cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Belay_zeabissinya

በፈተና ብዛት ተስፋን እንደመዛቅ፣ በየለም ዓለም ላይ ኑሮን ማቆላመጥ ይህ ነው ሰው ማለት እየተፈተኑ በድሎት መራመድ ..... +251941537799 ሃሳብና አስተያየት ካለ በዚህ ይጠቀሙ:- @belay25

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
303
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
-530 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

መጣጣር ከንቱ ነው ሁልጊዜ ለሥጋ ጾምን ካላወቅን አትገኝም ጸጋ ካለመጾም ሊያገኝ መንፈስ ቅዱስን ጸጋ ብሎ ጠራው አንድ ሰው ልጁን ከበገና ዝማሬ ዓለም ማረፊያናት መኖሪያ ገነት ከሚለው የተወሰደ
Mostrar todo...
"መወለድዕ ይታወቅ ዘንድ የሞት ቀንዕ እስኪደርስ ለውስጥዕ ስላም የሚሰጥኽንና ለሰዎችም የሚጠቅም ነገር ብቻ አድርግ" ምድርን አዕዱ ብሎ ከባረካት አዳም ጀምሮ ይቺ ምድር እጅግ የብዙ ብዙ ሰዎችን አፍርታለች። ምንም እንኳን ምድር እስከ ጠረፏ ሰዎችን ብታመርትም በምድር ላይ ካሉ ሰዎች ግን እጅግ የብዙ ብዙ የሚባሉት ሳናውቃቸው መወለዳቸውንም ሳንረዳ ያለፉ ቁጥራቸው የትየ ለሌ ነው። ምድርን ሳይቀላቀሉ ደግሞ በሰዎች መሻት ብቻ የተጨናገፉ ቤቱ ይቁጠረው ነገር ግን የታወቁትን እኛም እንትና እኮ ለእኔ መንገድ ጠራጊ ነው፣ እንደ እንትና መሆን እሻለው ብለን የምንመኛቸው ሰዎች እንደተወለዱት ከተወለድን፣ ሁሉን እናደርግ ዘንድ የእኛ ፍቃድ ብቻ የሚጠይቅ ከሆነ ስለምን ተወልደን ጭንጋፎች ሆንን? ስለምንስ ለሰዎች መሰላል መሆን ተሳነን፣ ወደዚች ምድር ስንቀላቀል አንድ መክሊት እንዳለን ተረድተን ስላን የእራሳችንን የልብ ትርታ ብቻ እንዳናጤን ጠላት ይበዛብንም ዘንድ ስለምን ፈቀድን? ከእራሳችንስ አልፈን ስለ ለሰዎች ከፍ ማለት የማንሰራስ ስለምን ይሆን? ለዚህም እኮ ነው ሰው ክቡር ሆኖ ሳለ አላወቀም ያለው ደራሲው። ሰው ክቡር መሆኑን ሲያውቅ ሰው የሚያሰኘውን ሥራ ይሰራል ነገር ግን ክቡር መሆኑን ካላወቀ የስጋ ፍቃዱን እየፈጸመ ይሞታል። ምናልባት ምሳሌ የምናደርጋቸው ሰዎች ሰው ሆነው ይሆን?  እጅግ በጣም ደግሞ የሚያስገርመው እንደሚሞት እያወቀ ሙት የሆነ ሥራ መስራቱ ነው። ተወዳጆች አእምሮ ከተሰጠን  መልካም ፍሬን እናፈራ ዘንድ ግድ አለብን። ሁላችንም ለእኛ ብለን የምንሰራ ከሆነ እንዴት ባለእንጀራችንን እንጎዳለን ይህን በማድረጋችን በእኛስ ላይ አበሳ እያበዛን እንዴት አይመስለን? ብዙ ጊዜ እጆቻችንን ከመቀሰራችን በፊት ነገሮችን ከእራሳችን ብንጀምር ብዙ ነገሮች ቀላል ይሆኑ ነበር። እስኪ ማነው ለያዘው ነገር ታማኝ የሆነ? ማነው የሚሻውን እስኪያገኝ ድረስ የያዘውነ አክብሮ የያዘ? ማነው ታማኝ አገልጋይ የሆነ? ማነው ያለ መማለጃ ሁሉን ለህሊናው የሰራ? እረ ማነው አቋራጭ መንገድን ያልሻተ? ማነው የወንድሙን እንጀራ ያልተመኘ? ማነው በክፉዎች መንገድ ያሌደ? ማነው በውሸታሞች ወንበር ያልተቀመጠ? ማነው ከአምላኩ ፍቃድ ፈቀቅ ያላለ? በእውነት መንገድ ለሚሄዱ ቀናውንም መንገድ ላልሳቱ በምድር መልካምነታቸው በሕይወት ባይገለጥ እንኳን ከሞት በኋላ ከፍ ከፍ ይላሉ። ታዲያ ከተወለድን ሰውም ከተባልን ለማይጠፋው መልካምነት ስለምን አንባክንም በዛ ውስጥ እውነተኛ ሰላም አለና።  መልካም ቅዳሜ ✍በላይ ጌትነት 04/05/2016 ገጹ ለብዙዎች ይደርስ ዘንድ ለወዳጅዎት ያጋሩ https://t.me/autismfact
Mostrar todo...
Autism Spectrum Disorder

ይህ ገጽ በልዩ ፍላጎት ዙሪያ ለሰዎች ያስተምራሉ፣ትምህርትም ይሆናሉ የምላችውን ሃሳቦች የማሰፍርበት የሥራ ማስታወቂያዎችም የምለቅበት፣የዕለት የሥራ ውሎዬን የምዘግብበት ነው በላይ ጌትነት 0941537799

"ተወልደ ኢየሱስ በቤተልሔም ዘይሁዳ...ዮም ፍስሃ ኮነ--" ዛሬ የአዳር መርዓ ግብር በፈርንሳይ ለጋሲዎን  መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስትያን ተሰይሚያለው ሁሉም ምዕመን የጌታ ፍቅር ገዶት የተሰባሰበ ነው። ሊቃውንት አባቶች በቤተመቅደሱ የዕለቱን ስብዓት እያደረሱ ነው በዚች ቅጽበት "በጎል ሰከበ በአጥርት ተጠብለለ--" የሚለውን ወረብ ሁሉም በአሴት ያደረሰበት ሰዓት ነው። ጌታ በጨርቅ ተጠቀለለ፣በበረትም ተኛ፣ የሁሉ ባለቤት የሆነ ጌታ በእንሰሶች ማዕል ውልደቱን አደረገ ምን ዓይነት ትዕትና፣ምን ዓይነት ፍቅር ነው። ይህ ሁሉ በእርሱ የሆነለት ከሁሉ ያነሰ ሆነ በበደል ተገፍቶ ያነሰው አዳምን ያነሳ ዘንድ እርሱ ከሁሉ ያነሰ ሆነ በበረትም ተኛ በጨርቅም ተጠቀለለ ብለን ከመጨረሳችን ከቤተመቅደስ ወጣው በግቢው ውስጥ ብዙ ነገር ይታያል የሰንበት ተማሪዎች ብራብ አብልታቹኽኛል? ብጠማ አጠጥታችሁኛል? የሚለውን የጌታ ቃል ይፈጽሙ ዘንድ በሥራ ተወጥረዋል። ከፊሉ ሽንኩርት በመላጥ ተወጥሯል፣ ከፊሉ ውሃ ይቀዳል፣ ከፊሉ እንጀራ ወደ አዳራሹ ያግዛል ወጣቶች የሚያርዱትን በሬ የቀና ይሆን ዘንድ ቢላዋ ይሞርዳሉ፣ ግቢው በልዩ-ልዩ-ሥራ በያዙ ምዕመናን ተወጥሯል። ይህ ሁሉ ሰው ማንም አልጠራውም የጌታ ፍቅር ገዶት ከቤቱ ተሰበሰበ እንጂ እኔም በትዕይንቱ እየተደመምኩኝ ሰንበት ተማሪዎችን አልፌ ወደ ሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ አመራው አዳራሹ በእንጀራ ተሞልቷል፣ ቆይ ይህን ሁሉ ማን ሊበላው ነው? እጅግ የብዙ ብዙ እንጀራዎች ተሰድረው ይበሉ ዘንድ ንጋቱን የሚጠባበቁ ናቸው። ክርስቶስ በእራሱ የመሰላቸው  ምዕመኑ የመወለዱን ዜና ሲሰሙ አሴት እያደረጉ ለስጋቸው ደግሞ እንዳይጨነቁ ሰንበት ትምህርት ቤቱ ወገቡን ታጥቆ የሰበሰበው እንጀራ ነው። ይህን ጹዕፍ በማሰፍርበት ሰዓት እንኳን የእንጀራው ሽታ ወደ አፍንጫዩ እየመጣ ማወዱን አላቆመም፣(ልዩ ልዩ ማዕዛ እየመጣ ሲያውድ እራሱ ያለው ድስታ) ድንቹ፣ሽንኩርቱ፣ካሮቱ ተበልቶ! እሳት መግቢያውን እየጠበቀ ነው። ይህ ሁሉ ስለ ጌታ ልደት የሚሆነ ነው። በዚህም ልቤ አሴት አደረገ በዚህም ሥፍራ በመገኘቴ ደስታዩ ወደር የለውም። በዚህ ክርስቶስ አለ ከድንግል የተወለደው ከዚህ አለ። እርስ በእርሳችን አልተጠራራንም፣ ክርስቶስ ግን በቅጥሩ ሰበሰበን፣ ማንም ብትቀሩ! ብሎ ማስፈራሪያ ያደረገ የለም የክርስቶስ ፍቅር ግን ከደጁ ጣለን፣ ሐዋሪያው ቅዱስ ጴጥሮስ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው እንዳለ እውነትም በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው። ከዓለሙ ጫጫታ ወጥተን ነፍሳችን አሴት የሚያደርግበትን የሚሰጠን ከዚህ አለና በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው። በመወለዱ ለምተምኑ እንኳን ለዓለም መድኃኒት ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሰን አደረሳችሁ። በሉ ወደ ቤተመቅደስ ልግባ አንፈራጹ ሰባ ሰገል የሚለው ወረብ እየቀረበ ነው። ✍በላይ ጌትነት 27/04/2016 ፈረንሳይ ለጋሲዎን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስትያን ግቢ ውስጥ የተፃፈ
Mostrar todo...
"በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው" ዛሬ የአዳር መርዓ ግብር በፈርንሳይ ለጋሲዎን  መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስትያን ተሰይሚያለው ሁሉም ምዕመን የጌታ ፍቅር ገዶት የተሰባሰበ ነው። ሊቃውንት አባቶች በቤተመቅደሱ የዕለቱን ስብዓት እያደረሱ ነው በዚች ቅጽበት "በጎል ሰከበ በአጥርት ተጠብለለ--" የሚለውን ወረብ ሁሉም በአሴት ያደረሰበት ሰዓት ነው። ጌታ በጨርቅ ተጠቀለለ፣በበረትም ተኛ፣ የሁሉ ባለቤት የሆነ ጌታ በእንሰሶች ማዕል ውልደቱን አደረገ ምን ዓይነት ትዕትና፣ምን ዓይነት ፍቅር ነው። ይህ ሁሉ በእርሱ የሆነለት ከሁሉ ያነሰ ሆነ በበደል ተገፍቶ ያነሰው አዳምን ያነሳ ዘንድ እርሱ ከሁሉ ያነሰ ሆነ በበረትም ተኛ በጨርቅም ተጠቀለለ ብለን ከመጨረሳችን ከቤተመቅደስ ወጣው በግቢው ውስጥ ብዙ ነገር ይታያል የሰንበት ተማሪዎች ብራብ አብልታቹኽኛል? ብጠማ አጠጥታችሁኛል? የሚለውን የጌታ ቃል ይፈጽሙ ዘንድ በሥራ ተወጥረዋል። ከፊሉ ሽንኩርት በመላጥ ተወጥሯል፣ ከፊሉ ውሃ ይቀዳል፣ ከፊሉ እንጀራ ወደ አዳራሹ ያግዛል ወጣቶች የሚያርዱትን በሬ የቀና ይሆን ዘንድ ቢላዋ ይሞርዳሉ፣ ግቢው በልዩ-ልዩ-ሥራ በያዙ ምዕመናን ተወጥሯል። ይህ ሁሉ ሰው ማንም አልጠራውም የጌታ ፍቅር ገዶት ከቤቱ ተሰበሰበ እንጂ እኔም በትዕይንቱ እየተደመምኩኝ ሰንበት ተማሪዎችን አልፌ ወደ ሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ አመራው አዳራሹ በእንጀራ ተሞልቷል፣ ቆይ ይህን ሁሉ ማን ሊበላው ነው? እጅግ የብዙ ብዙ እንጀራዎች ተሰድረው ይበሉ ዘንድ ንጋቱን የሚጠባበቁ ናቸው። ክርስቶስ በእራሱ የመሰላቸው  ምዕመኑ የመወለዱን ዜና ሲሰሙ አሴት እያደረጉ ለስጋቸው ደግሞ እንዳይጨነቁ ሰንበት ትምህርት ቤቱ ወገቡን ታጥቆ የሰበሰበው እንጀራ ነው። ይህን ጹዕፍ በማሰፍርበት ሰዓት እንኳን የእንጀራው ሽታ ወደ አፍንጫዩ እየመጣ ማወዱን አላቆመም፣(ልዩ ልዩ ማዕዛ እየመጣ ሲያውድ እራሱ ያለው ድስታ) ድንቹ፣ሽንኩርቱ፣ካሮቱ ተበልቶ! እሳት መግቢያውን እየጠበቀ ነው። ይህ ሁሉ ስለ ጌታ ልደት የሚሆነ ነው። በዚህም ልቤ አሴት አደረገ በዚህም ሥፍራ በመገኘቴ ደስታዩ ወደር የለውም። በዚህ ክርስቶስ አለ ከድንግል የተወለደው ከዚህ አለ። እርስ በእርሳችን አልተጠራራንም፣ ክርስቶስ ግን በቅጥሩ ሰበሰበን፣ ማንም ብትቀሩ! ብሎ ማስፈራሪያ ያደረገ የለም የክርስቶስ ፍቅር ግን ከደጁ ጣለን፣ ሐዋሪያው ቅዱስ ጴጥሮስ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው እንዳለ እውነትም በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው። ከዓለሙ ጫጫታ ወጥተን ነፍሳችን አሴት የሚያደርግበትን የሚሰጠን ከዚህ አለና በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው። በመወለዱ ለምተምኑ እንኳን ለዓለም መድኃኒት ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሰን አደረሳችሁ። በሉ ወደ ቤተመቅደስ ልግባ አንፈራጹ ሰባ ሰገል የሚለው ወረብ እየቀረበ ነው። ✍በላይ ጌትነት 27/04/2016 ፈረንሳይ ለጋሲዎን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስትያን ግቢ ውስጥ የተፃፈ
Mostrar todo...
Mostrar todo...
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን Ethiopian Orthodox Tewahdo Church

ሠላም ለእናንተ ይሁን እህት ወንድሞቼ ገድለ ክርስትና የሚለውን ጥናታዊ ፅሑፍ ለማጠቃለል ይረዳኝ ዘንድ እነዚህን ጥያቄዎች በመመለስ ተጋድሎ ላይ እንዲሳተፉ በአክብሮት እጠይቃለው።
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
አንዳንድ ሰዎች ሥማቸውን ከመቃብር በላይ ጸፈው ከማለፍ ባለፈ ትውልድ ተሻጋሪ ስራዎችን ሰርተው ያልፋሉ ከነዚህ ሰዎች መካከልም አዲስ ዓለማየውሁ አንዱ ናቸው። ብዙዎች በጽሕፈት ሥራቸው ቢያውቋቸውም በመልካምነታቸው የሚዘክራቸውም አለ እናንተም ይህን ስታውቁ እነዚህ ሰው እውነትም ሰው ነበሩ ትላላችሁ። ይህ ከላይ የጠቀስኩላችሁ ተቋም የነዚህ ታላቅ ሰው ቤት ነበር ታዲያ ባለቤታቸው ከረፉ በኋላ ልባቸው በመነካቱ ይህ ስፍራ ለወደቁ ልጆች የሚያድጉበት፣እንክብካቤም የሚያገኙበት ይሁን ብለው በባለቤታቸው ስም ክበበ ፀሐይ ተብሎ ማስታወሻም እንዲሆን በማድረጋቸው ዛሬ ልጅ የሌላቸው ልጃቸውን አቅፈው የሚወጡበት፣ደስታንም የሚዝቁበት፣የሚጣሉ ልጆችም እፎይታን የሚያገኙበት ሥፍራ ሆኗል። በፍቅር እስከ መቃብር የፍቅርን አያልነት እንዳሰፈሩት እሳቸውም ባለቤታቸው ወ/ሮ ክበበ ፀሐይ ካረፉ በኋላ ትዳር በቃኝ ብለው በቃላቸው ታምነው ኑረው ያረፉ ታላቅ ሰው ናቸው። መቼም ይህን ስነግራችሁ ደስ እያለኝ ነው በአዲስ ዓለማየሁ ዘመን የነበሩ ብዙ ሰዎች ነበሩ እንደ እሳቸው የሚታወስ ነገር ስለሌላቸው አናውቃቸውም ታዲያ በዘመናችንም ብዙ ሰዎች አለን ምናልባት ከዘመናት በኋላ እስኪ እራሳችንን ሰዎች በምን ያስታውሱናል?ያን ጊዜ ምን ማድረግ እንዳለብን እንረዳ ይሆናል። ይህ ሲባል ግን እውቅና ለማግኘት እንዳልሆነ ልብ ሊባል ይገባል እውነትን ሥራዎችን ስንከውን የመጀሪያው ተደሳቾች እራሳችን ነን እናም ሁላችንም በያዝነው ሥራ ሊሆን ይችላል ትዳር ተማሪነትም ሊሆን ይችላል ብቻ ግን በያዝነው ማንኛውም የኑሮ መሰረት ነው ባልነው ነገር ታማኝ የምንሆን ከሆነ እውነት ከፍ ታደርገናለች። በላይ ጌትነት 12/04/2016 ዓ.ም አገልግሎትና መረጃ ለማግኘት 0941537799 (በላይ ጌትነት) 0954842701 (ትዛዙ አበበ)
Mostrar todo...