es
Feedback
ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

Ir al canal en Telegram

ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

Mostrar más

📈 Análisis del canal de Telegram ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

El canal ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias (@drsofonias) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 19 967 suscriptores, ocupando la posición 1 154 en la categoría Medicina y el puesto 1 678 en la región Etiopía.

📊 Métricas de audiencia y dinámica

Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 19 967 suscriptores.

Según los últimos datos del 26 junio, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de -547, y en las últimas 24 horas de -20, conservando un alto alcance.

  • Estado de verificación: No verificado
  • Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 24.05%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 7.27% de reacciones respecto al total de suscriptores.
  • Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 4 805 visualizaciones. En el primer día suele acumular 1 453 visualizaciones.
  • Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 9.

📝 Descripción y política de contenido

El autor describe el recurso como un espacio para expresar opiniones subjetivas:
ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 27 junio, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Medicina.

19 967
Suscriptores
-2024 horas
-1217 días
-54730 días
Archivo de publicaciones
የደም አይነት እና አመጋገብ 1) የ ኦ (O)ደም ዓይነት የአመጋገብ ስርዓት ይህ የደም ዓይነት ከሌሎች ቀድሞ የነበረ ጥንታዊ ሲሆን ከእንስሳት አዳኞች የተወረሰ የደም ዓይነት ነው፡፡ የዚህ ደም ባለቤቶች ዓሣ፣ የባህር ምግብ፣ ቀይ ስጋ፣ ጨው፣ ዶሮ፣ ሲኳር ድንችና የመሳሰሉትን ምግቦች እንዲያዘወትሩ ይመከራል፡፡በዚያውም ልክ እንቁላል፣ የእንስሳት ተዋጽኦዎች፣ ስንዴና ባቄላን ከገበታቸው ማራቅ አለባቸው፡፡ 2) የ ኤ (A) ደም ዓይነት የአመጋገብ ስርዓት ይህ የሰው ልጆች ወደ እርሻ ሲገቡ በተፈጠረው የአመጋገብ ለውጥ ምክንያት የተከሰተ የደም ዓይነት ነው፡፡ በዚያ ዘመንም የሰው ልጆች ለመኖነት ፊታቸውን ወደ አትክልቶች በማዞራቸው ምክንያት በጊዜ ሂደት እጅግ የዳበረ የምግብ ማላም ስርዓትን አዳበሩ፡፡ በአንጀታችው ውስጥ የሚገኙት የባክቴሪያዎች ዓይነትና ቁጥርም እጅግ ተበራከተ፡፡ የዚህ ደም ባለቤቶች ፖም፣ አቮካዶ፣ ሰላጣ፣ ካሮት፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ባቄላ፣ እርጎ፣ የስንዴ ዳቦና ፓስታ እንዲመገቡ ይመከራል፡፡ ነገር ግን እንቁላል፣ ስጋ እና ሌሎች የእንስሳት ተዋጽኦዎችን በተገቢው መንገድ ለማብላላት አንጀታቸው አልዳበረም፡፡ 3) የ ቢ (B) ደም ዓይነት የአመጋገብ ስርዓት የጥንቶቹ አዳኞች ወደ ሒማሊያስ ተራሮች በመሰደድ እንስሳትንም በማላመድ የአርብቶ አደር ሕይወትን መምራት ሲጀምሩ የተፈጠረ የደም ዓይነት ነው፡፡ ቀይ ስጋ፣ ዓሣ፣ እርጎ፣ ዓይብ፣ ወተት፣ ሙዝ፣ አረንጓዴ ቅጠላማ አትክልቶች፣ ወይንና አናናስ ተስማሚ ከሚባሉት ምግቦች መካከል ሲጠቀሱ ዶሮ፣ ስንዴ፣ ቲማቲም እንዲሁም ለውዝ እንዳይመገቡ ይመከራል፡፡ 4) የ ኤቢ (AB) ደም ዓይነት የአመጋገብ ስርዓት ኤቢ የደም ዓይነት በቅርብ ጊዜ የተከሰተ ሲሆን ከዓለም ህዝብም በአምስት ፐርሰንቱ ውስጥ ብቻ ይገኛል፡፡ የዚህ ደም ባለቤቶች ስጋንና ሌሎች የእንስሳት ተዋጽኦዎችን መፍጨት ቢችሉም የጨጓራቸው አሲድ መጠን ዝቅተኛ በመሆኑ ምክንያት የተመገቡት ምግብ በስብ መልክ ይከማቻል፡፡ ፍራፍሬዎችና አረንጓዴ አትክልቶች፣ ሀብሀብ እና ወይን፣ እንደ ቱና እና ሰርዲን ያሉ የባህር ምግቦችን ማዘውተር ተገቢ ሲሆን ከበቆሎ፣ የበሬና አሳማ ስጋ እነዲሁም ከአልኮሆልና ቡና መራቅ ያስፈልጋቸዋል፡፡

ለጤናችን ጠቃሚ መረጃ የጉሮሮ አክታ መብዛት ውድ ስለ ጤናዎ ምን ያውቃሉ ጠቅላላ እውቀት ቤተሰቦች እንዴት ዋላችሁ ዛሬ ስለአክታ ከመጠን በላይ መመረት ይዘንላችሁ ቀረብን !!! በመተንፈሻ አካላት ላይ
ለጤናችን ጠቃሚ መረጃ የጉሮሮ አክታ መብዛት ውድ ስለ ጤናዎ ምን ያውቃሉ ጠቅላላ እውቀት ቤተሰቦች እንዴት ዋላችሁ ዛሬ ስለአክታ ከመጠን በላይ መመረት ይዘንላችሁ ቀረብን !!! በመተንፈሻ አካላት ላይ መጠነኛ የሆነ አክታ ወይም ንፍጥ በአይነቱም የማጣበቅ ፣የመዝለግለግ እና ነጭ ቀለም ያለው ሲሆን በአንዳንድ ምክንያቶች ከመጠን ያለፈ የአክታ መብዛት ያጋጥማል ከነዚህም ውስጥ :- • የመተንፈሻ አካላት ላይ ኢንፌክሽን ካለ • አለርጅ ካለ • ለተለያዩ ኬሚካል መጋለጥ ካለ • የሳንባ ህመም • የአሲድ ወደ ላይ መመለስ ከአክታ መብዛት ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ ነገሮች 1. አክታ ከመጠን በላይ መወፈር(Thick mucus) ፡-ይህ አይነት ለውጥ በዋነኝነት የሚከሰተው ንፍጥ አምራች ክፍሎች ሲደርቁ ነው። 2. የከለር መቀየር ፦የአክታ ከለር አለርጅ ፣ጉንፋን፣እንፌክሽን ካለ ይቀየራል። 3. ደም የቀላቀለ አክታ ፦ይህ ለውጥ የሚታየው የጉሮሮ መቆጣት ሲኖር ፣መድረቅ፣ደጋግሞ ጉሮሮን ለማጽዳት መሞከር / አክታን ለማስወጣት መሞከር። * ዶክተር አለ ይህ አይነት የጤና ችግር ሲያጋጥመዎት ሀኪም ከማማከረዎ በተጨማሪ በቤት ውስጥ ምን ማድረግ እንዳለበዎት ይጠቁመዎታል። • የፈላ ውሀ መታጠን • ጭንቅላትን ከፍ አድርጎ መተኛት • አክታን አለመያዝ • ውሀ በጨው አድርጎ መጉመጥመጥ • አለማጨስ ወይም ከሚያጨስ ሰው ጋር አለመቀመጥ • አለርጅ/የሚያባብስ ነገርን ማስወገድ • ፍራፍሬን መመገብ • የአልኮል መጠጥን መቀነስ • በቂ ውሀ መጠጣት @DrSofonias

ስለ እርግዝና ያልተሰሙ አስደናቂ እውነታዎች 1. የጠዋት ሕመም (morning sickness) የሚባለው ሁሌ ጠዋት የሚከሰት አይደለም፡፡ ብዙ ሴቶች ቀኑን ሙሉ አንዳንዶች ድግሞ ጠዋት፣ግማሽ ቀን ወይም ማታ ስሜቱ ሊታያቸው ይችላል፡፡ 2. እረጃጅምና ዕድሜያቸው ከ35 ዓመት በላይ የሆኑ ሴቶች መንታ ልጅ የመውለድ ዕድላቸው ሰፊ ነው፡፡ ከቤተሰብ ውስጥ መንታ የወለደ ሰው ካለና ዕድሜዎት ከ35 በላይና ረጅም ከሆኑ መንታ ልጅ የመውለድ ዕድል አልዎት፡፡ 3. የደም መጠኖ ይጨምራል፡፡ በልብዎ የሚሰራጨው የደም መጠን ከ40 እስከ 50 በመቶ ይጨምራል፡፡ 4. የልብዎ መጠን በእርዝመትም በወርድም ይጨምራል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ተጨማሪ ደም ለመርጨስ ሲል ይለጣጣል፡፡ 5. እርግዝና ከተከሰተበት ከመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ጡት ወተት ለማምረት ይዘጋጃል:: 6. ልጅዎ ይሰማዎታል፡፡ ጆሮ ቀደም ተብለው ከሚሰሩት የህፃኑ አካለት አንዱ ሲሆን ልጅዎም የእለት ተዕለት ንግግሮን ይሰማል፡፡ በተለይ ከ6 ወራት ጀምሮ ብቻዎን ስላልሆኑ ልጅዎን ያናግሩ፡፡ 7. ልጆ ከእርስዎ ቀድሞ ይበላል፡፡ ማንኛውም የሚመገቡት ቫይታሚንና ማእድናት ልጆ ከተጠቀመ በኃላ ነው የቀረው ወደ እርሶ የሚደርሰው፡፡ ለዚህም ነው በእርግዝና ጊዜ ጥሩ ጥሩ ነገር መመገብ ለልጆ ጤንነት ወሳኝ ነው የሚባለው፡፡ 8. በእርግዝና ጊዜ ምግብ ቀስ ብሎ ወደ ትንሹ አንጀት ስለሚሄድ ሆድ በጋዝ ሊሞላ ይችላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የአይነምድር ድርቀት ሊያጋጥም ይችላል፡፡ ስለሆነም ለብ ያለ ውሃ በብዛት መጠጣት ሊያስታግሰው ይችላል፡፡ 9. የግብረስጋ ግንኙነት ማድረግ ይቻላል፡፡ይሕ ማለት ዕርግዝናው ጤናማ እስከሆነ ብቻ ነው፡፡፡ ውስብስብ የሆነ እርግዝና ከሆነ ግን ሐኪም ማማክር ግድ ይላል፡፡ ህፃኑ በእንሽርት ውሃ ውስጥ ስከለሚሆን ከመራቢያ አካል ጋር ግንኙነት ስለማይኖረው ወሲብ መፈፀም ደህንነቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 10. ጫማሽ ላይበቃሽ ይችላል፡፡ እግርሽ በሆርሞን ምክንያት ስለሚጨምርና ስለሚያብጥ ጨማዎችሽ ላይበቁሽ ይችላሉ፡፡ 11. ሴት ልጅ ካረገሽ በህፃኗ ማህፀን ውስጥ እንቁላል ከዚህ ወቅት ጀምሮ መፈጠር ይጀምራል፡፡ ስለሆም የልጅ ልጅሽን እንደተሸከምሽ ልታስቢ ይገባል፡፡ ወንድ ልጅ ከሆነ ግን ስፐርም አይኖረውም፡፡ ስፐርም የሚፈጠረው በረአፍላ ዕድሜው ላይ ሲደርስ ነው፡፡ 12. የእንግዴ ልጅ ከእናቱ ወደ ልጁ ምግብ ለማስተላለፍ ብቻ የሚጠቅም ሳይሆን ልጁን ከባክቴሪያና ከኢንፌክሽን ይጠብቃል፡፡ እባክዎን ይህን ጠቃሚ መረጃ ለወገኖ እንዲደርስ share በማድረግ ይተባበሩን! @DrSofonias

በጣም ጠቃሚ መልእክት ዛሬ ስለ ለምጽ (ለምጥ) በሽታ እና መፍትሔው እናያለን። የለምጽ በሽታ የሚከሰትበት ምክንያት በቆዳ ውስጥ ያሉት ቀለም የሚያመነጩ ሕዋሳት ሲሞቱ ነው በማለት የሳይንስ ዓለም ይተነትነዋል። በሽታው በቆዳ ላይ ነጣ ያሉ ነጠብጣቦች እንዲወጡ ወይም የተወሰነ የቆዳ ክፍል እንዲነጣ ያደርጋል። ይህ በሽታ በአንዳንድ ተጠቂዎች ላይ በመጀመሪያ ከነጣው የቆዳ ክፍል አልፎ የማይስፋፋ ሲሆን በሌሎች ላይ ደግሞ ወደ መላው ሰውነታቸው በፍጥነት ይሰራጫል። ለበርካታ ዓመታት ቀስ በቀስ እየተስፋፋባቸው የሚሄድ የበሽታው ተጠቂዎችም አሉ። ለምጽ የሚያስከትለው የሕመም ስሜት ካለመኖሩም በላይ በንክኪ አይተላለፍም። በሽታው ዘርና ቀለም የማይለይ ከመሆኑም በላይ ሴቶችንና ወንዶችን እኩል ያጠቃል። ሆኖም የበሽታው መነሻ እስከ አሁን በውል አልታወቀም። የበባህላዊ ህክምና ለየት የሚያደርገው ነገር ቢኖር እውን የሆነ እና የማያዳግም መፍትሔ በአበው ጠበብት አባቶች እና የጥበብ ሊሂቃን ዘንድ ያለ ምንም ቴክኖለጂ ያለ ምንም ናሙና ከ ፈጣሪ በተሰጣቸው ጸጋ መፈወሳቸው ሲሆን። የዘመናዊ ህክምና አሰጣጥ ለየት የሚያደርገው ነገር ደግሞ የበሽታ አምራች ኃይል እራሱ የዘመኑ ስልጣኔ ይሆን እና! ፊቱን ዞር በማድረግ ደግሞ ላመረተው በሽታ የሚሆን ማስታገሻ መድኃኒት በማምረት ህብረተሰቡን የእድሜ ልክ ጥገኛ ይሆን ዘንድ ይገደዳል። ይህ ማለት ሁሉም የባህል ህክምና አሰጣጥ እያደነቅኩ ወይም ሁሉም የዘመናዊ ህክምና አሰጣጥ እየነቀፍኩ ሳይሆን የኢትዮጵያ ቅርስ እና ተሰጥኦ የሆነው የጥንት ጥበብን በማንኳሰስ የተለያየ አጸያፊ ስም በመስጠት የምዕራባውያን ስልጣኔ አጉልቶ በማየት የሚሸረብ ሴራ ሳይ ጊዜ ቅሬታ ፈጥሮብኝ የሰጠኃት አስተያየት ናት። እንጂ ዘመናዊ ህክምናም ብዙ መልካም እና ወደር የሌላቸው ህክምና የሚሰጥበት የተለያዩ ንቅለ ተከላዎች፤ የወሊድ ክንዉኖች፤ የተለያዩ ትሪትመንቶች፤በተለያየ አደጋ የሚደርሱ ጉዳቶች የሚሰጥ ህክምናዎች የተለያዩ በሽታ ፈጣሪ ዶክቶሮች የተመረቱ ወረርሽኞች እና የመሳሰሉት በማስታገስ ወደር አይገኝለትም። ቢሆንም ግን ቅሉ ተወደደም ተጠላም ቀዳሚው የአበው ጥበብ እና የባህል ህክምና መሆኑን ልበ በሉልኝ። ወደጉዳዬ ስመለስ የለምጽ (ለምጥ) በሽታ መፍትሔ ።።።።።።።።የለምጽ መድኃኒት።።።።።።።።።። በምስሉ የምትመለከቷት ዕጽ ወርቅ በሜዳ ትባላለች። የወርቅ በሜዳ ሥር እና ቅጠል አንድ ላይ በማድረቅ በመደቆስ ከገብስ ጠላ ጋር አብሮ በመጥመቅ አልያም ከ ጽራይ የገብስ ጠላ ጋር ! #የወርቅ በሜዳ ዶቄት አንድ የሻይ ማንኪያ #ከገብስ የጠለለ ጠላ ግማሽ ሌትር ጋር ጨምሮ አሳድሮ ጧት በባዶ ሆድ ቀስ እያሉ መጠጣት። ይህ ድርጊት ከ 7 ቀን እስከ 21 ቀን በተደጋጋሚ ይጠቀሙ ሙሉ ለሙሉ ይወገዳል። በተጨማሪም የወርቅ በሜዳ ቅጠል እና ሥሩ ጨቅጭቆ ለሁለት 7 ይጠመቁ። ለ 20 ደቂቃ ያክል ከጥምቀት በኃላ በሽታው ያለበት ቦታ ጸሐይ ላይ ሁኖ ማስመታት። ይህ ጥበብ እንደቀልድ ባታዩት ምክሬ ነው ምክንያቱም ሙሉ መፍትሔ በዓይኔ ያየሁበት ጥበብ ነው። ወርቅ በሜዳ የለምጽ መፍትሔ ማት የተለያዩ አሰጣጥም አላት። የሚከለክለው፦ #የፍየል እና የላም ስጋ መብላት ለአንድ አመት ያክል አይመከርም። #የሰው ጥላ እና ሰው ከሚዞርበ ቦታ ርቀን እንጠቀመው ሼር @DrSofonias

የማኅፀን በር ጫፍ ካንሰር ሕመሙ ሲጀምር ምንም ዓይነት ምልክት አያሳይም። ቫይረሱ በሰውነት ውስጥ ገብቶ ምልክቶች ለማሳየት በርካታ ዓመታትን ስለሚፈጅበት ምልክቶቹን በቶሎ አውቆ ወደ መፍትሄ ለመሄድ ያስቸግራል። ሕክምና ሳያገኝ ሲቆይና ቫይረሱ በሰውነት ውስጥ የሚኖረው ሥርጭት እየበዛ እና እየሰፋ ሲሄድ ግን ምልክቶቹ መታየት ይጀምራሉ። ምልክቶቹ መታየት የሚጀምሩበት ደረጃም በሽታው ከቅድመ ካንሰርነት ወደ ካንሰርነት የሚሸጋገርበት ወቅት ነው። የማኅፀን በር ካንሰር መኖሩን ከሚጠቁሙት ዋና ዋና ምልክቶች መካከል ደግሞ የበሽታው ምልክት መደበኛ ባለሆኑ ጊዜያት ህመም አልባ የሆነ ደም ከማኅፀን መፍሰስ መጀመር አንዱ ነው። ለምሳሌ፤ ከመደበኛ የወር አበባ ጊዜ ውጪ፣ ከግብረ ስጋ ግንኙነት በኋላ፣ ከማረጥ በኋላ፣ ብልትን ከታጠቡ በኋላ ሊሆን ይችላል። ከዚህ በተጨማሪም የሚታየው ምልክት መጥፎ ጠረን እና ውሃማ ቀለም ያለው የማኅፀን ፈሳሽ መውጣት፣ የጐን፣ የወገብ እና የእግር ህመም ስሜት መሰማት፣ የሽንት ቧንቧ ወይም የፊንጢጣ መድማት፣ የእግር እብጠት፣ እንዲሁም የሽንት ወይም የሰገራ ማምለጥ (fistula) ዋና ዋናዎቹ ናቸው። የማኅፀን በር ጫፍ የቅድመ ካንሰር ምርመራ ምንድነው? የማኅፀን በር ጫፍ የቅድመ ካንሰር ምርመራ ዕድሜያቸው ከ23-49 ዓመት ለሆኑ ማናቸውም ሴቶች የሚደረግ ምርመራ ነው፡፡ ምርመራው እጅግ ቀላል እና አስተማማኝ ከመሆኑም ሌላ ውጤቱንም ወዲያውኑ ለማወቅ ያስችላል፡፡ በመሆኑም ይህን ምርመራ ያካሄደች ሴት በማኅፀን በር ጫፍ ላይ ካንሰር ከመከሰቱ በፊት አመላካች የሆኑ ለውጦች መኖራቸውን ለማወቅ ትችላለች ማለት ነው፡፡ የማኅፀን በር ጫፍ ቅድመ ካንሰር ሊድን ይችላልን? የማኅፀን በር ካንሰርን አስቀድሞ በሚደረግ ጥንቃቄ እና ምርመራ መከላከል ይቻላል። ለበሽታው መንስኤ የሆኑትን ነገሮች በማስወገድም ለበሽታው ያለውን ተጋላጭነት መቀነስ ይቻላል። የቅድመ ካንሰር ምርመራን በማድረግ የማኅፀን በር ካንሰር ከመከሰቱ ከአስር ዓመት በፊት አስቀድሞ ማወቅ የሚቻል ሲሆን በወቅቱ ከተደረሰበት እንዲሁም በሐኪም የሚታዘዝ ህክምና እና መድሃኒት በአግባቡ ከተወሰደ ከበሽታው ሙሉ ለሙሉ መዳን ይቻላል፡፡ ሆኖም በሽታው ቀድሞ ካልታወቀ እና ለረጅም ጊዜ ሥር ከሰደደ ሕክምናውም የዚያኑ ያህል አስቸጋሪ እና የመዳን እድልም የጠበበ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ የትኛዋም የግብረሥጋ ግንኙነት የምታደርግ ሴት ከ23 እስከ 49 ዓመት የሆነች ሴት የቅድመ ካንሰር ምርመራውን በማድረግ ራሷንም ሆነ ቤተሰቧን ከአደጋ ልትጠብቅ ይገባል፡፡

የልብ ህመም የማስጠንቀቂያ ምልክቶች/Warning Signs of Heart Attack ለልብ ህመም አስተዋጽኦ የሚያደርጉ በጣም ብዙ ነገሮች አሉ ከነዚህም መካከል፦ ※ ዕድሜ ※ የዘር ሃረግ ※ ከፍተኛ
የልብ ህመም የማስጠንቀቂያ ምልክቶች/Warning Signs of Heart Attack ለልብ ህመም አስተዋጽኦ የሚያደርጉ በጣም ብዙ ነገሮች አሉ ከነዚህም መካከል፦ ※ ዕድሜ ※ የዘር ሃረግ ※ ከፍተኛ የደም ግፊት ※ ከፍተኛ የኮሌስትሮል መጠን ※ ከመጠን ያለፈ የሰውነት ክብደት ※ የተመጣጠነ ምግብ አለመውሰድ ※ አልኮል መውሰድ ※ ጭንቀት ※ እንቅስቃሴ አለማድረግ ለልብ ህመም በሽታ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ። ✔ የልብ ህመምን በጊዜ ወይም በፍጥነት ለማወቅ የሚከተሉትን ጠቃሚ ምልክቶች ይማሩ ወይም ይወቁ፦ 1. የድካም ስሜት እና የትንፋሽ ማጠር። 2. ላብ ማላብ፦ ቀን እና ሌሊት። 3. የምግብ አለመፈጨት፣ ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ። 4. የደረት ህመም፣ ግፊትና ምቾት ማጣት። 5. በመላው ሰውነት ላይ የሚከሰት ህመም።

ለጤናችን ጠቃሚ መረጃ ሰላም ውድ የገፃችን ተከታታዮች አንድ ቆየት ባለ ጽሁፍ ላይ ስለ ጥቁር አዝሙድ ዘይት ጥቅም አስነብቤያችሁ እንደነበር ይታወሳል ብዙዎቻችሁ ስለ አጠቃቀሙ ጠይቃችሁናል እንደውም አንድ አዝናኝ ኮመንት አንብቤያለሁ አሱም ምን ይላል መሰላችሁ " አጠቃቀሙን ንገሩን ሥጋ ሰታችሁ ቢላዋ እንደመከልከል ነው" ይላል እውነት ለመናገር ይህን ኮመንት ካነበብኩኝ በኋላ ቢለዋውን ፍለጋ ብዙ መረጃዎ ካገላበጥኩኝ በኋላ ቢላዋውን ይዤ መጥቻለሁ ተከታተሉኝ፦ • ለካንሰርና እባጮች አንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከ አንድ የሻይ ማንኪያ የተፈጥሮ ማር ጋር በመቀላቀል ከቁርስ ግማሽ ሠዓት በፊት ይጠቀሙ። • ለስኳር በሽታ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከተፈጥሮ ማር ጋር በመቀላቀል በቀን ሁለት ጊዜ ይጠቀሙ። ካርቦሃይድሬት ያላቸውን ምግቦች በመጨመር ስኳርን በማቆም የአመጋገብ ለውጥ ያድርጉ። • ለተቅማጥ አንድ የሻይ ማንኪያ ጥቁር አዝሙድ ዘይት ከአንድ ኩባያ እርጎ ጋር በመቀላቀል በቀን ሁለት ጊዜ ይጠቀሙ። • ለደረቅ ሳል ግማሽ የሻይ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከቡና ጋር በመቀላቀል በቀን ሁለት ጊዜ ይጠቀሙ። ጀርባዎና ደረትዎን በዘይት ይሹት። • ለጆሮ ህመም በስሱ የተቆላ አንድ የሻይ ማንኪያ ጥቁር አዝሙድ ይውሰድ ከዚያም ጥቂት የኦሊቭ ዘይት ጠብታዎች በመጨመር በደንብ ይቀላቅሉት። ሰባት ጠብታ በሲሪንጅ ውስጥ ይክተቱ ከዚያም ጠዋት እና ማታ ጆሮዎ ውስጥ ይጨምሩ። • ለዓይን ህመም እና ለእይታ ችግር ወደ መኝታ ከመሄድዎ ከግማሽ ሠዓት በፊት የአይን ቆብዎን በጥቁር አዝሙድ ዘይት ይሹት። ግማሽ የሻይ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከአንድ ኩባይ የካሮት ጭማቂ ጋር በመቀላቀል ይጠጡ። • ለፊት ፓራሊሲስ አንድ የሻይ ማንኪይ ዘይት ለብ ባለ ውሃ ውስጥ በመጨመር እንፋሎቱን ይታጠኑ። • ለጉንፋን እና ፍሉ አንድ የሻይ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከማር ጋር በመቀላቀል ከቁርስ በፊት ይውሰድ። በእያንዳንዳቸው የአፍንጫ ቀዳዳ ውስጥ ጥቂት ጠብታዎች ይጨምሩበት። • ለሃሞት ጠጠር እና ለጉበት ጠጠር አንድ ትልቅ ማንኪያ የጥቁር አዝምድ ፍሬ ከማር ጋር በብርጭቆ ውስጥ ይቀላቅሉት ጥቂት ለብ ያለ ውሃ ይጨምሩበት። በመጨረሻም በመጨረሻም አንድ የሻይ ማንኪያ ዘይት ይጨምሩበት ይህን ውህድ በየቀኑ ጠዋት ጠዋት ይጠጡ። • ለአጠቃላይ ጤንነትና ደህንነት አንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ፍሬ ከአንድ የሾርባ ማንኪያ ማር ጋር በመቀላቀል በየቀኑ ይጠቀሙ። ወይም ግማሽ የሾርባ ማንኪያ ዘይት ከማር ጋር በመቀላቀል ከቁርስ በፊት በየቀኑ ይጠቀሙ። • ለፀጉር መሳሳት እና ያለ ዕድሜ ሽበት በመጀመሪያ ፀጉርዎን ይታጠቡ ከዚያም በቂ የሆነ የኦሊቭ ዘይት ከጥቁር አዝሙድ ዘይት ጋር በመቀላቀል ይቀቡት። ከአንድ ሠዓት ቆይታ በኋላ ያለቅልቁት ወይም ይታጠቡት። • ለራስ ህመም እና ማይግሬን ከግንባርዎ ግራ ክፍል ትንሽ ዝቅ ብሎ ወይም ቴምፕል በሚባለው የጥቁር አዝሙድ ዘይት በመቀባት ይሹት። ጥቂት ጠብታዎች በአፍንጫዎ ቀዳዳ እና ጭንቅላትዎ ላይ ያድርጉ። በቀን ሁለት ጊዜ ጥቂት የጥቁር አዝሙድ ፍሬና ማር ይብሉ። • ለማስታወስ ችሎታ ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጥቁር አዝሙድ ከግማሽ የሻይ ማንኪያ ማር ጋር በመቀላቀል በቀን ሶስት ጊዜ ይመገቡ። • ለአፍ ኢንፌክሽን ቫይረስ ጥቂት የጥቁር አዝሙድ ፍሬ በአፍዎ ውስጥ ከ 10 - 15 ደቂቃ ይያዙት። • ለጡንቻ ህመም አንድ ማንኪያ ጥቁር አዝሙድ ከማር ጋር በመቀላቀል በቀን ለሶስት ጊዜ ይውሰድ። የቅልጥም መረቅ በየቀኑ ይጠጡ። የቻሉትን ያክል ዘቢብ በየቀኑ ይመገቡ። • ለሪህና ጀርባ ህመም የጥቁር አዝሙድ ዘይት ሞቅ በማድረግ የሚያምዎትን ቦታ ይሹት። በየቀኑ የጥቁር አዝሙድ ፍሬ እና ማር ይመገቡ። • ለሆድ ህመም በአንድ ትልቅ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ፍሬ ከማር ጋር በመቀላቀል ይጠቀሙ። ጥቂት የፔፐርሜንት ሻይ ይጠጡ ከዚያም የረሃብ ስሜት ከተሰማዎት የተቀቀለ ሩዝ ውሃ ይጠጡ። • ለጥርስ ህመምና ድድ ኢንፌክሽን በኩባያ የሎሚ ጭማቂ በማድረግ ጥቂት የጥቁር አዝሙድ ፍሬ ይጨምሩበት ከዚያም ያፍሉት። ከዚያም የፈላው ሎሚ ቀዝቀዝ ሲል በዚህ ውህድ ፈሳሽ አፍዎን ይጉመጥመጡበት/ይታጠቡበት። • ለሆድ ትላትል ሁለት የሻይ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ፍሬ ከግማሽ ኩባያ ሎሚ ጋር በመቀላቀል ይህን ውህድ ያሙቁት። ከዚያም ቡርሽ ወይም ሌላ ነገር በመጠቀም የሆድና ጉልትዎን አካባቢ ይሹት። መልካም ጤንነት!!

ጠቃሚ መረጃ ውድ የፔጃችን ቤተሰቦች ዛሬ ደግሞ የኩላሊት ጠጠር ህመምና አመጋገብ እናያለን መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ለወዳጆ ሼር ያድርጉት የኩላሊት ጠጠር ህመምና አመጋገብ የኩላሊት ጠጠር በሽታ ከ 10 ሰው አንድ ሰው ላይ በህይወት ዘመኑ ሊከሰትበት የሚችል በሽታ ነው፡፡የኩላሊት ጠጠር በሽታ በጣም ትናንሽ የሆኑና ጠንካራ የሆኑ ጠጠሮች ሲሆኑ በኩላሊት ውስጥ በመጠራቀም የተለያዩ ማዕድናት ጨው መጠንን በመጨመር የሽንትን መጠን ይቀንሳሉ፡፡በመሆኑም የአመጋገብ ለውጥ በማምጣት የኩላሊት ጠጠርን መቀነስ ይቻላል፡፡ ለኩላሊት ጠጠር በሽታ እንደመንስዔ የሆኑ የአመጋብ ሁኔታዎች ከፍተኛ የሆነ የፕሮቲን ምግቦች ከፍተኛ የሆነ የሶዲየም አወሳሰድ ዝቅተኛ የሆነ የፈሳሽ አወሳሰድ መኖር ከፍተኛ የሆነ የኦክሳሌት መጠን የያዙ ምግቦችን በብዛት መመገብ፡፡ ለውዝ፣ቀይስር እና ስፒናሽ በውስጣቸው ከፍተኛ የሆነ የኦክሳሌት መጠን በመያዛቸው ለካልሺየም ኦክሳሌት የኩላሊት ጠጠር ያጋልጣሉ ይህ ማለት ግን እነዚህን ምግቦች ሙሉ በሙሉ ከምግባችን ውስጥ ማስወገድ አለብን ማለት አይደለም ግን ስንመገብ በመጠኑ መሆን አለበት፡፡ እንዲሁም በጣም ከፍተኛ ፕሮቲን ያላቸውን ምግቦች ደግሞ ለካልሺየም ፎስፌት ጠጠር ያጋልጣሉ፡፡እንዲሁም ከፍተኛ የሆነ የሶዲየም አወሳሰድና ዝቅተኛ የፈሳሽ አወሳሰድ ለዩሪክ አሲድ እና ሳይቲን ጠጠር ያጋልጣል፡፡ አመጋገብን በተመለከተ የኩላሊት ጠጠር በሽታ እንዳይዘን ከተያዝንም ለመቆጣጣር እነዚህን ማድረግ አለብን እነሱም በብዛት ውሃ መጠጠት የጨው አወሳሰድን መቀነስ ከእንሰሳት ተዋጽኦ የሚገኙ ፕሮቲኖችን መቀነስ ምክንያቱም እነዚህ ምግቦች በብዛት ከተመገብን ለኩላሊት ጠጠር የመጋለጥ ዕድላችን ይጨምራል፡፡ በመሆኑም ከእጽዋት የሚገኙ ፕሮቲኖችን በብዛት መመገብ ለምሳሌ ባቄላ፣ምስር፣አኩሪ አተር፣ አተር እና ሽንብራ የመሳሰሉትን መመገብ ያስፈልጋል፡፡ የኦክሳሌት ንትረ ነገር በውስጣቸው በብዛት ያለባቸውን ምግቦች መቀነስ፡፡ በካልሺየም የበለጸጉ ምግቦችን በብዛት መመገብ ለምሳሌ ወተትና የወተት ተዋጽኦች አትክልትና ፍራፍሬዎችን በብዛት መመገብ በተለያም የሚኮመጥቱ ፍራፍሬዎችን በውስጣቸው ቫይታሚን ሲ የያዙትን መመግብ የኩላሊት ጠጠርን ለመቀነስ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ በውስጣቸው ብዙ ኦክሳሌት ንጥረ ነገር ያላቸውን ምግቦች ለምሳሌ ቀይስር እና ስፒናሽ ምግቦችን በካልሺየም ከበለጸጉ ምግቦች ጋር መመገብ የኩላሊት ጠጠር እንዳይፈጠር ይረዳል ምክንያቱም ካልሺየም ከኦክሳሌት ጋር አንጀታችን ውስጥ በመጣበቅ ጠጠር እንዳይፈጥር ስለሚያደርግ ነው፡፡ @DrSofonias

ስለ ገንፎ አንድ ነገር ልበላቹ #ገንፎ| የሰንበት_የማለዳ_ቁርስ በአኅጉራችን አፍሪቃ ገንፎ መደበኛ ምግብ ነው፡፡ የበቆሎ- ገንፎ፣ የገብስ- ገንፎ፣ … ከልዩ-ልዩ የእህል ዘሮች ጋር ተደባልቆና ተቀይጦ ይዘጋጃል፡፡ ይህ አመጋገብ ለጤና ተስማሚ ከመሆኑ ባሻገር ለአካል ጥንካሬ፣ ለኃይልና ሙቀት ከፍተኛ ድርሻ አለው፡፡ ፈረንጆች ‹‹you are what you eat›› የሚሉት ብሂል አላቸው፤ ሰው ማጀቱን ይመስላል እንዲል የሀገሬ ሰው፡፡ ወይም ‹‹ሆድን በጎመን ቢሸነግሉት፣ ጉልበት በዳገት ይለግማል›› እንዲል- የሀገሬ ገበሬ፡፡ የአኅጉራችን ሰዎችን የሰውነት ጥንካሬ ስንመለከት ከአመጋገባቸው ይትባህልና ልማድ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ለዚህ ነው የእግር ኳስ ጨዋታ ሜዳ ላይ ንክች ሲያደርጉን ፍንግል የምንለው፡፡ ሁሉ አዝዕርት እያለን የአመጋገብ ባህላችንን ማስተካከል ባለመቻላችን ደቃቆች ሆነናል፡፡ በጣም ምግብ መራጭ ህዝቦች ነን፡፡ ይህ ጎድቶናል፡፡ ገንፎን በሀገራችን ልዩ ልዩ አካባቢዎች ለምሳሌ ጋምቤላ፣ ቤንሻንጉል፣ ደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ላይ ጎላ ብሎ በአመጋገብ ልማዳቸው ውስጥ ቢኖርም፣ በአብዛኛው የሀገራችን ክፍል ግን የዘወትር ምግብ ከመሆን ይልቅ የልዩ ልዩ ማኅበራዊ ኹነቶች፣ የበዓላት እና አልፎ- አልፎ በምግብ ጠረጴዛ ላይ የሚቀርብ ምግብ ሆኗል፡፡ በደቡብ ኢትዮጵያ ባሉ ማኅበረሰቦች አካባቢ የሚዘጋጀው የቡላ ገንፎ እጅግ ከፍተኛ ሙቀትና ኃይል ከመስጠቱ ባሻገር፣ ከአራስነት ለመጥናት እንደ መድኃኒትነት ሁሉ ያገለግላል፡፡ ይህን ባህል ወደ ሰሜኑም፣ ምስራቁም የኢትዮጵያ ክፍል ማዳረስ ይኖርብናል፡፡ ላጤዎችም ቢሆኑ፣ ብዙ ጊዜ ገንፎን ለምግብነት ሲመርጡት አይስተዋልም፡፡ እንደውም አንዳንዱ ‹‹እኔ አራስ ነኝ እንዴ-ገንፎ የምመገበው›› ሲልም ይስተዋላል፡፡ በእርግጥ አማራጭ የአመጋገብ ሥርዓት እንዳንፈልግ ከሚያደርጉን ምክንያቶች አንዱ የምግብ ፍጆታ አቅርቦታችን፣ ሲበስል የሚፈጀው ጊዜ እና የአዘገጃጀቱ ሂደቶች ውስብስብነት ናቸው፡፡ ሆኖም፣ ገንፎ ማዘጋጀት በጣም ቀላል ሥራ ነው፡፡ ግዴላቸሁም ገንፎ አዘገጃጀትን አሁን አብረን እንሞክረውማ?! በደንብ ትወዱታላቸሁ፡፡ መሞክር ማንን ገደለ፡፡ ለዚህ ክረምት ደግሞ ኃይልና ሙቀትንም እንድናገኝ ተመራጭ ምግብ- ገንፎ ነው፡፡ ገንፎ ለመሥራት ምን ያስፈልገናል? 1. የገንፎ እህል (ዱቄት) 2. ጨው 3. ትንሽ ቅቤ ወይም ዘይት 4. በርበሬ ወይም ሚጥሚጣ (እንደ ምርጫችን) #አዘገጃጀቱ ~መጀመሪያ በድስት ውሃ እንጥዳና ልክ መፍላት ሲጀመር ትንሽ ጨው መጨመር፤ ~ውሃው ሲፈላ፣ ትንሽ በብርጭቆ ውሃ ቀንሰን እናስቀምጣለን፣ ~ቀጥሎ ሥራችን የሚሆነው ደግሞ ቀስ እያልን ዱቄቱን መጨመር እና በማማሲያ የጨመርነውን የገንፎ ዱቄት እንዳይጓጉልብን ተጠንቅቀን ማሸት- ማሸት-ማሸት ይኖርብናል። እንዳያርብንም የእስቶቩን መጠን መቀነስ ወይም ከእሳቱ ላይ እያወረድን በመድንብ ገንፎውን ማሸት ይኖርብናል፡፡ ~ቀጥሎስ፣ የገንፎውን መሐሉን ጎድጎድ አድርገን በብርጭቆ የቀነስነውን የፈላውን ውሃ ጠብ እናርግና ከድነን እንዲበስል እናደርገዋለን ~እንደገና ደግመን እናሸውና ትንሽ ውሃ ጠብ እናደርጋለን፤ አሁንም ደግመን እንዲበስል እንከድነዋል ~በነገራችን ላይ እንደበሰለ በሽታው ብቻ ማወቅ ይቻላል፡፡ እንዴት ካላችሁ እህል እህል የሚል ከሆነ ገና ነው ማለት ስለሆነ፣ ልክ እንደቅድሙ ውሃ ጠብ አድረግን እንከድነዋለን። ~አለበለዚያም በማንኪያ ቀምሰን ማረጋገጥ እንችላለን አሁን ገንፏችን በስሏል፤ ከዚህ በኋላ ለመመገብ ሰሃናችን ቅቤ ወይም ዘይት ዙያውን በመቀባት እናዘጋጅና የሰራነውን ገንፎ ወደ ሰሃናችን እንገለብጠዋለን፡፡ ~የገለበጥነውን ገንፎ በክብ ቅርፅ በማዘጋጀት መሐሉን ቀስ ብለን በማንኪያ እንከፍተውና ቅቤ ወይም ዘይት በማድረግ ቀጥሎ ደግሞ በርበሬ በመጨመር ማዋሃድ እና ትኩስ ትኩሱን- መመገብ፡፡

የሰው ልጅ የራሱ የሆነ የተለየ የሰውነት ጠረን አለው። ይህ የሰውነት ጠረን ጤናማ ቢሆንም በአንዳንድ ሰዎች ዘንድ ግን ከመጠን ያለፈ ይሆንና ከራስ አልፎ ሌሎችንም ሊረብሽ ይችላል። ሰውነታችን ኤክሶክራይን (exocrine) እና አፖክራይን (apocrine) የተሰኙ ሁለት አይነት ላብ አመንጪ እጢዎች አሉት። ኤክሶክራይን የተባሉት እጢዎች በሁሉም የሰውነታችን ክፍል የሚገኙ ሲሆን፥ የአፖክራይን እጢዎች ደግሞ ጉርምስናን በሚያመላክቱና ፀጉር በሚወጣባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ናቸው። የአፖክራይን እጢዎች ፕሮቲንና ስባማ ንጥረ ነገሮችን ያመነጫሉ፤ ይህም ነው ለሰውነት ጠረን መፈጠር ምክንያት የሚሆነው። ከመጠን ያለፈ ላብ እና የብብት ጠረንን ሁላችንም ልንከላከለው የምንፈልገው ጉዳይ ነው። ቅመም የበዛባቸው ምግቦችን እንደ ነጭ ሽንኩርት፣ ዝንጅብል እና ማጣፈጫዎችን አዘውትሮ መመገብ እንዲሁም ከላብ ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ባክቴሪያዎች ለሰውነት ጠረን መለወጥ በምክንያትነት ይጠቀሳሉ። ንፅህናን መጠበቅ፣ የአየር ማቀዝቀዣዎችን መጠቀም፣ እንደ አየር ሁኔታው ሳሳ ያሉ ልብሶችን መልበስ፣ ልብሶቻችን በአጭር ጊዜ ልዩነት መቀየር፣ ቅመም የበዛባቸውን ምግቦችን ከመመገብ መቆጠብ፣ ፀረ ባክቴሪያ የሆኑ ሳሙናዎችን መጠቀም እና ዲዮድራንት ወይም የላብ ማጥፊያ ከመጠቀማችን በፊት ብብታችን ደረቅ መሆኑን ማረጋገጥ ለችግሩ በመፍትሄነት ይነሳሉ። የሰውነት ጠረንን በተለይም የብብት መጥፎ ጠረንን ለማስወገድ ከፍተኛ ጥረትን የሚጠይቅ ነው። ኬሚካሎችን ለመጠቀም ካልፈለጉና እየተጠቀሙት ያለው ዲዮድራንት የሚያረካ ውጤት ካላስገኘልዎ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ቢሞክሯቸው መልካም ውጤት ያስገኛሉ ይላል የሄልዚ ላይፍ ላንድ ድረ ገጽ ዘገባ። 1. ቤኪንግ ሶዳ ቤኪንግ ሶዳ የፍሪጅ እና ላውንደሪዎችን መጥፎ ጠረን ለማስወገድ እንደሚረዳው ሁሉ የብብት ጠረንን ለማስተካከል እንደሚያግም ይነገራል። ጥቂት ቤኪንግ ሶዳ ከበቆሎ ዱቄት ጋር በመቀላቀል ከብብት ውስጥ መክተት ቆዳችን ደረቅ እና ንጹህ እንዲሆን ያደርጋል። 2. የብብት ጸጉርን አለመላጨት ሁሉም ነገር ሲፈጠር በምክንያት ነው፤ በሰውነታችን የሚወጡ ጸጉሮችም ለባክቴሪያ መፈጠር እና ለብብት ጠረን መቀየር ምክንያት የሚሆን እርጥበትን መሳብ አቅም አላቸው። እናም የብብት ጸጉርን መላጨት (ሼቭ ማድረግ) ለባክቴሪያዎች መራባት እድል ይፈጥራል ማለት ነው። የብብት ጸጉራችንን ከላጨን በኋላ የምንጠቀመው ቅባት ወይም ክሬምም የቆዳ መቆጣትን ሊያስከትል ስለሚችል የብብት ጸጉርዎን ከመላጨት ይቆጠቡ ይላል መረጃው። 3. የሻይ ዛፍ ዘይት የተለያዩ ቆዳ ነክ ችግሮችን እና መጥፎ የሰውነት ጠረንን ከሻይ ዛፍ በሚገኘው ዘይት ማከም ይቻላል። የዚህ ዛፍ ዘይት በጸረ ባክቴሪያ እና ጸረ ፈንገስ ይዞታው ነው የሚታወቀው። መጠነኛ የሻይ ዛፍ ዘይት ከሮዝ አበባ ውሃ ጋር ቀላቅሎ ብብትን መቀባት መጥፎ ጠረንን ለማስወገድ ይረዳል። 4. ተፈጥሯዊ ሳሙና መላ ሰውነታችንን በተፈጥሯዊ ሳሙና መታጠብ መጥፎ የሰውነት ጠረንን ለማስወገድ ይጠቅማል። ከወይራ ዘይት እና ሶዳ እንዲሁም ከፍየል ወተት የሚዘጋጁ ተፈጥሯዊ ሳሙናዎችን መጠቀም የቆዳ ውበትን ከመጠበቅ ባለፈ ማራኪ ጠረንን ያላብሳል ተብሏል። 5. አልኮል እንደ ቮድካ ያሉ ሽታ አልባ የአልኮል መጠጦችን በስፕሬይ ብብትን መርጨት መጥፎ ጠረንን እና ባክቴሪያዎችን ለማስወገድ ይረዳል። ይሁን እንጂ አልኮል ልንጠቀም የሚገባው ልብስ ከመልበሳችን በፊት ነው። 6. ሎሚ ሎሚ የቆዳችንን ፒ.ኤች ደረጃ ለማስተካከል ያግዛል። የሎሚ ቁራጭን ከብብታችን ስር በማድረግ ለ15 ደቂቃ መቆየት ቀኑን ሙሉ መልካም መዓዛ እንዲኖረን ይረዳል። 7. የአፕል ጭማቂ የአፕል ጭማቂ፣ ውሃ እና የሎሚ ጭማቂ በደንብ በማዋሃድ በመርጫ (ስፕሬይ) ውስጥ ማስገባት፤ ከዚያም ውህዱን በጠዋት ልብስ ከመልበሳችን በፊት ብብታችንን መርጨት ለመጥፎ ጠረን መከሰት ምክንያት የሆኑ ባክቴሪያዎችን ለማጥፋት ከፍተኛ ድርሻ አለው። 8. ሀይድሮጅን ፐርኦክሳይድ ሀይድሮጅን ፐርኦክሳይድን ከውሃ ጋር በመቀላቀል ብብትን መርጨትም እንዲሁ የብብት ጠረንን ለማስተካከል እንደሚጠቅም ነው የሚነገረው። በአጠቃላይ የሰውነት ጠረንን ለመጠበቅ በዋነኝነት ንጽህናችንን ለመጠበቅ ትኩረት ልንሰጥ ይገባል።

በጨጓራዎ ውስጥ የሚመነጨውን ከመጠን በላይ አሲድ(Hyperacidity) በቀላሉ በማስወገድ የቃር ችግሮን በነዚህ ምክሮች ያስወግዱ ምግብን እንዲፈጭ የሚያደርግ ከጨጓራ የሚመነጭ ፈሳሽ ጋስትሪክ ጁስ ይባላል፡፡ የሚመነጨው አሲድ ማለትም ሐይድሮክሎሪክ አሲድ የበዛ እንደሆነ ሐይፐርአሲዲቲ ተብሎ ይታወቃል፡፡ ይህ ነው በጨጓራ ላይ ቁስል የሚያስከትለው፡፡ ከመጠን በላይ አሲድ በጨጓራችን ውስጥ መከሰቱን የሚሳብቁ ምልክቶች 1. የሚያቃጥል የሕመም ስሜት ከጨጓራ ተነስቶ እስከ ደረት አልፎም ጉሮሮ ጋር የሚደርስ ቃር፡፡ 2. መራራ አሲድ ወደ ጉሮሮ ወይም አፍ መድረስ፡፡ 3. ሆድ መነፋት፡፡ 4. ደም ወይም ጥቁር ነገር የቀላቀለ አይነምድር፡፡ 5. ደም የተቀላቀለ ትውኪያ፡፡ 6. ማግሳት፡፡ 7. ምግብ ያለመፈጨት ችግር፡፡ 8. ስቅታ፡፡ 9. ማቅለሽለሽ፡፡ 10. ያለምንም ምክንያት ክብደት መቀነስ፡፡ 11. ደረቅ ወይም ፉጨት ያለው ሳል ወይም ዘላቂ የጉሮሮ ቁስል፡፡ 12. የጆሮ ሕመም፡፡ ከመጠን በላይ አሲድ በጨጓራችን ውስጥ እንዲከሰት የሚያደርጉ አባባሽ ምክንያቶች 1. ብዙ ምግብ መመገብ ወይም ከተመገቡ በኃላ ወዲያውኑ ጋደም ማለት፡፡ 2. ከልክ ያለፈ የሰውነት ክብደት፡፡ 3. ከባድ ምግብ ተመግበው በጀርባ መተኛት ወይም ወዲያውኑ አጎንብሰው ስራዎችን መስራት፡፡ 4. በመኝታ ጊዜ ምግብ መመገብ፡፡ 5. ውጥረት፡፡ 6. አሲድ ያላቸው እንደ ብርቱካንና ሎሚ ፍራፍሬዎችን መመገብ፣ከዚህ በተጨማሪ ቲማቲም፣ቸኮሌት፣ነጭና ቀይ ሽንኩርት ወይም ቅመም ወይም ቅባት ያላቸውን ምግቦች መመገብ፡፡ 7. የአልኮል፣የለስላሳና ካፊን ያለባቸው ቡናና ሻይ ምግብዎችን መመገብ፡፡ 8. ሲጋራ ማጨስ ፡፡ 9. ነፍሰጡር መሆን፡፡ 10. አንዳንድ መድኃኒቶች እንደ አስፕሪን፣አይቢፕሮፍን፣አንዳንድ የጡንቻ ማፍታቻ ወይም የደም ግፊት ሕክምና መድኃኒቶችን መውሰድ፡፡ መፍትሔ 1. ቅመም የገባበትና ማጣፈጫ ያለበትን ወይም የተጠበሰ ምግብ አይብሉ፡፡ 2. አልኮል መጠጦችን ያስወግዱ፡፡ 3. ወተት፣ክሬም፣ቅቤ ይመገቡ፡፡ 4. ሙዝ፣ማንጎ፣ሐብሐብና ቴምር የዘውትሩ፡፡ 5. ምግብዎን ቶሎ ቶሎ አይመገቡ፡፡ በደንብ አኝከው ይዋጡ፡፡ 6. በቀን ቢያንስ 8 ብርጭቆ ውሃ ይጠጡ፡፡ 7. ጣፋጭ ፣ቆምጣጣና ከፊኖ ዱቄት የተዘጋጁ ምግብዎችን አይመገቡ፡፡ 8. ጠዋት ፍራፍሬ፣ምሳ የተቀቀለ አትክልት መብላት ያሻል ከምግብ በፊት ሁል ጊዜ አንድ ኩባያ አጥሚት ይጠጡ፡፡ 9. በእግር መሄድ ያዘውትሩ ፡፤ 10. በተቻለ መጠን ደስተኛ ይሁኑ፡፡ 11. ያለ ሐኪም ትዕዛዝ ፀረ- አሲድ መድኃኒት በመግዛት በመድኃኒት ባለሙያ ምክር ይውሰዱ፡፡ መልካም ልምምድ መልካም የጤና ጊዜ ይሁንልዎ! እባክዎን ይህን ጠቃሚ መረጃ ለወገኖ እንዲደርስ Share በማድረግ ይተባበሩን! በቴሌግራም 👇 @DrSofonias