1 474
Suscriptores
Sin datos24 horas
-37 días
-2130 días
Archivo de publicaciones
የኑሮ ውድነትን ለመከላከል ከተማ አስተዳደሩ በርካታ ስራዎችን እየከወነ መሆኑ ተገለፀ።
የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባ እና የግብረ ሀይሉ ሰብሳቢ አቶ ጃንጥራር አባይ የገቢያ ማረጋጋት፣ ኑሮው ውድነት መከላከልና ኢትዮጵያ- አዲስ አበባ ታምርት ከተማ አቀፍ ንቅናቄ ግብረ ኃይል ጋር የ90 ቀናት ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄዱ።
የኑሮ ውድነት ለመከላከል ከተማ አስተዳደሩ በርካት ስራዎችን እየሰራ መቆየቱ ይታወቃል። ስለሆነም የገበያ ዋጋን ማረጋጋት ላይ ዋነኛ መፍትሄ ለማምጣት ኢ-መደበኛ የንግድ ስራ የሚያካሂዱ የህግ ማዕቀፍና ደንቦች ተዘጋጅተው ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩን አቶ ጃንጥራር አባይ ገልፀዋል።
ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አያይዘውም በጥራት፣ በብዛትና በጊዜ ላይ ያተኮረ ስራ በዕቅድ መስራት አስፈላጊ በመሆኑ በተዘጋጀው የ90 ቀናት ዕቅድ ላይ በጋራ በመወያየት ስኬታማ ስራ በመስራት የህዝብን የኑሮ ውድነት ጥያቄዎችን መመለስ አስፈላጊ ነው ብለዋል።
በሌላ በኩል ከተማ አስተዳደሩ የኑሮ ውድነትን ለመከላከልና ገበያን ለማረጋጋት አዳዲስና ሰፋፊ የንግድ ማዕከላትን በመገንባት፣ መደበኛ ያልሆኑ ንግዶችን በመከላከል፣ አምራች ኢንዱስትሪውን በመደገፍ፣ ከተማ ግብርና በማጠናከር እና ንግድና ህብረት ስራ አቅራቢዎችን በመደገፍ በርካታ ስራዎችን በመፈፀሙ የተሻለ ውጤት መመዘገቡንም አብራርተዋል::
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ዛሬ ጠዋት "ብሩህ አዕምሮዎች፣ በክህሎት የበቁ ዜጎች" በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀውን የቴክኒክና ሞያ ቴክኖሎጂ አውደርዕይ በይፋ ከፍተናል።
“ኢትዮጵያ የምትበለጽገው የራሳችንን የሰው ሀይልና የተፈጥሮ ሀብት አቀናጅቶ በማልማት ነው” በሚል ጽኑ አቋም በሰራናቸው ስራዎች የብልጽግና መሰረት እየተጣለ ይገኛል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የቴክኒክና ሞያ ተቋማት ለሀገር ብልፅግና ያላቸውን የማይተካ ሚና በአግባቡ በመገንዘብ ለዘርፉ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት አመርቂ ውጤቶችን ማስመዝገብ ጀምሯል።
በከተማ አስተዳደሩ እየተከነወኑ ባሉ የልማት ስራዎች ውስጥ የቴክኒክና ሞያ ተቋማት የእጅ ስራ ውጤት የሆኑ የተለያዩ ተኪ እና ጥራት ያላቸዉ ግብዓቶችን ከማቅረብ ጀምሮ የሰለጠነ የሰዉ ሀይል በማፍራት በበርካታ ስራዎች ላይ አሻራቸውን ማሳረፍ መጀመራቸው የሀገራችን ብልጽግና የሚሳካው በቴክኖሎጂ አመንጪ ኢትዮጵያውያን ለመሆኑ ትልቅ አብነት ነው።
ለዛሬው አውደርዕይ የቀረቡትን የቴክኖሎጂ ስራዎች ላይ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ያበረከታችሁ ሰልጣኞችን፣ አሰልጣኞችን፣ ባለሞያዎችን እና መላውን አመራር አመሰግናለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በዛሬው ዕለት ከተማ አቀፍ የክረምት በጎ ፍቃድ ስራዎችን በይፋ አስጀምረናል።
ከለውጡ ወዲህ የበጎ ፍቃደኝነት አገልግሎት የአንድ ወቅት የንቅናቄ ስራ ብቻ ሳይሆን የሁሌ ተግባር እና ባህል ማድረግን ታሳቢ በማድረግ ተቋም መስርተን፣ ተቋማዊ አሰራርን በመዘርጋት ባከናወንነው ስራ የሚሊዮኖች እንባ ታብሷል።
በዛሬው ዕለት ያስጀመርነው የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎትም የበርካቶች እምባ የሚታበስበት፣ ለአቅመ ደካሞች 2,500 ደረጃቸውን የጠበቁ ቤቶች በመገንባት የዘመሙ ጎጆዎች የሚቃኑበት፣ ለ500,000 ሰዎች ማዕድ በማጋራት የክረምት የኑሮ ጫናን ማለፍ የምናስችልበት፣ ወላጅ የሌላቸዉ 440 ህፃናት አሳዳጊና ተንከባካቢ ቤተሰቦች የሚያገኙበት፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞችን በመትከል ከተማችንን አረንጓዴ የምናለብስበት እና ሌሎች በርካታ ስራዎችን የምንሰራበት አያሌ ዝርዝር ተግባራትን ያቀፈ ነው።
በምሳሌነት የምንገልጻችሁ የከተማችን ባለሀብቶች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች እና ተቋማት በሙሉ በተለመደው መልኩ በገንዘባችሁ፣ በጉልበታችሁ እና በእውቀታችሁ አብራችሁን እንድትሰሩ ጥሪዬን እያቀረብኩ፤ እስካሁን ላበረከታችሁት ታሪካዊ አስተዋጽኦ አመሰግናለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ የጥናትና ፕሮጀክት ትግበራ ዳይሬከቶሬት ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ታከለ ደሲሳ በአዲስ አበባ ከተማ የፅዳት አሰተዳደር ኤጀንሲ የፕሮጀክትና ላንድፊል አስተዳደር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር በመሆን ተሹመዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ለአቶ ታከለ ደሲሳ መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንላቸው ይመኛል፡፡
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከመምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከመምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት
መዲናችን አዲስ አበባ፣ፅዱ፣ ውብ፣ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ብርሃን የነገሰባት እና ከማንኛውም የአደጋ ስጋት የተጠበቀች ከተማ እንድትሆን ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት በቀጣይ 90 ቀናትም ከልዩ የንቅናቄ አጀንዳዎች ጋር አስተሳስሮ በብቃት እና በውጤታማነት መፈፀም እንደሚገባ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አስታወቁ።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ይህን ያስታወቁት የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት በከተማዋ ሁሉንም አካባቢዎች በጽዳት በመጠበቅ የትኛውንም ለአደጋ ስጋት አጋላጭ የሆኑ ችግሮችን አስቀድሞ ለመከላከል እና ፈጣን ምላሽ ለመስጠት በዛሬዉ እለት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ከተጠሪ ተቋማት፣ ከቄራዎች ድርጅት፣ከዉኃና ፍሳሽ ባለስልጣን፣ ከክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጆች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ባካሄደው የዉይይት መድረክ ላይ ነው።
በመድረኩ ላይ በመዲናችን የተለያዩ ቦታዎች በተለይም በአየር መንገድ ዙሪያ ላይ የሚገኙ የቆሻሻ ቦታዎች እንዳይኖሩ በማድረግ ፣ የህገወጥ የእርድ ስርዓትን በመከላከል፣በዙሪያዉ ያሉ ወንዞችን በፅዳት በመጠበቅ እና ቆሻሻን በተገቢው ግዜ በማስወገድ በተለይም በቦሌ አየር መንገድን አካባቢ በፅዳት በመጠበቅ በበረራ ላይ ችግር ሊፈጥሩ የሚችሉ አእዋፋትን አስቀድሞ መከላከል እንደሚገባ በቢሮ ሃላፊ ማእረግ ም/ ዋ/ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ ባቀረቡት ሪፖርት አመልክተዋል ፡፡
ሪፖሪቱ ከቀረበ በሁዋላ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አክለው እንደገለፁት መዲናችን አዲስ አበባ አለም አቀፋ ተቀባይነት በተለያዩ ዘርፎች እያገኘች ካለችበት አንዱ አየር መንገዷ መሆኑን ጠቅሰዉ ይህንን የአገራችን ክብርና ኩራት የሆነ ተቋም አገልግሎቱን አስተማማኝ ለማድረግ በሚያደርገው ጥረት በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት በኩል አስፈላጊው እገዛ እና ትብብር በማድረግ ረገድ በርካታ ተግባራት እየተከናወነ ይገኛል ይህንንም አጠናክረን መቀጠል ይገባናል ብለዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ለቀጣይ 90 ቀናት የክረምት የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎትን ከበጎ ፈቃድ ስራዎች ጋር በተቀናጀ አግባብ መፈፀም በሚቻልበት አጀንዳዎች ላይ ከተቋማት አመራሮች ጋር የጋራ የውይይት መድረክ ተካሄደ።
በአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ፅ/ቤት በከተማ አስተዳደሩ ለቀጣይ 90 ቀናት የሚከናወኑ ልዩ የንቅናቄ አጀንዳን መሠረት በማድረግ በዛሬው እለት በፅ/ቤቱ ከህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን የሥራ ሃላፊዎች ጋር በቀጣይ 3 ወራት በሚከናወኑ ዋና ዋና የሥራ እቅዶች ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል።
በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በመሩት በዚህ የውይይት መድረክ ላይ በቀጣይ 90 ቀናት በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት እና በጎ ፈቃድ ስራዎች ጋር በተቀናጀ አግባብ የሚፈፀሙት ዋና ዋና ሥራዎች መካከል የማእድ ማጋራት፤ ብሎክን መሰረት ያደረገ የንቅናቄ ስራዎች፤ የጤና ዘርፍ የበጎ ፈቃድ ስራዎች፣
የክረምት ትምህርት፣የከተማ ፅዳት እና ውበት ስራዎች፣ የአደጋ ስጋት መከላከልና እና የፋይዳ ምዝገባ ስራዎች በልዩ ትኩረት እንደሚፈፀሙ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በዚሁ ወቅት የቀጣይ 90 ቀናት የክረምት የበጎ ፈቃድ እና የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ስራዎች እና ሌሎችንም የንቅናቄ ስራዎች ከመደበኛ ዕቅድ ጋር አስተባብሮ እና አሳተሳስሮ መምራት ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
አክለውም ከሰኔ 5 እስከ ጳጉሜ 5 የሚቆየው ይህ ልዩ የንቅናቄ አጀንዳ በክብርት ከንቲባችን እና ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ባስቀመጡት አቅጣጫ መሠረት የሚፈፀም እንደመሆኑ በእቅድ የተለዩ አጀንዳዎቻችን እና ዋና ዋና ሥራዎቻችን ከብሎክ እስከ ወረዳና ማእከል እንዲሁም በሁሉም ባለድርሻ አካላትና በህዝባችን ተሳትፎ በልዩ ተነሳሽነት እና መሰጠት ሊፈፀም እንደሚገባም አመልክተዋል።
በዚህም ሃላፊነታችንን እና ተልእኳችንን በአግባቡ በመወጣት በአዲስ አመት አዲስ አበባን በበለጠ ከፍታ ማየት ይገባናል ሲሉ የገለፁት ኢንጅነር ወንድሙ ሁሉም ሥራዎቻችንም በጠንካራ የህዝብ ግንኙነት እና የሚዲያ ስራዎች ታግዘው ሊከወኑ ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል።
የ90 ቀናት የልዩ ንቅናቄ ስራዎች እና ተግባራትም በየወቅቱ እንደሚገመገም እና ውጤታማ ድጋፍና ክትትል በማድረግ በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት እና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራዎች ላይ እምርታዊ ለውጥ በሚያመጣ መልኩ ለመፈፀም የተቀናጀ ርብርብ እንደሚደረግ የጋራ ግንዛቤ ተፈጥሯል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ኃላፊ የነበሩት አቶ ገዛኸኝ ደሲሳ የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በመሆን ተሹመዋል ።
የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ሆነው ለተሾሙት አቶ ገዛኸኝ ደሲሳ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ይመኛል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ኃላፊ የነበሩት አቶ ገዛኸኝ ደሲሳ የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በመሆን ተሹመዋል ።
የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ሆነው ለተሾሙት አቶ ገዛኸኝ ደሲሳ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ይመኛል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲን በዋና ዳይሬክተርነት የመሩት ዶ/ር እሸቱ ለማ የቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሹመዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት ዶ/ር እሸቱ ለማ የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲን ዋና ዳይሬክተር ሆነው በመሩባቸው ጊዜያት መዲናችን አዲስ አበባ ፅዱ እና ውብ እንድትሆን ለሰጡት ብቃት ያለው እና ውጤታማ አመራር ልባዊ ምስጋናውን አየገለፀ በአዲሱ የሃላፈነት ቦታቸው ስኬታማ የአመራር ዘመን እንዲሆንላቸው ይመኛል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ፅ/ ቤት
ሰኔ 05/2017 ዓ.ም
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከመላው ኢትዮጵያ ከተወጣጡ መምህራን ጋር ተወያዩ
ሰኔ 5/2017 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ከመላው ኢትዮጵያ ከተወጣጡ መምህራን ጋር መወያየታቸውን ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተለያዩ ዘርፎች ጋር የምናደርገውን ውይይት በመቀጠል ዛሬ ከመላው ኢትዮጵያ ከተወጣጡ መምህራን ጋር የሚነሱ ጉዳዮችን በማዳመጥ እና ለእቅድ ስራችን ግብዓት የሚሆኑ ሃሳቦችን በመውሰድ ውይይት አድርገናል ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።
