cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

በእንተ ቅዱሳን

ሁላችንም በዚህ መንፈሳዊ ቻናል ስለ አበው አባቶቻችን እንማማር ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር ሥም እጠይቃለሁ። ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት join ብለው አባል ይሁኑ።

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
219
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

✞✞✝ የሰኔ 23 ✝✞✞ ✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖✝ እንኳን አደረሳችሁ✝ ❖ ❖ ✝ሰኔ 23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት +"+ ✝ቅዱስ_ሰሎሞን ንጉሠ እሥራኤል✝ +"+ =>መፍቀሬ ጥበብ: ¤ጠቢበ ጠቢባን: ¤ንጉሠ እሥራኤል: ¤ነቢየ ጽድቅ: ¤መስተሣልም (ሰላማዊ) . . . እየተባለ የሚጠራው ቅዱስ ሰሎሞን የታላቁ ነቢይና ንጉሥ ልበ አምላክ ቅዱስ_ዳዊትና የቅድስት ቤርሳቤህ (ቤትስባ) ልጅ ነው:: ከ3ሺ ዓመታት በፊት የተወለደው ቅዱስ ሰሎሞን እስከ 12 ዓመቱ ድረስ በቤተ መንግሥት ከአባቱ ጋር አድጉዋል:: +ቅዱስ ዳዊት 70 ዘመን በሞላው ጊዜ የአካሉን መድከም አይቶ አዶንያስ በጉልበት እነግሣለሁ ቢልም አልተሳካለትም:: እግዚአብሔር ሰሎሞንን መርጧልና ገና በ12 ዓመቱ ነገሠ:: ልበ_አምላክ አባቱ ዳዊት ነፍሱ ከሥጋው ከመለየቷ በፊት መከረው:: "ልጄ ሆይ! ልብህን ስጠኝ:: ፈጣሪህንም አምልክ" አለው:: +ቅዱስ ሰሎሞን እንደ ነገሠ በገባዖን ለእግዚአብሔር መስዋዕትን አቀረበ:: ጌታም ተገልጾ "ምን ትፈልጋለህ?" አለው:: ሰሎሞንም ልክ እንደ አባቱ ማስተዋልን: ልቡናን ለመነ:: በዚህም ጌታ ደስ ስለተሰኘ "አልቦ እምቅድሜከ: ወአልቦ እምድኅሬከ - ከአንተም በፊት: ከአንተም በኋላ እንዳንተ ያለ ጠቢብና ባለጠጋ ሰው የለም: አይኖርም" ብሎት ተሠወረ:: ቅዱስ ሰሎሞን ለ40 ዓመታት በእሥራኤል ላይ ነገሠ:: +ግሩም በሆነ ፍትሑ: በልዩ ጥበቡ ዓለም ተገዛለት:: እግዚአብሔር የመረጣት የእኛዋ ንግስተ_ሳባ /አዜብ/ማክዳም ትፈትነው ዘንድ ሒዳ ምኒልክን (እብነ_መለክን) ጸነሰች:: በኋላም ታቦተ_ጽዮንና ሥርዓተ ኦሪት መጣልን:: ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን ድንግል_ማርያም ከእነሱ ዘር እንደምትወለድ ነግሮት ነበርና ያበጀሁ መስሎት ሴቶችን አብዝቶ ነበር:: +ነገር ግን:- ¤አንደኛ ሰው (ሥጋ ለባሽ) ነውና: ¤ሁለተኛ ደግሞ ከብዙ ሴቶች መካከል ከአንዷ እመ_ብርሃን ትገኛለች መስሎት ነበር:: ነገሩ መንገድ ስቶበት ከአሕዛብ (ከፈርዖን ልጅ) ጋር በመወዳጀቱ ለጣዖት አሰገደችው:: እግዚአብሔር እጅግ አዘነ:: +በራዕይ ተገልጦ "ስለ ወዳጄ ስለ ዳዊት ስል በአንተ ላይ ክፉን አላደርግም" አለው:: ታላቁ ነቢይ ሰሎሞን ይህንን ሲሰማ ወደ ልቡ ተመለሰ:: ማቅ ለብሶ: አመድ ነስንሶ በፍጹም ልቡ አለቀሰ:: ንስሃ ገባ:: መፍቀሬ ንስሃ ጌታችንም ንስሃውን ተቀበለው:: +የይቅርታው መገለጫም ተወዳዳሪ የሌላቸውን 5 መጻሕፍት ገለጠለት:: ተናገራቸው:: ጻፋቸው:: እሊሕም:- 1.መጽሐፈ ጥበብ 2.መጽሐፈ ተግሣጽ 3.መጽሐፈ መክብብ 4.መጽሐፈ ምሳሌ 5.መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ናቸው:: +ቅዱስ ሰሎሞን ልዩ የሆነውን ቤተ_መቅደስ በመስራቱም ይደነቃል:: ደጉ ንጉሥ: ጠቢብና ነቢይ ሰሎሞን በዚህች ዕለት በ52 ዓመቱ ዐርፎ ወደ ፈጣሪው ሔዷል:: +"+ አባ_ኖብ +"+ =>ዳግመኛ በዚህ ቀን ታላቁ ሰማዕት አባ ኖብ አርፏል:: በዚሕ ስም የሚጠሩ ብዙ ቅዱሳን ቢኖሩም ዋናው ይኼው ቅዱስ ነው:: +አባ ኖብ እንደ ገዳማውያን በበርሃ የተጋደለ: እንደ ሊቃውንት መጻሕፍትን ያመሰጠረ: በተለይ ደግሞ በዘመነ ሰማዕታት ጭንቅ ጭንቅ መከራዎችን የተቀበለ አባት ነው:: ስለ ገድሉ ብዛት "ኃያል ሰማዕት": አንገቱን ስላልተቆረጠም "ሰማዕት ዘእንበለ ደም" ይባላል:: ዘመነ ሰማዕታትን ካለፉ 72ቱ ከዋክብትም አንዱ ነው:: =>ከመፍቀሬ ጥበብ ቅዱስ ሰሎሞን: ከኃያሉ ሰማዕት አባ ኖብ በረከትን አምላካችን ይክፈለን:: =>ሰኔ 23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን (ንጉሠ እሥራኤል) 2.ቅዱስ አባ ኖብ (ሰማዕት ወጻድቅ) 3.ቅዱሳን መርቆሬዎስ: ፊልዾስና ቶማስ (ሰማዕታት) ❖ወርኃዊ በዓላት 1፡ ቅዱስ ዳዊት ልበ አምላክ 2፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት 3፡ ቅዱስ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ 4፡ አባ ሳሙኤል 5፡ አባ ስምዖን 6፡ አባ ገብርኤል 7፡ ቅዱስ ዳንኤል ነቢይ =>+"+ የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ:: ደስ አያሰኙም የምትላቸውም ዓመታት ሳይደርሱ: ፀሐይ: ጨረቃና ከዋክብትም ሳይጨልሙ . . . አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ: ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ:: ሰባኪው:- "ከንቱ: ከንቱ: ሁሉ ከንቱ ነው" ይላል:: +"+ (መክ. 12:1-9) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን":: የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር @beintakidusan @beintakidusan @beintakidusan
Mostrar todo...
ሰውን እርሳውና ፈጣሪህን አስደስት! – ሙሃዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ካላገባህ → « መቼ ነው የምታገባው? »- ካገባህ → « መቼ ነው ልጅ የምትወልደው?»- ሁለት ልጅ ካለህ → «መቼ ነው ሶስተኛ የምትደግመው?»- ትዳርህ ጥሩ ካልሆነ → «ፍቺ እያለ ለምን እንዲህ ትሆናለህ»- ከትዳር አጋርህ ስትፋታ → « ምነው ትንሽ ታግሰህ በነበረ?»- ጥብቅ ሰው ከሆንክ → « ምነው ከሰው አትቀላቀልም? »- ከሰዎች ተቀላቅለህ ስትጨዋወት → « ምነው ወሬ አበዛህ?»- ቁም ነገረኛ ሰው ከሆንክ → « ምን አይነት ሻካራ ሰው ነህ?»- በጥቂቱ ቀልደኛ ከሆንክ → «ቁምነገር የለህም»- አንዳንዴ ቁም ነገረኛ አንዳንዴ ቀልደኛ ስትሆን → «የምትጨበጥ ሰው አይደለህም»በቃ ሁሌም ማውራት ነው!ስትወፍር → ያወራሉስትከሳም → ያወራሉ ረዥም ከሆንክ → ያወራሉ አጭር ከሆንክ → ያወራሉ መካከለኛ ከሆንክ → ያወራሉ ደደብ ከሆንክ → ያወራሉ ጎበዝ ከሆንክ → ያወራሉድሃ ከሆንክ → ያሾፉብሃልሃብታም ከሆንክ → ይቀኑብሃልስራ ከሌለህ → ይንቁሃል ስራ ስትሰራ → ያሙሃል# ፌስቡክ ረዥም ስትፅፍ → «አሳጥረው»አጭር ስትፅፍ → «አብራራው»ምንም ካልፃፍክ → « ጸሎት አድርግ እንጂ?»ዝም ስትል → « ምከረን እንጂ»ሐቅ ስትፅፍ → « ለምን ፃፍከው!»ከተሳሳትክ → «ድሮም‘ኮ ..»ክረምት ሲሆን → «ወየው ብርዱ»በጋ ሲሆን → «አረረ ሙቀቱ» ሰዎች ሁሌም ሙሉ በሙሉ እርካታ አይሰማቸውም! ሰውን እርሳውና ፈጣሪህን አስደስት! @Moralitiy @Moralitiy
Mostrar todo...
💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕 ከትንሳኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ 💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕 @beintakidusan @beintakidusan 🌹ሰኞ- ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን @beintakidusan 🌹ማክሰኞ- ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29 @beintakidusan 🌹ረቡዕ- አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን @beintakidusan 🌹ሐሙስ- አዳም ሐሙስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን @beintakidusan @beintakidusan 🌹አርብ- ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና @beintakidusan @beintakidusan 🌹ቅዳሜ- ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል @beintakidusan @beintakidusan 🌹እሁድ- ዳግም ትንሳኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል። 💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕 @beintakidusan @beintakidusan @beintakidusan 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
Mostrar todo...
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !! ++ የጌታችን ሕማማት በሊቃውንት አንደበት ! "ታመመ፤ ሞትን ከተቀበለበት ከሥጋ ተዋሕዶ በመስቀል ላይ በፈቃዱ ለሥጋውያን ሞተ ባሕርየ መለኮት ሥጋን ተዋሕዶ በማኅፀን ካደረ ጀምሮ ሥጋ ገንዘቡ እንደ መኾኑ በሥጋ ይኸንን ሥርዓት ፈጸመ፡፡ ለማይመረመር ለመለኮቱ ባሕርይ እንደሚገባ ደግሞ እርሱ ኅብስት አበርክቶ ዂሉን ያጠግባል፤ አይራብም፤ አይጠማም፤ አይደክምም፤ አያንቀላፋም፤ አይታመምም፤ አይሞትም፤ ሕይወትን ለዂሉ ይሰጣል፡፡ ዳግመኛ በዚያ በሲኦልተ ገዝተው ያሉ ነፍሳትን ያድን ዘንድ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወረደ፤ በመለኮቱም ሲኦልን በዘበዘ" 📚የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ ቄርሎስ "እጆቹን እግሮቹን በተቸነከረባቸው ችንካሮች መወጋቱንም እናምናለን፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ ‹እርሱ ደዌያችንን ወሰደ፤ ሕማማችንንም ተሸከመ፤ እኛን ለማዳን ኃጢአታችንንም ለማስተስረይ መከራ ተቀበለ› እንዳለ፤ በባሕርዩ ሕማም የሌለበት ሲኾን በሥጋ የታመመ ነው፡፡ በእርሱ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ድነናል፤ በተገረፈና በተቸነከረም ጊዜ በመከራው ዂሉ መለኮትን ሕማም ተሰማው የሚል ሰው ቢኖር የተለየ የተወገዘ ይሁን" 📚ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ጎርጎርዮስ "እርሱ መቼም መች ከመለኮቱ ሳይለይ የሰውነትን ሥራ ዂሉ ገንዘቡ አደረገ፤ ይኸውም መራብ፣ መጠማት፣ መንገድ በመሔድ መድከም፣ በመስቀል ላይ መሰቀል፣ በብረት ችንካር መቸንከር ነው፡፡ በሰውነቱ መቸም መች ሰው ነው፤ በአምላክነቱም ሰውን የፈጠረ ነው፤ ነገር ግን ከማይከፈል ተዋሕዶ በኋላ መከፈል የለበትም፡፡ ሰው እንደ መኾኑ ስለ እኛ የታመመው፣ የሞተው እርሱ ነው፤ በመለኮቱ ግን መቸም መች አይታመምም፤ አይሞትም። ሕማምንና ሞትንም አይቀበልም፤ በሞቱ ሞትን ያጠፋው እርሱ ነው፤ ሲኦልንም የበዘበዘው እርሱ ነው" 📚የአንጾኪያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ዲዮናስዮስ "ነፍሱን ከሥጋው በለየ ጊዜ ያን ጊዜ በሲኦል ፈጥኖ ብርሃን ታየ፤ ጌታችን በአካለ ሥጋ ያይደለ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ሔደ ሲኦል ተነዋወጠች፤ መሠረቶቿም እፈርስ እፈርስ አሉ፡፡ ምድርን ያለ ጊዜዋ እንዳታልፍ ክብርት ደሙን በምድር ላይ አፈሰሰ፤ ከኅልፈት ጠበቃት በእርሷ ያለውንም ዂሉ ጠበቀ፡፡ ስለ ፍጥረት ዂሉ ሥጋውን በመስቀል እንደ ተሰቀለ ተወው፤ ነፍሱ ግን ወደ ሲኦል ወረደች ከዚያ ተግዘው የነበሩ ነፍሳትን አዳነች፤ ሲኦልንም በዘበዘች፡፡ ፍጥረትንም ዂሉ ገንዘብ አደረገች፤ ሥጋውም በመቃብር ያሉ ሙታንን አስነሣ፤ ነፍሱም በሲኦል ተግዘው የነበሩ ነፍሳትን ፈታች" 📚የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ አትናቴዎስ "ከብርሃን የተገኘ ብርሃን፣ ከባሕርይ አምላክ የተገኘ የባሕርይ አምላክ፣ የተወለደ እንጂ ያልተፈጠረ፣ በባሕርዩ ከአባቱ ጋር አንድ የሚኾን፤ ዂሉ የተፈጠረበት፤ ያለ እርሱ ግን ምንም ምን የተፈጠረ የሌለ፤ በሰማይ በምድር ያለውም ቢኾን፤ እኛን ስለ ማዳን ከሰማየ ሰማያት ወርዶ በግብረ መንፈስ ቅዱስ ከቅድስት ድንግል ማርያም ፍጹም ሰው ኾነ፡፡ የሠላሳ ዘመን ጐልማሳ ኾኖ በጲላጦስ የሹመት ዘመን ስለ እኛ ተሰቀለ፤ ስለ እኛም ታመመ፤ ሞተ፤ ተቀበረ" 📚ሠለስቱ ምእት "ምትሐት ያይደለ በእውነት ተራበ፤ ተጠማ፤ ዳግመኛም ከኃጥአን፣ ከመጸብሐን ጋር በላ፤ ጠጣ፤ ያቀረቡለትንም በላ፡፡ ራሱን አሳልፎ ለመስቀል ሰጠ፤ እጁን፣ እግሩን ተቸነከረ፤ ጐኑን በጦር ተወጋ፤ ከእርሱም ቅዱስ ምሥጢር የተገለጠበት ደምና ውኃ ፈሰሰ (ወጣ)" 📚ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ "የሚሠዋ በግ እርሱ ነው፤ የሚሠዋ ካህን እርሱ ነው፤ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም መሥዋዕት የሚቀበል እርሱ ነው፡፡ በፈቃዱ መከራን በሥጋው የተቀበለ መከራንም ዂሉ የታገሠ እርሱ ነው፤ እንደ በግ ሊሠዋመጣ፤ በግ በሚሸልተው ሰው ፊት እንደማይናገር አልተናገረም፤ በአንደበቱ ሐሰት አልተገኘበትም" 📚ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ በሥጋ መወለድ፣ በመስቀል መከራ መቀበል፣ መሞት፣ መነሣት፣ገንዘቡ የኾነ እርሱ እግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ ስለዚህ በመስቀል ላይሳለ ከጥንት ጀምሮ በመቃብር ያሉ ሙታንን ዂሉ አስነሣ" 📚ሰማዕቱ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ፊልክስ "ሙሴም ሞትን ያጠፋ ዘንድ አልቻለም፤ እርሱንም ይዞ ገዛው እንጂ፤ ከእርሱም በኋላ የተነሡ ነቢያትንም ዂሉ ሞት ገዛቸው እንጂ፤ ክርስቶስ ግን በቸርነቱ ለዂሉ ሕይወትን ሰጠ" 📚የሮማ ኤጲስ ቆጶስ ቅዱስ አቡሊዲስ "በመስቀል በሥጋ ተሰቅሎ ሳለ ለመለኮት ከሥጋ መለየት የለበትም፤ አንዲት ሰዓትም ቢሆን የዐይን ጥቅሻ ያህል ስንኳ ቢሆንም መለኮት ከትስብእት አልተለየም፣ በመቃብር ውስጥ በሰላም መለኮት ከትስብእት አልተለየም" 📚የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አዮክንድዮስ "ከአብ ጋር አንድ እንደ መኾንህ ሞት የሌለብህ አንተ ነህ፤ ከእኛ ጋር አንድ እንደ መኾንህ በፈቃድህ የሞትህ አንተ ነህ፤ በመቃብር ያደርህ አንተ ነህ፤ በኪሩቤል ላይ ያለህ አንተ ነህ፤ ከሙታን ጋር በመቃብር የነበርህ አንተ ነህ፡፡ በአንተ ሕማምና ሞትም ድኅነት ተሰጠ፤ ከሙታን ጋር የተቈጠርህ አንተ ነህ፤ ለሙታንም ትንሣኤን የምትሰጥ አንተ ነህ፤ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በመቃብር ያደርህ አንተ ነህ፡፡ በዘመኑ ዂሉ ከአብ ከመንፈስቅዱስ ጋር የምትኖር አንተ ነህ፤ በመለኮት ሕማም ሳይኖርብህ በሥጋ የታመምህ አካላዊ የእግዚአብሔር ቃል አንተ ነህ" 📚የኪስኪስ ኤጲስ ቆጶስ ቅዱስ ኤራቅሊስ "ኃጢአታችንን ለማሥተስረይ በሥጋ እንዲህ ታመመ፤ እንደ ሞተ ከነፍሱም በተለየ ጊዜ ሥጋውን እንደ ገነዙ እናምናለን" 📚የኢየሩሳሌም ኤጲስ ቆጶስ ቅዱስ ዮሐንስ "ነቢይ ዳዊት ‹ነፍሴን በሲኦል አትተዋትም፤ የባሕርይ ልጅህንምሙስና መቃብርን ያይ ዘንድ አሳልፈህ አትሰጠውም› አለ፡፡ ይህምጌታ በተዋሐደው አካል ያለውን የነፍስና የሥጋ ተዋሕዶያስረዳል፤ የቀና ልቡና ዕውቀት በእርሱ ጸንቶ ይኖር ዘንድ፡፡ ዳዊት እንደ ተናገረው እውነት ኾነ፤ ነፍስ መለኮትን ተዋሕዳ ወደ ሲኦል ወርዳለችና፡፡ ሥጋም ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በመቃብር ሳለመለኮት ከሥጋ አልተለየም፤ አምላክ ሰው የመኾኑን እውነትያስረዳ ዘንድ፡፡ መለኮት ነፍስን ተዋሕዶ በአካለ ነፍስ የሲኦልምሥጢርን ገልጦ ፈጽሟልና በሲኦልም በቁራኝነት አልተያዘምና" 📚የቆጵሮስ ደሴት ኤጲስ ቆጶስ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ "ክርስቶስ በራስ ቅል ሥፍራ ተሰቀለ" ማለት ከዚያ ዘመን ጀምሮ እስከ ምጽአት ድረስ በሚነሱ ክርስቲያኖች ጭንቅላት ውስጥ ክርስቶስ ተሰቅሎ ይኖራል ማለት ነው። በእኔና በእናንተ ጭንቅላት ውስጥ ተሰቅሎ መኖር አለበት ማለት ነው። ፍቅሩ፣ መከራውና የመስቀሉ ነገር በጭንቅላታችን ተቋጥሮ እንዲኖር እንዳንረሳው ምንጊዜም ተቀርጾብን እንዲኖር ነው። አሁንም በጭንቅላታችን ውስጥ ክርስቶስ ተሰቅሎብን ይኖራል አይወርድም። ዛሬ የመስቀሉ ሥፍራ ቀራንዮ አይደለም የእኛ ጭንቅላት ነው። ቀራንዮ ዛሬ ይተረካል እንጂ መስቀሉ የለም። መስቀሉ ያለው በምእመናን ጭንቅላት ውስጥ ነው" 📚ሊቀ ሊቃውንት አለቃ አያሌው ታምሩ #ምንጭ ፦ https://eotcmk.org/a/የጌታችን-መከራ-በሊቃውንት-አንደበት እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻማ ወድካም ዓመ ከመ ዮም ፤ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ      እግዚአብሔር ለብርሃነ ትንሣኤሁ በፍስሓ ወበሰላም !               🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 https://telegram.me/beintakidusan https://telegram.me/beintakidu 👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
Mostrar todo...
የጉልባን ታሪክ 💦💦💦💦 https://telegram.me/beintakidusan ➛ ጉልባን ከባቄላ ክክ ከሰንዴ ወይም ከተፈተገ ገብስ እና ከሌሎችም ጥራጥሬዎች ጥሬውን ወይም ከክቶ እንደ ንፍሮ ተቀቅሎ የሚዘጋጅ ምግብ ነው ። የዕለተ ሐሙስ ሥርዓተ ጸሎት ከተፈጸመ በኋላ ምእመናን ወደ ቤታቸው ሄደው ጉልባን ሠርተው ይመገባሉ ። ለዚህም ሁለት ትውፊታዊ መሠረት እንዳሉት ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ያስረዳሉ እንመልከት፦ ፩ የኦሪት ምሳሌ ለመፈጸም እስራኤል ለ215 ዓመታት በግብጻውያን በባርነት ተይዘው በግፍ ተጨቁነው መኖራቸው ይታወቃል የእግዚአብሔር ፍቃድ ሁኖ እግዚአብሔር ሙሴን ፈርኦንን ህዝቤን ልቀቅ ብሎሀል ብለህ ንገረው ብሎት ነበር ። ሙሴም ፈርኦንን እግዚአብሔር ህዝቤን ልቀቅ ብሎሀል አለው ፈርኦንም እስራኤል እለቅ ዘንድ እግዚአብሔር ማነው ? እግዚአብሔርን አላቅም እስራኤንም ደግሞ አለቅም በማለት አሻፈረኝ ብሎ ነበር ። እግዚአብሔርም የኃይል ስራውን በሙሴ አሳየ በመጨረሻም እምቢ ሲል እግዚአብሔር ከእንስሳትም ከሰውም ወገን በመልአክ በሞተ በኩር ግብጽ ተቀሰፈች በዚህም ፈርኦን ደንግጦ ሕዝበ እስራኤል ለመልቀቅ ተገዷል ። በዚህ ጊዜ ህዝቡ ለመውጣት ስለቸኮሉ በቤት ያለውን እህል ያልተፈጨውን ንፍሮ ቀቅለው የተፈጨውን ቂጣ ጋግረው በልተው ነው ጉዞ የጀመሩት ። እስራኤልም ከግብፅ ከወጡ በኋላም የነጻነት በዓላቸውን ሲያከብሩ ያልቦካ ኪጣ ጋግረው ንፍሮ ቀቅለው በግ አርደው ከባርነት በወጡበት ዕለት የነበረውን ሁኔታ ያስቡ ዘንድ ታዘዋል ። (ዘጸ ፲፫ ፥፩) ፋሲካ የሚለውም '' ፓሢሕ '' ከሚለው ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ማለፍ መሻገር ማለት ነው ። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምሴተ ሐሙስ በአልዓዛር ቤት ተገኝቶ ከደቀመዛሙርቱ ጋር ይህን በዓል አክብሯል ። እኛም አሰቀድሞ በሙሴ ላይ አድሮ ሕገ ኦሪትን የሠራ ሕዝቡንም መርቶ ከነዓን ያደረሰው እርሱ ራሱ እግዚአብሔር የሰውን ስጋ ለብሶ ክርስቶስ ተብሎ መገለጡን በማመን ፤ ክርስቶስ ራሱ አዲሱን ሕግ ከመሥራቱ አሰቀድሞ ከደቀመዛሙርቱ ጋር በዓለ ፋሲካን እንዳከበረ ሁሉ እኛም አዲስ ኪዳን ጥላ /ምሳሌ/ የሆነውን ሥርዐት እኛ ጉልባን በመመገብ ለመታሰቢያ እናደርጋለን ። https://telegram.me/beintakidusan ፪ የኀዘን ሳምንት መሆኑን ለማጠየቅ ፦ እንደ ሀገራችን ባሕል ንፍሮ እንባ አድርቅ ይሉታል ። ብዙ ጊዜም ለለቀስተኞች ይሠራል ። አንድም ሞት ተናግሮ አይመጣምና ሞት በድንገት ሲመጣ ለእንግዳ መሸኛ ቶሎ ሊደርስ የሚችል ምግብ ንፍሮ ስለሆነ በተለይም በገጠራማ አካባቢዎች ለልቅሶ ቤት ንፍሮ የመቀቀል ልማድ አለ ። https://telegram.me/beintakidusan ➛ በሰሙነ ሕማማት ወቅት ምዕመናን በጌታችን መከራ ፣ ሞት እና በድንግል ማርያም ኀዘን ምክንያት ኀዘንተኞች ስለሆኑ ይህንኑ ለማመልከት ጉልባን ይመገባሉ ። የጉልባን ክርስቲያናዊ ትውፊት ይህንን ይመስላል እኛ ምዕመናን በቤተችን እንዲሰራ በመጠየቅ በመስራት ይህን ትውፊት ማስቀጠል ይኖርብናል። 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 https://telegram.me/beintakidusan https://telegram.me/beintakidusan https://telegram.me/beintakidusan
Mostrar todo...
ሰሙነ ህማማት ዘሐሙስ (ጸሎተ ሐሙስ) በቤተ ክርስቲያን የተለያዩ ስያሜዎች ያሏቸው በርካታ ድርጊቶች የተፈጸሙበት ዕለት ነውና ጸሎተ ሐሙስ ይባላል፡፡ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን የተዋሐደ አምላክ፣ መሆኑን ለመግለጥና ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እስኪይዙት ድረስ ሲጸልይ ያደረበት ነውና ጸሎተ ሐሙስ ተባለ፡፡ ማቴ. 26፣ 36-46 ዮሐ.17 #ሕፅበተ_ሐሙስ_ይባላል ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትሕትና ዝቅ ብሎ አጥቧል፡፡ ይህም የሚያሳየው የዓለምን ሁሉ ኃጢአት ለማጠብ የመጣ መሆኑን ነው፡፡ ይህን ለማስታወስ ዛሬም ካህናት በተለይም ሊቃነ ጳጳሳት፣ የደብር አስተዳዳሪዎች፤ «በመካከላችን ተገኝተህ የእኛንና የሕዝብህን ኃጢአት እጠብ እኛም የአንተን አርአያ አንዘነጋም የሌላውን እግር እናጥባለን፤» ሲሉ በቤተ ክርስቲያን የተገኙትን ምእመናንን እግር በወይንና በወይራ ቅጠል ያጥባሉ፡፡ #የምስጢር_ቀን_ይባላል ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ በዚህ ዕለት ተመሥርቷልና፡፡ ይኸውም «ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ሥጋዬ ነው፡፡ እንካችሁ ብሉ» ጽዋውንም አንስቶ አመሰገነ «ይህ ስለ እናንተ ነገ በመስቀል የሚፈስ ደሜ ነው ከእርሱም ጠጡ» በማለት፤ እኛ ከእርሱ ጋር፣ እርሱ ከእኛ ጋር አንድ የምንሆንበትን ምስጢር ከጠላት ዲያብሎስ ሰውሮ፣ ለደቀ መዛሙርቱ የገለጠበት ቀን በመሆኑ የተሰጠ ሥያሜ ነው፡፡ በዚህ ዕለት ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በንስሐ ታጥቦ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለመቀበል ይዘጋጃል፡፡ #የሐዲስ_ኪዳን_ሐሙስ_ይባላል ምክንያቱም መሥዋዕተ ኦሪት ማለትም በእንስሳት ደም የሚቀርበው መሥዋዕት ማብቃቱን ገልጦ፣ ለድኅነተ ዓለም ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ «ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው በደሜ የሚሆን ሐዲስ ኪዳን ነው፡፡ ከእርሱ ጠጡ» በማለቱ ይታወቃል /ሉቃ. 22፣20/ ኪዳን ማለት በሁለት ወገን መካከል የሚደረግ ውል፣ ስምምነት፣ መሐላ ማለት ነው፡፡ በዚህ መሠረት ጌታችን ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ዘለዓለማዊውን ቃል ኪዳን በራሱ ደም የፈጸመበት ዕለት ስለሆነ የሐዲስ ኪዳስ ሐሙስ ተባለ፡፡ #የነጻነት_ሐሙስ_ይባላል ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱ፣ የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡ ጌታችን ስለ ሰው ልጅ ነጻነት ሲናገር «ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም ባርያ ጌታዉ የሚያደርገውን አያውቅምና ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ» በማለት /ዮሐ. 15፣15/፤ ከባርነት የወጣንበት ልጆች የተባልንበትን ቀን የምናስብበት በመሆኑ ሊቃውንቱ የነጻነት ሐሙስ አሉት፡፡ እያንዳንዱ ክርስቲያንም ከኃጢአት ባርነት ርቆ፣ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያወዳጀውን መልካም ሥራ በመሥራት ሕይወቱን መምራት ይኖርባታል፡፡ ባሮች አልላችሁም ተብለናልና፡፡ 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 https://telegram.me/beintakidusan https://telegram.me/beintakidusan 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
Mostrar todo...
​​​​በሰሙነ ሕማማት የሚፈጸ ሥርዓቶች 1, ስግደት :- በሰሙነ ሕማማት 41 ጊዜ ኪርያላይሶን 12 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት እየተዜመ እጅግ አብዝቶ ይሰገዳል። 2, ጸሎት :- በሰሙነ ሕማማት ከ24 ሰዓት ውስጥ 10 የጸሎትና የንባብ ሰዓታት ይገኛሉ እነዚህም ከጠዋቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት እንዲሁም ከምሽቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት ናቸው። በእነዚህም ሰዓታት የጌታን ስቃይ ለማዘከር መዝሙረ ዳዊትና ግብረ ሕማማት ድርሳነ ማኅያዊ አብዝተው ይጸለያሉ። 3, ጾም :- በሰሙነ ሕማማት ብዙ አዝማደ መባልዕት / አዘውትረን የምንመገባቸው ምግቦች አይበሉም። በዚህም ሳምንት እስከ ምሽቱ #አንድ_ሰዓት እንድንጾም; ይኸውም ቆሎ;ዳቦ;ወኃና ጨው ብቻ እንደታዘዙ በግብረ ሕማማት ላይ ተጽፎ ይገኛል። 4, አለመሳሳም :- አይሁድ ጌታችንን ለመስቀል እየተንሾካሾኩ ስለተመካከሩና ይሁዳ ጌታችንን በመሳም አሳልፎ ስለሰጠው መሳሳም አይፈቀድም። መስቀልም በዘመነ ኦሪት የወንጀለኛ መቅጫ የእርግማን ምልክት ስለ ነበር ጌታችን በክቡር ደሙ ቀድሶ የድል አርማ እስኪያደርግልን ድረስ አንሳለመውም ገላ.3:13 ማቴ.10:38 ማቴ. 26:29 5. አክፍሎት :- እመቤታችን; ያዕቆብና ዮሐንስ የጌታችን ትንሳኤ ሳናይ እህልና ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤው መቆየታቸውን በማሰብ የሚጾም ነው። 6, ጉልባን :- ከባቄላ ከስንዴ ከገብስ የሚዘጋጅ በጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ሲሆን ትውፊቱም የስቅለቱ ሐዘን መግለጫ ነው። 7, ጥብጠባ :- ይህ ምዕመናን በሰሙነ ሕማማት የፈጸሟቸውን ኃጢአቶች ለካህን እየተናዘዙ በወይራ ቅጠል ቸብቸብ እየተደረጉ ስግደት የሚቀበሉበት ነው። ይህም የጌታ ምሳሌ ነው። 8, ቄጠማ :- ጌታችን ብርሃነ ትንሳኤዉን እንደገለጠልን የምናስብበት ሲሆን የእሾህ አክሊል በመድፋቱ ምሳሌም በራሳችን ላይ እናስረዋለን። እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻም ወድካም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሳኤሁ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም። ☞@FireAbehu https://telegram.me/beintakidusan https://telegram.me/beintakidusan https://telegram.me/beintakidusan
Mostrar todo...
+ በርባን ይፈታልን + ሕዝቡ ‹በርባን ይፈታልን! ክርስቶስ ግን ይሰቀል!› ማለታቸውን ስንሰማ መቼም ሁላችንም ማዘናችንና ‹ምን ዓይነት ክፉዎች ናቸው?!› ብለን መውቀሳችን አይቀርም፡፡ ወዳጄ ሆይ! እባክህን እስቲ አይሁድንና ጲላጦስ ለአፍታ እንተዋቸው! አንተ ብትሆን ኖሮ ከጌታና ከበርባን ማናቸውን ትፈታለህ? የእስክንድርያው ትምህርት ቤት ዲን የነበረው ሊቅ ‹‹በሥጋው ክፉ ነገርን የሚሠራ ሁሉ በርባንን ፈትቶ ክርስቶስን አሰረው ፤ መልካም ነገርን የሚያደርግ ደግሞ ክርስቶስን ፈትቶ በርባንን አስሮታል›› ይላል፡፡ ወዳጄ ሆይ! አንተ በሰውነትህ ላይ ፈትተህ የለቀቅከው ማንን ነው? በርባንን ነው ወይንስ ጌታን ነው? በርባንን ፈትተኸው ከሆነ ዛሬውኑ በንስሓ ተመልሰህ ፈጣሪህን በሰውነትህ ውስጥ አክብረው፡፡ ‹በርባንን የፈታሁት እኮ ወድጄ አይደለም! ሁኔታዎች አስገድደውኝ ነው› ብለህ እንደ ጲላጦስ ለራስህ ይቅርታ ማድረግና እጅህን መታጠብ አይበጅህም፡፡ ይልቅስ አሁኑኑ ጌታህን ፈትተህ በርባንን የተባለ ኃጢአትን ስቀለው! ያን ጊዜ የክርስቶስ መሆንህ ይታወቃል፡፡ ‹‹የክርስቶስ ኢየሱስ የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ምኞቱ ጋር ሰቀሉ›› ተብሎ ተጽፎአልና፡፡ (ገላ. ፭፥፳፬) ሕዝቡ ‹በርባን ይፈታ› ብለው ቢጮኹም ሁሉም ለበርባን ፍቅር አላቸው ማለት አይደለም፡፡ ሊቃነ ካህናቱ ባያባብሏቸው ኖሮ በዚያች ዕለት ሊያስፈቱት የሚፈልጉት ሌላ እስረኛ ዘመድ ያላቸውም ሰዎች መኖራቸው አይቀሬ ነው፡፡ ሆኖም ሊቃነ ካህናቱ ለጌታችን ካላቸው ጥላቻ የተነሣ ሕዝቡን ተለማምጠው በርባን እንዲፈታ አስደረጉ፡፡ ዛሬ በርባንን አግኝተን ‹በርባን ሆይ ማን ነው ያስፈታህ?› ብለን ብንጠይቀው ምናልባትም ‹የሰው መውደድ ይሥጥ ማለት ነው! የሚወደኝ ሕዝብ ነዋ ጮኾ ያስፈታኝ!› ማለቱ የማይቀር ነው፡፡ ሆኖም ሊቃነ ካህናቱና ተከታዮቻቸው ግን ‹በርባን ይፈታ› ብለው የጮኹት ለበርባን ፍቅር ኖሯቸው ሳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ በነበራቸው ጥላቻ ምክንያት ነው፡፡ ስለዚህ በርባንን ከሞት ፍርድ አድኖ ያስፈታው ሕዝቡ ሳይሆን ጌታችን ነበር፡፡ ጌታችን በዚያች ዕለት የበርባንን ሞት ወስዶ የእርሱን ሕይወት ለበርባን ሠጠው ፤ የበርባንን ሰንሰለት አስፈትቶ እርሱ ታሰረ ፤ ከበርባን ጓደኞች ጋር በርባን ሊሰቀል በነበረበት ቦታም ተሰቀለ፡፡ ወዳጄ ሆይ! ልብ ብለህ ከተረዳኸው በርባን እኮ አንተው ነህ! ለበርባን ከተደረገለት ለአንተ ያልተደረገ ነገር ካለ እስቲ ንገረኝ! እንደ በርባን ክርስቶስ ሞትህን ወስዶ ሕይወቱን ፣ እስራትህን ወስዶ ነጻነትን አልሠጠህምን? ይህንን ያደረገውም ለአንተ ብቻ ሳይሆን ለአዳም ልጅ ሁሉ ነው ፡- ‹‹የእስረኛው በርባን (ወልደ አባ) መፈታቱ አምላካዊ ምሥጢርን የሚያስታውስ ነው፡፡ በኃጢአቱ ምክንያት በሲኦል ውስጥ ታሥሮ የነበረው አዳምን በአዳኙ መሰቀል ምክንያት መድኃኒት አግኝቶ ነጻ መውጣቱን ያስታውሳል›› / ‹‹እስመ ተፈትሕዎቱ ለወልደ አባ ሙቁሕ ያዜክር ምሥጢራተ አምላካዊ ያሌቡ ግዕዛነ አዳም ዘኮነ ሙቁሐ ውስተ ሲኦል በእንተ ኃጢአቱ ወረከበ መድኃኒተ በስቅለተ መድኅን›› እንዲል፡፡ በዚያች የዕለተ ዓርብ ረፋድ ላይ ያስፈታውን የማያውቀው ይህ ወንበዴ ሰንሰለቱ ተፈትቶ ወደ ቤቱ ሲሔድ ጌታችን ግን ለመከራና ለመስቀል ተሠጠ፡፡ እውነቱንስ ለመናገር እኛ ክርስቲያኖች በርባን በመፈታቱ ላይ ላዩን ብናዝንም ውስጥ ውስጡን ግን ደስ ብሎናል! ‹‹…በርባን ቢሰቀል ኢየሱስ ቀርቶ ምን ይጠቅመናል ሽፍታ ሞቶ እንኳን ኢየሱስን ሰቀሉት የሞቱን መድኃኒት …›› ብለው መሪጌታ ፍቅሩ ሣህሉ በበገናቸው ጨርሰውታል፡፡ (#ሕማማት ) ለሁሉም ይደርስ ዘንድ ሼር ያድርጉ https://telegram.me/beintakidusan https://telegram.me/beintakidusan https://telegram.me/beintakidusan 👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
Mostrar todo...
#ሰበር_ዜና #13_አገልጋዮችን_ከየትኛውም_ቤተክርስቲያን_አግደናል . #ወቅታዊና_ሁሉም_ሰው_ሊያነበው_የሚገባ_መግለጫ . #ይድረስ_በመላው_አለም_ለምትገኙ_ቅዱሳን_አገልጋዮች_የቤተክርስቲያን_መሪዎች ............. እነዚህ ከታች የተዘረዘሩት አገልጋዮች በሙሉ በክርስቶስ ቤተክርስቲያን ላይ በፈጠሀሩት ተደራራቢ ችግር ምክንያት በመላው አለም በሚገኙ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያናት የታገዱ ናቸው። በመሆኑም ቅዱሳን እነዚህን ከታች የተጠቀሱ 13 አገልጋዮችና አጋሮቻቸውን በየትኛውም የአምልኮ ስፍራ ላይ እንዳይገኙ፣ ህዝበ ክርስትያኑ እንዲቃወማቸው እና እንዲጠየፋቸው ስንል በትህትና እጠይቃለን። እኛም እነዚህ አገልጋዮች ባሉበት ላናገለግል፣ በደረሱበት ላንደርስ ወስነናል። . . . . 1፦ አቶ ቅናት 2፦ አቶ ክፋት 3፦ አቶ ትዕቢት 4፦ ወ/ሮ ተንኮል 5፦ አቶ ምቀኝነት 6፦ አቶ ዘረኝነት 7፦ እህት መለያየት 8፦ ወንድም ራስ ወዳድ 9፦ አቶ ሀሜት 10፦ ወንድም አድመኝነት 11፦ እህት እኔነት 12፦ አቶ ጥላቻ 13፦ እንዲሁም ወ/ሪት ጠብ ዘሪን ከማንኛውም አገልግሎት ላይ አግደናቸዋል። #ግልባጭ * በሃገር ውስጥ እና በተለያዩ ዓለም ላሉ ክርስቲያን ወንድሞችና እህቶች። * በሃገር ውስጥና በውጭ ላሉ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች፣ መሪዎች፡፡ እባክዎ ይሄ መልዕክት እንደ ግልባጭ እዲደርስ ሼር ያድርጉት። እግዚአብሔር ይባርክዎ፡፡ ለመቀላቀል👇👇 @ https://telegram.me/beintakidusan https://telegram.me/beintakidusan https://telegram.me/beintakidusan 🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊
Mostrar todo...
#የአብይ ፆም 6ተኛ ሳምንት ገብርሄር ይባላል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ/ አደረሰን #ገብርሄር ማለት ታማኝ አገልጋይ ማለት ነው #እኛም የእግዚአብሔር ልጆች በቃሉ ታምነን ወንጌሉን ተምረን እነደ አቅማችን ሰላሳ ስልሳ መቶም ያማረ ፍሬ አፍርተን የክብሩ ወራሽ የመንግስቱ ቀዳሽ ለመሆን ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለዚህ ክብር ያብቃን አሜን፫ ( ማቴዎስ ወንጌል 25፤14-30) ፤ወደ ሌላ አገር የሚሄድ ሰው ባሮቹን ጠርቶ ያለውን ገንዘብ እንደ ሰጣቸው እንዲሁ ይሆናልና፤ ለእያንዳንዱ እንደ ዓቅሙ፥ ለአንዱ አምስት መክሊት ለአንዱ ሁለት ለአንዱም አንድ ሰጠና ወደ ሌላ አገር ወዲያው ሄደ። ፤ አምስት መክሊትም የተቀበለው ሄዶ ነገደበት ሌላም አምስት አተረፈ፤ እንዲሁም ሁለት የተቀበለው ሌላ ሁለት አተረፈ። አንድ የተቀበለው ግን ሄዶ ምድርን ቈፈረና የጌታውን ገንዘብ ቀበረ። ፤ ከብዙ ዘመንም በኋላ የእነዚያ ባሮች ጌታ መጣና ተቆጣጠራቸው። አምስት መክሊት የተቀበለውም ቀረበና ሌላ አምስት መክሊት አስረክቦ። ጌታ ሆይ፥ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ አምስት መክሊት አተረፍሁበት አለ። ፤ ጌታውም። መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው። ሁለት መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ። ጌታ ሆይ፥ ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ ሁለት መክሊት አተረፍሁበት አለ። ጌታውም። መልካም፥ አንተ በጎ፥ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፥ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው። ፤ አንድ መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ። ጌታ ሆይ፥ ካልዘራህባት የምታጭድ ካልበተንህባትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤ ፈራሁም ሄጄም መክሊትህን በምድር ቀበርሁት፤ እነሆ፥ መክሊትህ አለህ አለ። ፤ ጌታውም መልሶ እንዲህ አለው፦ አንተ ክፉና ሃኬተኛ ባሪያ፥ ካልዘራሁባት እንዳጭድ ካልበተንሁባትም እንድሰበስብ ታውቃለህን? ስለዚህ ገንዘቤን ለለዋጮች አደራ ልትሰጠው በተገባህ ነበር፥ እኔም መጥቼ ያለኝን ከትርፉ ጋር እወስደው ነበር። ፤ ስለዚህ መክሊቱን ውሰዱበት አሥር መክሊትም ላለው ስጡት፤ ላለው ሁሉ ይሰጠዋልና ይበዛለትማል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል። ፤ የማይጠቅመውንም ባሪያ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጡት፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል። #እግዚአብሔር ፆሙን የምህረት ያድርግልን። 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 #የአብይ ፆም 6ተኛ ሳምንት ገብርሄር ይባላል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ/ አደረሰን #ገብርሄር ማለት ታማኝ አገልጋይ ማለት ነው #እኛም የእግዚአብሔር ልጆች በቃሉ ታምነን ወንጌሉን ተምረን እነደ አቅማችን ሰላሳ ስልሳ መቶም ያማረ ፍሬ አፍርተን የክብሩ ወራሽ የመንግስቱ ቀዳሽ ለመሆን ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለዚህ ክብር ያብቃን አሜን፫ ( ማቴዎስ ወንጌል 25፤14-30) ፤ወደ ሌላ አገር የሚሄድ ሰው ባሮቹን ጠርቶ ያለውን ገንዘብ እንደ ሰጣቸው እንዲሁ ይሆናልና፤ ለእያንዳንዱ እንደ ዓቅሙ፥ ለአንዱ አምስት መክሊት ለአንዱ ሁለት ለአንዱም አንድ ሰጠና ወደ ሌላ አገር ወዲያው ሄደ። ፤ አምስት መክሊትም የተቀበለው ሄዶ ነገደበት ሌላም አምስት አተረፈ፤ እንዲሁም ሁለት የተቀበለው ሌላ ሁለት አተረፈ። አንድ የተቀበለው ግን ሄዶ ምድርን ቈፈረና የጌታውን ገንዘብ ቀበረ። ፤ ከብዙ ዘመንም በኋላ የእነዚያ ባሮች ጌታ መጣና ተቆጣጠራቸው። አምስት መክሊት የተቀበለውም ቀረበና ሌላ አምስት መክሊት አስረክቦ። ጌታ ሆይ፥ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ አምስት መክሊት አተረፍሁበት አለ። ፤ ጌታውም። መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው። ሁለት መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ። ጌታ ሆይ፥ ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ ሁለት መክሊት አተረፍሁበት አለ። ጌታውም። መልካም፥ አንተ በጎ፥ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፥ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው። ፤ አንድ መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ። ጌታ ሆይ፥ ካልዘራህባት የምታጭድ ካልበተንህባትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤ ፈራሁም ሄጄም መክሊትህን በምድር ቀበርሁት፤ እነሆ፥ መክሊትህ አለህ አለ። ፤ ጌታውም መልሶ እንዲህ አለው፦ አንተ ክፉና ሃኬተኛ ባሪያ፥ ካልዘራሁባት እንዳጭድ ካልበተንሁባትም እንድሰበስብ ታውቃለህን? ስለዚህ ገንዘቤን ለለዋጮች አደራ ልትሰጠው በተገባህ ነበር፥ እኔም መጥቼ ያለኝን ከትርፉ ጋር እወስደው ነበር። ፤ ስለዚህ መክሊቱን ውሰዱበት አሥር መክሊትም ላለው ስጡት፤ ላለው ሁሉ ይሰጠዋልና ይበዛለትማል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል። ፤ የማይጠቅመውንም ባሪያ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጡት፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል። #እግዚአብሔር ፆሙን የምህረት ያድርግልን። 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 https://telegram.me/beintakidusan https://telegram.me/beintakidusan https://telegram.me/beintakidusan 👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆 👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
Mostrar todo...