cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ዜና ቤተክርስቲያን

የተለያዩ በቅድስት በቤተክርስቲያን ዙሪያ መነሻ ያደረጉ ዜናዎችን ከቤተክርስቲያን ልሳናት ከሆኑ ምንጮች በማቅርብ መረጃ መለዋወጥ።

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
1 591
Suscriptores
Sin datos24 horas
-27 días
-1130 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Photo unavailableShow in Telegram
👉ዛሬ ሐምሌ 7 ቅድስት ሥላሴ ለአብርሃም የተገለጡበት የይስሐቅንም መወለድ የአበሠሩበት፡ በቤቱም የተስተናገዱበት ዕለት ነው፡፡ እንኳን አደረሳችሁ "ሀገራችንን ከጥፋት፡ህዝባችንን ከስደት ከሞት ይታደጉልን።🙏❤🥰 ቅድስት ሥላሴ በዕለተ ቀናቸው ያላሰብነውን ደስታ ይስጡን፡ መልካም እለተ ሰንበት ይሁንልን።🙏❤
Mostrar todo...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
በዓለ ጰራቅሊጦስ፤ ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ይህቺን ቅድስት ዕለት የቤተ ክርስቲያን የልደት ቀን ናት ብሏታል። እውነት ነው፥ቤተ ክርስቲያን በቀራንዮ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ላይ ስትመሠረት ተፀነሰች፥ የጰራቅሊጦስ ዕለት ተወለደች፥ምክንያቱም በዚያች ዕለት ሁሉም የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ተሰጥቶአት ምሉዐ ጸጋ ሆናለችና ነው።ይህንንም በጥምቀት ለተወለዱ፥በሜሮን ለከበሩ፥በሥጋ ወደሙ ለታተሙ ልጆቿ ስታድል ትኖራለች። የተሰጠንን ጸጋ ያጽናልን፥በጸጋ ላይ ጸጋ ይጨምርልን።
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
#ከድርሳነ #ሚካኤል #ዘሰኔ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አምነን በባሕርይ በህልውና አንድ አምላክ ብለን ክብር ምስጋና ይግባውና በዛሬው ዕለት እግዚአብሔር ቅዱስ ሚካኤልን በወገኖቹ በመላእክት ሁሉ ላይ ከክብሩና ከገናንነቱ ጋራ እንደሾመው እንናገራለን። ንዑድ ክቡር የሚሆን የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል ተአምራቱ ብዙ የብዙ ብዙ ነውና ስለዚህ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት የቅዱስ ሚካኤልን በዓል በየወሩ በአሥራ ሁለት ቀን እናከብር ዘንድ አዘውናል ጸሎቱና በረከቱ ከኛ ጋር ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን። ምንጭ፦ ድርሳነ ሚካኤል ዘሰኔ ቁጥር 133-134 "ይህም የከበረ መልአክ ክብር ይግባውና በጌታችን ፊት ስለ ሰው ልጆችና ስለ ፍጥረትም ሁሉ ይለምናል ይማልዳልም" - ስንክሳር ዘወርኀ ሰኔ ቁጥር ፲ 👉"ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል" ዳን. 12፥1 👉"ማኑሄም የእግዚአብሔርን መልአክ፦ ነገርህ በደረሰ ጊዜ እንድናከብርህ ስምህ ማን ነው? አለው። የእግዚአብሔርም መልአክ። ስሜ ድንቅ ነውና ለምን ትጠይቃለህ? አለው።" መሳ. 13፥17-18 👉"ከክፉ ነገር ሁሉ ያዳነኝ መልአክ" ዘፍ. 48፥16
Mostrar todo...
👍 1 1
Photo unavailableShow in Telegram
ለበዓለ ዕርገቱ እንኳን አደረሳችሁ +++++ "ወበዕርገቱ ጼሐ ለነ ፍኖተ ሰማያት ወአርኀወ ለነ ኆኀተ ሰማይ::" ትርጉም፦ "በዕርገቱም የሰማያትን ጎዳና ጠረገልን የሰማይንም ደጅ ከፈተልን::" (ድርሳነ ማሕየዊ) ++++ "ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ። በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና፤ ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ። ወደ ምሄድበትም ታውቃላችሁ፥ መንገዱንም ታውቃላችሁ።" (ዮሐ. 14፥1)
Mostrar todo...
🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
ከበዓታ ለማርያም በረከት ረድኤት ይክፈለን። ከቤተ መንግሥቱ ግቢ ውስጥ ያለሽ ታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም:-ለሀገራችን ቅን መሪ፥ለቤተ ክርስቲ ያናችን ቅን አገልጋይ አድዪን።በአማላጅነትሽ ኢትዮጵያ አገራችንን፥ተዋህዶ ሃይማኖታችንን ከነደደ እሳት አውጪልን፥የመከራውን ዘመን አሳጥሪልን።
Mostrar todo...
4
"ያልታወቁ ስንባል የታወቅን ነን፤ የምንሞት ስንመስል እነሆ ሕያዋን ነን፤ የተቀጣን ስንሆን አንገደልም፤ ኀዘንተኞች ስንሆን ዘወትር ደስ ይለናል፤ ድሆች ስንሆን ብዙዎችን ባለ ጠጎች እናደርጋለን፤ አንዳች የሌለን ስንሆን ሁሉ የእኛ ነው።" ~ ፪ኛ ቆሮንቶስ ፮: ፱-፲
Mostrar todo...
👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
አማላጃችን ሚካኤል ሆይ ፈጥኖ ደራሻችን ሚካኤል ሆይ የጌታን ዙፋን ከሚያጥኑ ሱራፌል ካህናት አንዱ ሰማያዊ ካህን አንተ ነህ ። የሰማያውያን ሊቃነ መላእክት ሁሉ አንተ አለቃቸው ነህ ። ይልቁንም የልዑላንም ልዑል አንተ ነህና በጠራሁህ ጊዜ ሁሉ በይቅርታና በቸርነት ድረስልኝ አትራቀኝ። (መልክአ ሚካኤል) ቅዱስ ሚካኤል ከክፉ ጠላት ይጠብቀን፤ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን።
Mostrar todo...
👍 4
Photo unavailableShow in Telegram
#13ቱ_ሕማማተ_መስቀል👇 1. አክሊለ ሦክ (ወደ 70 የሚደርስ ራስ ቅሉ ላይ የተተከለ የብረት እሾኽ የያዘ ዘውድ ወይም አክሊል) 2. ተኰርዖተ ርእስ (ራሱን በዘንግ ወይም በዱላ መመታቱ/መቀጥቀጡ) 3. ተጸፍኦ መልታሕት (ጉንጩን ወይም ፊቱን በጥፊና በቦክስ መመታቱ) 4. ሰትየ ሐሞት (ተጠማሁ ብሎ ስለ ውሃ ፋንታ መራራ ሐሞትን መጠጣቱ) 5. ወሪቀ ምራቅ (በፊቱ በአካሉ ላይ በንቀትና በጥላቻ በመሳለቅ በመዘባበት ፊቱ ላይ ምራቅ መትፋታቸው) 6. ተቀስፎ ዘባን (6,666 ጊዜ የሾለ አጥንትና ብረት በታሰረበት ጅራፍ መገረፉ) 7. ተአስሮ ድኅሪት (የፍጥኝ ወደኋላ መታሰሩ ...በአፍ ጢሙ መደፋቱ) 8. ፀዊረ ጒንደ ዕፀ መስቀል (የሚሰቀልበትን የእንጨት መስቀል መሸከሙ) 9. ሳዶር (ቀኝ እጁ ከመስቀሉ ጋር የተጣበቀበት ችንካር) 10. አላዶር (ግራ እጁ ከመስቀሉ ጋር የተጣበቀበት ችንካር) 11. ዳናት (ቀኝ እግሩ መስቀሉ ከቆመበት ፍልፍል ግንድ ጋር የተጣበቀበት ችንካር) 12. አዴራ (ግራ እግሩ መስቀሉ ከቆመበት ፍልፍል ግንድ ጋር የተጣበቀበት ችንካር) 13. ሮዳስ (ደረቱ ከመስቀሉ ጋር እንዲጣበቅ ከታሰረበት ሽቦ ጋር ልቡ ላይ የተቸነከረ...) አሥራ ሦስቱ ሕማማተ መስቀል የሚባሉት እሊህ ናቸው ብዙውን አንድ ብዙውን አንድ እያሉ በመቁጠር መናገር ነው እንጂ የመከራው ብዛት የስቃዩ ጽናት በቁጥር የሚገለጽ ሆኖ አይደለም!!! ጌታ ሆይ! ሕማምህ ይፈውሰን ዘንድ ቁስልህ እንዲሰማን ማስተዋልን ስጠን 🙏🙏🙏 እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም ዓመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ እግዚአብሔር በፍሥሓ ወበሰላም አሜን! ምንጭ ፦ ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ
Mostrar todo...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
❝ ወደ መሬት ወድቀን በሰገድን ጊዜ ኃጢአት እንዴት ወደ ታች ጎትታ እንደጣለችን እናስታውሳለን። ዳግመኛም ከወደቅንበት በተነሣን ጊዜ የእግዚአብሔር ጸጋ እና ምሕረት እንዴት ከመሬት እንዳነሣንና የሰማዩን ርስት እንደሰጠን እንመሰክራለን።❞ ቅዱስ ባስልዮስ ዘየዐቢ
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
« በፋሲካ ሰሞን የጽድቅ አምላክ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የእግዚአብሔር ሀገር ወደምትሆን ወደ ደብረ ዘይት አቅራቢያ ቀረቡ ብዙ ሕዝብ ብዙ አዛውንትና ሕፃናት የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው ሆሳዕና በአርያም እያሉ ተቀበሉት ፣ ኀይልን ይሰጣቸው ዘንድ በአህያ ውርንጫ ተቀምጦ በፍጹም ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ ። ›› « መድኀኒትሽ ቀረበ ደረሰ አደባባይሽን ተመልከቺ ፤ በሕዝብሽ ደስ ይበልሽ ፤ ከአብርሃም ጋራ የተወዳጀ ከእንድርያስ ጋር በባሕር ላይ የተጓዘ ፤ ከዮሐንስ ጋር ወደ ዮርዳኖስ የወረደ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ቃል ኪዳን ያደረገ ፤ በሰንበት ቀን የዞረ ሆሳዕና ተባለለት ለዳዊት ልጅ ሆሳዕና በአርያም ይሁን እያሉ በአህያ ውርንጫ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሀገር በምስጋና ገባ ›› ሲል ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ስለ በዓሉ ድባብ ጠቅለል ባለመልኩ ነግሮናል ። ይህንን ታላቅ የምስጋና በዓል እያሰብን በአንድ ልብ በአንድ ቃል ለማመስገን አምላከ ቅዱስ ሚካኤል ይርዳን።
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.