cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ቃርሚያ

ነፃ ጠቃሚ ሀሳብ ጥበብ በጨዋ ደንብ @azg21

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
142
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ጣፋጭ ውሸት የሚጣረሱ ሀሳቦችን የመያዝ ባህሪ (Cognitive Dissonance) አንድ ቀበሮ የወይን ፍሬ ያይና ለመብላት ይቋምጣል። ሙክክ ብሎ የበሰለውን ትልቅ ፍሬ ለማውረድም ተንጠራራ፡፡ የፊት እግሩን የወይን ግንዱ ላይ አስደገፈና አንገቱን ወደ ፍሬዋ አንጠራራ፤ ሊደርስባት ግን አልቻለም፡፡ በዚህ እየተናደደ እንደገና እድሉን ለመሞከር ወሰነ ፤ ራሱን በሚገባ አዘጋጅቶ ወደ ላይ ተወረወረ። አፉ ግን ቀዝቃዛ አየር ብቻ ቀዝፎ ተመለሰ፡፡ ለሶስተኛም ጊዜም ዘሎ ቢሞክር ወደ ኋላ ወደቀና ተፈጠፈጠ፡፡ ፍሬው ይቅርና አንዲት ቅጠል እንኳን ግን አልወደቀችም፡፡ ቀበሮውም አፍንጫውን አዞረና ‹‹ይህ ፍሬ ሲጀምር አልበሰለም፤ ለጎምዛዛ ፍሬ እንዲህ የሚያደርገኝ ምንድን ነው? ብሎ ወደ ጫካው ፈረጠጠ፡፡" - ግሪካዊው ገጣሚ አይሶፕ የተለመዱ የምክንያታዊነት ስህተቶች ከሆኑት መካከል አንዱን ለማስረዳት ይህንን አፈ ታሪክ ፈጥሮ ነበር፡፡ ይህም የአስተሳሰቦች መጣረስ ነው፡፡ እሱ በፈጠረው በዚህ ታሪክ ውስጥ የቀበሮው የአስተሳሰብ መጣረስ የተፈጠረው ቀበሮውን የሆነ ነገር ለማድረግ ሲፈልግና አልሳካለት ሲለው ነው፡፡ ይህ ታሪክ ከሚከተሉት ሶስት መንገዶች መካከል በአንዱ ውስጥ ማለፉ የግድ ነው፡፡ አንደኛው መንገድ እንደ ምንም ብሎ ፍሬዋን ማውረድ ነው። ሁለተኛው ችሎታው በቂ አለመሆኑን አምኖ መቀበል፣ ሶስተኛው ደግሞ የተፈጠረውን ነገር ወደ ኋላ ተመልሶ እንደገና በመተርጎም ሃሳብ መቀየር ነው፡፡ #የመጨረሻው አማራጭ የሚጣረሱ አስተሳሰቦችን ችግር የመያዝ የእሱ ነጸብራቅ ምሳሌ ነው። (Cognitive Dissonance) በቅርቡ የአሸባሪው የህውሀት ቡድን አመራሮች በነፃ መለቀቃቸው ይታወቃል።ይህ በብዙሀኑ ህዝብ ዘንድ ትልቅ መደናገረን ፈጥሯል።መጀመሪያ መንግስት በህውሀት እና እሱን በሚደገፋ ምዕራብውያን ላይ ከፍተኛ ህዝባዊ ዘመቻ ማድረጉ ይታወሳል። በየሚዲያውም ህውሃት ለመስማትና ለማየት የሚቀፉ ግፎችን በንፁሀን ህዝብ ላይ እንደፈፀመ እያሳዩን ነበር። አሁን ደግሞ ጦርነቱ ባልተጠናቀቀበት እና ህውሀት ይበልጥ ለመዋጋት በተዘጋጀበት ጊዜ ለነዚህ ሰዎች ምህረት እና ይቅርታ ማድረግ እንዳለብን ይነግሩናል። እውነታው ግን መንግስት ርህራሄ ወይም ሰብዓዊነት ተሰምቶት ሳይሆን የምዕራባውያን ጫናን መቋቋም ስላልቻለ ይመስለኛል። የከሰረ የዲፕሎማሲ አቋሙ ብዙ ዋጋ አስከፍሎታል። እናም ይህንንን ችግሩን ሽፋን ለመስጠት ስለ ይቅርባይነት እና ስለ ምህረት ከክርስቶስ በላይ ሊሰብከን ይሞክራል።መንግስት ስህተቱን ማመን አይፈልግም። ከዚህ በተቃራኒው የወሰነው ውሳኔ ብዙ ችግሮችን እያስተናገደም እንኳን ቢሆን ሰላም የሚያመጣ ውሳኔ እንደሆነ ይነግረናል። በየጊዜውም ይህንን ኢ-ምክንያታዊ አቋሙን የሚደግፍለትን ጣፋጭ ውሸት ይፈበርካል። ገጣሚው እንዲህ ይላል "የጎበዙን ቀበሮ ጨዋታ የፈለግከውን ያህል መጫወት ትችላለህ፣ በዚህ መንገድ ግን የወይኑን ፍሬ አታገኘውም::" መነሻ ሀሳብ (The Art of clearly thinking) ሮልፍ ዶብሊ #አቤል የስብዕና ልህቀት @Human_intelligence @Human_intelligence
Mostrar todo...
ኮኮብ ቆጣሪዎችንና አፈጮሌ ፖለቲከኞችን አትመኗቸው!!! ፎረር ኢፌክት (Forer Effect) አንባቢዬ ሆይ ሊያስደነግጥህ ይችላል ግን እኔ በግል አውቅሃለሁ። አንተንም እንዲህ እገልፅሃለሁ፡፡ ‹‹ሌሎች እንዲወዱህና እንዲያደንቁህ በጣም ትፈልጋለህ፡፡ ለራስህም ምክንያታዊና አስተዋይ ለመሆን ትፈልጋለህ፡፡ ያልተጠቀምክበትና ሁሌ የሚቆጭህ እምቅ ችሎታ አለህ፡፡ የተወሰኑ ድክመቶች ቢኖሩብህም የምታስተካክላቸው አይነት ናቸው፡፡ ፆታዊ ግንኙነትህ የተወሰኑ ችግሮችን ፈጥሮብሃል፡፡ ከውጭ ለሚያይህ ስነ ስርዓትህን የጠበቅህ እና ራስህን የምትቆጣጠር ብትመስልም ውስጥህ ግን ይጨነቃል፤ ይፈራል፡፡ ‹‹የወሰንከውን ውሳኔዎች ትክክለኛነት ወደኋላ እየተመለስክ የምትጠይቅባቸው ጊዜያት አሉ፡፡ ብዙ አማራጮችንና ለውጦችን ትፈልጋለህ፡፡ ይህንን የሚያደናቅፉብህ ነገሮች ሲበዙም ትበሳጫለህ፡፡ ራስህን እንደገለልተኛና ነጻ አሳቢ ስለምታይ ትኮራለህ፡፡ የማንንም ሀሳብ ሳታረጋግጥ አትቀበልም፡፡ ለሌሎች ራስህን ሙሉ በሙሉ ግልጽ ማድረግ ተገቢ እንዳልሆነ ታውቃለህ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ተግባቢ፣ ትሁት ፣ተጫዋች ትሆናለህ ፤ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ዝምተኛ እና ሰው የማታምን ትሆናለህ፡፡ አንዳንዶቹ ፍላጎቶችህ ፈጽሞ መሆን የማይችሉ ይመስላሉ አንተ ግን እንደምታደርጋቸው ታምናለህ ፡፡›› ራስህ ታውቀዋለህ? ምን ያህል ገልጬሃለሁ? እስኪ ከ 1 (በጣም ደካማ) እስከ 5 (በጣም ጥሩ) ማርክ ስጠኝ፡፡ የስነ ልቦና ባለሞያው በርትራም ፎረር በ1948 አሁን ከላይ ያቀረብኩትን ጽሁፍ ራሱ አዘጋጅቶ ነበር፡፡ ከዚያም ሁሉም ተማሪዎች እንዲያነቡት ሰጣቸው፡፡ እያንዳንዳቸውም በየግል እንደተጠኑና ጽሁፉም የባህሪያቸው ገላጭ የጥናት ውጤት መሆኑም ተነገራቸው። ካነበቡ በኋላም ከ 1-5 ውጤት እንዲሰጡት ጠየቃችው፡፡ ተማሪዎቹም በአማካይ 4.3/5 ሰጡት፡፡ በዚህም 86% ትክክል ነህ አሉት፡፡ ይህ ምርምር በቀጣዮቹ አስርት አመታት ለብዙ ጊዜ በተለያዩ ሰዎች ላይ ተደጋግሞ ተሰርቷል፤ ውጤቱም ተመሳሳይ ነበር። አንተም ቢሆን ከ 4 ነጥብ በታች እንዳልሰጠኸኝ አምናለሁ፡፡ ሰዎች ራሳቸውን ለመለየት የሚሞክሩት እንዲህ ባሉ አለም አቀፋዊ መገለጫዎች ነው፡፡ ሳይንስ ይህንን አሳሳች ዝንባሌ ፎረር አፌክት ወይም (Barnum effect) ይለዋል፡፡ ይህ ዘርፍ እነዚህ የተሳሳቱ ሳይንሶች ለምን በትክክል እንደሚሰሩ ያወራል። አስትሮሎጂ(ኮኮብ ቆጣሪዎች) የእጅ ጽሁፍ ምርምር፣ መዳፍ ማንበብና የሙት ማናገር ጥበብ ወዘተን አስታውስ፡፡ ከፎረር ኢፎክት ጀርባ ያለው ምንድን ነው? #በመጀመሪያ ደረጃ በፎረር ጽሁፍ ውስጥ ዓረፍተ ነገሮቹ በጣም ጠቅላላና ለሁሉም ሰው የሚሆኑ ናቸው፡፡ #ሁለተኛ አንዳንድ እኛን የማይገልጹንን ነገር ግን ደስ የሚሉንን ዓረፍተ ነገሮች የመቀበል አባዜ አለብን፡፡ ለምሳሌ «በራስህ የምታስብ በመሆንህ ትኮራለህ» የሚለውን ሀሳብ ተመልከት፡፡ ምንም ጭንቅላት የሌለው፣ ማንንም እየተከተለ የሚኖር መሆን ማን ይፈልጋል? እውነታው ግን ያ ላይሆን ይችላል። #ሶስተኛ ‹‹የአሉታ ተጽዕኖ›› የሚባለው ነገር ሚናውን ይጫወታል። የተዘረዘሩት ዓረፍተ ነገሮች በሙሉ አዎንታዊ ሃሳቦች ብቻ የያዙ ናቸው፡፡ #አራተኛ የስህተቶች ሁሉ አባት የሆነ ነው የማረጋገጥ መድሎዕ (confirmation bias) አለ፡፡ ሳናስበው የሚስማማንና የሚመስለንን ነገር ሁሉ እየተቀበልን ሌላውን እንተዋለን ወይም ደግሞ እውነትም ውሸትም ለማለት የሚከብዱ ሀሳቦችን በመጠቀም ሰዎች እውነት የሚመስለውን እንዲመርጡ የማድረግ ጥበብ ነው። የጠ/ሚኒስትራችንን ንግግሮችና ፁሁፎች ልብ ካላችሁት በእንደዚህ አይነት ጥበብ (Forer Effect) የተካኑ ናቸው።በህዝብ ዘንድ ተወዳጅነት ካገኙትበት ምክንያትም አንዱ በforer effect የበለፀጉ ንግግሮቻቸው ነው። ንግግሮቹ ከላይ የተጠቀሱት አራቱም ባህሪዎች ይንፀባረቁበታል። ለዚህም ነው ንግግሮቹ ሁሉን የሚያስደስቱና ሁሉንም ህዝብ የሚገልፁ የሆኑት ነገር ግን የጠ/ሚኒስትሩንም ሆነ የፓሪቲያቸውን ግልፅ አቋም አያሳዩም።አጨቃጫቂ እውነታዎችን አድበስብሰው ያልፋሉ፤ እናም ሁልጊዜም ሁሉንም የሚያስደስት ቀጭን መንገድ ይፈልጋሉ።ለጊዜው ሁሉንም ሳይስከፉ ቢያልፋም አቋማቸው በተግባር ሲገለፅ ግን ብዙ ተቃውሞ ይገጥማቸዋል። ምክንያቱም ሁሉንም ማስደሰት የማይቻል ነገር ነውና ሁሉንም ለማስደሰት የሚያደርጉት ጥረትም አቋም የለሽ እንዲሆኑ አርጓቸዋል። አንዳንድ ጊዜ ንግግሮቻቸውና ተግባራቸው ፍፁም የማይገናኙ ይሆናሉ።ይህም ንግግሮቻቸው እውነተኛውን አቋማቸውን ስለማይገልፁ ነው። ታዲያ እንደዚህ አይነት መሪዎችን ከንግግሮቻቸው ይልቅ ተግባራቸውን በማየት ብቻ ነው አቋማቸውን ማወቅ የሚቻለው። መነሻ ሀሳብ (The Art of clearly thinking) ሮልፍ ዶብሊ #አቤል የስብዕና ልህቀት @Human_intelligence @Human_intelligence
Mostrar todo...
ሕይወት የምትጀምረው መቼ ነው? ሁለት ሰዎች በአንድ ጉዳይ ላይ ይከራከሩ ነበር፡፡ አንዱ፣ “ሕይወት የምትጀምረው ልክ አንድ ጽንስ በተጸነሰበት ቅጽፈት ነው” በማለት ያንን እምነቱን በግለት ያስተጋባል፡፡ ሌላኛው ደግሞ፣ “አይደለም! ሕይወት የምትጀምረው የተጸነሰው ልጅ የመጀመሪያውን ትንፋሽ ወደመተንፈስ ደረጃ ሲደርስ ነው” በማለት የተጋጋለ ምላሹን ይናገራል፡፡ ይህንን ሃሳብ ሳይለቁ ለሰዓታት ሲከራከሩ የተመለከተ አንድ ሰው እያዋዛ አንድን ትምህርት ትቶላቸው አለፈ፣ “ሁለታችሁም ተሳስታችኋል፤ ሕይወት የምትጀምረው ሰው የተፈጠረለትን ዓላማውን ሲያውቅና ያንን መከተል ሲጀምር ነው”!!! ዓላማችንን እንወቅ! በግለት እንከታተለው! እንኑረው! የስብዕና ልህቀት @Human_intelligence @Human_intelligence
Mostrar todo...
የዝቅተኝነት ስሜት ድብቅ ምልክቶች ብዙ ሰው ከሚታገላቸው ስሜቶች አንዱ የዝቅተኝነት ስሜት (Inferiority complex) ነው፡፡ የዝቅተኝነት ስሜት ማለት እኛ ከሌላው ሰው እንዳነስን ወይም በሌላው ሰው እንደተበለጥን ሲሰማን ማለት ነው፡፡ ይህ ስሜት በትክክለኛው መንገድ ካልተያዘ እያንዳንዱ ንግግራችን እና ተግባራችን ውስጥ ጣልቃ የመግባት አቅም አለው፡፡ ይህ ጣልቃ ገብነቱ ደግሞ ከዓላማችን እንድንወጣና እንዲሁም ከባድ የሆነ ማሕበራዊ ቀውስ ውስጥ እንድንገባ ያደርገናል፡፡ የዝቅተኝነት ስሜት እንዳለብን ለማወቅ ከፈለግን የሚከተሉትን መመዘኛዎች እንመልከታቸው፡- 1. ስለሰዎች ጤና-ቢስ ወሬን ማራባት፡፡ ይህ የዝቅተኛነት ስሜት መገለጫ መነሻው እኛ የምንነሳው ሌላውን ስንጥልና የእኛ ሁኔታ የሚደምቀው የሌላውን ሰው ስም ስናጠፋ ሲሆን ብቻ ሲመስለን ነው፡፡ ይህ ስህተት የሚመጣው ደግሞ በራሳችን መቆምና ማደግ እንደማንችልና የተበለጥን እንደሆንን ስናስብ ነው፡፡ ስሆነም ወደፊት ከመራመድ ይልቅ ሌላውን ማደናቀፍ፣ ለማደግ ከመስራት ይልቅ ሌላውን ማድቀቅ . . . ይቀናል፡፡ በራሱ የሚተማመን ሰው የሰውን ነገር በማውራትና ሰውን በማሳነስ እሱ የሚተልቅ ስለማይመስለው የራሱ ስራ ላይ የሚያተኩር ሰው ነው፡፡ 2. ስለገቢ መጠንና ስለ ቁሳቁስ ጉራ መንዛት፡፡ ይህ የዝቅተኛነት ስሜት መገለጫ መነሻው ያለንን ነገር አጉልቶ በማሳየት ከሰዎች በላይ እንደሆንን የማሳየት ጡዘት ነው፡ ስለደሞዛችን፣ ስላለን ቤት፣ ሰለምናሽከረክረው መኪናም ሆነ ስለሌሎች ንብረቶቻችን ለሰው የማውራትና ሰዎች እንዲያውቁሉን የመጦዝ ዝንባሌ መነሻው ከፍተኛ የዝቅተኛነት ስሜት ነው፡፡ በራሱ የሚተማመን ሰው ባለው ቁሳቁስ የመደሰት፣ ቤተሰብን የመገንባት፣ ችግረኞችን የመርዳትና ለወደፊቱ የበለጠ የመሻሻሻል ስራ ስለሚበዛበት ለእዩልኝና ለእወቁልኝ ጊዜም የለው፡፡ 3. ተግባርንና ግብን አጋንኖ ማውራት፡፡ ይህ የዝቅተኛነት ስሜት መገለጫ መነሻው ከሌሎች ጋር ተፎካክረን እንዳሸነፍንና ስኬታማ ሰዎች እንደሆንን በማሳየት ያለንን የዝቅተኝነት ስሜት የመሸፈን ጥማት ነው፡፡ የዚህ ቀውስ ትልቁ ክስረት ያለው እንዳደረግንና እንደምናደርግ የምናንጸባርቃቸውን ነገሮች አእምሯችን በርግጥም እንዳከናወንናቸው ስለሚተረጉማቸው ምንም ሳንሰራና የትም ሳንደርስ በወሬ ብቻ እንደደረስን አምነን በመቀበል ኋላ መቅረት ነው፡፡ እኛ ስለሆነውም ስላልሆነውም የተጋነነ ጀብዳችን ስናወራ አለም አምልጦን ይሄዳል፡፡ ያለብን የዝቅተኝነት ስሜት መገለጫው እነዚህም ሆኑ ለሎች ዋናው ቁም ነገር የዚህ የስሜት ቀውስ ምንጩን በመለየት የነጻነት መንገድ መጀመሩ ላይ ነው።
Mostrar todo...
✍«ዝምታ ወርቅ አይደለም» «ልብ ብለው ያንብቡት»(በዳንኤል ክብረት) ✍ሰውዬው ከሚስቱ ሌላ አንዲት ሴት ወደደና እፍ ክንፍ አለ፡፡ ልጁን እና ሚስቱን እየተወ ከዚህችኛይቱ ጋር ማምሸት፣ ብሎም ማደር ጀመረ፡፡ በመጨረሻም አንድ ቀን ወደ ሚስቱ መጣና ድንገተኛ የሆነ ጥያቄ አቀረበ፡፡ «እኔ እና አንቺ እንድንፋታ እፈልጋለሁ፤ ለምን ብለሽ ምክንያቱን አትጠይቂኝ፡፡ መፋታት ብቻ እፈልጋለሁ፡፡ ደግሞም ሌላ ቀን አይደለም ፣ ነገ እንዲሆን እፈልጋለሁ» አላት፡፡ ሚስቱ በሁለት ነገሮች ተጨነቀች፡፡ በአንድ በኩል ምንም ነገር አትጠይቂኝ ብሏታል፡፡ በሁለተኛ ነገር ልጇ ወደ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ፈተና ልትቀመጥ ጥቂት ቀናት ቀርቷታል፡፡ «ባልፈልገውም፣ ባልስማማበትም፤ ካልክ የግድ እቀበለዋለሁ፡፡ ነገር ግን በኛ ምክንያት ልጃችን መጎዳት የለባትምና የአንድ ወር ጊዜ ያህል እንታገሥ፡፡» አለችው፡፡ እርሱም አሰበና «ጥሩ አንድ ወር መታገሥ አያቅተኝም፤ ነገር ግን በዚህ አንድ ወር ውስጥ ሽማግሌ መላክ፣ ምክንያቱን መጠየቅ የለም፤ ስለ ፍቺው ማናችንም ምንም ነገር ማንሣት የለብንም፤ በዚህ ቃል ግቢ» አላት፡፡ እርሷም «እስማማለሁ፤ ግን አንተም የምነግርህን ለመፈጸም ከተስማማህ ነው፤ ታድያ በዚህ አንድ ወር ጠዋት ጠዋት ከዕንቅልፌ ስነሣ፣ ማታ ማታም ወደ አልጋዬ ስሄድ ያኔ የሠርጋችን ዕለት አቅፈህ እንደ ወሰድከኝ አድርገህ አቅፈህ ትወስደኛለህ» ስትል ጠየቀችው፡፡ ነገሩ ያልጠበቀው እና ያልተለመደ ዓይነት ቢሆንበትም፣ ቀላል እና ሊያደርገው የሚችል ስለሆነ እሽ ብሎ ቃል ገባላት፡፡ አንዱ ወር ተጀመረ፡፡ ጠዋት ጠዋት ከዕንቅልፏ ስትነሣ አቅፎ፣ ከፍ አድርጎ፣ ወደ በረንዳ ካደረሳት በኋላ ወደ ሥራው ይሄዳል፡፡ ማታ ማታም እንዲሁ አቅፎ ወደ አልጋዋ ይወስዳታል፡፡ ስለ ፍችው አይነጋገሩም፡፡ እየዋለ እያደረ ሲሄድ የሰውነቷ ጠረን፣ የምትለብሳቸው ልብሶቿ፣ የዓይኖቿ እና የፀጉሯ ሁኔታ፣ የገላዋ ልስላሴ እና የአካሏ ቅርጽ እየሳቡት መጡ፡፡ በየቀኑ እያቀፈ ሲያወጣት እና ሲያስገባት ሰውነቷ እየቀለለው፤ ለርሱም እርሷን አቅፎ መሸከሙ አንዳች እንግዳ የሆነ የደስታ ስሜት እየፈጠረለት መጣ፡፡ ከራሱም ጋር ሙግት ጀመረ፡፡ «ለምንድን ነው እንፋታ ያልኳት፤ አሁን የሚሰማኝን ስሜት ያህል ስሜት ከአዲሷ ወዳጄ ጋር ለምን አይሰማኝም? ለምንስ ነበር ይህንን ነገር እንዳደርገው ቃል ያስገባችኝ ? ይህን የመሰለውን ገላዋን፣ እንዲህ የሚማርከውን ጠረንዋን፣ እንዲህ የሚያስደስተውን ፈገግታዋን፣ እንዲህ የተዘናፈለውን ፀጉሯን፣ እንዲህ ልዩ የሆነውን አካሏን እንዴት እስከ ዛሬ አላስተዋልኩትም ?እርሷ ናት ከኔ ጋር የነበረችው ወይስ እኔም ከርሷ ጋር ነበርኩ?» የወሩ መጨረሻ እየደረሰ መሆኑን ሲያውቅ ከእርሷ መለየቱ ጨነቀው፡፡ እንዲያውም ይህ ሁኔታ የፈጠረበትን እንግዳ ስሜት እየወደደው መጣ፡፡ ነግቶ እና መሽቶ እርሷን አቅፏት እስከሚወስዳት በጉጉት መጠበቅ ጀመረ፡፡ በሌላም በኩል ደግሞ በዚህ ድርጊቷ በውስጡ ያሳደረችበትን ስሜት እያሰበ ያደንቃትም ጀመር፡፡ ብልህነቷን፣ አስተዋይነቷን እና በቀላል ድርጊት ቀልቡን ልትገዛው መቻሏን ሲያስበው «ምን ዓይነት አስገራሚ ሴት ናት?» ይላል፡፡ ወሩ ሊያልቅ ሁለት ቀን ሲቀረው የመፋታቱን ሃሳብ በውስጡ መረመረው፡፡ ነገር ግን አላገኘውም፡፡ በዚህ ሁኔታ መፋታቱ ደግሞ ለሕይወቱ የማይፈታ ዕንቆቅልሽ እንደሚሆንበት እያሰበ ተጨነቀ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በዚህ አንድ ወር ውስጥ ፍችን በተመለከተ ላለመነጋገር ቃል ተግባብተዋልና እንዴት አድርጎ ይናገር፡፡ ዛሬም በደስታ ስሜት አቅፎ ከአልጋዋ እንደወሰዳት ሁሉ ማታ ወደ አልጋዋ መለሳት፤ ከበፊቱ እጅግ በጣም ቀለለችው፤ አሳዘነችውም፡፡ በወሩ መጨረሻ ወደ አዲሲቱ ወዳጁ ዘንድ ሄደና «የፍችውን ሃሳብ ሠርዤዋለሁ ፡፡ እኔና ባለቤቴ ፍቅር የሌለን መስሎኝ ነበር፡፡ እኛ ግን ለካስ ፍቅር አላጣንም፡፡ ያጣነው ሁለት ነገሮች ብቻ ነው፡፡ #መነጋገር እና #መቀራረብ፡፡ ለዚህ ያደረሰንም አለ መቀራረባችን እና አለመነጋገራችን ብቻ ነው፡፡ አሁን ግን መነጋገር ባንችል እንኳን መቀራረብ ግን ችለናል፡፡ ዛሬ ደግሞ መነጋገር እንችላለን፡፡ ስለዚህ ሌላ የሚሆንሽን ፈልጊ» አላት፡፡ ሴትዮዋ ተናደደችና በጥፊ መታችው፤ ከአጠገቧ የነበረውንም ውኃ ቸለሰችበት፤ «ይሄ ለብዙው ኃጢአቴ የተከፈለ ቅጣት ነው» እያለ ወጥቶ ሄደ፡፡ ከዚያም ወደ አበባ መሸጫ ሱቅ ውስጥ ገባ፡፡ ያኔ ሲጋቡ የገዛላትን ዓይነት አበባ ገዝቶ ወደ ቤቱ ከነፈ፡፡ ጓደኛዬ "ትዳር ማለት አግብተው የሚኖሩት ሳይሆን በየጊዜው የሚጋቡት ነው" ያለው እውነቱን ነው፡፡ "ትዳር እንደ አሥራ ሁለተኛ ክፍል ፈተና አንድ ጊዜ አልፈውት ሰርተፊኬቱን የሚሰቅሉት አይደለም" ያለው እውነቱን ነው፡፡ ትዳር እና ተክል እንክብካቤ ይፈልጋሉ፡፡ እንዲሁ ቢያድጉ ይደጉ ተብለው የሚተው ነገሮች አይደሉም፡፡ «ልክ እዚህ ሀገር ችግኝ የመኮትኮት፣ የማጠጣት፣ የመከባከብ እና የማሳደግ እንጂ የመትከል ችግር እንደሌለብን ሁሉ፤ እኛም ጋር የመጋባት ችግር የለም፡፡ ፍቅር ግን ማግባትን ብቻ ሳይሆን ማጠጣትን፣ መኮትኮትን፣ ማረምን፣ ከብት እንዳያበላሸው አጥር ማጠርን፣ በየጊዜው ማዳበርያ መጨመርን ጭምር ይፈልጋል፡፡ በርግጥ በዕድሉ የሚበቅል ዛፍ እንዳለው ሁሉ በእድሉ የሚኖር ትዳርም ይኖር ይሆናል፡፡ ይህ ግን ሕይወትን ለራስ ጥረት ሳይሆን ለአጋጣሚዎች ብቻ አሳልፎ መስጠት ነው» ያለው እውነቱን ነው፡፡ እኔ አልሰማሁትም እንጂ እርሱስ ተናግሮ ነበር፡፡» መኪናውን አቆመና ወደ ግቢው ውስጥ ገባ፡፡ በረንዳ ላይ ትጠብቀው የነበረችው ባለቤቱ የለችም፡፡ በሩንም አንኳኳ፡፡ የሚከፍት ግን አልነበረም፡፡ ደግሞ ሲያንኳኳ ገርበብ ብሎ የተዘጋው በር በራሱ ጊዜ ተከፈተ፡፡ ባለቤቱ ግን በዚህች በወሩ ሠላሳኛ ቀን ሳሎንም የለችም፡፡ እየተገረመም፣ ግራ እየተጋባም ወደ መኝታ ቤቱ ዘለቀ፡፡ አልጋው ላይ ፈገግ እንዳለች ጋደም ብላለች፡፡ አበባውን እንደያዘ ጠጋ አለና በእጁ ጉንጯን ነካው፡፡ ቀዝቅዟል፡፡ በቁልምጫ ጠራት፡፡ መልስ ግን አልነበረም፡፡ ግራ ተጋብቶ ዓይንዋን ገለጥ አደረገው፡፡ ሊገለጥለት ግን አልቻለም፤ በርከክ አለና ሰውነቷን ደባበሰው፤ ቀዝቅዟል፡፡ «የመጨረሻው ቀን ነው፤ ይህችን ቀን ማየት አልፈልግም፤ ለልጄ ስል እስከዛሬ ታግሻለሁ፤ በቃኝ» የሚል ጽሑፍ ራስጌዋ ላይ አገኘ፡፡ እርሷ ፍችውን አትፈልገውም፤ ስለዚህም ሳትፋታ ሞተች፡፡ በርሱ ውስጥ የነበረውን የሃሳብ ለውጥ አላወቀችም፤ ምክንያቱም ላይነጋገሩ ቃል ተግባብተው ነበርና፡፡ እርሷ የዛሬዋን ቀን በስጋት እና በጭንቀት ነበር የጠበቀቻት፡፡የመለያያቸው ቀን፤ የሕይወቷን ግማሽ የምታጣበት ቀን፡፡ የማትፈልገውን ነገር የምታደርግበት ቀን ናትና፡፡ እርሱ ግን የዛሬዋን ቀን በጉጉት ነበር የጠበቃት፡፡ የሚነጋገሩባት ቀን፤ ፍችውን እንደተወው የሚነግርባት ቀን፤ ፍቅሩን የሚነግርባት ቀን፤ ይቅርታ የሚጠይቅባት ቀን፤ ለፍቅሩ ሲል ትንሽም ብትሆን ቅጣት ከፍሎ የመጣባት ቀን፤ በእርሱ እና በባለቤቱ መካከል የመነጋገር እና የመቀራረብ እንጂ፣ የመዋደድ እና ስሜት ለስሜት የመስማማት ችግር እንደሌለ መረዳቱን የሚገልጥባት ቀን ናትና፡፡ ይቀጥላል..
Mostrar todo...
«ዝምታ ወርቅ አይደለም» የቀጠለ ግን ምን ያደርጋል፤ ሁለቱም ይህንን በየልባቸው ያውቁታል እንጂ አልተነጋገሩም፤ ሃሳባቸውንም በሌላ መንገድ አልተለዋወጡም፡፡ በዚህ የተነሣም በችግሩ መፍቻ ቀን ዋናው ቸግር ተፈጠረ፡፡ ሁለት የትዳር ነቀርሳዎች፡- አለመቀራረብ እና አለመነጋገር፡፡ አብረው አንድ አልጋ ላይ እያደሩ፤ አብረው እየበሉ፤ አብረው እየኖሩ የማይቀራረቡ ባል እና ሚስት አሉ፡፡ አንድ አልጋ ላይ የሚተኙት አንድ አልጋ ላይ መተኛት ስላለባቸው ብቻ ነው፡ ከመጋባታቸው በፊት የነበራቸው ጉጉት እና ናፍቆት አሁን የለም፡፡ ሳይተኙ እንቅልፍ ይወስዳቸዋል፡፡ አብረው ይበላሉ፤ በአንድ ማዕድ መሆኑ፣ አንድ ጠረጲዛ ላይ መሆኑ እንጂ ያኔ በፊት ለምሳ ሲገባበዙ የነበረው ናፍቆት እና ጉጉት የላቸውም፡፡ ዝም ብሎ መብላት ብቻ፡፡ እያንዳንዷን ቀን ልዩ፣ ደስታ የሚፈጠርባት እና ከትናንት የተለየች ለማድረግ አይጥሩም፡፡ ዛሬም እንደ ትናንቱ፣ ነገም እንደ ዛሬ ነው፡፡ በስንት ልመና በስንት ጥየቃ፣ በስንት ደጅ ጥናት በስንት ጥበቃ፣ እንግዲህ ምን ቀረሽ አገባሁሽ በቃ፣ እንደተባለው ይሆንባቸዋል፡፡ አገባኋት በቃ፤ አገባሁት በቃ፤ ከንግዲህ ምን ቀረ? ብለው ያስባሉ፡፡ ሰው ተፈጥሮ አላለቀም፡፡ በየጊዜው ነው የሚፈጠረው፡፡ ፈጣሪም ሰውን እንደ ተወለደ እንዲያልቅ አላደረገውም፡፡ በየቀኑ፣ በየሰዓቱ፣ በየደቂቃው ላስተዋለው ሰው እንግዳ ፍጥረት ነው፤ አዳዲስ ነገር ይታይበታል፡፡ ይህ ግን መቀራረብን ይጠይቃል፡፡ ባል እና ሚስት ከተቀራረቡ ሳይፋቱ በየቀኑ ይጋባሉ፤ ጋብቻቸው እየታደሰ ይሄዳል፡፡ የትናንቷ ሚስት ከዛሬዋ ትለያለች፤ የዛሬው ባልም ከትናንቱ የተለየ ነው፡፡ ለውጥ፣ ዕድገት፣ ብስለት፣ አለ፡፡ መልክም ተለውጧል፡፡ ግን ቀርቦ የሚያየው ያስፈልገዋል፡፡ የዚያ ባል ችግሩ ሚስቱን አግብቷት እንጂ ቀርቧት አያውቅም ነበር፡፡ አብሯት ይኖራል እንጂ ከርሷ ጋር አይኖርም ነበር፤ ምድር በፀሐይ ዙርያ ስለምትዞር ይመሻል ይነጋል እንጂ በእነርሱ የተለየ የሕይወት ጉዞ ምክንያት አይመሽም አይነጋም፡፡ በማክሰኞ እና በረቡዕ መካከል ከስሙ በቀር በሕይወታቸው ውስጥ ልዩነት የለውም፡፡ ሌላው ችግር ደግሞ ያለ መነጋገር ነው፡፡ መነጋገር ማለት በሚያውቁት ቋንቋ ማውራት ማለት አይደለም፡፡ እርሱንማ ከብትም ሲገናኝ እምቧ እምቧ ይባባላል፡፡ ይህ ግን መነጋገር አይደለም፡፡ በየጊዜው፣ በየሰዓቱ፣ ሁለመናን መለዋወጥ ማለት ነው፡፡ ካልተነጋገሩበት የምሥራች፣ የተነጋገሩበት መርዶ ይሻላል፡፡ ካልተነጋ ገሩበት ፍቅር የተነጋገሩበት ጠብ ይበልጣል፡፡ ካልተነጋገሩበት ስጦታ የተነጋገሩበት ንጥቂያ ይሻላል፡፡ ባል እና ሚስቱ ባለመነጋገራቸው ችግሩን በሁለት አቅጣጫ ፈቱት፡፡ የሁለቱም ፍላጎት ችግሩን ላንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ መፍታት ነበር፡፡ የሁለቱም ፍላጎት ፍቺ የሚባለውን ነገር ላለማየት ነበር፡፡ የሁለቱም ፍላጎት ሠላሳኛዋን ቀን መገላገል ነበር፡፡ ነገር ግን ባለ መነጋገር ምክንያት በሁለት አቅጣጫ ሆነ፡፡ እርሷ ሞትን መረጠች፤ እርሱ ደግሞ ይቅርታን መረጠ፡፡ ችግሩ የመጣው በዚህ ጉዳይ ላለመነጋገር ሲወስኑ ነው፡፡ እርሷ በጉዳዩ ትጨነቃለች፤ ለምን ይሆን ከኔ መለየት የፈለገው? የሚለው ጥያቄ ያሳስባት ነበር፡፡ በሃሳብ ብዛትም እየከሳች ሄዳ ነበር፡፡ ለዚህም ነበር በየቀኑ ሲያቅፋት ትቀልለው የነበረው፡፡ እርሱ ግን መቅለሏን እንኳን ለመጠየቅ ፈራ፡፡ እርሱ ከራሱ ጋር እንጂ ከእርሷ ጋር አይነጋገርም ነበር፡፡ እናም አንዳንድ ጊዜ አስፈላጊ ቢሆንም እንኳ፤ በትዳር ውስጥ ግን ዝምታ ወርቅ አይደለም፡፡ ዳንኤል_ክብረት @Human_intelligence @Human_intelligence
Mostrar todo...
ግሩም አባባሎች "ያለምክንያት የሚወድህን አምላክ እያሰብክ ያለምክንያት የሚጠሉህን ሰዎች እርሳቸው።" "እያንዳንዱ ቀን ትንሽ ህይወት ነው ከእያንዳንዱ ህይወት ቀን ጀርባ አዲስ ህይወት አለ፣እያንዳንዱ ጠዋት ትንሽ ወጣት እያንዳንዱ የሌለት እንቅልፍ ትንሽ መሞት ነው።" አርተር ሾፐን ሀወር "ፍቅርን ማያዉቁ ሰዎች ፍቅር እዉር ነዉ ይላሉ፤ እኔ እላለሁ አይን ያለዉ ብቸኛ ነገር ፍቅር ብቻ ነዉ፤ ከፍቅር ዉጭ ሁሉንም ነገር እዉር ነዉ።" ኦሾ "የተሳሳቱ ሰዎች ሃይማኖትን በተሳሳተ መንገድ ይጠቀማሉ ፡፡ በዚህ ምክንያት ሃይማኖት ለላቀ ተጋድሎ እና ለከፋ መከፋፈል አስተዋጽኦ ያደርጋል ፡፡" ዳላይ ላማ "ዛሬን ለሰይጣን ነገን ደግሞ ለእግዚአብሔር አትስጡ።" ቅዱስ ጎሮጎርዮስ "ጥሩ ምላስ ስውር ማህተብ ያላት የዘመኑ ሰርተፊኬት ናት" "መስታወቱን መስበር ከፊቱ የቆመውን እውነት አይቀይረውም" " ጨዋ ሰው በሌሎች ሰዎች መጎሳቆል ላይ የራሱን ምቾት አይገነባም እርሱ የሌሎችን ሰዎች ምቾት ለማደላደል የራሱን ምቾት ይረሳልና " አቡነ ሺኖዳ "ህይወትህ ቀላል እንዲሆንልህ አትፀልይ፡፡ ጥንካሬ እንድታገኝ ፀልይ እንጂ፡፡ በአቅም ልትሰራው የምትችለውን ነገር ለማግኘት አትፀልይ፡፡ ልትሰራው ካሰብከው ነገር ጋር የሚመጣጠን ሀይልን እንድታገኝ ፀልይ፡፡ከዚያ አስደናቂው ነገር 'የሰራህው ስራ' ሳይሆን 'አንተ' ትሆናለህ፡፡" ፊሊፕ ብረክስ ."በዓመቱ ውስጥ ምንም ሊከናወን የማይችልበት ቀን ሁለት ቀናት ብቻ ናቸው ፡፡ አንደኛው ትናንት ሌላኛው ደግሞ ነገ ይባላል ፡፡ ዛሬ ለመውደድ ፣ ለማደግ እና ከሁሉም በላይ ለመኖር ትክክለኛው ቀን ዛሬ ነው።" ዳላይ ላማ
Mostrar todo...
ሰላም ቤተሰቦቼ እንዴት ናቹ የናንተው ቃርሚያ በ YouTube በጣም ምርጥ አዝናኝ .አስተማሪ . እና ወቅታዊ መሰናዶዎችን ይዝን መተናል subscriber በማደረግ ቤተሰብ እንድትሆኑ በአክብሮት ጋብዘናል https://youtube.com/channel/UCUsROypgcN9zwJQCtBNlWCg እናመሰግናለን
Mostrar todo...
ስህተትን የምትደጋግም ሰው ነህ? ራስህን መዝነው! (“ራስን ማሸነፍ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ ውስጥ የተወሰደ) ከዚህ በታች የሰፈሩትን አስር የመጠይቅ ነጥቦች ለራሳችሁ ፍጹም እውነተኛ በመሆንና መልስን በመስጠት ምን ያህል አንድን ስህተት የምትደጋግሙ መሆናችሁን ለማየት ሞክሩ፡፡ 1. ባለህበት እንደምትረግጥ ይሰማሃል? 2. አንድ እንቅፋት ሲያጋጥምህ ለመፍትሄ የሚሆኑ አዳዲስ መንገዶችን የመሞከር መነሳሳቱ የለህም? 3. ደጋግመህ እዚያው ችግር ላይ ራስህን ስለምታገኘው፣ አጉል ባህሪዎችንና ልማዶችን ለማቆም ያቅትሃል? 4. ግብህን ለመምታት ለምን እንዳልቻልክ ጊዜ ወስደህ ለማሰብና መፍትሄ ለማግኘት ብቃቱና መነሳሳቱ እንደሌለህ ይሰማሃል? 5. አጉል ልማዶችህን ለመቀየር ባለመቻልህ በራስህ ላይ የማዘንና የመበሳጨት ዝንባሌ አለህ? 6. “ሁለተኛ አልደግመውም” ያልከውን ስህተት ደግመህ ደጋግመህ ስታደርገው ራስህን ታገኘዋለህ? 7. አዳዲስ የመሻሻል መንገዶችን በመሞከር “ከመድከም” ይልቅ ባሉበት መቀጠል ቀላል እንደሆነ ታስባለህ? 8. ባለህ ዲሲፕሊን የማጣት ሁኔታ ምክንያት ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ያጠቃሃል? 9. ነገሮች በጠበካቸው መልኩ ካላገኘሃቸው ጨክኖ ከመቀጠል ይልቅ የጀመርከውን ራስን የመለወጥ ጉዞ ለማቋረጥ እንደምክንያት ትጠቀምበታለህ? 10. ስለምትደጋግማቸው ስህተቶች የቅርብ ወዳጆችህ ሲጠቁሙህ የመከላከልና የመቆጣት ዝንባሌ ይታይብሃል? ከላይ ለተጠየቁት አስር ጥያቄዎች ከግማሽ በላይ ለሆኑት “አዎ” የሚል መልስ ከሰጠህ ስህተትን የመደጋገም ዝንባሌ ሊኖርህ ስለሚችል ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ለውጥን ለማስተናገድ ጥረት አድርግ፡፡ ስህተትን ከመደጋገም ይልቅ ራስን በማሸነፍ ከስህተት የመማር ልምምድ ከሚሰጠን በርካታ ጥቅሞች መካከል ሶስቱን ላጋራችሁ፡፡ 1. የማያቋርጥ መሻሻል ቀና በልና ዙሪያህን ተመልከት፡፡ አሁን አንተ የደረስክበትን ደረጃ አይተህ ሊደረስበት ከሚቻለው ሌላ ደረጃ ጋር ስታነጻጽረው መሻሻልን ላትፈልገው አትችልም፡፡ መሻሻል ደግሞ የሚመጣው ያለፈውን ስህተት ላለመድገም በመወሰንና፣ ይልቁንም ካለፈው ስህተት በመማር ነው፡፡ 2. ጤናማ ድፍረት ጤናማው ድፍረት ያለንበትን ቦታ ስናውቅና አምነን ስንቀበል፣ በመቀጠልም የት መሄድ እንዳለብን ተገንዝበን አስፈላጊውን እርማት ስንወስድ የሚመጣ ነው፡፡ በዚህ መልኩ ካለማቋረጥ ስንሻሻል የምንሸማቀቅበት ነገር ስለማይኖረን ግልጽ ከመሆን የሚመጣ ድፍረት ማዳበት እንጀምራለን፡፡ 3. ለሌሎች አስተማሪ የመሆን እድል አንዳንድ ጊዜ በንባብና በመሳሰሉት ሁኔታዎች ከሰዎች ቅድመ-ልምምድ ያገኘናቸው ትምህርቶች ሙሉ ትርጉም እኛው ራሳችን በዚያ ሁኔታ እስክናልፍ ድረስ አይገባንም፡፡ ይህ ማለት፣ ወድቀን የተነሳንባቸውና ተሳስተን የታረምንባቸው ሁኔታዎች ከራሳችን አልፈን ሌሎችን አስከመምከር የምንደርስበት እውነተኛ አስተማሪያችን ነው፡፡ @Human_intelligence @Human_intelligence
Mostrar todo...
ሰላም ቤተሰቦቼ እንዴት ናቹ የናንተው ቃርሚያ በ YouTube በጣም ምርጥ አዝናኝ .አስተማሪ . እና ወቅታዊ መሰናዶዎችን ይዝን መተናል subscriber በማደረግ ቤተሰብ እንድትሆኑ በአክብሮት ጋብዘናል https://youtube.com/channel/UCUsROypgcN9zwJQCtBNlWCg እናመሰግናለን
Mostrar todo...