cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

አራይቫል የልማት እና መረዳጃ ማህበር

አራይቫል የልማት እና መረዳጃ ማህበር የአራይቫል አባል በመሆኖ 👉 የተቸገሩ ሙስሊም ቤቶችን ያንኳኳሉ 👉 መስጂዶች ንፁህ እና ያማሩ እንዲሆኑ ይረዳሉ 👉 በማህበሩ የታሰቡ ዕቅዶች ተፈፃሚ እንዲሆን ይረዳሉ። ቻናላችንን ስለተቀላቀሉ እናመሰግናለን🙏

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
370
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

🕋 የነገው የዐረፋ ቀን ምን ልስራ? 1⃣ዛሬ ሀሙስ አዳሩን በመተኛትህ አጅርን ማግኘትን አስበህ ቶሎ ተኛ. 2⃣ነገን ለመፆም ለስሁር ከፈጅር በፊት ቀድመህ ተነስተህ ስሁር ቅመስ ምክንያቱም አላህና መላኢኮች ስሁር በሚበሉ ሰው ላይ ሰለዋት ያወርዳሉ 3⃣የሌሊትም ሰላት ቢያንስ አራት ያህልን ስገድ ስትሰግድም በሱጁድህ ላይ ሆነህ የዱንያም የአኼራም መልካምን ነገር ለጌታህን በመዋደቅ ተለማመጠው 4⃣ፈጅር ሊደርስ ሲልም እዚያው በተቀመጥክበት ለተወሰነ ደቂቃ አላህን ምህረትን ጠይቀው 5⃣ ከሰላት ቡሀላ የሚባሉትን ዚክሮችን እንዲሁም ተክቢራ እንዳትዘናጋ 6⃣ከቻልክ ፈጅርን ሰግደህ የሰገድክበት ቦታም ላይ ፀሀይ እስክትወጣ ደርስ ቁጭ ብለህ አላህን አውሳ ወይም ቁርአንን ቅራ የጠዋትን ዚክርም ለማለት ሞክር 7⃣ፀሀይ ወጥቶ የተወሰነ ከፍ ካለ ቡሀላ ሁለት ረከዐ መስገድ ፈፅሞ እንዳንረሳ ይህ ካደረክ ሀጅና ኡምራ ያደረገ ሰው ያህል አጅር ታገኝበታለክ አደራህን እንዳያመልጥህ 8⃣ከተቻለክ ፀሀይ ከወጣበት ሰአት ጀምረህ ፀሀይ እስኪገባ የነገዋን ጁሙዐ ሙሉ ቀን ላለመተኛት ሞክር በዚክር በዱዐ በርታ ዱዐህም ምላሽ እንደሚያገኝ እርግጠኛ ሁን 9⃣ረፋድ ላይ የሚሰገደወወ የዱሀን ሰላትንም መስገድ እንዳትዘነጋ 🔟ይህም 👇👇👇👇👇ዱዐ : لا إله إلا الله وحده لا شريك له له الملك وله الحمد وهو على كل شيئ قدير በጣም አብዝተህ በለው ምክንያቱም የዐረፋ ቀን ከሚባሉ ዱዐዎች ሁሉ የሚበልጥ ዱዐ ነውና 1⃣1⃣የግዴታ ሰላቶችህን ሁሉም ወቅቱን ጠብቀህ ከመስገድ እንዳትዘናጋ ከፊትና ከሀላቸው ያሉት የጠበቁት ሱና ሰላቶችንም እንዲሁ ስገድ 1⃣2⃣ከአሱር ሰላት ቡሀላም ፀሀይ ለመግባት እስክትቀርብ ቁጭ ብለህ ቁርአንን አንብብ ከዚየም በዱዐህ ችክ ብለህ አላህን ተለማመጥ በዱዐህም ሀገራችንም ላይ ከሀገር ውጭ የሉ ደካሞችን አካት 1⃣3⃣በስተመጨረሻም ቀን ሙሉ የሰራህውን ኢባዳህ አላህ እንዲቀበልህና ፅናቱንም እንዲሰጥህ ተለማመጠው ዱዐህም ተቀባይነት እንዲኖረው እርግጠኛ ሁን 1⃣4⃣መግሪብ አዛን ሲልም ቶሎ አፍጥር በድጋሚ አላህን ከመለማመጥ እንዳትዘነጋ ምክንያቱም ለፆመኛ አላህ የማይመልስበት ዱዐ አለውና وباالله التوفيق አደራ እኔንም በዱዐ እንዳትረሱኝ 🙏
Mostrar todo...
የዑለሞች ስብሰባን በተመለከተ ዛሬም እንደቀጠለ ነው። የተሟላ መረጃ መደበኛ በሆኑ መልኩ እስኪወጣ ድረስ ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ከማሰራጨት እንቆጠብ። ዝርዝር መረጃዎች በተገቢው ቀንና ሰዓት ይገለጻሉ፣ አሁን ያለው ድባብም መልካም ነው፣ውጤቱም ጥሩ እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን _ ኢንሻ አላህ _ በዱዐ እንበርታ #ሁሉንአቀፍመጅሊስ @Abuki_Tube | @Abuki_Tube
Mostrar todo...
የኢድ አልፈጥር በዓል ላይ አስለቃሽ ጭስ ቦንብ በማፈንዳት ወንጀል የተጠረጠረው ኮንስታብል አንቡላ ኡቴ በዕለቱ በደረሰብኝ ድብደባ ግራ አይኔ እና ኩላሊቴ ላይ ጉዳት ደርሷብኛል ሲል ለፍርድ ቤቱ አስታወቀ። መርማሪ ፖሊስ በበኩሉ በዕለቱ አንድ የጭስ ቦንብ ሳይሆን 3 የጭስ ቦንብ ነው የፈነዳው ብሏል። ዕረቡ ግንቦት 1ዐ ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኢዳልፈጥር በዓል ላይ በመስቀል አደባባይ አካባቢ አስለቃጭ ጭስ ቦንብ በማፈንዳት ወንጀል የተጠረጠረው ኮንስታብል አንቡላ ኡቴ በዕለቱ በደረሰብኝ ድብደባ ግራ አይኑን እና ኩላሊቴ ላይ ጉዳት ደርሷብኛል ሲል ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት አስታወቀ። የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል አድማ ብተና ዘርፍ ባልደረባ የሆነው ኮንስታብል አንቡላ ኡቴ ባሳለፍነው ሚያዚያ 24 ቀን በተከበረው የኢዳል ፈጥር ባአል በአ/አ ከተማ በሰማታት መታሰቢያ ሙዚዬም አካባቢ በተመደበበት የወንጀል መከላከል ስራ ላይ እያለ ከፈነዳው አስለቃሽ ጭስ ቦንብ ጋር ተያይዞ ተጠርጥሮ ዛሬ ለኹለተኛ ጊዜ ካለጠበቃ ፍርድ ቤት ቀርቧል። ተጠርጣሪው ኢድ አልፈጥር በዓል በተመደበበት ሥራ ላይ በአጋጣሚ ሳላውቅ የፈነዳብኝ አስለቃጭ ጭስ ቦንብ ሲፈነዳብኝ ጭሱ ወደ ህዝቡ እንዳይሄድ ወዲያው ሸገር ባስ ውስጥ ወርውሬ ከትቻለሁ፤ በአካባቢው የነበሩት ሰዎች ግን የፌደራል ፖሊስ ልብስ ለብሼ ሳለሁ አንገቴን አንቀው ባደረሱብኝ ድብደባ የግራ አይኔና ኩላሊቴ ላይ ጉዳት አድርሰውብኛል ሲል ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል። ተጠርጣሪውን ያቀረቡት ኹለት መርማሪ ፖሊሶች ባሳለፍነው ሚያዚያ 26 ቀን ጀምሮ ለተጨማሪ ምርመራ በተሰጣቸው የ10 ቀን ጊዜ ውስጥ የሰሩትን የምርመራ ውጤት ለችሎቱ አቅርበዋል። በዚህም የሦስት ሰዎች ምስክርነት ቃል መቀበላቸውንና የሥራ ሀላፊዎችን ቃል መውሰዳቸውን፣ የተጠርጣሪው የግል ስልክ ምርመራ እንዲደረግ ለብሔራዊ መረጃ ደህንነትና ለኢትዮ ቴሌኮም ደብዳቤ መጻፋቸውን አብራርተዋል። የፋይናንስ ድጋፍ እንዳለውና እና እንደሌለው ለማጣራት ለባንኮች ደብዳቤ መጻፋቸውን ተናግረዋል። ግብረአበሮችን ተከታትሎ የመያዝ ሥራ ለመስራትና ምርመራ አጠናቀው ለሚመለከተው ዓቃቢህግ ለመስጠት ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። በፍርድ ቤቱ በኩል ግብረአበር ለመያዝ ማለት ምን ለማለት እንደሆነ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል። ከፍንዳታው በፊት ከአንዲት ሴት በአካል ማዋራቱን እና በወቅቱ ስልክ ተደውሎለት ሲያወራ እንደነበር ጠቁመው ይህን ተከትሎ ግብረአበር ካለ የመያዝ ሥራ እንደሚሰራ አብራርተዋል። ተጠርጣሪው በበኩሉ “የፈነዳው ቦንብ አውቄ አደለም ባጋጣሚ እንጂ ምንም አይነት ወንጀል እኔ አልሰራሁም በኔ የደረሰ ችግር የለም” ሲል ምላሽ ሰጥቷል። ከደቡብ ክልል ዳውሮ ዞን ለሥራ መምጣቱን ገልጾ፤ ጠያቂ ዘመድ እንደሌለው ወላጆቹን በሞት በማጣቱ ትንሽ ወንድሙን በሱ እርዳታ እንደሚያስተምር በመግለጽ ዋስትና እንዲፈቀድለት ፍርድ ቤቱን ጠይቋል። መርማሪዎቹ በበኩላቸው በዕለቱ አንድ የጭስ ቦንብ ሳይሆን 3 የጭስ ቦንብ ነው የፈነዳው ያሉ ሲሆን፤ ተጠርጣሪው ከተመደበበት የሥራ ምድብ ውጪ በህዝብ መሀል ሆኖ ነበር ያሉ ብለዋል። ሲጀመር አስለቃሽ ጭስ ቦንብ ይዞ ህዝብ መሀል መቆም አይፈቀድም ይሁንና እንዲወጣ ታዞ ሳይወጣ ቀርቷል ኹከትና ብጥብጡም በዚህ መነሻ ነው የተነሳው ሲሉ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በዚህ መነሻ በመንግስትና በግል ድርጅቶች ላይ የደረሰው የንብረት ጉዳት ፍርድ ቤቱ እንዲረዳላቸውና ለተጨማሪ ምርመራ 14 ቀን እንዲፈቅድላቸው ጠይቀዋል። ጉዳዩን የተከታተለው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀሪ ምርመራ ማድረግ እንደማያስፈልግ በመግለጽ ለተጨማሪ ምርመራ 13 ቀናትን በመፍቀድ የምርመራ ውጤት ለመጠባበቅ ለግንቦት23 ቀን 2014 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ ዘግባለች። ©አዲስ ማለዳ @Abuki_Tube | @Abuki_Tube
Mostrar todo...
አሁን አንዋር መስጅድ! ደማቹ ደማችን ነው!! አማራነት እምነት ከሆነ እኔ ሙስሊም ነኝ!! @Abuki_Tube | @Abuki_Tube
Mostrar todo...
00:49
Video unavailableShow in Telegram
ወላሂ ይለያሉ‼️ ጀግኖቹ የረጲ ተማሪዎች ሰላት ቢፈቀድላቸውም ገና ያለተመለሱልን ጥያቄዎች አሉ በማለት በምታዩዋቸው መልኩ አሸብርቀው አንድነታቸውን እያሳዩ ይገኛል!! #የኔ ትውልድ #በሰላት_አልደራደርም #ሂጃቤ_መገለጫዬ @Abuki_Tube | @Abuki_Tube
Mostrar todo...
1.37 MB
04:03
Video unavailableShow in Telegram
ይህን ቪዲዮ ተመልከቱት ሼርም አድርጉት❗️❗️❗️ እንደነዚህ አይነት ጀግና ትውልድ እየመጣልን ነው አልሐምዱሊላህ "ፈቀዳችሁልንም አልፈቀዳችሁልንም ሰላታችንን ከመስገድ ማንም አያስቆመንም " ጀግና ተማሪ በትምህርት ሃላፊዎች ፊት ከተናገረው‼ #እንሰግዳለን_እንማራለን! #በሰላት_አንደራደርም! @Abuki_Tube | @Abuki_Tube
Mostrar todo...
6.70 MB
የምስራች ለከሠአት ተማሪዋች የአስር ሠላት በአንሧር መስጂድ እንድንሠግድ ተፈቅዶልናል ። #አየር_ጤና #እንሰግዳለን_እንማራለን ! #በሰላት_እነደራደርም @Abuki_Tube | @Abuki_Tube
Mostrar todo...
3.29 KB
መብትህን ለመጠየቅ ካልተኛል መብትህን ታገኛለህ‼️ የአየር ጤና ትምህርት ቤት ጀግኖች ከከሰዓት ሲማሩ የዐስር ሶላትን ወጥተው መስገድ እንዲችሉ ተፈቅዶላቸዋል። @Abuki_Tube | @Abuki_Tube
Mostrar todo...
አልጨረስንም!! በሰላት አንደራደርም!! በተማሪዎች የሰላት ክልከላ ዙርያ ከመንግስት አካላት ጋር የአዲስ አበባ መጅሊስ አመራር ከሆኑት ከሸኽ ሱልጣን አማን ሃር በቃል ደረጃ ተማሪዎች ከት/ቤት ወጥተው እንዲሰግዱ ስምምነት ላይ መደረሱን ለማወቅ ችለናል:: ሆኖም ካለፉ ልምዶቻችን አንፃር ይህ ስምምነት ከቃል ወርዶ መመርያ ላይ መስፈር ይኖርበታል:: እስከዝያም ድረስ የተማሪዎችን ደህንነት ለመጠበቅ በፅሁፍ ለሁሉም ት/ቤት እና የፀጥታ አካላት ትዕዛዙ በተዋረድ እንዲደርሳቸው መደረግ ይኖርበታል:: መብታችን በሆኑ ጉዳዮች ላይ የትውልዱን ዕድሜ መጨረስ ይብቃ:: ከጅምሩም ልክ ያልነበረ ክልከላ በመሆኑ በአጭር ቀናት ውስጥ በተማሪዎች ላይ ጉዳት ያደረሱ የፀጥታ አካላትና መምህራን ላይ ህጋዊ እርምጃ ይወሰድልን:: ©ዛውያ ቲቪ ተግባራዊ ዳዕዋ! @Abuki_Tube | @Abuki_Tube
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
ሰበር ዜና ሶላትን አስመልክቶ ሙስሊም ተማሪዎች ወጥተው እንዲሰግዱ ከስምምነት ተደረሰ። Mujib Amino ▬▬▬▬▬▬▬▬▬●●▬▬▬▬▬▬▬▬▬ ሚያዚያ 03/2014 ሰኞ በተለይም ካለፈው ሳምንት ወዲህ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የሴኩላሪዝም ጽንሰ ሐሣብ abuse በማድረግ ሙስሊም ተማሪዎች በእምነታችው በግዴታነት የተደነገገውን ሶላት ወደውጪም ቢሆን ወጥታችሁ አትስገዱም በማለት ሕገ መንግስታዊ የኃይማኖት ነጻነታቸውን ሲገፍ ቆይቷል። በዛሬው እለትም ቢሆን የተለያዩ ትምህርት ቤቶች ላይ ሶላትን አስመልክቶ ከተማሪዎች ጋር አላስፈላጊ ግብግብ ሲፈጸም ነበር። የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዋና ፕሬዝደንትን የሆኑት መሪያችን ፣ አባታችን ፣ የሕዝባችን ጠበቃ የሆኑት ሸይኽ ሱልጣን አማን በየእለቱ የመንግስት ቢሮዎችንና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ካለእረፍት ሲወተውቱ ቆይተዋል። በዛሬው እለትም ከአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ጋር በነበረው ውይይት የአዲስ አበባ መጅሊስ ፕሬዝደንት ሸይኽ ሱልጣን አማንና ባልደረቦቻቸው ባደረጉት ትግል ተማሪዎች ወደውጪ ወጥተው እንዲሰግዱ አቅጣጫ መሰጠቱን ለማወቅ ተችሏል። በአሁኑ ሰዓትም በስምምነት ላይ የተደረሰውን የተማሪዎችን የሶላት ጉዳይ በፁሁፍ እንዲደርስና ለሁሉም ክ/ከተሞች በግልባጭ እንዲደርስ በመነጋገር ላይ ይገኛሉ። ትግላችን ይቀጥላል! ▬▬▬▬▬▬▬▬▬ የቴሌግራም ቻናል-https://t.me/MujibbinISLAM @Abuki_Tube | @Abuki_Tube
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.