1 474
Suscriptores
Sin datos24 horas
-37 días
-2130 días
Archivo de publicaciones
የከተማችን አንዱ ድምቀት የሆነው 24ኛውን የታላቁ ሩጫ የጎዳና ውድድር ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ፣ ሚኒስትሮች፣ አምባሳደሮች፣ ብርቅዬ አትሌቶቻችን እንዲሁም የከተማችን ነዋሪዎች በተገኙበት ዛሬ ማለዳ አስጀምረናል።
ታላቁ ሩጫ ላለፉት 24 ዓመታት ኢትዮጵያን ለዓለም እያስተዋወቀ የቆየ ሲሆን የዘንድሮውን ውድድር ለየት የሚያደርገው አዲስ አበባ ተዉባ፣ መንገዶቿ ሰፍተዉ፣ አምረዉና ደምቀዉ ዓለም አቀፍ የስበት ማዕከል መሆን በጀመረችበት ወቅት የተካሄደ መሆኑ ነው።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር 5ኛ ዓመት የብልፅግና ፓርቲ የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ "ህዳር ሲጸዳ" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ያለው የጽዳት ንቅናቄ በዛሬው እለትም ቀጥሏል።
በዚሁ የፅዳት ዘመቻ ላይ የየካ ክፍለ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ከፍያለው ተሾመ፣ የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ፀሀይ ዮናስ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ከፍተኛ ባለሙያ ወ/ሮ አለምገና ቱጂን ጨምሮ የክፍለ ከተማ፣ የወረዳ አመራሮች፣ የፅዳት አስተዳደር ባለሙያዎች፣ የደንብ ማስከበር ኦፊሶች አባላት እንዲሁም የወረዳው ማህበረሰብ ተሳታፊ ሆነዋል።
በዕለቱ በጽዳት ንቅናቄው ላይ የተገኙት የየካ ክፍለ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ከፍያለው ተሾመ በርካታ የፅዳት ስራዎችን በመስራት ከተማችን ፅዱ እና የነዋሪዎቿ የምትመች ንፁህ ከተማን በመፍጠር ከሌሎች የአለም ከተሞች ተወዳዳሪ ማድረግ መቻሉን ገልፀው ሁል ጊዜ አካባቢን ማፅዳት ባህል ማድረግ ይገባልም ብለዋል።
የወረዳ 03 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ፀሀይ ዮናስ በበኩላቸው 5ኛ ዓመት የብልፅግና ፓርቲ የምስረታ በዓል በተለያዩ ኩነቶች እየተከበረ ያለ ሲሆን ፓርቲዉ ወደ ስልጣን ከመጣ ወዲህ በተለየ ትኩረት ሲያከናዉን የቆየዉን የከተማ ዉበት እና የአካባቢ ፅዳት ተጠቃሽ መሆናቸዉን ገልፀዉ ነዋሪዎች ፅዳትን የዘወትር ሥራ በማድረግ ሁሉንም ቀጠናና ብሎክ ሞዴል ለመፍጠር ያለአግባብ ባልተፈቀዱ ቦታዎች ቆሻሻን የሚጥሉ አካላት በህግ የሚያስቀጣ መሆኑን በማስረፅ ቆሻሻን ብቻ ሳይሆን በታኝና አንድነታችን የሚሸረሽሩ አስተሳሰቦችን ጭምር ማረም እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ከፍተኛ ባለሙያ ወ/ሮ አለምገና ቱጂ እንደገለጹት ለሶስትና አራት ዓመታት አዲስ አበባ ከተማ የቱሪዝም መዳረሻና ለኑሮ ምቹ ከተማ እንዲትሆን ከተማ አስተዳደሩ ዘርፈ-ብዙ ተግባራትን ማከናወኑን አንስተው አዲስ አበባ እንደስሟ ታላላቅ የልማትና የሰው ተኮር ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑንና ፅዳት የስልጣኔ ምልክት ስለሆነም የሁሉም ማህበረሰብ ተሳትፎ የሚጠይቅ አስታዉቀዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የጋራ መኖሪያ ቤት ቀሪ ማጠናቀቂያ ግንባታ ላይ ምሽት እና ቀን ለተሰማሩ ሰራተኞች የማእድ ማጋራት ስራ ተሰራ ።
በአያት ሳይት 2 የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ቀሪ የማጠናቀቂያ ስራ ለመስራት ምሽት እና ቀን ለተሰማሩ ሰራተኞች ነው ማእድ ማጋራቱ የተደረገው።
በሰአቱ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ወንድሙ ሴታ እንዳሉት ለነዋሪ ተላልፈው ግንባታቸው ባለመጠናቀቁ ቆመው የነበሩ ቤቶችን ለመስራት ምሽት እና ቀን የተሰማራችሁ ሰራተኞች እያንዳንዳችሁ የምታበረክቱት አስተዋፅኦ የጀመርነውን ጉዞ እንድናሳካ ቀላል የሚባል ባለመሆኑ ኢትዮጵያ ታመሰግናችኋለች ብለዋል።
በአዲስ የስራ ባህል የግንባታ ስራውን በማቀላጠፍ ከተማ አስተዳደሩን እያገዙ ያሉ ስራ ተቋራጮች እና ማህበራትን በማመስገን ከሌላችሁ ላይ ለሰራተኞቻችሁ በማካፈላችሁ እና ማእድ በማጋራታችሁ በድጋሚ እናመሰግናለን ያሉት ደግሞ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቅድስት ወ ጊዮርጊስ ናቸው ።
ከተማ አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ እየተከታተለ ያለውን ስራ በመስራታችሁ የታሪክ ተቋዳሽ ናችሁ እና ልትኮሩ ይገባችኋል በማለት የተናገሩት ደግሞ አቶ ሽመልስ ታምራት የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሲሆኑ መጨረሻውን ለማየት ደግሞ ከዚህ የበለጠ ሀላፊነታችሁን ተወጥታችሁ ቤቶቹን ሙሉ በሙሉ ነዋሪ እንዲገባባቸው ማድረግ አለባችሁ ብለዋል።
የማእድ ማጋራት የተደረገው በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ስር የሚገኙ ስራ ተቋራጮች እና ማህበራትን በማስተባበር ነው።
A.A Housing Development & Administration Bureau
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ለነዋሪዎች በእጣ የተላለፉ ቤቶችን ለመኖሪያ ምቹ ለማድረግ የሚሰራው ስራ ያለበት ደረጃ ተጎበኘ
ጉብኝቱ ትኩረት ያደረገው በ40/60 የቤት ልማት መርሀ ግብር በእጣ ተላልፎ የማጠናቀቂያ ስራ እየተሰራ በሚገኝበት የአያት ሳይት 2 የቤቶች እና የመሰረተ ልማት ግንባታ ያለበት ደረጃ ነው።
በምልከታው በተለይም በር እና መስኮት ላልተገጠመላቸው ቤቶች የአልሙኒየም እና መስታወት ማመርት እና መግጠም ስራ ያለበት ደረጃ ጥሩ የሚባል ነው ያሉት በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አገጣጠሙ ላይ የሚታዩ የተወሰኑ ችግሮች ማስተካከያ እንዲደረግባቸው አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
ከመሰረተ ልማት አቅርቦት አንፃርም የውስጥ ለውስጥ መንገድ ስራ ዝርጋታ የአፈር መቁረጥ ስራ መጀመሩ ፤ የውሀ ከፍተኛ እና መካከለኛ መስመር ዝርጋታ መጀመሩ ፤ የፍሳሽ ማንሆል ማስቀመጥ እና መስመር ዝርጋታ እንዲሁም የመብራት ፖል መትከል እና እና መስመር ዝርጋታ መጀመሩን መመልከት ተችሏል።
የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽንም ለመሰረተ ልማት ዝርጋታው ምቹ ሁኔታ የመፍጠር ስራ እየሰራ እንደሚገኝ መመልከት ተችሏል።
በጉብኝቱ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ወንድሙ ሴታን ጨምሮ የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብረሀም ታደሰ ፤ የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቅድስት ወ/ጊዮርጊስ ፣ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታምራት እንዲሁም የኮርፖሬሽኑ እና የቅርንጫፍ መሰሪያ ቤቱ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
A.A Housing Development & Administration Bureau
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ለልጆቻችን ጠንካራ ሀገር ለማስረከብ ተቋም በመገንባት ፣ በማስከበር እና በማስቀጠል ሁላችንም ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል፡፡
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዳጉ በቀጥታ ስርጭት ፕሮግራሙ በኮሪደር ልማት ዙሪያ ከከፍተኛ አመራሮች ጋር ቆይታ አድርጓል። በዚሁ ፕሮግራም ላይ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት አመራሮቾ ያነሷቸው አንኳር ነጥቦች እንደሚከተለው ቀርቧል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት ምስረታ በዓልን አስመልክቶ የፅዳት ዘመቻ መርሃ ግብር ተካሄደ
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ "ህዳር ሲፀዳ ፅዱ እና ውብ አዲስ አበባን መፍጠር" በሚል የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት ምስረታ በዓልን አስመልክቶ የፅዳት ዘመቻ መርሃ ግብር ተካሂዷል።
በወረዳ 9 በተካሄደው የአንድ ማዕከል ፅዳት ዘመቻ መርሃ ግብር ላይ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ካባ መብራቱ ጨምሮ ሌሎች የክፍለ ከተማና ወረዳ አመራሮች፤ የፀጥታ አካላትና ጥሪ የተደረገላቸው ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።
የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ካባ መብራቱ እንዳሉት አካባቢን ማፅዳት የስልጡን ማህበረሰብ መገለጫ እንደመሆኑ ሳምንታዊው የፅዳት ዘመቻ እንደተጠበቀ ሆኖ ህዳር 12 ድረስ በሁሉም ወረዳዎችና ብሎኮች ላይ በየዕለቱ አካባቢን ማፅዳትና ንፅህናውን መጠበቅ ይገባል ብለዋል።
ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አክለውም ብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ እንደሚገኝ በመጠቆም ፓርቲው ሰው ተኮር በመሆኑ በአየር ብክለት ምክንያት በዜጎች ላይ የጤና እክል እንዳይከት ከተማዋን ውብ፣ ፅዱና አረንጓዴ በማድረግ ሂደት ውጤታማ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።
#laftocommunication
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
" ህዳር ሲታጠንን ወደ ህዳር ሲጸዳ !! "
በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር "ህዳር ሲታጠንን ወደ ህዳር ሲጸዳ !! " በሚል መሪ ቃል በ10ሩም ወረዳ በሚገኙ ብሎኮች የጽዳት ንቅናቄ ተካሄደ።
የጽዳት ዘመቻው ዋና ዓላማ ህዳር ሲታጠንን ወደ ህዳር ሲጸዳ ማህበረሰቡ አስተሳሰቡን በመቀየር አካባቢውን ከአየር ብክለት በመጠበቅ ቆሻሻ ሀብት መሆኑን እንዲረዳ ማስቻል እንደሆነ ተገልጿል።
በጽዳት ዘመቻው ላይ የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አማን አንዱዓለም እደተናገሩት ህዳር ሲታጠን በሚል በባህላዊ መንገድ ቆሻሻ ተሰብስቦ ይቃጠል ነበር አሁን ማጠኑን በማስቀረት ወደ ማጽዳት ዘመቻ እየሔድን ነው፤ አዲስ አበባን እንደ ስሟ አዲስ እና ውብ በማድረግ ከሌሎችች የአለም ከተሞች ተወዳዳሪ በማድረግ ነዋሪዎቿ አካባቢያቸውንና ጤንነታቸው የተጠበቀ በአስተሳሰብ የበለፀጉ በኢኮኖሚ ያደጉ እዲሆኑ እንደሚገባና ቆሻሻ ሃብት መሆኑን ማስገንዘብ ያስፈልጋል ብለዋል።
የክፍለ ከተማው ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሰለ ይትባረክ በበኩላቸው ክፍለ ከተማውን የጽዳት ተምሳሌት ለማድረግ በርካታ ተግባራት በማከናወን በተለይም ጽዳት የአንድ ወቅት ስራ ሳይሆን የሁልጊዜ ተግባራችን ለማድረግ ህብረተሰብ ተኮር እንዲሆን በትኩረት እየተሰራ ይገኛል በህዳር ወር ቆሻሻን ከማቃጠል ወደ ህዳር ሲጸዳ በማረም ቆሻሻ ሀብት በመሆኑ ከማቃጠል ይልቅ በአግባቡ በማስወገድ ጥቅም ላይ ማዋል ይገባል ብለዋል።
በክፍለ ከተማው በ10ሩም ወረዳ በሚገኙ ብሎኮች በተካሄደው ጽዳት ዘመቻው የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች ፣ የሃይማኖት አባቶች ፣ የጸጥታ አካላት ፣ የጽዳት አምባሳደሮችና የአካባቢው ነዋሪዎች ተሳትፈውበታል።
Gullele communication-ጉለሌ
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ከንቲባ አዳነችን አቤቤ፣ የአዲስ አበባ ምክር ቤት አፈጉባኤ እንዲሁም የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ሃላፊዎች ቦሌ ካርጎ ቡልቡላ እስከ አቃቂ ድልድይ ያለውን የአረንጏዴ ልማት ስራ ጎብኝተዋል::
ዛሬ የተጎበኘው የአረንጏዴ ልማት በክፍለከተማው የተገነባ ሲሆን በውስጡም:-
- 13 ኪ/ሜ የሚሸፍን የአረንጏዴ ልማት ስራን
- አራት ዘመናዊ የህዝብ መዝናኛ ፓርኮች
- ሁለት የህጻናት መጫዎቻ ሜዳዎች
- አንድ የስፖርት ሜዳ
- አምስት ዘመናዊ የህዝብ መገልገያ የጋራ መጸዳጃ ቤቶች
- ደረጃውን የጠበቀ ሰፊ የእግረኞች መንገድ
- በከተማው ስታንዳርድ መሰረት የተሰራ የህንጻዎች እድሳት
- ፋውንቴኖች
- የመዝናኛ ፓርኮች
- የህዝብ መናፈሻ ቦታዎችን ያካተተ ስራ ነው::
5ኛ ዓመት የብልፅግና ፓርቲ የምስረታ በዓል'ን ምክንያት በማድረግ "ህዳር ሲፀዳ" የጽዳት ዘመቻ ንቅናቄ ተካሄደ።
"ህዳር ሲፀዳ" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው የፅዳት ዘመቻ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የየካ ወረዳ 08 ዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ መሳይ ተካልኝ በአሁኑ ሰዓት 5ኛ ዓመት የብልፅግና ፓርቲ የምስረታ በዓል በተለያዩ ኩነቶች እየተከበረ ያለ ሲሆን ከአገራዊ ለውጡ ወዲህ በተለየ ትኩረት ሲከናዉን የቆየዉን የከተማ ዉበት እና የአካባቢ ፅዳት ተጠቃሽ መሆናቸዉን ገልፀዋል። ነዋሪዎች ፅዳትን የዘወትር ሥራ በማድረግ ሁሉንም ቀጠናና ብሎክ ሞዴል ለመፍጠር ያለአግባብ ባልተፈቀዱ ቦታዎች ቆሻሻን የሚጥሉ አካላት በህግ የሚያስቀጣ መሆኑን በማስረፅ ቆሻሻን ብቻ ሳይሆን በታኝና አንድነታችን የሚሸረሽሩ አስተሳሰቦችን ጭምር ማረም እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
በመቀጠልም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ባለሙያ እንደገለጹት ለሶስትና አራት ዓመታት አዲስ አበባ ከተማ የቱሪዝም መዳረሻና ለኑሮ ምቹ ከተማ እንዲትሆን ከተማ አስተዳደሩ ዘርፈ-ብዙ ተግባራትን ማከናወኑን አንስተው አዲስ አበባ እንደስሟ ታላላቅ የልማትና የሰው ተኮር ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑንና ፅዳት የስልጣኔ ምልክት ስለሆነም የሁሉም ማህበረሰብ ተሳትፎ የሚጠይቅ አስታዉቀዋል።
በመጨረሻም የየካ ክ/ከተማ ብልጽግና ፖርቲ ጽ/ቤት ሴት ሊግ ሰብሳቢ ወ/ሮ ዉዴ ሰጡሌ አዲስ አበባ የሁላችን ከተማና ታላላቅ አለምአቀፍ ጉባኤዎች ስለምከናወኑ ነዋሪው የዘወትር ተግባር አድርጎ እንዲተገብሩ ጥሪ አስተላልፈው ሁሉም ነዋሪ ብሎኩን ፅዱ የማድረግ ተግባር የሁሉም ነዋሪ ሚናዉን መወጣት አለበት ብሏል።
በመጨረሻም የወረዳዉ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ፍቅሩ የፅዳት ዘመቻ መርሃ-ግብሩን አስጀምረዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇?Addis Ababa City Manager's OfficeGER1
Telgram:-
??👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
