es
Feedback
ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

Ir al canal en Telegram

ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

Mostrar más

📈 Análisis del canal de Telegram ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

El canal ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias (@drsofonias) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 19 949 suscriptores, ocupando la posición 1 157 en la categoría Medicina y el puesto 1 681 en la región Etiopía.

📊 Métricas de audiencia y dinámica

Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 19 949 suscriptores.

Según los últimos datos del 27 junio, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de -557, y en las últimas 24 horas de -23, conservando un alto alcance.

  • Estado de verificación: No verificado
  • Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 26.07%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 6.79% de reacciones respecto al total de suscriptores.
  • Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 5 203 visualizaciones. En el primer día suele acumular 1 354 visualizaciones.
  • Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 10.

📝 Descripción y política de contenido

El autor describe el recurso como un espacio para expresar opiniones subjetivas:
ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 28 junio, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Medicina.

19 949
Suscriptores
-2324 horas
-1257 días
-55730 días
Archivo de publicaciones
የቆለጥ ፍሬ መደበቅ (Cryptorchidism) ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ማለት:- ===== ↪በህፃናት ላይ በብዛት የሚታይ የዘር ፍሬ አንዱ ወይም ሁለቱም ቆለጥ ውስጥ አለመገኘት ነው። ↪ቤተሰብ ወንድ ልጅ እደተወለደ ሁለት የዘር ፍሬ መኖሩን ማረጋገጥ ዘግይቶ ከታወቀ እስከ መሀንነት እና የዘር ፍሬ ካንሰር (testicular cancer - Seminoma) አስከፊ ውጤት ያመጣል። ↪አንዲሴንዲግ ቴስትስ (UDT/MDT) ይባላል። ✒የዘር ፍሬ ሆድ አከባቢ ሳይወርድ ሊቆይ ይችላል እስከ 6 ወር እድሜ ። ከ6 ወር በኋላ በሰርጀሪ መስተካከል አለበት። ✒ስዕላዊ ምርመራ አይፈቀድም ከ6 ወር እድሜ በፊት። ✒ሰርጀሪ (Orchiopexy ተመራጭ ነው) ✒የሆርሞን ህክምና አይመከርም ✒የተሳካ ኦፕሬሽን ተሰርቶ የዘር ፍሬው በቦታው ከተመለሰ መካንነት እና የዘር ፍሬ ካሰርን ይቀንሳል እንጂ ሙሉ ለሙሉ አይከላከልም። ✒ተገቢ ምክርና ክትትል ያስፈልገዋል ለህመምተኛው ያስፈልጋል። ✒በፅንስ ጊዜ በ3-5 ሳምንት ውስጥ የወንድ የዘር ፍሬ ይፈጠራል ከ28 ሳምንት በኋላ በአልትራ ሳውድ ማየት ይቻላል። ተጋላጭ :- ======= ✴በሰዓቱ የተወለደ ህፃን በሰዓቱ -3% ✴ያለድሜ የተወለደ (<37 ሳምንት) ህፃን -30% ✴ሲወለድ ትንሽ ክብደት ከሆነ ✴መንታ ሆኖ መወለድ ✴እናት ሆርሞን መዳኒት (Estrogen) ምትጠቀም ከሆነ ✴በቤተሰብ ✴በፊት የወረደ ተመልሶ ወደ ሆድ መመለስ በተለያየ ምክንያት ምልክት :- ======= ✒የዘር ፍሬ 1 ወይም ከሌለ የዘር ፍሬ ቆለጥ ውስጥ ከሌለ - 📌80% - ይነካሉ ወደ ሆድ አከባቢ 📌20% -አይዳሰስም - በኦፕሬሽን 20-40% ብቻ ይገኛል 📌40% ለዘር ፍሬ ካንሰር ይጋለጣል ✒ተያያዠ ህመም ይኖራል - * የሽት መውጫ ቀዳዳ ያለቦታው መገኘት * በቤተሰብ ካለ * የሆድ እቃ ወደውጭ መውጣት (omepacele ,Gastrichisis) * ወዘተ ምርመራ :- ======= 📌ደም - ሆርሞን 📌ስእላዊ - አልትራ ሳውንድ (abdominal & pelvic),CT scan - MRA (Magnetic resonance angiography)- ተመራጭ 📌ሌሎች

እረረ ላሽ❗️... አይነፋም " 😂😂😂 🤔 ቆይ ግን ላሽ ምንድነው⁉️ 👍 አንዱን ልጅ ጠርታችሁ "አቢ ላሽ ማለት ምን ማለት ነው" ብላችሁ ብትጠይቁት "ላሽ ማለትማ በቃ መተው ወይም መፋታት ነዋ" ብሎ ልመልስላችሁ ይቺላል 😂😂 👉 እናት እና አባቶቻችን ቢጠየቁ ደሞ "ላሽ ማለትማ ሌሊት በተኛንበት መታ የራስ ፀጉር የምትበላ እና መላጣ የሚታረግ ነፍሣት ነች" ይላሉ:: 😂 የዘመኑ ልጅ ይሄንን ቢሰማ ምን ይላል?." What ... እረረ ላሽ... አይነፋም❗️ " 😂😝😂 👨‍⚕️ወደ ቁም ነገሩ እንምጣ እና በሕክምናውስ ላሽ ማለት ምን ማለት ነው? ምክንያቱስ ምንድነው ⁉️ ✍️ ላሽ በእንግሊዘኛው Alopecia ይባላል:: ይህም ህፃናትን ጨምሮ በሁለም የእድሜ ክልል የሚገኙ ሰዎች ላይ ሊከሰት የሚችል የጸጉር መመለጥ በሽታ ነው :: 👉 ይህ በሽታ በየትኛዉም የሰዉነት ክፍሎች የሚገኝ ጸጉር ሊያጠቃ ይችላል፡፡ ብዙ ጊዜ ግን የራስ ቅል ጸጉርን ያጠቃል፡፡ 👩‍🦲🧑‍🦲 🔷የበሽታዉ መንስኤ ምንድን ነዉ? 👉 ህፃናት ላይ የሚታየው የራስ ፀጉር መመለጥ ምክንያቱ የፈንገስ ኢንፌክሽን ወይም ቆሮቆር ሲሆን ይሄም ከታከመ ሙሉ ለሙሉ ይጠፋል:: 👉 ህፃናት ላይ በአደጋ ወይም በ እሳት ቃጠሎም የ ተወሰነ ቦታ መላጣ ሆኖ ሊቀር ይቺላል:: 👉 አዋቂዎች ላይ ደሞ ዋናው መንስኤ በተፈጥሮ የተለያዩ በሽታዎችን የሚከላከልው የሰዉነት በሽታ መከላከያ ስርዓት(Immune system)ሴሎች የሰውነት ፀጉርን በሚያጠቁበት ጊዜ ላሽ (Alopecia areata) ይከሰታል:: 👉 ላሽ እንደ ሥኳር በሽታ፤ ለምጥ፤እንቅርት ጋር መጠነኛ ተያያዥነት አለዉ:: 👉 ከምግብ ቫይታሚን እጥረት ጋር ምንም አይገናኝም❗️ 👉 በዘር ሊሄድ ይቺላል እስከ 20 የሚደርሱ ሰዎች ተመሳሳይ ችግር በቤተሰባቸዉ (በዘር) ሊታይ ይከሰታል የላሽ በሽታ አይነቶች በሽታዉ በተለያየ የክብደት ደረጃ ይከሰታል፤ ከአነስተኛ የራስ ቅል ፀጉር መመለጥ(Alopecia areata ) እስከ ሙሉ የራስ ቅል ፀጉር መመለጥ (Alopecia Totalis) ከዚያም በከፋ መልኩ በሁሉም የሰዉነት ክፍሎች የሚገኝ ጸጉር መመለጥ (Alopecia Universalis) በአብዛኛዉ ጊዜ በጥቂት ወራት አንዳንዴም በአመታት ጊዜ ዉስጥ ፀጉር እንደገና ሊበቅል ይችላል፤ ነገር ግን ዳግም የመብቀል እድል በተከሰተዉ ምልጠት መጠን ይወሰናል፤ መጠኑ አነስተኛ የሆነ ላሽ በአንድ አመት ዉስጥ ሙሉ ለሙሉ የመብቀል እድል ከፍተኛ ሲሆን ከግማሽ በላይ የሚሆን የፀጉር መመለጥ መልሶ የመብቀል እድሉ አናሳ ነዉ፡፡ ዳግም የሚበቅለዉ ፀጉር ነጭ ሊሆን ይችላል፡፡ ላሽ በህክምና ይድናል ላሽ ሙሉ በሙሉ ፈዉስ የለዉም፤ መጠነኛ ላሽ ካለባቸዉ 5 ሰዎች ዉስጥ 4ቱ በአንድ አመት ጊዜ ዉስጥ ያለምንም ህክምና ፀጉራቸዉ ሙሉ በሙሉ ሊበቅል ይችላል፡፡ ነገር ግን ከመነሻዉ ሰፋ ያለ የፀጉር መመለጥ ያጋጠማቸዉ ሰዎች ዳግም የመብቀል እድል ሰፊ አይደለም፡፡ ለላሽ የሚሰጡ ህክምና አይነቶች የሚከተሉት ናቸው:: • Steroid creams and scalp applications - በቀን ሁለት ጊዜ መላጣ ቦታዎች ሊይ ይቀባል • Local steroid injections - በመርፌ የሚሰጠዉ መድሐኒት በ 4-6 ሳምንት ዉስጥ ይደገማል፤ ይህ መድሐኒት የቆዳ መሰርጎድ (መሳሳት) ሊያስከትል ይችላል) • Steroid tablets - ይህ በኪኒን መልክ የሚሰጥ • Dithranol cream • Contact sensitisation treatment. • Ultraviolet light treatment (PUVA • Minoxidil lotion • Immunosuppressant tablets include sulfasalazine, methotrexate, ciclosporin, and azathioprine.. • Tofacitinib and ruloxitinib ጠቃሚ መረጃዎች ------------------ • ወንዶች ፀጉራቸዉ እስኪበቅል ድረስ ቀሪዉን ፀጉር መላጨት ጥሩ ስሜት ይፈጥራል፤ የራስ ቅል ቆዳ ለፀሃይ ብርሃን እንዳይጎዳ መሸፈን አስፈሊጊ ነዉ • ሴቶች ፀጉራቸዉ እስኪበቅል በዊግ መሸፈን ምንም ጉዳት የለዉም፤ የመብቀልን ሂደት አያዉክም፤ በተጨማሪ በጥንቃቄ ዊግ መቀጠል ይቻላል • አርተፊሻል የአይን ሽፋሽፍት፤ ቅንድብ፤ እርሳስ፤ ኩል የመሳሰለትን በጊዜያዊነት መጠቀም ይቻላል • ዳግም የሚበቅለዉ ፀጉር ነጭ በሚሆንበት እና ለረጅም ጊዜ ቀለሙ ሳይስተካከል ከቆየ፤ ይህም የሚረብሸን ከሆነ ጊዜያዊ የፀጉር ቀለም መጠቀም ይቻላል

አልኮልና ሽንት ┈┈•✦•┈┈┈ ☞ አልኮል ስንጎነጭ ሽንት ያመላልሰናል፤ አልኮል መጠጦች በብዛት የሚያሸኑን ለምንድነው? ጤና ላይ ችግር አለውን? መቀነስስ እንችላለን? ለነዚህ ጥያቄዎች ሰርቫይቫል ምላሽ አለውና ያንብቡት። . አልኮል መጠጥ አሻኚ( diuretic) ነው፤ ማለትም አልኮል ስንጠጣ ከጠጣነው በላይ ያሸነናል፤ ይህ የሚሆንበት ምክንያት አልኮል አርጊኒን ቫሶፕረሲን ( arginine vasopressin) ወይም ፀረ-አሸኚ ሆርሞን ( anti-diuretic hormone (ADH)) ላይ ጣልቃ በመግባት ስለሚጨቁነው ነው፤ የዚህ ሆርሞን ስራ ኩላሊታችን ውኃን ወደ ደም እንዲመለስ ማድረግ ነው፡፡ ነገር ግን በአልኮል_ተፅእኖ ምክንያት በሰውነታችን ውስጥ የሚዘዋወረው ውኃ በኩላሊት አማካኝነት ወደ ደም በመመለስ ፋንታ በሽንት መልክ እንዲወጣ ይገደዳል፡፡ . አልኮል በተጎነጨን ቁጥር ሂደቱ እየተደመረ የምንሸናውም እየጨመረ ይሄዳል፤ ይህ ሂደት በሰውነት ላይ የፈሳሽ ብክነት( dehydration ) እንዲፈጠር ያደርጋል። ምክንያቱም ውኃ ወደ ደም እንዲመለስ፣ ኩላሊት ላይ ተፅእኖ የሚፈጥረው ሆርሞን(ADH) ተጨቁኖ ስለሚገኝ ነው፡፡ ሌላኛው ምክንያት ደግሞ አልኮል የሽንት ፊኛን የማነሳሳት ባሕሪ አለው፤ በመሆኑም በቂ የሆነ ሽንት እንኳን በፊኛችን ባይኖረንም የሽንት መጣሁ ስሜት እንዲኖረን ያደርጋል፡፡ . ☞ ሽንት የሚመረትበት አንፃረ ጊዜ ምን ያክል ነው? ❤በጤናማ ጊዜያት አንድ ሰው በሰዓት ከ60-80 ሚሊ ሊትር ሽንት ያመርታል፤ ነገር ግን # አልኮል ስንጎነጭ ተጨማሪ 120 ሚሊ ሊትር ሽንት እንዲመረት ያደርጋል፤ ዝቅተኛ የውኃ መጠን ሰውነታችን እያለው ወይም ተጠምተን እያለ በላዩ ላይ አልኮል መጠጣት፣ ሰውነታችን ውስጥ ሊቆይ ይገባ የነበረውን ውኃ በሽንት መልክ እንዲወጣ ስለሚደርግ፣ የውኃ ድርቀት( dehydrated) ሁኔታ ይፈጠርብናል፡፡ በአልኮል መጠጥ ላይ በተጨማሪ የማላብና ❤የማስመለስ ሁኔታ ካለ የምናጣው የሰውነት ፈሳሽ በእጅጉ ይጨምራል፡፡የሰውነት ፈሳሽ ብክነትን ለመቀነስ አልኮል ከመጠጣት በፊት ውኃ በመጠጣት በጥሩ ይዘት ( hydrated) ላይ መገኘት ጥቅም ያለው ቢሆንም ዞሮ ዞሮ አልኮል ስንጎነጭ የሽንት ሂደት እንዲወጣ ስለሚያደርገው አልኮል ላይ ከቆየን የሰውነት # ውኃ_ድርቀት መፈጠሩ አይቀርም፡፡ . ☞ ይህንን ሁኔታ መቀነስ እንችላለን ወይ? አልኮል ስንጎነጭ ጎን ለጎን ውኃ ወይም ለስላሳ መጠጦች መጠጣት በአልኮል አማካኝነት የምናጣውን የሰውነት ፈሳሽ # በግማሽ ሊቀንስ ይችላል፤ የሰውነት ፈሳሽ መጠን ከተጠበቀ በቀጣይ ቀን የሚፈጠረው ❤ የሃንጎቨር ሁኔታም ሊቀንስ ይችላል፤ ነገር ግን ምንም እንኳን አልኮል በብዛት እየተጎነጨን ጎን ለጎን ውኃ መጠጣታችንን ብንቀጥልም የሰውነት ፈሳሽ ብክነት ማጋጠሙ አይቀርም፤ ምክንያቱም ኩላሊት ውኃውን ወደ ደምና አባላተ-አካላት ለመመለስ በአልኮል ተፅእኖ ስለሚደርስበት በቆይታ ጊዜ የሰውነት ውኃ በሽንት መባከኑ አይቀርም፡፡ . በመሆኑም አንድ ሰው ያለውኃ አልኮል መጠጥ ብቻ እየጠጣ ብዙ ሊቆይ አይችልም፤ ምክንያቱም የሰውነት ፈሳሽ በሙሉ በመባከን ሊሞት ይችላልና፡፡ የአልኮል ተፅእኖን ለመቀነስ እንዲሁም ሃንግኦቨር ለመቀነስ ❤ በቀጣይ ቀን ውኃ በብዛት መጠጣት በእጅጉ ሊረዳ ይችላል፡፡ እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ @DrSofonias

ኢትዮጵያ : ሦስተኛው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ተከሰተ #Ethiopia | ሦስተኛው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ መከሰቱን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ተደሰ ገለጹ። ዶክተር ሊያ በኢትዮጵያ ባሳለፍነው ሳምንት ብቻ 5 ሺህ 547 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተናግረዋል፡፡ በአንድ ቀን ውስጥ ከ1ሺህ በላይ ሰዎች መያዛቸውን የገለጹት ሚኒስትሯ÷ የወረርሽኙ መጠን ከዚህ በፊት ካለው በእጅጉ መጨመሩን ተናግረዋል። የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በአሁኑ ሰአት ቫይረሱ የሚገኝበት ሰው ቁጥር ምጣኔ በእጅጉ መጨመሩ የሚያሳየው ሦስተኛው የኮቪድ 19 መረርሽኝ በኢትዮጵያ መከሰቱን እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡ ማህበረሰቡም ከዚህ በፊት የሚያደርገውን ጥንቃቄ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ሚኒስትሯ አሳስበዋል፡፡

የሞተ ሰው አንገቱ ረጅም ነው። =================== የሰውለሰው ድራማ የመጨረሻ ክፍል የመጨረሻ ትእይንት ላይ አንድ ሰው መቃብር ቦታ ቆሞ የህይወት ታሪክ (Eulogy) ያነባል። "....አቶ አስናቀ አሸብር ፈሪሀ እግዚአብሄር ልዩ መታወቂያቸው የሆነ ትልቅ ትንሹን በታላቅ ትህትና የሚያከብሩ የተቸገረ ሰው አይተው ማለፍ የማይሆንላቸው ደግና ሩህሩህ ሰው ነበሩ።" በሀገራችን ረጅም አንገት የውበት ምልክት ተደርጎ ስለሚወሰድ በህይወት ሲኖር ሰውየው አንገቱ ረጅምም ይሁን አጭር ሲሞት ግን "አንገቱ ረጅም ነው።" ይባላል። በላቲን De mortuis nil nisi bene ይላሉ። ስለሞተ ሰው ጥሩ ያልሆነ ነገር መወራት የለበትም አይነት። የምንወደው ሰው በሞት ሲለየን መልካም ጎኑ በከፍተኛ ጉልበት ወደ ትዝታችን ስለሚመጣ ጥሩ ያልሆኑ ነገሮቹን ለማስታወስ የሚተርፍ ጉልበት አይኖረንም። አብረን እያለን ብዙ ስሜት የማይሰጡን ነገሮች በሞት ከተለየን በኋላ ትዝ ሲለን የስሜት ጉልበቱ ከፍተኛ(hypercathected) ነው። ትዝታ የሚባለው የሙዚቃ ቅኝት በሞት ወይም በሌላ ምክኒያት የተለዩትን ሰው ሲያስቡ የሚኖረው የስሜት ግፊት የወለደው ስልት ነው። "...ባስታወስኩሽ ቁጥር እንደዚህ መሆኔ፣ ምን ይሁን ሚስጥሩ አልገባኝም እኔ።" ጌታቸው ካሳ "...የናፍቆት ፈረሱ የፍቅር መጓዣው፣ ትዝታ ብቻ ናት የሰው ልቡን መግዣ።" ማህሙድ አህመድ። ሰዎች ሙት ወቃሽ መሆን የማይፈልጉበት ሌላኛው ምክንያት ራሱን የማይከላከል፣ የማይሞግትን ሰው መውቀስ ፍትሀዊ አይደለም ከሚል መነሻ ይመስላል። የምንወደው ሰው እንደተለየን ከእውነታው ባለፈ ሁኔታ ጥሩ ጎኑን ብቻ ማስታወስ ተፈጥሯዊ ነው። ጊዜ እያለፈ ሀዘን እየቀነሰ ሲመጣ የተለይንን ሰው ጥሩ ጎን እንዲሁም ጥሩ ያልሆነውንም ማስታወስ እንችላለን

"ሚስቴን በጣም ስለምወዳት ከእሷ ጋር አይቆምብኝም።" ==================================== ከሚወዷት ፍቅረኛ ወይም ሚስት ጋር የብልት አለመቆምና በተቃራኒው ከሴተኛ አዳሪ ጋር ምንም ስንፈት አለመኖር ማዶና ፑታና ኮምሌክስ (Madonna Putana Complex) የሚባል የስንፈተ ወሲብ አይነት ነው። ይህ ክስተት በተለይ ሚስቶች ልጅ ከወለዱ በኋላ የመከሰት እድሉ ከፍ ያለ ነው። ይህ ስነ ልቦናዊ ኮምፕሌክስ ያለባቸው ሰዎች የፍቅር ስሜት ላላቸው ሰው የሴክስ ፍላጎት አይኖራቸውም፡፡ "በጣም ስለምወዳትና ስለምሳሳላት ለሷ የሴክስ ፍላጎት አይመጣልኝም።" ይላሉ። የሴክስ ፍላጎት ላላቸው ሰው ደግሞ የፍቅር ስሜት የላቸውም፡፡ መንስኤው በልጅነት ሴክስ እንደባለጌ ነገር በተደጋጋሚ ሲነገራቸው አእምሯቸው ውስጥ ሴክስና ፍቅር ሳይዋሀዱ እንደ ዘይት እና ውሀ ሳይዋሀዱ ሲቀመጡ የሚፈጠር ነው። እነዚህ ሰዎች ሴቶችን ሁሉ በሁለት ይከፍላሉ፡፡ ንፅህት እና ባለጌ፡፡ የሚሰማቸውም ፍቅር በሁለት የተከፈለ ነው፡፡ ንፁህ ፍቅርና የብልግና፡፡ ሚስቶቻቸው ልጅ ከወለዱ በኃላ እንደ ሚስት ሳይሆን እንደ እናት ማየት ይጀምራሉ፡፡ ሴክስ ፎሮይድ እንደሚለው ሁሉንም ፀባይ የሚወስን አይሁን እንጂ ከአካላዊ ድርጊቱ ግን የዘለለ ስነ ልቦናዊ እና መንፈሳዊ ትርጉም ያለው እንደሆነ እርግጥ ነው፡፡ ሴክስ 'ባለጌ ነገር' እየተባለ በሚነገርበት ሁኔታ ውስጥ ማደግ የሚያስከትለው ተፅዕኖ ምን ይሆን? ሴክስ አብዛኛው ነገሩ የሚካሄደው በእግሮች መሀል ሳይሆን በጆሮዎች መሀል (አእምሮ ውስጥ) ነው፡፡

ገና ከመወለዱ ሱስ አስቸገረው! ==================== ሲወለድ ክብደቱም ሆነ ጤንነቱ ኖርማል ነው። ድንቡሽቡሽ ያለ ነው። በሁለተኛው ቀን "እሪ" ብሎ ማልቀስ ጀመረ። እናቱ ብታባብለው ብታባ
ገና ከመወለዱ ሱስ አስቸገረው! ==================== ሲወለድ ክብደቱም ሆነ ጤንነቱ ኖርማል ነው። ድንቡሽቡሽ ያለ ነው። በሁለተኛው ቀን "እሪ" ብሎ ማልቀስ ጀመረ። እናቱ ብታባብለው ብታባብለው ለቅሶው አልቆም አለ። በተደጋጋሚ አስመለሰው። ላብበላብ ሆነ። ሰውነቱ መንቀጥቀጥ ጀመረ። ሀኪሞቹ ያሉትን ምርመራዎች ሁሉ ቢሰሩለትም ምንም ሊገኝ አልቻለም። እናቱንም መመርመር ጀመሩ። ከዛ እሷ ሄሮይን የተባለው ዕፅ ሱሰኛ እንደሆነች ደረሱበት። ለካ ህፃኑ ማህፀን ውስጥ እያለ እናቱ ሄሮይን ስትጠቀም እሱም በደሟ አማካኝነት ይደርሰው ነበር። ከተወለደ በኋላ ግን ወተት ውስጥ መጠኑ በጣም ዝቅተኛ ስለሆነ የለመደውን አላገኘም። ገና ከመወለዱ ሱስ አስቸገረው። እናቶች የሚወስዷቸው ሱስ አስያዥ ነገሮች (ከቡና ጀምሮ) ከእነሱ አልፎ ልጆች ላይም ተፅእኖ እንደሚያደርስ አስታውሶ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም! ዶ/ር ዮናስ ላቀው

✍ #ብጉር 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ ⏩ #ብጉር በቆዳ ላይ የሚገኙ የፀጉር ቀዳዳዎች በቅባት እና በሞቱ የቆዳ ሴሎች ሲሞሉ ወይም ሲደፈኑ የሚከሰት የቆዳ ችግር ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ ብጉር ነጭ ወይም ጥቁር ጫፍ አንዳንዴም ቀያይ ነጠብጣቦች በቆዳ ላይ ሊታዩ ይችላሉ፡፡ ነጠባጣቦቹ መጠናቸው ሊለያይ ይችላል፤ ህመም ሊኖራቸውም ላይኖራቸውም ይችላል፡፡ ብዙውን ጊዜ ብጉር በፊት ላይ የሚወጣ ቢሆንም በአንገት፣ ደረት፣ ትከሻ እና ጀርባም ላይ ሊወጣ ይችላል፡፡ ⏩ #ብጉር በማንኛውም ሰው ላይ ሊያጋጥም የሚችል ነው፡፡በአብዛኛውን ግን ብጉር በጉርምስና ወይም በወጣትነት እድሜ ውስጥ ያሉት ላይ ይበረታል፡፡ በሂህ ጊዜ የመጣ ከሆነ እድሜ በጨመረ ቁጥር እየቀነሰ ሲመጣ ጥቂቶች ላይ ግን አብሮአቸው ይኖራል፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ግን አንዳንድ ጊዜ ብጉር በሆርሞን ችግር ምክንያት ህፃናት ላይ ሊታይ ይችላል፤ በእርግዝናም ወቅት የመከሰት እድል አለው፡፡ ⏩ #ምልክቶቹ 🔺 ነጭ/ ጥቁር ጫፍ ያላቸው ነጠብጣቦች 🔺 ትናንሽ ቀያይ ህመም ያላቸው ነጠብጣቦች 🔺 ቀያይ ጫፍ ላይ ትንሽ መግል ያላቸው ነጠብጣቦች 🔺 ተለቅ ያሉ ጠጣር ህመም ያላቸው እብጠቶች 🔺 ህመም ያላቸው መግል የያዙ ከቆዳ ስር ያሉ እባጮች ⏩ #ብጉር #መንስኤው 🔺 ቅባትማ የቆዳ አይነት መኖር 🔺 የፀጉር ቀዳዳዎች በቅባት እና በሞቱ ሴሎች መዘጋት 🔺 ባክቴሪያዎች 🔺 የአንዳንድ ሆርሞኖች ስራ መጨመር (ለምሳሌ Androgen) ⏩ #ብጉር ቅባት አመንጪ እጢዎች (Sebaceous gland) በሚበዙበት የቆዳ ክፍል አካባቢ ነው የሚወጣው፡፡ እነዚህም ፊት፣ ግንባር፣ ደረት፣ የላይኛው የጀርባ ክፍል እና ትከሻን ያጠቃልላል፡፡ ⏩ #የፀጉር ቀዳዳዎች ከቅባት አመንጪ እጢዎች ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡ የእነዚህ ቀዳዳዎች ግርግዳ ሲያብጡ ነጣ ያለ አናት ይኖራቸዋል፤ ወይም ደግሞ አናታቸው ክፍት ከሆነ ሲጠቁር ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ ቀዳዳዎቹ በባክቴሪያ እና ቅባት ይሞላሉ፡፡ ⏩ #ቀያይ ከፍ ከፍ ያሉ ውስጣቸው ነጭ የሆኑ ነጠብጣቦች የሚፈጠሩት ደግሞ የፀጉር ቀዳዳዎች በቅባት ከመዘጋታቸው በላይ በባክቴሪያ ሲጠቁ ነው፡፡ ⏩ #ብጉርን #ምን #ሊያባብሰው #ይችላል? 🔺 የሆርሞን መለዋወጥ ወይም መዛባት 🔺 አንዳንድ መድሐኒቶች 🔺 አመጋገብ (የተጠበሱ ምግቦች፣ በካርቦሀይድሬት የበለፀጉ ምግቦች) 🔺 ጭንቀት ወይም ውጥረት 🔺 ሸካራ ሳሙና መጠቀም እና በጣም የሞቀ ውሃ መጠቀም 🔺 የፀጉርና ቆዳ መጠበቂያ ውጤቶች በተለይ በውስጣቸው የሚያሳክክ ንጥረ ነገር የያዙ ከሆነ ⏩ #ተጋላጭነት #የሚጨምሩ #ሁኔታዎች 🔺 የጉርምስና የእድሜ ክልል 🔺 የሆርሞን መዛባት 🔺 የዘር ተጋላጭነት 🔺 ቅባትማ ነገሮችን በቆዳ ላይ መጠቀም 🔺 ቆዳን የሚፈገፍጉ (የሚፈትጉ) ነገሮች 🔺 ጭንቀት ⏩ #ብጉርን #መከላከል #ይቻላል? 🔺 ብጉርን በዘላቂነት መከላከል ባይቻልም እንዳይባባስ የሚወሰድ እርምጃዎችና ጥንቃቄዎች ግን አሉ። ከነዚህም መካከል፦ 🔺 በዝግታ ወይም በጣም ሳያሹ መታጠብ ለቆዳዎ ጤንነት አስፈላጊ ነው። በጣም ማሸት፣ መጥረግ፣ መፈተግ ወይም መፈግፈግ ተገቢ አይደለም። 🔺 በጣም እንዳያልብዎ መጠንቀቅ። ላብ እንዲያልበን የሚያደርጉ እንቅስቃሴዎች ካደረግን በኋላ ወዲያው መታጠብ። 🔺 ፀጉርዎ ቅባት ካለው ወይም ከበዛበት መታጠብ 🔺 ጭንቀትን አለማብዛት 🔺 አንዳንድ የፀጉር መንከባከቢያ ምርቶችን መጠቀም ማቆም፤ እንደ ጄል፣ ክሬምና የመሳሰሉት 🔺 ፊትዎን ቶሎ ቶሎ ከመንካት መቆጠብ 🔺 ለስላሳ የኮተን ልብሶችን መጠቀም፤ በተለይ ከቆዳ ጋር ንክኪ ያላቸው ከሆነ 🔺 ከቅባት እና ኬሚካል ጋር ያለዎትን ግንኙነት መቀነስ ለምሳሌ እንደ ፔትሮሊየም ያሉትን 👉👉 #ስለ ብጉር ችግር ከባለሙያ ጋር ይማከሩ !ለመማከር 8809 ላይ ይደውሉ ! ከጧት 2፡00 ሰዓት እስከ ማታ 2፡00 ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ የጤና ባለሙያዎች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!! (በጤና ባለሙያ ከድጃ )

በድጋሚ የተፖሰተ ዶክተር ሶፎኒያስ ኤርሚያስ ነኝ ቪማክስ የስንፈተ ወሲብ መዳኒት ብዙዎቻቹ በ inbox የምትጠይቁኝ ነገር ነው vimax ስለሚባለው የስንፈተ ወሲብ መዳኒት ትንሽ ነገር ልበል እንደምታውቁት በማህበራዊ ሚድያ ብስፋት የሚያስተዋዉቁት ነገር ነው። ከማህበራዊ ሚድያ ደሞ እውነተኛ ነገር ማግኘት አዳጋች ነገር ነው እናም ዝም ብላቹ ከፊስቡክ ወይም ከቴሌግራም የሚለቀቁትን ማስታወቅያዎች አምናቹ ምንም አይነት መዳኒት ባትገዙ ጥሩ ነው በጣም አደገኛ ሊሆንባቹ ይችላል በተለይ የዉስጥ ደዌ ችግሮች ያሉባቹ በጣም መጠንቀቅ ይኖርባቹሃል የህክምና ባለሞያዎን ማመከር አለባቹ የወንድ ብልት ያለመቆም ችግር ምልክቶች የብልት አልቆም ማለት የብልት ቆሞ ያለመቆየት/ ቶሎ መልፈስፈስ የግብረ ስጋ ግንኙነት ፍላጎት መቀነስ የቁመት ማጠር እና/ የመቀጠን ችግር ቶሎ የመጨረስ ችግር በአጠቃላይ ከለይ የጠቀስኳቸው የስንፍፈተ ወሲብ ችግሮች እንዳለባቹ ካረጋገጣቹ ችግሩን በህክምና ሞክራቹ ለዉጥ ከሌለዉ ደግሞ ሌሎች ስንፈተ ወሲብን ሊያክሙ የሚችሉ መድሃኒቶች አሉ ግን ኬት ማግኘት እንዳለባቹና የትኞቹ ናቸው ትክክለኛና ፈዋሽ የሆኑትን ማወቅ ይኖርባቹኃል ቢያንስ ቢያንስ ስለ መዳኒቶቹ Google ላይ ማጣራት እና Original ምን አይነት እንደሆነ መለየት ትችላላቹ የጎንዮሽ ጉዳቱቹ ምንምን እንደሆኑ Google ይነግራቹኃል በህክምና ሞክራቹ ወይም ሀኪም ማማከር ፈርታቹ መዳኒት ለመጠቀም የምትፈልጉ በጥያቅያቹ መሰረት ስለ Vimax የተወሰነ ነገር ልበላቹ እና ኬት እንደምታገኙ አድራሻ ለምትጠይቁኝ ሰጣቹኃለው Vimax Originally የካናዳ ምርት ሲሆን ጥቅሞቹ 1 የብልት አልቆም ማለት ቆሞ ያለመቆየት ቶሎ መልፈስፈስ ችር ላለበት 2 የቁመት እና የዉፍርት ችግር 3 ቶሎ የመጨርስ ችገር/የዘር ፈሳሽ የማምለጥ vimax አወሳሰድ/አጠቃቀም እንዷ ብልቃጥ 60capsule/60እንክብል ነው ምቲዘው ባለ 30capsule የምቲዝም አለች ግን እኔ የማወራው ስለ original ነው አወሳሰዱ በቀን አንድ አንድ ቢሆን ይመከራል በቀን ሁለት ሁለትም መውስድ ይቻላል። Side Effect/የጎንዮሽ ጉዳት እነሱ እንደሚሉት ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት አያመጣም ይበሉ እንጅ እኔ ከማቃቸው ተጠቃሚዎች እንደተረዳሁት የጨጓራ በሽታ ያለባቸው ላይ ለመጠቀም አስቸጋሪ ነው ነግር ግን ጎን ለጎን የጨጓራ መዳኒት እየወሰዱ የሚጨርሱም አሉ ከዚ ዉጪ ሌላ ምንም አይነት ጎዳት የለዉም አንድ አንዶች ላይ አላርጂክ ከሞሆን በስተቀር። የሚከለክላቸው ነገሮች መዳኒቱን መጠቀም ከጀመራቹ መዉሰድ/መጠቀም የሌለባቹህ ነገሮች .አልኮል/አረቄ ነገሮች ናቸው። መዳኒቶቹን መግዛት የምትፈልጉ እኔ ትክክለኛው Original Vimax አስመጪዎችን ስልካቸውን ልሰጣቹህ እችላለው መዳኒቱ ሀገር ዉስጥ እንዲሸጥ ገና ፍቃድ ስላላገኘ በዚም ምክንያት ዋጋው በጣም የተጋነነ ነው በዛ ላይ አስመጪዎቹ እየሸጡ ከተያዙ ወይም እጃቸው ላይ ከተገኘ የሚቀጡ ነው የሚሆኑት እናም ብዙ ጊዜ እራሳቸውን ደብቀው ነው የሚሸጡት ነገር ግን እኔ በትክክል ስለማዉቃቸው ችግር አይኖርም መዳኒቱም ፍቃድ ሊያገኝ በሂደት ላይም ስለሆን ብዙም አያሳስብም። በተጨማሪም የኔ ምክር ነው ጫት እየቃማቹ መዳኒቱን ባትወስዱ/ባትጠቀሙ ጥሩ ነው ቢያንስ መዳኒቱን እስክጨርሱ ጫቱን ብተዉት እላለው ስለ ጫት የጎንዮሽ ጉዳቶች በቅርቡ ፅፍላቹኃለው የአስመጪዎችን ስልክ እና አድራሻ በብዛት inbox ላይ ስትጠይቁኝ የነበራቹ ስልካቸው 0992484672 በ inbox ለማግኘት https://t.me/Sellerman12 አመሰግናለው እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ https://t.me/DrSofonias https://t.me/DrSofonias

በድጋሚ የተፖሰተ ዶክተር ሶፎኒያስ ኤርሚያስ ነኝ ቪማክስ የስንፈተ ወሲብ መዳኒት ብዙዎቻቹ በ inbox የምትጠይቁኝ ነገር ነው vimax ስለሚባለው የስንፈተ ወሲብ መዳኒት ትንሽ ነገር ልበል እንደምታ
በድጋሚ የተፖሰተ ዶክተር ሶፎኒያስ ኤርሚያስ ነኝ ቪማክስ የስንፈተ ወሲብ መዳኒት ብዙዎቻቹ በ inbox የምትጠይቁኝ ነገር ነው vimax ስለሚባለው የስንፈተ ወሲብ መዳኒት ትንሽ ነገር ልበል እንደምታውቁት በማህበራዊ ሚድያ ብስፋት የሚያስተዋዉቁት ነገር ነው። ከማህበራዊ ሚድያ ደሞ እውነተኛ ነገር ማግኘት አዳጋች ነገር ነው እናም ዝም ብላቹ ከፊስቡክ ወይም ከቴሌግራም የሚለቀቁትን ማስታወቅያዎች አምናቹ ምንም አይነት መዳኒት ባትገዙ ጥሩ ነው በጣም አደገኛ ሊሆንባቹ ይችላል በተለይ የዉስጥ ደዌ ችግሮች ያሉባቹ በጣም መጠንቀቅ ይኖርባቹሃል የህክምና ባለሞያዎን ማመከር አለባቹ የወንድ ብልት ያለመቆም ችግር ምልክቶች የብልት አልቆም ማለት የብልት ቆሞ ያለመቆየት/ ቶሎ መልፈስፈስ የግብረ ስጋ ግንኙነት ፍላጎት መቀነስ የቁመት ማጠር እና/ የመቀጠን ችግር ቶሎ የመጨረስ ችግር በአጠቃላይ ከለይ የጠቀስኳቸው የስንፍፈተ ወሲብ ችግሮች እንዳለባቹ ካረጋገጣቹ ችግሩን በህክምና ሞክራቹ ለዉጥ ከሌለዉ ደግሞ ሌሎች ስንፈተ ወሲብን ሊያክሙ የሚችሉ መድሃኒቶች አሉ ግን ኬት ማግኘት እንዳለባቹና የትኞቹ ናቸው ትክክለኛና ፈዋሽ የሆኑትን ማወቅ ይኖርባቹኃል ቢያንስ ቢያንስ ስለ መዳኒቶቹ Google ላይ ማጣራት እና Original ምን አይነት እንደሆነ መለየት ትችላላቹ የጎንዮሽ ጉዳቱቹ ምንምን እንደሆኑ Google ይነግራቹኃል በህክምና ሞክራቹ ወይም ሀኪም ማማከር ፈርታቹ መዳኒት ለመጠቀም የምትፈልጉ በጥያቅያቹ መሰረት ስለ Vimax የተወሰነ ነገር ልበላቹ እና ኬት እንደምታገኙ አድራሻ ለምትጠይቁኝ ሰጣቹኃለው Vimax Originally የካናዳ ምርት ሲሆን ጥቅሞቹ 1 የብልት አልቆም ማለት ቆሞ ያለመቆየት ቶሎ መልፈስፈስ ችር ላለበት 2 የቁመት እና የዉፍርት ችግር 3 ቶሎ የመጨርስ ችገር/የዘር ፈሳሽ የማም

የግል ሐኪምዎ የሆነው ሙዝ! 👉በስትሮክ የመሞት አደጋን ከ50-60 በመቶ ለመቀነስ ያስችላል!!! 👉ለስኳር ህመምና ለደም ማነስ ሙዝን መመገብ ይመከራል! በኢትዮጵያ እንደተገኘ የሚነገርለትና በዓለማችን በስፋት እየተመረተ ለምግብነት የሚውለው ሙዝ እጅግ በርካታ ጠቀሜታዎች አሉት፡፡ ሙዝ ከምግብ ይዘቱ በተጨማሪ ለተለያዩ በሽታዎች ፈውስ ሊያስገኙ የሚችሉ ንጥረ ነገሮችንም አካቶ ይዟል። ብዙዎቻችን ሙዝን ለምግብነት በማዋል ለሰውነታችን ሃይልና ሙቀት ለማግኘት እንደምንችል ከማወቅ የዘለለ ነገር አስበን አናውቅም፡፡ ነገር ግን ሙዝ በውስጡ የያዛቸው ተፈጥሮአዊ የስኳር ወይም የጣፋጭ ምንጭ የሆኑት ግሉኮስ፣ ስክሮስ፣ እና ፍሩክቶስ የተባሉት ንጥረነገራት ከሙዝ የፋይበር (የቃጫነት) ተፈጥሮ ጋር ተዳምረው መጠነሰፊ ጠቀሜታዎችን ይሰጣሉ። ከበርካታ የሙዝ ጠቀሜታዎች መካከል ጥቂቶቹን ከዚህ እንደሚከተለው ለማየት እንሞክራለን፡፡ ♦1. ለአእምሮ እድገት ሙዝ በውስጡ ከፍተኛ የፖታሺየም ንጥረነገርን ይዟል፡፡ ይህም ንጥረ ነገር የአንጐልን የሥራ ብቃት ለማሻሻል እና ለማሳደግ እንዲሁም ንቁና ጤናማ አዕምሮ እንዲኖረን በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ ♦2. ለስትሮክ በሙዝ ውስጥ ያለው ፖታሺየም፣ የደም ሥርዓትን በማስተካከል ባልታሰበ ሁኔታና በድንገት የሚከሰተውን የስትሮክ ችግር ለመከላከል ያግዛል። ሙዝ በሰው ልጆች የአመጋገብ ሥርዓት ውስጥ ተካቶ ዘወትር ለምግብነት የሚውል ከሆነ፣ በስትሮክ ምክንያት የሚመጣውን ድንገተኛ ሞትና የአካል ጉዳት ከ50-60 በመቶ ለመቀነስ ያስችላል፡፡ ♦3. ለደም ግፊት ሙዝ በተፈጥሮው በውስጡ የሚይዘው ዝቅተኛ የጨው መጠን በመሆኑ የደም ግፊትን ለማረጋጋት ይረዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በውስጡ ያለው ፖታሺየም የደም ግፊትን ለማስተካከልና በግፊት ሳቢያ የሚከሰቱ ከባድ የጤና ችግሮችን ለመከላከል ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ ♦4. ለጨጓራ ህመም አብዛኛዎቻችን ሙዝ ከበድ ያለ ምግብ እንደሆነ በማሰብ፣ ሙዝ የጨጓራ ህመማችንን እንደሚያባብስብን ስንናገር እንደመጣለን፡፡ ይሁን እንጂ ሙዝ ለጨጓራ ችግሮች ሁነኛ መፍትሔ ነው። ሙዝ በባህርይው በጣም ለስላሳ በመሆኑ በጨጓራ ላይ መጨናነቅን የማይፈጥር ሲሆን የጨጓራ አካባቢን በመሸፈን፣ የጨጓራ ውስጥ አሲድን በማስተካከልና በማመጣጠን የጨጓራ ቁስለት እንዳይፈጠር ለማድረግ ያስችላል፡፡ ♦5. ለድብርት ሙዝ በውስጡ የሚይዘውና ትራይፕቶፋን የተባለው ንጥረ ነገር በሰውነታችን ውስጥ ሴሮቶኒን የባለ ሆርሞን እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡ ይህ ሆርሞን አይነተኛ ተግባሩ ሰውነታችንን ከድካምና ከድብርት በማላቀቅ ወደተሻለ ስሜት ውስጥ እንድንገባ ማድረግ ነው፡፡ ♦6. ለሆድ ድርቀት በሙዝ ውስጥ የሚገኘው ፋይበር ለምግብ መፍጨት ሥርዓታችን ከፍተኛ ጠቀሜታን ይሰጣል፡፡ የምግብ መፍጨት ሥርዓትን የሚያከናውኑት የሰውነታችን ክፍሎች በቂ የውሃ መጠን እንዲኖራቸው በማድረግ ሆድ ድርቀትን ይከላከላል፡፡ አንጀት የተለሳለሰ እንዲሆን በማድረግ ከሰውነታችን መውጣት የሚገባቸው አላስፈላጊ ነገሮች (ቆሻሻዎች) እንዲወገዱ ለማድረግ ይረዳል፡፡ ♦7. ለስኳር ህመም ሙዝ በውስጡ ከፍተኛ ቫይታሚን B6 የያዘ ነው። ይህም በደም ውስጥ የሚኖረውን ከፍተኛ የስኳር መጠን እንዲቀንስ በማድረግ፣ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘውን የስኳር መጠን ለመቆጣጠር ያስችለናል፡፡ ከስኳር መብዛት ጋር ተያይዞ የሚከሰተውን የጠዋት ህመምንም ያስቀራል፡፡ ♦8. ሙዝና ደም ማነስ በሙዝ ውስጥ የሚገኘው የብረት ማዕድን ጠቀሜታው በደማችን ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው የሔሞግሎቢን ምርት እንዲኖር ማድረግ ነው፡፡ ይህም በሔሞግሎቢን እጥረት ሳቢያ የሚከሰተውን የደም ማነስ እንዳይከሰት ያደርጋል፡፡ ♦9. ሙዝ ለስካር ሙዝ ከወተትና ከማር ጋር ተደባልቆ ለምግብነት ሲውል በከፍተኛ መጠጥ ወይም በስካር ሳቢያ የሚከሰትን ሃንግኦቨር (ያደረ ድምር) በቀላሉ ያስወግዳል፡፡ በመጠጥ ሳቢያ የተጐዳን ሰውነት እንዲነቃቃና ብርታት እንዲያገኝ በማድረግ ረገድም ሙዝ ከፍተኛ ሚናን ይጫወታል፡፡ የሲጋራ እና መሰል ሱሶች ተጠቂ የሆኑ ሰዎች ሱሱን ለማቆም እንዲችሉ ሙዝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡ ♦10. ለሞቃታማ አየር በሞቃታማ የአየር ንብረት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ሙዝን ቢመገቡ ሰውነታቸው ሙቀቱን እንዲቋቋም በማድረግ፣ የተረጋጋና የተስተካከለ የሰውነት ሙቀት እንዲኖረን ያደርገናል፡፡ ♦11. የሙዝ ተጨማሪ ጠቀሜታዎች በወባ ትንኝ የተነደፈ ሰው ወይንም በማንኛውም ተናካሽ ወይም ተናዳፊ ነፍሳት የተነደፈ (የተነከሰ) ሰው በሙዝ ልጣጭ የውስጠኛው ክፍል የተነደፈበትን (የተነከሰበትን) ቦታ በደንብ በማሸት እብጠቱን መቀነስ ይችላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ንድፍያው (ንክሻው) የፈጠረበትን የማቃጠልና የመለብለብ ስሜት ለማስወገድ ይችላል፡፡ 👉 ጫማዎን ከጠረጉና ቆሻሻውን ካስወገዱ በኋላ በሙዝ ልጣጭ ቢወለውሉት ጫማዎ እንደመስታወት ያበራልዎታል። 👉 ፍሪጅዎ መጥፎ ጠረን (ሽታ) ካመጣብዎ አንድ ሁለት ሙዞችን ያስቀምጡበት፡፡ የፍሪጅዎ ጠረን በቅጽበት ይቀየራል፡፡ 👉 ሰውነትዎ በድካም ወይም በህመም ከተጐዳና የምግብ ፍላጐት ከሌለዎ አንድ ሙዝ እንደምንም ይመገቡ፡፡ ሰውነትዎ ሲበረታና የምግብ ፍላጐትዎ ሲጨምር ይታወቅዎታል፡፡ በአጠቃላይ ሁላችንም እንደቀላል የምናየውና ብዙም ትኩረት የማንሰጠው ሙዝ ለከፍተኛ የጤና ችግር የሚዳርጉንን በሽታዎች ለመከላከልና ለማስወገድ ይረዳናል፡፡ ታዲያ ይህን የግል ሐኪምዎ የሆነ ፈዋሽ ፍሬ በፍሪጅ ውስጥ ከተው አያበላሹት፡፡ ንፋስ ያለበት ያልታመቀ አየር ለሙዝ የሚስማማ ነውና - በዚያ ያኑሩት፡፡ ------መረጃ ሐይል ነው! 👉 በሽርፍራፊ ሰከንድ የተሰራች ስህተት የሰውን ህይወት እንደምታጠፋ ሁሉ፡ በሰከንዶች ቅፅበት የደረሰች መረጃ ህይዎትን ለማትረፍ ሰበብ ትሆናለችና እባከዎት የሚለቀቁ ጤናነክ መረጃዎችን ለሌሎች ወገኖች ለማድረስ ሼር ቢያደርጉላቸው መልካምነት ነው፡፡ ተጨማሪ የተለያዩ የጤና ነክ መረጃዎች እንድደርስዎ የቴሌግራም ቻናሌን ይቀላቀሉ @DrSofonias

ፈፅሞ ችላ ልንለው የማይገባ ጉዳይ ማናችንም ቢሆን በዚህ አሳሳቢ ነገር ልብ በሉ ወገኖቼ የጆሮ ኢንፌክሽን የጆሮ ኢንፌክሽን የጆሮን ትቦና የመሀከለኛውን ክፍል ያጠቃል፡፡ ሁለት ዓይነት የጆሮ ኢንፌክሽን ያለ ሲሆን የመሀከለኛው የጆሮን ክፍል የሚያጠቃው ኢንፌክሽንና የጆሮ ትቦ የሚጠቃው ኢንፌክሽን በመባል ይታወቃሉ፡፡ በአጠቃላይ የጆሮ ኢንፌክሽን ምልክቶች 1. ጆሮ ሕመም 2. የመስማት ለውጥ 3. ማቅለሽለሽ 4. ማስታወክ 5. የራስ ምታት 6. ራስ ማዞር 7. ጆሮ አካባቢ እብጠት 8. መግል በጆሮ መውጣት 9. ትኩሳት 10. ማሳከክ ስሜት 11. ኃይለኛ ውጋት ናቸው፡፡ የጆሮ ኢንፌክሽን አምጪና አባባሽ ምክንያቶች 1. የጆሮ ኢንፌክሽን በዋናነት Streptococcus pneumonia በተሰኘ ባክቴሪያ አንዳንዴም በቫይረስ ይመጣል፡፡ 2. ጉንፋን፣ ከጉሮሮ ኢንፌክሽን፣ ከአፍንጫ አለርጂ፣ ከሳይነስ ኢንፌክሽን፣ወይም በአካባቢ ካለ ቁስል ጋር ሊያያዝ ይችላል፡፡ 3. የውስጥ ወይም የውጭ የጆሮ ክፍል ኢንፌክሽን ወይም በጆሮ ከበሮ ላይ በደረሰን አደጋ ሊከሰት ይችላል፡፡ 4. ፍጥነት ካለው ነፋስና ለኃይለኛ ድምፅ መጋለጥ እንዲሁም በጥፊ መመታት የጆሮ ከበሮን አደጋ ላይ የሚጥሉ ሁኔታዎች ለጆሮ ኢንፌክሽን አጋላጭ ምክንያቶ ናቸው፡፡ የሚከተለውን ማድረግ ይጠቅማል 1. በጆሮ ጠብ የሚደረግ ፀረ-ተዋህሲያን መድኃኒት በሐኪም ትዕዛዝ በአግባቡ መውሰድ። 2. ልጆን pneumococcal የተሰኘውን ፀረ-ጆሮ ባክቴሪያ የያዘ ክትባት ወቅትቱን ጠብቀው ማስከተብ። 3. ልጆን ቢችሉ ከ6 ወር በላይ እስከ አንድ ዓመት ጡት ያጥቡ። 4. ከጉንፋን ወይም ከሌላ ሕመም ጋር የተያያዘ ከሆነ ከዋናው በሽታ ጋር እየተሻለ ስለሚሄድ በትዕግስት መጠበቅ። 5. በጆሮ ደም ወይም መግል እየፈሰሰ ከሆነ በአስቸኳይ የሕክምና ባለሙያ ማየት። 6. ጆሮን በንፁሕ ጥጥ መወተፍ። 7. እስከዚያው አስፕሪን ወይም ፓናዶል ሁለት ፍሬ በቀን ሦስት ጊዜ መውሰድ። 8. በጆሮ ምንም ነገር ያለመጨመር። 9. ሲጋራ አያጭሱ ወይም ከሚያጨስ ሰው ይራቁ። 10. አምፒሲሊን (ቴትራሳይክሊን) ሁለት ፍሬ በቀን አራት ጊዜ ለአንድ ሣምንት መውሰድ፡፡ ተጨማሪ የተለያዩ የጤና ነክ መረጃዎች እንድደርስዎ የቴሌግራም ቻናሌን ይቀላቀሉ @DrSofonias