cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ወይጉድ ኢንተርቴይመንት 🤣

#ወይጉድ ኢንተርቴይመንት የመዝናኛ የቁም ነገር ቻናል ነው ባላችሁበት ማዝናናት የቻናላችን አላማ ነው! ከኛ ጋ ሲሆኑ አትርፍው ይዝናናሉ ወቅታዊ የጥበብ አለም ወሬዎች በየቀኑ ይደርሶታል። አስተያየት ጥቆማ ካሎት አድርሱን

Mostrar más
Etiopía8 272Amárico5 954La categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
1 380
Suscriptores
-124 horas
-107 días
-3230 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Photo unavailableShow in Telegram
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️ የTelegram TON wallet ከHamster Kombat ጋር መስራት መጀመራቸውን አሁን ከደቂቃዎች በፊት አሳውቀዋል። ይህ ማለት እውነተኝነቱን ከፍ ያደርገዋል። ነገር ግን መቼ list እንደሚደረግ አላሳወቁም ። ያልጀመራችሁ ብትጀምሩ የተሻለ ነው። ከስር ያለውን link እየተጫናችሁ መጀመር ትችላላችሁ👇👇👇 https://t.me/hamster_Kombat_bot/start?startapp=kentId2101920214
Mostrar todo...
🕯 ብዙ ሰው ስለ TapSwap         ይጠይቃል   📈Tap Swap በቅርቡ የተለቀቀ       Airdrop ሲሆን በ Solona        Crypto የተደገፈ ነው 📈 Solona Coin already Market       ላይ List የተደረገ ስለሆነ ጥሩ          መተማመኛን ይሰጣል 📈አሁን ላይ 1solona Coin 176$       ዋጋ አለው 🔼በአሁኑ ሰዐት ከ25 Million ሰዎች      TapSwap እያደረጉ ይገኛሉ ⌛ አንድ ሳምንት ያህል ስለሚቀረው       የቻናላቹትን ያህል መስራት ትችላላችሁ 🕯 ምን ያህል Coin በምን ያህል      Solona Coin እንደሚቀየር አሁን     ላይ Accurate መናገር ባይቻልም       10Millon Coin 1 solona Coin     or 176$ ዋጋ ሊኖረው የሚችልበት      Estimation አሉ 🟢 ያልጀመራችሁ ከታች ያለው ሊንክ          በመጫን መጀመር ይችላሉ https://t.me/tapswap_mirror_2_bot?start=r_2101920214 💵ለመጀመሪያ 2500 Coin      ይሰጣችሁል plus Task ላይ      በመሄድ Solona wallet      በማገናኘት እና Social      Addresቸውን Follow በማድረግ     300,000 coin ማግኘት ይችላሉ ➡️ስለዚህ በ300k + Coin ጀመራችሁ        ማለት ነው
Mostrar todo...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
tap swap በቀላሉ ገንዘብ የማግኛ ዘዴ ነው   በቀላሉ ታብ እያረጋቹ task እየሰራቹ  coin ትሰበስባላችሁ ግን እዚ ጋር ነው ትልቁ ሚስጥር እስከ  may 30ነው ጨዋታው የሚቀጥለው ግን ጨዋታው ካለቀ በኋላ ኮይናችሁን በፍፁም እንዳትሸጡ እንዳትቀይሩ ያዙት‼️...ስትይዙት እንደ ዶላር ኮይናችሁ የመሸጫ ብራችሁ ይጨምራል ስለዚህ ማቆየቱ ጥቅም አለው እናንተም በዚህ ሊንክ እየገባችሁ ቶሎ መስራት ትችላላችሁ 👇👇 https://t.me/tapswap_mirror_2_bot?start=r_2101920214 🎁 +2.5k Shares as a first-time gift
Mostrar todo...
👍 1
ነገር በምሳሌ ድ ን ጋ ይ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ትልቅ ቤት ይሆናል። 🪨 ድንጋይ ቢያጎኑት፣ ተመልሶ ባናት። 🪨 ድንጋይ ለካብ፣ ቂጣ ለራብ። 🪨 ድንጋይ ለረገጠ ፍለጋ የለውም፣ ውሃ ለጠጣ ሽታ የለውም። 🪨 ድንጋይ ላይ ተቀማጭ፣ የባለጌ ተለጣጭ። 🪨 ድንጋይ ላይ ውሃ ማፍሰስ። 🪨 የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም። 🪨 የድንጋይ ልብ፣ የኩበት ግንብ የለውም። 🪨 ቅል ባገሩ ድንጋይ ይሰብራል። 🪨 ድንጋይ ወርዶ እዘብጥ ያርፋል፣ ያላገኘው ይተርፋል። 🪨 የድንጋይ ንፍሮ፣ የብረት ቆሎ። 🪨 ድንጋይ ወደሰማይ ቢወረወር፣ ተመልሶ ከምድር። 🪨 ካብ አይገባ ድንጋይ። 🪨 ድንጋይ ሲያረጅ መጭ ያበቅላል። 🪨 የድንጋይ መቀመጫና የባዕድ ፍቅር እያደር ይቆረቁራል። 🪨 ጣጣ ፈንጣጣ፣ ድንጋይ ፈለጣ። 🪨 የማይችሉት ድንጋይ ሲያወጡት ደረት፣ ሲያወርዱት ጉልበት ይመታል።      
Mostrar todo...
👍 2
አንዴ ብቻ አስቡ! አካባቢያችሁን አፅንዖት ሰጥታችሁ ተመልከቱ፣ ዙሪያችሁን በጥንቃቄ ቃኙ፣ ምን እየተደረገባችሁ እንደሆነ በቅርበት ተከታተሉ። ሁላችንም በሰዎች ተከበናል፣ በማህበረሰባችን ክበብ ውስጥ እንገኛለን፣ ብዙ ጊዜ ምርጫችንም የሚሆነው ከዛው ከምንሰማውና ከምናየው ነገር ውስጥ ነው። እናም አብዝታችሁ ልትጠነቀቋቸው የሚገቡ ሰዎች አሉ። አነዚህ ሰዎች ሰነፍ ጥቅመኛ ሰዎች ናቸው፣ ከስንፍናቸው በላይ የሚፈልጓችሁ ለጥቅም ብቻ ነው፣ ምንም ሳይሰሩ ከድካማችሁ ውጤት ተካፋይ፣ አንዳች ነገር ሳያቃኑ እናንተ በሰራችሁት ስራ ለመመስገን ይጥራሉ፣ ስልጣን ካላቸው በስልጣናቸው፣ ገንዘብ ካላቸው በገንዘባቸው፣ እውቀት ካላቸው በእውቀታቸው ሊያጠቋችሁ ይፈልጋሉ። እድገታችሁ እንደ ጭካ ውስጥ እሾ ያቆስላቸዋለው፣ ለውጣችሁ ያለወትሮው ያንገባግባቸዋል፣ እንደነሱ ሰነፍ፣ እንደነሱ ጥቅምን ብቻ እንዳታስቡ ሊያደርጓችሁ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። አዎ! ከእንደዚህ አይነት ሰዎች ለመራቅ አንዴ ብቻ አስቡ፣ ከነዚህ ሰዎች ለመለየት ከንግግራቸው በላይ ተግባራቸውን ብቻ ተመልከቱ። ለምን አብዝተው ይፈልጓችኋል? እስከ መቼ አብረዋችሁ ይሆናሉ? ምን እስኪያገኙ ከጎናችሁ ይቆማሉ? ምን ያህል ያለምንም ጥቅም ዋጋ ሊከፍሉላችሁ ዝግጁ ናቸው? እራሳችሁን ጠይቁ፣ በዙሪያችሁ ያሉትን ሰዎች መርምሩ። ሲኖራችሁ ይመጣሉ፣ ሳይኖራችሁ ስትቀሩ ያጠለሿችኋል፤ ስታገኙ ከጎናችሁ ናቸው፣ ስታጡ ብትፈልጓቸውም አታገኟቸውም፣ ጥቅም ባለበት አሉ፣ እርዳት በሚያስፈልጋችሁ ሰዓት ወሬያቸውም አይኖርም፣ ደብዛቸው ይጠፋል። እራሳችሁ ላይ ተጨማሪ ሸክም አትጨምሩ፣ ከነርሱ መለየት ካለባችሁ በፍጥነት ተለዩአቸው፣ መራቅ ካለባችሁ በጊዜ ራቋቸው። ጥቅማችሁ ሲቀር እናንተም እንደምትቀሩ እወቁ። የሰው ልጅ ሚስጥር ነው፣ የሰው ልጅ ተመርምሮ አይታወቅም ነገር ግን ተግባሩ በትንሹም ቢሆን የማንነቱን ገፅታ ያስረዳልና እርሱን ባወቁት ልክ መጠንቀቅ ያስፈልጋል። አዎ! ጀግናዬ..! ለራስህ ሃላፊነት አለብህ። ራስህን ከአደጋ የመጠበቅ፣ አካባቢህን በአጋዥ ሰዎች የመክበብ፣ የስራ ከባቢህን የማፅዳትና ሁሌም በአዎንታዊ መንገድ እንድታድግ የሚያግዝህን ማህበረሰብ የመፍጠር ሃላፊነት አለብህ። አካባቢህን ለማፅዳት ጊዜ እንደሌለህ እወቅ። አካባቢህ ማለት አንተ ነህ፣ የምትቀርበው እያንዳንዱ ሰው የህይወት አቅጣጫህንና ግንዛቤህን የመቀየር አቅም እንዳለው አስተውል። በስልጣናቸው ከሚመኩ፣ በገንዘባቸው በሚታመኑ፣ የህይወት ዘመናቸውን በሙሉ ከመስጠት መቀበልን ከሚመርጡ፣ ለሰውነትህ ክብርና ቦታን ከማይሰጡ ሰዎች ራቅ። ስንፍና እንደ በሽታ ነው፣ ማንም በሰነፎች መሃል ቢወድቅ ከስንፍና የሚያመልጥበት እድል አይኖረውም። ነፃነትህ በእጅህ ነውና ለራስህ ፍላጎትና መብት ለመቆም ሰነፍ አትሁን፣ ዙሪያህን በጠቃሚ ሰዎች ለማጠርም ምንም ሀፍረት አይሰማህ። ሰዎች ይቆሙልህ ዘንድ በቅድሚያ አንተ ለራስህ መቆም እንዳለብህ እወቅ። 🙏መልካም ምሽት ተመኘሁ 💚💛❤ 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://youtube.com/@Weygud18 https://youtube.com/@Weygud18
Mostrar todo...
👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
ግለ ታሪክ - ጄሚ ፎክስ 🎭 ጄሚ ፎክስ በ1959 ዓ.ም ቴክሳስ ውስጥ ተወለደ:: ባለ ብዙ የጥበብ ተሰጥኦ መገለጫ የሆነው ፎክስ በትወና ስራዎቹ ብቻ ሳይሆን በሙዚቃ ስራዎቹም ይታወቃል። የፎክስ ሁለገብነት፣ ማራኪነት እና ተጫዋችነት በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን አትርፎለታል። ከበርካታ ተወዳጅ ስራዎቹ መካከል የሬይ ቻርለስን መንፈስ ያለምንም እንከን ያሳየበት ስራ ዋነኛው ሲሆን ላሳየው አስደናቂ የትወና ችሎታም የአካዳሚ ሽልማትን አግኝቷል። ይህ እንከን የለሽ ትወና ሰፊ አድናቆትን ከማስገኘቱም በላይ በመዝናኛ ኢንደስትሪ ውስጥ አይረሴ የሆነም ስራ ነው። ከትወና ስራዎቹ ባሻገር ፎክስ በሙዚቃ ስራዎቹም ሽልማቶችን አግኝቷል፣ በምርጥ R&B ዘርፍ ትልቁን የግራሚ ሽልማት ማሸነፍ ችሏል ። መድረክን ያለፍርሀት በቀልድና በሙዚቃ እያዋዛ መምራት የሚችለው ሁለገቡ የጥበብ ሰው ፎክስ የስኬት ጉዞው በጽናት እና በቆራጥነት የታጀበ መሆኑን ብዙዎች ይመሰክራሉ:: በቆዳ ቀለሙ ምክንያት ሲደርስበት የነበረው መገለል ያልበገረው ሌላ ነገር ይበግረዋል ብሎ ማሰብ ዘበት ነው የሚሉ ብዙ ጥቁር አሜሪካውያን ናቸው። የበጎ አድራጎት ስራዎቹን ብዙ ሰው እንዲያውቅበት የማይፈልገው አርቲስቱ ከ5 በላይ የበጎ አድራጎት ስራዎች ውስጥ ተሳታፊ እንደሆነ ይገመታል። በፊልም፣ በሙዚቃ እና በአጠቃላይ በመዝናኛ ዓለሙ ላይ ያሳረፈው የማይጠፋ አሻራ የልዩ ተሰጥኦ፣ መገፋትን የመቋቋም እና የርህራሄ ድብልቅን ያካተተ ነው። የእሱ ጉዞ ለብዙዎች በተለይም በቆዳ ቀለማቸው ምክንያት ለሚገለሉ ሰዎች ምሳሌ ሆኖ ያገለግላል:: 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://youtube.com/@Weygud18
Mostrar todo...
እረፍቴ ባንተ ነው! ፨፨፨/////////፨፨፨ ከራስ ጋር ንግግር፦ "ትናንቴ ከባድ ነበር ነገር ግን ባንተ ለዛሬ በቅቼያለሁ፣ ዛሬዬ ከባድ ነው ነገር ግን ባንተ ለነገ እንደምበቃ አምናለሁ፣ እንዲሁ ነገዬ ቢከብድ፣ ከአቅሜ በላይ ቢሆን፣ የማልችለው፣ የማልቋቋመው ፈተና ውስጥ ቢከተኝ እንኳን ሁሉን ባንተ ማለፍ ለምጄያለሁና ከቶ አልፈራም፣ በፍፁም አልሸበርም። ሸክሞቼ እንዴት እንደሚወርዱ አላውቅም፣ ጭንቀቶቼ እንዴት እንደሚጠፉ አይገባኝም፣ ችግሮቼ መቼ በእኔ ላይ ስልጣን እንደሚያጡ፣ መቼ ተፈተው እንደምመለከት አላውቅም። ነገር ግን አንድ ነገር አውቃለሁ ምንም ነገር በእኔ አቅም አልሆነም፣ አንዳች ነገር በእኔ ጥረት አልተስተካከለም። ሁሉ የሆነልኝ በሚወደኝ አባቴ፣ በሚሳሳልኝ ፈጣሪዬ፣ ሁሌም በሚያስብልኝ አምላኬ ቅዱስ እግዚአብሔር እንደሆነ አውቃለሁ። የእውነት ግን እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን አለ? ማንም። ህይወት እኮ እርሱ ነው፣ ሰውስ ቢሆን ያለርሱ ማነው? ማንም። እንደ ልጅነቴ እንዴት ተስፋ እንዳልቆርጥ እንደምታበረታኝ ሳስብ በጣም እደነቃለሁ፣ ምንም በሌለበት ባንተ እንድታመን፣ ከባዱን ባንተ እንዳልፍ ሃይል ሆነሀኛልና ሁሌም አመሰግንሃለሁ። አዎ! እረፍቴ ባንተ ነውና የትም አልሔድም፣ ሰላሜ አንተ ነህና ማንንም አልፈልግም፣ የልባዊ ሃሴቴ ምንጭ አንተ ነህና ከማንም አልጠብቀውም። እለት እለት ሳስብህ እደነቃለው፣ ስራህ ያስደምመኛል፣ የምታስብልኝ ነገር እጅጉን ይገርመኛል፣ ባደረክልኝ እያንዳንዱ ነገር ሁሌም ፍቅርህን አየዋለሁ፣ ጥበቃህ ኬት አንስቶ የት እንዳደረሰኝ ሳስብ እንዲሁ ቃላት ያጥረኛል። እኔ የማውቀው አውቅ ዘንድ የፈቀድክልኝን ብቻ ነው፣ አንተ ግን ከዚህ በላይ ብዙ የማላውቃቸው፣ ያላየኋቸው ነገሮችን እንዳደረክልኝ አምናለሁ። ላንተ ድንቅ ስራ እኔ አንድ ማስረጃ ነኝ፣ ከእኔም ውጪ በሰዎች ህይወት ላይ ተዓምራትህን አይቻለሁ። እኔ በሰውነቴ በስራህ እገረማለሁ፣ አንዳንዴማ መገረሜ አምላክነትህን ከመርሳቴ የመነጨ ይመስለኛልና ይቅር በለኝ። በሰውኛ አይን የሰው ልጅ ከሚያደርገው እያስተያየው ክብርህን አውርጄዋለሁ፣ በተገደበው ማንነቴ ያንተንም አቅም ገደብ አበጅቼለታለሁና ይቅር በለኝ። አንተ አምላኬ ነህ፣ ላደረክልኝ ብቻ ሳይሆን ላላደረክልኝም ጭምር ዘወትር ከልቤ አመሰግንሃለሁ።" አዎ! ጀግናዬ..! የሚገባህንም የማይገባህንም ለማግኘት ብዙ ወጥተሃል፣ ብዙ ወርደሃል፣ እዚም እዛም ሔደሃል፣ የሰው ፊት ገርፎሃል፣ ተገፍተሃል፣ ትልቅ ዋጋም ከፍለሃል ጥረትህን የሚያየውና ድካምህ የሚገባው ግን እግዚአብሔር አምላክህ ብቻ ነው። የሰው ልጅ እንዳንተው ደካማ ነውና ከራሱ የግል ጉዳይ በላይ ያንተን ድካምና ፈተና የመረዳት አቅሙ የለውም፣ በትንሹ ቢረዳህም ሊያግዝህ የሚችለው በጥቂቱ ነው። አንጀት አርሱ ድጋፍ፣ ልብ አድርሱ ስጦታ፣ ታሪክ ቀያሪው ተግባር የሚከናወነው በሰው ሳይሆን በፈጣሪ ብቻ እንደሆነ አስታውስ። ህይወትህን ከልብህ ተመልከት፣ ውስጥህን መርምረው፣ እራስህን ለሰው ባጋለጥከው ልክ ለአምላክህ ገልጠህ አሳየው፣ በሰው ከመታመንህ በላይ በእርሱ ታመን፣ ሳታስበው ያደረገልህን አስታውስ። እንዲሁ የሃሳብህ ትልቅነት ላንተ እንጂ ለእርሱ አይደለምና ከእግዚአብሔር ጋር ተዓምር የመሰሉ ተግባራትን ለመፈፀም ቅንጣት ታህል እንዳትፈራ። ያስጀመረህ እርሱ ነውና የሚያስጨርስህም እርሱ እንደሆነ እመን። እፁብ ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🌅🌞🏞 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://youtube.com/@Weygud18 https://youtube.com/@Weygud18
Mostrar todo...
👍 1
👍ብልጥ ሁን! የተሻለ ነገር ይገባኛል ብለህ የምታስብ ከሆነ ከእኔ ይሻላሉ ብለህ ከምታስባቸው ሰዎች ጋር ህብረት ፍጠር፣ የህይወቴን ጥራት መጨመር እፈልጋለሁ ካልክ ህይወታቸው ጥራት ያለውን ሰዎች ሁን ብለህ አጥና፣ ገቢዬን ማሳደግ አለብኝ ካልክ በአቋራጭ ከበለፀጉት ሳይሆን ልክ እንዳንተ ከዜሮ ተነስተው የራሳቸውን ቢዝነስ ከገነቡ ሰዎች ቁጭ ብለህ ተማር፣ ስኬታማ የፍቅር ወይም የትዳር ህይወት እንዲኖርህ ከተመኘህ ዝቅ ብለህ በትህትና የተሳካ የፍቅር ወይም የትዳር ህይወት ያላቸውን ሰዎች ህይወታቸውን መርምር፣ የመግባባት ደረጃቸውን አጥና፣ የአብሮነታቸውን ሃይል ተመልከት፣ እርስበእርስ ያላቸውን የመከባበር ልማድ ላንተ በሚሆን መልኩ ወደራስህ ውሰድ። ብልህ ሰው ብለሃቱ የሚገለፅበት አንደኛው መንገድ ከእርሱ ከሚሻሉት ለመማር ያለው ትጋት ነው። ጤናማ ያልሆነ የበታችነት ወይም የበላይነት ፉክክር ከጥፋት በቀር ሌላ የሚያተርፍለት ነገር እንደሌለ ያውቃል። ጥራት ያላቸው ሰዎች ምንያህል ህይወቱ ላይ ጥራትን መጨመር እንደሚችሉ፣ ምንያህል ውጤታማና ስኬታማ የህይወት ተሞክሮዎችን እንደሚያካፍሉት በሚገባ ያውቃል። አዎ! ጀግናዬ..! ብልጥ ሁን! የትም ብትሔድ፣ ምንም ብትሰራ፣ እንዴትም ብትሰራ ካንተ የሚያንስ እንዲሁም ካንተ የሚበልጥ ሰው መኖሩን እወቅ። በምትበልጠው ፊት ደረትህን አትንፋ፣ እራስህና የተሻልክና ምርጡ ሰው አድርገህ አትቆልለው ይልቅ በምትችለው መንገድ የበታችህን እርዳው። ለጌታም ጌታ፣ ለመሪም መሪ እንዳለ አስታውስ። እንዲሁ ካንተ የሚሻል፣ በልምድም በስራ ጥራትም፣ በገቢም በኖሩ ደረጃም፣ በእውቀትም በማስተዋልም የሚበልጥህ ሰው ብታገኝ እራስህን የበታችነት አዘቅ ውስጥ መክተት አቁም። ይልቅ ለራስህ ብለህ ብልጥ ሁን፣ ወዳጅህ አድርገው፣ ዝቅ ብለህ ከርሱ ተማር፣ ቀርበህ አካሔዱን መርምር፣ የሚጠቅሙህን የህይወት መርሆች ኮርጅ። ምንም ሰጣገባ ውስጥ መግባት አያስፈልግም። ማንም ከርሱ የሚሻለውን ወንድሙን ቢያሰናክለው አንድም የራሱ አሰናካይ ከፊቱ እንዳለ እያሰበ በጥርጣሬ ይጓዛል ሌላም በስራ ተሽሎ የመገኘትን መርህ ያዛባል። አዎ! የተፅዕኖ ፈጣሪውን ስም ከማጥፋት እንዴት ተፀዕኖ መፍጠር እንደቻለ፣ እንዴት ለዛ ከፍታ እንደበቃ፣ እንዴት ያንን ስብዕና እንደገነባ መመርመር እጅግ ትልቅ ትርፍ አለው። ምቀኝነት ዞሮ ዞሮ መዘዙ ለራስ ነው፣ ለሰው ክፋትን መመኘት፣ በሰው ውድቀት እራስን ቀና ለማድረግ መሞከር፣ በበዛ ጥላቻ፣ በማይገባ ኢጎ (EGO) የተሻለ ሰው ባዩ ቁጥር ድክመቱን መዘርዘርና በቅናት መንጨርጨር ከትርፉ ጉዳቱ የሚያመዝን ከንቱ ተግባር ነው። ብልጦች ቢሆንላቸው ዙሪያቸውን የተሻሉና ከፍታ ላይ በሉ ሰዎች ቢሞሉት ይመርጣሉ። ከአሸናፊዎች ጎራ ከተቀላቀልክ አንተም አንድ ቀን አሸናፊ የማትሆንበት ምክንያት አይኖርም። የምር የህወትህ እድገትና መሻሻል የሚያሳስብህ ከሆነ ጤነኛ ካልሆነው ፉክክር እራስህን አውጣ፣ በምትኩ ከምትፎካከራቸው ሰዎች ልምድ ውሰድ፣ ተማር፣ የቅርብ ወዳጅም አድርጋቸው። ልክ እንደ ብልሆቹ በሰዓቱ ዝቅ ብለህ በጊዜህ ከፍታን ተጎናፀፍ። 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://youtube.com/@Weygud18 መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏 🎙ግሩፑን ለማግኘት               👇👇👇         @Mtshaf_bicha         @Mtshaf_bicha ❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ 👉አሰተያየት ካላችሁ 📩 @Eyos18     አድርሱን              📗📒📕📗📒📕                 Join&share                   @EyosC1        📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚 ┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
Mostrar todo...
👍 1
Sex💋💋or love❤️❤️
Mostrar todo...
Sex
Love
Sex💋💋or love❤️❤️
Mostrar todo...
Sex
Love