cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Let's Save Orthodoxy and humanity( ሰብእናንና ኦርቶዶክሳዊነትን እንታደግ)!!⁉️

ሰብእናንና የመንፈስ ልዕልናን ካዳበሩ ቤተሰቦች ጋር በመተባበር በሰብእናና በኦርቶዶክሳዊነት ላይ የሚፈጸምን(የተፈጸመን) ሥርዓታዊ፣መዋቅራዊ፣ሕጋዊ፣መናፍስታዊ፣ስነልቦናዊ ..ጥቃቶችንና አጥቂዎችን እንዲሁም ከጥቃት የመዳኛ መንገዶችን(መፍትሔ) የሚመለከትበት ቻናል ነው::

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
851
Suscriptores
-224 horas
-107 días
-630 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

01:05
Video unavailableShow in Telegram
"አማኝ ናት፥ ሀይማኖት አላት፥አባት ትወዳለች፥ታሪክ አላት" ----------------------------------------------- ሐሰተኛ ቆዳና ቆብ ለበስ የሰለጠኑ አጥፊዎችን ተጠቅመው የኢትዮጵያን ሕዝብ ለማፍዘዝ የሰሩት ተንኮል....👆
Mostrar todo...
2.71 MB
ብፁዐን ሊቃነ ጳጳስት አባቶቼን አንድ ልጅ አባቱን በፍቅርና በትህትና ግብረመልስ እንደሚያቀርብለት ሁሉ በሹክሹክታ ያይደለ በአደባባይና በግልጸጽ እነሆ እወቅሳለሁ፦ ባለፈፉት 50 ዓመታት በቀጥታና በግልጽ የቤተክረሰስቲያንን ቀኖና በተለይ ክብረ ክህነትን፣ ልዕልና ሲኖዶስንና የምእመናን በክርስቶስ አንድመሆን የሚፈታተኑ አያሌ ነገሮች በዐይናችሁ ፊት ተፈጽሟል። የሩቁን ትተን የቅርብ ዘመኑን እንኳ ብንመረምር  በሚገባ ፍጥነት እርማት አትመስዱም፣ የሚመለሰውን መልሶ የሚያምፀውን አታወግዙም። በዚህ መሠረት በዝምታችሁ ተበረታትቶ ወደ ከፍተኛ ጥፋት የተሸጋገሩና ልማድና ሕግ እሽከመሆን የደረሱ ክፋቶች በዝተዋል። በምእመናን ከሚታወቁት መካከል ጥቂቶቹን ለምሳሌ:- 1) ከሲኖዶስ ጉባኤ ተስፈንጥረው ወጥተው በጀዋር የዘሮኝችና አሳዳጆች የፖለቲካ ቡድን ቴሌቪዥን ላይ "የተያዘ ክህነት የለም፣ ሥራችሁን ቀጥሉ" በማለት የቋሚ ሲኖዶሱን ውሳኔ በፖለቲካ የሻሩትን የቀድሞ አቡነ ሳዊሮስ፣ ዜና ማርቆስና ፣ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ላይ ምንም እርምጃ አልወሰዳችሁም 2) በኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ጉባኤ ላይ በአደባባይ "ለምንሊክ ተፈናቃይና ለማኝ  ቀያችሁን ጥላችሁ የሄዳችሁ እናንተ ናችሁ ---- ታቦት ወደ ሰሜን አይወርድም እንዴ? ለምን እኛን "አገሌዎችን ይወደናል?" እያለ ጎሣን እየቀደሰ ሃይማኖትን እያረከሰ ዘረኝነት በከደባባይ የሰበከ ቄስ በላይን አልቀጣችሁም 3) በዘር ፖለቲካ የሚጨፈጨፈውን ክርስቲያን የበለጠ ለማስጨረስ በዘር ፖለቲካ አገልጋይነት ዓለም ያወቀውን እና "በኦሚያ ሰው የሚሞተው እምዬ ምኒልክ እያለ እንጂ ክርስቶስን ብሎ የሞተ የለም" ብሎ የሰበከውንና የአሁኑን የብልጽግና ፓርቲ የጎሣ ሲኖዶስ በውጭ አገር ድጋፍ የሚያሰባስብ "ቄስ" ሳሙዔል ብርሃኑ አልተቀጣም 4) በዘረኝነች አብዶ የትግራይን ኦርቶዶክሳዊያን በማሳሳትና የወያኔን የዘረኝነት ነቀርሳ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ለማድረግ ለዓመታ የሚደክመውን "አባ" ሠረቀ ብርሃን ምንም አልተባለም 5) በትግራይ ቤተክነት ሆነናል በማለት ክርስቶስን ሳይሆን የጎሣን ፖለቲካ የሚያገለግሉ ጳጳሳትና ካህናት አልተቆነጠጡም 6) በዓመት የተመዘገበ ግማሽ ሚሊዮን  ሕፃናትን በውርጃ እንገድላለን። ሲኖዶሱ በግልጽ ይህ በአደባባይ ቀኖናችንን ጠቅሶ አላወገዘንም 7) አዲስ አበባ ውስጥ ብቻ በመረብ ላይ መረጃው የወጣ 60ሺ ሰዶማዊ አለ። ይህ ግልጽ ተግሣጽ፣ የንስሐ ጥሪና ውገዘት ተላልፎበት ምመናን አልተጠነቀቅንም 8) 65 በመቶ ወጣ በ16 ዓመቱ በዝሙት ይጠመዳል። ሲኖዶሱ ስለዘመኑ ወጣቶችና ቤተሰብ ምንም አላለም። 9) ትዳር እንደ አሕዛብ ለተፈቀደ ሩካቤ ሆኖ ክርስቲያናዊ ትርጉሙን አጥቷል 10) ክርስቲያኖች በዘረኛ ፓርቲዎች ሥር እየተደራጁ ሲፋጁና ጥላቻ እንደ እሣት ሲንቀለቀል ሲኖዶሱ የዚህን አይነት ፖለቲካ የሚከተሉና የሚመሩ የጥምቀት ልጆች አላወገዘም። ---- ወዘተ። ይህ ተጠራቅሞ በእኛ በምእመናን የኃጢአትና የርኲሰት ሕይወት ጋር ተደምሮ ጎርፎ ሆኖ እያጠፋን ነው። አሁን አባቶች ይህን የሁላችንንም የቀኖና ጥሰትና በግልጽ እንደ ሕዝብና መሪዎች የፈጸምነውን ክፋት ዘርዝራችሁ በትምህርትና በውግዘት ከጠፋንበት እንድተጥሩንና ከሞት የማያተርፈን መሞጋገሱን ለጊዜው ብንገታው ይበጀናል። ሞትን የሚያመጣ ዝምታና የጥፋት ሰላም ምናልባት የሚወደደው  ሥጋዊ ድሎትና የምቾት ኑሮ አደንዝዞ የነፍስን ነገር ላስረሳው  ቁስ አምላኪ እንጂ  የክርስቶስን አደራ ለተቀበሉትና ዓለምን ለናቁት አይሆንም። ሌላው ቀርቶ ምእመንም ከነፍሱ ነገር የሚበልጥበት ሊኖር እንደማይገባ አስተምህራችሁ በዓለም ውስጥ የትርህምትና የቅድስና ሕይወት እንዲኖር መመራት ይገባል ወቀሳዬን ፈጽሜአለሁ። ተግባራዊ ድርሻው የአባቶች ነው። አንድም በተለመደው መቀጠል ወይንም እውነታውን ተጋፍጦ የተጠራንበት የክርስትናን ስሟን በሚመጥን መልክ እንድንገለጥ ማድረግ።  ይህን እንድጽፍ ያነሳሳኝ ይህ መልእክት ነው 😃👉 https://l.kphx.net/s?d=5661582271829333716&extra=Q1RSWT1FVCZMTkc9YW0=&g=c82b378cb8975fbf75b15afb810fac8a
Mostrar todo...
በሰሜን አሜሪካ የአዲሱ ሲኖዶስ አስተባባሪ ኮሚቴ ሊቀመንበር ቄስ ሳሙኤል ጀቤሳ በፊንፊኔ እና አካባቢው የሚኖሩ የኦሮሞና ሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ተወላጆች በነቂስ ወጥተው አዲሱን ሲኖዶስ እንዲደግፉ ጥሪ አቀረቡ።

Good Example how false narrations are developed. This article can give those of you who are still asleep about how ethnicity idol worshipers you can produce, reproduce, recycle and refabricate false narrations that has led 36 years for genocide against Orthodox Christians and the Amhara.
Mostrar todo...
Oromo_of_Tana_river_How_OLF_and_Ethnic_elits_creat_false_narrations.pdf1.70 MB
Mostrar todo...
fበካምፓላ ያሉ አባቶች ዛሬ ጎበኙኝ!!! የነበረን መርሃግብር  ምን ይመሰላል? ታዋቂ አባቶች በእለቱ አብረውኝ ነበር!!!

የነፈንታሁን ዋቄ አቋም ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያናችን ባሸከመቻቸው በ151ኛ በተመዘገበው ዳዊት በተናገረው መርሆ ላይ የተመሠረተ ሆኖ ከፋኖ መፈክር ጋራ ተቀራራቢ ቢመስልም፦ እነ ፈንታሁን ይዘው የተነሱት ከፋኖው ለየት ያለ ቅዱስ ጳውሎስ የመንፈስ ሰይፍ ብሎ የገለጸው ረቂቅ ትጥቅ ነው፡፡ ይህ ረቂቅ ትጥቅ በ149 ነኛው መዝሙረ ዳዊት ላይ እንደሚከተለው የሰፈረው ነው፡፡ “ወከመ ይእሥሮሙ ለነግስቶሙ በመዋቅህት ፡፡ ወለክብራኒሆሙኒ በእደ ሰናስለ ሐጺን፡፡ ከመ ይግበር ኩነኔ ዘጽሑፍ ላዕሌሆሙ፡፡ ክብር ይእቲ ዛቲ ለኩሉ ጻድቃኑ” የሚለው ቃል ነው፡፡ ይህም ማለት፦ “መሪወቻቸው ሞራለ ቢሶች ሲሆኑ እግሮቻቸውን በእግር ብረት እጆቻቸውን በዛንጅር አስረው በተጻፈው ሕጋቸው ይቀጧቸው ዘንድ ለተመረጡት እድል ተሰጣቸው” ይህን የዳዊትን ሀሳብ ክርስቶስ ለዮሐንስ በራእይ “ወዘሰ በመጥባሕት ይቀትል ሀለዎ ይሙት በመጥባህት፡ ወዘሂ ውእቱ ትዕግስቶሙ ወብጽዕት ሃማኖቶሙ ለቅዱሳን፡ ወኢአንክሮቱ ለሰይጣን” ብሎ ገለጸው ፡፡ (ራእየ ዮሐንስ 13፡ 10)፡፡ እነ ፈንታሁን ብዙወቹ ከሚከሰሱበት ከሰይጣን ወጥመዶች ከዝሙት ከስለት ገንዘብ ከዘረፋና ከመወላወል ገለል ያሉ እንደ ቀዳሜ ሰማእቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ “እናንት አንገተ ደንዳኖች ልባችሁና ጆሯችሁ ያልተገረዘ እውነቱን የምትቃወሙ” (የሐዋ 7፡51) እያሉ ከቀኖናው ከነገረ መለኮቱ ርቀው ያሉትን ለመገሰጽ እግዚአብሔር ያደላቸው በልዕለ አእሞሮ ላይ ያሉ ናቸው፡፡ 4ኛ ዶክተር ዮናስ ለሲኖዶሱ የሰጡትን ከንቱ ውዳሴ የቤተ ክርስቲያንችን አስተምህሮ አንኮታኩቶ ሲጥለው ከዚህ በታች የሰፈረውን እንመልከት፡፡ “ወኤጲስ ቆጶስሰ ዘነሥአ ክህነተ እምእግዚአብሔር ከመ የዐቀብ ሥጋ ውሰነፍስ እምኀጉል በከመ ነፍስ ትከብር እምሥጋ ከማሁ ክህነትኒ ትትሌዓል በክብር እመንግሥት ወይእቲ ተ አሥሮ ለዘይደልዎ ኩነኔ ወትፈትሖ ለዘይደልወ ፋትሐ፡፡ ወበከመ ክህነት ትትሌዐል እመንግሥት ወከማሁኬ ትትሌዐል ኩነኔሁ ለዘይትቃረና ለክህነት ይፈደፍድ እምኩነኔሁ ለዘይትቃወሞ ለንጉሥ”(ፍ አ 9፡289_290) ፡፡ ማለትም፦በእግዚአብሔር ፈቃድ ላይ የተመሠረተ ክህነት በምዳራዊ ፈቃድ ጉስቁላና በቅድስና ተዐቅቦ የተለየ ስልሆነ በምድራዊ ፈቅድ ላይ ከተጻፈው ሕግ በላይ ነው፡፡ በብጽዕናውና በቅድስናው ከምድራዊው መንግሥት በላይ ስለሆነ ከምድራዊውም ሕግ በላይ ነው፡፡ ምድራዊውንም ሰማያዊውንም ሕግ በምሳሌነት አክብሮ በማስከበር ከመንግሥት የላቀ ከፍተኛ ልዕለ አእምሮ አለው፡፡ ሲኖዶሱ በዚህ ሁሉ ድርብርብ ተቀብዖቱ ከመንግሥት የላቀ ሥልጣንና ሀላፊነት አለበት፡፡ ምድራዊው መንግሥት በሥጋዊ ፍላጎት ተፈትኖ ሀላፊነቱን ረስቶ ራሱ ከሰራውና አስፈጽመዋለሁ ብሎ ከማለለት ህግ በታች ሲወድቅ ፦ ሲኖዶሱ የመገሰጽ ብሎም ህዝብ የካደው መንግስት የተሰነዘረበትን የአመጽ ዱላ ሰባብሮ እንዲጥለው የማስተማር ግዴታ አለበት፡፡ ህዝብ የተሰነዘረበትን የአመጽ ብትር ሰባብሮ እንዲጥለው የተቀደሰው ሲኖዶስ በሚያደርገው ቅስቀሳ፡ ከሀዲው መንግሥት ከሚሰነዘረበት የአመጽ በትር ሲኖዶሱ ሳያፈገፍግ ከህዝብ በፊት ድብደባውን የመቀበል ግዴታ አለበት፡፡ ዶክተር ዮናስ ለዘመናችን ሲኖዶስ የሰጡት ከንቱ ውዳሴ ተንኮታኩቶ እንደወደቀና እነ ፈንታሁን ዋቄ በቀኖናችን ላይ መቆማቸውን ከዚህ በላይ ክ 1 እስከ 4 በዘረዘርኳቸው አንቀጾች ካሳየሁ በኋላ ለዶክተር ዮናስና ለመሰሎቻቸው ከዚህ በታች በማቀርባት በ5ኛዋ አንቀጽ የተማኅጽኖ ጥሪ በማቅረብ ሀሳቤን እቋጫለሁ፡፡ 5ኛ ለዶክተር ዮናስና ለመሰሎቻቸው የቀረበ የተማሕጽኖ ጥሪ፦ ዶክተር ዮናስ ብሩ ሆይ! ለጽሑፈዎ መነሻ አድርገው ለፋኖና ለነ መመምህር ፋንታሁን ለሰጡት ምክር ራሰዎ “The Imperative Comparative: Lessons from the EOTC and Fano” ያሏትን እኔም ሐሳበዎን ለመቃወም “The Imperative Comparative: Lessons from the EOTC and Fano” ያሏትን እንደመግቢያ አድርጌ ተጠቅሜአታለሁ፡፡ የተቃውሞ ጽሑፌን በገባሁባት ለመውጣት ብቻ ሳይሆን ለማቀርብለዎ ጥሪ መገቢያ ካደረኳት ሌላ የተሻለ ሀሳብ ስላላገኘሁ ጭምር እንደ መግቢያ ያደረኩትን ለመጥሪያነት ተጠቅሜ መደምደሚያ ባደርጋት ስነጽሑፍ ነውር አያደርግብኝምና በመግቢያየ የጀመርከበትን የተቃውሞ ሐሳብ የጥሪየ ተማኅጽኖ አድርጌ ሳቀርብለዎ በደጊመ ቃልነት እንዳይሰለቹ አደራየ ጥብቅ ነው ፡፡ የዘመናችንን ሲኖዶስ ከፋኖ ጋራ ፖለቲከኞችን ከነፈንታሁን ዋቄ ጋራ በማነጻጸር ሲኖዶሱን እያደነቁ፦ ፋኖንና የፋኖ ደጋፊወችን ከፈንታሁን ዋቄ ጋራ ደምረው የነቀፉበት ሀሳብ እንድንማርበት ያቀረቡልንና በመቀጠለም “The same screwed up culture is what has allowed መምህር Fantahun Waqe to jump out of the woods of the 18 th century and cacophonize the 21 st century” ብለው ያቀረቡትን ከቤተ ክርስቲያናችን መርሆ ጋራ መጋጨቱን አሳይቻለሁ፡፡ የገለጹበት መንገድ ከቤተ ክርስቲያናችን ቀኖናዊ መርሆ ጋራ የተቃረነ ቢሆንም፡ ባነጋጋሪነቱና በቀስቃሽነቱ አእምሮየን ቀስቅሶ የሲኖዶሱን ዝቅጠት በትኩረት እንድመለከተው አድርጎኛል፡፡ ይዝለቁበት አይዘለቁበት እርግጠኛ ባልሆንም የዘመናችን ዲያቆናት እነ ፈንታሁን ዋቄ አሁን የሚመሩበት መንገድ ቀዳሜ ሰማእት የምንለው ቅዱስ እስጢፋኖስ የሄደበትን ሐዋርያዊ ትውፊት እንዳይ አድርጎኛልና አመሰግነወታለሁ፡፡ ይሁን እንጅ እንደ መልካም ምሳሌ አድርገው ያቀረቡት ሲኖዶስ በቀኖናችን ሲመዘን መወገዝ መወገድ የሚገባው እንጅ ለመልካም ምሳሌነት መጠቀስ እንደማይገባው ራሱ ሲኖዶሱ በራሱ ይመስክራል፡፡ እርሰዎ የሲኖዶሱን ስህተት እንደ መልካም ምሳሌ አርገው ማቅረበዎ እኔ አይደለሁም ቀኖናችን ይቃወመወታል፡፡ ታዲያ ይህን ቀኖናዊ ተቃውሞ በአኮቴት ተቀብለው አመለካከተወን አስተካክለው፡ ለቤተ ክርስቲይናችንም የሚጠቅመው ቀኖናውን መከተል መሆኑን ተገንዝበው ፡ ሲኖዶሱ ብልጽግናን መከተሉን እርግፍ አርጎ ትቶ ቀኖናችንና ዶክትሪናችንን በመከተል እነ ፋንታሁን ጸንተው የቆሙበትን የቅዱስ እስጢፋኖስን ምሳሌ ይከተል ዘንድ በነካ እጀዎ በጽሑፍ የጥሪ መልእክት እንዲያቀርቡለት በትህትና እጠይቀወታለሁ ፡፡ ይህን ቢያደርጉ ለቆሙላት አገረዎም ለቤተ ክርስቲያናችንም እንደሚበጅ እርግጠኛ ሆኜ ልገልጽለወ እወዳለሁ፡፡ እግዚአብሔር መልካም መሪወችን ለኢትዮጵያ ይፍጠር !
Mostrar todo...
👆👆👆👆👆 አምስቱ የጎሣ ጳጴሳት አዕማደ ምሥጢራት:- የሕወሃት እና የኦነግ-ኦሮሙማ/ብሎጽግና ጳጳስ ለመሆን ማሟላት ከሚገባህ መስፈርት መካከል 1) በጥምቀት ሰው ሁሉ ከሥላሴ በመወለድ አንድ አዲስ ዘር መሆኑን በመካድ ሰዎችን በነገድና በቋንቋ የሚለያዩና የሚበላለጡ መሆናቸውን ማመን እናጰየሐዋርያት ቀኖናን መኔድ 2) አማራ የተባለ ነገድ መጥላት 3) የኢትዮጵያን ረዥምና አዎንታዊ ታሪክ በጎሣ ርእዮተ ዓለም አንጻር በሐሰት ትርክት መቀየርን መቀበል 4) ክብረ-ሰብእ ተጨፍሎቆ በበክብረ ጎሣ/ብሔረሰብእ መቀየሩን ማመን 5) ታላቋቋን አገር በትኖ በአገር ውስጥ አገራት ለመፍጠር አማራና ኦርቶዶክስ ክርስትናን ማጥቃት ናቸው
Mostrar todo...
ከወይኑ ግንድ ያልተቆረጡ በወይኑ ጥፍጥና ከልባቸው ጣፋጭ ነገር የሚመነጭ እውነተኛ እረኞች ሞትን ሳይፈሩ ምስክሮች ሆነዋል።መጽሐፍ አብነት አድርገን እንድንከተላቸው ያዘዘን እነዚህን ነው።ዛሬ ራሳቸውን ለድሎት የሚያሰማሩ፥ለማንጋው የማይራሩ ጨካኞችን ተከትለን መሰነካከል አይገባም።የጸኑትን መመልከት ነው ያለብን።የዛሬዎቹን ከተመለከትን ስንኳንስ ክርስቲያን እንደ ሰው እንኳ ማሰብ አንችልም።የወደቁትን ትተን የበረቱትን እንመልከት።የወደቁትን አብነት የሚያደርግ ራሱ የወደቀ ነው።ዘወትር ልቦችንን ስበው ወደ ልዕልና የሚያወጡ ቅዱሳንን እንመልከት። የእግዚአብሔርን ቃል የነገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ እንዳለን ቅዱስ ጳውሎስ ።ዕብ 13:7
Mostrar todo...
http://www.youtube.com/@Orthodox_Secular_FantahunWakie ===================== እንደ አንድ የክርስቲያን ቤተሰብ አባል ራሳችንን እንፈትሽ ፡- ቅጣት የጠራነው በሚከተሉት ግልጽና እንኳንስ በሌሎችና በአግዚአብሔር እኛው ራሳችን በየከተማውና በየገጠሩ  ሲፈጸም በዓይናችን በምናየው የክርስቲያኖች ርኵሰት ነው፡- (1) የክርስቲያን ሴቶች ነፍሰ ገዳይነት፡- በዓመት ወደ 1,000,000 ሕፃናት በክርስቲያን ሴቶች ይገደላሉ (ውርጃ) (https://pubmed.ncbi.nlm.nih.gov/28825902/)። ይህ ቁጥር በኦሮሚያና በቡኒሻንጉል፣ በወያኔ ምከኒያት በአፋርና በአማራ፣ በትግራይ ሕዝብ በጦርነት ከሚያልቀው ነፍስ ይበልጣል። (2)  ትዳርን ማፍረስ፡- በኢትዮጵያ ውስጥ በሴቶች ከሚፈጸሙ ትዳርን የማፍረስ አጠቃላይ ብዛት 70 በመቶ በኦርቶዶክሶች ይፈጸማል (https://core.ac.uk/reader/234691210). ትዳርን ማርከስ፦ በአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ፌደራል  መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአንድ ችሎት ብቻ ከመስከረም 7 ቀን 2012- እስከ ሰኔ 8 ቀን  2014 (እ.አ.አ)   16,035 ጥንዶች ትዳራቸውን አፍርሰዋል (  https://www.facebook.com/265784033571676/posts/divorce-in-the-capital-ethiopia-staggeringly-high-some-are-still-with-an-opinion/512951702188240/) \ (3) የወጣት አመንዝራነት፡- በ2014 ዓ.ም. ዕድሜቸው ከ15-24  የተማሪ ወጣቶች  አመንዝራነት (የወዲፊቶቹ አገር ተረካቢዎች) ፡-በ2014 ለጥናት በናሙና (ሎተሪ) ተመልምለው መጠይቅ ከተደረገላቸው ወጣቶች  መላከል 41.4%  አመንዝራ ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ 37.1% ከሁለትና ከዚያ በላይ ሰው ጋር ያመነዝራሉ፤     (https://bmcpublichealth.biomedcentral.com/articles/10.1186/1471-2458-14-301) (4)የወጣት ሱሰኝነት፡-  የዩኒቭረሲቴ ተማሪዎች  by 67%, 67%, እና 33%  በቅደም ተከተል የጫት፣ የሲጋራ፣ የአልኮል ሱሰኞች ናቸው  (https://www.researchgate.net/publication/353241458_Substance_Abuse_and_Legal_Consideration_in_Ethiopia ) (5)  ሰዶማዊነት፡- ቱሪሰት ከሚርመሰመስባቸው ከላሊበላ፣ ጎንደር፣ ባህር ዳር፣ ሐዋሳ፣ አርባ፣ ምንጭ፣ አዳማ፣ ወዘተ ያለውን የሰዶማዊያን መረጃ ሳንጨምር በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ  በ2021 (እ.አ.አ)  ራሳቸውን በግልጽ ሰዶማዊ ነን የሚሉና የገለጡ ሰዎች 60,000 ናቸው (https://africlaw.com/2021/10/01/time-to-consider-decriminalising-homosexuality-in-ethiopia/) የኃጢአታችንና የርኵሰታችን ውጤቱ፡- በመጽሐፍት እንደተነገረ  ለዘረኛ፣ አመንዝራ፣ ርኵስ፣ ነፍሰገዳይ፣ ሰዶማዊ ትውልድ የሚገባው  ቅጣት  ነው (ዘሌ 18፣22፤ ሕዝ 11፣21፤ ኢሳ 1፣20፤ ዘኁል 5፣27)። በፍቅሩ ጽናት ሙሉ በሙሉ በዘንጋኤ አንዳንጠፋና ስሙም ከምድር አንዳይደመሰስ በቅጣቱ በኩል የእግዚአብሑር ይጠራናል።  ጥሪው ይህ የሚካሄደው ጥፋት አንዲያበቃ ንስሐ ግቡ ነው።  በትንቢተ አሞጽ 4፥11 "ሰዶምንና ገሞራን እግዚአብሔር እንደ ገለበጣቸው፥ እንዲሁ ገለበጥኋችሁ፥ እናንተም ከእሳት ውስጥ እንደ ተነጠቀ ትንታግ ሆናችሁ፤ ነገር ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡"  እንዳለው አግዚአብሔር እኛም ከላይ በጥቂቱ ያነሳናቸው እጅግ አጸያፊና በእግዚአብሔር የተጠላ፣ ክርስቲያኖች ነን በሚሉ ሰዎች የሚፈጸም ርኵሰትና ኃጢአት ውጤት ፍሬው፡- 👇🏿 (1) ዘርኝነት፡- የንዑስ ማንነት ፖለቲካ ያሳወረው መንግሥትና የፖለቲካ ንቅንቃዎች ክርስቲያኖችን በቡድን መካፈል (ከክርስቶስ የወይን ግንድነት ላይ የነበራቸውን ቅርንጫፍነት ቆርጦ መጣል (የነፍስ ሞት)) (1ዮሐ 2፣11፤ ዮሐ ቀ5፣5) (2) የእርስበርስ ጦርነትና ሥርዓታዊ ፍጅት፡-  በዘረኝነት ፖለቲካ የሚፈጸም ጦርነት መተላለቅ፣ እንድ ክርስቲያን ሕዝብ በጅምላ መገደልና መሳደድ፣ በመዋቅራዊ እቅድ ለድኽነት መጋለጥ (3) መበታተንና ድንዛዜ፡-  አለመግባባትና አለመዋስተዋል፣ በከንቱ ንግርት፣ በባዶ ተስፋ ራስን ከጥፋት አለመከላከል፣ ድንዛዜ (4) በጎችን በተኩላ የሚያስጠብቅ እረኛ መብዛት፡- ከክርስትና አስተምህሮ ውጭ በሆነ መንፈስ በዘር መከፋፈል፣ እርኛውና በጉ አለመግባባት፣ የግልና የሠፈር ጀግና አበጅቶ ንጉሥ አንደሌለው ንብ መበታተን፣ በድሎትና ምቾት ፍተወት ኃላፊነትን መዘንጋት፣ ወንጌልን ለሆድ አገልግሎት መዋል 💠መፍትሑው፡- 1- ንስሐ መግባት፣ ጾም፣ ጸሎት፣ ምጽዋት፣ ይርታን የሕይወታችን መገለጫ ማድረግ፤ 2- ትዳርን መልሶ መቀደስ3- አመንዝራና ሰዶማዊውን ከአጠገባችን ማስወገድ (ንስሐ እንዲገባ የሚገባውን ትምህርትና ጠቃሚ ቅጣት መስጠት)፤ 4- ከሱሰኝነት ሁሉ ራስን ነፃ በመዋጣት አካላችንን ለእግዚአብሔር በቅዱስ ቁርባን መቀደስ፤ 5- ዘረኝነትና ዘረኞችን መቃወምና ራስን ከማንኛውም እግዚአብሔር ከማይቀደስበት ኢክርስቲያናዊ የቡድን አደረጃጀት መለየትና በክርስትና እና ከመልካሞች ጋር በሰብእና መሥፈርት ብቻ መደራጀት፣ መተባበር፣ ኃይል መሆን፤   6- ሐሰትን፣ ኢክርስቲያናዊ፣ ኢሰብአዊና ኢ-ሀገራዊ ርእዮቶች፣ ትርክቶችና የአስተዳደር ሥርዓትን ያለ ይሉኝታ መቃወም፣ በምንም መንግድ  አለመተባበር፤ 7- ከዘረኞችና አራዊታዊ መንፈስ ካደረባቸው መሪዎችና ስብስቦች ተለይቶ ሰውን በሰውነቱ ብቻ ከሚቀበሉ ጤናማዎች ጋር በመደራጀት የጥፋትን ሠራዊት ፊት ለፊት መግጠም —- ድል ከእግዚአብሔር ወገኖች ጋር ናውና ክፋትና ክፉዎች ይሸነፋሉ!!!  —-ኦሪት ዘሌዋውያን 26፣6-7   በምድራችሁም ላይ ሰላምን እሰጣለሁ፥ ማንም ሳያስፈራችሁ ትተኛላችሁ፤ ክፉዎችንም አራዊት ከምድራችሁ አጠፋለሁ፥ ሰይፍም በምድራችሁ ላይ አያልፍም። ጠላቶቻችሁንም ታሳድዳላችሁ፥ በፊታችሁም በሰይፍ ይወድቃሉ። ከከንቱ ልፋት ራስን መጠበቅ፡- ዘረኝነትን ሳይተዉ፤ ማመንዝረን ሳያቆሙ፤ ውርጃና ሰዶምን እየፈጸሙ፤ ትዳርን እያረከሱ፤ በሱስ እየናወዙ፤ ጾምና ጸሎት፣ ምጽዋትንና ይቅርታን ሳይታጠቁ  የአጋንንትን ሠራዊት ማሸነፍ አይቻልም!!!  https://t.me/Fantahun_Wakie
Mostrar todo...
Orthodoxy and Secularism

Share your videos with friends, family, and the world

Photo unavailableShow in Telegram
ለብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወቅዱስ ጳውሎስ በዓል:- እንኳን አደረሳችሁ!
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.