cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

መንፈሳዊ ጥያቄዎች - spiritual questions

በዚህ ቻናል መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ ይካሄዳል ሁላችሁ ተሳተፉ ጥያቄ ና አስተያየት ካላችሁ በዚህ ላኩ ና አናግሩን 👇👇👇👇👇 @SendSpiritualquestionBot " ስለዚህ በሰው ፊት #ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው #በአባቴ ፊት #እመሰክርለታለሁ፤"" (የማቴዎስ ወንጌል 10:32) 👇👇 ለሁሉም የኦርቶዶክስ አማኝ ይደርስ ዘንድ በቅንነት share አድርጉ

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
2 124
Suscriptores
Sin datos24 horas
-87 días
-5730 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Photo unavailableShow in Telegram
ሐመረ ኖኅ የዜማ መሳሪያ መሸጫ የሐምሌ ወር ልዩ ቅናሽ አድርገናል ፈጥነው ለሚገዙ አምስት ደንበኞች ስ.ቁ.+251988232340 @habmisget
Mostrar todo...
ማንኛውን ለድርጅትዎ ወይም ለቻናልዎ ሎጎ ማሰራት ከፈለጉ ወይም የዩቲዩብ ተምኔል በጥራት እንሰራለን አናግሩን @habmisget
Mostrar todo...
ዕለተ ሠሉስ ዕለተ ተስዕሎ/የጥያቄ ቀን ይህ ቀን ጌታችን በዕለተ ሰኑይ/ሰኞ/ በተናገረውና ባደረገው ላይ አይሁድ ጥያቄ ያቀረቡበት እርሱም መልስ በመስጠት ያስተማረበት ዕለት ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የጥያቄ ቀን ይባላል። ከዚህ በተጨማሪም በዚህ ዕለት በቤተ መቅደስም ረጅም ትምህርት ስላስተማረ የትምህርት ቀንም ይባላል፡፡ ይኸውም ከሃይማኖት የራቁትን፣ ከፍቅረ እግዚአብሔር የተለዩትን አስተምሮ ማቅረብ፣ መክሮ መመለስ እንደሚገባ ሲያስተምር ነው፡፡ በዚህ ዕለት አይሁድ ጌታን የተንኮል ጥያቄ ጠይቀውታል። ጌታም አይሁድን ጥይቋቸዋል። አይሁድ የጠየቁት ጌታ ባደረገው አንጽሖተ ቤተ መቅደስ ምክንያት ለጸሐፍትና ፈሪሳውያን ይኸውም ትምህርት ማስተማር፣ ተአምራት ማድረግ፣ ገበያ መፍታትን በማን ሥልጣን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ?» የሚል ነበር፡፡ በዕለተ ሠሉስ(ማግሰኞ ዕለት) ፍጥረትን(ዕፅዋትን) በቃሉ የፈጠረውን አምላክ በዕለተ ሠሉስ አይሁድ ጠየቁት። ቀዳሜ ፍጥረት አዳም በዚህች ዕለት የተፈጠረቺውን ዕፀ በለስን በልቶ ከእግዚአብሔር ፊት በተሸሸገ ጊዜ " አይቴ ሀሎከ አዳም?" "አዳም ሆይ ወዴት ነህ" ብሎ አዳምን በገነት የጠየቀውን አምላክ አይሁድ በምድር ጠየቁት። "ዘስልጣኑ ዲበ መትከፍቱ" የተባለውን አምላክ አይሁድ "ይህን በማን ስልጣን ታደርጋለህ?" አሉት። ለሐዋርያት ስልጣነ ክህነትን የሰጠ፤ ነሥታትን የሚሾም፣ የሚሽረውን አምላክ አይሁድ ግን ስለስልጣኑ ጠየቁት። "ነገሥታት በእንቲአከ ይገድፉ ጌራ ወእጠቆሙ ይፈትሁ ሐራ(ነገሥታት ስላንተ ዘውዳቸውን ያወርዳሉ። ሰራዊቶቻቸውም ትጥቃቸውን ይፈታሉ።) የተባለለትን ጌታ አይሁድ ግን ከሮም መንግስት ሊያጋጩት የተንኮል ጥያቄ ጠየቁት። ይህን የታገሰ የጌታችኝ ትሕትና ምን ይደንቅ፣ ምን ይረቅ። አይሁድ ይህን "ይህን በማን ስልጣን ታጀርጋለህ?" ብለው መጠየቃቸው የሚያደርጋቸውን ተግባራት ዅሉ በራሱ ሥልጣን እንዲያደርግ አጥተውት አልነበረም፤ ልቡናቸው በክፋትና በጥርጥር ስለ ተሞላ እንዲሁም ጌታችን ሲያደርጋቸው የነበሩ ተአምራትና ድንቅ ድንቅ ሥራዎች የካህናት አለቆችን ስላስቀኗቸው ጌታችንን ከሮማ መንግሥት ባለ ሥልጣናት ጋር ለማጋጨት የቀየሱት ስልት ነበር። ጌታ ይህንን በራሴ ስልጣን አደርጋለሁ ብሏቸው ቢሆን ገበያ መፍታት፣ ነጋድያንን ማባረር የመንግስት ድርሻ ነው። ይሄስ በሮማ መንግሥት ላይ የተነሳ ነው ብለው ለመክሰስ ነበር አላማቸው። "እግዚአብሔርሰ ልበ ይሬኢ/እግዚአብሔርስ ልብን(የልብን ሐሳብ) ያያል" እንዲል እግዚአብሔር ወልድ የተባለ ማዕምረ ኅቡዓት የሆነ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጸሐፍት፣ ፈሪሳውያንን የልባቸውን ሐሳብ እውቆ እንዲህ ብሏቸዋል። "እኔ ደግሞ አንዲት ነገር እጠይቃችኋለሁ፤ እናንተም ያችን ብትነግሩኝ እኔ ደግሞ እነዚህን በምን ሥልጣን እንዳደርግ እነግራችኋለሁ" ብሎ አንዲት ጥያቄ ጣየቃቸው። "የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረች? ከሰማይን ወይስ ከሰው?" አላቸው። እነርሱም እርስ በርሳቸው ሲነጋገሩ። ከሰማይ ብንል። እንኪያስ ስለ ምን አላመናችሁበትም? ይለናል፤ ከሰው ግን ብንል፥ ዮሐንስን ሁሉም እንደ ነቢይ ያዩታልና ሕዝቡን እንፈራለን አሉ። ለኢየሱስም መልሰው። አናውቅም አሉት። እርሱም ደግሞ። እኔም በምን ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ አልነግራችሁም አላቸው።" ማቴ 21 ÷ 24-27 ጌታም እንዲህ ብሎ ከመለሰላቸው በኋላ አንድ ምሳሌ ነገራቸው ቅዱስ ማቴዎስ እንዲህ ይተርከዋል። ---------- 28፤ ነገር ግን ምን ይመስላችኋል? አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበሩት፤ ወደ አንደኛው ቀርቦ። ልጄ ሆይ፥ ዛሬ ሂድና በወይኔ አትክልት ሥራ አለው። 29፤ እርሱም መልሶ። አልወድም አለ፤ ኋላ ግን ተጸጸተና ሄደ። 30፤ ወደ ሁለተኛውም ቀርቦ እንዲሁ አለው እርሱም መልሶ። እሺ ጌታዬ አለ፤ ነገር ግን አልሄደም። 31፤ ከሁለቱ የአባቱን ፈቃድ ያደረገ ማን ነው? ፊተኛው አሉት። ኢየሱስ እንዲህ አላቸው። እውነት እላችኋለሁ፥ ቀራጮችና ጋለሞቶች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በመግባት ይቀድሙአችኋል። 32፤ ዮሐንስ በጽድቅ መንገድ መጥቶላችሁ ነበርና፥ አላመናችሁበትም፤ ቀራጮችና ጋለሞቶች ግን አመኑበት፤ እናንተም ይህን አይታችሁ ታምኑበት ዘንድ በኋላ ንስሐ አልገባችሁም።" ከላይ ጌታ ለአይሁድ የነገራቸውን ምሳሌ ሊቃወንተ ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ተርጉመውታል። ታላቅ ልጅ የተባሉት ጸሐፍት ፈሪሳውያን ናቸው። ታናሽ ልጅ የተባሉት ደግሞ ኃጥአን መጸብሐን ናቸው። ታላቁ ልጅ እሄዳለሁ ብሎ እንደቀረ ጸሐፍት ፈሪሳውያንም ኦሪትን ተቀብለው በወንጌሉ ሳያምኑ ቀርተዋልና። ታናሹ ልጅ ደግሞ አልሄድም ብሎ እንደሄደ ኃጥአን መጸብሐንም ሕጉን ካፈረሱ በኋላ በወንጌል አምነዋልና። እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻማ ወድካም አመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ እግዚአብሔር ለብርሃነ ትንሣኤሁ በፍስሐ ወበሰላም። ምክረ አበው በቴሌግራም 👇 @mekra_abaw በዩቲዩብ ማግኘት ለምትፈልጉ https://www.youtube.com/channel/UCfWtKqb7qsxjXey4kN_tykg?sub_confirmation=1
Mostrar todo...
✝️ላሐ ማርያም በግዕዝና በአማረኛ ✝️ መጽሐፈ ላሐ ማርያም ስለ ጌታ ሕማማተ መስቀልና እመቤታችን የተወደደ ልጂ ወዳጇን መንገላታት እያየች በኀዘን ስለአፈሰሰችው የአንብዐ ላሕ (የለቅሶን እንባን) መሪር ጽንዐ ኀዘን የሚናገር ቅዱስ አባ ሕርያቆስ የደረሰው ነው :: ሼር ይደረግ በvideo ለማግኘት 👇👇👇 https://www.youtube.com/channel/UCfWtKqb7qsxjXey4kN_tykg?sub_confirmation=1 🔴ዘወትር ምክረ አበውለማግኘት ሰማያዊውን ነክታችሁ ተቀላቀሉ ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ 🤍 @mekra_abaw 💚 🤍 @mekra_abaw 💛 🤍 @mekra_aba
Mostrar todo...
ላሐ ማርያም.pdf43.83 MB
✝️ ድርሳነ ማሕየዊ 👉" መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ ። " /ማቴ ፫:፫ / ሼር ይደረግ በvideo ለማግኘት 👇👇👇 https://www.youtube.com/channel/UCfWtKqb7qsxjXey4kN_tykg?sub_confirmation=1 🔴ዘወትር ምክረ አበውለማግኘት ሰማያዊውን ነክታችሁ ተቀላቀሉ ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ 🤍 @mekra_abaw 💚 🤍 @mekra_abaw 💛 🤍 @mekra_aba
Mostrar todo...
ድርሳነ ማሕየዊ.pdf48.93 MB
መልክአ ማሕየዊ.PDF2.16 MB
የሰሙነ_ሕማማት_ሰኞ መርገመ_በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ አድሮ በማግሥቱም ከቢታኒያ ሲመጡ ተራበ፡፡ (ማር.11፤11-12) ቅጠል ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ወደ በለሲቱ ቀረበ፤ ነገር ግን ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ ከአሁን ጀምሮ ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ ብሎ ረገማት። በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ናት፤ ፍሬ የተባለች ሃይማኖትና ምግባር ናት፤ ከእስራኤል ፍቅርን፤ ሃይማኖትን፤ ምግባርን ፈለገ አላገኘም፤ እስራኤል (ሕዝበ እግዚአብሔር) መባልን እንጂ፤ ደግ ሰው አይገኝብሽ ብሎ ረገማት፤ በመርገሙ ምክንያት እርሱ ከለያቸው በስተቀር ደግ ሰው ጠፋባት፡፡ በለስ ኦሪት ናት፤ ኦሪትን በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛት ኦሪትና ነቢያትን ልሽር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ በማለት ፈጸማት፤ ሕገ ኦሪትን ከመፈጸም በቀር በእርሷ ድኅነት አላደረገባትምና፤ ፍሬ በአንቺ አይሁን አላት፤ ደኅነት በአንቺ አይደረግብሽ ብሏታልና እንደመድረቅ ፈጥና አለፈች፡፡ በለስ ኃጢአት ናት፤ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነች ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አገኛት፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል፤ ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሰሩት ደስ ደስ ያሰኛል፤ ኋላ ግን ያሳዝናል፤ ወደ እርሷም ሄዶ ማለትም ከኃጥአን ጋር ዋለ፤ ኃጥእ ከመባል በቀር በአንደበቱ ሐሰት፤ በሰውነቱ ክፋት እንዳልተገኘበት ለማመልከት ፍሬ አላገኘባትም አለ፤ በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውም፤ በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር ለማለት ነው፤ ስትረገም ፈጥና መድረቋም፣ በአዳም ምክንያት ያገኘችን ዕዳ በደል በእርሱ ካሣነት እንደጠፋችልን ለመግለጽ ነው፡፡ አንጽሆተ_ቤተ_መቅደስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፦ ጌታችን በለስን ከረገማት በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ሄደ፤ ቤተ መቅደስ፣ ቤተ ጸሎት፣ ቤተ መሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምስያጥ (የንግድ ቤት) ሆኖ ቢያገኘው ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች፤ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸው፤ ገርፎም አስወጣቸው፤ ይህም የሚያሳየው ማደሪያው ቤቱ የነበርን የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢአታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡ በዚህ በሰሙነ ሕማማት ካህናትና ምእመናን በቤተክርስቲያን ተገኝተው ወዛቸው ጠብ እስኪል ድረስ በነግህ፤ በሠለስተ፣ በስድስቱ ሰዓት፤ በተሰዓቱ ሰዓትና በሠርክ መላልሰው ሲሰግዱና ሲጸልዩ ይሰነብታሉ፤ በተለይም ካህናት በማንኛውም አገልግሎት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፤ ምክንያቱም የደረሰብን መከራ ኀዘኑን እና 5ሺ ከ5መቶ ዘመን የሰው ልጅ በጨለማ ይኖር እንደነበረ ለማዘከር ነው፡፡
Mostrar todo...
ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ በሰሙነ ሕማማት ሰኞ የተሰጠ ትምህርት ርግመተ በለስ
Mostrar todo...
Semayat_ዲ_ን_ሄኖክ_ኃይሌ_በሰሙነ_ሕማማት_ሰኞ_የተሰጠ_ትምህርት_GG_WjA7HrDs_140.mp310.10 MB
ቋንቋ የነሽ ድንግል.m4a1.81 MB
ደባርቅ በዛሬው ዕለት ሀዘኗን በምህላና በጸሎት እንዲሁም ጥቁር በመልበስ አሰምታለች ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት @mekra_abaw
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.