1 474
Suscriptores
Sin datos24 horas
-37 días
-2130 días
Archivo de publicaciones
'ቆሻሻን በአግባቡ ከተጠቀምንበት ሀብት ነወ።"
አቶ ሰኢድ አሊ የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ
በልደታ ክ/ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት የመልሶ መጠቀም ባዛርና ኤግዚቢሽን ተከፈተ።
በፕሮግራሙ የተገኙት የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሰኢድ አሊ ቆሻሻ በአግባቡ መወገድ ከቻሉ ሀብት ናቸው በመሆኑም አካባቢያችንን በማጽዳትና ቆሻሻውን መልሶ በመጠቀም የተለያዩ ጥቅም ላይ የሚውሉ ቁሳቁሶችን አየሰራን እንገኛለን ብለዋል።
አቶ ሰዒድ አክለውም በዛሬው ዕለት የተከፈተው ባዛር የስራዎቻችን ውጤቶች ናቸው ስለዚህ ከነዋሪዎቻችን ጋር በጋራ በመሆን አካባቢያችንን በማጽዳት ክ/ከተማችንን ውብና ጽዱ እናደርጋታለን ብለዋል።
የክ/ከተማው ዋና ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ተረፈ በበኩላቸው ቆሻሻ መልሶ በመጠቀም ወደ ገንዘብ መቀየር የሚቻል በመሆኑ አካባቢያችንን በማጽዳትና ቆሻሻውን ወደ ሀብት የመቀየር ስራ እየሰራን እንገኛለን ብለው የተዘጋጀው ባዛርም የተወገዱ ቆሻሻዎችን መልሶ በመጠቀም በእጅ የተሰሩ የተለያዩ ቁሳቁሶች ናቸው ብለዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ጠሮ መስጊድ አካባቢ ሚያዝያ 16 /2016 ዓ.ም ሌሊት 11 ስአት ላይ አንድ ግለሰብ እያስገነቡት ላለው ቤት ግንባታ የሚያገለግል ከፍተኛ መጠን ያለው የአፈር ክምር እና ድንጋይ ግንባታው ከሚካሄድበት ስር ባሉ ቤቶች ላይ ተንዶ በቤቶቹ ተኝተው የነበሩ 4 ሴቶችና 3 ወንዶች በድምሩ 7 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል::
የአደጋውን መንስኤ በተመለከተ በፖሊስና በዘርፉ ባለሙያዎች የሚሰጡ ሙያዊ መረጃዎች እንደተጠበቀ ሆኖ በአዲስ አበባ ከተማ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን እና በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በኩል የግንባታው ሂደት የአደጋ ደህንነት መስፈርትን ጠብቆ ባለመሰራቱ አደጋው መከሰቱን ያመላክታል::
የከተማ አስተዳደሩ በደረሰው አደጋ የተሰማውን ሃዘን እየገለፀ ለተጎጅ ቤተሰቦች ሁሉ መፅናናትን ይመኛል::
ከአደጋው ጋር ተያይዞ ለአደጋው መከሰት ምክንያት የሆነውን አካል አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ ህጋዊ ተጠያቂነትን የሚያረጋገጥ መሆኑንም ይገልጻል::
የአዲስ አበባ ከተማ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን በቀጣይ በግንባታ ስራ ላይ የሚሰማሩ ስራ ተቋራጮች ፣ አሰሪ የህንፃ ባለቤቶች፣ በግንባታ ወቅት እና ከግንባታ በኋላ አስፈላጊውን የደህንነት ጥበቃ ማሟላት እንደሚገባቸው በአፅንኦት እየገለፀ ይህን ጥንቃቄ ሳያደርጉ በሰውና በንብረት ላይ ለሚደርሱ አደጋዎች በህንፃ አዋጁና መመሪያ መሠረት የተጠናከረ የህግ ተጠያቂነትን እንደሚያሰፍን ያስታውቃል ::
ባለስልጣኑ አክሎም የግንባታ ተረፈ ምርት መንገድ ላይ ማከማቸትና የሰዎችንና የትራፊክ እንቅስቃሴን ማስተጓጎል ፣ የግንባታ ዝቅተኛውን መስፈርት ሳያሟሉ ፣ ከደረጃ በታች የሆኑ የግንባታ ቁሳቁሶችን መጠቀም ለአደጋ የሚያጋልጡ በመሆናቸው፣ እያንዳንዱ አማካሪ ፣አልሚዎችና ኮንትራክተሮች እነዚህን መስፈርቶች ጠብቀው ካልተንቀሳቀሱ የህግ ተጠያቂነት እንዳለባቸው ያስገነዝባል:::
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ባለስልጣኑ በአዋጅ የተሰጠውን ተግባርና ሀላፊነት መሠረት በማድረግ አስፈላጊውን የግንባታ መስፈርት ባላሟሉ አልሚዎች ፣ አማካሪዎችና ኮንትራክተሮች ላይ የህግ ተጠያቂነትን እንደሚያረጋግጥ በድጋሚ በአፅንኦት ይገልጻል::
Boost this post to reach up to 13677 more people if you spend $14.
ኤጀንሲው የተቋሙን መለያ ሎጎ አና ብራንዲንግ ይፋ አደረገ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ ለመንጌስትና ለግል ተቋማት እንዲሁም ለከተማዋ ነዋሪ ግንዛቤ በመፍጠር : ደረቅ ቆሻሻን በአግባቡ መሰብሰብ ማስወገድና መልሶ ጥቅም ላይ እንዲውል ትኩረት ባደረገ መልኩ በአዲስ አበባ ዩንበርስቲ አለ የስነ- ጥበባት ት/ቤት እንዲዘጋጅ ያደረገውን አዲስ መለያ ሎጎና የብራንዲንግ ስራ ተጠናቆ በዛሬው እለት የተቋሙ አመራሮች በተገኙበት ርክክብ ተካሂዷል፡፡
መለያ ሎጎው እና የብራንዲንግ ስራው የተቋሙን ራዕይ ፣ ተልእኮና ፣ እሴት በሚገልፅ መልኩ የተዘጋጀ ነው፡፡
በአርማው ላይ የተቀመጠው ሁለት ፈጣን ክብ መስመሮችን የያዘ ሲሆን ይህም "Cleansing" (ፅዳት) "C" የሚለውን ምህፃረ ቃል የያዘ ነው። ይህም የተቋሙን ዋና ዓላማና ተግብራይ ይወክላል። የመስመሮቹ ቅርፅ ከፊደልነት ባሻገርም የመጥረግ መልክ ያላቸው መስመሮች ሲሆኑ ፅዳትን : ንፅህናን እና ፈጣን የፅዳት አገልግሎትን ያመላክታል። በተጨማሪም ሁለት ግማሽ ክብ የሆኑበት ምክንያት ተቋሙ ማህበረሰብ አቀፍ የፅዳት አገልግሎት እንደሚሰጥና የሚያከናውናቸው ተግባራትን በጋራ ትብብር እንደሚሰራ ያመላክታል።
በሁለተኛው የሎጎ ክፍል ላይ የተቀመጠው ወካይ ምስል በዋናነት የተቋሙን ዘመናዊ የቆሻሻ አሰባሰብና አወጋገድ : የአፀዳድ ስርዓትን እና የመልሶ መጠቀም ተግባራትን የሚያሳይ ነው። ይህ ወካይ ምስል በአለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቅ ሲሆን ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ለመረዳት ያቀለዋል። በተጨማሪም መሀል ላይ ያለው የመልሶ መጠቀም ምልክት ግንዛቤ መፍጠርን : የማያቆርጥ የተሟላ አገልግሎት መስጠትን : ቆሻሻን ወደ ሀብትነት መቀየርን : ታታሪነትን አና በቅንጅት መስራትን ያመለክታል።
በቀለም ደረጃ ሰማያዊው ቀለም ንፅህናን : ውሃን : ብልሀነትን : ጥልቅ አሳቢነትን : ሰላማዊነትን : ትኩረት መስጠትን : ምሉዕነትን ፣ መረጋጋትን ፣ ምርምርን ፣ አለምአቀፋዊነትን ፣,በቴክኖሎጂ መታገዝን ፣ ተደራሽነትን የሚገልፅ ሲሆን አረንጓዴ ቀለሙ ደግሞ መልሶ መጠቀመን ፣ የሰው ሀይል ልማትን ፣ እድገትን ፣ ምርታማነትን ፣ ሚዛናዊነትን ፣ ስነምህዳራዊ ስምምነትን ፣ ፍሬያማነትን ፣ ሰላምን ፣ መታደስን ፣ ጤንነትን ፣ ህይወትን ፣ ለውጥን ያመላክታል።
በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ላይ የሚደርስ ስርቆትና አደጋን በጋራ እንከላከል!
በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ላይ የሚፈፀም ስርቆትና የሚደርስ አደጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መጥቷል፡፡
ስርቆትና ውድመት እየደረሰባቸው ከሚገኙ የኤሌክትሪክ መሠረተ-ልማቶች መካከል በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የተገዙ ትራንስፎርመሮች፣ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ገመዶች እና የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች ይገኙበታል፡፡
በኤሌክትሪክ መሠረተ-ልማቶች ላይ ስርቆትና ጉዳት ያደረሰ ማንኘውም አካል በቴሌኮሙኒኬሽንና ኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት አውታሮችን ለመጠበቅ በወጣው አዋጅ ቁጥር 464/97 መሰረት እስከ 10 ዓመት ፅኑ እስራት ይቀጣል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በተቋሙ የተገጠመን የኤሌክትሪክ ቆጣሪ ያሰናከለ ወይም እንዲሰናከል የፈቀደ ወይም የኤሌክትሪክ ፍጆታን እንዳይመዘገብ ያደረገ ማንኛውም አካል እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እንደሚቀጣ የኢነርጂ አዋጅ 810/2006 ይደነግጋል፡፡
በዚሁ አዋጅ አቀንፅ 28 መሰረት የኤሌክትሪክ ኃይል የሰረቀ፣ በህገ-ወጥ መንገድ ከሌላ መስመር ጋር ያገናኘ፣ መስመሩን የሰናከለ ወይም የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲሰረቅ፣ ከሌላ መስመር ጋር እንዲገናኝ ወይም መስመሩ እንዲሰናከል ያደረገ እስከ 5 ዓመት የሚደርስ ፅኑ እስራት ወይም በገንዘብ እንደሚቀጣ ያስረዳል፡፡
ስለሆነም በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች ላይ የሚደርስ ስርቆትና ጉዳት መከላከልና እንደራስ ንብረት አድረጎ መጠበቅ የሁሉም ሃላፊነት ሊሆን ይገባል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ህብረተሰቡ ሃላፊነት የጎደላቸው ግለሰቦች በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ላይ አደጋ ሲያደረሱም ሆነ አጠራጣሪ ነገር ሲመለከት በአካባቢው ለሚገኝ የፀጥታ አካል፣ የአስተዳደር አካላት ወይም ለተቋሙ በማሳወቅ ችግሩን በጋራ መከላከል ይገባል፡፡
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የአዲስ አበባ ከተማ ሰራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የክፍለ ከተሞች ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤቶችን የ9 ወራት ማዘጋጃቤታዊ አገልግሎት ሰራዎች አፈፃፀም ገመገመ::
በግምገማ መድረኩ በቀረበው የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ የሪፎርም ስራዎች፣ የቅንጅታዊ አሰራር ፣የድጋፍ እና ክትትል እና የመደበኛ አገልግሎት ስራዎች አፈፈፃፀም ከተቀመጠው ሰታንዳርድ አንጻር ስለ መፈፀሙ በዝርዝር በሪፖርት ቀርቦ ተገምግሟል::
በሪፖርቱ የክፍለ ከተማ ሰራ አስኪያጆች የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አሰጣጥን በማሳለጥ: በብቃት በማስተባበር: የብልሹ አሰራርን በመታገል እና ተጠያቂነትን በማስፈን ረገድ የተከናወኑ ተግባራት በቀረበው ሪፖርት ተመላክቷል::
በተለይም እንደ ከተማ የተዘረጋውን የቅንጅታዊ አሰረር ፎረም መሰረት በማድረግ በአራቱ ተጠሪ ተቋማት በሲቨል ምዘገባ እና በነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ በፅዳት አሰተዳደር ኤጀንሲ ፥በእሳት እና ድንገተኛ አደጋ ሰጋት ሰራ አመራር ኮሚሸን እና በአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ የሚሰጡ አገልግሎቶች ወጥ በሆነ መንገድ በሰታንዳርድ እንዲሰጡ የቅንጅታዊ አሰራር ፎረሙ አበረታች ውጤቶችን ማስመዝገብ እንዳስቻለ ተመላክቷል::
ከዚሁ ጎን ለጎን የአዲስ አበባ ከተማ ሰራ አሰኪያጅ ጽ/ቤት ከክፍለ ከተሞች እና በወረዳዎች ያካሄደውን የድጋፍ እና ክትትል ሪፖርት በሰነድ በማቅረብ ሰፊ ውይይት ተካሄዷል::
በምክትል ከንቲባ ማአረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሰራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን በዚሁ ወቅት የተጠሪ ተቋማት በየደረጃው የሚገኙ ተቋሞቻቸውን በማብቃት ረገድ ወጥ በሆነ መንገድ እንዲደግፉ የተነሳውን ጥያቄ በቀሪ 3 የሰራ ወራት ወሰደን የምንሰራበት ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል::
በተጨማሪም በቴክኖሎጅ ትግበራ ረገድ በፅዳት አስተዳደር:በሲቪል ምዝገባ እና በነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ የአገልግሎት አሰጣጥን የሚያዘምኑና እርካታን የሚጨምሩ ሆነው እንዲተገበሩ የተጀመረውን ሰራ አጠናክረን ከማስቀጠል በተጨማሪ ችግር ፈች የሆነ ድጋፍና ክትትላችንም ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል::
ክብርት ወ/ሮ ሂክማ በተለይም በቀሪ ወራት በፅዳት ረገድ በሁሉም ክ/ ከተሞች ሞዴል ወረዳዎችን የመፍጠር ሰራ በትኩረት መሰራት እንደሚኖርበት አቅጣጫ አሰቀምጠዋል ::
ከዚሁ ጋር በተያየዘ የቅድመ አደጋ የመከላከል እና የጎርፍ አደጋ ሰጋት ያለባቸውን የተለዮ አካባቢዎችን ቀድሞ በመከላከል እና በቅንጅት በመሰራት አደጋ የመቀነስ ሰራዎችን መሰራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል ::
የኤልክትሪክ አገልግሎትን በተመለከተ የእንጨት የኤሌክትሪክ ምሰሶዎችን በኮንክሪት የመቀየር ሰራዎች:- አገልግሎት የማይሰጡ የመንገድ መብራቶች እንዲሰሩ እና አገልግሎት እንዲሰጡ በየክፍለ ከተሞች ተመዝግበው እና ተለይተው በየደረጃው ካለ የተቋማቱ መዋቅር ጋር በጋራ በመሰራ ህዝብን ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል::
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
+8
ሁሌም ቃላችንን እንጠብቃለን !!
ትጋት ፣ ፅናት ፣ ውጤት !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ኤፍኤም 97.1 ጋር በመተባበር የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ከሆኑ የፅዳት አምባሳደሮች (ሻምበል አርቲስት ስዩም ዘለቀ: አርቲስት ሙሉነህ ዘለቀ እና የፅዳት አምባሳደር ሰለሞን ፀሐይ) እና የማህብረሰብ ተወካዮች ጋር በከተማው ፅዳት ላይ የተካሄደ ውይይት ላይ ያተኮረ ካለፈው ሳምንት የቀጠለ ክፍል ሁለት የሬድዮ ፕሮግራም እንዲከታተሉት በአክብሮት እንጋብዛለን::
መዲናችን ጽዳቷ በዘላቂነት የተጠበቀ ከአፍሪካ በንጽህናዋ ቀዳሚ ተወዳዳሪ እንድትሆን ለማድረግ እየተከናወነ ባለው ተግባር ዘመናዊና ሳይንሳዊ የቆሻሻ የአወጋገድ ስርአት ዝርጋታ ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ ዋ/ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ቅድስት ወልደ ጊዮርጊስ አስታወቁ::
ወ/ሮ ቅድስት ወ/ጊዮርጊስ ይህን ያስታወቁት በዛሬው እለት የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ እየተጠና ባለው የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ስርአቱን ለማዘመን ለ20 ዓመታት የሚያገለግል የተቀናጀ ደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ማስተር ፕላን ረቂቅ ሰነድ ላይ ያካሄደው የውይይት መድረክ ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ነው::
ወ/ቅድስት በዚሁ ወቅት አክለውም የከተማችን አዲስ አበባ የጽዳት ጉዳይ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍተኛ ለውጥና መሻሻል እየታዬበት እንደሆነ ጠቁመው ከተማዋ ወደ ስማርት ሲቲነት በምታደርገው የለውጥ ሂደት የመዲናዋ ጽዳት ሳይንሳዊነትንና ዘመናዊነትን ለማላበስ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል::
የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ለማ በበኩላቸው ባለፉት አምስት አመታት ከተማዋን ፅዱና ውብ ለማድረግ የተሰሩ ስራዎች ውጤታማ እንደነበሩ አንስተው ይህንን ለማስቀጠልና በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ በተለይ ለቀጣይ 20 ዓመታት ተግባራዊ የሚሆን የተቀናጀ የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ማስተር ፕላን ላይ በአንጋፋው ዩኒቨርሲቲ ጥናት ማስጠናቱን ተናግረዋል፡፡
ጥናቱ ስራ ላይ ሲውልም የተሻለ ስራ ለመስራት ያግዛልም ብለዋል፡፡
ጥናቱ በደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብ ማጓጓዝና አወጋግድ እንዲሁም ከፖሊስና ደንቦች ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን የያዘ ነው ተብሏል፡፡
በአውደ ጥናቱ ላይም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ : የዩኒቨርሲቲ ሙህራንና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በአዲስ አባና ከተማና አካባቢዉ ለእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች ፈጣን ምላሽ በመስጠት 11 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ከውድመት ማዳን መቻሉ ተገለጸ
*****************
ባለፉት ዘጠኝ ወራት በመዲናዋ ለተከሰቱ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች ፈጣን ምላሽ በመስጠት 11 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ከውድመት ማዳን ተችሏል፡፡
በአዲስ አበባ የእሳት ቃጠሎ፣ በግንባታ ወቅት የሚከሰት አደጋ፣ የጎርፍ በተደጋጋሚ ከሚከሰቱ አደጋዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
ባለፉት ዘጠኝ ወራት በመዲናዋ እና አካባቢዋ 392 አደጋዎች አጋጥመው 670 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ሲወድም የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በአደረጉት ርብርብ 39 ሰዎችን ከእሳት አደጋ፤ 85 ሰዎችን ደግሞ ከሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች በድምሩ 124 ሰዎችን በሕይወት መታደግ ሲችሉ ፤ 11 ነጥ 5 ቢሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ከውድመት ማዳን ችለዋል።
በሌላ በኩል ለኮንስትራክሽን፣ ተቆፍረው ክፍት በተቀመጡ ጉድጓዶች ምክንያት በደረሰ አደጋ የሰዎች ህይወት አልፏል ።
በዘጠኝ ወራት የደረሱ አደጋዎች ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የንብረት ውድመት መጠን በ37 ሚሊዮን ብር ቀንሷል።
ህብረተሰቡ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎችን የመከላከልና መቆጣጠር ስራን እንዲያግዝ የእሳትና አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን አሳስቧል።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎት በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
