cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

"ስለመጻሕፍት ከመጻሕፍት መንደር እንዘምራለን!"

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
16 218
Suscriptores
Sin datos24 horas
+287 días
+21430 días
Distribuciones de tiempo de publicación

Carga de datos en curso...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Análisis de publicación
MensajesVistas
Acciones
Ver dinámicas
01
....እንጨምር ... "ተባረኪ ችግሩ አላዛር ከታሪክ ዉጭ ሆኖ ነው የሚያየኝ ። እኔ ደግሞ ታሪክ ልስራ እየለፋሁ ነው ። ጊዜዬን ለጭቁን ህዝቦች ነፃ መውጣት መስጠት ነበረብኝ ። ለምወደው ድርጅቴ መስጠት ነበረብኝ “ አዳም ፣ 242 ) :: በመሆኑም አላዛር ለተባረኪ የማይደፍር “ ፈሪ” ወይም የማይገባው “ ደደብ “ ወይም “ ከግል ስሜቱ መውጣት የከበደው ራስ ወዳድ ነው”( መረቅ ፣ 240 ) “ አማን በአዕምሮዬ መጣ :: አላዛር የሆነ ሴታ ሴት መሰለኝ። የሆነ ያልወለደኝ እማማ :: ጡት ባያጠባኝም የሆነ የወለደኝ ምንትስ። የምወደውን ልጅ ስሮጥና ስሸሽ አስታውሼው ፣ ስረጋጋ ፣ በዝምታ በልቤ እንዲህ አልኩት ፣ ማዘሬ ነህ ምንድነህ ?” (መረቅ ፣ 248) ። በላካናውያን እሳቤ ተፈጥሯዊው እውነት ትራውማ ነው እንጂ በትዕምርታዊ እርከን ዉስጥ ያለ ነገር አይደለም :: ለዚህም ነው ፋንታሲ ይህንን ትራውማ ለማከም ለሚደረገውን ጥረት መድረክ ሆኖ ብቅ የሚለው( fantasy is a setup ):: ይህ የእሷ እጣ ፈንታ ብቻ አይደለም ፤ በዘመኑ የነበሩ ወጣቶች ጣጣ ነው፤ ይህም ወጣቶቹ የወል ልቦናን ገንብተው የወል እርካታን ለመገንባትና ለማግኘት የሚዳክሩት ፣ በዢዤክ እሳቤ (Collective jouissance) ዉስጥ የሚታይ ነው :: ስሎቬኒያዊው ስሎቮን ዢዤክ እንዲህ ይላል፦ Nationalism thus becomes ‘the privileged domain of the eruption of enjoyment into the social field.’ The ‘national Cause’ is then cleverly related to Lacan’s concept of ‘the Thing’, which is closely linked with the concept of jouissance; it is itself a materialization of jouissance. እንደውም ብሔርተኝት ፣ ፋሺዝም ፣ ናዚዝምና ሌሎችም በዚህ በ Collective jouissance ውስጥ የሚታዩ ናቸዉ ይላል :: ይህም በረቀቀ መንገድ የሌሎችን ወሲባዊ እርካታን ቀንብበው ለዓላማቸው የሚያውሉ ደስታ ስራቂዎች (ብልጦች) አሉ ይለናል :- "What is at stake in ethnic tensions is always the possession of the national Thing: the ‘other’ wants to steal our enjoyment (by ruining our ‘way of life’) and/or it has access to some secret, perverse enjoyment. In short, what gets on our nerves, what really bothers us about the ‘other,’ is the peculiar way he organizes his enjoyment. In short, what gets on our nerves, what really bothers us about the ‘other,’ is the peculiar way he organizes his enjoyment. ( Slavoj Žižek ፥ 22 ) " ይህንን ሃሳብ በሜሎስ ነቅናቂ እሳቤ እናጠናክረው : “ ወሲብ ትልቅ ጉልበት ነው የወሲብን ስልጣን ወጣቶች ልብ ውስጥ እንይወጣ አድርገህ አምቀህ ለጫጫታ ትጠቀምበታለህ ። በየአቅጣጫው ታፍነውና አንድ የፖለቲካ መውጫ ብቻ ቀዳዳ ካበጀህለት ባሪያ አገኘህ ማለት ነው “ (መረቅ፥162) እዚህ ጋር በተለይ ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ፣ መረቅና የስንብት ቀለማት ረቂቅ በሆኑ የስነ ልቦና ፤ የታሪክ፣ የፖለቲካ ፣ የማህበረሰብ እሳቤዎችና እጅግ በላቀ እና በተዋጣለት ኪነጥበባዊ አለም ውስጥ የተሰሩ ናቸው :: በመሆኑ እነዚህ ብሉይ (Classic ) ስራዎች በላካንያን እሳቤ በዋነኛነት በ " fantasy Structure ፣ desire እና Collective Jouissance " ውስጥ ለመተንተን ሁነኛ ማዕቀፎች መሆን ይችላሉ። ይህም አዳም ረቂቅ ፈላስፋና አሳቢ፣ ጥልቅ አንባቢና የተዋጣለት ደራሲ መሆኑን ከስራዎቹ መረዳት ይቻላል :: *** ይህ ፅሁፍ ይድነቃቸው ሰለሞን (Ph.D) ለኢትዮጲስ ጋዜጣ ፣ ጥቅምት 11 ቀን 2011 ዓ.ም በወጣው ፅሁፍ ገፋፊነት ምክንያት የተፃፈ ነው ። በዚህም የእሱ ፅሁፍ የተሳሳታቸውን ወሳኝ ጉዳዮች ለማረም ያለመ ነው። ለዚህም ሲባል የእሱን ቴክስቶች (ከመረቅ የወሰዳቸውን ተጠቅሜያለሁ) ለንፅፅር እዲመች :: ለተጨማሪ ንባብ ምክንያት ስለሆንከኝ ምስጋና ይድረስህ :: © Teshale Kebede Bedriya
9205Loading...
02
የላካኒያን ሳይኮአናሊሲስ እና መረቅ *** በእርግጥ "መረቅ " በኪነ ጥበብ ምትሃት ፣ በእሳቤ ጥራትና በፍልስፍናው ጥልቀት በከባዱ የሚያነቃንቅ ብሉይ ስራ ነው። እውቁ ፈረንሳዊው የሳይኮአናሊሲስ ጠበብት ዣክ ላካን፣ ሳይኮአናሊሲስ ላይ ትልቅ ተፅዕኖ የፈጠረ ፈላስፋ ነው። ፍሩድን በጥልቀት ያጠናና በስራዎቹም ሥነ - ፅሁፍን ፣ ፊልም ፣ ፖለቲካና በማህበረሰብ ጥናት ላይ ተጽዕኖውን ማሳረፍ የቻለ አሳቢ ነው። እንደ ላካን እሳቤ "ሰው '' በዋናነት የህይውት ዘይቤው የተበጀውና መንገዱን የተቀየሰለት ቋንቋን መጠቀም ከጀመረበት ቅፅበት ጀምሮ በሚገነባው ኢ-ንቁ የአዕምሮው ክፍል ነው :: ይህም “Unconscious mind is structured like a language” ይላል። የላካንያን ኢንቁ ቋንቋ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ትዕምርቶችና መዋቅሮች ማከናወኛ (ሚዲየም፣ ስቴጅ ) ጭምር ነው። በዋናነት አንድ ህፃናን ከተወለደ በኋላ ራሱን የሚያውቀው በእናቱ ጡት አማካይነት ነው። በዚህ ጊዜ ጨቅላው እራሱን መለየት አይችልም፤ ይልቁን ፍፁም እርሱነቱንና አካባቢውን ማገናዘብ ባልቻለበትና እራሱን በእናቱ የመስለባቸውን ደረጃዎች ያልፋል :: ጨቅላው ከእናቱ ጡት እንደተነጠል ( ከ6 እስከ 18 ወራት ያለውን ጊዜ ይሸፍናል) የእኔነት ምስሉን መቅረጽ ይጀምራል። የእናቱ አንድ አካል እንዳልሆነም ይረዳል። ይህን ego form የሚያደርግበት እርከን ላካን Imaginary order ሲል ሰይሞታል። ይህን imaginary order በማለፍ በትዕምርትና በቋንቋ ወደተዋቀረው ስርዓት ውስጥ የሚገባው ጨቅላው እናቱም ብትሆን ከሙሉ እሱነቱ የተነጠለች (M)Other እንደሆነች ይረዳል። ሕጻኑም የደስታና የእርካታ ምንጩን ትቶ በማህበረሰቡ አስቀድሞ ወደተሰሩት ፍላጎቶች ፊቱን ያዞራል። (unreplaceable lack ) በሌላ አገላለጽ ህፃኑ ተፈጥሯዊ ፍላጎቱ ፋንታሲ ወደ ፋንታሲ ሽግግር ያደርጋል :: በዚህም ህጻኑ ከተፈጥሯዊ እሱነቱ ወጥቶ በቋንቋና በትምዕርት ወደ ተዋቀረው ስርዓት ውስጥ ይገባል። ይህንን የቋንቋ ስርዓት በአርስቶትል አባባል ... “Automation:-Signifiers of the signifiers) ነው። ይህም ተፈጥሮኣዊ እሱነቱና እርካታውን ሙሉ በሙሉ የሚያጣበትና የሌሎች ፍላጎት (desires of the Other) ለተፈጥሯዊው ፍላጎቱ አማራጭ ሆኖ የሚመጣበት ነው ። ስለዚህ የላካንያን ሳይኮአናሊሲስ መሰረት የሆኑት ሶስቱ እርከኖች ማለትም Imaginary፣ Symbolic እና Real order፣ ለትዕምርታዊ ዓለም ተገዢ ይሆናሉ፡፡ በዚህም ተፈጥራዊ እውነት (real ) ሙሉ በሙሉ በቋንቋ ስለ ማይወከል ከቋንቋ ውጪ ይሆናሉ ፤ ይህንን ለካን ( Symbolic castration) ይለዋላል :: በዚህ በቋንቋ የሚመራው ግለሰብ እነዚህን ጉዳዮች በሌላ ማህበሰባዊ እውነታ (social reality) ይተካሉ :: ስለዚህም ተፈጥራዊው እውነት እና እርካታው (enjoyment) ፣ ስነ-ልቦናዊ ምስቅልቅሎሽ ( trauma) በመሆን ወደሌላ ምናባዊ አለም ወይም ፋንታሲ ሽግግር (transference) ያደርጋሉ። በዚህም ተፈጥራዊ እውነታ እና እርካታ ፋንታሲ ውስጥ ይገባሉ :: በዚህም መሰረት መረቅን በላካን ለማንበብ የተደረገውን ጥረት እንይ ፦ "ከሁሉ ለመሸሽ የምችል ዓይነት ወደ አማን ደረት ተጣበቅሁ ። አማን ጓደኛዬ ነው ፣ ጓደኛዬ ነበር፣ እና ምን አለበት? አይኖቼን ገርበብ አድርጌ አላዛርን አስባለሁ። አላዛር አ አይኖቹን ጨፍኖ እየተልቆሰቆሰ ሲያቅፈኝ። በፀሃያማ ቀን በቀስታ ታኮኝ ሲቆም ። በሃሳቤ እዛና እዛ ስቀባዥር አማን አናቴን ሲስመኝ ሰማሁት :: አላዛርን ማለም አቆምኩ :: ግራ በመጋባት ምልክት ቀና ብዬ አየሁት :: ቀና ብዬ እያየሁት ሳለሁ ሳልጠብቀው አፌ ላይ ሙሉ በሙሉ ሳመኝ ። በፍጥነት ከእቅፉ ተላቀቅሁና ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ቆም ብዬ ጃኬቴንና ሱሪዬ አስተካከልኩ። “ የት ነው? “አለኝ “ቤት ለመሄድ ነበር “ተራዬ እንዳልሆነ አውቃለሁ ” መኪና የለም ::ትንሽ ረጋ በይ :: ተራሽ ገና ነው” የምመልሰው አልነበረኝም ..... ይህ ሁነት በመጋቢት 1969 ተባረኪ የወጣቶች ሊግ ሰላማዊ ሰልፍ በተደረገበት ሌሊት ነው። በመጀመሪያ ተባረኪ ሰላማዊ ሰልፉን ለመሳተፍ ፈርታ ስታመነታ ነበር ። ሆኖም ፍራቻዋን ለትግል አጋሯ አማን (የእሷም ፣ የአላዘርም አብሮ አደግ) በቁንጽል ወይም በዝርዝር አትነግረውም፡፡ “ ፈሪው ወዳጄ አላዛር በልቤ ጥርጣሬ አስገብቶ ሳይሆን ይቀራል ፤ ለአማን ልነግረው አልደፈርኩም ። ግን ደግሞ የጠላቴን አይን እያየሁ ግንባሩ ላይ መጮህ እፈልጋለሁ ...” (መረቅ ፥ 246።) ከትዕምርታዊ ስርዓት ይልቅ ፣ ነገሩን በቀጥታ ለማየት ከፈለግን ተፈጥሯዊው ፍላጎት እንደሆነ እንረዳለን ። ነገር ግን ይህ ተፈጥሯዊ ፍላጎት ለማግኘት ለአማን የሚቻል አይደለም ፤ ይህም የአማን ፍላጎት ወደ ፋንታሲ ውስጥ ተሻጋሪ ይሆናል ። በመሆኑም አማን ተባረኪ የዓላዛር ፍቅረኛ መሆኗ እያወቀ እሷን ከመመኘት አላገደውም፤ ይህም ተፈጥሯዊ ፍላጐቱ ለማርካት የነበረውን ማንኛውም አጋጣሚ ከመሞከር ወደኋላ አላለም ፤ ይህም ተባረኪ በአማን አዕምሮ ውስጥ የምትንሳፈፍ ለተፈጥሮኣዊ ፍላጎቱ መልስ ሰጪ ናትና ። እዚህ ጋር የስሎቮን ዢዤክን ሀሳብ ላምጣ ፦ "For a Man ,the relationship with a women is possible only in as much as she fits his formula " ይላል :: ለዚህም አካላዊ ባይሆንም በፖለቲካው መድረክ የነበራቸው ግንኙነት ለዚህ ወሲባዊ ፍላጎት ልዋጭ ሆኖ መቅረቡን እናያለን። እንዲህ ትላለች ቴቤ ፦ " ....አማንን ሩካቤ ስጋ እምቢ ብላውም ባማረ መልክ በፖለቲካ ተራክበናል። እኔ እንደማልረሳው እሱም አይረሳኝም " ትላለች (መረቅ፥293 )። ..ሌላ እንጥቀስ ... ” የስላማዊ ሰልፉ ማግስት በመሽሽ ላይ እያለሁ ፣ ትዝ ያለኝ ብቸኛ እናቴና አላዛር ነበሩ። ለብቻዬ በኮሮኮንች ላይ እየተወለካከፍኩ ስሮጥ የከበበኝ ጨለማ ማሃል የታወሱኝ እማማና አላዛር ነበሩ። ፍቅር ከዋናው አላማዬ በላይ የሚንሳፈፍ ጉድ የለዉም (መረቅ ፥ 246)” እዚህ ጋር ተባረኪ ፣ እናቷና ዓላዛር ተያይዘው የመጡት ሁለቱም ለተፈጥሯዊ ፍላጎቷ መገኛ ቢሆኑም የነበረችው በትርክት ውስጥ ስለሆነ አታገኛቸውም ። ምክንያቱም ትዕምርታዊ አለም ተፈጥሮኣዊ እዉነት (real ) እርካታ ( jouissance) በቋንቋ አይወከሉም ፤ ይህም እንዴት ወደ ፋንታሲ ሽግግር እንደሚደርግ ከላይ አይተናል ። ይህንን ክፍተት በፋንታሲ ከተያዘ በኋላ ለሌሎች ፍላጐት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ፤ በዘመኑ የነበረው ፋንታሲ ውስጥ መጫወት የሚችል ርዕዮት ዓለም ደግሞ ማርክሲዝምና ሌኒንዝም ነው፡ ፡ በመሆኑም የማርክስ ርዕዮት ዓለም የእናቷና የዓላዛር ተቀናቃኝ ሆኖ ይመጣል ። ዢዤክ እንደሚለው (fantasy is narative) ፋንታሲ ትርክት በመሆኑ በወቅቱ የነበረው የማርክሲስም ርዕዮተ አለም አዕምሮዋን መቆጣጠር መቻሉና አዕምሮዋ ውስጥ ያለዉ የፋንታሲ መዋቅር ወዲህ በእናቷና ዓላዛር እሳቤ ወዲያ በርዕዮተ ዓለሙ ለሁለት ተከፍሎ እናያለን።
10Loading...
03
Media files
10Loading...
04
ለክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሐነ ትንሳዔው አደረሳችሁ። በዓሉ የሠለም፣ የጤና፣ የፍቅር እንዲሆን ከመጻሕፍት ዓለም - Book Shelf ይመኛል።
7440Loading...
05
ትዝ ይላቹሀል? Phsyics እና Maths ላይ የነበሩ solve አርጉ ምንባላቸው problems? እና ደሞ እነዛ የMaths ረዣዥም equations? The value of 'x' ፍለጋ ብዙ ወረቀት እኮ ነው የጨረስነው። አንድ መስመር ጥያቄ ተሰጥቶን 2 ባዶ ወረቀት ለመልስ ሲያስከትሉልን የነበረው ጭንቀት አረሳውም። ከelementary እስከ ዩኒቨርሲቲ maths በጣም ከባድ ትምህርት ነው። ብዙ ለፍተን . .አጥንተን ነው የምንሰራው። ነገ Maths ነው ፈተናው ሲባል ሌሊቱ ይለያል. .እንቅልፍ አይታሰብም ነበር። ዛሬ ላይ ሆኜ ያን ሁሉ ትግል ሳስብ ቆጨኝ። ያን ሁሉ አቅሜን ያዋልኩበት ልፋት አሁን ላይ ትምህርት ጨርሼ ህይወትን ለብቻዬ ስጋፈጣት ምንም ጥቅሙ አልታይ አለኝ። ዛሬ ህይወት በብዙ አቅጣጫ ትፈትናለች። The value of 'X'ን ስለመፈለግ ያን ሁሉ ከምንማር አሁን ለሚገጥሙን ፈተናዎች መፍትሄ ፍለጋ ብንማር ምን ነበረበት? እንዲሁ በምኞት ሀሳብ ስሞላ እነዛን በስንት ጥረት የሸመደድኳቸውን equations ተጠቅሜ የአሁን ውጣውረዴን መፍታት ያምረኛል። በነዛ word problems ውስጥ ዛሬ የሚገጥመኝ የህይወት እንቅፋት ተተንትኖ ከነ አሰራሩ ተፅፎበት በነበር ብዬ እጓጓለሁ። አሁን የሚገጥመን የሴትነት ፈተና ፣ የትዳር ችግር ፣ ድብርት ፣ ብቸኝነት ፣ አምኖ መካድ ፣ የልብ ስብራት ፣ ስራ ማጣት ፣ ራስን መጥላት በየትኛው equation ነው solve ሚደረገው? እኚህን ቻሌንጆች በየትኛው የትምህርት ክፍለ ጊዜ ነው የተማርነው? አልተማርንም! ዛሬ ብዙ የህይወት ገፃችንን ቢወስድም ለትምህርት የሰጠነውን ያህል ቦታ ተሰጥቶት ግን አላወቅነውም። ትምህርት አያስፈልግም አልልም። ነገር ግን ያን ያህል ሁሉን ረስተን አቅማችንን invest ልናደርግበት አይገባም። አሁን ባለንበት ሁኔታ የተማርነው እውቀት አብዛኛው የሚጠፋ ነው። የሚቀረውን ደሞ ለሆነ ድርጅት ግብዐት ሆነን በመስራት ብንጠቀመው ነው (እሱም ከተገኘ)። ከስራ ውጪ ግን ብዙውን የህይወት መንገዳችንን ሚይዝ ከተለያዩ ሰዎች ጋ መኖር ፣ ትዳር ፣ እናትነት ፣ አባትነት አለ። ቀላል አይደሉም....እስክንኖርባቸው አዲስ ናቸው። ማወቅ ፣ መዘጋጀት ፣ መጠንከር አለብን። ሁሌ ደሞ አልጋ በአልጋ አይሆኑም ማጣት ፣ መውደቅ ፣ መሰበር ይኖራቸዋል. .ለዚህስ ከማደጋችን ጋ ሚመጣ እውቀት መኖር የለበትም? ስንት ልጅ ነው ደህና ወላጅ ኖሮት እንዲህ አይነት ስለ ህይወት ትምህርት የሚያገኘው? . .አላውቅም! ግን በቃ ትምህርት የሰጠነው እድሜ አይገባውም። እሱ ላይ ብቻ መደገፍ የለብንም. .አላማችን ሊሆን አይገባም። ከልጅነት ጀምሮ ከትምህርት ጎን ለጎን ራሳችንን ምንሰራበት ህይወት ሊኖረን ይገባል። ውስጣችን ያለውን አቅም ፣ የተፈጠርንለትን አላማ ነው ማጠንከር ያለብን። እንጂማ ትምህርት ብቸኛ መንገዳችን ከሆነ 12 ላይ ወይም ዩኒቨርሲቲ ላይ ሲያልቅ ራሳችንን በማጣት እንጎዳለን። ወዴት እንደምንሄድ ሲጠፋን...ህይወታችንን በምን ማስቀጠል እንደምንችል ግራ ሲገባን አጉል አወዳደቅ እንወድቃለን። ማንፈልገውን ትምህርት በብዙ ፈተና ተምረን. .የሚገባን ቀርቶ የሚያኖረንን ስራ እንኳን ስናጣ አናሳዝንም? ለመኖር ፣ ላለመወቀስ ፣ ላለመውደቅ ብለን እንደገና ማንፈልገው ፣ ሰው ያሰመረልን መንገድ ላይ መሄድ ደሞ ይታክታል። ስለ ነገኣቹ . .ስለ ህይወታቹ አስቡ. .አላማችሁን ለዩና እሱን ዋና መንገዳቹ አድርጉት. .ራሳቹ ላይ ስሩ! ስኬት በትምህርት ብቻ አይደለም! © Nejat Hussen
7755Loading...
06
Media files
6280Loading...
07
ያለፈውን ታሪክ፣ የማህበረሰቡን ዕሴትና ዕውቀት በጭፍን ማጥላላትና መናቅ የመሰልጠን መንገድ አድርገን እየሄድንበት ያለው መንገድ ቆም ብለን ለመረዳት እንኳ ጊዜ ያለን አይመስልም፡፡ የማጥላላት ዘመቻውም የሚያጋፍረው መድረኩን የያዘው ዘመንኩ ወይም ተማርኩ ባዩ ነው፡፡ ፈላስፋው Valentin Mudimbe ከላይ በጠቀስኩት መጽሃፉ እንዳሰፈረው፣ ከ1950ዎቹ ጀምሮ ቢያንስ ነጭ ቅኝገዥዎች የአፍሪካን መሬት ለቀው ቢወጡም በእነሱ ቦታ "ጥቁር ቅኝገዥዎች" ወይም ልሂቃን ተተክቷል፡፡ በምዕራቡ ዓለም የቅኝግዛታዊ ዲስኮርስና ዕውቀት ተኮትኩተው ያደጉት አፍሪካውያን ቀድሞ ቅኝ ገዢዎች ሲከውኑት የነበረውን ነገር በአንድም ሆነ በሌላ አቅጣጫ ቀጠለ እንጂ አልተቋረጠም፡፡ ነጭ ቅኝ ገዥዎች የተኩት አፍሪካውያን የፖለቲካ ልሂቃን ከምዕራቡ ዓለም ሥርዓት ወይም ተቋማት ጋር ያላቸው ግንኙነት የጌታና የሎሌ ወይም የጥገኝነት እንዲሆን ያደረገውም ይኸው የቅኝአገዛዝ ሌጋሲ ነው፤" …colonialism should have produced a body of knowledge on the means of exploting dependencies." በሃገራችን ኢትዮጵያም የሆነውና እየሆነ ያለው ይኸው የቅኝ አገዛዝ ማዕከላዊ እሳቤ ከትምህርት ስርዓታችን አንስቶ እስከ ፖለቲካዊ መድረኮች ተሞልቷል፡፡ እውቀት ከሌሎች ሃገራት ተፈልጎ የሚመጣ እንጂ ከራሳችን አንጥረን ማውጣት እንደምንችል ሊገለጥልን እንዳልቻለ የምዕተ-ዓመት ጉዟችን ምስክር ነው፡፡ አዳምም ይህንን በደመነፍስ የሚደረግ ጉዞ አጥብቆ ይተቻል፡፡ "የኢትዮጵያ ምሁራን ሲሰለጥኑና ዘሮቻቸውን ሊያሰለጥኑ ሲፈልጉ መጽሃፎች ይጽፋሉ፡፡ በነዚህ መጽሃፎች ውስጥ የሚጠይቁት አንድ ዋነኛ ጥያቄ እኔ ምን አለኝ? ሳይሆን እነሱ ምን አላቸው? ነው አሉ፡፡ …ካላመናችሁ ጃፓን እንደምን ሰለጠነችን አንብቡ፡፡" (785) ፕ/ር ማዕምር መናሰማይ "A Critical Dialogue between Fifteen and Twenty first Century Ethiopia"በተሰኘው ጥናታቸው ያለፉትን ሶስት የመንግስት ስርዓቶችን (አጼ ኃይለ ሥላሴ፣ ደርግና ኢህአዴግ)ኢትዮጵያን ለማዘመን የሄዱበት መንገድና ዘይቤ "ፍዝዝመና" (passive modernization) ሲሉ ሰይመውታል፡፡ ይህም ማለት በልማት ስም ምዕራባዊ ለመምሰል መሞከር፣ በምዕራቡ ዕውቀትና ሥነ-ዘዴ ላይ በመመስረት ልማት ለማምጣት ያደረጉትን ያልተሳካ ሙከራ ነው ፍዝ ዝመና ብለው የጠሩት።፡ ይህ ፍዝ ዝመና ሃገር በቀል ዕውቀቶችን፣ እሴቶችን፣ እይታዎችንና ባህሎችንና ተቋማትን አፈራርሶ በምዕራቡ እሳቤ የመተካት ሙከራ ነው ይላሉ። የዚህ ውጤትም በሃገሪቱ ውስጥ መልከ-ብዙ ቀውስና ምስቅልቅሎሾችን አስከትሏል፡፡ "…the failure of modernization in Ethiopia is also the failure of knowledge: of Ethiopia and of modernization." አዳም ረታ በ'እቴሜቴ ሎሚ ሽታ' በሰዓሊና በሃያሲ መስኮት ገረሱ በኩል የዘመኑን ሁኔታ እንዲተነትን፣ እንዲተችና እንዲተረጉም አጭቶታል፡፡ መስኮት በተለይ ፈረንጅ ያልነካው ወይም 'ያልባረከው' ነገር ፋይዳ ቢስ ለሚያደርጉና የፈረንጅ እውቀት የሁሉም ነገር መመዘኛ አድርገው ለተቀበሉ የዘመኑ ወጣቶችን በየጋዜጣው ይተቻል፡፡ ሃገር በቀል እሴቶቻችንም ወደ መድረኩ ይመልሳቸዋል፣ ይተነትናቸዋል፣ አንዳች እውነት ፈልቅቆ ለማውጣት ይተጋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ መስኮት አስቀድሞ ይከተለው የነበረው የ"አብስትራክት ኤክስፕረሺንንዝም" የአሳሳል ዘይቤ በመተው፣ የሃገር በቀል ዕውቀትና experience መሰረት ያደረገ "ተነካናኪ" ወይም "ቅርባዊነት" የተሰኘ የአሳሳል ዘይቤ ፈጥሯል፡፡ ክፍለ ዘመን የተሸገረው የተቃወሰው ጉዟችን ዳግም መታደስ የሚችለው፤ ከራሳችን ጋር እርቅ አውርደን ነጋችንን ለማሳመር የመስኮት ገረሱን ፈለግ ከመከተል የተሻለ ሌላ ምን ምርጫ ሊኖረን ይችላል?! © Teshale Kebede Bedriya
1 0135Loading...
08
አዳም ረታ እንደ postcolonial ፈላስፋ **** "…ቅኝ አልተገዛንም ብለው ጉራ እየነፉ በየቀኑ ግን የተገዥነት አገልግሎት ይሰጣሉ" (የስንብት ቀለማት፣24) አዳም ረታ በተለይ ኋላ ላይ ባሳተማቸው 'እቴሜቴ የሎሚ ሽታ' እና 'የስንብት ቀለማት' ውስጥ የ-postcolonialism ፍልስፍናዊ እሳቤዎችን ጎልቶ ይንጸባረቅባቸዋል፡፡ አድዋ ላይ ቅኝ ገዥዎችን ድል አድርገን መልሰናል የሚለው ኩራታችን አፋዊ እንጂ ከልብ የመነጨ እንዳልሆነ በላቀ ኪናዊ ውበትና ጥልቅ መረዳቱን ገልጦ አስነብቦናል፡፡ ነጻነታችንን እና የስልጣኔ አሻራዎቻችን እንደልቃቂት አውጥተን ጥለን ፈረንጅ ለመምሰል የተጋጋጥንባቸው የሕማም ዓመታት እንደገና እንድናጤናቸው በድርሰቶቹ ብዙ ገስጾናል፡፡ እኛ ግን ከራሳችን ጋር መታረቅ ተስኖን እዚያው'ጋ ነን… እንደመነሻ፣ ከድህረ-አድዋ በኋላ እንደወረደ ተቀብለን ከተጋትናቸው ጉዳዮች መካከል እውቅት፣ ስልጣኔ፣ የተቋማት ግንባታ፣ ቁሳዊ ልማት፣ ርዕዮታዊ መረዳት…ከውጭ ሃገር እንደሸቀጥ አምጥቶ በየቦታው የሚከፋፈል አድርጎ የመረዳት ሥሁት ግንዛቤ አንዱ ነው፡፡ ይህንን መነሻ በማድረግ እውቀት በተውሶ ለማምጣት ከአንዱ ሃገር ወደ ሌላ ሀገር ስንዞር አንድ አንድ ክፍለዘመን ተሻገርን፡፡ በሃገር ውስጥ በፈረንጅ አፍ እያወራን በስልጣኔ ብርሃን ለመጥለቅለቅ በሚል የቋንቋ ትምህርት ቤቶች ከፈትን፡፡ "የአውሮፓ የስልጣኔ መንገድ" በመከተል ካለንበት 'ጨለማ ወጥተን' ልክ እንደ'ሰለጠኑት' ሃገራት በ'ብርሃን' መንገድ ለመጓዝ በሚል እዚህም እዚያም ባጀን፡፡ ኋላ ላይ የመጡት መንግስታትና የፖለቲካ ልሂቃንም አንዴ ሶሻሊዝም ሌላ ጊዜ የልማታዊ መንግስት ሞዴል አምጥተው ለመተግበር ሞከሩ፡፡ ሙከራው ግን ከቀውስ ወደ ቀውስ ከመሸጋገር ያለፈ አንድ ስንዝር እንኳ ፈቅ እንድንል አላገዘንም፡፡ለምን?... አዳም ይህንን የህማም ጉዟችንን እንደ ከያኒ ሥነውበታዊ ፍኖቱን ሳይለቅ፤ እንደ አሳቢ ደግሞ ከሥነዕውቀታዊ ከፍታው ሳይወርድ ገልጦ ያሳየናል፡፡ ታመን እንዳልታመምን በማስመሰል የመጣንበትን ሥሁት መንገድ ዳግም እንድናጤነው ይወተውተናል፡፡ ከህማማችን የምንፈወስበት መውጫ መንገዱን ጭምር ይጠቁመናል፡፡ እዚህ'ጋ ለማስታወስ ያህል postcolonialism የቁም ፍቺው እንደሚያመለክተው ከ-colonialism ቀጥሎ የሚመጣ ሥርዓት ሳይሆን፣ የኮሎኒያሊዝም ሌጋሲዎችን በተዘዋዋሪ መንገድ በድህረ ቅኝ ግዛት የቀጠሉ መሆኑንና ይህም በሃገሬው ነባር ባህል፣ ዕውቀት፣ እሴት፣ ማህበራዊ መስተጋብር…ላይ ከፍተኛ ተቃርኖ እንደፈጠረ የሚያትት ዕሳቤ ነው፡፡ አፍሪካዊው ፈላስፋ Valentin Mudimbe 'The Invention of Africa' በተሰኘው መጽሃፉ እንዳሰፈረው፣Colonialism ማለት ቅኝገዥዎች የቅኝ ተገዥውን ሃገርና ማህበረሰብ በሃይል በመቆጣጠር አንድም የተፈጥሮ ሃብቱን አሟጦ ወደ ምዕራቡ ዓለም የመላክ ሲሆን፣ ይህንን ብዝበዛ ቀጣይነት እንዲኖረው ደግሞ የቅኝተገዥው ማህበረሰብ ማንነታዊ መሰረት እንደገና የማዋቀርና የመቅረጽ ስራ ይሰራል፡፡ በሌላ በኩል ማንነትን እንደገና የመበየንና የመቅረጽ ሂደት የስልጣን ተዋረዱ ሳይዛነፍ እንዲቀጥል፣ ቅኝ ተገዥዎች በዚህ የሃይል ተዋረድ ቦታቸው የተገዥነትና ጥገኝነት መሆኑን በሥነዕውቀታዊ፣ በተረክና በሌሎችም ይስሙላ ሳይንሳዊ ምርምሮቻቸው ላይ እውነታነት እንዳለው የሚያትት ዕሳቤ ነው፡፡ ህንዳዊቷ ፕ/ር Ania Loomba ታዲያ 'Colonialism/ Postcolonialism' በተሰኘው መጽሃፏ ይህንን የቅኝ ግዛታዊ ዲስኮርስና ተረክ ከስር መሰረቱ መረዳትና ይኸ ተረክ በድህረ-ቅኝግዛት ዘመንም እንዴት እንደቀጠለ ማወቅ እጅግ አስፈላጊ ነው ትላለች፡፡ ቅኝአገዛዝ በታሪክ ሁለትዮሻዊ ተቃርኖ (binary opposition) በመፍጠር አደገኛና ውስብስብ ተረኮችን ፈጥሯል፡፡ አውሮፓን ወይም ምእራቡ ዓለም "እኛ" በሚለው ጎራ ውስጥ በማስገባት "ከምዕራቡ ዓለም ውጪ ያለውን ማህበረሰብ ደግሞ "ሌሎች" (others) በሚለው ጎራ መድቧቸዋል፡፡ ይህን የሁለትዮሻዊ ዓለም (west-east) ተረክ አውሮፓውያን ለራሳቸው ያላቸውን ምስልና ከአውሮፓ ውጭ ባሉ ሕዝቦች መካከል አለ የሚሉትን የልዩነት መስመር ለማስመር ጉልህ ሚና ተጫውቷል፡፡ ለአብነትም አውሮፓውያን "የሰለጠኑ"፣ በ"አመክንዮ ታግዘው ማሰብ የሚችሉ"ና ዕውቀታቸው ለሌሎችም "አርዓያ መሆን የሚችል" አድርገው ሲቀርጹት፤ በአንጻሩ ከአውሮፓ ውጪ ያለው ማህበረሰብ ደግሞ "ያልሰለጠነ"፣ ስሜቱን "መግራት ያልቻለ" አድርገው ፈርጀውታል፡፡ እንዲሁም ነባር ባህሉንና እሴቱን እድገትና ለውጥ ለማምጣት የ"ማያስችል" አድርገው በይስሙላ ሳይንሳዊ ጥናቶቻቸው ጭምር አስደግፈው ለማሳመን ችሏል፡፡ ታዲያ ከ19ኛው ክ/ዘ አንስቶ እየኖርንባት ያለችው ይህች ዓለም በዚህ ቅኝት ነው የተበጃጀችው፡፡ ቅኝአገዛዝ "አበቃ" ቢባልም መልኩን በመቀየር ከአውሮፓ ውጭ ባሉ ሃገራት የትምህርት ስርዓት፣ የመንግስት አወቃቀር፣ የባህል ዘርፍ…ውስጥ ሰርጾ በመግባት ህልውናውን ማስቀጠል ችሏል፡፡ የ-postcolonial አሳብያንና ስራዎቻቸውም ከትናንት የተሻገሩ የቅኝገዥዎች ሌጋሲዎቻቸውን በዛሬው አስተሳሰባችን፣ የህይወት ዘይቤያችንና ተቋሞቻችን ውስጥ እንዴት ተተግባሪ እንደሚሆኑ ያሳዩናል፡፡ አዳም ልክ እንደ postcolonial ፈላስፎች፣ ቅኝ ገዥዎች ሃገራችንን በሃይል ወርረው በመያዝ ለዓመታት ባይቆዩም፣ ቅኝግዛታዊ አስተሳሰባቸውን፣ የህይወት ዘይቤያቸውን፣ የአገዛዝ ስልታቸውንና ዕቅዳቸውን አውቀንም ይሁን ሳናውቅ ተቀብለን እየተገበርነውና እየኖርነው እንዳለ ከመጣንበት የትናንትናው መንገድ ሰበዞችን እየመዘዘ ይወቅሰናል፡፡ "ባዴ [ፈረንጅ] የተለየ ብሩህ አይደለም ብለው የነዘነዙኝ በባዴ ቅኝ ገዥዎች ራሳቸውን እንዲጠሉ ጥልቅ ትምህርት የወሰዱና ዛሬም ከእነሱ እግር ስር የማይጠፉ ወገናቸውን ባዴ በቀደደላቸው መንገድ የሚቀረቅቡ ነጋዴዎች ናቸው፡፡" (ስ.ቀ፣ 23)-ይህን የተባሉት ራሱን የ"ወርቃማው ትውልድ" ወይም የ"ያ ትውልድ" አባላት ነው ለሚሉት አብዮተኞች የተሰነዘረች ትችት ነች፡፡ ትልቁ አሳቢና ሳይካትሪስት ፍራንዝ ፋኖን 'Black Skin White Mask' በተሰኘው መጽሃፉ የጥቁሮች የበታችነት ሥሜት (Inferiority complex) ምንጩ የ" Colonial discourse" ነው ይላል፤ "…colonialism not only exploits but dehumanize and objectifies the colonized subject." ፋኖን የቅኝ ግዛታዊ ዲስኮርስ በቅኝ ገዢው ግለሰብ ሥነ-ልቦና ውስጥ እንዲሰርጽ ያደረገበት መንገድ ደግሞ ግለሰቡ የወጣበትን ማህበረሰብ ታሪኩን፣ ማህበራዊ እሴቱን ዋጋ በማሳጣትና በማጥፋት በማጥፋት ከትውስታው ማህደር እንዲፋቅ በማድረግ በምትኩ የነጭ የበላይነት ተፈጥሮኣዊ አድርጎ የሚቀበልና እሱን ለመምሰል የሚሞክር ግለሰብ ሆኗል ይለናል፡፡ "…የአገራችንን መልካም ታሪክ እንጥቀስ ስንል ዐይኖቻቸው ቀልተው 'the past is a foreign country' (ያለፈው ዘመን ባዕድ አገር ነው) ይሉናል፡፡…የነጭና የጥቁር ተራቾች ግን ታሪክ አስፈላጊ አይደለም……ያውም ደብተራ የዘባረቀው ብለው ለምን የታሪክ ምሁር እንደሆኑ ግን አይነግሩንም፡፡…የባዕድ ደብተራ የጻፈውን ግን ያምኑታል፡፡"(ስ.ቀ፣ 23)
8716Loading...
09
Media files
8050Loading...
10
በአማዞን ቤት ፡ እያንዳንዱ መፅሀፍ ሲሸጥ ደወል ይደወል ነበር ። 🔔 ጄፍ ቤዞስ ፡ እ.ኤ.አ. በ 1995 ላይ በትንሽ ጋራጅ ውስጥ አማዞንን የመሰረተ ጊዜ ፡ የሚጠቀሙበት ሰርቨር ብዙ የኤሌትሪክ ሀይል ስለሚፈልግ ፡ በስራ ሰአት ሚስቱ የፀጉር ማድረቂያ መጠቀም ፡ ወይም በቫኪዩም ክሊነር ቤት ማፅዳት አትችልም ነበር ። .... ከዛም ይህን ድርጅት ከመሰረቱ ከቀናት በኋላ ቢዝነሱን ሰፋ አድርገው ሀያ የሚሆኑ ሰራተኖችን ቀጥረው ፡ በዌብሳይታቸው ገብቶ መፅሀፍ የሚገዛ ሰው መጠበቅ ጀመሩ ። እና በዛን ወቅት ወደ አማዞን ዌብሳይት የሆነ ሰው ገብቶ አንድ መፅሀፍ ሲታዘዝ ፡ በአማዞን ቤት ደስታ ይሆናል ። አስገራሚው ነገር አማዞን ሽያጭ በጀመረባቸው በነዚህ ሳምንታት ፡ አንድ መፅሀፍ ሲታዘዝ ፡ ደወል ይደወላል 🔔 ይሄኔ የአማዞን ሰራተኞች የሆነ ሰው በኦንላይን መፅሀፍ እንደገዛቸው ያውቃሉ ፡ እና ፡ ይህን ከአማዞን መፅሀፍ ያዘዘው ሰው ስም ለማየት ኮምፒውተሩን ይከባሉ ። ...... ማለትም በቀን ውስጥ አስር ጊዜ ሽያጭ ከፈፀሙ ፡ አስር ጊዜ ደወል ይደወል ነበር ማለት ነው ። ሆኖም አማዞን ብዙም ሳይቆይ ከሚጠበቀው በላይ ብዙ ትእዛዞች መቀበል በመጀመሩ አንድ መፅሀፍ ሲሸጥ ደወል መደወል ያቆመው በሳምንታት ውስጥ ነው ። .... ዛሬስ. ..... ያ. .. አንድ መፅሀፍ ሲሸጥ ደወል ይደውል የነበረው አማዞን በአንድ ቀን ከስድስት ሚሊዮን በላይ የተለያዩ እቃዎችን ይሸጣል ። እንደድሮው ቢሆን በቀን ውስጥ ስድስት ሚሊየን ጊዜ ደወል ይደወል ነበር ማለት ነው ። .... እያንዳንዱን ስኬቱን ደወል በመደወል ያበስር የነበረው አማዞን ፡ አንድ መፅሀፍ ሲሸጥ በደስታ ያጨበጭብ የነበረው አማዞን ፡ ዛሬ ላይ ከ1,525,000 በላይ ጊዜያዊና ቋሚ ሰራተኞችን ቀጥሮ ያሰራል ። እንደምንም በቆጠባት አስር ሺህ ዶላር ቢዝነስ የጀመረው ጄፍ ቤዞፍ አሁን 197 ቢሊየን ዶላር ሀብት በስሙ አስመዝግቧል ። ...... ነገ በተሻለ ጉልበት ለመንቀሳቀስ ሀይል ይሆነን ዘንድ በያንዳንዱ ትናንሽ ስኬት ፡ እንደጄፍ ቤዞስ በደስታ ደወላችንን እናንሳ 🔔 ........ ፎቶ ፡ የአሁኑ ቢሊየነር ጄፍ ቤዞፍ አማዞንን በመሰረተበት ወቅት © Wasihune Tesfaye
1 2613Loading...
11
Media files
1 1450Loading...
12
ክርስቶስ እና ሶቅራጥስ ሐሳብ ወይስ ስሜት?አንዱን ከሌላው ነጥሎ ማየት ከባድ ነው። ሐሳብ ስሜት ይወልዳል ፤ ስሜት ሐሳብ ይፈጥራል። ነገር ግን አንደኛው አባት ሌላኛው ልጅ ሊሆኑ ግድ ነው። ህፃን ልጅ እንደተወለደ ስሜት አለው ፤ ሐሳብ ግን የለውም። ሐሳብ የሚፈጥረው በስሜቱና በአካባቢው እየተመራ ነው። ስሜት ከልብ ሐሳብ ደግሞ ከአእምሮ እንደሆነ በተለምዶ ይታሰባል። ያንኑ ተከትለን ስንነጉድ ስሜትን በሐሳብ መግራት እንደ ስልጣኔ ይዘወተራል። የስሜት ቁንጮ ፍቅር ነው። የሐሳብ ቁንጮ ደግሞ አመክንዮ ነው። ስለዚህ ከአሁን በኋላ ስሜት እና ሐሳብ በማለት ፈንታ ክርስቶስ እና ሶቅራጥስ እያልኩ እቀጥላለሁ። ክርስቶስ ፍቅርን ፣ ሶቅራጥስ አመክንዮን ኖሩ ፤ ሰበኩ። ዳሩ ግን የሁለቱም መጨረሻ በሞት ፍርድ መቀጣት ነበር። ሁለቱም "አደገኛ" ነበሩና። ልዩነታቸው እየሱስ ሞትን ድል መንሳቱ ነው። አያችሁ ፍቅርን የያዘ ሞትን እንኳን ያሸንፋል። ሎጂክ የያዘ ቢበዛ ክርክር ቢያሸንፍ ነው። ስለዚህ ሚሊዮን ግዜ ከሶቅራጥስ ጋር ባህማስ ከመዝናናት ከክርስቶስ ጋር ጓንታናሞ ብታሰር እመርጣለሁ። © Tewodros Shewangizaw
1 2696Loading...
13
Media files
1 2030Loading...
14
ስብሐት ስለ ደራስያን ምን ይላል? ማስተርፒስ ወደ አማርኛ ስነፅሁፍ እየመጣች ነው ―ስብሐት ገብረእግዚአብሔር የዘነበ ወላን "ልጅነት" ካነበበ በኋላ ዶስቶቭስኪ ሲፅፍ ዝርክርክ ነበር። በቴክኒክ ረገድ ያልተዝረከረከው ‘ወንጀልና ቅጣት’ ብቻ ነበር። ታድያ ማንበቡ ሲጥምህ እንኳንም ተዝረከረከ ነው የምትለው። ―ስብሐት ስለ ዶስቶቭስኪ በአማርኛ ስነፅሁፍ ውስጥ እንደ አዳም ረታ የተዋጣለት የአጭር ልብወለድ ደራሲ የለም። ―ስብሐት ስለ አዳም ረታ(ልብ ማለት ያለብን ስብሐት አብዛኛዎቹን የአዳም ረዣዥም ልብወለዶች ለማንበብ አልታደለም ካፒታልን ያነበብኩት በደርግ ዘመን መፅሀፉን ወደ አማርኛ እንዲመልስ በተዋቀረው ኮሚቴ አባል ሆኜ ነው። ሰዎች ማርክስ ቤተሰቡን አስርቦ ነው የፃፈው ይላሉ። ፍልስፍናው ሲገባህ አውራጃም በተራበ ነው የምትለው። ―ስብሐት ስለ ካርል ማርክስ አደፍርስን ሳነበው "ሌቱም አይነጋልኝን" በእንግሊዝኛ የተተየበ 65 ገፅ ላይ ደርሼ ነበር። ከዛ በፊት አማርኛ ለስነፅሁፍ ብቁ አይደለም የሚል እምነት ነበረኝ። ዳኛቸው በአማርኛ መፃፍ እንደሚቻል ከሰተልኝ። ―ስብሐት ስለ ዳኛቸው ወርቁ ፍሩይድ ተአምረኛ ነበር። ወደ ራሱ ውስጥ ገብቶ የመረመረ ጂኒየስ ነው። እራሱ በርቶለት የኔንም ውስጤን አበራልኝ። ―ስብሐት ስለ ፍሩይድ በአሉ ጎበዝ አለቃ ነው። ከዛ ቀጥሎ ነው ደራሲነቱን የማደንቀው። በአሉ ባህሪውም መልኩም የስነጽሑፍ ችሎታውም ያማረ ሰው ነበር። ‘አይገኝም እንጂ እንዳማሩ መሞት’ የሚለውን የአንዳንድ ግዜ ህግ ጥሶታል። ―ስብሐት ስለ በአሉ ግርማ በዛኛው አለም አራት የአጭር ልብወለድ ጠበብቶች አሉ። አንደኛው ጊ ደ ሞፓሳ ነው። ሞፓሳ በ43 አመቱ ከ400 በላይ አጭር ልብወለድ ያመረተ ጎበዝ ደራሲ ነበር። ምን ያደርጋል ቂጥኝ በአጭር አስቀረው(ስብሐት ከአይኑ እንባ ዱብ አለ) ―ስብሐት ስለ ጊ ደ ሞፓሳ ፀጋዬ የኛ ዎሌ ሾይንካ ነው። ኦክስፎርድ ድረስ ሄዶ ስነፅሁፋችንን አለማቀፋዊ ያደረገ ደራሲ ነው። ―ስብሐት ስለ ፀጋዬ ዲክንስ የታችኛውን ማህበረሰብ ህይወት ነው የፃፈው። እንደ ሩስያ ስነፅሁፍ እንባ በእንባ ነው የሚያደርግህ። የእንግሊዝ ነገሥታትና ልኡላን ዲክንሰን አነበቡት። ከዛ በኋላ ነው ድሆችን የሚረዳ ድርጅት በእንግሊዝ መቋቋም የጀመረው። ዲክንስ በስነፅሁፉ ጉልበት በሃገር ደረጃ ማህበራዊ ተፅእኖ መፍጠር የቻለ ታላቅ ደራሲ ነው። ―ስብሐት ስለ ቻርልስ ዲክንስ ኃይለመለኮት መዋእል ‘ጉንጉን’ ውስጥ አማርኛን ከነለዛዋ ከነማእረጓ ፅፎ አስደነቀኝ። ደግሞም ኃይለመለኮት ብእሩ ብቻ ሳይሆን አንደበቱም ርቱእ ነው። ―ስብሐት ስለ ኃይለመለኮት ፕሩስት አይሁድ ነው። የፈረንሳይ አይሁድ። ጂንየስ ነው። አይሁድ መሆን ጂኒየስ ያደርጋል መሰለኝ። ሰባት ልብወለድ ጽፏል። ስለ ራሱ ነው የፃፈው። በልብወለዱ ውስጥ ያሉት ሁለት መቶውም ገፀባህሪያት ፈረንሳይ ውስጥ በሕይወት ያሉ ሰዎች ናቸው። በፈረንሳይኛ ነው ያነበብኩት። ፈረንሳይኛን እንደሱ የሚያውቅበት ደራሲ የለም። ―ስብሐት ስለ ማርሴል ፕሩስት ጋሽ ሐዲስ አለማየሁ ቆንጆ ስታይል ነው ያላቸው። ተረታዊ አቀራረባቸውን እወደዋለሁ። በአማርኛ የሚፅፉ ቶልስቶይ ልትላቸው ትችላለህ። ―ስብሐት ስለ ሐዲስ አለማየሁ ኒቼ ከዘመናዊ ታላላቅ ፈላስፎች አንዱ ነው። ግማሽ ጎኑ ፖላንድ ነው። በጣም ብሪሊያንት ነበር። ከኤግዚስቴንሽያሊዝም አያቶች አንዱ ነው። ፍልስፍናው በጣም ተፅእኖ ፈጣሪ ነው አሁን ድረስ። ኒቼ የቂጥኝ በሽታ ነበረበት። በዚሁ ጦስ አብዶ ነው የሞተው። ―ስብሐት ስለ ፍሬድሪክ ኒቼ ከበደ ሚካኤል በዘመናቸው ለነበረ ትውልድ ትክክለኛ ደራሲ ናቸው። ለአሁኑ ትውልድ ግን እንጃ። ምክንያቱም ስራቸው ግብረገብ ይበዛበታል። ቢሆንም መደነቅ ይገባቸዋል። ―ስብሐት ስለ ከበደ ሚካኤል አልቤር ካሙ ጋዜጠኛም ፈላስፋም ደራሲም ነበር። ደግሞም ሰው ነው። ላመነበት ነው የሚኖረው። በእኛ ዘመን ካሙን እና ሳርትርን ያላነበበ ኢንተሌክችዋል ወጣት አልነበረም። ስራቸው ፍልስፍናም ምርምርም ነበር። ―ስብሐት ስለ አልቤር ካሙ ከተርጓሚዎቻችን መሐል ያነበብኳቸው እና የወደድኳቸው ሳህለሥላሴ ብርሃነማርያም፣ ባሴ ሃብቴና መስፍን አለማየሁ ናቸው። በተለይ ባሴ በሲራኖ ትርጉሙ አስደንቆኛል። ―ስብሐት ስለ ተርጓሚዎች ገተ የጀርመን የስነጥበብና የባህል አባት ነው። በአውሮፓ የመጀመሪያውን ሮማንቲክ የሆነ አብይ ልብወለድ የፃፈው ገተ ነበር። ፎስት ይባላል። ፎስት የታወቀ የጀርመን ሌጀንድ ሲሆን ገተ በስነፅሁፍ ህያውና ዘለአለማዊ አድርጎታል። ―ስብሐት ስለ ዎልፍጋንግ ገተ ብርሃኑ ዘርይሁንን ሳገኘው ከኔ የባሰ አይናፋር ነው። ማእበልን ጀምሬ መጨረስ አልቻልኩም። አፃፃፉ ጥሩ ነበር። ግን የረሃብ ሰቆቃውን ተቋቁሜ ማንበብ አልቻልኩም። እንዴት ችሎት ጻፈው! ―ስብሐት ስለ ብርሃኑ ዘርይሁን © Tewodros Shewangizaw
1 8019Loading...
15
Media files
1 3883Loading...
16
ግዜው 1865 ነበር። የአለማችን ታላቁ የልብወለድ ደራሲ "ወንጀልና ቅጣት" የተሰኘውን ልብወለድ ገና መፃፍ ከመጀመሩ በሃይለኛ ማዕበል ተመታ። ከመጀመሪያ ሚስቱ ጋር ፍቺ ከፈፀመ ብዙም ሳይቆይ የሚጥል በሽታው የአልጋ ቁራኛ አደረገው። በመከራ ላይ መከራ የተደራረበበት ደራሲ ብዙም ሳይቆይ ታላቅ ወንድሙን በሞት ተነጠቀ። እራሱ በእዳ እስከ ጭንቅላቱ የተዘፈቀው ደስታየቭስኪ የወንድሙን እዳም ጨምሮ ወረሰ። ደስታየቭስኪን ለዚህ ሁሉ እዳ የዳረገው ቁማር ወዳድነቱ ነበር። አበዳሪዎችም ወዲያውኑ በሩን ማንኳኳት ጀመሩ። እዳውን ቶሎ ካልከፈላቸው እስር ቤት እንደሚያስወረውሩት ዛቱበት። ከ10 አመት በፊት የተከለከሉ መጻሕፍትን በማንበብ ወንጀል የሞት ፍርድ ተፈርዶበት ከቅጣቱ ለጥቂት ነው ያመለጠው። በምትኩ ወደ ሳይቤሪያ ተግዞ የ4 አመት እስራት ከባድ የጉልበት ስራ ጋር ተፈረደበት። በዚህ የተነሳ እስር ቤትን አጥብቆ ይፈራል። ከእስራት ለማምለጥ የመፃህፍቱን ህጋዊ ባለቤትነት በ3000 ሩብል(በዛሬ ግምት $80000) ሸጠ። በተጨማሪም ሌላ አንድ ወጥ ልብወለድ ለመፃፍ ተስማማ። በስምምነቱ መሰረት ለመፃፍ የተስማማው ልብወለድ "The Gambler"("ቁማርተኛው") ነበር። ቁማርተኛው የቁማር እዳውን ለመክፈል ስለ ቁማርተኛ ልብወለድ መፃፉ ፈገግ ያስብላል። ይሁን እንጂ ደስታየቭስኪ በወንጀልና ቅጣት በጣም በመመሰጡ ቁማርተኛውን መፃፉን ለግዜው ወደ ጎን ተወው። ግዜ እየገሰገሰ ቁማርተኛውን ፅፎ ለማስረከብ አንድ ወር ግዜ ብቻ ቀረው። ጓደኞቹ ለደህንነቱ በማሰብ ልብወለዱን በጋራ ፅፈው ለመጨረስ ሃሳብ አቀረቡለት። ደስታየቭስኪ ሴራውን ይነግራቸውና እያንዳንዳቸው የታሪኩን ከፊል ይጽፋሉ። በመጨረሻ ደስታየቭስኪ ያለቀውን ረቂቅ ተመልክቶ ያርመዋል። ደስታቭስኪ በጓደኞቹ አሳቢነት ቢነካም ባልፃፈው መጽሐፍ ሽፋን ስሙን ለማስቀመጥ አልፈቀደም። ያለው አማራጭ አንድ ብቻ ነው―ልብወለዱን መፃፍ። ያውም በፍጥነት! ወዲያውኑ አጭር ፅህፈት(stenography) የምታስተምር ጓደኛው ጋር ደውሎ ምርጥ ተማሪውን እንድትጠቁመው አደረገ። አስተማሪዋም ያለ ምንም ማመንታት አና የተባለችውን ጎበዝ ተማሪ ጠቆመችው። በግዜው ስቴኖግራፊ ትጋት የሚጠይቅ መስክ ነበር። ስቴኖግራፊ ለመማር ከተመዘገቡ 150 ተማሪዎች መሐል 125ቱ በወሩ ትምህርታቸውን አቋርጠው ነበር። አና ገና የ21 አመት ወጣት ነበረች። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ከመጨረሷ ወዲያውኑ ስቴኖግራፊ መማር ጀመረች። ደስታየቭስኪ በቅርቡ የሞተው አባቷ በጣም ተወዳጅ ደራሲ ነበር። እሷም ብትሆን የደስታየቭስኪን ታሪኮች እያነበበች ነው ያደገችው። ደስታቭስኪን ማግኘት ብቻም ሳይሆን ለሱ መስራቱ ጭምር ጥልቅ ስሜት ፈጠረባት። በሚቀጥለው ቀን ልክ ከቀኑ 5:30 ደስታየቭስኪ በር ላይ ተገኘች። "ቀድመሽም ሆነ አርፍደሽ" እንዳትደርሺ ተብሎ በጥብቅ ተነግሯታል። ደስታየቭስኪ አንዳንድ ጥያቄዎችን ከጠየቃት በኋላ ያንኑ ከሰአት ሥራቸውን ጀመሩ። እሱ ልብወለዱን በቃል ይነግራታል፤ እሷ በአጭሩ ትፅፈዋለች። ማታ ላይ ታርመዋለች። ለሚቀጥሉት 25 ቀናት አና በየቀኑ ደስታየቭስኪ ቤት ከ6:00 እስከ 10:00 ተገኘች። ለሻይ በየመሐሉ እረፍት ከመውሰዳቸው ውጪ ልብወለዱን በመጨረስ ተጠመዱ። ቀናት በነጎዱ ቁጥር ደስታየቭስኪ ለአና ጥሩ ስሜት እያዳበረ መጣ። ሲጠራትም "ትንሿ እርግብ" እያለ ነበር። ቁምነገረኝነቷን፣ ጥልቅ ስሜቷን ወደደው። ደማቅ መንፈሷ ጥልቅ ድብርቱን ማደብዘዝ ብቻም ሳይሆን ከአስጨናቂ የሃሳብ ጎርፍ ይገላግለው ነበር። እሷም በደግነቱ፣ በሚያሳያት ክብር፣ ሃሳቦቿን በማዳመጡ እና ዋጋ በመስጠቱ፣ እንደ ረዳት ሳይሆን እንደ እኩያ ስለሚቆጠራት ተማረከች። ነገር ግን ይህ የመከባበር እና የመዋደድ መንፈስ የታላቅ ፍቅር ዘር መሆኑን ሁለቱም ገና አልተረዱም ነበር። አና በፃፈችው ማስታወሻ ላይ እንዲህ አስፍራ ነበር፦ "አንድ ቀን ደስታየቭስኪን እንዲህ ስል ጠየቅኩት፦ 'ለምንድነው ሁል ግዜ ስለ መከራ የምትፅፈው? እስኪ ስለ ደስተኛ ግዜያቶችህ ንገረኝ' 'ደስታ? እስከአሁን ደስተኛ ሆኜ አላውቅም። ገና ደስታን ለማጣጣም እየጠበቅኩ ነው'" ሁለቱም በግዜው ያላወቁት ነገር ደስታ ጠርዛቸው ላይ እያንዣበበ ነበር። አና ድጋሚ እንዲያገባ እና ደስተኛ እንዲሆን መከረችው። ገጠመኙን አና እንዲህ ታስታውሰዋለች፦ "እና ድጋሚ አግባ ነው የምትዪኝ? ምን አይነት ሚስት? ደግ ወይስ ብልህ?" "ብልህ ሚስት አግባ" "እኔ እንኳን ብሆን ደግ ሚስት ነው የምመርጠው። ታዝንልኝና ትወደኛለች። ስለ ጋብቻ ካነሳን አይቀር አንቺስ ለምን አላገባሽም?" "ሁለት ሰዎች ለጋብቻ ጠይቀውኝ ነበር። ጥሩ ሰዎች ነበሩ። ሁለቱንም አከብራቸዋለሁ ነገር ግን አላፈቀርኳቸውም። እኔ ደግሞ ማግባት የምፈልገው ለፍቅር ነው" "እውነትሽን ነው! ለደስታኛ ጋብቻ መከባበር ብቻውን አይበቃም" የመጨረሻ የስራ ቀናቸው ህዳር 10 ነበር። በአና ታላቅ እርዳታ ደስታየቭስኪ የማይቻለውን አድርጓል። በ26 ቀናት አንድ ሙሉ ልብወለድ ፅፎ አጠናቋል። በተስማሙት መሰረት 50 ሩብል($1500) ሞቅ ካለ ምስጋና ጋር ሰጣት። በዚህ ግዜ ደስታየቭስኪ አንድ ነገር ተገነዘበ። ከአና ጋር የነበራቸው ቆይታ የህይወቱ ብርሃን ነበር። እንደገና እንደማያገኛት ሲያስብ መንፈሱን ጨለማ ወረሰው። አናም እንደዚሁ ነበር የተሰማት። ስራቸው፣ አስደሳች ንግግሮቻቸው ሕይወቷን በደስታ ይሞሉላት ስለነበር አሁን ሁሉም ነገር ትርጉምየለሽ ሆነባት። ያለሷ ህይወት አልጥምህ ያለው ደስታየቭስኪ ሌላኛው ልብወለዱን ወንጀልና ቅጣትን ለመጨረስ እንድታግዘው አናን በድጋሚ ጋበዛት። የመጀመሪያ ሥራቸውን ካጠናቀቁ ከ10 ቀናት በኋላ ቤቱ ስትደርስ ሞቅ ባለ ፈገግታ ተቀበላት። ወዲያውኑ አዲስ ለመፃፍ ያሰበውን ልብወለድ ሴራ ይነግራት ጀመር። ሴራውን መናገር እንደጀመረ ዋናው ባለታሪክ የራሱ የደስታየቭስኪ አምሳያ እንደሆነ ግልፅ እየሆነ መጣ። ባለታሪኩ ከደስታየቭስኪ ጋር ተመሳሳይ እድሜ ያለው አርቲስት፣ በልጅነቱ በመከራ የተፈተነ፣ ብዙ የሚወዳቸውን ሰዎች ያጣ፣ በማይድን በሽታ የተያዘ፣ ሃዘንተኛ፣ ተጠራጣሪ፣ ደግ ግን ስሜቱን በአግባቡ መግለፅ የማይችል፣ የበቃ አርቲስት ግን እሱ በሚያልመው መልኩ ስኬታማ ያልሆነ ነው። የአርቲስቱ ትልቅ ስቃይ ደግሞ አንያ ከምትባል ወጣት ሴት ጋር በፍቅር መውደቁ ነበር። አንያ ብልህ፣ ረጋ ያለች፣ ተወዳጅ ሴት ናት። ይህ አርቲስት ገፀባህሪ ደግሞ አልመጥናትም፣ አትገባኝም የሚል ፍርሃት አለበት። በዚህ ቅፅበት ደስታየቭስኪ ከሷ ፍቅር እንደያዘው አና ተረዳች። የፍቅር ጥያቄዬን አትቀበለኝም ብሎ በመፍራቱ ከልብወለድ ጀርባ ተደብቆ እየነገራት እንደሆነ አወቀች። ደስታየቭስኪ አናን እንዲህ ሲል ጠየቃት፦ "ይህ ሕመምተኛ፣ በእዳ የተዘፈቀ ሽማግሌ ለአንዲት ብሩህ ወጣት ምን ሊያቀርብላት ይችላል? ከእሱ ጋር በፍቅር መተሳሰር ለሷ ከባድ መስዋእትነት መክፈል አይሆንም? በመጨረሻስ ፀፀት አይወርሳትም? በአጠቃላይ በእድሜ እና በአመለካከት በጣም የምትራራቀው ሴት ከኔ አርቲስት ጋር በፍቅር መውደቅ ይቻላታል? በስነልቡና መነፅር ይህ ስህተት ይሆን? ለዚህ ጉዳይ ነበር አስተያየትሽን የፈለግኩት አና" "ለምን አይቻልም? ይቻላል እንጂ! ገፀባህሪዋ ባዶ አይደለችም። ደግና ብሩህ ናት። ከአርቲስቱ ጋር በፍቅር ልትወድቅ ትችላለች። ፀፀትም አይኖርባትም" ደስታየቭስኪ ጥቂት ዝም አለና እንዲህ አላት፦ "እራስሽን በልጅቷ ቦታ አድርጊ። አርቲስቱ እኔ ብሆን የምትወጂኝ ይመስልሻል?"
1 3786Loading...
17
"በደንብ እንጂ። ህይወቴን በሙሉ እወድሃለሁ" አናና ፍዮዶር ወዲያውኑ ተጋቡ። አና እና ደስታየቭስኪ ሲጋቡ እሷ የ21 አመት ወጣት፣ እሱ ደግሞ የ47 አመት ጎልማሳ ነበሩ። ልክ የተረት መፃህፍት ላይ እንዳሉ ታሪኮች ነበር ፍቅራቸው። ለ14 አመት ፍቅራቸው የሚያስቀና፣ ደስታቸው ሙሉ ሆኖ ከኖሩ በኋላ ደስታየቭስኪ በ61 አመቱ ከዚህ አለም በሞት ተለየ። አና ከደስታየቭስኪ ሞት በኋላ ብዙ የእናግባሽ ጥያቄዎች መጥተውላት ነበር። ገና 35 አመቷ ነው። አሁንም ውብ ናት። አሁንም በህይወት እንደተሞላች ነው። ብሩህ ጭንቅላት አላት። አና ግን ሁሉንም ጥያቄዎች በእንቢታ መለሰች። ምክንያቱ ምን ይሆን? ከረዥም አመታት በኋላ አንድ ጋዜጠኛ ይህንኑ ጥያቄ ጠየቃት፦ "አና ቆንጆ ነሽ። ወጣት ነሽ። ብልህ ነሽ። ለምን ዳግመኛ አላገባሽም?" አናም መለሰች፦ "ከደስታየቭስኪ በኋላ ማንን ላግባ? ቶልስቶይ እንደሆነ አግብቶ ወልዷል!" የአና መልስ አንጀት አርስ ነው። ደስታየቭስኪን የሚያክል ስብእና ጋር የኖረች ሴት ተገዳዳሪ ስብእና ያለው አቻ ለማግኘት ብትቸገር አይገርምም። © Tewodros Shewangizaw
1 4977Loading...
18
Media files
1 1622Loading...
19
Media files
1 4060Loading...
20
“የኢትዮጵያ ሕዝብ እፎይ ብሎ አያውቅም፡፡” crossing the same river twice... አንዳንዱ የአደባባይ ወሬያችን፣ ኹነታችን እና ድርጊያችን መሠረተ ነገሩ የማይለዋወጥ ይመስላል፡፡ የዛሬ ስድሳ ዓመት አያቴን ያስነባ ድርጊት ዛሬ አባቴን ያሳቅቃል፤ የዛሬ ዐርባ ዓመት እናቴን ያስገረመ ወሬ ዛሬ አንቺንም ዋው 😮 ያስብላል፡፡ ዛሬ አንቺን ተስፋ የሚያሳጣ ኹነት፣ ትናንት ከትናንት ወዲያ አባትሽን እና አያትሽን የተወለዱበትን ቀን ያስረገመ ይኾናል፡፡ አንዳንዴ የቆዩ መጻሕፍትን ወይ ጽሑፎችን ስታነቢ፣ የትኛው ዘመን ላይ እንዳለሽ ግራ ይገባሻል፡፡ ይሄን ብሶት እገሌ ትናንት አልፖሰተውም? ይሄን ታሪክ ቅድም አልሰማኹትም? … ያስብልሻል፡፡ ከፌስቡክ አቅም የዛሬ ዐሥር ዓመቱን ፖስትህን ሲያስታውስህ፣ “አኹንም እዚያው ነን?” ትላለኽ፡፡ የተኖረ የምንገርብ ያህል እንዲሰማን የሚያደርገው ብዙ ነው - በተለይ በአገር ጉዳይ፡፡ ዴ ዣ ቩ ማለት ያ ሳይኾን አይቀርም፡፡ (ነው ወይስ በጊዜ እያሳፈሩ ከዘመን ዘመን እያመላለሱን ይኾን? - መንፈሳዊ ቢሉ ሳይንሳዊ ታይም ትራቭል🧐) ይሄ ከሥር የምታነቢውን ቃል የተናገረው (ነፍሱ በክብር ትረፍና) ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን ነው፤ በ1984 ዓ.ም.!! የዛሬ 31 ዓመት!! * * * “የኢትዮጵያ ሕዝብ መከራ ተሸካሚ ነው፡፡ በተደጋጋሚ የጦርነት ድግስ ይደገስለታል፡፡ ድግሱ አዳራሽ ውስጥ ሆ ብሎ ይቃጠላል፡፡ ለዚህ በኔ አስተያየት የተለያዩ ምክንያቶች አሉት፡፡ “ልቡ ውስጥ የምታበራዋን ነጻነት የሚላትን እሳት ለራሱ ለማስቀረት ጦርነት ውስጥ ገብቶ ይቃጠላል፡፡ አንገቱን ቀና አድርጋ የምታንቀሳቅሰው ይቺ ነጻነት ወዳድነቱ ነች፡፡ ይህችን በውስጡ የምትነድ ባህርይውን ገዥዎቹ ለራሳቸው ጥቅም ያውሉዋታል፡፡ ሁለት ባላባቶች ማዶ ለማዶ ያዋጉታል፡፡ ከውጪም ጠላት ሲመጣበት ያው ነው፡፡ “ነጻነቱን እጅግ ይወዳል፡፡ በዚህም ከሌላው ይለያል፡፡ መከራውን ችሎ አንጀቱን ቋጥሮ ባዶ እግሩን ያለ ስንቅ ያለ ደሞዝ ለነጻነቱ ይሞታል፡፡ በወንድሞቹ በአፍሪካውያን ዘንድ፣ በጎረቤቶቹ በአረቦች ዘንድ ያስከበረው ይሄው ባህርይው ነው፡፡ ዛሬም ቢሆን ያው ባህርይው እየገፋፋው ይታለላል፡፡ እፎይ ብሎ አያውቅም፡፡ የሚያጫርሰው አመራር ሁልጊዜም ይከሰትበታል፡፡ “በውስጥ ለራሳቸው ጥቅም እርስ በርሱ ያፋጩታል፡፡ በውጪውም ለነጻነቱ ቀናኢ ስለሆነ፣ እሱን ለሞት አጋፍጠው እንደገና አናቱ ላይ ፊጥ ይላሉ፡፡ በዚህም አጥንቱን ይሰብሩታል፡፡ “እኔ ደግሞ አንድ ገበሬ አጠገብ ቁጭ ብዬ እህ ማለትን እወዳለሁ፡፡ ካንድ አርበኛ ወታደር፣ ካንዲት የወታደር ሚስት፣ ከአንድ ቄስ፣ ሼህ፣ … ከሁሉም እህ ብዬ እማራለሁ፡፡ “ሁሉም አንደበታቸው እንባ አዘል ነው፡፡ እሮሮ ያፈልቃል ልሳናቸው፡፡ ሕይወታቸው ሁሉ ብሶት ነው፡፡ ይሄ ነው ባጠቃላይ የአገሪቱ ገጽታ፡፡ ብእሬን ወደ ትራጄዲ የሚስበውም ይሄው ነው፡፡” (ቤዛ መጽሔት፤ 1984 ዓ.ም.) ***ለእስከመቼ ይኾን የተናገረው? © Theodros Atlaw
1 6465Loading...
21
የትኛው ልብወለድ መፅሀፍ ላይ እንዳነበብኩት ትዝ ባይለኝም ሁላችንም ለወላጆቻችን ሁሌም ልጆች ነን የሚል ቁምነገር ማንበቤን አስታውሳለሁ። ለምን የ80 አመት አዛውንት አትሆንም። ለእናትህ አሁንም ህጻን ነህ። መጀመሪያ ዳይፐር ያደረገችልህ እናትህ ናት። ቂጥህን የጠረገችልህ፣ እንባህን ከአይንህ ያበሰችልህ፣ ንፍጥህን ከአፍንጫህ ያናፈጠችህ እናትህ ናት። ገላህን መጀመሪያ ያጠበችህ፣ ልብስህን ያለበሰችህ እናትህ ናት። የመጀመሪያ ምግብህን ከጡቷ ያጠባችህ እናትህ ናት። ወተት መጀመሪያ ያጠጣችህ አሁንም እናትህ ናት። ዛሬ አድገህ ትልቅ ሆነህ፣ የእናትህን እርዳታ ምንም ባትፈልግም ለእናትህ ግን ሁሌም ያው ያ ንፍጣም፣ ቅዘናም ልጅ ነህ። ያ አልቃሻ ደካማ ህፃን ነህ። እናትህ በመጀመሪያ የምታስታውስህ ገና በለጋነትህ በነበረህ ገፅታ፣ ባህሪ፣ ጠባይ ነው። እና ዛሬ ጎልምሰህ ጠንካራ ብትሆንም ለእናትህ ግን ያ በሁለት እግሩ ቀጥ ብሎ መቆም እንኳን የማይችለው ደካማ ህፃን ነህ። ለዚህ ነው የአለም አንደኛ ብልህ ሰው መሆንህን አለም ሁሉ ቢቀበለው ለእናትህ ግራ የሚገባ እንግዳ ነገር የሚሆንባት። የዋህ እያለህ ጀምሮ ነዋ የምታውቅህ። በፊዚክስ አለም ውስጥ ሶስት እጅግ ብልህ ሰዎች አሉ። ሁለቱ አይዛክ ኒውተን እና አልበርት አንስታይን ናቸው። ሶስተኛው ሰው የዛሬ ጨዋታችን ዋና ጉዳይ ነው። የፊዚክስ ሌክቸሮቹ እጅግ ድንቅ ናቸው። Feynman's Lectures of Physics ብላችሁ ጉግልን ብትጠይቁት በሶስት ቅፅ የተጠረዘ ዳጎስ ያለ ጥራዝ ያቀብላችኋል። የዚህ ፊዚስት ስም ሪቻርድ ፌይንማን ይባላል። ፌይንማን የሚደንቀው ጥልቅ የፊዚክስ መረዳቱ ብቻ ሳይሆን የተረዳውን ፅንሰሃሳብ በለዛ አስውቦ የሚገልጥበት ጥበቡም ጭምር ነው። ፌይንማን charismatic ነው። በአማርኛ ግርማ ሞገሳም የሚለው አፌን አልሞላልኝም። ለማንኛውም ይህ ሳይንቲስት የአለም እጅግ ብልሁ ሰው ተብሎ ተመርጦ ነበር። ይሄንን የሰማችው እናቱ የአለም ብልህ ሰው የእኔ ልጅ ከሆነ ከባድ ችግር ውስጥ ነን ብላለች። የትኛውም ብልህ ግለሰብ ተመርጦ ቢሆን ኖሮ የግለሰቡ እናት እንዲሁ ነበር የምትለው። አየህ በምድር ላይ ከእናትህ የበለጠ አብጠርጥሮ የሚያውቅህ የለም። በሰማይም ቢሆን!! © Tewodros Shewangizaw
1 7706Loading...
22
Media files
1 4501Loading...
23
ፍቅር እስከ መቃብር ሁለት ወጣት ኢትዮጵያውያን ከሃገራቸው ብዙ ርቀት እየሩሳሌም ላይ ተገናኙ። ወጣቱ ሃገራቸውን በዲፕሎማትነት ሊያገለግሉ በ1937 በእየሩሳሌም ከትመው ነበር። በግዜው እየሩሳሌም በእንግሊዝ ግዛት አስተዳደር ስር ነበረች። ወጣቱም በዛ የኢትዮጵያ ቆንሲል ሆኑ። በቆይታቸው አንዲት ውብ ኢትዮጵያዊት ተዋወቁ። ኢትዮጵያዊቷ ኢትዮጵያ ውስጥ ተወልዳ በሁለት አመቷ ወደ እየሩሳሌም መጣች። አያቷ ለመመንኮስ ወደ እየሩሳሌም ሲመጡ ነበር ህፃኗን ይዘው የመጡት። ህፃኗ በእየሩሳሌም በአያቷ መልካም አስተዳደግ ውብ ወጣት ሆነች። ሁለቱ ወጣቶች ወዲያውኑ ተጋቡ። ምንም እንኳን ፍሬ ለማየት ባይታደሉም ደስተኛ እና የሚያስቀኑ ጥንዶች ነበሩ። ሁለቱ ባለትዳሮች በባልየው ስራ ምክንያት አውሮፓ እና አሜሪካ በሚዘዋወሩበት ወቅት እንኳን ተለያይተው አያውቁም። በ1954 ግን ኃያሉ ሞት ለያቸው። ወይዘሮዋ በህመም አረፉ። አርፈው አስከሬናቸው አያታቸው ወደ አሉበት ቅድስት እየሩሳሌም ባለቤታቸው ወስደው በጌቴሰማኒ የመጨረሻው እንዲሆን አደረጉ፡፡ ጎልማሳው ብርቱ ሃዘን ገባቸው። በአዲስአበባ የሚገኘውን መኖሪያ ቤታቸውን በባለቤታቸው ስም ለተሰየመ በአዲስአበባ ከተማ ምክር ቤት ለሚተዳደር የልጆች ማሳደጊያ በስጦታ ሰጡ። ጎልማሳው ዳግመኛ አላገቡም። አርባ አመት በብቸኝነት ኖረው በ1995 አረፉ። ባለታሪኮቹ ሃዲስ አለማየሁ እና ክበበ―ጸሐይ በላይ ነበሩ። ፍቅራቸውም እስከ መቃብር ነበር! © Tewodros Shewangizaw
1 8776Loading...
24
Media files
1 5572Loading...
25
ለመኖርህ በህይወት መገኘት ብቻ ዋስትና አይሆንም። በሌሎች ኃይልን የተጎናጸፉ ባለጡንቻዎች ለመኖርህ ማረጋገጫ ካልሰጡህ በስተቀር።  ድንገት አንድ ጠዋት የጦር መሣሪያ ጥይት በቤትህ ጣሪያ አናት ላይ ሲርከፈከፍ ትነቃለህ። ገና ህይወትን በመጀመሪያህ ሰዓት ይመጣና “ለዓላማዬ ተማገድልኝ” የሚል ጉልበተኛ ደጅህን ይቆረቁራል፣ እጣፈንታህን  ይወስንልሃል።   የዘመኔን ወጣት ምስቅልቅል ሥነ ልቡናው ፣ ፍርሃቱ፣ ተስፋ ቢስነቱ፣ የዛለ መንፈሱን ይወክላል። ህይወት ይሏት ፍዳ ተጭናበት   አሳሩን ይበላል። ተራኪው በዚህኛው ክፍል የገፈቱ ቀማሽ ነው። ታድያ ይህ የማይሽር ጠባሳ ከትውልድ ትውልድ እየተሸጋገረ ገና ከእናታቸው ማህፀን ብቅ እንኳን ላላሉት  ለመጻዒ ትውልዶች እጣፈንታቸው ዛሬ እየተሠራላቸው እንዳልሆነ ማን ደፍሮ መናገር ይችላል? — የ “ያ ትውልድ” — ከተማዋ ትታመሳለች። ብዙ ነገሮች መናድ ይጀምራሉ። ሀገሬው ሰማዩን ሲያርስ ንጉሡን ሲከስስ ይውላል። ወጣቱ ያነገባትን ተስፋ ይዞ  በስሜት  እየተመራ በአንድ አቅጣጫ ብቻ የለኮሳት እሳት መልሳ ራሱን ትበላዋለች። “አብዮት ልጆቿን በላች” የተባለለት የ60ዎቹ ትውልድ ገፅታ ልብ ይሏል። — ጥላ (shadow) ሲገፈፍ — አንድ ግለሰብ ለመካድ ወይም ለመጨቆን የሚሞክረውን ንቃተ ህሊና የሌለውን፣ የተጨቆነ እና ብዙውን ጊዜ የማይፈለጉትን የእራስ ገጽታዎችን ይወክላል። የግል ጥላው ልንገነዘበው ወይም መጋፈጥ የማንፈልገውን የራሳችንን ማንነቶች ያቀፈ ነው። ለምሳሌ፦ ተቀባይነት የሌላቸው ግፊቶች፣ ምኞቶች ወይም በማኅበራዊ ደረጃ የማይፈለጉ ባሕርያት  ወዘተረፈ.. ዩንግ እንደሚለን እነዚህ ማንነቶች ባልተቀበልናቸውና በካድናቸው ቁጥር በእኛ ላይ  ኃይል እያገኙ እና ከቁጥጥራችን  እየወጡ ተገቢ ያልሆኑ ድርጊቶችን እስከመፈጸም ሊያደርሰን ይችላል። ስለዚህ ጥላን ማቀናጀት የጁንግ የግለሰባዊነት ፅንሰ-ሀሳብ አስፈላጊ አካል ነው - የግል እድገት እና ራስን የማወቅ ሂደት። ጥላውን በመቀበል እና  በማዋሓድ ግለሰቦች የበለጠ ሙሉ፣ ትክክለኛ እና በሥነ-ልቡና የተዋሓዱ እንዲሆኑ ያስችላል —ይለናል። ማኅበረሰብ የተዋቀረበት ጠንካራ መሠረት መፈረካከስ ሲጀምር፦ ግለሰብ  በደህና ጊዜ ሸሽጎ ያኖራት ነውሩ የሚፈራው እና የሚገዛለት ነገር ሲያጣ ከጓዷ ወጥቶ አደባባይ ላይ ርቃኑን ይቆማል። እንግዳ ማንነቶች ብቅ ብቅ ማለት ይጀምራሉ። ሥርአት አልበኝነት፣ ስግብግብነት፣ ሌብነት፣ ጭካኔን የመሳሰሉ የሰው ልጅ አውሬያዊ ባሕሪዎች ጥርሳቸው አግጥጠው መታየት ይጀምራሉ። ይህም ማኅበረሰባዊ መልክ ሲይዝ እኛን ይመስላል። መጽሐፏ ቆም ብለን እራሳችንን እንድናይ ትጋብዘናለች። — የሰፈሩ የተከበረ አድባር — ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል ትልቅ ቦታ የሚሰጠው እና ማንነቱን የመሠረተበት አንድ አይነኬ፣ አይመረመሬ አድባር አለው። በወለፈንዴነት የምንመላለስባትን ህይወት ትርጉም የምትለብሰው በዚህ አድባር በኩል ነው። ይኽን አድባር የወከሉት ካህኑ የተራኪው የማደጎ አባት ናቸው። የቅድስና ምሳሌ እርሳቸው ናቸው። እርሳቸው የሰፈሩ አድባር፤ የማይናዱ የሚመስሉ የማኅበረሰብ ዕሴት፤ እልፎች የተመረኮዙት ተሰባሪ የማይመስል ምርኩዝ ናቸው። በጊዜ ጉልበተኝነት ከዕለታት በአንዱ ቀን የዚህ አድባር መገለጫ እንደቅርፊት ከላዩ ላይ እየተገፈፈ ድራሹ ይጠፋል። የተጠለሉበት ቤት ምሰሶው የጊዜ ፈርጣማ ክንድ ሲያርፍበት ይዘምማል። ከዕለታት በሌላኛው ቀን ደግሞ  የጊዜ አውሎ ነፋስ ጣሪያውን ገንጥሎ መጠለያ አልባ ቤተኛ ያደርገናል። በመጨረሻም ማገሩ ይወድቃል። ያ ባለግርማ በምልአት የቆመ የሚመስለው ዋርካ  ዳግመኛ እንዳንጠለልበት ሆኖ ይፈርሳል። ድንገት በዙሪያችን ባዶነት ያረባል። — የመጨረሻው መጀመሪያ ነጥብ — ይሄ መጽሐፍ ከፈጠራ ልቦለድነት ከፍ ያለ ኮርኳሪ፣ መተከዣ የሚሆኑ ጥልቅ ሀሳቦችን ይዳስሳል። ሥነ ጽሑፋዊ ውበቱ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ አይደለም። ሁሉም ሊያነበው የሚገባ መጽሐፍ ነው። ይህን ውብ ድርሳን ለሰጠንን ለእሱባለው አበራ ንጉሤ እጅ ነስተናል።🙏
1 9947Loading...
26
ፀሓይ ከጨለማዬ ምን አለሽ? — ዳሰሳ | Yodit Amanuel —    “ቀለም በቀንድ (በብልቃጥ) ሳለ ጨለማ ነው፤ በተጻፈ ጊዜ ግን ብርሃን ነው። ቀለም በቀንድ ሳለ ድዳ ነው፤ በተጻፈ ጊዜ ግን መላሰኛ ነው። ቀለም በቀንድ ሳለ ጭምት ነው፤ በተጻፈ ጊዜ ግን እንደሰከረነው። ሁሉንም ይለፈልፋል።” —ከዘነብ ኢትዮጵያዊ፣ መጽሐፈ ጨዋታ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ— ከመጽሐፏ ማለፊያ እግረ መንገዳችንን ጨልፈን እነሆ በረከት... ደራሲው ከዚህ በፊት ያልተሞከረ አዲስ “ማሕሌታይ” የተባለ የድርሰት አጻጻፍ ስልት  እንደጻፈው በመጽሐፉ ማሳረጊያ ላይ ይነግረናል። ይህ መጽሐፍ በኢትዮጲያዊው የዜማ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ሦስት የዜማ ስልቶች ባሕርይ በግዕዝ፣ ወመቋሚያ፣ ዕዝል ወጸናጽል፣ አራራይ ወከበሮ በተወከሉ ሦስት  ክፍሎች የተዋቀረ ሲሆን በዋናነት ጦርነት፣ ቀቢፀ ተስፋ፣ ፀፀት፣ ህላዌ፣ ነፃ ፍቃድ በጥልቀት ይዳስሳል። በመጀመሪያው ማለትም በ “ግዕዝ ወመቋሚያ” በተወከለው ክፍል ደራሲው የግዕዝን ዜማዊ ባሕርይ በመመሰል በዚህኛው ክፍል ጠንካራና ጠጣር ፍልስፍናዎችን ትዝብቶችን በሦስተኛ ተራኪ መደብ፣ ሁሉን አወቅ (omniscient)  አንጻር ይተርክልናል። በ“ሰማይ አይታረስ፣ ንጉሥ አይከሰስ” ሁሉም ነገር ቀዝቃዛ ይመስላል። በስሜት ተካልበው ከደጃቸው ያኖሩት ባዕድ፣ ከመጡበት መንገድ የሚነፍሰው ንፋስ ከቀልብ ያልተረገጠ ዳናቸውን እያጠፋ መነሻ ቢስ አድርጓቸዋል። ከትላንት ሲያሻግሯቸው የነበሩ ድልድዮችን አፈራርሰው ዳግም በትውስታ እንዳይመለሱባቸው ሆነዋል። ትዝታቸው ደብዛው ጠፍቶ ድንገት ከየትም እንደመጡ፣ ግር በተሰኙ ሕዝቦች የተመላች ከተማ፣ ማንም በማንአለብኝነት ህመምና ጉስቁልናውን ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ባላየ ባልሰማ የሚተላለፍባት በውል ያልተቃኘን የዘመን መልክ በዚህ ባልታወቀው ሦስተኛ መደብ ተራኪ ከየጓዳው  መጋረጃውን እየገለጠ ትዝብቱን ያስቃኘናል። ዐበይት ከሆኑት የፍልስፍና ዘርፎች ዲበአካላዊ (metaphysical) የሆኑ ጥያቄዎችን እያነሣ ሲብሰለሰል እናገኘዋለን። ለምሳሌ፦ በገፅ 31 ላይ እንዲህ ይላል፦ “ይህ ዓለም ፈጣሪና መጋቢ አለውን? ወይስ የሰው ልጅ የመለኮት ሥራ ሳይሆን ከአጽናፈ  ዓለሙ ጋር ወደ መኾን የመጣ የዐቢይ ፍንዳታ ክስተት ውጤት ነው? አምላክ የሰውን ልጅ ፈጠረ ወይስ የሰው ልጅ አምላክን?” ...በማለት የሰው ልጅ የህላዌን ወለፈንድነት (Absurdity) ለማምለጥ የሸሸገባት ድንኳኑን ህልው መሆን፣ አለመሆኗን ተያያዥ ኈልቆ መሳፍርት ጥያቄዎችን እያነሣ የሰውን ልጅ መሠረተ ምሥጢር ለመፍታት ሲበረብር ይታያል። — ነፃ ፍቃድ / free will — በነፃ ፍቃድ (Free will)  እና በተወስኗዊነት (determinism) ፅንሰ ሀሳብ በፍልስፍና፣ በሥነ መለኮት እና በሥነ ልቡና ውስብስብና አከራካሪ ሲሆን። በፍልስፍናው ዘርፍ ዲበአካላዊ (metaphysics) ላይ የተመሠረተው ነገረ ህላዌ (existentialism) ሥር የሚዳሰስ እሳቤ ነው። በነጻ ፍቃድ ላይ በርካታ ቁልፍ አመለካከቶች አሉ። — ነፃ ፈቃድ — የሰው ልጅ ሙሉ በሙሉ በውጫዊ ሁኔታዎች ወይም አስቀድሞ የተወሰነ የክስተቶች ሰንሰለት ሳይወሰን በነፃነት ምርጫ እና ውሳኔ የማድረግ ፍቃድ አለው የሚለው አመለካከት። — ተወስኖአዊነትት / Determinism — የሰዎች ድርጊቶች እና ምርጫዎች ጨምሮ ሁሉም ክስተቶች የሚወሰኑት በቀደሙት ክስተቶች እና በተፈጥሮ ሕግጋት ነው የሚለው አመለካከት ነው። ምርጫችን ከቁጥጥራችን ውጪ የሆኑ ነገሮች ውጤት ተደርጎ ስለሚወሰድ የነጻ ምርጫን እና የሞራል ኃላፊነትን ይፈታተናል። ሌላኛው፦ — ተኳሃኝነት / compatibilism — ነፃ ምርጫን እና ተወስኖአዊነትን ለማስታረቅ የሚሞክር የመካከለኛ ደረጃ እይታ። ታዲያ በ“ፀሓይ ከጨለማዬ ምን አለሽ?” መጽሐፍ ላይ ከተነሡት አያሌ ጭብጦች ውስጥ ነፃ ፍቃድ አንደኛው ነው። በመጽሐፉ በገፅ 41) እንዲህ ሲል ይጠይቃል፦ “በምልዕተ ዓለሙ ውስጥ የሰው ልጆችን ዕድል ፈንታ የሚወስን ኃይል አለ? የተጻፈው ይፈጸም ዘንድ ግድ አይደለምን? ወይስ ነገረ ፍርቱና እና የአርባ ቀን ዕድልም ያረጀ ያፈጀ የአቅመቢሶች ተረት ነው?” ...ይቀጥልናም፦ “በነፃ ፍቃድ መኖር ውስጥ ሙሉ ለሙሉ የመሸከም ነገር በሰው ልጅ እጅ ላይ ብቻ እንዲወድቅ ይኾናል። ኃላፊነትን በመውሰድ ውስጥ ተጠያቂነት ይከተላል። ቀናው ሲፀድቅ፣ ስሁቱ ደግሞ በሥጋውም በነፍሱም ይኮነናል። ነገር ግን በደግም፣ በክፉም ከሞት በኋላ እስከዘላለም የሚፀና ፍርድ ለመቀበል የአንድ ሰው እድሜና ህይወት በቂ ነው?”  ...ብሎ በገፅ 41 ነፃ ፍቃድ፣ “እጣፈንታና የዕለት እንጀራ” ብሎ በሰየማት ንዑስ ርእስ ሥር መብሰልሰሉን ይቀጥላል። ሁለተኛው ክፍል በ“ዕዝል ወጸናጽል” ይወከላል። በዚህ ክፍል ተራኪው ከሦስተኛ መደብ ወደ አንደኛ መደብ ተራኪነት ሽግግር ያደርጋል። — ሽግግር / transcend — ይህ የተራኪውን የሰብዕና ሽግግር በአንድ ግለሰብ አንፅሮተ ዓለም ምልከታ ከመነሻ ተነሥቶ ወደ ምንምነት የሚሸጋገርበትን መሥመር ተከትሎ የተራኪውን በልጅነት ያለውን የህላዌ አረዳድ (ከነገሮች ሁሉ መለኪያነት ማዕከላዊነት) ተነሥቶ ቀስ በቀስ እየተገፈተረ ከጨዋታው ሜዳ እስከወጣበት የወጣትነት ጊዜው ያደረገውን የህይወት አረዳድ  ሽግግር አስፍሮል። በህይወት ዘመናቸው በቅድስና ተመላለሱ ስለሚላቸው የተራኪው ስለ ካህኑ የማደጎ አባቱ እንዲህ ሲል ይመሰክራል፦ “ጠባያቸውና ምግባራቸው ጠንካራ ነው። ከዓለም ፍቃድ ራሳቸውን አግልለዋል። የንጽህናን ዝናር ታጥቀዋል።” (ገፅ 55) ...ሆኖም ህይወት መልኳን እየቀየረች ጀንበር እያዘቀዘቀች ስትመጣ ቀስ በቀስ እምነቱ መፈረካከስ፣ ተስፋውም መሟጠጥ ቢጀምርም  በዚህ  ክፍል ጭላንጭል ብርሃን ማየት የተሳነው አይመስልም። — ቀቢፀ ተስፋ — በመጽሐፉ የሚዳሰስው ሌላኛው ጭብጥ ቀቢፀ ተስፋ ነው።  በህይወት መድከም እና ስለወደፊት ምስል ከሳች አንዳችም ነገር ማጣት ተስፋ ቢስነት ነው። የሁላችንም የልብ ጓዳ ቢበረበር ቢያንስ ለአንድ ጊዜ በዚህ ዓይነት ስሜት ውስጥ አልፈናል። — ኢምንትነት — በውጪው ዓለም ያለውን ትርምስ  ሽሽት ወደ ውስጥ የሚደረግ ጉዞ እና  በውስጣዊ ዓለም ከተንሰራፋው ጥልቅ እና  አስፈሪ ጨለማ  ጋር መፋጠጥ፣ በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን  ተራኪው ከመታዘብ እና ከመብሰክሰክ ያለፈ እዚህ ግባ የሚባል እንኳን ተሳትፎ እንደሌለው ሲረዳ የማይቀረውን የህይወት ስንክሳር ይጋፈጣል።  ተራኪያችን በስተመጨረሻም የሰው ልጆች እድል ፈንታቸው በእጃቸው ላይ እንዳልሆነች ከእነርሱ ቁጥጥር ውጪ መሆኑንና ሌሎች በእነርሱ ላይ አቅም እንዳላቸው ሲገልጽ  እንዲህ ይላል፦ '“በድንገት ከእንስሳ በታች እንደሆንኩ እንዲሰማኝ ሊያደርጉኝ የሚችሉ ሰዎች ደጃፌን በየትኛውም ቅፅበት ቢያንኳኩ ላስቆማቸው አልችልም። ኢምንት ነኝ።'” (ገፅ 109) በመጨረሻም በ “አራራይ ወከበሮ” የተወከለው  የመጽሐፉ ሦስተኛ  ክፍል ህልው በመሆናችን የማይቀርልን የህይወት  ድለቃ ህማም ሲቃኝ፦ — ጦርነት — ዛሬ እያለፍንበት ያለውን የህይወት ምስቅልቀል በትክክልም የዚህኛውን ዘመን ትውልድ ወካይ ተደርጎ የተገለጸው አንደኛ መደብ ተራኪ የጦርነትን አሰቃቂነት ይነግረናል። በዚህ ውስጥ እልፍ  የተረሣ እና ችላ የተባሉ የግለሰብ ህይወቶች ሰሚ የሌላቸውን የጣር ድምፆችን ያወጣሉ።
1 5878Loading...
27
Media files
1 5101Loading...
28
A well read woman is a dangerous creature. ”በሚገባ ያነበበች ሴት አደገኛ ፍጡር ናት!“ ይህ አባባል በመጀመሪያ ወደ አእምሮዬ የጠራት የትኩሳቷ ሲልቪ ናት። ስብሀት እንደነገረን ሲልቪ አፏ ሰፊ፤ ፈረንሳይኛዋ የማይጠገብ፤ ወሲብ በጣም የምትወድ፤ በሳልና ማንበብ ነፍሷ የሆነ፤ እራሷም አጫጭር ልብወለዶችን መጻፍ የምትሞካክር ውብ ፈረንሳዊት ናት። ሲልቪ በመጀመሪያ ከስብሀት ጓደኛ ተመስገን ጋር የፍቅር ግንኙነት ነበራት። ስብሀት ተመስገንን ፍለጋ ከቤቱ ሲሄድ ሲልቪን ብዙ ግዜ ያገኘታል። ተመስገን ከሌለ ከሲልቪ ጋር ወሬ ይጀምራሉ። ቀስ በቀስ ይቀራረባሉ። ስለ ታላላቅ ደራሲዎችና ስላነበቡት መጽሐፍት ለረጅም ሰዓት ያወራሉ። ስነ-ጽሁፍ ይበልጥ ያቆራኛቸዋል። ግንኙነታቸው ወደሚቀጥለው ደረጃ ተሸጋግሮ ሲልቪ እና ስብሀት ፍቅር ይጀምራሉ። የቀድሞ ጓደኛዋን ተመስገንንም ምክንያት ፈጥራ ትለየዋለች። ከቆይታ በኋላ ተመስገን ሌላ አዲስ የሴት ጓደኛ ይይዛል። ስብሀትም ከሲልቪ ጋር በመለያየቱ ይቆጭ እንደሆነ ተመስገንን ይጠይቀዋል። ተመስገንም ሲመልስ፦ “አእምሮዋ ምላጭ የሆነች ሴት ሙሉ በሙሉ ሴት አትመስለኝም። ሲልቪ ስለ ኢትዮጲያ የምትጠይቀኝን ጥያቄዎች ለመመለስ እራሱ ብዙ አስፕሮ መዋጥ ይጠበቅብኝ ነበር። አሁን አንዲት ጅል ቢጤ ፈረንሳዊት አግኝቻለሁ። መጽሐፍ ባለበት ዝር አትልም። በጣም ተስማምታኛለች” ታዲያ ይህ አባባል ሲገለበጥ እያንዳንዷ ከነጭራሹ የማታነብ ሴት ሁሉ ጅልና ተራ ናት አይልም። ብቻ በዚህ አለም ላይ ሁለት አይነት ሴቶች አሉ—ጭንቅላታቸውን ለማሰብ የሚጠቀሙበት እና ጭንቅላታቸውን ሂዩማን ሄር ለማንጠልጠል የሚጠቀሙበት። © Tewodros Shewangizaw
2 08713Loading...
29
Media files
1 9425Loading...
30
#አልተዘዋወረችምን እንዳነበብኳት (የግል ምልከታዬ) የአሌክስ አንፅሮ አለም አስደማሚ ነው። ብዕሩ ትብ ናት። ትርክቷ መሳጭ ነው። ህላዌን እየታከከች ወደ አርያም ይዛ ትነጉዳለች። በአሌክስ የትረካ መስኮት የወጣች ነፍስ ከአዕምሮ በላይ የሆኑ ተሻጋሪ ሀቆችን ሳትመረምር አትመለስም። የአሌክስ ራዕየ ልቦና (imagination) አያስደምም፣ አያስደንቅም። ያስደነግጣል! የሰዎችን ነፍስ እንዲረዳ ተመርቋል። አሌክስ በሆነ ዘመን በሴት ነፍስ ተፈጥሮ ነበረ። (በፍቅርሲዝም ሀይማኖት መሰረት 😂) አሁን ወንድ ነው። የሁለቱንም አለም በሚገባ የተረዳ ፀሀፊ ነው። በአልተዘዋወራችም ውስጥ የተነሱ የፍቅር፣ ቅናት፣ እጣፈንታ፣ ውሳኔ እና የውሳኔው ውጤት፣ የሆነው ሁሉ ስለምን ሆነ፣ ማን ምን አጠፋ? ምን ገጠመው? እንዴት? መቼ፣ በመጨረሻም በምን ተጠናቀቀ? የሚሉ ጥያቄዎች አብዛኛዎቹ ተመልሰዋል። የተመለሱበት መንገድ እጅግ አሳማኝ በሆነ መልኩ በመሆኑ በእርግጥም አንበብው ሲጨርሱ "እንዴት ያለ ውብ ታሪክ ነው!?" በማለት በእርካታ መፅሐፉን ይከድነዋል። መፅሐፉን ከከደነ በኋላ ግን የቀረ ነገር፣ ያልተመለሰ ጥያቄ መኖሩ ይህ መፅሐፍ ከውስጣችሁ እንዳይወጣ ሆኖ ለቀናት ያብሰለስላቹሀል። ለምሳሌ የማህደረ ሰላም እናት ሶስት ልጆችዋን ለምን ጥላ ጠፋች? በርግጥ ምክንያቷን በገደምዳሜ ተገልፇል። ምክንያቷን በወረቀት ፅፋ ለባሏ ሰጥታ ነው የሄደችው። ወረቀቷ የያዘችው መልዕክት አልተገለፀም። ለምን? እዚህ ጋ ነው አሌክስ አንባቢን መንፈሱን ስቅዝ አድርጎ በመያዝ በግምት እንዲብሰለሰል የሚያደርገው። ድንቅ ደራሲ ብቻ ነው ይህን የሚያደርገው። ጥያቄው መሰረታዊ ነው። ብዙ ግትልትል የጥያቄ ጓዞችን ይዞ ይመጣል። ይህ ነው ታሪኩን ከጨረሳችሁ በኋላ እረፍት የሚነሳችሁ። የማህደረሰላም አባት ከውስጤ አልወጣም፣ ስሜቱን ጎረጎርኩ፣ ልጆቹ የሱ አይደሉምን? ሃይሚ ጠቁማለች cues? የሚመላለስብኝ የመፅሀፉ ዋነኛ ጭብጥ ነው። ተመልሰን ወደዚህ እንመጣለን ..... "አበባም ይሁን ድንጋይ፣ በግድ እስካሸከሙን ድረስ ያው ሸክም ነው።" ..... ምናልባት የማህደር እናት፣ አብርሽ፣ ማህደርሰላም እና ዮናስ የተጫነባቸውን አልያም የመጣላቸውን ገፀበረከት የተቀበሉበት ሁኔታ .... እያልኩ ወደ ውስጥ ጠልቄ ከነፍሳቸው እየቀዳሁ፣ ለነፍሴ ትርጉም እየፈለኩ ዋተትኩ ..... ሁሉን ጨርሶ ቢነግረን እንዲህ እብሰለሰል ነበረ? አይመስለኝም። እንኳንም አልነገረኝ! አሌክስ አብረሃም መፅሀፍትን ሁሉንም አንብቤያቸዋለሁ። ለ11 አመት እዚሁ ፌስቡክ የማውቀው ምርጥዬ ነው። ለፅሁፉ የሚመርጠው የአተራረክ አንፃር (viewpoint) አንደኛ መደብ የሚባለውን ነው። "እኔ" ብሎ ራሱን አስተዋውቆ፣ የሰማውን፣ ያየውን፣ የገጠመውን፣ የህይወት ምልከታውን፣ ትዝብቱን እየተረከ አንባቢን እስከመጨረሻዋ ገፅ ይዞ ይሄዳል። ከዚህ ቀደም፣ ዙቤይዳ፣ አልሀምዱሊላህ ደህና ናት፣ ዶክተር አሸብር፣ ሀኑን፣ ከእለታት ግማሽ ቀን እና ሌሎችም የፃፋቸው ታሪኮች በአንደኛ መደብ የተተረኩ ናቸው። ይህን የአተራረክ መንገድ መንገድ ስብሀትን ጨምሮ ብዙዎች ሄደውበታል። በርግጥም ከነበረ፣ ካየና በታሪኩ ከተሳተፈ ሰው መስማት ልዩ ነገር ነው። አደራረጉን ላወቀበት ምርጥ የአተራረክ አንፃር ነው። አሌክስ ማስተር አድርጎታል። የስነፅሁፍ ሀያሲያን ይህ መደብ ውስንነት አለው ይላሉ። ተራኪው አመለካከቱንና በነገሮች ላይ የሚሰጠው ፍርድ ከሱ የህይወት ምልከታና ተሞክሮ አንፃር ስለሆነ ወጥነት የለውም ይላሉ። ለተደራሲ ትችትና ትሩጋሜ በሩን ስለሚዘጋ በአንድ አንፃር ብቻ መፃፍ የራሱ ክፍተት አለበት። ይህን ክፍተት ለመሙላት ድንቅ ደራሲዎች ባለብዙ ወገን አንደኛ መደብ አተራረክን አስተዋውቀዋል። እዚህ ጋ ነው አሌክስ በአልተዘዋወረችም ከፍ ብሎ፣ ጎልምሶና ገኖ የመጣው። የሌሎችን viewpoint ከነሱ ከራሳቸው አንፃር ለማቀበል የሰራው ስራ እጅግ አመርቂ ስራ ነው። በ360° ታሪኩን እየተዟዟረ ያስቀኘናል። አሌክስ መፅሐፉን አንብባችሁ ከጨረሳችሁ በኋላ እንኳ አይፋታችሁም። ሌላ የቤት ስራ ይሰጣቹሀል። ገፀባህሪያትን ከእምነት፣ ከሰብዓዊነት፣ ከፀባይ፣ ከፍቅር እና ከትዳር ከመቶ ነጥብ እንድትሰጡ ይፈትናቹሀል። ይህ መልመጃ ከባድ ፈተና ውስጥ ይከታቹሀል። (ይህ አቀራረብ ለመፅሐፍ ክበብ ውይይት እጅግ ጠቃሚ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።) አሌክስ በመፅሀፍ ሽፋን ትግል እንድገጥም ያደረገኝ የመጀመሪያው ፀሀፊ ነው ብዬ አስባለሁ። ገፀባህሪያትን ከተለያዩ አቅጣጫዎች በመሳየት የሚገርም የገፀባህሪያት አቀራረፅ ዘዴን ተከትሏል። ለምሳሌ ማህደረ ሰላም ጠይም ነች። ካነበባችሁ በኋላ ከውስጣችሁ አትወጣም። ጠይም ነች (አሌክስ በገለፃት ልክ ለመግለፅ አልችልም። ማንም አይችልም) አንድ አንፃር ይቀራል። የማህደረ ሰላም አባት አንፃር ይህ የሚያሟላው የራሱ የታሪክ አውድ አለ ብዬ አምናለሁ። ስለዝህች ውብ ነፍስ ከተለያየ አቅጣጫ እያሳየን ነፍሳችንን ያቃትተዋል። ከአብርሽ አቅጣጫ (ጅል ብቻ አይደለም፣ ራስወዳድ ከንቱ ነው) ከራሷ፣ ከሀይማኖት (ስምን ሴጣን ያወጣዋል) ከቶማስ (ቂዥቢው ) ስነፅሁፍ የተመረቀ ነው። ፀሀፊ ነኝ ብሎ ሌሎችን የሚተች ነው። ምንም ነገር አይመቸውም። ለማህደረ ሰላም ግን ልቡ ሳሳ። አንድ ነገር ፃፈ። የፃፈው አንድ ፅሁፍ ስለከንፈሯ ሁለት ቃል ነው፣ እንዲህ ይላል "የማህደረሰላም ከንፈር!" (ከንፈሯ ምን ቢመስል ነው 🤔) ዮናስ (ይህ ሰው የሚገርም ነው ኡፍፍፍፍ ስደት፣ ስቃይ፣ ተስፋ፣ ፍቅር፣ ቅንነት፣ ለቤተሰብ የሚከፈል መስዋዕትነት) እና ሌሎችም በሁሉም መነፅር ልጅቷን ማሳየቱ በርሷ ጫማ ውስጥ ሆነን አብረናት ተደስተን፣ አዝነን፣ ቆዝመን፣ ተብሰልስለን ብቻ አብረናት እንድነዋትት አድርጎናል። (ስታሳዝን 😢) አንድ ቦታ ላይ የሆነችውን ለጎሮቤታቸው ስትነግረው፣ በጣም ስትነግረው በጣም ይናደዳል፣ (ልክ አንባቢ እንደሚናደደው) እንዲህ ይወርዳል ምልልሳቸው 👇 “እናስደብድበው ይሆን!?” አለኝ ሳቄ አመለጠኝ፡፡ “ምን ያስቅሻል? ጥርሳም… ይኼ ሸርሙጣ ... መቅመስ አለበት! ለመሆኑ ምንድን ነው ሥራው?” “ደራሲ!” “ያው “ሸርሙጣ” ማለት’ኮ ነው! አንቺ ስንት ሰው እያለ ምን አልከሰከሰሽ? እኔ ወርቅ እጅ ያለው ሜካኒክ እድርሽ አልነበር? እውነቴን’ኮ ነው በዚህ ስታልፊ ስንት ሠራተኞቼ ናቸው አንችን እያዩ አአአአአአ ብለው ሥራ የሚፈቱት የነበር … !? ሴቶች ስትባሉ ሕዝብ መኻል ካለ ንብ፣ መድረክ ላይ የሚዘል ዝንብ ትወዳላችሁ... አልተዘዋወረቸም ገፅ 87 በአፃፃፍ ቴክኒክ ደረጃ መፅሐፉን አንዴ ገልጠው ማንበብ ከጀመሩ ማስቀመጥ ከባድ ነው። የድርጊቶቹ ወዲያው ወዲያው መለዋወጥ pacing በሚገባ መከወኑን ያሳያል ምነው ቢሉ፣ ማንበብ ከጀመራችሁ፣ አታቆሙም! ከአንድ ሁነት ወደ ሌላው ሲሻገር አተራረኩን በ transition በኩል ልምዱ የካበተ ፀሀፊ ያደርገዋል። አውዱን ለማመላከት effortlessly ቅይር ሲያደርገው ነገር ሳያንዛዛ ያመሰጥረዋል። የመፅሀፉ አወቃቀር ለንባብ ምቹ ነው። ምልልስን ከገለፃ ሲያዋድድ አሌክስ ልዩ ነው። ለምሳሌ የሚከተለውን ምስል ከሳች ገለፃ ተመልከቱት
2 21912Loading...
31
በመካከላችን እንደ ወተት የነጣ ልብስ የለበሱ ሶስት ክብ ጠረጴዛዎች አሉ። ሁሉም ጠረጴዛዎች ላይ፣ የሚያንፀባርቁ ሹካና ማንኪያዎች ተደርድረው፣ መኻላቸው ላይ፣ ብርጭቆ ውስጥ የቆሙ ደማቅ ፅጌረዳዎች ተቀምጠዋል። በቀኝ በኩል ባሉት ሰፋፊ ውርደ ሰፊ መስኮቶች ላይ፣ ጣል የተደረጉት ስስ ነጫጭ መጋረጃዎች፣ ከውጭ በሚገፋቸው ነፋስ ረጋ ብለው ይንቀሳቀሳሉ። ነፋሱ ከውጭ ሲገፋቸው፣ መጋረጃዎቹ የእርጉዝ ሴት ቀሚስ መስለው፣ በአየር ይወጠሩና መልሰው ይረግባሉ። ነፋስ እያረገዙ ነፋስ የሚያስወርዱ መጋረጃዎች። በዚያው ገፅ ላይ ትንሽ ወረድ ብሎ ገለፃውን እንዲህ ይቀጥላል 👇 " የወይን ጠርሙስ ነው .....ዘንበል ብሎ: ከውስጡ እንደ ፏፏቴ ቁልቁል ይወርዳል ..... ቀይ ደም የመሰለ ፏፏቴ ..... ጨነቀኝ። ቀጥሎ በመጋረጃው በኩል የሚገባው ስስ ነፋስ፣ ወደ አውሎ ንፋስ ተቀይሮ ቤቱን የሚገለባብጠው፣ የጠርሙስ ወይን ወደ ጎርፍ ተቀይሮ እንደ ባህር ቤቱን የሚሞላው ....." እያለ ይቀጥላል። ገፅ 46 ከቋንቋው ማማር፣ ከገለፃው ምስል ከሳችነት በላይ የልቦለድ ቴክኒክን በውስጡ ይዟል። ንግርት (forshadowing) የሆነ ክፉ ነገር እያንዣበበ ነው። በተምሳሌት symbolism የተገለፀ። ነፋስ ማርገዝ፣ ነፋስ ማስወረድ፣ የደም ፏፏቴ፣ አውሎ ንፋስ,፣ የገፀባህሪያት የዕድገትና የለውጥ ጉዞ character Arc ውብ በሆነ መልኩ እየወጣ እየወረደ ከኑባሬያቸው ጋር ተሰናስሎ ይታያል። ቅን፣ የዋህና ንፁህ የነበሩ በደረሰባቸው የህይወት የጠየመ ጉዞ ፈላስፋ ይሆናሉ። በአልተዘዋወረችም በርካታ ጭብጦች ተዳሰዋል ተስፋ፣ ቀቢፀተስፋ፣ ፀፀት፣ ፍቅር፣ ስደት፣ ህላዌ፣ የህይወት ትርጉምን ፍለጋ፣ ወሲብ ብዙ ብዙ ....... እባካችሁ አንብቡት 👐 © Muktarovich Ousmanova
2 5126Loading...
32
Media files
1 8402Loading...
33
ይኼን ፊደል አትናቀው! ተዋነይ ቅኔ ዘርፎበታል! ሔኖክ የግዜ ቆጠራ ጥበቡን አስፍሮበታል! እልፍ መጽሀፍት ተጽፈውበታል! ይኼን ፊደል አትናቀው። ይህ ፊደልኮ ቢያንስ የ4,500 አመት እድሜ ባለጸጋ ነው። ሌላው ሌላው ቢቀር እንኳን እድሜው እንድታከብረው ያስገድድሃል። እንግሊዝ የራሱ ፊደል የለውም። ሀያ ስድስት ፊደላትን ከላቲን አስር ቁጥሮችን ከህንድ ተውሶ ይጠቀማል። ለአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ግን ግእዝ አባታችን ነው። ግዕዝ የተውሶ አይደለም። ግዕዝ የራሳችን ነው። ግእዝ የላቲን ፊደል የሌሉት ብዙ ጠቃሚ እሴቶች አሉት። ለምሳሌ እንግሊዝኛ በግዕዝ ፊደል መጻፍ ቢጀምር ከcapitalization, spelling and pronunciation ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ሁሉ ይቀላሉ። የግዕዝ ፊደል አይደለም ለሀገር በቀል ቋንቋዎች ለባእዱም ምቹ እና ተስማሚ ነው። እንግሊዝ ታዲያ ብልጥ ነው ፤ ይሉኝታ ቢስ ነው። ዛሬ በዩኒቨርስቲዎቻቸው ውስጥ እያስተማሩበት ነው። ነገስ? ከነገወዲያስ? እኛ የነሱን ብልጭልጭ ለማግበስበስ ቤታችንን ጥለን ሄደናል። ባለቤት የሌለው ቤት ደግሞ ለሌባ ምቹ ነው።ካሁን ቀደም እንጀራን አይረባም ፣ ጥቅም የለውም ብለህ ንቀህ በርገርና ፒዛ የመሳሰሉትን ”ጀንክ ፉድ“ ስታግበሰብስ ፈረንጅ ቀደመህና ጤፍን ላፍ አድርጎ የባለቤትነት መብቱን ወሰደብህ። አሁን ጤፍ ለጤና ተስማሚ glutton free መሆኑን ፈረንጅ ሲነግርህ እንደገና ተመልሰህ ግር ብለህ ወደ እንጀራ። አባቶቻችን ጾም ለስጋም፣ ለነፍስም እንደሚተርፍ ያስተማሩንን ስታጥላላ ኖረህ ዛሬ ፈረንጅ ስም ቀይሮ intermittent fasting ሳይንሳዊ ነው ብሎ አበው ከሺ አመታት በፊት የነገሩህን ጥበብ ዛሬ ነጭ ሲነግርህ አፍህን ከፍተህ ሰፍ ትላለህ። እንላለን! እንዲያው የምንገርም ጉዶች እኮ ነን። ነጭ ካልነገረን አናምንም የምንል ጉዶች!! ይሄም ብቻ አይደለም። አባቶቻችን ስለ ጸሎትና አርምሞ ብዙ አስተምረውናል። ዛሬ ከውጪ transcendental meditation ወዘተርፈ እየተባለ የሚነገረን ሁሉ አዲስ አይደለም። እዚሁ እኛ ጋር የነበረ፣ ያለ ጥበብ ነው። የራሳችንን አባቶች አንሰማማ። የራሳችንን መጻህፍት አናነብማ። ግእዝ አንችልማ። የደብተራ ቋንቋ ብለን እናናንቃለና። ታዲያ ውጤቱ ምንድነው? መደንቆር! በስጋም በመንፈስም መደህየት! ሌላ ሳይንሳዊ እውነታ ልንገርህ። መቼም ሳይንስ ካልተባልክ የሚነገረው ሁሉ እውነት አይመስልህም። እና ሳይንስ እንዲህ ይላል፦ ከእንቅልፍህ እንደተነሳህ በቀዝቃዛ ውሃ ታጠብ። በባዶ ሆድህ 1 ሊትር ውሃ ጠጣ። ከዛ ለ45 ደቂቃ ምግብ አትብላ። ይህ ሳይንስ እንደ አዲስ የሚነግርህ ነገር እኮ አዲስ አይደለም። በጠዋት የምትጠመቀው ጸበል፤ በጠዋት የምትጠጣው ጸበል ነው። ግን በቤተክርስቲያን በኩል የሚነገር ከሆነ ኋላቀር ነው ብለን ደምድመናላ!! ተው የአባቶቻችንን ጥበብ ያዝ። አባቶቻችን ፍጹም አልነበሩም ግን ጠቢብ ነበሩ። እንደምንንቃቸው አይደሉም። አሁንም አልረፈደም። ግዕዝ ተማር። አባቶቻችን ሊነግሩን የፈለጉትን ለመረዳት የምንችለው ያንግዜ ብቻ ነው። ፈረንጅ ግዕዝ ተምሮ ያገኘውን ቁምነገር በእንግሊዝኛ ሰፍሮ ስለራስህ እስኪነግርህ አትጠብቅ።አለበለዚያ በፊደሉም እንደ እንጀራው የበይ ተመልካች ሆነን መቅረታችን ነው። በእጅ የያዙት ወርቅ ሆኖብን የትም የጣልነውን ሀብት ፣ ፈረንጆቹ አቧራውን አራግፈው ሲያጌጡበት ያኔ መቆጨት እንጀምራለን።ወርቅን ዛሬ ወርቅ ማለት ልመድ!ስለዚህ ግዕዝን በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ ማካተት የማይቀር ጉዳይ መሆን አለበት ፤ መዘግየት የለበትም። © Tewodro Shewangizaw
2 6238Loading...
34
Media files
2 3260Loading...
35
Media files
3 08010Loading...
36
በጣም የሚቀፈኝ ነገር ቢኖር መጽሀፍ ይዞ እያነበቡ ፎቶ መነሳት ነው። እንዲህ የሚያደርጉ ማንበባቸውን ፎቶው እንዲናገርላቸው ነው። ታዱያ በንግግራቸው ወይም በጽሁፋቸው ውስጥ የመጽሀፉ ቁምነገር የለም። ልብ በሉ! ቁምነገሩ ማንበብ ነው እንጂ ማንበብን ማሳወቅ አይደለም። አያችሁ መጻህፍት ማንበብ ልክ እንደ ወሲብ ነው። ወሲብ በአደባባይ አታደርጉም ወይም እያደረጋችሁ ፎቶ አትነሱም። ከተዘጋ በር ጀርባ በጥልቅ ስሜት የሚከወን ተግባር ነው። ውጤቱስ? ውጤቱ እርግዝና ነው። በአደባባይ ለሁሉም ይታያል። የንባባችሁ ውጤትም በንግግራችሁ፣ በአስተሳሰባችሁ በግልጽ ለሁሉም ይታያል! መልካም የአለም የመጻህፍት ቀን!!! © Tewodros Shewangizaw
2 9918Loading...
37
👉 🌿Ethiopian digital library🌿 A library in which you can get many ✅reference books 📚 ✅Textbooks ✅Freshman course ✅Amharic fictions ✅Premium applications ✅Extreme serious books 📚 ✅TOP BOOKS SERIOUS 📚 Join and share 👇👇 https://t.me/ethiolibrary1 https://t.me/Ethiolibrary1Bot #Share Ethiopian digital library Highschool library Pro bot
1 6232Loading...
38
በቃላትኛ: ብልሀት: በጉልህ: "እመት: ደስታ" ብዬ: ጽፌ: ከፊት: ለፊቴ: አኖርኩት: ጽሑፉን: አንብበው፤ ድንገት: መልስ: ቢሰጡኝ።እንዳላየ: እየለዩ: መጽሐፍ: ፍለጋቸውን: ቀጠሉ። እንደ: ድብብቆሽ፣ ሳውቅዮሽ: እየተጨዋወትን: ሰአቱ: ገፋ። ፊቴን: ወደመስኮቱ: መለስ: ባደርግ፤ አንዲት: ዘለግ: ያለች፣ ፀጉረ: ረዥም: ወጣት: መጣችና፣ "እማማ: ደስታ: የት: ጠፍተው: ኖረዋል! እኛ: ላይ: ታች: ስንፈልግዎ። ይኸንን: ሎሚ: ለምን: ለሰው: ሰጡት?" በማለት: በአለንጋ: ጣቶቿ: ወደ: እኔ: ጠቆመች። አተኩረው: አዩኝና: "የእኔ: ሎሚ: አይደለም" አሏት። እንግሊዘኛቸው: የሀገሬው: ነዋሪ: ቃናና: ጥራት: አለው። አይ: ተመሳስሎ: ነው። ምን: እንዴት: ቢሆን፤ የቀበና: ወንዝ: ባልቴት፤ እመት-ደስታ: እንግሊዝ: ምድር: ደርሰው?! አይ: የማይመስል: ነገር: ነው። " የእኔ: ወንድም: ሀበሻ: ነህ?" ብለው: ሲያናግሩኝ፤ እግሮቼ: ተሳሰሩ፣ ከንፈሬም: ቆረፈዱ። እንዴት፣ ምን፣ እንደምመልስ: ጠፋኝ። ጥቂት: አምጬ፣ "አዎን" የሚል: ቃል: ከውስጤ: ወጣ። ፈጠን: ብለው: ሄደው: ወንበር: አመጡና: ከአጠገቤ: ተቀመጡ። "እዚህ: ሰፈር: መሬት: ይመራሉ: ንግስቲቱ: የሚል: ጭምጭምታ: ሰምቼ: የመጣሁ: ሀገር: ጎብኚ: ነኝ። ምትረዳኝ ነገር: ቢኖር?" ከተጎናፀፉት: ወርቃማ: በፍታ: ስር: ከደረታቸው: ላይ: የተጎበጎበ የመሬት: መልከአ-ምድር: ንቅሳት: ነገር: ታየኝ። "እማማ: ደስታ: አይደሉም: እንዴ!" ስል: ብጮህ፤ "እኔስ: መሆኑን: ነኝ። አንተ: ማን: ትሰኛለህ?" አሉ: "እኔንማ: ሊያስታውሱኝ: አይችሉም። ዘመኑ: እሩቅ: ነው። በርስት: የተነሳ..." ብዬ: ሳልጨርስ፤ እጃቸውን: አንስተው:- " በቃ! በቃ! በቃ!÷ የመሬት: የርስትን: ነገር: አታንሳብኝ": አሉና: ጉንጬን: በስሱ: ዳሰስ: አድርገው: ሲሄዱ፤ ተከትዬ፣ "እንዴ! ምንድነው: ነገሩ!፤ ምን: የተባለ: ንፋስ: ነው: እዚህ: ያደረስዎት?" ስል: ጮህኩኝ። መሀረባቸውን: አውጥተው: ገፃቸውን: እየደባበሱ፣ "ርስት: ፍለጋ: ነው: ንፋስ: አይደለም" አሉና: በፈገግታ: "ደሞስ: ቢሆን: ሠማህ: ወይ: ወገኔ: ንፋስ: አበቦችን: ከማሳመም: ሌላ: ምን: ተግባር: አለው: ብለህ!" ብለውኝ: ተሰወሩ። ያንን: ምሽት፤ በቴሌቭዥንም፣ በራዲዮም፣ ከምስራቅ: የመጣ: ሀይለኛ: አብሎ: ንፋስ፤ እጅግ: ብዙ: የእንግሊዝ: ገጠሮችን: እንዳወከ፤ ከየአቅጣጫው: ተነገረ፣ ተሰማ።" ገፅ 104-105 ጃርሶ ሞትባይኖር ኪሩቤል፣ ከኪነታዊ ሕይወቱ ውጪ ፖለቲከኛም ነበር። ከ19 60ዎቹ መጀመሪያ እስከ 70 ዎቹ አጋማሽ የኢሕአፓ አባል ሆኖ ከፍተኛ እንቅስቃሴ አድርጓል። እንደምታውቁት ጠልሰም ምትሃታዊ የደብተራ ስዓል ክህሎት ቢሆን ጃርሶ ደግሞ አዲስ ጠልሰማዊ የስነፅሁፍ ዘርፍ አስጀምሯል። ይዘቱ ብቻ ሳይሆን የተፃፈበት ቋንቋ እና ክህሎት ራሱ ምትሃታዊ በመሆኑ አዲስ ዘርፍ ቢሆን ማጋነን አይሆንም። የተራቀቁ የአውሮፓ ከተሞችን የኑሮ ዘይቤ እና ታሪክ በዱሮ አማርኛ መተረክ መቻል በራሱ ምትሃትን ይጠይቃል። እስቲ ከምትሃት ነክ ታሪኮቹ ሁለቱን ጀባ እንበላችሁ አንደኛ ". . .በማግስቱ ከየብርሌው የሚዋኘው የየኔታ ጭራ ንቃይ ለደንበኛው ሁሉ ሲታይ ጉድ እየተባለ ይወራ ጀመረ ። ከጉሮሮአቸው ተጣብቆ በትንታ የሚረብሹ ደንበኞች ጩኸት ማሰማት ጀመሩ ። <<እንዴ! ወለላ ምንድነው ነገሩ ? በሰንበሌጥ ይሁን ቃጫ አለቅን'ኮ! . . . ወለላ ሁለት ጠላ ጠማቂዎች በሽልንግ ቀጥረው ጋኑን ፣ ደንበጃኑን ፣ ማጣሪያውን ፣ ነጠላውን ጥድት አስደረጉት ። የየኔታ ጥሩነህ ጭራ ብናኝ ከወዴት እንደሚመጣ አልታወቀም ። ከብርሌ ሁሉ ተሰግስጎ ይታይ ጀመር ። . . . አቶ ታመነ ጠጋ ብሎ <<ወለላዬ ፣ የእኛ ሰው ለምን አይን ተፈጠረብህ ብሎ ነው የሚቀና ። ለምን እርስዎ?>> አላቸው ። << የእጀ-ሰብ ፀላኢ የሚያውቁ ወዳጅ አሉኝ ። ነገ ምሽት . . . ጠጅ-ሣርና አሪቲ ከቤቱ ነስንሰው የእጁን መደጎሚያ ቋጥረው ይጠብቁኝ>> ብሏቸው ወጣ ። . . . በማግስቱ ይማሩ ጉንዶ እና ስልቻ ዙሪያውን እንደ ሲባጎ የየኔታ ጭራ ቋጥሮት ተገኘ ። " የየኔታ ጥሩነህ ጭራ ( ከገጽ 28 - 29) ፦ ሁለተኛ " እትዬ: ማሚቴ: ገብሬ ፤ ዛር: ስላለባት: ሽቱ: ትጠጣለች። እትዬ: ማሚቴን: የሚያውቃት: ሁሉ: በሽቱ: ጠጪነትዋ: ያውቋታል። ጠረኗ: የባህር: ዕጣን: እና: ሉባንጃ: ነው። ሽቱ: ተቀብታ: አታውቅም። << የሰው: እንኳን: ሲሸተኝ: ትንፋሼ: ያበረክትብኛል>> ትላለች። <<ትንፋሼ>> የምትለው: በቀን: የምትቆጥረው ፥ ሃያ: አንድ: ሺህ: አንድ ፥ : የማይጨምር፣ የማይቀንስ: እስትንፋሷ: ነው። እንደ: መጥፎ: ዐመል: አብሯት: የአረጀ: ልማድ: በመሆኑ: ስትቆጥረው: እንኳ: አያስታውቅባትም። ሁለት: አንጎል: የአላት: ይመስል: በአንደኛው: ሃሳብና: ንግግር: ስታካሂድ: በሌላኛው: ትንፋሿን: ትቆጥራለች። እትዬ: ማሚቴ: የሠፈራችን: ትዕንግርት: ነበረች።" የሊባኖስ ሽቱ (ገጽ 87) በተረፈ ጃርሶ ከሸገሯ የወግ እመቤት መዓዛ ብሩ ጋር ያደረገው ቃለምልልስ እጅግ ጠቃሚ ስለሆነ You tube ውስጥ ገብታችሁ እንድትሰሙት እንመክራለን። ይህን መጽሐፍ ለሕትመት እንዲበቃ ያደረጉትን ጋሽ ክብሩንም እጅግ እናመሰግናለን። በዚህ መጽሐፍ መግቢያ ላይ ደራሲው የጨረሳቸው እና በቅርቡ ለሕትመት የሚበቁ የረጅም ልቦለድ መጻሕፍት እንዳሉት ቢጠቅስም ይኸው ዓመታቱ እየነጎዱ ስለሆነ ቢፈጥን ይበጀዋል። ክብረት ይስጥልን የቀበናው ጃርሶ ሞት ባይኖር! The Reviewer is the managing editor of Think Ethiopia © Think Ethiopia
2 8743Loading...
39
ስለጃርሶ (9.4) ርእስ፦ ከደመና በላይ ጸሐፊ፦ ጃርሶ ሞት ባይኖር ኪሩቤል ይዘት፦ አጫጭር ልቦለድ Rating : 9.4 ጃርሶ ሞትባይኖር ኪሩቤል ተወልዶ ያደገው እዚሁ አዲስ አበባ ቀበና አካባቢ ነው። በተለይም "አስኮ ጌታሁን" የተሰኘችው ስምንት አጫጭር ልብ ወለዶችን የያዘችው መፅሐፉ እጅግ ታዋቂ ናት ። በቀድሞው አጠራሩ "የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ" በአሁኑ "ዶቼ ቨለ ራዲዮ" ደግሞ፣ ከ1973 እስከ 1992 ድረስ 44 የ የአጫጭር ልብ ወለድ ታሪኮቹ በራሱ ተራኪነት ለአድማጮች ተላልፈዋል። ከነዚህ ውስጥ ስምንቱ እዚሁ መፅሐፉ ውስጥ ተካተዋል።"የአዲሳባ ልጆች"፣ "ስምንተኛ ዲ"፣ "ጆርዳን" እና የመሳሰሉት ናቸው። በነገራችን ላይ ምትሃታዊ ስነፅሁፍ እና የአፃፃፍ ስልት የምናውቅ አይመስለኝም።ስለምትሃት በደረቁ መፃፍ እንደ ሃሪ ፖተር እና ናርኒያ መሰል ድርሳናት ተምኔታዊ ዓለም በመገንባት ሊከወን ቢችል እንኳ የአፃፃፍ ስልቱን ራሱን ምትሃታዊ ማድረግ ግን የተለየ ክህሎት ይጠይቃል። የጃርሶን አዲሱን ድርሳን ሲያነቡ ቃላቱ ራሳቸው ከወረቀቱ ላይ እየበረሩ ወደ ዓይንዎ ሲሰርፁ ሊታዘቡ ይችላሉ። የጃርሶ አጫጭር ተረኮች ውስጥ ያለው ገፀ ባህርይ በአውሮፓ የሚኖር ሰዓሊ እና ደራሲ ነው። የራሱን ስም በየታሪኮቹ ስንቅር ስለሚዶላቸው እውን ታሪክ ይሁን የልቡናው ውልደት ግራ ያጋባል፣ ምትሃትም አይደል? ለምሳሌ ከሳላሳ ዓመት በፊት ቀበና ወንዝ ስለሚያውቃቸው ሴት ሲያወራ አብረውት አንዱ አውሮፓ ቤተመጻሕፍት የተቀመጡ ይመስላሉ። " በወጣትነት ዘመኔ፤ የስነ-ጽሑፍን አድማስ: እየቃኘሁ፤ በለጋ አዕምሮ፤ በጉጉ: መንፈስ፤ ህይወትን፣ "ልወቅሽ-ታውቂኝ"፤ እያልኩኝ: ስፍጨረጨር፤ ዙሪያዬ: ሁሉ፤ በግጥም: ውበት፣ በቃላት: ኃይል፤ ሊገለፅ: እንዲችል: ብዬ፤ ከሃሳብ፣ ከፊደል: ጋር: ስሟገት: ሳለሁ፤ እቤታችን: ከሚመጡት: የእናቴ: ወዳጆች: አንደኛዋ፤ ስሙኒም፣ ሽልንግም፣ የእህል: ዱቄቱንም፤ እንጀራውንም፤ አስቋጥራ: ከምትሸኛቸው: መሳኪን: አንደኛዋ: "እመት: ደስታ" ይሰኙ: ነበር። "እመት: ደስታን" አይቶ፤ ለሥዕል: የማይመኝ፣ ድም፣ ሰምቶ: "ምን: ይሆን: የህይወታቸው: አይነትና: ጠረን?" ብሎ: የማይመሰጥ: ከያኒ: አይገኝም። እንዲሁ: ሲያዩዋቸው፤ ተመራመሩኝ፣ ፈልጉኝ፣ እሹኝ: የሚል: አይነት: ፊደል: ከላህያቸው: ይነበባል። እኔም: ሆዬ፤ እንኳን: ደርሰውብኝ፤ ፈልጌ፣ አስሼ፣ የምመራመር: አይነት: በለስ: በመሆኔ፤ "እመት-ደስታ" ብዬ: በመሰየም÷ ከግጥም: ወደ: ስድ: ጽሑፍ: ዓምድ: የተሻገርኩበትን፤ የመጀመሪያዬን: ተረክ በአፍላው: እድሜዬ: ጻፍኩኝ። ከረዥሙ: በአጭሩ፤ ቀበና: ወንዝ: ዳር፤ ሀኪም: ሜዳ: ከሚሰኘው: መንደር: በታች፤ ጭቃ: ምርግ፤ አንዲት: ክፍል: ቤት: ተዘግተው: የሚኖሩ፤ አፅመ-ርስታቸውን: ፍርደ-ገምድል: ዳኛ፣ በግፍና: በውሸት: ምስክሮች: ተነጥቀው፣ ራሳቸውን: የሳቱ፤ የተረፈች: ህይወታቸውን፤ ከጨለማ: ክፍላቸው፤ እሳቸው: እራሳቸው፣ አንዴ: ዳኛ፣ አንዴ: ጠበቃ፣ አንዴ: ከሳሽ፣ አንዴ: ተከሳሽ: በመምሰል: ተውኔት፤ የገዛ: ድምፃቸውን ሲያዳምጡ፤ ወፍ: ጪጪ: ጪጪ: የሚልላቸው:ሴት: ነበሩ።" ገፅ 102 ዋናው ገፀባህሪይ ጠልሰም ቢጤ የሆኑትን እና የመሀከለኛው ዘመን የቤተስኪያን ስዕሎችን በየአውሮፓ ከተማ የጥናት ጉባኤ እየተገኘ የሚመረምር ደብተራ ወይ ያፈረሰ ቄስ ይመስላል። ከእነዚህ ከተሞች ሆኖ በናፍቆት ወለድ ቁጭት ስለሀገሩ (ቀበና) ሲፅፍልን ግን ምታት ነገር በየመሃሉ እየከተተ ስልቱን ያለማምደናል። ቃላቶቹ ፍልስፍና ወለድ ስለሆኑም ጭምር ብዙ ያመራምራሉ። " የእመት: ደስታን: ሕይወት: መርምሬ፤ ፅፌ: ያስነበብኳቸው ሁሉ፤ ለጊዜው: በጥልቁ: ነበር: መንፈሳቸው: የተነካው። የመሬትን፣ የርስትን: ነገር፤ ቁጣና: መከራ፣ ጣጣ፣ ግፍን: በደልን: አስታወሳቸው። ይህ: የሆነው፣ ሳይጋነን÷ ከ33፣ከ34: ዓመታት: በፊት ነበር። ጊዜ ተተክቶ፣ ሰባት: ባህር፣ ሦስት: ውቂያኖስ፣ 60ወንዞች: አቋርጩ፤ ብዙ: የብስ: እግሬ: ረግጦ፣ ብዙ: ብዙ: ነገር፤ ሰው: እንደሆነው: ሆኜ፣ አይሆነው: ሆኜ፤ ዛሬ: እዚህ: አካል: ሰውነቴ: ካለበት: እንግሊዝ: ምድር፣ ሎንዶን፤ እንደገና: እመት: ደስታን: አገኘኋቸው። አብሮኝ: የኖረን፤ የልማድ፣ የአመል: ሙያ፤ እንደወትሮው: ሁሉ: ከአንድ: ቤተ-መጻሕፍት: ጥግ: ይዤ፤ ስቸከችክ፤ እመት: ደስታ፤ በቀጥታ: ወደተቀመጥኩበት: መጥተው፤ ካልጠፋ: መቀመጫ፣ ካልጠበበ: ቦታ፤ እየገፋፉኝ፤ ከመደርደሪያው: መጽሐፍ: ለማውጣት: ይታገላሉ። የጸሀፊ: አንጎል: አንዳንዴ፤ ያለፈ: ትውስታውን፤ የሌሊት: ህልሙንና የቀን: የእውኑን: ትእይንት: ስለሚያጠናግር፤ እራሴውኑ: መላልሼ: በመጠየቅ: "እውን: የማየውን: እመት: ደስታን: ነውን? ከሆነስ: እንዴት: ሳያረጁ? ደሞስ: ምንስ፣ ነፋስ: ቢነፍስ: ነው፤ ከቀበና: ወንዝ፣ ከስንት: ባህር: ባሻገር: ከሎንዶን: ምድር: ያሳረፋቸው? ደሞስ: ከ30: ዓመታት: በኋላ: እንደገና፤ ቦታ: እርስት: ብለው፤ ከእኔ: ጋር: መጋፋት: ምን: አመጣው?" እያልኩ: ስጠይቅ፤ እንኳን: የዘንድሮ: አቅለቢስ: ሰው፤ ድሮም: ቢሆን: ሰው: ይመሳሰላል: እና፤ "ድንገት: ተመሳስለውስ: ቢሆን? አማርኛ: ተናጋሪ: በግንባሩ: አይለይም። ፈረንጁም፣ አፍሪካውም፣ ጃማይካውም: የሚናገረው: ነው: ዛሬ....." እንዲህ: እንዲህ: እያልኩኝ: ሳሰለስል፤ ድንገት: ነጠቅ: ብለው: ከአጠገቤ: ሄዱ። አስቤ: ሳልጨርስ፤ ደሞ: ተመልሰው: መጡ፤ እና: ያልጠፋቸውን: መጽሐፍ: ፍለጋ፤ ከንቱ: ይባዝኑ: ጀመር። " ገፅ 103 ጃርሶ ያለ ማብራሪያ የሚጥላቸው አባባሎች አሉት። ለአብነት "ዓለም የወደዳትን ጥሬ ከብስል ታላምን " የሚለውን ፈሊጥ እስካሁን እየተመራመርኩበት ነው፣ በብቃት ላብራራልኝ ወሮታውን እከፍላለሁ። ጃርሶ ከደራሲነቱ ባሻገርም ሠዓሊና የሙዚቃ ባለሙያ ነው። በልጅነቱ የካቶሊክ ኃይማኖት ተከታይ፣ በወጣትነቱ ኢ–ዓማኒ፣ ከ19 76 ዓም ጀምሮ እስካሁን ደግሞ የአይሁድ (Judaism) እምነትን የሚከተለው ጃርሶ፣ የሙዚቃ ሥራውን በአብዛኛው ለመንፈሳዊ ዓላማ እንደሚጠቀምበት ይናገራል። "ከቶ: ምንድነው: ነገሩ? "ፈደለ:ፈጠረ: ነው:: ፊደል:ፍጥረት:ነው። እና: አንድ: ናቸው" ብለው÷ መምህራችን: ጥንት: ያስተማሩኝ: ከአንጎሌ: ደወለ። የሰላሳ: አራት: አመቱ: ፊደል፤ ቀንና: ኮከብ: ቆጥረው: ተመልሰው: ወደእኔው: መጡብኝ: ይሆን?÷ ተነስቼ: ወደ: ውጭ: ወጣ ብዬ: አየር: ተቀብዬ: ስመለስ፤ የሉም። ከተቀመጥኩበት: ወንበር: : ሎሚ: አኑረዋል። ምንድነው: ብልሀቱ? ሎሚዋንም: የሀገርቤት: ሎሚ: እንደሆነች: ጠረኗ: ነገረኝ። እመት: ደስታ: እራሳቸው: ናቸው፣ ሎሚ: ከመዳፋቸው: አይጠፋም: ነበር፤ ትዝ: ይለኛል። እሳቸው: ናቸው! ደንቃራ: እንዳይሆን: ጠረጠርኩኝ። ሎሚዋን: እያሻሸሁ: ሳሸታት: ተመልሰው: መጡ። ይግረምህ: ብለው፤ የባሰውን: ከጉልበቴ: ጋር: ይታሸሹ: ያዙ። ምኞታቸው: ግን: ያሮጊት: አልመስልህ: አለኝ። ከአካሄዳቸውም: የልጃገረድም: አይነት: ነገር: ይመስላል።
2 3621Loading...
....እንጨምር ... "ተባረኪ ችግሩ አላዛር ከታሪክ ዉጭ ሆኖ ነው የሚያየኝ ። እኔ ደግሞ ታሪክ ልስራ እየለፋሁ ነው ። ጊዜዬን ለጭቁን ህዝቦች ነፃ መውጣት መስጠት ነበረብኝ ። ለምወደው ድርጅቴ መስጠት ነበረብኝ “ አዳም ፣ 242 ) :: በመሆኑም አላዛር ለተባረኪ የማይደፍር “ ፈሪ” ወይም የማይገባው “ ደደብ “ ወይም “ ከግል ስሜቱ መውጣት የከበደው ራስ ወዳድ ነው”( መረቅ ፣ 240 ) “ አማን በአዕምሮዬ መጣ :: አላዛር የሆነ ሴታ ሴት መሰለኝ። የሆነ ያልወለደኝ እማማ :: ጡት ባያጠባኝም የሆነ የወለደኝ ምንትስ። የምወደውን ልጅ ስሮጥና ስሸሽ አስታውሼው ፣ ስረጋጋ ፣ በዝምታ በልቤ እንዲህ አልኩት ፣ ማዘሬ ነህ ምንድነህ ?” (መረቅ ፣ 248) ። በላካናውያን እሳቤ ተፈጥሯዊው እውነት ትራውማ ነው እንጂ በትዕምርታዊ እርከን ዉስጥ ያለ ነገር አይደለም :: ለዚህም ነው ፋንታሲ ይህንን ትራውማ ለማከም ለሚደረገውን ጥረት መድረክ ሆኖ ብቅ የሚለው( fantasy is a setup ):: ይህ የእሷ እጣ ፈንታ ብቻ አይደለም ፤ በዘመኑ የነበሩ ወጣቶች ጣጣ ነው፤ ይህም ወጣቶቹ የወል ልቦናን ገንብተው የወል እርካታን ለመገንባትና ለማግኘት የሚዳክሩት ፣ በዢዤክ እሳቤ (Collective jouissance) ዉስጥ የሚታይ ነው :: ስሎቬኒያዊው ስሎቮን ዢዤክ እንዲህ ይላል፦ Nationalism thus becomes ‘the privileged domain of the eruption of enjoyment into the social field.’ The ‘national Cause’ is then cleverly related to Lacan’s concept of ‘the Thing’, which is closely linked with the concept of jouissance; it is itself a materialization of jouissance. እንደውም ብሔርተኝት ፣ ፋሺዝም ፣ ናዚዝምና ሌሎችም በዚህ በ Collective jouissance ውስጥ የሚታዩ ናቸዉ ይላል :: ይህም በረቀቀ መንገድ የሌሎችን ወሲባዊ እርካታን ቀንብበው ለዓላማቸው የሚያውሉ ደስታ ስራቂዎች (ብልጦች) አሉ ይለናል :- "What is at stake in ethnic tensions is always the possession of the national Thing: the ‘other’ wants to steal our enjoyment (by ruining our ‘way of life’) and/or it has access to some secret, perverse enjoyment. In short, what gets on our nerves, what really bothers us about the ‘other,’ is the peculiar way he organizes his enjoyment. In short, what gets on our nerves, what really bothers us about the ‘other,’ is the peculiar way he organizes his enjoyment. ( Slavoj Žižek ፥ 22 ) " ይህንን ሃሳብ በሜሎስ ነቅናቂ እሳቤ እናጠናክረው : “ ወሲብ ትልቅ ጉልበት ነው የወሲብን ስልጣን ወጣቶች ልብ ውስጥ እንይወጣ አድርገህ አምቀህ ለጫጫታ ትጠቀምበታለህ ። በየአቅጣጫው ታፍነውና አንድ የፖለቲካ መውጫ ብቻ ቀዳዳ ካበጀህለት ባሪያ አገኘህ ማለት ነው “ (መረቅ፥162) እዚህ ጋር በተለይ ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ፣ መረቅና የስንብት ቀለማት ረቂቅ በሆኑ የስነ ልቦና ፤ የታሪክ፣ የፖለቲካ ፣ የማህበረሰብ እሳቤዎችና እጅግ በላቀ እና በተዋጣለት ኪነጥበባዊ አለም ውስጥ የተሰሩ ናቸው :: በመሆኑ እነዚህ ብሉይ (Classic ) ስራዎች በላካንያን እሳቤ በዋነኛነት በ " fantasy Structure ፣ desire እና Collective Jouissance " ውስጥ ለመተንተን ሁነኛ ማዕቀፎች መሆን ይችላሉ። ይህም አዳም ረቂቅ ፈላስፋና አሳቢ፣ ጥልቅ አንባቢና የተዋጣለት ደራሲ መሆኑን ከስራዎቹ መረዳት ይቻላል :: *** ይህ ፅሁፍ ይድነቃቸው ሰለሞን (Ph.D) ለኢትዮጲስ ጋዜጣ ፣ ጥቅምት 11 ቀን 2011 ዓ.ም በወጣው ፅሁፍ ገፋፊነት ምክንያት የተፃፈ ነው ። በዚህም የእሱ ፅሁፍ የተሳሳታቸውን ወሳኝ ጉዳዮች ለማረም ያለመ ነው። ለዚህም ሲባል የእሱን ቴክስቶች (ከመረቅ የወሰዳቸውን ተጠቅሜያለሁ) ለንፅፅር እዲመች :: ለተጨማሪ ንባብ ምክንያት ስለሆንከኝ ምስጋና ይድረስህ :: © Teshale Kebede Bedriya
Mostrar todo...
👍 3
የላካኒያን ሳይኮአናሊሲስ እና መረቅ *** በእርግጥ "መረቅ " በኪነ ጥበብ ምትሃት ፣ በእሳቤ ጥራትና በፍልስፍናው ጥልቀት በከባዱ የሚያነቃንቅ ብሉይ ስራ ነው። እውቁ ፈረንሳዊው የሳይኮአናሊሲስ ጠበብት ዣክ ላካን፣ ሳይኮአናሊሲስ ላይ ትልቅ ተፅዕኖ የፈጠረ ፈላስፋ ነው። ፍሩድን በጥልቀት ያጠናና በስራዎቹም ሥነ - ፅሁፍን ፣ ፊልም ፣ ፖለቲካና በማህበረሰብ ጥናት ላይ ተጽዕኖውን ማሳረፍ የቻለ አሳቢ ነው። እንደ ላካን እሳቤ "ሰው '' በዋናነት የህይውት ዘይቤው የተበጀውና መንገዱን የተቀየሰለት ቋንቋን መጠቀም ከጀመረበት ቅፅበት ጀምሮ በሚገነባው ኢ-ንቁ የአዕምሮው ክፍል ነው :: ይህም “Unconscious mind is structured like a language” ይላል። የላካንያን ኢንቁ ቋንቋ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ትዕምርቶችና መዋቅሮች ማከናወኛ (ሚዲየም፣ ስቴጅ ) ጭምር ነው። በዋናነት አንድ ህፃናን ከተወለደ በኋላ ራሱን የሚያውቀው በእናቱ ጡት አማካይነት ነው። በዚህ ጊዜ ጨቅላው እራሱን መለየት አይችልም፤ ይልቁን ፍፁም እርሱነቱንና አካባቢውን ማገናዘብ ባልቻለበትና እራሱን በእናቱ የመስለባቸውን ደረጃዎች ያልፋል :: ጨቅላው ከእናቱ ጡት እንደተነጠል ( ከ6 እስከ 18 ወራት ያለውን ጊዜ ይሸፍናል) የእኔነት ምስሉን መቅረጽ ይጀምራል። የእናቱ አንድ አካል እንዳልሆነም ይረዳል። ይህን ego form የሚያደርግበት እርከን ላካን Imaginary order ሲል ሰይሞታል። ይህን imaginary order በማለፍ በትዕምርትና በቋንቋ ወደተዋቀረው ስርዓት ውስጥ የሚገባው ጨቅላው እናቱም ብትሆን ከሙሉ እሱነቱ የተነጠለች (M)Other እንደሆነች ይረዳል። ሕጻኑም የደስታና የእርካታ ምንጩን ትቶ በማህበረሰቡ አስቀድሞ ወደተሰሩት ፍላጎቶች ፊቱን ያዞራል። (unreplaceable lack ) በሌላ አገላለጽ ህፃኑ ተፈጥሯዊ ፍላጎቱ ፋንታሲ ወደ ፋንታሲ ሽግግር ያደርጋል :: በዚህም ህጻኑ ከተፈጥሯዊ እሱነቱ ወጥቶ በቋንቋና በትምዕርት ወደ ተዋቀረው ስርዓት ውስጥ ይገባል። ይህንን የቋንቋ ስርዓት በአርስቶትል አባባል ... “Automation:-Signifiers of the signifiers) ነው። ይህም ተፈጥሮኣዊ እሱነቱና እርካታውን ሙሉ በሙሉ የሚያጣበትና የሌሎች ፍላጎት (desires of the Other) ለተፈጥሯዊው ፍላጎቱ አማራጭ ሆኖ የሚመጣበት ነው ። ስለዚህ የላካንያን ሳይኮአናሊሲስ መሰረት የሆኑት ሶስቱ እርከኖች ማለትም Imaginary፣ Symbolic እና Real order፣ ለትዕምርታዊ ዓለም ተገዢ ይሆናሉ፡፡ በዚህም ተፈጥራዊ እውነት (real ) ሙሉ በሙሉ በቋንቋ ስለ ማይወከል ከቋንቋ ውጪ ይሆናሉ ፤ ይህንን ለካን ( Symbolic castration) ይለዋላል :: በዚህ በቋንቋ የሚመራው ግለሰብ እነዚህን ጉዳዮች በሌላ ማህበሰባዊ እውነታ (social reality) ይተካሉ :: ስለዚህም ተፈጥራዊው እውነት እና እርካታው (enjoyment) ፣ ስነ-ልቦናዊ ምስቅልቅሎሽ ( trauma) በመሆን ወደሌላ ምናባዊ አለም ወይም ፋንታሲ ሽግግር (transference) ያደርጋሉ። በዚህም ተፈጥራዊ እውነታ እና እርካታ ፋንታሲ ውስጥ ይገባሉ :: በዚህም መሰረት መረቅን በላካን ለማንበብ የተደረገውን ጥረት እንይ ፦ "ከሁሉ ለመሸሽ የምችል ዓይነት ወደ አማን ደረት ተጣበቅሁ ። አማን ጓደኛዬ ነው ፣ ጓደኛዬ ነበር፣ እና ምን አለበት? አይኖቼን ገርበብ አድርጌ አላዛርን አስባለሁ። አላዛር አ አይኖቹን ጨፍኖ እየተልቆሰቆሰ ሲያቅፈኝ። በፀሃያማ ቀን በቀስታ ታኮኝ ሲቆም ። በሃሳቤ እዛና እዛ ስቀባዥር አማን አናቴን ሲስመኝ ሰማሁት :: አላዛርን ማለም አቆምኩ :: ግራ በመጋባት ምልክት ቀና ብዬ አየሁት :: ቀና ብዬ እያየሁት ሳለሁ ሳልጠብቀው አፌ ላይ ሙሉ በሙሉ ሳመኝ ። በፍጥነት ከእቅፉ ተላቀቅሁና ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ቆም ብዬ ጃኬቴንና ሱሪዬ አስተካከልኩ። “ የት ነው? “አለኝ “ቤት ለመሄድ ነበር “ተራዬ እንዳልሆነ አውቃለሁ ” መኪና የለም ::ትንሽ ረጋ በይ :: ተራሽ ገና ነው” የምመልሰው አልነበረኝም ..... ይህ ሁነት በመጋቢት 1969 ተባረኪ የወጣቶች ሊግ ሰላማዊ ሰልፍ በተደረገበት ሌሊት ነው። በመጀመሪያ ተባረኪ ሰላማዊ ሰልፉን ለመሳተፍ ፈርታ ስታመነታ ነበር ። ሆኖም ፍራቻዋን ለትግል አጋሯ አማን (የእሷም ፣ የአላዘርም አብሮ አደግ) በቁንጽል ወይም በዝርዝር አትነግረውም፡፡ “ ፈሪው ወዳጄ አላዛር በልቤ ጥርጣሬ አስገብቶ ሳይሆን ይቀራል ፤ ለአማን ልነግረው አልደፈርኩም ። ግን ደግሞ የጠላቴን አይን እያየሁ ግንባሩ ላይ መጮህ እፈልጋለሁ ...” (መረቅ ፥ 246።) ከትዕምርታዊ ስርዓት ይልቅ ፣ ነገሩን በቀጥታ ለማየት ከፈለግን ተፈጥሯዊው ፍላጎት እንደሆነ እንረዳለን ። ነገር ግን ይህ ተፈጥሯዊ ፍላጎት ለማግኘት ለአማን የሚቻል አይደለም ፤ ይህም የአማን ፍላጎት ወደ ፋንታሲ ውስጥ ተሻጋሪ ይሆናል ። በመሆኑም አማን ተባረኪ የዓላዛር ፍቅረኛ መሆኗ እያወቀ እሷን ከመመኘት አላገደውም፤ ይህም ተፈጥሯዊ ፍላጐቱ ለማርካት የነበረውን ማንኛውም አጋጣሚ ከመሞከር ወደኋላ አላለም ፤ ይህም ተባረኪ በአማን አዕምሮ ውስጥ የምትንሳፈፍ ለተፈጥሮኣዊ ፍላጎቱ መልስ ሰጪ ናትና ። እዚህ ጋር የስሎቮን ዢዤክን ሀሳብ ላምጣ ፦ "For a Man ,the relationship with a women is possible only in as much as she fits his formula " ይላል :: ለዚህም አካላዊ ባይሆንም በፖለቲካው መድረክ የነበራቸው ግንኙነት ለዚህ ወሲባዊ ፍላጎት ልዋጭ ሆኖ መቅረቡን እናያለን። እንዲህ ትላለች ቴቤ ፦ " ....አማንን ሩካቤ ስጋ እምቢ ብላውም ባማረ መልክ በፖለቲካ ተራክበናል። እኔ እንደማልረሳው እሱም አይረሳኝም " ትላለች (መረቅ፥293 )። ..ሌላ እንጥቀስ ... ” የስላማዊ ሰልፉ ማግስት በመሽሽ ላይ እያለሁ ፣ ትዝ ያለኝ ብቸኛ እናቴና አላዛር ነበሩ። ለብቻዬ በኮሮኮንች ላይ እየተወለካከፍኩ ስሮጥ የከበበኝ ጨለማ ማሃል የታወሱኝ እማማና አላዛር ነበሩ። ፍቅር ከዋናው አላማዬ በላይ የሚንሳፈፍ ጉድ የለዉም (መረቅ ፥ 246)” እዚህ ጋር ተባረኪ ፣ እናቷና ዓላዛር ተያይዘው የመጡት ሁለቱም ለተፈጥሯዊ ፍላጎቷ መገኛ ቢሆኑም የነበረችው በትርክት ውስጥ ስለሆነ አታገኛቸውም ። ምክንያቱም ትዕምርታዊ አለም ተፈጥሮኣዊ እዉነት (real ) እርካታ ( jouissance) በቋንቋ አይወከሉም ፤ ይህም እንዴት ወደ ፋንታሲ ሽግግር እንደሚደርግ ከላይ አይተናል ። ይህንን ክፍተት በፋንታሲ ከተያዘ በኋላ ለሌሎች ፍላጐት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ፤ በዘመኑ የነበረው ፋንታሲ ውስጥ መጫወት የሚችል ርዕዮት ዓለም ደግሞ ማርክሲዝምና ሌኒንዝም ነው፡ ፡ በመሆኑም የማርክስ ርዕዮት ዓለም የእናቷና የዓላዛር ተቀናቃኝ ሆኖ ይመጣል ። ዢዤክ እንደሚለው (fantasy is narative) ፋንታሲ ትርክት በመሆኑ በወቅቱ የነበረው የማርክሲስም ርዕዮተ አለም አዕምሮዋን መቆጣጠር መቻሉና አዕምሮዋ ውስጥ ያለዉ የፋንታሲ መዋቅር ወዲህ በእናቷና ዓላዛር እሳቤ ወዲያ በርዕዮተ ዓለሙ ለሁለት ተከፍሎ እናያለን።
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
ለክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሐነ ትንሳዔው አደረሳችሁ። በዓሉ የሠለም፣ የጤና፣ የፍቅር እንዲሆን ከመጻሕፍት ዓለም - Book Shelf ይመኛል።
Mostrar todo...
👍 5
ትዝ ይላቹሀል? Phsyics እና Maths ላይ የነበሩ solve አርጉ ምንባላቸው problems? እና ደሞ እነዛ የMaths ረዣዥም equations? The value of 'x' ፍለጋ ብዙ ወረቀት እኮ ነው የጨረስነው። አንድ መስመር ጥያቄ ተሰጥቶን 2 ባዶ ወረቀት ለመልስ ሲያስከትሉልን የነበረው ጭንቀት አረሳውም። ከelementary እስከ ዩኒቨርሲቲ maths በጣም ከባድ ትምህርት ነው። ብዙ ለፍተን . .አጥንተን ነው የምንሰራው። ነገ Maths ነው ፈተናው ሲባል ሌሊቱ ይለያል. .እንቅልፍ አይታሰብም ነበር። ዛሬ ላይ ሆኜ ያን ሁሉ ትግል ሳስብ ቆጨኝ። ያን ሁሉ አቅሜን ያዋልኩበት ልፋት አሁን ላይ ትምህርት ጨርሼ ህይወትን ለብቻዬ ስጋፈጣት ምንም ጥቅሙ አልታይ አለኝ። ዛሬ ህይወት በብዙ አቅጣጫ ትፈትናለች። The value of 'X'ን ስለመፈለግ ያን ሁሉ ከምንማር አሁን ለሚገጥሙን ፈተናዎች መፍትሄ ፍለጋ ብንማር ምን ነበረበት? እንዲሁ በምኞት ሀሳብ ስሞላ እነዛን በስንት ጥረት የሸመደድኳቸውን equations ተጠቅሜ የአሁን ውጣውረዴን መፍታት ያምረኛል። በነዛ word problems ውስጥ ዛሬ የሚገጥመኝ የህይወት እንቅፋት ተተንትኖ ከነ አሰራሩ ተፅፎበት በነበር ብዬ እጓጓለሁ። አሁን የሚገጥመን የሴትነት ፈተና ፣ የትዳር ችግር ፣ ድብርት ፣ ብቸኝነት ፣ አምኖ መካድ ፣ የልብ ስብራት ፣ ስራ ማጣት ፣ ራስን መጥላት በየትኛው equation ነው solve ሚደረገው? እኚህን ቻሌንጆች በየትኛው የትምህርት ክፍለ ጊዜ ነው የተማርነው? አልተማርንም! ዛሬ ብዙ የህይወት ገፃችንን ቢወስድም ለትምህርት የሰጠነውን ያህል ቦታ ተሰጥቶት ግን አላወቅነውም። ትምህርት አያስፈልግም አልልም። ነገር ግን ያን ያህል ሁሉን ረስተን አቅማችንን invest ልናደርግበት አይገባም። አሁን ባለንበት ሁኔታ የተማርነው እውቀት አብዛኛው የሚጠፋ ነው። የሚቀረውን ደሞ ለሆነ ድርጅት ግብዐት ሆነን በመስራት ብንጠቀመው ነው (እሱም ከተገኘ)። ከስራ ውጪ ግን ብዙውን የህይወት መንገዳችንን ሚይዝ ከተለያዩ ሰዎች ጋ መኖር ፣ ትዳር ፣ እናትነት ፣ አባትነት አለ። ቀላል አይደሉም....እስክንኖርባቸው አዲስ ናቸው። ማወቅ ፣ መዘጋጀት ፣ መጠንከር አለብን። ሁሌ ደሞ አልጋ በአልጋ አይሆኑም ማጣት ፣ መውደቅ ፣ መሰበር ይኖራቸዋል. .ለዚህስ ከማደጋችን ጋ ሚመጣ እውቀት መኖር የለበትም? ስንት ልጅ ነው ደህና ወላጅ ኖሮት እንዲህ አይነት ስለ ህይወት ትምህርት የሚያገኘው? . .አላውቅም! ግን በቃ ትምህርት የሰጠነው እድሜ አይገባውም። እሱ ላይ ብቻ መደገፍ የለብንም. .አላማችን ሊሆን አይገባም። ከልጅነት ጀምሮ ከትምህርት ጎን ለጎን ራሳችንን ምንሰራበት ህይወት ሊኖረን ይገባል። ውስጣችን ያለውን አቅም ፣ የተፈጠርንለትን አላማ ነው ማጠንከር ያለብን። እንጂማ ትምህርት ብቸኛ መንገዳችን ከሆነ 12 ላይ ወይም ዩኒቨርሲቲ ላይ ሲያልቅ ራሳችንን በማጣት እንጎዳለን። ወዴት እንደምንሄድ ሲጠፋን...ህይወታችንን በምን ማስቀጠል እንደምንችል ግራ ሲገባን አጉል አወዳደቅ እንወድቃለን። ማንፈልገውን ትምህርት በብዙ ፈተና ተምረን. .የሚገባን ቀርቶ የሚያኖረንን ስራ እንኳን ስናጣ አናሳዝንም? ለመኖር ፣ ላለመወቀስ ፣ ላለመውደቅ ብለን እንደገና ማንፈልገው ፣ ሰው ያሰመረልን መንገድ ላይ መሄድ ደሞ ይታክታል። ስለ ነገኣቹ . .ስለ ህይወታቹ አስቡ. .አላማችሁን ለዩና እሱን ዋና መንገዳቹ አድርጉት. .ራሳቹ ላይ ስሩ! ስኬት በትምህርት ብቻ አይደለም! © Nejat Hussen
Mostrar todo...
👍 3 2
ያለፈውን ታሪክ፣ የማህበረሰቡን ዕሴትና ዕውቀት በጭፍን ማጥላላትና መናቅ የመሰልጠን መንገድ አድርገን እየሄድንበት ያለው መንገድ ቆም ብለን ለመረዳት እንኳ ጊዜ ያለን አይመስልም፡፡ የማጥላላት ዘመቻውም የሚያጋፍረው መድረኩን የያዘው ዘመንኩ ወይም ተማርኩ ባዩ ነው፡፡ ፈላስፋው Valentin Mudimbe ከላይ በጠቀስኩት መጽሃፉ እንዳሰፈረው፣ ከ1950ዎቹ ጀምሮ ቢያንስ ነጭ ቅኝገዥዎች የአፍሪካን መሬት ለቀው ቢወጡም በእነሱ ቦታ "ጥቁር ቅኝገዥዎች" ወይም ልሂቃን ተተክቷል፡፡ በምዕራቡ ዓለም የቅኝግዛታዊ ዲስኮርስና ዕውቀት ተኮትኩተው ያደጉት አፍሪካውያን ቀድሞ ቅኝ ገዢዎች ሲከውኑት የነበረውን ነገር በአንድም ሆነ በሌላ አቅጣጫ ቀጠለ እንጂ አልተቋረጠም፡፡ ነጭ ቅኝ ገዥዎች የተኩት አፍሪካውያን የፖለቲካ ልሂቃን ከምዕራቡ ዓለም ሥርዓት ወይም ተቋማት ጋር ያላቸው ግንኙነት የጌታና የሎሌ ወይም የጥገኝነት እንዲሆን ያደረገውም ይኸው የቅኝአገዛዝ ሌጋሲ ነው፤" …colonialism should have produced a body of knowledge on the means of exploting dependencies." በሃገራችን ኢትዮጵያም የሆነውና እየሆነ ያለው ይኸው የቅኝ አገዛዝ ማዕከላዊ እሳቤ ከትምህርት ስርዓታችን አንስቶ እስከ ፖለቲካዊ መድረኮች ተሞልቷል፡፡ እውቀት ከሌሎች ሃገራት ተፈልጎ የሚመጣ እንጂ ከራሳችን አንጥረን ማውጣት እንደምንችል ሊገለጥልን እንዳልቻለ የምዕተ-ዓመት ጉዟችን ምስክር ነው፡፡ አዳምም ይህንን በደመነፍስ የሚደረግ ጉዞ አጥብቆ ይተቻል፡፡ "የኢትዮጵያ ምሁራን ሲሰለጥኑና ዘሮቻቸውን ሊያሰለጥኑ ሲፈልጉ መጽሃፎች ይጽፋሉ፡፡ በነዚህ መጽሃፎች ውስጥ የሚጠይቁት አንድ ዋነኛ ጥያቄ እኔ ምን አለኝ? ሳይሆን እነሱ ምን አላቸው? ነው አሉ፡፡ …ካላመናችሁ ጃፓን እንደምን ሰለጠነችን አንብቡ፡፡" (785) ፕ/ር ማዕምር መናሰማይ "A Critical Dialogue between Fifteen and Twenty first Century Ethiopia"በተሰኘው ጥናታቸው ያለፉትን ሶስት የመንግስት ስርዓቶችን (አጼ ኃይለ ሥላሴ፣ ደርግና ኢህአዴግ)ኢትዮጵያን ለማዘመን የሄዱበት መንገድና ዘይቤ "ፍዝዝመና" (passive modernization) ሲሉ ሰይመውታል፡፡ ይህም ማለት በልማት ስም ምዕራባዊ ለመምሰል መሞከር፣ በምዕራቡ ዕውቀትና ሥነ-ዘዴ ላይ በመመስረት ልማት ለማምጣት ያደረጉትን ያልተሳካ ሙከራ ነው ፍዝ ዝመና ብለው የጠሩት።፡ ይህ ፍዝ ዝመና ሃገር በቀል ዕውቀቶችን፣ እሴቶችን፣ እይታዎችንና ባህሎችንና ተቋማትን አፈራርሶ በምዕራቡ እሳቤ የመተካት ሙከራ ነው ይላሉ። የዚህ ውጤትም በሃገሪቱ ውስጥ መልከ-ብዙ ቀውስና ምስቅልቅሎሾችን አስከትሏል፡፡ "…the failure of modernization in Ethiopia is also the failure of knowledge: of Ethiopia and of modernization." አዳም ረታ በ'እቴሜቴ ሎሚ ሽታ' በሰዓሊና በሃያሲ መስኮት ገረሱ በኩል የዘመኑን ሁኔታ እንዲተነትን፣ እንዲተችና እንዲተረጉም አጭቶታል፡፡ መስኮት በተለይ ፈረንጅ ያልነካው ወይም 'ያልባረከው' ነገር ፋይዳ ቢስ ለሚያደርጉና የፈረንጅ እውቀት የሁሉም ነገር መመዘኛ አድርገው ለተቀበሉ የዘመኑ ወጣቶችን በየጋዜጣው ይተቻል፡፡ ሃገር በቀል እሴቶቻችንም ወደ መድረኩ ይመልሳቸዋል፣ ይተነትናቸዋል፣ አንዳች እውነት ፈልቅቆ ለማውጣት ይተጋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ መስኮት አስቀድሞ ይከተለው የነበረው የ"አብስትራክት ኤክስፕረሺንንዝም" የአሳሳል ዘይቤ በመተው፣ የሃገር በቀል ዕውቀትና experience መሰረት ያደረገ "ተነካናኪ" ወይም "ቅርባዊነት" የተሰኘ የአሳሳል ዘይቤ ፈጥሯል፡፡ ክፍለ ዘመን የተሸገረው የተቃወሰው ጉዟችን ዳግም መታደስ የሚችለው፤ ከራሳችን ጋር እርቅ አውርደን ነጋችንን ለማሳመር የመስኮት ገረሱን ፈለግ ከመከተል የተሻለ ሌላ ምን ምርጫ ሊኖረን ይችላል?! © Teshale Kebede Bedriya
Mostrar todo...
👍 7
አዳም ረታ እንደ postcolonial ፈላስፋ **** "…ቅኝ አልተገዛንም ብለው ጉራ እየነፉ በየቀኑ ግን የተገዥነት አገልግሎት ይሰጣሉ" (የስንብት ቀለማት፣24) አዳም ረታ በተለይ ኋላ ላይ ባሳተማቸው 'እቴሜቴ የሎሚ ሽታ' እና 'የስንብት ቀለማት' ውስጥ የ-postcolonialism ፍልስፍናዊ እሳቤዎችን ጎልቶ ይንጸባረቅባቸዋል፡፡ አድዋ ላይ ቅኝ ገዥዎችን ድል አድርገን መልሰናል የሚለው ኩራታችን አፋዊ እንጂ ከልብ የመነጨ እንዳልሆነ በላቀ ኪናዊ ውበትና ጥልቅ መረዳቱን ገልጦ አስነብቦናል፡፡ ነጻነታችንን እና የስልጣኔ አሻራዎቻችን እንደልቃቂት አውጥተን ጥለን ፈረንጅ ለመምሰል የተጋጋጥንባቸው የሕማም ዓመታት እንደገና እንድናጤናቸው በድርሰቶቹ ብዙ ገስጾናል፡፡ እኛ ግን ከራሳችን ጋር መታረቅ ተስኖን እዚያው'ጋ ነን… እንደመነሻ፣ ከድህረ-አድዋ በኋላ እንደወረደ ተቀብለን ከተጋትናቸው ጉዳዮች መካከል እውቅት፣ ስልጣኔ፣ የተቋማት ግንባታ፣ ቁሳዊ ልማት፣ ርዕዮታዊ መረዳት…ከውጭ ሃገር እንደሸቀጥ አምጥቶ በየቦታው የሚከፋፈል አድርጎ የመረዳት ሥሁት ግንዛቤ አንዱ ነው፡፡ ይህንን መነሻ በማድረግ እውቀት በተውሶ ለማምጣት ከአንዱ ሃገር ወደ ሌላ ሀገር ስንዞር አንድ አንድ ክፍለዘመን ተሻገርን፡፡ በሃገር ውስጥ በፈረንጅ አፍ እያወራን በስልጣኔ ብርሃን ለመጥለቅለቅ በሚል የቋንቋ ትምህርት ቤቶች ከፈትን፡፡ "የአውሮፓ የስልጣኔ መንገድ" በመከተል ካለንበት 'ጨለማ ወጥተን' ልክ እንደ'ሰለጠኑት' ሃገራት በ'ብርሃን' መንገድ ለመጓዝ በሚል እዚህም እዚያም ባጀን፡፡ ኋላ ላይ የመጡት መንግስታትና የፖለቲካ ልሂቃንም አንዴ ሶሻሊዝም ሌላ ጊዜ የልማታዊ መንግስት ሞዴል አምጥተው ለመተግበር ሞከሩ፡፡ ሙከራው ግን ከቀውስ ወደ ቀውስ ከመሸጋገር ያለፈ አንድ ስንዝር እንኳ ፈቅ እንድንል አላገዘንም፡፡ለምን?... አዳም ይህንን የህማም ጉዟችንን እንደ ከያኒ ሥነውበታዊ ፍኖቱን ሳይለቅ፤ እንደ አሳቢ ደግሞ ከሥነዕውቀታዊ ከፍታው ሳይወርድ ገልጦ ያሳየናል፡፡ ታመን እንዳልታመምን በማስመሰል የመጣንበትን ሥሁት መንገድ ዳግም እንድናጤነው ይወተውተናል፡፡ ከህማማችን የምንፈወስበት መውጫ መንገዱን ጭምር ይጠቁመናል፡፡ እዚህ'ጋ ለማስታወስ ያህል postcolonialism የቁም ፍቺው እንደሚያመለክተው ከ-colonialism ቀጥሎ የሚመጣ ሥርዓት ሳይሆን፣ የኮሎኒያሊዝም ሌጋሲዎችን በተዘዋዋሪ መንገድ በድህረ ቅኝ ግዛት የቀጠሉ መሆኑንና ይህም በሃገሬው ነባር ባህል፣ ዕውቀት፣ እሴት፣ ማህበራዊ መስተጋብር…ላይ ከፍተኛ ተቃርኖ እንደፈጠረ የሚያትት ዕሳቤ ነው፡፡ አፍሪካዊው ፈላስፋ Valentin Mudimbe 'The Invention of Africa' በተሰኘው መጽሃፉ እንዳሰፈረው፣Colonialism ማለት ቅኝገዥዎች የቅኝ ተገዥውን ሃገርና ማህበረሰብ በሃይል በመቆጣጠር አንድም የተፈጥሮ ሃብቱን አሟጦ ወደ ምዕራቡ ዓለም የመላክ ሲሆን፣ ይህንን ብዝበዛ ቀጣይነት እንዲኖረው ደግሞ የቅኝተገዥው ማህበረሰብ ማንነታዊ መሰረት እንደገና የማዋቀርና የመቅረጽ ስራ ይሰራል፡፡ በሌላ በኩል ማንነትን እንደገና የመበየንና የመቅረጽ ሂደት የስልጣን ተዋረዱ ሳይዛነፍ እንዲቀጥል፣ ቅኝ ተገዥዎች በዚህ የሃይል ተዋረድ ቦታቸው የተገዥነትና ጥገኝነት መሆኑን በሥነዕውቀታዊ፣ በተረክና በሌሎችም ይስሙላ ሳይንሳዊ ምርምሮቻቸው ላይ እውነታነት እንዳለው የሚያትት ዕሳቤ ነው፡፡ ህንዳዊቷ ፕ/ር Ania Loomba ታዲያ 'Colonialism/ Postcolonialism' በተሰኘው መጽሃፏ ይህንን የቅኝ ግዛታዊ ዲስኮርስና ተረክ ከስር መሰረቱ መረዳትና ይኸ ተረክ በድህረ-ቅኝግዛት ዘመንም እንዴት እንደቀጠለ ማወቅ እጅግ አስፈላጊ ነው ትላለች፡፡ ቅኝአገዛዝ በታሪክ ሁለትዮሻዊ ተቃርኖ (binary opposition) በመፍጠር አደገኛና ውስብስብ ተረኮችን ፈጥሯል፡፡ አውሮፓን ወይም ምእራቡ ዓለም "እኛ" በሚለው ጎራ ውስጥ በማስገባት "ከምዕራቡ ዓለም ውጪ ያለውን ማህበረሰብ ደግሞ "ሌሎች" (others) በሚለው ጎራ መድቧቸዋል፡፡ ይህን የሁለትዮሻዊ ዓለም (west-east) ተረክ አውሮፓውያን ለራሳቸው ያላቸውን ምስልና ከአውሮፓ ውጭ ባሉ ሕዝቦች መካከል አለ የሚሉትን የልዩነት መስመር ለማስመር ጉልህ ሚና ተጫውቷል፡፡ ለአብነትም አውሮፓውያን "የሰለጠኑ"፣ በ"አመክንዮ ታግዘው ማሰብ የሚችሉ"ና ዕውቀታቸው ለሌሎችም "አርዓያ መሆን የሚችል" አድርገው ሲቀርጹት፤ በአንጻሩ ከአውሮፓ ውጪ ያለው ማህበረሰብ ደግሞ "ያልሰለጠነ"፣ ስሜቱን "መግራት ያልቻለ" አድርገው ፈርጀውታል፡፡ እንዲሁም ነባር ባህሉንና እሴቱን እድገትና ለውጥ ለማምጣት የ"ማያስችል" አድርገው በይስሙላ ሳይንሳዊ ጥናቶቻቸው ጭምር አስደግፈው ለማሳመን ችሏል፡፡ ታዲያ ከ19ኛው ክ/ዘ አንስቶ እየኖርንባት ያለችው ይህች ዓለም በዚህ ቅኝት ነው የተበጃጀችው፡፡ ቅኝአገዛዝ "አበቃ" ቢባልም መልኩን በመቀየር ከአውሮፓ ውጭ ባሉ ሃገራት የትምህርት ስርዓት፣ የመንግስት አወቃቀር፣ የባህል ዘርፍ…ውስጥ ሰርጾ በመግባት ህልውናውን ማስቀጠል ችሏል፡፡ የ-postcolonial አሳብያንና ስራዎቻቸውም ከትናንት የተሻገሩ የቅኝገዥዎች ሌጋሲዎቻቸውን በዛሬው አስተሳሰባችን፣ የህይወት ዘይቤያችንና ተቋሞቻችን ውስጥ እንዴት ተተግባሪ እንደሚሆኑ ያሳዩናል፡፡ አዳም ልክ እንደ postcolonial ፈላስፎች፣ ቅኝ ገዥዎች ሃገራችንን በሃይል ወርረው በመያዝ ለዓመታት ባይቆዩም፣ ቅኝግዛታዊ አስተሳሰባቸውን፣ የህይወት ዘይቤያቸውን፣ የአገዛዝ ስልታቸውንና ዕቅዳቸውን አውቀንም ይሁን ሳናውቅ ተቀብለን እየተገበርነውና እየኖርነው እንዳለ ከመጣንበት የትናንትናው መንገድ ሰበዞችን እየመዘዘ ይወቅሰናል፡፡ "ባዴ [ፈረንጅ] የተለየ ብሩህ አይደለም ብለው የነዘነዙኝ በባዴ ቅኝ ገዥዎች ራሳቸውን እንዲጠሉ ጥልቅ ትምህርት የወሰዱና ዛሬም ከእነሱ እግር ስር የማይጠፉ ወገናቸውን ባዴ በቀደደላቸው መንገድ የሚቀረቅቡ ነጋዴዎች ናቸው፡፡" (ስ.ቀ፣ 23)-ይህን የተባሉት ራሱን የ"ወርቃማው ትውልድ" ወይም የ"ያ ትውልድ" አባላት ነው ለሚሉት አብዮተኞች የተሰነዘረች ትችት ነች፡፡ ትልቁ አሳቢና ሳይካትሪስት ፍራንዝ ፋኖን 'Black Skin White Mask' በተሰኘው መጽሃፉ የጥቁሮች የበታችነት ሥሜት (Inferiority complex) ምንጩ የ" Colonial discourse" ነው ይላል፤ "…colonialism not only exploits but dehumanize and objectifies the colonized subject." ፋኖን የቅኝ ግዛታዊ ዲስኮርስ በቅኝ ገዢው ግለሰብ ሥነ-ልቦና ውስጥ እንዲሰርጽ ያደረገበት መንገድ ደግሞ ግለሰቡ የወጣበትን ማህበረሰብ ታሪኩን፣ ማህበራዊ እሴቱን ዋጋ በማሳጣትና በማጥፋት በማጥፋት ከትውስታው ማህደር እንዲፋቅ በማድረግ በምትኩ የነጭ የበላይነት ተፈጥሮኣዊ አድርጎ የሚቀበልና እሱን ለመምሰል የሚሞክር ግለሰብ ሆኗል ይለናል፡፡ "…የአገራችንን መልካም ታሪክ እንጥቀስ ስንል ዐይኖቻቸው ቀልተው 'the past is a foreign country' (ያለፈው ዘመን ባዕድ አገር ነው) ይሉናል፡፡…የነጭና የጥቁር ተራቾች ግን ታሪክ አስፈላጊ አይደለም……ያውም ደብተራ የዘባረቀው ብለው ለምን የታሪክ ምሁር እንደሆኑ ግን አይነግሩንም፡፡…የባዕድ ደብተራ የጻፈውን ግን ያምኑታል፡፡"(ስ.ቀ፣ 23)
Mostrar todo...
👍 4

👍 6 1