ ደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ስፍራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በነገው እለት ይካሄዳል። 🌲🌳🌴🌿☘️🌲🍀🍀☘️☘️☘️☘️🌳🌳🌳🌳🌳🌳🌳🌳🌳🌴 “የምት
+1
በተለምዶ "ቆሼ" ተብሎ በሚጠራው የረጲ ደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ስፍራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በነገው እለት ይካሄዳል። 🌲🌳🌴🌿☘️🌲🍀🍀☘️☘️☘️☘️🌳🌳🌳🌳🌳🌳🌳🌳🌳🌴 “የምትተክል ሀገር፣ የሚያጸና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል የአዲስ አበባ ከተማ አመራሮች፣ የጽዳት አስተዳደር ኤጄንሲ አመራሮችና ሰራተኞች ፣ የክ/ከተማና የወረዳ የዘርፉ አመራሮችና አጠቃላይ ሰራተኞች 6ኛዙር የአረንጓዴ አሻራ መረሀ ግብርን ቅዳሜ ሀምሌ 27 ቀን/2016 ዓ.ም ከማለዳው 12:00 ሰዓት ጀምሮ በረጲ ደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ስፍራ በድምቀት ያካሂዳሉ። ኑ .... ረጲ ቆሼን አረንጓዴ ካባ እናልብሰው!!

photo content
+7

የአዲስ አበባ ለውጥ ሃብትን በመቆጠብ፣ ለተገቢው የጋራ ልማት ብቻ በማዋል እና ለዜጎች ትኩረት በመስጠት እየተተገበረ ያለ፣ ፈጠራና ፍጥነት ላይ የተመሰረተ፣ ቀጣይነት ያለው ነው። ስራው የከተማችን ነዋሪዎች ትብብር ጎልቶ የታየበት እና ከከተማ እስከ ፌደራል ያሉ የመሰረተ ልማት መስሪያ ቤቶች ቅንጅት የተረጋገጠበት ነው። በመሆኑም፣ በኮሪደር ልማት ስራችን ህንጻዎቻችሁን በከተማችን ስታንዳርድ እና ዲዛይን መሰረት ያሳመራችሁ እንዲሁም ለእግረኛ መተላለፊያ እንዲሆን ምቹ በማድረግ የሰራችሁ የህንጻ ባለቤቶች፣ ከሁሉም በላይ የመገልገያ ቦታዎችን ክፍት በማድረግ ከተማችን 24 ሰዓት የማትተኛ እና የምትንቀሳቀስ እንድትሆን አገልግሎት አሰጣጣችሁን የለወጣችሁ፣ በአጠቃላይ የኮሪደር ልማቱን ዓላማ ያሳካችሁ የከተማችን ነዋሪዎችን ሁሉ በራሴ እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ። ስንተባበር እንዲህ አይነት ፈጣን፣ ሰፊ ፣ ጥራትና ቀጣይነት ያለው ለውጥ ማስመዝገብ እንችላለን። አሁንም ይህን ስራ በሌሎች የከተማችን አካባቢዎችም ስለምናስፋፋው በላቀ ትብብር እና በቅርበት እጅ ለእጅ ተያያዘን መስራታችንን እንድንቀጥል ጥሪዬን አቀርባለሁ። ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በአዲስ አበባ ከተማ ከወረገኑ ማከፋፈያ ጣቢያ ወጪ የመሬት ውስጥ ተቀባሪ መስመር ላይ በደረሰ ስርቆት የተቋረጠው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት በተደረገው ከፍተኛ ርብርብ ትላንት ምሽት እኩለ ሌሊት 6፡
በአዲስ አበባ ከተማ ከወረገኑ ማከፋፈያ ጣቢያ ወጪ የመሬት ውስጥ ተቀባሪ መስመር ላይ በደረሰ ስርቆት የተቋረጠው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት በተደረገው ከፍተኛ ርብርብ ትላንት ምሽት እኩለ ሌሊት 6፡00 ጀምሮ ወደ አገልግሎት መመለሱ ተገልጿል። በዚህ አጋጣሚ መሰል ጉዳትና ስርቆት ለኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ መንስኤ አንዱ በመሆኑ፤ ሁላችንም መሰረተ ልማቱን በመጠበቅ የበኩላችንን አስተዋፅኦ እናድርግ ሲል አገልግሎቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡ #የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክአገልግሎት

photo content
+7

የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ በ2016ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2017ዓ.ም ዕቅድ ዙሪያ ውይይትና የላቀ አፈጻጸም ለነበራቸው ወረዳዎች፣ክፍለ ከተሞችና የጽዳት አምባሳደሮች የእውቅና መርሀግብር አካሄደ። የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ዶክተር እሸቱ ለማ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ሲሆኑ እንደ ኤጀንሲ በዓመቱ ዕቅድ አፈጻጸም እመርታ የታየበት በተለይ ማህበረሰቡን በቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ላይ ግንዛቤ ኖሮት በባቤትነት የፅዳትን ባህል እንዲያዳብሩ የግንዛቤ ስራ ተሰርቷል። በዚህም ውጤት ማምጣት ተችሏል። ከዚህ በተጨማሪ በህገወጥ መንገድ ቆሻሻን በሚያስወግዱ ግለሰቦችና ተቋማት ላይ እርምጃ ለመውሰድ በደንብ ቁጥር 150/2015 ወጥቶ የነበረውን በደንብ ቁጥር 167/2016 በማሻሻል ወደ ተግባር ገብተናል። ሲሉ ተናግረዋል። ለውይይት የሚሆነውን ሰነድ ያቀረቡት አቶ ሳድቅ ሽኩር የኤጀንሲው ም/ዋና ዳይሬክተር ናቸው። በቀረበው ሰነድ ላይ በግንዛቤ ሆነ በመልሶ መጠቀም ስራዎቻችን በበጀት አመቱ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገብንበት ነበር። በቀጣይም በመልሶ መጠቀም፣ የማጓጓዝ ስራዎች፣ የቅብብሎሽ ጣቢያዎች ግንባታ፣ የቅንጅት ስራዎቻችን ትኩረት ሰጥተን የምንሰራባቸው ይሆናል። በቀረበው ሰነድ ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን ውይይቱን የመሩት አቶ ሙላት ተገኝ የኤጀንሲው ም/ ዋና ዳይሬክተርና ዶክተር እሸቱ ለማ ናቸው። በቀረቡ አስተያየትና ጥያቄዎች ላይ ምላሽ የሰጡት አቶ ሙላት በቅንጅታዊ አሰራሮች ላይ ለውጦች አሉ በማለት ሌሎች በኤጀንሲያችን የሚከወኑ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ኤጀንሲው ብቻ ሳይሆን ሁሉም ትኩረት አድርጎ ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል። ዶክተር እሸቱ በማጠቃለያ ንግግራቸው ከምንም በላይ ተቋማዊ አሰራር እንዲዘረጋ ከማድረግ አንጻር በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል። በቀጣይም ከተማዋ በጽዳት የተመሰከረላት እንድትሆን ህብረተሰቡ ላይ በጎ ተጽዕኖ በመፍጠር ሁላችንም የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል። በመጨረሻም በአመቱ የላቀ አፈጻጸም ለነበራቸው ክ/ ከተሞች፣ ወረዳዎች፣ የጽዳት አምባሳደሮችና የሽርክና ማህበራት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። በውይይቱ ላይ የከተማ፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች፣ የጽዳት አምባሳደሮችና የኤጀንሲው ሰራተኞች ተገኝተዋል።

ከመስቀል አደባባይ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ድረስ ያለው የኮሪደር ልማት። ለልጆቻችን የምናወርሰው ንፁህ ከተማን፣ ቀልጣፋ የስራ ባህልን፣ ዘመን ተሻጋሪ የፈጠራ ውጤትን፣ ዘመናዊ የአኗኗር ዘይቤን፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ የችግር አፈታትን እና በራስ የመተማመን ብቃትን ነው። ውብ አዲስ! አዲስ ተስፋ፤ አዲስ መንፈስ ከንቲባ አዳነች አቤቤ See less

የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ከክ/ከተማና ወረዳ የዘርፉ አመራሮች ፣ የፅዳት አምባሳደሮች ፣ አርቲስቶች ፣ የህብረት ሽርክና ፅዳት ማህበራት ፣ የግል የፅዳት ድርጅቶቸ እና ጥሪ የተደ
+8
የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ከክ/ከተማና ወረዳ የዘርፉ አመራሮች ፣ የፅዳት አምባሳደሮች ፣ አርቲስቶች ፣ የህብረት ሽርክና ፅዳት ማህበራት ፣ የግል የፅዳት ድርጅቶቸ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ጋር በጋራ በመሆን የ2016 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀም እና የ2017 ዓ.ም ዕቅድ ውይይት በኤልያና ሆቴል በማድረግ ላይ ይገኛል።

photo content
+3

የመሬት መንሸራተት አደጋ እንዴት ይከሰታል? መፍትሔዉስ? በዘንድሮ ክረምት በመሬት መንሸራተት ባጋጠመ አደጋ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ለአሰከፊ ሰብአዊና ቁሳዊ ጉዳት ተዳርገዋል። ለመሆኑ የመሬት_መንሸራተት አደጋ መንስኤዎች ምንድናቸዉ? የተለያዩ ሳይንሳዊ ምንጮች እንደሚያሳየው የመሬት መንሸራተት በተለያዩ ምክንያቶች ይከሰታል። 👉የዳገታማ አካባቢ ተፈጥሮአዊ ተዳፋት በመንገድ ስራ፣ በእርሻ፣ በግንባታና በሌሎች ሰው-ሰራሽ ምክንያቶች ሲቀየር እንዲሁም የውሃ መውረጃ ቦይ ያለጥናት ለውጥ ሲደረግ አፈር ለናዳ ይጋለጣል። 👉 በከባድ ዝናብ ወቅት ከፍ ያለ የውሃ መጠን ወደ መሬት ውስጥ ሰርጎ በመግባት የአፈር ቅንጣቶችን በማራስ ልል ያደርጋል። በዚህ ጊዜ በየቦታው ምንጮች ይፈጠሩና ውሃ ውስጥ ውስጡን ቁልቁል መውረድ ሲጀምር ከላይ የአፈሩ ክብደት እና ከታች የተዳፈቱ ስበት በውሃ ለራሰው መሬት መደርመስ ምክንያት ይሆናሉ። 👉 ዳገታማ አካባቢ የሚገኙ ደኖች ሲጨፈጨፉ አፈሩን አቅፈው የሚይዙ የዛፎች ስሮች ስለሚበሰብሱ አፈሩ በቀላሉ ለናዳ ተጋላጭ ይሆናል። 👉 የመሬት መንቀጥቀጥ፣ የጅረት መሸርሸር፣ የከርሰ ምድር ውሃ ለውጥ እና እሳተ ገሞራ የመሬት መንሸራተት ያስከትላሉ። አደጋዉን ለመከላከል መፍትሄዉ ምንድነዉ? 👉ተፈጥሮአዊ ክስተቶችን መከላከል ባይቻልም ቢያንስ በሰው-ሰራሽ ምክንያት የሚከሰቱ ናዳዎችን ማስወገድ ወይም መቀነስ ይቻላል። 👉 ላይ ዛፎችን አለማስወገድና ቦታው ቀድሞ የተራቆተ ከሆነ ረጅምና ጠንካራ ስሮች ያሏቸውን እፀዋት መትከል አፈርን ለማቆየት ይረዳል። 👉 ውሃ መሄጃ በማጣት ወደ መሬት በከፍተኛ መጠን ሰርጎ እንዳይገባ የውሃ መውረጃ ቦዮችን ማዘጋጀት ናዳ ይቀንሳል። 👉 መንሸራተትና የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል በኮረብታ ላይ ያለውን አፈር ሊይዙ የሚችሉ የማቆያ ግድግዳዎችን እና እርከኖችን መገንባት ይረዳል። 👉 ውሃ እንዳያሰርጉ የድንጋይ ስንጥቆችንና መገጣጠሚያዎችን መግጠም ወይም ማስወገድም አስፈላጊ ነው። 👉 በላይ ደግሞ ለመሬት መንሸራተት ተጋላጭ በሆኑ ቦታዎች ቤቶችንና ሕንፃዎችን አለመገንባት እና ለመኖሪያነት አለመጠቀም በእጅጉ ይመከራል። 👉ዳገታማ አካባቢ መንገድና ሌሎች ግንባታዎችን ማከናወን አስገዳጅ በሚሆንበት ጊዜ የውሃ መውረጃ ቦዮች በተጠና ሁኔታ ሊሰሩ ይገባል። ፕሮፌሰር ገብሬ ይንትሶ ለእሳትና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በነፃ መስመር 939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ! ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et