es
Feedback
ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

Ir al canal en Telegram

ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

Mostrar más

📈 Análisis del canal de Telegram ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

El canal ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias (@drsofonias) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 19 946 suscriptores, ocupando la posición 1 156 en la categoría Medicina y el puesto 1 680 en la región Etiopía.

📊 Métricas de audiencia y dinámica

Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 19 946 suscriptores.

Según los últimos datos del 28 junio, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de -539, y en las últimas 24 horas de -5, conservando un alto alcance.

  • Estado de verificación: No verificado
  • Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 25.64%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 7.06% de reacciones respecto al total de suscriptores.
  • Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 5 115 visualizaciones. En el primer día suele acumular 1 408 visualizaciones.
  • Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 9.

📝 Descripción y política de contenido

El autor describe el recurso como un espacio para expresar opiniones subjetivas:
ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 29 junio, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Medicina.

19 946
Suscriptores
-524 horas
-1197 días
-53930 días
Archivo de publicaciones
#ትርፍ አንጀት (appendicitis) ትርፍ አንጀት በቀኝ በታችኛው የሆድ ክፍል ትልቁ አንጀት ላይ ተቀጥላ የምትገኝ ትንሽ አካል ናት፡፡ #የትርፍ_አንጀት_ሕመም_በምን_ይከሰታል? የትርፍ አንጀት ሕ
#ትርፍ አንጀት (appendicitis) ትርፍ አንጀት በቀኝ በታችኛው የሆድ ክፍል ትልቁ አንጀት ላይ ተቀጥላ የምትገኝ ትንሽ አካል ናት፡፡ #የትርፍ_አንጀት_ሕመም_በምን_ይከሰታል? የትርፍ አንጀት ሕመም የሚመጣው በትርፍ አንጀትና በትልቁ አንጀት መካከል የሚገኘው አንገት ሲዘጋ ነው፡፡ ይህ በሠገራ፤ በሆድ ውስጥ ትላትል፣ በቁስ አካል ወይንም በካንሰር አልያም በኢንፌክሽን ምክንያት ሊዘጋ ይችላል፡፡ #የትርፍ_አንጀት_ሕመም_ምልክቶች • ማቅለሽለሽና ማስመለስ • ከእምብርት አካባቢ ጀምሮ ወደ ታችኛው የቀኝ የሆድ ክፍል የሚወርድ የህመም ስሜት • የምግብ ፍላጎት ማጣት • ትኩሳት • አየር ለማስወጣት መቸገር • ለመንቀሳቀስ መቸገር #የትርፍ_አንጀት_ምርመራ • የቃልና አካላዊ ምርመራዎች • የሆድ የቴሌቭዝን ምርመራ • የደምና የሸንት ምርመራ #የትርፍ_አንጀት_ሕክምና ምንም ዓይነት ምግብ ወይንም መጠጥ ወይንም ሕመም ለማስታገስ የሚወሰዱ የቤት ውስጥ መድኃኒቶች እንዳይወሰዱ ይመከራል፡፡ ይህም ያበጠው ትርፍ አንጀት እንዳይፈነዳ ያደርጋል፡፡ • በቀዶ ጥገና የትርፍ አንጀቱን ቆርጦ ማውጣት ይህም በህክምናዉ የምንለዉ ዋነኛው ሕክምና ሲሆን መግል የያዘ ትርፍ አንጅት መጀመሪያ መግሉን በማስወገድ አልያም ፀረ ባክቴሪያ መድኃኒቶችን በመጠቀም የቀዶ ጥገና ጊዜው የሚራዘምበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል፡፡ *ቀዶ ጥገናው ከተደረገ በ12 ሰዓት ውስጥ እቅስቃሴ መጀመር ይችላል። መልካም ጤንነት!! ሼር ማድርግ እንዳትረሱ ከቻላቹ በየ ግሩፑ አድርጉ የሥነ አዕምሮና የሥርዐተ ፆታ ኤክስፐርት በ Dr Sofonias የሚቀርቡ አስተማሪ ዝግጅቶችን ያገኙበታል እኔን ለማማከር የምትፈልጉ በቴሌግራም ሊንኩን በመንካት ታጉኙኛላቹ https://t.me/DrSofonias

ከአመጋገብ ጋር የተያያዘ የአእምሮ ህመም ========================== ሞዴል ኢሳቤሌ ካሮ ከአመጋገብ ጋር የተያያዘ የአእምሮ ህመም አለባት። የሰውነት ቅርፅ በጣም ያሳስባታል። እስዋ በጣ
ከአመጋገብ ጋር የተያያዘ የአእምሮ ህመም ========================== ሞዴል ኢሳቤሌ ካሮ ከአመጋገብ ጋር የተያያዘ የአእምሮ ህመም አለባት። የሰውነት ቅርፅ በጣም ያሳስባታል። እስዋ በጣም ወፍራም እንደሆነች ነው የምታስበው። በዚህ ምክኒያት ለመክሳት ትንሽ ምግብ ብቻ ትመገባለች። ከላይ የተጠቀሰው ፀባይ ቅብጠት የሚመስላቸው ሰዎች አሉ። በዘመናዊነት ምክኒያት የመጣ ፋሽን የሚመስላቸውም አይጠፉም። ነገር ግን ከሰውነት ቅርፅ ጋር የተያያዘ ጭንቀትና የተዛባ አመለካከት ከመቶ ሴቶች ሁለቱ ላይ የሚከሰት የአእምሮ ህመም ነው። አንዳንድ ሰዎች የሰውነት ቅርፃቸው ስለሚያሳስባቸው ከባባድ ስፖርቶችን በመስራትና የተለያዩ የምግብ አይነቶችን (Diets) በመመገብ ለማስተካከል ይሞክራሉ። ይህ ጥሩ የህይወት ዘዬ ነው። ነገር ግን እነዚህ ነገሮች በጣም የሚያሳስቧቸውና ከሚገባው በላይ የአእምሮ ጉልበታቸውን የሚወስዱ ከሆነ የአእምሮ ህክምና ባለሞያ ማማከር ሊረዳ ይችላል። ሰዎች ባላቸውና በሚፈልጉት ሰውነት መካከል ልዩነት ሲኖር ሁለት አማራጭ ይኖራቸዋል። አንደኛው ሰውነታቸው በአእምሯቸው የሳሉትን እንዲመስል ለመለወጥ መጣጣር ሲሆን ሁለተኛው አካላቸውን እንዳለው እንዲቀበለው አእምሯቸውን መለወጥ ነው። የአእምሮ ህክምና ላይ ሰዎች ሁለተኛውን ማድረግ እንዲችሉ እገዛ እናደርጋለን። ሞዴል ኢሳቤሌ ክብደት እንዳትጨምር በቀን አንዲት ቸኮሌትና በአንድ ሲኒ ሻይ በልታ የምትውልባቸው ቀናት ነበሩ። አንዳንድ ቀን ራሷን ትስት ነበር። በመጨረሻም በ28 አመቷ በዚሁ ህመም ምክኒት ህይወቷ አልፏል። የሥነ አዕምሮና የሥርዐተ ፆታ ኤክስፐርት በ Dr Sofonias የሚቀርቡ አስተማሪ ዝግጅቶችን ያገኙበታል እኔን ለማማከር የምትፈልጉ በቴሌግራም ሊንኩን በመንካት ታጉኙኛላቹ https://t.me/DrSofonias

#ከፍተኛ_ላብ 1. ምክንያቱ የማይታወቅ ሊሆን ይችላል። ይህም 6 ወርና ከስድስት ወር በላይ የቆየ ይሆንና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ምልክቶች ሊያሳይ ይችላል። • በቀኝና ግራ ሰውነት ክፍል ላይ እኩ
#ከፍተኛ_ላብ 1. ምክንያቱ የማይታወቅ ሊሆን ይችላል። ይህም 6 ወርና ከስድስት ወር በላይ የቆየ ይሆንና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ምልክቶች ሊያሳይ ይችላል። • በቀኝና ግራ ሰውነት ክፍል ላይ እኩል መታየት • የለት ከእለት ስራን ያደናቅፋል • ቢያንስ ከሳምንት አንዴ ይከሰታል • ከ25 አመት በታች ይጀምራል • በቤተሰብ ውስጥ ያለበት ሊኖር ይገባል • ማታ ማታ ላብ አይኖርም 2. ምክንያቱ የሚታወቅ ሆኖ • በሌሎች የተለያዩ በሽታዎች እንዲሁም በአንዳንድ መድኃኒቶች አማካኝነት ይመጣል። #ከመጠን ያለፈ የሰውነት ላብ በ3 አይነት መንገድ ይከሰታል። ሀ. በጭንቀት ጊዜ፡ በዋናነት መዳፍ፣ ውስጥ እግርና ብብት ላይ ይከሰታል ለ. የተወሰነ ቦታ ብቻ የሚከሰት ሐ. አጠቃላይ ሰውነት ላይ የሚከሰት #ምክናያት፡ በብዛት ምክንያቱ አይታወቅ • የስኳር በሽታ • የጭንቅላት እጢ • የህብለ ሰረሰር ጉዳት • የኩላሊት ቆብ ቀዶ ጥገና • ሰውነት ላይ የስብ ክምችት መፈጠር • የተለያዩ መድኃኒቶች • ለረጅም ጊዜ አልኮል መጠጣት • የሳንባ ነቀርሳ በሽታ፣ የልብ በሽታ #ምን_እናድርግ? • ከመጠን ያለፈ የመዋቢያ ሽቶ አለመቀባት • የግል ንፅህና መጠበቅ • ልብስን ቶሎ ቶሎ መቀየር • ሙቀት በሚሆንና ብዙ ህዝብ በተሰበሰበ ቦታ ወፍራምና የተደራረበ ልብስ አለመልበስ • ጭንቀት፥ ብስጭትን ማስወገድ • ብዙ ጊዜ ነፋሻማ ቦታ ላይ መዝናናት • የስኳር በሽታ ካለ መታከም • ውፍረትን መቀነስ • ለረጅም ጊዜ አንድ ቦታ አለመቀመጥ/ በተለይ ሙቀት በሚሆን ጊዜ • የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ካደረግን በኋላና አድካሚ ስራ ከሰራን በኋላ ሰውነታችንን በሳሙና መታጠብ።

የኢትዮጲያዊያን እናት የደግነት ጥግ አንድ ሆነው ተፈጥረው ሺ ሆነው ኖረዋልና እናመሰግናለን አልባሽ፤ አጉራሽ እናት እንዴት መታደል ነው የሰላም እረፍት ይሁንልዎት የኔ እናት ዶክተር አበበች ጎበና #
የኢትዮጲያዊያን እናት የደግነት ጥግ አንድ ሆነው ተፈጥረው ሺ ሆነው ኖረዋልና እናመሰግናለን አልባሽ፤ አጉራሽ እናት እንዴት መታደል ነው የሰላም እረፍት ይሁንልዎት የኔ እናት ዶክተር አበበች ጎበና #የኢትዮጵያልጅ #የኢትዮጲያንእናት

ፈስቡክ እና ቴሌግራም ምንም ዳታ ሳይበላብን ለመጠቀም አዲስ አፕ በጣም ፈጣን ሞክሩት እኔ ተመችኛል @telecomBirr

የድድ በሽታ/ ኢንፍላሜሽን/ ጅንጅቫይተስ/የድድ ኢንፍላሜሽን/ ብዙ ጊዜ የሚከሰት የድድ/የጥርስ ዙሪያ ላይ ህመም ሲሆን መቆጥቆጥ፣ ቅላትና እብጠት በድድዎ ላይ እንዲከሰት ያደርጋል:: ብዙውን ጊዜ ህመሙ መጠነኛ የሆነ ምልክት ስለሆነ ያለው ታማሚው ሳያስተውለው ሊያልፍ ይችላል:: ጅንጅቫይተስ በብዛት የሚከሰተው የአፍ ውስጥ ንፅህናን በደንብ በማይጠብቁ ሰዎች ላይ ሲሆን በዚህ የተነሳ በድድና ጥርስ ላይ የሚጋገር ነገር /plaque/ እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡ ይህ የተጋገረው ነገር በዐይን የማይታዩ ባክቴሪያዎችን የያዘ ነው፡፡ ጤናማ ድድ ጠንካራና ቀላ ያለ ሮዝ ቀለም ያለው ሲሆን የድድ ላይ ህመም ሲከሰት የሚከተሉትን ምልክቶች ሊያሳይ ይችላል፡፡ • ጥርሶን በሚቦርሹበት/በሚፍቁበት/ ወቅት በቀላሉ መድማት • የላላ እና የተነፋ ድድ • ሲነካ ህመም መኖር • የድድ እብጠት • የድድዎ መልክ መቀየር • መጥፎ የአፍ ጠረን መከሰት ናቸው;; ህመሙ እንዲባባስ የሚያደርጉት ደግሞ የሚከተሉት ናቸው፡፡ • የአፍ ጤንነት /ንፅህና/ በደንብ አለመጠበቅ • ሲጋራ መጨስ • የስኳር ህመም • እርጅና • የአፍ ድርቀት • የሆርሞን ለውጥ በተለይ በሴቶች ላይ እርግዝና ወቅት በወር አበባና የእርግዝና መከላከያ እንክብል በሚወስዱበት ጊዜ ሊከሰት ይችላል፡፡ ታዲያ ይህን ህመም ለማከም በቤት ውስጥ ማድረግ የሚገቡን የህክምና ዘዴዎች አሉ፡፡ 1. የጥርስ ህክምና ባለሙያው በሚያዘው መሰረት መደበኛ የሆነ የጥርስ እጥበት ማድረግ 2. ለስለስ ያለ የጥርስ ቡርሽ መጠቀምና ቢያንስ በአንድ ወር ቢበዛ በሁለት ወራት መቀየር 3. በቀን ሁለቴ አሊያም ከእያዳንዱ ምግብ መርሃግብር በኃላ አፍዎን ማፅዳት 4. የጥርስ ህክምና ባለሙያዎ ካዘዘልዎ የጥርስ ማጠቢያ አንቲሴፕቲክ መጠቀም ናቸው፡፡ በወቅቱ ካያስከትላል፡፡ ጅቫይተስ/የድድ እንፍላሜሽን/ ብዙ ጊዜ የሚከሰት የድድ/የጥርስ ዙሪያ ላይ ህመም ቢሆንም በወቅቱ ካልታከመ ግን ወደ ከፋ ቀጠይ የህመም ደረጃ ይሸጋገራል፡፡ ይህ በሽታ ፔርዮዶንታቲስ የምባል ሲሆን የጥርስ ደጋፊ የሆኑት የጥርስ አቃፊ አጥንትን የሚያጠቃ በሽታ ነው፡፡ በሽታው ድድን እና የጥርስ አቃፊ አጥንትን በመብላት፤ የሻህላ ክምችት በጥርሳችን እንዲኖር በመማድረግ · መጥፎ የአፍ ጠረን · የደድ በቀላሉ መድማት · ማድዳችን እንዲሸሽ · የጥርስ መነቃነቅ ብሎም · የጥርስ መውለቅን ያስከትላል፡፡

የድካም ስሜት የሚሰማዎ ለምን እንደሆነ ያውቀሉ? (በዶ/ር ሶፎኒያስ ኤርሚያስ) • አካል ብቃት እንቅስቃሴ አያደርጉም • በቂ ውሃን አይጠጡም • አይረን የሚባል ንጥረ ነገር ያላቸውን ምግቦች አያዘወትሩም • ቁርስዎን አይመገቡም • ለጤና ተስማሚ ከሆኑ ምግቦች ይልቅ ጣፋጭ እና ቅባታማ ምግቦችን ይመገባሉ • የሥራ ቦታዎ የተዘበራረቀ እና ያልተስተካከለ ከሆነ ነው • በሥራ ምክንያት ሰለሚያመሹ በቂ እንቅልፍ አለማግኝትዎ ነው፡፡ ጤና ይስጥልኝ

ቡግር ደህና ሰንብች ~~~~ቡግርን ለማጥፋት~~~~ ቆዳ ትልቁ የሰውነት አካል ክፍል (Organ) ሲሆን እጅግ በጣም ብዙ ጠቀሜታዎችም አሉት:: የቆዳ ህዋሶች (cells) ከውስጠኛው የቆዳ ክፍል (derms) ወደ ውጨኛው የቆዳ ክፍል (epidermis) በሚያደርጉት ጉዞ በየጊዜው ይቀየራሉ:: እነዚህ ህዋሳት በሚያረጁ ሰዓት ወደ ውጨኛው የቆዳ ክፍል ይቀርባሉ:: ከዚህ ላይ ከሌሎች ተመሳሳይ ህዋሳት ጋር በመሆን ጠንካራ የሆነ ቆዳን ከተለያዩ bacteria እና viruses የሚከላከል layer የፈጥራሉ:: ከ hair follicle ዉስጥ, ትንንሽ ወዝ (sebeum) አመንጭ እትዕኢ (glands) አሉ:: ወዝ ከ ቆዳ ህዋሳት ጋር በመሆን ወደ ውጨኛው የቆዳ ክፍል (epidermis) ይጉአዛል:: ነገርግን ብዙ ወዝ : የሞቱ የቆዳ ህዋሳት ወይም ቆሻሻ ከቆዳችን ላይ በሚኖርበት ሰዓት ጉዞውን ይረብሻል:: በዚህ ጊዜ የጉዞ መስመሩ ይዘጋል:: ባክቴሪያዎችም በዚህ ምቹ ሁኔታ ተሳታፊ ይሆናሉ:: ይህ መንስኤ acne vulgaris የተባለ ሁኔታ የፈጥራል:: acne vulgaris ብዙዉን ጊዜ የሚከሰት የቡግር አይነት ነው:: ቡግር ብዙን ጊዜ ጎረምሳ/ኮረዳ (teenagers) የሚታይ ቢሆንም በማንኛዉም የእድሜ ደረጃ ያሉትን ህፃናትም ላይ ሳይቀር ይታያል:: እናም ቡግርን ለማጥፋት ምን ማድረግ አለብን? እስኪ የተወሰኑትን እንመልከት:: 1. ፊትዎን በእጅዎ መነካካትያቁሙ! o እጃችን ብዙ ስራዎችን የምንሰራበት እና በቀላሉ በባክቴሪያ የሚጠቃ የአካል ክፍል ነው:: እጅዎን በየጊዜው ይታጠቡ:: (እንዴት መታጠብ እንዳለበዎት ከዚህ በፊት በለጠፍነው ፎቶ ማየት ይችላሉ) 2. ፊትዎን በቀን ሁለቴ የታጠቡ o ጧት እና ማታ ሞቅ ባለ ዉሃ በሳሙና ይታጠቡ:: 3. የምተቀሙትን cosmotics በደንብ ይመልከቱ •Cosmotics ብቻውን ቡግር ባያስከትልም ሲገዙ “oil-free” ወይም “noncomedogenic” የሚል የተፃፈባቸው ቢሆን ይመረጣል:: ከዚህ በተጨማሪ ለቆዳዎ የሚስማማውን የፋብሪካ ውጤት በደንብ ለየተው ይዎቁ:: ከላይ የተጠቀሱትን አድርገው አሁንም ችግሩ ካልተቀረፈ የሚከተለዉን ጥቆማ ይመልከቱ 4.. ጭንቀትን ያስዎግዱ o አንዳንድ የጭንቀት ባህርያት ቆዳን ይጎዳሉ:: ለምሳሌ ፊትን መንካት ማሸት: የግል ንጽሕናን አለመጠበቅ: የተዛባ የአመጋገብ ስርዓት.. o በተጨማሪም ሰውነታችን በጭንቀት ጊዜ በሚካሄደው የchemical ዉህደት የቆዳችንን መልክ የመቀየር አቅም አለው:: ለምሳሌ:- ወዝ የማመንጨት ደረጃ ይጨምራል:: የሄን ሁሉ አድርገው አድርገው ለውጥ የለዉም? እንግዲያውስ የመጨረሻዉን መፍትሄ ይመልከቱ! 5. የጤና ባለሙያ ያማክሩ! ማጋራት ደግ ነው! ዶ/ክ ሶፎ ስለ ጤናዎ በፍጥነት ዘወትር በየቀኑ አዳዲስ መረጃ ይፈልጋሉ አስተማሪ የቴሌግራም ቻላናችንን ቤተሰብ ይሁኑ

የሽንትዎ ቀለም ስለሰውነትዎ ጤና ምን ይነግርዎታል? ሽንት ኩላሊት ደምን አጣርቶ የሚያስወጣው ክፍል ሲሆን 95% ውሀ 5% ኤሌክትሮላይቶች እና ቆሻሻዎች ናቸው ። ጤናማ እና በቂ ፈሳሽ በሚዎስዱበት ጊዜ ሽንትዎ ብዙ የጎላ ቀለም በሌለው እና ነጣ ያለ ቢጫ ቀለም መካከል ነው፡፡በቂ ፈሳሾችን በማይወስዱበት ጊዜ ሽንትዎ ይበልጥ የተከማቸ ሲሆን ወደ ጠቆር ያለ ቢጫ ወይም የዓምበር ቀለም ይለወጣል ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የሽንት ቀለም እና መጠን እየዎሰዱ ያሉትን የውሀ መጠን ፣ ምግብ ፣ ቫይታሚን ጠቋሚ ነው። የተወሰኑ ምግቦች ፣ አንቲባዮቲኮች ፣ የህክምና ሁኔታዎች እና ቀለሞች እንዲሁ ለጊዜው የሽንት ቀለም ይቀይራሉ ፡፡ ከዚህ ቀጥሎ የተለያዩ የሽንት ቀለም አይነቶች እና ምክንያቶች እናያለን ። 1. በጣም ነጭ ከሆነ ከመጠን በላይ ውሀ እየጠጡ እንደሆነ ያመለክታል ። ይህም የተለያዩ በደም ውስጥ የሚገኙ ንጥረ ነገሮችን በተለይም ፓታሽየም እና ሶድየም መጠናቸው እንዲያንስ ያደርጋል ይህም የልብ ጡንቻን ይጎዳል ። 2. ጥቁር ቢጫ - ይህም በቂ ውሀ እየወሰዱ እንዳልሆነ ወይም ኬቶን በሽንት ውስጥ መኖር ሊሆን ይችላል ። በቂ ውሀ አለመውሰድ ደግሞ ለኩላሊት ጠጠር ፣ የሰውነት ፈሳሽ መቀነስ ፣ የኤሌክትሮላይት መዛባት ያስከትላል ። ኬቶን የሚፈጠረው በቂ የሆነ ስኳር (glucose ) ሳያገኝ ሲቀር እና ቅባት (fat) ለሴሎች ጉልበት ሲጠቀም ነው ። ይህም በሽንት መልክ ይወጣል ። ከፍተኛ የኬቶን መጠን አደገኛ የስኳር በሽታ ጉዳትን (DKA) ተከትሎ ሊመጣ ይችላል ። አነስተኛ መጠን ከሆነ ለረጅም ጊዜ ካልተመገብን ሊከሰት ይችላል ። 3. ደማቅ ቢጫ - ከበቂ በላይ ሰው ሰራሽ ቫይተሚን ቢ እየወሰዱ ከሆነ 4. ቀይ- ይህ የሚፈጠረው ደም በሽንት ውስጥ ሲኖር ነው ። ይህም በኩላሊት ጠጠር ፣ የኩላሊት እና የሽንት ፊኛ ኢንፌክሽን ፣ የፕሮስቴት እጢ ካንሰር ፣ የኩላሊት ካንሰር ፣ ከባድ ስፓርት 5. ጥቁር ብርቱካናማ / ቡናማ - የጉበት ችግር ያመለክታል ። የጉበት ፣ የሀሞት ቀረጢትና የቱቦዎች ችግር ተከትሎ የቢሊሩቢን በደም ውስጥ መብዛት ጋር ተያይዞ የሚከሰት ነው። 6. ሀምራዊ - አነስተኛ ደም በሽንት ውስጥ ሲኖር ወይም ቀይ ስር ከበላን 7. ሰማያዊ - የካልስየም መብዛት /hypercalcemia 7. አረፋ ካለ - ፕሮቲን በሽንት ውስጥ መኖር ፤ ይህም የኩላሊት ቁስለት ፣ የኩላሊት ጠጠር ፣ የልብ እና የኩላሊት መድከም ፣ የተለያዩ የካንሰር አይነቶች 8. ብዙ የሚሸኑ ከሆነ - በሽንት ውስጥ የስኳር መኖር ነው ፤ ይህም የስኳር በሽታ ያመለክታል ። @DrSofonias

ስለዚህ ጉዳይ በደንብ እዳብራራላቹ በተደጋጋሚ ግዜ በጠየቃቹ መሰረት እንሆ በደንብ ግልፅ አድርጌ ነው የፃፍኩላቹ መልካም ንባብ ስንፈት ወሲብ ፤ እንቅልፍ ነሺው ችግር ማህበረሰባችን ዝግ በመሆኑ ብዙ የማንወያይባቸው ችግሮች ሞልተዋል፡፡ አንዱ ስንፈተ ወሲብ ነው፡፡ እስኪ በዚህ ችግር ዙሪያ እንነጋገር፣ መፍትሄ ያለውም ወዲህ ይበል፡፡ የስንፈተ ወሲብ ችግርን ለማስወገድ አማን በላይ (መሪ ራስ) የግበረ ወሲብ ድክመት ፈውስ በማለት የሚከተሉትን 7 የመፍትሄ መንገዶች ከእፀዋት ማዘጋጅት እንደሚቻል ዘርዝረዋል፡፡ 1. መንስኤ እሰኪት (ሚያነሳሳ፣ የሚያነቃቃ) 2. መጽንኤ እስኪት (የሚያጠነክር) 3. ምፍትሄ ስኪት (የሚፈታ) 4. ዘኢያወርድ ገትር ( የማያስወርድ፣ የማስቸኩል) 5. ጸላኤ ወሲብ (አይነ ጥላ) (የግብረ ስጋ ጥላቻ ወይም ፋራቻ) 6. በሴት ላይ የሚደርስ የግብረ ስጋ ጥላቻና ፍራቻ 7. የውሃ ሽንት ለሚንጠባጠበውና ለሚከለክለው ፈረንጆች ደግሞ “ኢሬክታይል ዲስፋንክሽን” ይሉታል፡፡ ይህ ችግር በሴቶች የመነቃቃት ችግር ሲሆን በወንዱ ደግሞ የመከወን ብቃት ማነስ ነው፡፡ ከመከወን ብቃት አንፃር የወንዱን ችግር በ4 ይከፈላል፡፡ ምንም የመይቆም፣ በከፊል የሚቆም(ብቁ ያልሆነ አቋቋም)፣ የሚቆም ግን ወደ ስራ ሲገባ የሚወድቅና በራሱ ጊዜ አልፎ አልፎ የሚቆም፡፡ የብልት መቆም የብዙ ሕይወታዊ ክንዋኔዎች ማለትም የአንጎል፣ የሆርሞን፣ የስሜት፣ የአመጋገብ (የኃይል መጠን)፣ የጡንቻ፣ የደም ዝውውድና የሌሎችም ሕይወታዊ ክንውን ውጤት ነው፡፡ የአንዱ በትክክል አለመስራት ችግሩን ሊያባብሰው ይችላል፡፡ ክስተቱ በጤና ላይ ችግር ያስከትላል፡፡ ድብርትና ጭንቀት በማስከትል፣ በራስ መተማመንን በማውረድና ማህበራዊ/ቤተሰባው ግንኙነትን በማበላሸት ኑሮን ያበላሻል፡፡ የጭን ቁስል በመሆኑ ለጓደኛ እንኳ ተነገሮ ወደ መፍትሄ የሚሄድበት አይደለም፡፡ በሀገራችን ነገሩ እንደ ወንድነት መለኪያ በመወሰዱ በኑሮ ላይ ያለው ጫናና በባህርይ ላይ ያለው ጉዳት በቀላሉ የሚገመት አይሆንም፡፡ ለስንፈተ ወሲብ/ የብልት አለመቆም ዋናው ምክንያት የደም ዝውውር እክል ሲገጥመው ነው፡፡ ደም ወደ ተፈለገበት ቦታ ሂዶ ማሞቅና ማቆም ካልቻለ ብልት ይሰንፋል፡፡ የደም በተፈለገው ቦታ በተፈለገው መጠን አለመድረስ የችግሩ መንስኤ ነው፡፡ ስንፈተ ወሲብ ትልቅ የጤና ችግር ነው፡፡ ችግሩን ለማስወገድ የሰው ልጅ ብዙ ውጣ ወረድ አልፏል፡፡ የተለያዩ እጸዋትን ተጠቅሟል፡፡ የሌሎች እንስሳትን ቆለጥና የብልት ክፈሎች ለችግሩ መፍትሄ ይሆነው ዘንድ ተመግቧል፡፡ በዚህም ምክንያት ነብር ለህገወጥ አደን ተጋልጧል፡፡ የዘር ፍሬውን በቀዶ ጥገና በሌሎች እንስሳት ማለትም በጦጣ፣ በፍየል፣ በአጋዘን ቀይሮ አይቶታል፡፡ በብልቱ ውስጥም የብረት ጉማጅ አስከማስገባት ደርሷል፡፡ ይህን ችግር ለማስወገድ ያልወጣው ዳገት፣ ያልቧጠጠው ተራራ የለም፡፡ የኤልክተሪክ ንዝረትም በመልቀቅ ሞክሮታል፡፡ በዚህ ሁሉ ልፋት መካከል በ1998 (እ.ጎ.አ) “ቪያግራ” (sildenafil (Viagra) የሚባል የሚዋጥ መድኃኒት (የጨው አይነት ነው) ተሰራ፡፡ በታሪክ፣ በፍጥንት የተሸጠ መድኃኒት ቢኖር “ቪያግራ” ነው፡፡ በ3 ወር ውስጥ በብዛት በመታዘዝ ጫፍ ላይ ካሉት መድኃኒቶች አንዱ ነው፡፡ ለዚህ መድኃኒት የአሜሪካ የምግብና መድኃኒት አስተዳደር “ጥቅም ላይ ይዋል” የሚል ፈቃድም ሰጥቶታል፡፡ ይህ መድኃኒት ከሌሎች ሙከራዎች በተሸለ ችግሩን ለማቃለል ችሏል፡፡ ቢሆንም፣ብዙ የጎንዮሽ ጉዳት እንዳለበት ይታወቃል፡፡ “ታዲያ፣ መፍትሄው ምንድን ነው?” የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም፡፡ ችግሩ ያለባችሁ ወይም ሊከሰትብኝ ይችላል ብላችሁ ለምትሰጉ ወንድሜቼ ያለኝ ምክር፣ “አመጋገባችሁን አስተካክሉ፤ ውፍረት ካለባችሁ ቀንሱ፤ ስፖርት ስሩ ፤ የአካል እንቅስቃሴ አዘውትሩ፤ ከሚያበሰለስል ሀሳብና ጭንቀት ውጡ፣ ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች እንደ ደም ብዛት፣ ውፍረት፣ ስኳር፣ የልብና ተያያዥ በሽታዎች፤ ከመጠን ያለፈ የደም ኮሌስትሮልና ስብ ያሉ ነገሮችን በአኗኗር ዘይቤ አስወግዱ” የሚል ነው፡፡ በተጨማሪም ከእፅና ሱስ እንዲሁም እንደ ማጨስ ካሉ አጉል ልማዶች ራሳችሁን ነፃ አውጡ፡፡ እህቶችም፣ ባለቤቶቻችሁን ከላይ የተዘረዘሩ መፍትሄዎችን እንዲተገብሩና ከስነ ልቦና ጫና ነፃ እንዲሆኑ እርዷቸው፡፡ የሥነ አዕምሮና የሥርዐተ ፆታ ኤክስፐርት በ Dr Sofonias የሚቀርቡ አስተማሪ ዝግጅቶችን ያገኙበታል እኔን ለማማከር የምትፈልጉ በቴሌግራም ሊንኩን በመንካት ታጉኙኛላቹ https://t.me/DrSofonias

እነሆ ሌላ አስደሳች አዲስ ነገር! በአዲሱ የቴሌብር መተግበሪያ በቀላሉ የአየር ሰዓት ሲገዙ ስጦታ ይበረከትልዎታል፡፡ ቴሌብር የሞባይል መተግበሪያን የአንድሮይድ ተጠቃሚዎች apps ethiotelecom et አውርደው በቀላሉ ማግኘት ትችላላቹ https://t.me/telecomBirr

የወንድ የዘር ሴሎች በላፕቶፕ እና በጠባብ ፓንት ምክንያት ይጎዳሉ? ለወንድ መሃንነት ተጠያቂ የሚደረጉ ብዙ ነገሮች አሉ። ብዙ የተሳሳቱ ምክንያቶች የሚሰነዘሩ ሲሆን አብዛኞቹ ሙቀት ከሚፈጥሩ ቁሶች ጋር የተያያዙ ናቸው። ጥብቅ ያለ ፓንት፣ ላፕቶፕ፣ ሳውና እና ሙቅ ውሃ ዘር ፍሬ ላይ ሙቀት ስለሚፈጥሩ ብዙ ሰዎች የመሃንነት መንስኤ ናቸው ብለው ያስባሉ። እርግጥ አንዳንዶቹ ልምዶች አሉታዊ ተጽእኖ ቢኖራቸውም ሌሎች ደግሞ ምንም ጉዳት የማይፈጥሩ ናቸው። የሴንተር ፎር ሜል ፈርቲሊቲ ዳይሬክተር የሆነው ዶክተር ኤድመንድ ሳቤነ በዚህ ጉዳይ ላይ እንደሚከተለው ማብራሪያ ይሰጣል፦ ጥብቅ ያለ ፓንት ጠበቅ ያለ ፓንት አሳስቧቸው ቦክሰር ብቻ የሚያደርጉ ብዙ ወንዶች አሉ። ጠበቅ ያለ ፓንት የዘር ፍሬዎችን ከሰውነት ጋር አነካክቶ ስለሚይዝ ብዙ ወንዶች ይፈሩታል። ዶክተር ሳቤነ ግን የሚከተለውን ይላል፦ “ጥናቶች የሚናገሩት ለውጥ እንደሌለው ነው። እኛም ታካሚዎችን የምንመክረው የተመቻቸውን እንዲለብሱ ነው።” ላፕቶፕ ብዙ ሰዎች ላፕቶፕ ታፋቸው ላይ አስቀምጠው ይጠቀማሉ። ላፕቶፕ ሙቀት ስለሚያመነጭ ከግዜ በኋላ የዘር ፍሬዎች ሙቀት ይጨምራል። ይህንን ሙቀት የሚቀንሱ አንዳንድ ሞዴሎች ቢኖሩም ዶክተር ሳቤነ ላፕቶፕን ዴስክ ወይም ጠረፔዛ ላይ አስቀምጠን እንድንጠቀም ይመክራል። ሳውና እና ሙቅ ውሃ ውስጥ መቀመጥ ሙቅ ሳውና ውስጥ ተቀምጠን እንኳ የዘር ፍሬዎች እራሳቸውን ማቀዝቀዝ ይችላሉ። ሙቅ ውሃ ውስጥ በተቀመጥንበት ግን የዘር ፍሬዎቻችን ሙቀቱን መቋቋም ሊከብዳቸው ይችላል። በዚህ ሁኔታ የዘር ፍሬዎች ሙቀት ከሚመከረው የሙቀት መጠን ከፍ ይላል። የዘር ጉዳይ ካሳሰብዎ ውሃውን ያቀዝቅዙ ይላሉ ዶክተሩ። ስልክ ስልክዎን ከዘር ፍሬዎ ያርቁ ይላል ዶክተር ሳቤነ። “በስልክ ላይ ብዙ ምርምር ሰርተናል። የወንድ ነባዘር ለስልክ ራዲዬሽን ሲጋለጥ ጉዳት ይደርስበታል” አደንዛዥ እጽ አንዳንድ እጾች ነባዘር ላይ አሉታዊ ተጽእኖ አላቸው። ሲጋራ ማጨስ ማቆም ፍሬአማነትን ይጨምራል። አጫሾች ላይ የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው ነባዘራቸው ላይ የተወሰነ ቶባኮ ይኖራል። እነዚህ ኬሚካሎች የነባዘር ቁጥርን ይቀንሳሉ። የወንድ ነባዘር የሚንቀሳቀስበት ፍጥነትም ቢሆን ይቀንሳል። ቶባኮ ስፐርም ውስጥ ያለው ዲኤንኤ እንዲበተን ምክንያት ይሆናል። ዶክተር ሳቤነ ተካሚዎቹ ማጨስ እንዲያቆሙ ያሳስባል። በተለይ ለመውለድ በሚሞክሩበት ግዜ። ስቴሮይድ አንዳንድ ሰዎች አናቦሊክ ስቴሮይድ ቴስቶስትሮንን ስለሚጨምር ለፍሬአማናት ጥሩ ነው ብለው ያስባሉ። እውነታው ግን በተቃራኒው ነው። የዘር ፍሬዎች በሰውነት ውስጥ በቂ ቴስቶስትሮን አለ ይሉና ስራቸውን ያቆማሉ። ለመውለድ በሚሞክሩበት ግዜ ስቴሮይድ ባይወስዱ ይመከራል።