cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ሁሉን በግጥም 🌹🌹🌹🌹

💞ለምን ወደድኩህ/ሽ? እንጃ🤷‍♀️🤷‍♂️ 💞ምንህ /ምንሽ ተመቸኝ ? እንጃ🤷‍♀️🤷‍♂️ 💞እንዴት ማረከኝ/ክሺኝ? እንጃ🤷‍♀️🤷‍♂️ 👉ይህ ነው ለእኔ ፍቅር💞ማለት፤ ➽ያለምላሽ ወዶ መገኘት፤ ➽በንፁህ ልብ ጠልቆ መዋኘት፤ 💁‍♂️💁‍ይህ ነው ለእኔ ፍቅር ማለት💞

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
194
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

#ምነው? ሄድኩኝ ባልሽኝ ቁጥር          ልቤን እየቀደድኩ፤ መጣሁ ባልሽኝ ቁጥር            ልቤን እየሰፋሁ፤ የፍቅርሽን ሸክም            ሽቅብ እየገፋሁ፤ ስንት ግዜ ታመምኩ?         ስንት ግዜ ለፋሁ? ይቅርብኝ .... ይቅርብኝ ይህ ፍቅርሽ ከእንግዲህ አልገጥምም ለስጋ አንቺነትሽ ከነፍሴ ክርክር፥ ልቤም ተበትኗል የሚጠገንበት የለውም አንድ ክር. በይ ሂጂ ልጣሽ ግድ የለኝም፤ በዳናሽ ማህተም የትዝታን ዜማ ሳዜም አልገኝም... ሂጂ... ይቅናልሽ ጎዳናው መንገድሽን ያርገው ጨርቅ፤ ከገዛ ራሴ ጋ እንዳልተጣላሁኝ ደሞ እስቲ ልታረቅ... እስቲ ልገስፀው ልጓም ላበጅለት እኔነቴ ይግራ፤ ቻው ልትል ነው ብዬ ነፍሴን እያስጨነኩ አልሆንም ደንባራ... ሂጂ... ጎዳናሽ ይጎዝጎዝ በክህደት ብቃይ ሳር፤ ጣለችኝ ብዬ ነው ልቤን እየኮነንኩ የምበላው አሣር... ተጓዥ... እስኪገባሽ ድረስ የፍቅርሽን ክፍተት የእምነትሽን ጎዶሎ፤ ሳያሳይሽ አይቀር ገፍተሽኝ ብትሄጂ በወደድሽው ሰው ላይ አመልሽን ጥሎ..!
Mostrar todo...
ወፌ ቆመች....እኔ """""""""""""     """ ተው አካሌ ፈርጥም፤ ቢገፉህ ቢቀጡህ፥በሰሚ ማጣት ጥም... ተው አካሌ ደንድን ዱላ ሲቃጡብህ፥ቆዳህን አበድን... ሲገፉህ አትውደቅ፥ ሲወቅጡህ አትድቀቅ፥ እንደ ግመል ተጓዝ፥በነካሽ ውሾች ፊት፤ እንደ እብቅ በትነው ክፋትን አንዘርዝር፥በመቻልህ ወንፊት፤ ኃላ ሲያሰልፉህ አሀዱ ሁንና፥ቅደም በሀሳብ ፊት... ተጓዝ አንተ ብቻ ተጓዝ አንተ ብቻ እንደ ገና ዳቦ በእሳት ደፍነውብህ፥መኖርህ ቢጋገር፤ ያበስልሀል እንጂ የጅራፋቸው ምት፥አያልፍም ከሰንበር... በል አካሌ ፈርጥም፥ በል አካሌ ደንድን፤ መገለል ነው የሚያደምቅ፥ ከጨካኞች ቡድን... ልብህን አስችለው በማፌዝ ከበውህ፥ቢሰሩብህ ታዛ፤ ፊትህ በለጎዱት እንትፍ... ባሉት ምራቅ፥ነፍስያህን አውዛ... ተው አካሌ ደ.ን.ድ.ን ተው አካሌ ፈ.ር ጥ.ም ከተራራው ተጓዝ በጎደፈ እጃቸው፥ቢጭኑብህ መስቀል፤ በበትራቸው ሀይል ቢደክም ቢዝልም፥እግርህ እንደ ቅጠል.... ተጓዝ አንተ ብቻ መሽሎኪያህን ፈልፍል፥በመቻልህ ስንጥር፤ ከዛ ሰማይ ስትደርስ ኤሎሄ በልና፥አስተምራቸው ፍቅር... #ተጓዝ_አንተ_ብቻ
Mostrar todo...
ገጣሚን አትውደጅ """""""'''''''''''''''''''''''''''''' አንገትሽ ነው መቃ ዝንጥፍ ያልሽ ለግላጋ ቁመትሽ ነው ሎጋ ሰማይ የተጠጋ የአፍንጫሽ ስልክክ የአለባበስሽ ልክ ሀገር የሚያማልል የእንስቶች ናሙና የሴት ሁሉ ምልምል እስቲ ሳቅ በይና ልባችን ይሰርጉድ በጉንጮሽ ዲምፕል ኡፍፍፍፍ...ያንቺማ ክትት ያለ አንጀት የማይሞላ ችቦ የመስከረም አደይ ቆንጂት የደም ገንቦ በብርቱካን ጡትሽ መንገድ ባልጎበኘው በሎሚ ተረከዝ ውዴ አንቺን ብሎ በውበትሽ ልክፍት ስንቱ ገባ መዘዝ አጀብ አ..ጀ..ብ ከብርጉድ የሚልቅ የጠረንሽ ሽታ እንደማለዳ ወፍ የድምፅሽ ስርቅታ የአዳም ዘር በሙሉ አንቺን ለማግኘት ሲል ተሳሳበ ቃታ በዲሞፍተር መውዜር ሞትን ቀመሳታ ደሞ ደሞ....የከንፈርሽ አ ወ ይ...የከንፈርሽ ሳሙኝ ሳሙኝ የሚል እንደ ህፃን ልጅ ከንፈር አንቺን አንዴ ስሜ ከዚያ ሲኦል ልግባ በእሳት ውሀ ልንፈር ከቆምሽበት ምድር ስትይ ቀና አፈር ምድር ክድት አ'ርጋው አካሌ ይግባ አፈር እያልኩኝ.....እያልኩኝ ሽቅብ ብክብሽም አትሞኚ ውዴ...እንደዛ አይደለሽም። አንቺዬ ስንኝ የሚቀልስ ገጣሚን አትውደጅ ብዕሩን ሲያነሳ ሀረጉን ሲሰድር ግጥሙን ሲያደረጅ ከሀሳቡ ማህደር ከትውስታው መንደር ሲጠቀም እልፍ ቃል አይምሰልሽ አንቺ ሁሉም ልክ አይደለም የሚለው አባባል ገጣሚ ደምቡ ነው ጥበብ ለማድመቅ ሲል እውነት ያለዝባል ስለዚህ አንቺ ልጅ ከመከም ደመ ግብ ጎፈሬ እንደ ፀሀይ ሙቂኝ ዋዪ በሰፈሬ ከጨረቃ አበራሽ ከምንጭ ውሀ ጠራሽ ከኮከቦች ደመቅሽ ከሰማያት ደረሽ አንቺ የገነት በሬ የፍቅር ጀንበሬ ምትሀቴ ፍቅሬ ሆዴ ገለመሌ ምናምን.....ምናምን እያለ ደራሲው በሰላ ብዕሩ መኖርሽን ቢኩል ከምናቡ ጋራ አይደለሽም እኩል! ..............አትሞኚ.............. አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)
Mostrar todo...
ሱስ አይሰለጥንም የተግሳጽ ማሰሮ አዝለሽ ከሄድሽበት ልስማ ብለሽ መጥተሽ ከተቀመጥሽ አይቀር አድምጪኝ ልንገርሽ ————————- የትንባሆ ቅሉ ሳንባን እስኪማግድ በዘብጥያው መሀል ቁልቁል ጣር ይነጉዳል በጨለማው መንገድ ትውልድ ይፈግማል ታድያ——————- ተቅበዝባዡ ስጋ በምሬት ሊከዳ ሊንደረደር ያልፋል ልማድ እየቆየ እያደር ያቅራል ግና——————— በአስተዋይ አካሄድ ስሜትን ቆንጥጦ መኖር እስኪበጀው ————————- ራስን በመግዛት ወጥመዱን ሊሰብረው በሚንደረደረው————- በዛ አግባብ ህይወት ማንነቱን ይግታው።                                                  ኢያሱ ከበደ                                                         ጥቅምት 21 2015 ዓ.ም
Mostrar todo...
ቀባሪው ከማን ነው መሬት አለቀሰች መሬት አኮረፈች መሬት ተረገጠች እና ምን አመጣች አኛም አለቀስን እኛም አኮረፍን እኛም ተረገጥን ከእንባ በስተቀር ምንም አላመጣን ባክህ  መላስልን የእንባችን ዘለላ ወገን እየሞተ ሆድ እየተታበ እንዴት ያሳብ ይሙላ ፈጣሪ ይመስገን ሟች እየሞተ ነው እኛን ያሳሰበን ገዳዪ ከእናተ ቀባሪው ከማን ነው                   አቤኔዘር (ፊደላዊ
Mostrar todo...
#እመቤቲቷ_ሙሽሪት : : አንቺ የ አምላክ ቅኔ የቅዱሳን ሀገር፣ ያየውልሽን ህልም በይ ስሚኝ ልናገር። እንዲ ነው ሀገሬ ላንዴ ጆሮ ስጪኝ፣ እኔን ብላቴና ሳትንቂኝ አድምጪኝ። ፡ ፡ የተፈናጠጠሽ አስተምሮሽ እንጂ ሰው አትንቂም አንቺ፣ በይ ህልሜን ልለፍፍ ተስፋ ቃሌን እንቺ። ቅዠታም ነክ አትበይ ባክሽ እንደ ዘበት፣ የዮሴፍን ታሪክ ባስተማረ አንደበት። : : አውቃለው ሀገሬ እራስ ወዳድነት እንዲህ ተንሰራፍቶ፣ ጭራው እራስ ሆኖ ሆድ ህሊናን ገዝቶ፣ "ሁሉን ለኔ ለኔ" የምትለው ሀረግ ጠፍንጋ ሳትገዛን፣ ሰው መሆን ነበረ ያንቺ ልኬት ሚዛን። : : እውነት ነው ሀገሬ ... መሠረት ወለሉ ካስማና ማህገሩ፣ ሰው መሆን ነበረ የቋንቋሽ ወሰኑ የእምነትሽ ድንበሩ። : : ዳሩ ምን ይረባል፣ እኛነት ጠውልጎ እኔነት አብቧል። ሁሉን ብችል እንጂ ከ ሀገር ሰፍቶ ሆዴ፣ አንድ ቁና ቢገኝ ተሰፍሮ መች ያልቃል ጉድሽና ጉዴ። : : እመቤቲቷ ሙሽሪት የተስፋዪቷ ሀገር፣ ያየውልሽን ህልም በይ ስሚኝ ልናገር። : : «ወደፊት ተራምደን ኋላችን ላይ ወጣን፣ ዳግም እንደገናም ጊዮን ወንዝን ጠጣን፣ ባንድነት ያሰርነው ነዶዋችንም ፀና፣ ሰው መሆን ከብረ ጉዞዋችንም ቀና፣ ያ የግብፅም ሽንኩርት ላይናፍቅ አለቀ፣ ዘፀሀት ሆነልን ማር ወተት ፈለቀ።» : : እንግዲ ይሄው ነው ሰርክ ደጋግሜ፣ እስኪሰምር ድረስ የማይልሽ ህልሜ። እውነት ነው ሀገሬ ቅዠታም ነክ አትበይ እንደው እንደ ዘበት፣ የዮሴፍን ታሪክ ባስተማረ አንደበት። #ሄኖክ_ብርሃኑ
Mostrar todo...
"አይንህን ለአፈር ከንፈሬን ሌላ ከንፈር" ያለ ፀብ : ያለ ጥል ብለሽ ስትሄጂ፥ "ግንጥል ጌጥ ላንጠልጥል" ያዩሽ ከመንገድ ነበረ አሉኝ - ቅንድቧ ሲነድ ልቧን በእልህ እየጎተተች አመድ ለአመድ፤ ነበረ አሉኝ ... ያ'ይኗ ሸፋሽፍት እየመለጠ ያ ዞማ ፀጉር እየተላጠ፤ ነበረ አሉኝ ... በክፍት አፍንጫሽ ጭስ እየጨሰ ሸክላ ገላዋ እየፈረሰ፤ ነበረ አሉኝ ... By dagmo yr
Mostrar todo...
ዋ አንተ ሰለሞን ! እኔም አንድ ሰሞን ባክኜ ነበረ በምኞት በመሻት አሁን ግን ቃልህን ዞሬ አነሳኋት "ቢመሽም ቢነጋ ... ቀናት ወር ቢቆጠር ንፋስ ቢወነጨፍ ወንዙ ቢገማሸር አዲስ ነገር የለም ከፈጣሪ በቀር !" (ሚካኤል.አ)
Mostrar todo...
እንዳገር የሀሳብ ጎጠኞች...     ከጉድጓዱ አፍ ላይ ለምለም ሳር ጎዝጉዘው     እስከመች እንውደቅ ሳናይ ስንረግጠው።     ያስቀመጥነው ድንበር በጥላቻ ከፍሎን     ከአንድነት በላይ ልዩነት አንግሰን     መኖርን ወደናል ከሰውነት ወጥተን። ደግሞ በዚህ ዘመን ባለንበት ዛሬ ከተማው ዱር ሆኗል ሰዉ ሆኖ አውሬ። ሁሉ ተናካሽ ነው ከራሱ ማይስማማ ከላዩ ደርቦ የጥላቻ አክራማ እንደያኔው ልማድ መተሳሰብ ቀርቷል ሁሉ በርጋጊ ነው ካምላኩ ተጣልቷል። ቀኝህን ሲመታህ ግራህን ዘርጋለት ልባሽህን ቢመኝ እጀጠባብህን በእምነት ጨምርለት፤ ንዋይ ቢጠይቅህ ለመስጠት አትሰስት። ይህ ሁሉ የወንጌል ቃል ጠቅላላ ተረስቷል፤ በነጣቂ ተኩላ ልቦናው ተበልቷል። በየሰፈረበት ጥጋጥጉ ቆሞ ሁሉ አቃሳች ነው ተውጧል በታሞ። መንደር እየሰፋ ሀገር በመጥበቡ እንዳገር ለመኖር አልፈቀደም ልቡ። ግና የሚያስፈራው በትውልዶች ሒደት ሀገር ስሟ እንዳይቀር ከቆይታ ብዛት፤ በታሪክ ድርሳን ላይ ነበረች በማለት። ገጣሚ፦ሊዮ ማክ ባሌ-ጎባ ተፃፈ፦01/02/2015ዓ.ም
Mostrar todo...
እስኪደፈርስ ሁሉም ፎካሪ በሆነበት፥ አካኪ ዘራፍ በሞላበት፥ የሁሉ ልብ አብጦ ሊፈነዳ፥ ጥጋብ ወጥሮ አዳር በረንዳ፤ በሁለት ዓለም ሰው 'ሚተራመሰው፥ በግራጫ ቀለም ቅሉ አንድ አይነት ነው፤ በዚህ ተለዋዋጭ ምድር፥ በድንገት 'ሚነፋ 'ሚያበጥር፥ ጊዜው ደርሶ እስኪለይ የሕልም ዓለም፥ እገ'ላለሁ እንጂ 'ሞታለሁ 'ሚል የለም። ሄኖክ ዘውዱ 22/12/2014 ዓ.ም
Mostrar todo...