1 474
Suscriptores
Sin datos24 horas
-37 días
-2130 días
Archivo de publicaciones
እንኳን ለ1445ኛው ዓ.ሂ ኢድ አል አድሃ/አረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ ኢድ አል አድሃ
ለመላው ሙስሊም ወገኖቻችን እንኳን ለ1445ኛው ዓ.ሂ ኢድ አል አድሃ/አረፋ በዓል አደረሳችሁ እያልኩ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአብሮነት እና የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።
በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ፤ ኢድ ሙባረክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
እንኳን ለ2016 የዒድ አል አድሃ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
የኢድ አል አድሃ በዓል የፈተናና የመሥዋዕትነት በዓል ነው፡፡ ነቢዩ ኢብራሂም በአላህ ትእዛዝ ልጃቸውን ለመሥዋዕትነት ያዘጋጁበት፤ ጽናታቸው ተፈትኖ ያሸነፉበት በዓል ነው፡፡ ለዚህ ጽናታቸውም ከአላህ ዘንድ ምትክ በግ ያገኙበት በዓል ነው፡፡
ከዚህ በዓል የምንማራቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ ማንኛውም ፈተና በጽናት ካለፉት ዋጋው ከፈተናው በላይ መሆኑን እንማርበታለን፡፡ ልጅን ያህል ነገር እንዲሠዉ መጠየቅ ከባድ ፈተና ነው፡፡ ልጅን ለመሥዋዕትነት ማዘጋጀት ደግሞ ከባድ ጽናት ነው፡፡ ከባድ ፈተና ከባድ ቆራጥነት ይፈልጋል፡፡ ከባድ ቆራጥነት ከባድ ውሳኔን ይጠይቃል፤ ከባድ ውሳኔም ታላቅ ዋጋን ያስገኛል፡፡
ኢትዮጵያን ታላቅና የበለጸገች ሀገር ለማድረግ ስንነሣ ፈተናው ከባድ እንደሚሆን እናምን ነበር፡፡ ሳይፈቱ የተከማቹ ሀገራዊ ችግሮች አሉ፡፡ በዘመናችን የተፈጠሩ አሁናዊ ችግሮችም አሉ፡፡ እነዚህ ሁለቱን በአንድ ጊዜ መጋፈጥ ይጠይቀን ነበር፡፡ ተራራውን መጋፈጥ ሳይሆን ተራራውን ማንሣት ይጠይቀን ነበር፡፡ ይሄንን ፈተና ለመጋፈጥ ከባባድ ውሳኔዎችን መወሰን ይገባን ነበር፡፡ እንደ ልጅ የምንወዳቸውን ሰዎች፣ ነገሮች፣ ቡድኖች፣ ወዳጆችና አካሄዶች ለመሠዋት መወሰን ነበረብን፡፡ መወሰን ብቻ ሳይሆን ማድረግም ነበረብን፡፡
ነቢዩ ኢብራሂም ልጃቸው ኢስማኤልን ሳይሆን በምትኩ ከአላህ የተሰጣቸውን በግ ሠዉተዋል፡፡ የእኛ ፈተና ከዚህም የባሰ ነበር፡፡ ሀገራችን ባከማቸቻቸው ዕዳዎችና ስብራቶች የተነሣ፣ ያለን አማራጭ የራሳችንን ነገር መሠዋት ብቻ ነበር፡፡ ሀገራችንን ለማዳን፣ የሕዝባችንን ዘላቂ ጥቅሞች ለማስከበር እና ከዛሬው የተሻለ ነገን ለመፍጠር ስንል፣ ብዙ ነገሮችን ሠዉተናል፡፡
ችግሮቻችን ቀስ ብለን እንድንሄድ አይፈቅዱልንም፡፡ በጥንቃቄ እንድንሮጥ እንጂ፡፡ የልማት ጥያቄዎቻችንን ለመመለስ እንደ ሕዝብ ሁላችንም የምንወዳቸውን ነገሮች ሠዉተናል፡፡ ከምንወደው አካባቢ ወደ ሌላ ሄደናል፡፡ ትዝታዎቻችንን ሠዉተናል፡፡ የባንዳውን ጩኸት ችለናል፤ ሀገርን ለመለወጥ ስንል ቤቶቻችንና ሕንጻዎቻችን እንዲፈርሱ ፈቅደናል፡፡ የመብራትና የውኃ መጥፋትን ታገሠናል፤ የመንገድ መዘጋትንና የአካባቢ መፈራረስን ተቀብለናል፡፡ ያለ መሥዋዕትነት የሚያድግ ሕዝብ፣ ያለ መሥዋዕትነት የሚበለጽግ ሀገር የለም፡፡ የኮሪደር ልማቱን በዚህ መልኩ በመሥዋዕትነት ነው የሠራነው፡፡ ፍሬው ግን እጅግ ጣፋጭ መሆኑን አይተናል፡፡
ሰላማችንን ለማስፈን በዚሁ መንገድ ነው መቀጠል ያለብን፡፡ ነፍጥን መጣል፤ ከጫካ መውጣትና የራስን ዋሻ ትቶ ወደ መስኩ መውጣትን ይፈልጋል፡፡ የራስን ኢጎ መሠዋትን ይጠይቃል፡፡ ምቾትንና ፍላጎትን መተዉን ይፈልጋል፡፡ ከመቀበል በላይ መስጠትን ይሻል፡፡ እንደ ኢብራሂም በጣም የምንሳሳለትን ነገር ለመሠዋት መቁረጥ ይፈልጋል፡፡ ሁላችንም ለመሥዋዕትነት ከተዘጋጀን የማይሳካ የሰላም መንገድ የለም፡፡ እንደ ልጅ ያሳደግናቸው ብዙ ልማዶች፣ ጠባዮች፣ አመለካከቶች፣ ርእዮተ ዓለሞችና አካሄዶች አሉን፡፡ እነርሱን ለሀገርና ለሕዝብ ጥቅም ስንል ለመሠዋት ዝግጁ ከሆንን፣ ውጤቱ ከሰላም በላይ ነው፡፡
ምክክር የሚሳካው የተሻለ ሐሳብና የላቀ ዕውቀት በማዋጣት ብቻ አይደለም፡፡ የተሻለ ሐሳብና የላቀ ዕውቀት ስላለን ብቻ የሠመረ ውጤት አናገኝም፡፡ ሌላ ወሳኝ ነገር ይፈልጋል፡፡ እርሱም መሥዋዕትነት ነው፡፡ የራስን ፍላጎት ለመሠዋት መቻል አለብን፡፡ ለትልቅ ግብ ሲባል ይቅርብኝ ማለት አለብን፡፡ ከእኔ የተሻለ ሐሳብና ልምድ፣ ዕውቀትና ጥበብ ሊኖር ይችላል ብለን ማመንና መቀበል አለብን፡፡ ለተሻለው ሐሳብ መገዛት አለብን፡፡ ልክ ልኩን ከመንገር፤ ነጥብ ከማስቆጠር፤ ጀግና ጀግና ከመጨዋት የወጣ ትኁት ሰብእና መያዝ አለብን፡፡ ይሄ ሁሉ መሥዋዕትነትን ይጠይቃል፡፡ እንደ ነቢዩ ኢብራሂም ያሳደግናቸውን ብቻ ሳይሆን አብረውን ያደጉትን ብዙ ጠባዮች ለመሠዋት መዘጋጀትን ይጠይቃል፡፡ መሥዋዕትነት የሚከፍሉ ዜጎች በበዙ ቁጥር፣ ምክክር የላቀ ውጤት ያስገኛል፡፡
የኮሪደር ልማታችን በየከተሞቻችን እንዲስፋፋ፤ ሰላማችን የጸና እና የማይደፈርስ እንዲሆን፤ ሀገራዊ ምክክሩ ኢትዮጵያ ውስጥ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ተካሂዶ እንዲሳካ - ያሳደግናቸውንና ያደጉብንን አንዳንድ ነገሮች መሥዋዕት ለማድረግ እንዘጋጅ፡፡ ሐሳቦቻችን ትጥቅ ይፍቱ፡፡ ከመተኮሻ ወደ ማረሻ እንመለስ፡፡ ከጠመንጃ ወደ ማጨጃ እንዛወር፡፡ ከዲሞትፈር ወደ ምክክር እንምጣ፡፡ ከብሔር ግጭት ወደ ሐሳብ ፍጭት እንሻገር፡፡ የምንወደውን፣ የምንፈልገውንና ያሳደግነውን እንኳን ቢሆን - ለሀገር ስንል ለመሠዋት እንዘጋጅ፡፡
መልካም በዓል ይሁን፡፡
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ስኔ 8 ቀን 2016 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ
የዛሬው ፅዳት እንደ እስልምና ብቻ ሳይሆን እንደ ኢትዮጵያዊነት የሆነ ነውና በዓሉን አክብራችሁ አጋርነታችሁን ስላሳያችሁን እናመሰግናለን የቂርቆስ ነዋሪ የእስልምና እምነት ተከታዮች
በነገው እለት የሚከበረው የኢድ አል አድሐ(አረፋ) በዓልን በማስመልከት በቂርቆስ ወረዳ 07 እስቴዲየም ዙሪያው የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ
ይህ ፅዳት የሆነው እንደ እስልምና ብቻ ሳይሆን እንደ ኢትዮጵያዊነት ነውና በዓሉን አክብራችሁ አጋርነታችሁን ስላሳያችሁን እናመሰግናለን ብለዋል የወረዳው ነዋሪ የእስልምና እምነት ተከታይ
ከሁሉም ቤተ እምነቶች የተውጣጡ ተወካዮችና የቂርቆስ ነዋሪዎች የተሳተፉበት ይኸው የጽዳት መርሃ ግብር ከማለዳው 12.00 ሰዓት ጀምሮ ተካሄዷል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዲላላ ሁላላ፣የክፍለ ከተማው ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘሪሁን ዘለቀን ጨምሮ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።
ሰኔ 8/ 2016
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager?is_from_webapp=1&sender_device=pc
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የጽ/ ቤቱ የ2016 ዓ.ም በጀት አመት የ11 ወራት መልካም የስራ አፈፃፀሞች ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገለፀ።
የአዲስ አበባ ከተማ የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የ2016 ዓ.ም በጀት አመት የ11 ወራት የስራ እቅድ አፈፃፀም መልካም የሚባል ነው ሲሉ በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ማሾ ኦላና ተናገሩ።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ማሾ ኦላና የማዘጋጃ ቤታዊ ዘርፉ ባለፋት 11 ወራት የእቅድ አፈፃፀም መድረክ ላይ እንደገለፁት በአገልግሎት አሰጣጥ ረገድ መሻሻል የታየባቸው ማለትም የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ከማዘመን አንፃር፣የአደጋ ስጋት ቅነሳና አገልግሎት ተደራሽነት፣የነዋሪዎች አገልግሎት አሰጣጥን ከማዘመን ሰፊ ስራዎች መሠራት ተችሏል ሲሉ ገልፀዋል።
አቶ ማሾ ኦላና አክለውም በስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ስር ያሉ ተጠሪ ተቋማት እየሰጡት ያለው አገልግሎቶች በማዘመን፣የክትትል እና የድጋፍ ስርአት ያሉበትን ደረጃ አሁን ካለዉ በተሻለ በሁሉም ተቋማት አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ሲሉ አሳስበዋል::
በሲቪል ምዝገባና በነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የተጀመሩ ስራዎችን በቴክኖሎጂ ለመስራት የተጀመሩ ስራዎች እንዲሁም ብልሹ አሰራርና ሌብነትን ለመቅረፍ የተወሰዱ እርምጃዎች በቀጣይም አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አቀጣጫ አስቀምጠዋል።
የቢሮውን የበጀት ዓመት የ11 ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በጽ/ቤቱ ሀላፊ በአቶ ወሰን መግራ የቀረበ ሲሆን፤ በቀረበው ሪፖርት ላይ ዉይይት ተደርጎበታል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ኤፍኤም 96. 3 ጋር በመተባበር ዘወትር በየሳምንቱ ሰኞ ከጠዋቱ 2 ስአት 30 እስከ 3 ስአት የሚያቀርብላችሁ ፕሮግራም በዚህ ሳምንት ትኩረቱን በጽዳት ሠራተኞች ላይ አድርጓል። በማህበራዊ ሚዲያ ገጻችን ይከታተሉት ዘንድ በአክብሮት ተጋብዘዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የኮሚሽኑን የድንገተኛ አደጋዎች ህክምና አገልግሎትን ለማሳደግ የሚያስችል ፍሬያማ ውይይት አካሄደ።
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት ተጠሪ ተቋም በሆነዉ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ማስልጠኛ ማዕከል ከሚሰጡ አገልግሎቶች አንዱ የሆነዉ የድንገተኛ አደጋዎች ህክምና /ፓራ ሜዲክ/ ስልጠና ክፍልን ወደ አካዳሚ ለማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ።
የከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ባዘጋጀው በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የኮሚሽኑ የፓራ ሜዲክ ስልጠና ክፍል ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ጋር በጋራና በትብብር ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ በዛሬው እለት ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓ.ም የተቋማቱ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ውጤታማ ውይይት ተካሂዷል።
በምክክር መድረኩ የማሰልጠኛ ማዕከሉ የፓራሜዲክ ስልጠና ክፍል እየሰጣቸዉ ያሉ የስልጠና ዓይነቶችንና አሁን ላይ ያሉበትን ዉስንነቶች በተመለከተ ለዉይይት መነሻ የሚሆኑ ገለጻ ተደርጓል።
በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ክብርት ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን የዉይይት መድረኩን በመሩበት ወቅት እንደተናገሩት የኮሚሽኑን የፓራ ሜዲክ ስልጠና ክፍል መደገፍ በተለይም በጤናዉ ዘርፍ ያሉ ተቋማት የበለጠ ኃላፊነት ያለባቸዉ በመሆኑ የከተማዉ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የፓራሜድክ ክፍሉን ወደስልጠና ማዕከል ለማሳደግ በሚደረገዉ ጥረት ሂደቱን በማስተባበርና በመምራት ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዮሀንስ ጫላ በኩላቸዉ እንደተናገሩት ኮሚሽን መ/ቤቱ የድንገተኛ አደጋዎች ህክምና አገልግሎትን ለማሳደግ በስልጠናዉ ዘርፍ የጀመራቸዉ ስራዎች አበረታች መሆናቸዉን ጠቅሰዉ ይኸን ክፍል መደገፍ የጤና ዘርፉን መደገፍ ኃላፊነታችን በመሆኑ የሚጠበቅብንን በተግባር እንወጣለን ብለዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ከሚገኙ ሆስፒታሎች የተገኙ ኃላፊዎች በበኩላቸዉ እንደተናገሩት የኮሚሽኑን የስልጠና ክፍል ከፍወዳለ ደረጃ ለማሸጋገር በስልጠና ማኑዋል ፣በባለሙያ፣ የክሊኒክ ክፍሉን በማደራጀትና በመሳሰሉት ጉዳዮች አስፈላጊዉን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛዉ የኮሚሽኑን ማስልጠኛ ማዕከል ለመደገፍ በተደረገዉ እንቅስቃሴ የከተማዉ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤትና የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ስራ ኃላፊዎች ለሰጡት ትኩረትና ድጋፍ ምስጋናቸዉን አቅርበዋል።
በዉይይቱ ማጠቃለያ ክብርት ወ/ሮ ሂክማ እንደተናገሩት የአዲስ አበባ ጤና ቢሮና በስሩ ያሉ የሆስፒታል ኃላፊዎች በቀረበላቸዉ ጥሪ መሰረት ለሰጡት ፈጣን ምላሽ አመስግነዉ በቀጣይ በሚኖረዉ መድረክ የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተዘጋጅቶ ወደተግባር እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የክፍለ ከተሞች ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤቶችን የ11 ወራት የእቅድ አፈፃፀም ገመገመ ::
የከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት የክፍለ ከተሞች ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤቶችን የ11 ወራት የእቅድ አፈፃፀም የገመገመ ሲሆን በመድረኩም የአፈፃፀም ሪፖርታቸው ቀርቦ ዉይይት ተካሂዶበታል።
በሪፖርቱ የክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት የተሰሩ የሪፎርም ስራዎች፣ የቅንጅታዊ አሰራር ፣የድጋፍ እና ክትትል፣የአገልግሎት አሰጣጥን ከማሻሻል፣ ከፅዳት አንፃር፣ ምቹ የስራ አካባቢን ከመፍጠር፣ አገልግሎትን በቴክኖሎጂ ከማዘመን ፣ ስራዎችን በስታንዳርድ ከመፈፀም እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከመፍታት አንጻር በሪፖርቱ በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል ::
በመድረኩ በቢሮ ሀላፊ ማአረግ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ዋና ሰራ አስኪያጅ ወ/ሮ ቆንጅት ደበላ ባለፋት 11 ወራት በሁሉም ክፍለ ከተሞች ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤቶች የተሰሩ ስራዎችን መልካም አፈፃፀሞች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አመልክተው በክፍተት የታዩትን በፍጥነት በቀሪ ጊዜ የማስተካከያ ስራ ማከናወን እንደሚገባ ተናግረዋል።
ወ/ሮ ቆንጅት አክለዉም በመብራት እና በፅዳት በኩል ያልተተገበሩ በተለይም በፅዳት ረገድ ከቅብብሎሽ ጣቢያና ከዞኒንግ ፅዳት ጋር በተያያዘ በሁሉም ክ/ ከተሞች በትኩረት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል::
በተጨማሪም አገልግሎትን በቴክኖሎጂ ከማዘመን አንፃር በሲቪል ምዝገባ እና በነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ የአገልግሎት አሰጣጥን የሚያዘምኑና አገልግሎቱን ቀላል የሚያደርጉ የተጀመሩ ስራዎች አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ቆሻሻን መልሶ በመጠቀም ወደ ሀብትነት መቀየር ላይ እየተሰሩ ያሉ የፈጠራ ውጤቶችን የሚያሳይ ዐውደ-ርዕይ ተከፈተ።
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት አዘጋጅነት የቀረበው ዐውደ ርዕይው ቆሻሻን መልሶ በመጠቀም ወደ ሀብትነት መቀየር ላይ እየተሰሩ ያሉ የፈጠራ ውጤቶችን የሚያሳይ ዐውደ-ርዕይ ተከፈተ።
ይህ የቀረበው ዐውደ ርዕይ አላማ ህብረተሰቡን ግንዛቤ በማስፋት ቆሻሻ ሀብት መሆኑን ለማሳየት ያለመ ሲሆን ፈጠራን በማበረታታት ቆሻሻን ለአገልግሎት መዋልን ያለመ ነው።
በዐውደ-ርዕይው ለጉብኝት፣ለተሞክሮ ማስፋትና ታዳጊዎችን በማበረታት፣ አካባቢን ከብክለት ለመከላለከል፣ እንዲሁም ቆሻሻ ሀብት መሆኑን ለማሳየት ነው ።
ዐውደ-ርዕይውን የከፈቱት የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አፈጉባኤ አቶ ወጋየሁ ሀይሉ ፤ የክፍለ ከተማው ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራ ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ድላየሁ ታምሬን ጨምሮ ሌሎችም አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተው ተመልክተውታል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
Lafto Communication- ላፍቶ
የአዲስ አበባ ከተማ ሰራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የከተማውን ኤሌክትሪክ አገልግሎት የ11 ወራት የስራ አፈፃፀም ገመገመ።
የከተማ ስራ አሰኪያጅ ፅ/ቤት የአዲስ አበባ ከተማ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያለፉት የ11 ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ከተቋሙ አመራሮች ጋር በጋራ በዛሬው እለት ሰኔ 5 / 2016 ገምግሟል።
በመድረኩ በተቋሙ ባለፉት 11 ወራት አገልግሎቶችን በስታንዳርድ ከመፈፀም፣ምቹ የስራ ከባቢዎችን ከመፍጠር፣ ፣የኮሙዩኒኬሽን ስራዎችን አጠናክሮ ከማስቀጠል፣የቅሬታ አፈታት ስርዓትን እና የደንበኞች እርካታን ከማሳደግ አንጻር በጥንካሬ እና በክፍተት የነበሩ አፈፃፀሞች በሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።
በተጨማሪም ቅንጅታዊ አሰራርን እና የሪፎርም ስራዎችን ከማጠናከር ፣የጥራትና የቁጥጥር ስራዎች እንዲሁም የመሰረተ ልማት አፈፃፀሞችና ሌሎች ስራዎች በመድረኩ ተገምግሟል::
በዉይይቱ ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ክብርት ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን እንደገለፁት ተቋሙ በመሠረተ ልማት ዝርጋታ እና የከተማውን ነዋሪ አዳጊ ፍላጎት ለሟሟላት እና አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል እያደረገ ያለው ጥረቶች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አመልክተዋል።
በሌላ በኩል ተቋሙ አገልግሎትን በስታንደርድ መሠረት ከመስጠት ፣ከባለሙያ ስነምግባር ጋር እና ከሀይል መቆራረጥ ጋር የሚታዩ ክፍቶቶችን በመለየት እንዲሁም ለአገልግሎት ጥያቄ ፈጣን ምላሽ መስጠት ላይ የተጠናከረ ስራ መስራት እንደሚገባ አሳስበው የቀጣይ የ2017 በጀት አመት እቅድ በልዩ ትኩረት የተቀመጡ የትኩረት አቅጣጫዎችን በማካተት እንዲዘጋጅ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በአደጋ ቅነሳ ዘርፍ የተሻለ ዉጤት ለማስመዝገብ እየተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገለጸ።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ተጠሪ ተቋም የሆነዉ የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት የ11 ወራት የስራ አፈፃጸም ዛሬ ሰኔ 5 ቀን 2016 ዓ.ም በጽ/ ቤቱ ተገምግሟል::
በግምገማ መድረኩ የኮሚሽኑ የአስራ አንድ ወራት አፈጻጸም ረፖርት ቀርቦ ዉይይት የተካሄደበት ሲሆን የኮሚሽኑ አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ የማልማት ስራዎችን በራስ አቅም ስለመተግበሩና በጎ ፈቃደኞች አሰልጥኖ ወደ ተግባር በማስገባት እንዲሁም አደጋን ፈጥኖ የመቆጣጠር አቅም ማደጉ በሪፖርቱ
ተብራርቷል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ አደጋን ለመቀነስና የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ የተለያዩ የሚዲያ አግባቦችን በመጠቀም የተከናወኑ ስራዎች ለህብረተሰቡ ተደራሽ ስለመደረጋቸዉና በዚህ ሂደትም የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ድጋፍ ከፍተኛ እንደነበረ ተገልጿል።
የግምገማ መድረኩን የመሩት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ከብርት ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን እንደተናገሩት የአደጋ ቅነሳ ስራን በተሻለ አቅም ለመፈጸም በተጠሪ ተቋማት ካሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ መዋቅሮች ጋር መቀናጀት እንደሚገባ ጠቅሰዉ ተቋማት የአደጋ ቅነሳ ስራን በእቅዳቸዉ አካተዉ የመሩበትን አግባብ የማጠቃላያ ምዕራፍ በተቋማቱ ጋር እንዲገመገም አሳስበዋል።
ክብርት ወ/ሮ ሂክማ አያይዘዉ በኮሚሽን መ/ቤቱ ያልተጠናቀቁ የሪፎርም ስራዎች ተካተዉ የ2017 የሪፎርም ስራዎች ዕቅድ ተዘጋጅቶ እንዲቀርብ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
በሪፖርቱ በቀረቡ አፈጻጸሞች ጥያቄና አስተያየቶች ቀርቦ በኮሚሽኑ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
