cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ትኩስ መረጃ Tekus Mereja

Breaking News Join Us

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
500
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

እንኳን ለሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ለፊቼ ጫምባላላ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
Mostrar todo...
የጎንደሩን ግድያ የፈፀመዉ ማን እንደሆነ እየተጣራ ነዉ! የአማራ ክልል መንግስት የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ዛሬ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት የፀጥታ ኃይሉ አጥፊ ግለሰቦችንና ቡድኖችን እያደነ እንደሆነም ኃላፊ አመልክተዋል፡፡ ማክሰኞ ዕለት በጎንደር ከተማ በአንድ ታዋቂ አባት መቃብር ላይ የተፈጠረውን የህይወት ማጥፋት፣ የአካል ጉዳትና የንብረት መውደምን ተከትሎ የነበረው አለመረጋጋት እየተሻሻለ መምጣቱን የአማራ ክልል መንግስት አስታውቋል። በጥቃቱ ህይወታቸው ያለፉ ወገኖች የቀብር ሥነ-ስርዓትም እየተከናወነ እንደሆነ ተመልክቷል።አንድ የዓይን እማኝ ዛሬ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ቢከፈቱም አንዳንድ የንግድ ተቋማት እንደተዘጉ ናቸው ብለዋል፡፡የአማራ ክልል የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰሞኑን በጎንደር የተካሄደውን ግድያ አውግዟል፡፡ ማክሰኞ ዕለት በጎንደር ከተማ የአንድ ታላቅ አባት የቀብር ሥነ-ስርዓትን ተከትሎ በንፁሐን ላይ የሞት የአካል ጉዳትና የንብረት ውድመት ተፈፅሟል፣ ያን ተከትሎ በከተማዋ አለመረጋጋት ሰፍኖ መቆየቱን የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ የአማራ ክልል መንግስት የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ዛሬ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት ከሁለቱም የሐይማኖት አባቶች ጋር ውይይቶች ተካሂደው የቀብር ሥነ-ስርዓት እየተካሄደ ነው፡፡የፀጥታ ኃይሉ አጥፊ ግለሰቦችንና ቡድኖችን እያደነ እንደሆነም ኃላፊ አመልክተዋል፡፡ የጉዳቱ መጠን ገና እየተጠና መሆኑን የተናገሩት አቶ ደሳለኝ ጉዳቱ ከሁለቱም ወገን ነው ብለዋል፡፡መንግስቱ የተባሉ የዓይን እማኝ በስልክ እንዳብራሩት ዛሬ በከተማዋ የተረጋጋ ሁኔታ ቢኖርም ሥራ ያልጀመሩ ሱቆችን ተመልክተዋል፡፡መሐመድ የተባሉ ሌላ የዓይን እማኝ “ቀብር አናስቀብርም” የሚል ጥያቄ ያነሱ ወገኖች እንደነበሩ ጠቁመው መጨረሻ ግን በተደረሰ ውይይት ቀብር ተፈፅሟል ነው ያሉት፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በጎንደር ከተማ የተፈፀመው ድርጊት እንደሚያወግዘው የአማራ ክልል የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ አስታወቋል፡፡ጉባዔው ትናንት ለአገር ውስጥ ብዙኃን መገናኛ ብቻ በሰጠው መግለጫ «በከተማዋ የተፈፀመው ድርጊት የማንንም ሐይማኖት አይወክልም ፣ የሐይማኖቶችን አስተምሮምሆነ እሴት ያልተከተለ ነው» ብሏል፡፡መንግስት አጥፊዎችን ተከታትሎ በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲያቀርብ፣ ህዝቡም እንዲተባበር ነው የጉባዔው አባላት ያመለከቱት፡፡ Via DW @YeneTube @FikerAssefa
Mostrar todo...
በሃይማኖት ሽፋን ግጭት በመቀስቀስ ጸረ-ኢትዮጵያ የሆኑ ሃይሎችን ፍላጎት ለማሳካት በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን የፌደራል የደህንነትና የጸጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ! ሚያዝያ 18 ቀን 2014 ዓ.ም በአማራ ክልል ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጎንደር ከተማ ከቀብር ስፍራ ጋር በተያያዘ በክርስትናና በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የተቀሰቀሰውን ግጭት መነሻ በማድረግ በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎችም በሃይማኖት ሽፋን ሁከትና ብጥብጥ በመፍጠር ጸረ-ኢትዮጵያ የሆኑ ሃይሎችን ፍላጎት ለማሳካት በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን የፌደራል የደህንነትና የጸጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቋል፡፡ የጋራ ግብረ ኃይሉ ዛሬ ለመገናኛ ብዙኃን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ ጸረ ኢትዮጵያ አቋም የሚያራምዱ የተለያዩ የውስጥና የውጭ ኃይሎች ብሔርን መሰረት ያደረገ የጥላቻ አጀንዳ በማሰራጨት ሃገሪቱን ወደ ቀውስ ለማስገባት ጥረት ሲያደርጉ ነበር፡፡ ህብረተሰቡ ለአመታት በገነባው ጠንካራ የሆነ የጋራ እሴት ይህ ሙከራ የከሸፈባቸው ኃይሎች፣ቀሪውን የሃይማኖት ካርድ በመምዘዝ በተለያዩ እምነት ተከታዮች ዘንድ መጠራጠርና ጥላቻ እንዲፈጠር ብሎም ወደ ግጭት እንዲያመራ በተለያዩ መንገዶች ሲቀሰቅሱ ቆይተዋል፡፡ በጎንደር የተከሰተው ግጭት በተለያዩ ዕምነቶች መካከል ግጭት በመቀስቀስ ወደ ሃገራዊ ቀውስ እንዲያመራ የሚደረገው ሴራ አካል መሆኑን ያመለከተው መግለጫው፤ በዚህ ድርጊት በተሳተፉ አካላት ላይ ተገቢ እርምጃ መወሰደ መጀመሩን ጠቁሟል፡፡ በዚህ መሰረት በጎንደር በተከሰተው ግጭት የተሳተፉና ሁከቱን ለማባባስ የተንቀሳቀሱ 280 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን አመልክቷል፡፡ እንደ መግለጫው፤ በጎንደር የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ በሌሎች አካባቢዎችም በተለያዩ እምነት ተከታዮች መካከል ሁከትና ብጥብጥ እንዲፈጠር የሚጋብዙ ቅስቀሳዎች እንዲሁም ሃሰተኛ መረጃዎችም በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች በስፋት እየተሰራጩ ይገኛሉ፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎችም የእምነት ተቋማትና ግለሰቦች ላይ ጥቃት በመፈጸም ግጭቱ ሃገራዊ ቅርጽ እንዲኖረው ሙከራ እየተደረገ ነው፡፡ የፌደራል የደህንትና የጸጥታ መዋቅር በድርጊቱ በሚሳተፉት ላይ ብቻ ሳይሆን ከኋላ በመሆን በሚዘውሩት ላይ በቂ መረጃና ማስረጃ ያለው በመሆኑ ተከታታይ እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ ያስታወቀው መግለጫው፤ ችግሩ ወደ ሌሎች አካባቢዎችም እንዲስፋፋ በየትኛውም የመገናኛ ዘዴ የሚቀሰቅሱ፤ በተለይም ደግሞ የማህበራዊ ትስስር ገፆችን በመጠቀም ሃሰተኛና የጥላቻ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት በህግ የሚጠየቁበት አግባብ መኖሩን የጠቆመው መግለጫው፤ በዚህ ህግወጥ ድርጊት የሚሳተፉ ባስቸኳይ ከድርጊታቸው እንዲታቀቡም በጥብቅ አሳስቧል፡፡ ኢትዮጵያውያን ለዓመታት የገነቡት በአብሮነትና በመከባበር ላይ የተመሰረተ ግንኙነት እኩይ ዓላማ ባነገቡ የውስጥና የውጭ ፀረ ሰላም ሃይሎች እኩይ ሴራ ለማስፈጸም የሚንቀሳቀሱ አካላት በሚፈጥሩት የግጭት አጀንዳ አይሸረሸርም ያለው መግለጫው፤ ህብረተሰቡ ለዘመናት ባዳበራቸው መልካም እሴቶች እንደዚህ አይነት የፈተና ወቅቶችን በውይይትና በሰከነ መንፈስ በመፍታት እንደሚያስመሰክር የጋራ ግብረ ኃይሉ እምነት መሆኑንም ጠቁሟል፡፡ ዛሬም ኢትዮጵያን ሌላ የግጭት አጀንዳ በመስጠት ለማተራመስ ሙከራ ቢደረግም በደኀንነትና በጸጥታ መዋቅሩ ከፍተኛ ጥረት በቁጥጥር ስር ውሏል ያለው የፌደራል የደህንነትና የጸጥታ የጋራ ግብረ ኃይል፤ ህብረተሰቡ ከመንግስት ጎን በመሆን ችግሩ እንዳይስፋፋ ያደረገው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አመልክቷል፡፡ @YeneTube @FikerAssefa
Mostrar todo...
በነገው እለት በአዲስ አበባ ለሚካሄደው ታላቁ የኢፍጣር ፕሮግራም ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ሚያዚያ 21 ቀን 2014 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከሚካሄደው ታላቁ የኢፍጣር ፕሮግራም ጋር ተያይዞ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከቅዱስ ኡራኤል አካባቢ ጀምሮ እስከ መስቀል አደባባይ እና በዙሪያዋ የሚገኙ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚሆኑ የፀጥታና የደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል። በዚህም መሰረት፦ - ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሀያ ሁለት ወይም ዘሪሁን ህንፃ አካባቢ ዝግ ይደረጋል፣ - ከወሎ ሰፈር ወደ መስቀል አደባባይ ወሎ ሰፈር ኦሎምፒያ፤ - ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ አሽከርካሪዎች አጎና ሲኒማ፤ - ከጦር ኃይሎች በሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ እና ከሜኪሲኮ ወደ ብሔራዊ ቴአትር ለሚጓዙ ሜክሲኮ አደባባይ፤ - ከጌጃ ሰፈርና ከጎማ ቁጠባ በሰንጋ ተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚጓዙ የቀድሞው ደሳለኝ ሆቴል መስቀለኛ ላይ፤ - ከጎማ ቁጠባ ወደ ብሔራዊ ለሚጓዙ ጎማ ቁጠባ ላይ እና ከሜክሲኮ ወደ ፖስታ ቤት ለሚሄዱ ሚትሮሎጂ አካባቢ እንዲሁም ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ኢሚግሬሽን ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በር አካባቢ፤ - ከተክለኃይማኖት በጎላ ሚካኤል ለሚመጡ ጎላ ሚካኤል መስቀለኛ ላይ እና ከተክለኃይማኖት ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ ለሚመጡ ተክለኃይማኖት ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ከተክለ ኃይማኖት በሶማሌ ተራ ወደ ባንኮ ዲሮማ ለሚመጡ አሽከርካሪዎች ሸዋ ሱፐር ማርኬት ጋር ዝግ የሚደረግ ይሆናል። - ከቀድሞ አትክልት ተራ አካባቢ በአሮጌው ፖስታ ቤት ወደ ቸርችል ጎዳና የሚወስደው መንገድ አሮጌው ፖስታ ቤት፤ - ከደጎል አደባባይ ወደ እሪ በከንቱ ደጎል አደባባይ ላይ እና ከአራት ኪሎ በፓርላማ ወደ ውጭ ጉዳይ የሚወስደው መንገድ ሸራተን ሆቴል መውረጃ ላይ፤ - ከአራት ኪሎ በብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ ለሚጓዙ አሽከርካሪዎች ብሔራዊ ቤተ መንግስት መስቀለኛ ላይ የሚዘጋ ሲሆን ከካዛንቺስ ሼል ወደ ፍል ውሀና ወደ ባምቢስ የሚወስዱት መንገዶች ካዛንስ ሼል ላይ ከቀኑ7፡00 ሰዓት ጀምሮ የኢፍጠር ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅበት ሰዓት ድረስ ዝግ የሚደረጉ ይሆናል። በተጨማሪም በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅመ ሰዓታት ተሽከርካሪዎችን አቁሞ መሄድ የተከለከለ ሲሆን ህብረተሰቡ ፕሮግራሙ በሠላም ተጀምሮ በሠላም እንዲጠናቀቅና ማንኛውም ዓይነት አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ በፖሊስ የመረጃ ስልኮች 0111 11 01 11 እና ነፃ የስልክ መስመር 991 ላይ በመደወልና መረጃ በመስጠት የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ የፀጥታና የደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል። @YeneTube @FikerAssefa
Mostrar todo...
በአዲስ አበባ ከተማ በኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ የተነሳ በአራት ክፍለ ከተሞች የውሃ አቅርቦት ተቋርጧል! በአዲስ አበባ ከተማ በኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ የተነሳ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ 12 ወረዳዎች ፣በቂርቆስ ክፍለ ከተማ 10 ወረዳዎች ፣በቦሌ ክፍለ ከተማ 3 ወረዳዎች እና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ 5 ወረዳዎች የሚገኙ ደንበኞች ከእሁድ እለት ጀምሮ ውሃ በበቂ ሁኔታ እያገኙ አለመሆኑን የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰርካለም ጌታቸው በተለይ ለብስራ ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡ በኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ የተነሳ ከዚህ ቀደም ውሃ በፈረቃ ያገኙ ለነበሩ አካባቢዎች አገልግሎቱን መስጠት መቸገራቸውን ያነሱት ዳይሬክተሯ በተለይ ውሃ በሳምንት አንዴ ያገኙ የነበሩ አካባቢዎች ላይ ችግሩ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ገልፀዋል። ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ችግሩን ለመፍታት ከአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በመናበብ በመስራት ላይ መሆናቸውን የሚናገሩት ዳይሬክተሯ በተለይ ከእሁድ ጀምሮ እስከ ድርብ ድረስ ባሉት ቀናት በርካታ ምሶሶዎች መውደቃቸውን ተከትሎ እና መሬት ውስጥ የነበረ ኬብል በመፈንዳቱ ዳግም የመጠገን ስራዎች ላይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ አሁን ላይ የፈረቃ ሂደቱ በመዛባቱ ባለስልጣኑ ባሉት ቦቲ ተሸከርካሪዎች ውሃ ለማዳረስ እየሰራ ሲሆን ችግሩን በአፋጣኝ ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል። የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ የተፈጠረው በቴክኒክ ችግር ምክንያት መሆኑን ለብስራት ሬዲዮ ያስረዱት በአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ በቀለ ክፍሌ ሲሆኑ ችግሩን ለመቅረፍ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ [ዳጉ ጆርናል] @YeneTube @FikerAssefa
Mostrar todo...
የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ስድስት ቅርንጫፎች ሠራተኞች በወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ! በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ስድስት የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ቅርንጫፍ ሠራተኞች በወንጀል ተጠርጥረው በክልሉ የጸጥታ ኃይሎች ዛሬ ሚያዚያ 20 ቀን 2014 ዓም በቁጥጥር ስር ውለው መታሰራቸው ታወቀ። ቅርንጫፍ መስሪያቤቶቹ በአዳማ፣ነቀምት፣ ጅማ፣ጊምቢ፣በደሌ፣መቱ ሲሆኑ ሁሉም መታሸጋቸው ታውቋል።የቅርንጫፍ ሠራተኞቹ በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና መታሰራቸውን የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ለሪፖርተር ያረጋገጠ ቢሆንም የታሰሩትን ሠራተኞች ብዛትና የታሰሩበትን ቦታ ከመግለጽ ተቆጥቧል። Via Reporter @YeneTube @FikerAssefa
Mostrar todo...
ከትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች ለተፈናቀሉ ተማሪዎች ዲግሪ እንደማይሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ! ከትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ተፈናቅለው በአደራ በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተምረው ለተመረቁ ተማሪዎች፣ መደበኛ ዲግሪ ሚኒስቴሩ ለመስጠት እንደሚቸገር ተገለጸ፡፡ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በትምህርት ሚኒስቴር ዋስትና ገብተው የተመረቁ ከትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች የተፈናቀሉ ከ4,000 በላይ ተማሪዎች መደበኛ ዲግሪ ስለተከለከልን ሥራ ለመቀጠርና ለመወዳዳር አልቻልንም ሲሉ ለሪፖርተር ተደጋጋሚ ቅሬታዎችን ሲያሰሙ ቆይተዋል፡፡ የእነዚሁ የተማሪዎች ቅሬታ የቀረበላቸው ትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ (ፕሮፌሰር) እንደተናገሩት፣ ‹‹የተማሪዎቹ ሙሉ መረጃ ሳይገኝ መደበኛ ዲግሪ ለመስጠት እንቸገራለን፡፡ ጦርነቱ ሲቆምና ሰላምና መረጋጋት በሰሜን ኢትዮጵያ በአስተማማኝ ሁኔታ ሲሰፍን ከመጡባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርት ያቆሙበት መረጃ ተሟልቶ ሲቀርብ ዲግሪው ይሰጣቸዋል፡፡ እስከዚያው ግን በተሰጣቸው ውጤታቸውን በሚገልጽ ሰርተፊኬት ሥራ መፈለግ ይችላሉ፤›› ብለዋል፡፡ ሚኒስትሩ ይህን ቢሉም ከትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች በጦርነት ሳቢያ ተፈናቅለው ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ለመመረቅ የተገደዱ ተማሪዎች ግን፣ ትምህርት ሚኒስቴር በአንድ ሴሚስተር የውጤት መግለጫ ወረቀት (በግሬድ ሪፖርት) አሰናብቶናል ሲሉ ቅሬታ ያሰማሉ፡፡ ይህ ወረቀት ደግሞ በሥራ ዓለም ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቀጠር እንደማያስችላቸው በመጥቀስ፣ ትምህርት ሚኒስቴር ዘላቂ መፍትሔ እንዲፈልግላቸው እየጠየቁ ነው፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ግን አሁን ካደረኩት የተለየ አማራጭ የለኝም የሚል ምላሽ ነው የሰጠው፡፡ ተጨማሪ ለማንበብ: http://bit.ly/36ZDgNi @YeneTube @FikerAssefa
Mostrar todo...
የአማራ ክልል መንግሥት ሽብር በሚፈጠሩ አካላት የማያዳግም እርምጃ እወስዳለው አለ! የአማራ ክልል መንግሥት በጎንደር ከተማ በተፈጠረው ግጭት ተገቢውን ክትትል አድርጎ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ።የአማራ ክልል ርዕሠ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) ፤ እንደ ሀገር ከገጠሙን ችግሮች ሙሉ በሙሉ ሳንላቀቅ ሃይማኖትን ምክንያት በማድረግ የእርስ በርስ ግጭት ለመፍጠር የሚታትሩ እኩይ አካላትን እንደማይታገሱ ተናግረዋል። ርዕሠ መሥተዳድሩ "ክልሉን የትርምስ ቀጣና ለማድረግ የሽብር ድርጊት በሚፈጠሩ አካላት ላይ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን" ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡ይህ ሙከራ ኢትዮጵያን ካለችበት ነባራዊ ሁኔታ ለባሰ ቀውስ የሚዳርግ በመሆኑ ድርጊቱ ሊወገዝ ይገባዋል ያሉት ርዕሠ መሥተዳድሩ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ወጣቶች ለሰላም ዘብ እንዲቆሙም አሳስበዋል። @YeneTube @FikerAssefa
Mostrar todo...
የወልዲያ ከተማ አስተዳዳር ‹‹ሰርጎ ገቦች››ን ለመለየት የነዋሪዎችን መታወቂያ ሊቀይር ነው! የወልዲያ ከተማ አስተዳደር በከተማው ውስጥ የሚገኙ ‹‹ሰርጎ ገቦችን›› ለመለየት እንዲቻል፣ የከተማዋ ነዋሪዎችን በሙሉ መታወቂያ ሊቀር እንደሆነ አስታወቀ፡፡በከተማው ውስጥ ካለው ሁኔታ አንፃር እየተለዩ የሚታሰሩ ግለሰቦች እንዳሉ የገለጸው የከተማ አስተዳደሩ፣ አዲስ መታወቂያ የሚወስዱ ሰዎች ያላቸውን መታወቂያ ከከተማዋ ወሳኝ ኩነት መረጃ ጋር እንደሚያመሳክር ገልጿል፡፡ ለወራት በሕወሓት ቁጥጥር ሥር ከቆየች በኋላ በታኅሳስ ወር ላይ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር በሆነችው ወልዲያ፣ ‹‹ሰርጎ ገቦች›› የቀድሞውን መታወቂያ መያዛቸውን ለሪፖርተር የተናገሩት የወልድያ ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ ዳዊት መሰለ (ዶ/ር)፣ በዚህም ምክንያት የከተማው አስተደዳር የከተማዋን ነዋሪዎች መታወቂያ ለመቀየር ውሳኔ ማስተላለፉን ገልጸዋል፡፡ እንደ ዳዊት (ዶ/ር) ገለጻ፣ ከዚህ ቀደም መታወቂያ ሲሰጥ የነበረው መረጃዎችን በመዝገብ ላይ በመጻፍ ብቻ የነበረ ሲሆን፣ ይህም በቀበሌዎች መካከል የሚጣራበት ሁኔታ እንዳይኖር በማድረጉ የተለያዩ ቀበሌዎች ላይ ከአንድ በላይ መታወቂያ ያላቸው ሰዎች አሉ፡፡ ‹‹ሰርጎ ገብ›› የተባሉትን ሰዎች ማንነት አብራርተው ባይገልጹም፣ የከተማዋ ነዋሪዎች መታወቂያ እንዲይዙ የሚያደርጉ የቀበሌ አመራሮች አሉ የሚል ጥርጣሬ እንዳለ አስረድተዋል፡፡ አሁን መታወቂያ የማደስ አገልግሎት እንዲቆም መደረጉን አክለዋል፡፡ Via Reporter @YeneTube @FikerAssefa
Mostrar todo...
የኩፍኝ፣ ፖሊዮና ቢጫ ወባ ወረርሽኝን ለመከላከል ያለመ የክትባት ሣምንት ሊካሄድ ነው! የኩፍኝ፣ ፖሊዮና ቢጫ ወባ ወረርሽኝን ለመከላከል ያለመ የክትባት ሣምንት ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ሊካሄድ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ድጉማ በሰጡት መግለጫ ÷ የአፍሪካ የክትባት ሣምንትን ምክንያት በማድረግ የሚከናወነው የክትባት ዘመቻው በተለይም በጸጥታ ችግር ምክንያት ክትባት ባልተሰጠባቸው ቦታዎች ይሰጣል ብለዋል፡፡ የክትባት ሣምንቱ ማህበረሰቡ በክትባት ጠቀሜታ ላይ ትክክለኛውን ግንዛቤ እንዲጨብጥ ለማድረግና የክትባት ተደራሽነትን ለማስፋት መሆኑንም አመላክተዋል፡፡ የክትባት ዘመቻው ዓላማ በወረርሽኝ ደረጃ ሊነሱ ይችላሉ ተብሎ የተሰጉትን ኩፍኝ፣ ፖሊዮ እና ቢጫ ወባን ለመከላከል መሆኑን የጠቆሙት ዶክተር ደረጄ፤ ይህም ተፈናቃይ ዜጎች ባሉባቸው አካባቢዎች በስፋት የሚሰጥ ይሆናል ብለዋል፡፡ ከወረርሽኝ መከላከል ባለፈ ለሕጻናት የአንጀት ተወሃሲያን መከላከያ፣ ቫይታሚን ኤ እና በምግብ እጥረት የተጎዱ ሕጻናትን በመለየት ሕክምና እንደሚሰጥ መናገራቸዉን የኢዜአ ዘገባ ያስረዳል። @YeneTube @FikerAssefa
Mostrar todo...