cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ፍኖተ-ወራዙት ዘኦርቶዶክስ ⛪

ይህ ፍኖተ-ወራዙት ቻናል መንፈሳዊ ትምህርቶችን የሚያገኙበት ሃይማኖታዊ ቻናል ነው። በዚህ ቻናል በመንፈሳዊ ሕይወትዎ የሚበረቱባቸውን መንፈሳዊ ጽሑፎችና መልእክቶች ባሉበት ሆነው መከታተል ይችላሉ።     መልእክት ወይም አስተያየትና ጥቆማ ካለዎት https://t.me/Tadiweszefinotewerazut https://t.me/TadiwesTeshager ✞ይላኩልን @Fenotewerazuteotc 👈ለግሩፕ

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
2 025
Suscriptores
Sin datos24 horas
-137 días
-5830 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

#ሞስኮ_ሩሲያ "የዘመኑ ፖለቲካ የሃይማኖት ጠላትነት ነው" ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ኪሪል የሞስኮ እና የመላው ሩሲያ የሁለተኛው የሩስያ አፍሪካ ጉባኤ ሐምሌ 27 ቀን 2023 ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ንግግር አድርገዋል። የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በአፍሪካ አህጉር. በአፍሪካ በክርስቲያኖች ላይ የሚደርሰውን ስደት በመጠቆም መሪዎችም በኃይላቸው አስፈላጊውን እንዲያደርጉ ተማጽኗል። በዛሬው ፖለቲካ ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውለው ሌላው የሃይማኖቶች ጠላትነት ነው። በአፍሪካ አህጉር ላይ እንደዚህ አይነት ክስተቶች በአደገኛ ሁኔታ መስፋፋታቸውን መግለፅ ያሳዝናል. እንደ አለመታደል ሆኖ እጅግ የከፋ ስደት የሚደርስባቸው ክርስቲያኖች ናቸው። ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም፣ የሩስያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ዋና መሪ እንደመሆኔ፣ በዚህ አሳዛኝ ሁኔታ ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር አቅምና እውነተኛ ሥልጣን ያላቸውን ሁሉ በትጋትና ከልብ በመማጸን፣ በአፍሪካ ስደት የሚደርስባቸውን ክርስቲያኖች ለመከላከል የተቻላቸውን ሁሉ እንዲያደርጉ አሳስባለሁ። ". ፓትርያርኩ ሩሲያ ከአፍሪካ ጋር ያላት ወዳጅነት “ሩሲያ የአፍሪካን አህጉር ከቅኝ ግዛት የምትጠቀምባት ምድር አድርጋ አይታ አታውቅም” ሲሉ ተናግረዋል። እና አክለውም “ሩሲያ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር በበላይነት እና በስልጣን ደረጃ በትዕቢት ተናግራ አታውቅም። በችግር ጊዜ ሁል ጊዜ አጋርነትን ለማሳየት እና እርዳታ ለመስጠት እንጥራለን። የአፍሪካ ሀገራት ለነጻነታቸው እና እራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ በሚታገሉበት አስቸጋሪ እና አሳሳቢ ወቅት ውስጥ በነበሩበት ወቅት ሩሲያ በንቃት ለመደገፍ ጥረት አድርጋለች እና በኋላም ከሀገሮች ጋር ሰላማዊ ኑሮ በመገንባት እና በርካታ የመሰረተ ልማት ፕሮጄክቶችን በማዘጋጀት ተባብራለች። እንዲህ ያለው ትብብር ዛሬም ድረስ መቀጠሉ የሚታወስ ነው።
Mostrar todo...
ሰንበት ተማሪነት! ...... ከላይም ከታችም ልትሰደብ ትችላለህ ... መሳሳት በፍጹም አይፈቀድልህም ... ምናልባት ከታናሽ እህትህ ጋር ሊሆን ይችላል ከጉባኤ አምሽተህ ወደቤት እየገባህ ያለኸው ... ነገር ግን የሚያየው ሁሉ ሰው ስም ያወጣልሃል ... ባለጌዎች ናቸው ልትባል ትችላለህ ፡፡፡ ሕጉን ስርአቱን የሚያውቀውም ... ዛሬ ቤተክርስቲያን የመጣውም ሊቆጣህ ሊያዝህ ይችላል፡፡፡ አንተ ግን ምንም አትልም ... በፍጹም ትህትና አገልግሎትህን ታገለግላለህ ... ምክንያቱም አንተ ሰንበት ተማሪ ነህ!! ሰንበት ተማሪ! ......... የጥምቀት ዕለት ጸሐይ ከልጅ ልጇ ጋር ልትወርድብህ ትችላለች ... ውሃ ጠምቶ ጠምቶ ሊያምርህ፡፡፡ በዚህም በዚያም በስራ የተወጠሩ ወጣቶች እየገፈተሩህ ምንጣፍ ይዘው ሊያነጥፉ ይችላሉ .... በዚህም መሀል መዝሙር ክፍሉ መጥቶ ሊጮህብህ ይችላል ፡፡፡ በስርዓት ዘምር! ድምጽህ አይሰማም ይልሃል .... አንተ ግን አስፓልቱን ሙሉ እየዘለልክ የዘመርኸው ውልብ ይልብህና እምባ ባይንህ ግጥም ይላል፡፡፡፡ ግን ምንም ማለት አይጠበቅብህም ... ለምንስ ታኮርፍና ... ምክንያቱም አንተ ሰንበት ተማሪ ነህና ! ........ የሆነ ችግር ሊፈጠር ይችላል ... ከተማ ይበጠበጣል ... አንተ አጣናህን ይዘህ ቤተክርስቲያን ትውላለህ ታድራለህ ... በለስ ከቀናህ ትፈነከታለህ፣ ትታሰራለህ ... የግንባር ስጋ ነህ ቤተክርስቲያን ላይ የሚወረወሩ ድንጋዮች በቀጥታ አንተን ነው የሚያገኙት ... ምክንያቱም አንተ ሰን..... .......... ወረብ ጥናት ፣ መዝሙር ጥናት ፣ ኮርስ ፣ አዳር መርሐ ግብር ... የገጠር አገልግሎት እያልክ መሄድ ነው ፡፡፡ በዚ መሀል ትምህርትህ ይከዳሃል ፤ ውጤት አይጠጋህም ፤ በትምህርትህ ላይ ትኩረት አድርግ ተብለህ ከማዘርህ ጋር ዱላ ቀረሽ ግብ ግብ ትለማመዳለህ ፤ አባትህ ማውራት አለብን ይልሃል፡፡፡ በዚ ሁሉ  መሀል የእናንተ ደብር ንግስ ይመጣል ... ክላስ መሄድ አይታሰብም ፤ በማግስቱ እግርስ ሰንበት ትምህርት ቤት እንዳይደርስ የሚል እገዳ ይወጣብሃል ፤ በማግስቱ ማግስት ግን ነጠላህን በአጥር ወርውረህ ሰንበት ትምህርት ቤት ትገኛለህ!! ምክንያቱን ከላይ ነግሬሃለሁ፡፡፡ ....... ሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ  አንዱ አባል እንኳን አንተ እሱም በውሉ በማያውቀው ምክንያት  ይጠላሃል፡፡ ጓደኞቹ ይደረባሉ ... ሕይወት ሊያስጠላህ ይችላል ፤ ከበሮም ላይሰጡህ ይችላሉ ... ፊትም ልትነሳ ትችላህ፤ ደግነቱ አንዱ እሁድ ለት ባለው መርሐ ግብር የታጣላ ሰው አለ ብሎ ይገላግልህንና ሰላምህን ታገኛለህ፡፡፡፡ ....... እንደኔ ደግሞ ዲቁና ከሞካከርክ ... ይሄ ይከተላል ፡፡፡ በመቅደስ አገልግሎት አንድ ቀለም ሳት ካለህ ... ድሮስ ከሰንበት ተማሪ የሚል ጽርፈት ከሽማግሎቹ ቄሶች ትሰማለህ .... ትሸማቀቃለህ ... ቅስምህ ሊሰበርም ይችላል፡፡፡ ...... በሁሉም ፈተናዎች ግን ... ጸጥ ብለህ ታገለግለህ ... ደስ ቢልህ .. ደስ ባይልህ .. ተሰሚነት ቢኖሮህ .. ባይኖርህ ... ያላንተ አይደምቅም ቢባልም ... ይሄን ልጅ ባናየው ቢባልም ፥ በዚሁ ሁሉ መሀል አንተ በትጋት፣ በታማኝነት ፣ በንጹህ ልብህ ታገለግላለህ ... ምክንያቱም አንተ ሰንበት ተማሪ ነህና!! ምንጭ fb Kallkidann Genetu https://t.me/Fenotewerazut
Mostrar todo...
ፍኖተ-ወራዙት ዘኦርቶዶክስ ⛪

ይህ ፍኖተ-ወራዙት ቻናል መንፈሳዊ ትምህርቶችን የሚያገኙበት ሃይማኖታዊ ቻናል ነው። በዚህ ቻናል በመንፈሳዊ ሕይወትዎ የሚበረቱባቸውን መንፈሳዊ ጽሑፎችና መልእክቶች ባሉበት ሆነው መከታተል ይችላሉ።     መልእክት ወይም አስተያየትና ጥቆማ ካለዎት

https://t.me/Tadiweszefinotewerazut

https://t.me/TadiwesTeshager

✞ይላኩልን @Fenotewerazuteotc 👈ለግሩፕ

Photo unavailableShow in Telegram
“… ያችኛይቱ ሔዋን ከአዳም ተገኝታ የተሠራችና አዳም ወደ እርስዋ እያየ ‘ይህች አጥንት ከአጥንቴ ይህች ሥጋ ከሥጋዬ ናት’ የሚላት ናት፡፡ ይህችኛይቱ ሔዋን ድንግል ማርያም ግን ከአዳም የተገኘች ሳትሆን አዳምዋ ክርስቶስ ሥጋው በጅራፍ ግርፋት ሲቆስልና አጥንቶቹ ሲቆጠሩ በጭንቀት እያየች ‘ይህ አጥንት ከአጥንቴ ነው ፤ ይህ ሥጋም ከሥጋዬ ነው’ የምትል ሔዋን ናት፡፡ የቀደመችዋ ሔዋን አዳምዋ በእርስዋ ምክንያት ጠፍቶ ‘አዳም ሆይ ወዴት ነህ?’ ተብሎ ሲፈለግ በዛፎች መካከል ሆኖ ከአባቱ ከእግዚአብሔር ‘ፈርቼ ተሸሸግሁ’ የሚል አዳም ነበረ:: ሁለተኛይቱ ሔዋን ድንግል ግን አዳምዋን ፍለጋ የምትጨነቅና ወዴት ነህ? ስትለው አዳምዋ ‘በአባቴ ቤት እኖር ዘንድ እንዲገባኝ አታውቁምን’ ብሎ የሚመልስላት ከአባቱ እቅፍ ያልተለየ አዳም እናት ናት፡፡ ለድንግል ማርያም ክርስቶስ ከእርስዋ የተገኘ አዳምዋ ብቻ ሳይሆን በቀናተኞቹ ቃየኖች አይሁድ በግፍ የተገደለባት አቤልዋም ጭምር ነው፡፡ ልዩነቱ የአቤል ደም ወንድሙን የሚከስስ ደም ሲሆን የእርስዋ ልጅ የክርስቶስ ደም ግን ‘ከአቤል ደም ይልቅ የሚሻለውን የሚናገር’ ‘ከኃጢአት ሁሉ የሚያነጻ ደም’ ነው" (የብርሃን እናት ገጽ 100 Deacon Henok Haile
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
#ሩሲያ ግምጃ ቤት ማርያም ወይም ንግስቲቱ ማርያም ቤተክርስቲያን ይባላል። ቤተክርስቲያኑ ቅርፁ በዘውድ ቅርፅ የተሰራ ነው። ንግስቲቱ ቤተክርስቲያን በመባልም ይጠራል። መልካም ቀን
Mostrar todo...
ይህን ሕዝብ በቅጡ ካላስተዳደራችሁት የዋዛ አይምሰላችሁ … ይህ ህዝብ አፄ ቴዎድሮስን ወልዶ የበላ፤ የአፄ ዮሐንስን አንገት ያስቆረጠ፤ በእምዬ ምንሊክ ሐውልት ላይ ቁማር የሚጫወት፤ አባባ ጃንሆይን (ሥዩመ-እግዚአብሔር) አንግሶ ያዋረደ፤ ቆራጡን መሪ ጓድ መንግሥቱ ኃይለማሪያምን አንቆራጦ ያባረረ (በቁሙ አስቀምጦ ቲያትር የሚያሳይ)፤. መሪዎቹን የሚፈራ- መሪዎቹን የሚጠላ መሪዎቹ የሚፈሩት-መሪዎቹ የማይወዱት ሠምና ወርቅ የሆነ ሕዝብ ነው፡፡ ይሕ ሕዝብ፡- ፍቅሩንም ጥላቻውንም በሆዱ የሚፈጅ ምሥጢረ ሥላሴ የሆነ ሕዝብ ነው፡፡ ይሕ ሕዝብ፡- ንጉሡ ጥለውት ጠፍተው (ተሰደው) ለራሡ የጎበዝ አለቃ በመፍጠር ፋሺሽቶችን ተዋግቶ አገሩን ነፃ ያወጣ፤ መንግሥቱም (ኃይለማሪያም)ወደ ዚምባቡዬ ሪፈር በተባለ ጊዜ ራሱን በራሱ ያስተዳደረ ጨዋና ንጉሡ ከሥደት ሲመለሱ አልጋውን ያስረከበ የዋህ ሕዝብ ነበር (አይገርምም?)፡፡ ይሕ ሕዝብ፡- በራሡ ቋንቋ ፍቅሩን አስከመቃብር የጻፈ፤ ሼክስፒርን ፈቶ የመግጠም ፀጋ (ዬ) የተሠጠው ሕዝብም ነው፡፡ ይሕ ሕዝብ፡- በቅዱስ ያሬድ በኩል ከሠማየ ሠማያት የመልአክትን ዝማሬ ሰምቶ ዜማ የሠራ ዜመኛ ሕዝብ ነው፡፡ ይሕ ሕዝብ፡- ጦርነትን በባዶ እጁ እንዳሸነፈ ሁሉ ኦሎምፒክንም በባዶ እግሩ ድል ያደረገ ጉደኛ ሕዝብ ነው፡፡ (ሮም ሁለቴ ጉድ ሆነች እንዳሉት የአውሮፓ ወሬኞች…) ይሕ ሕዝብ፡- የዓባይን ልጅ ውሀ ጠማው ተረቱን እያደሰ ሱዳንን አልፎ ግብፅን እስከ ሲናይ በርሀ ውሃ የሚያጠጣ ሳይተርፈው የሚቸር ውሃ የሚያደርግ ሕዝብ ነው፡፡ ይሕ ሕዝብ፡- ሌላው የአፍሪካ ሕዝብ የቀኝ ግዛት እባጩ ንፍፊት ሳይፈነዳለት አብዮት ያፈነዳና እውነተኛው መንገድ የእኔ ብቻ ነው ብሎ ባላብ አደርና በወዛደር በእናቸንፋለንና በእናሸንፋለን ጎራ ለይቶ አንድ ጥይትና ወጣት እስኪቀር ድረስ የሚጫረስ ግራ የገባው-ግራ -ዘመም ሕዝብ ነበር (ው)። ይሕ ሕዝብ፡- ከእናቱ ልጅ ይልቅ በመጽሐፍ ለሚያውቃቸው አብዮተኞች በማድላት ወንድሙን የሚገድል፤ አገር ለመገንጠልና ለማስገገንጠል እስ-በሱ የተጫረሰ ጉደኛ ሕዝብ ነው፡፡ ሲገርም!!! የሆነው ሆኖ… ይሕ ሕዝብ፡- መሪዎቹን የሚፈራ- መሪዎቹን የሚጠላ መሪዎቹ የሚፈሩት-መሪዎቹ የማይወዱት ፡፡ ሠምና ወርቅ የሆነ ሕዝብ ነው፡፡ ፍቅሩንም ጥላቻውንም በሆዱ የሚፈጅ ምሥጢረ ሥላሴ የሆነ ሕዝብ ስለሆነ በቅጡ አስተዳድሩት። ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን https://t.me/Fenotewerazut
Mostrar todo...
ፍኖተ-ወራዙት ዘኦርቶዶክስ ⛪

ይህ ፍኖተ-ወራዙት ቻናል መንፈሳዊ ትምህርቶችን የሚያገኙበት ሃይማኖታዊ ቻናል ነው። በዚህ ቻናል በመንፈሳዊ ሕይወትዎ የሚበረቱባቸውን መንፈሳዊ ጽሑፎችና መልእክቶች ባሉበት ሆነው መከታተል ይችላሉ።     መልእክት ወይም አስተያየትና ጥቆማ ካለዎት

https://t.me/Tadiweszefinotewerazut

https://t.me/TadiwesTeshager

✞ይላኩልን @Fenotewerazuteotc 👈ለግሩፕ

Photo unavailableShow in Telegram
ሃይማኖታችን ሒዊ ነው አላችሁኮ እንጅ እኛማ ተው ብለናል ብዙ ጊዜ ስለ ሰሜናውያን ህብረት ጩኸን ነበር አንሰማም አላችሁኮ🙊 የትግራይ ኦርቶዶክሳዊ ባለ ማተብ ስለ ጽዮን ዝም የማይል በባቢሎን ወንዞች አጠገብ ተቀምጦ ስለ ጽዮን የሚያለቅሱ ዳዊቶች ትመስሉን ነበር ለካ በጽዮን መቅደስ ውስጥ የምትዘሙቱ ውሉደ ኤሊ አፍኒንና ፊንሐሶች ሆናችሁ አሳዘናችሁንይ ስም ብቻ😁
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
ችግር ሲፈጠር ቀድሞ ችግር የሚፈጥረው ባለፈው የቤተክርስቲያኒቱን አንድነትና መሰረት የሚያናጋ እንቅስቃሴ ሲጀመር ቀድሞ የራሱን ችግር በቤተክርስቲያን ላይ ይዞ ብቅ ያለው ይሄው ፍኖተጽድቅ የሚባል ቴሌቪዥን ነበር። በማህበራዊ ሚዲያና በቤተክህነቱ ትግል ራሴን አርማለሁ የሚል ቃል ገብቶ ለጊዜውም ወደ ዘፈን የተቀየሩ መዝሙሮችን ከመልቀቅም ቆም ብሎ ነበር። አሁንም በቤተክርስቲያኒቱ ላይ በትግራይ ክልል የሚገኙ የሃይማኖት ሰዎች አንድነቷንና ቀኖናዋን የሚጥስ ነገር ሲፈጽሙ ፍኖተ ጽድቅም የራሱን አጀንዳ ሰፋ አድርጎ ይዞ ተከስቷል። ቤተክርስቲያኒቱ ችግር ውስጥ ናት ሲባል ችግር ይዞ የሚመጣው ይህ ፍኖተ ጽድቅ የሚባል የተሀድሶ አቀንቃኞች ቡድን ደጋግመን እንደተናገርነው የቤተክርስቲያኒቱ የውስጥ ፈተና ነው። በአሁኑ ሰዓት ይባስ ብሎ ተው የሚላቸው ሰው ጠፍቶ ጭራሽ ከጠቅላይ ቤተክህነቱም ፈቃድ አግኝተናል ማንም አያስቆመንም በሚል ትዕቢት ወደፊት እየመጡ ነው። ለምዕመናን በአጠቃላይ ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች የምንመክረው ሁሉን ነገር በትዕግስትና በዕውቀት እንከታተል፣ በሰዎች አንመራ፣ መስፈርታችን የቅድስት ቤተክርስቲያን ሥርዓትና ቀኖና እንጅ ታዋቂ ሰዎች ወይም ታዋቂ አዝማሪዎች(ዘመሪዎች) መሆን የለባቸውም። አብዛኞቹ ለገንዘብ ተገዥ ሆነዋል። ባለሀብቶቹን በድፍረት ጥፋተኞች ናቸው ብሎ ጥፋታቸውን የሚናገር ሰባኪም፣ ዘማሪም፣ መሪም አስተዳዳሪም የለም። ሐመር 🙏 የኔ አስተያየት፦ ይህ ስሙ እንጅ ግብሩ የቤተክርስቲያን ያልሆነ የውስጥ እሾህ ይሁዳ የሆነ የተሃድሶ ሚድያ ነው" ይሁዳ ስሙ ታማኝ ግብሩ ከሃዲ ፍኖተ ጽድቅ ቲቪም ስሙ የጽድቅ መሪ(መንገድ) ግብሩ አሳሳች የመናፍቃን መንገድ ጠራጊ ተሃድሶ ወነአምን በአኃቲ ቅድስት ቤተክርስቲያን
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.