cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

"ስለመጻሕፍት ከመጻሕፍት መንደር እንዘምራለን!"

Mostrar más
Advertising posts
16 181Suscriptores
+2124 hours
+837 days
+26530 days

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ይኼን ፊደል አትናቀው! ተዋነይ ቅኔ ዘርፎበታል! ሔኖክ የግዜ ቆጠራ ጥበቡን አስፍሮበታል! እልፍ መጽሀፍት ተጽፈውበታል! ይኼን ፊደል አትናቀው። ይህ ፊደልኮ ቢያንስ የ4,500 አመት እድሜ ባለጸጋ ነው። ሌላው ሌላው ቢቀር እንኳን እድሜው እንድታከብረው ያስገድድሃል። እንግሊዝ የራሱ ፊደል የለውም። ሀያ ስድስት ፊደላትን ከላቲን አስር ቁጥሮችን ከህንድ ተውሶ ይጠቀማል። ለአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ግን ግእዝ አባታችን ነው። ግዕዝ የተውሶ አይደለም። ግዕዝ የራሳችን ነው። ግእዝ የላቲን ፊደል የሌሉት ብዙ ጠቃሚ እሴቶች አሉት። ለምሳሌ እንግሊዝኛ በግዕዝ ፊደል መጻፍ ቢጀምር ከcapitalization, spelling and pronunciation ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ሁሉ ይቀላሉ። የግዕዝ ፊደል አይደለም ለሀገር በቀል ቋንቋዎች ለባእዱም ምቹ እና ተስማሚ ነው። እንግሊዝ ታዲያ ብልጥ ነው ፤ ይሉኝታ ቢስ ነው። ዛሬ በዩኒቨርስቲዎቻቸው ውስጥ እያስተማሩበት ነው። ነገስ? ከነገወዲያስ? እኛ የነሱን ብልጭልጭ ለማግበስበስ ቤታችንን ጥለን ሄደናል። ባለቤት የሌለው ቤት ደግሞ ለሌባ ምቹ ነው።ካሁን ቀደም እንጀራን አይረባም ፣ ጥቅም የለውም ብለህ ንቀህ በርገርና ፒዛ የመሳሰሉትን ”ጀንክ ፉድ“ ስታግበሰብስ ፈረንጅ ቀደመህና ጤፍን ላፍ አድርጎ የባለቤትነት መብቱን ወሰደብህ። አሁን ጤፍ ለጤና ተስማሚ glutton free መሆኑን ፈረንጅ ሲነግርህ እንደገና ተመልሰህ ግር ብለህ ወደ እንጀራ። አባቶቻችን ጾም ለስጋም፣ ለነፍስም እንደሚተርፍ ያስተማሩንን ስታጥላላ ኖረህ ዛሬ ፈረንጅ ስም ቀይሮ intermittent fasting ሳይንሳዊ ነው ብሎ አበው ከሺ አመታት በፊት የነገሩህን ጥበብ ዛሬ ነጭ ሲነግርህ አፍህን ከፍተህ ሰፍ ትላለህ። እንላለን! እንዲያው የምንገርም ጉዶች እኮ ነን። ነጭ ካልነገረን አናምንም የምንል ጉዶች!! ይሄም ብቻ አይደለም። አባቶቻችን ስለ ጸሎትና አርምሞ ብዙ አስተምረውናል። ዛሬ ከውጪ transcendental meditation ወዘተርፈ እየተባለ የሚነገረን ሁሉ አዲስ አይደለም። እዚሁ እኛ ጋር የነበረ፣ ያለ ጥበብ ነው። የራሳችንን አባቶች አንሰማማ። የራሳችንን መጻህፍት አናነብማ። ግእዝ አንችልማ። የደብተራ ቋንቋ ብለን እናናንቃለና። ታዲያ ውጤቱ ምንድነው? መደንቆር! በስጋም በመንፈስም መደህየት! ሌላ ሳይንሳዊ እውነታ ልንገርህ። መቼም ሳይንስ ካልተባልክ የሚነገረው ሁሉ እውነት አይመስልህም። እና ሳይንስ እንዲህ ይላል፦ ከእንቅልፍህ እንደተነሳህ በቀዝቃዛ ውሃ ታጠብ። በባዶ ሆድህ 1 ሊትር ውሃ ጠጣ። ከዛ ለ45 ደቂቃ ምግብ አትብላ። ይህ ሳይንስ እንደ አዲስ የሚነግርህ ነገር እኮ አዲስ አይደለም። በጠዋት የምትጠመቀው ጸበል፤ በጠዋት የምትጠጣው ጸበል ነው። ግን በቤተክርስቲያን በኩል የሚነገር ከሆነ ኋላቀር ነው ብለን ደምድመናላ!! ተው የአባቶቻችንን ጥበብ ያዝ። አባቶቻችን ፍጹም አልነበሩም ግን ጠቢብ ነበሩ። እንደምንንቃቸው አይደሉም። አሁንም አልረፈደም። ግዕዝ ተማር። አባቶቻችን ሊነግሩን የፈለጉትን ለመረዳት የምንችለው ያንግዜ ብቻ ነው። ፈረንጅ ግዕዝ ተምሮ ያገኘውን ቁምነገር በእንግሊዝኛ ሰፍሮ ስለራስህ እስኪነግርህ አትጠብቅ።አለበለዚያ በፊደሉም እንደ እንጀራው የበይ ተመልካች ሆነን መቅረታችን ነው። በእጅ የያዙት ወርቅ ሆኖብን የትም የጣልነውን ሀብት ፣ ፈረንጆቹ አቧራውን አራግፈው ሲያጌጡበት ያኔ መቆጨት እንጀምራለን።ወርቅን ዛሬ ወርቅ ማለት ልመድ!ስለዚህ ግዕዝን በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ ማካተት የማይቀር ጉዳይ መሆን አለበት ፤ መዘግየት የለበትም። © Tewodro Shewangizaw
Mostrar todo...
8👍 2
በጣም የሚቀፈኝ ነገር ቢኖር መጽሀፍ ይዞ እያነበቡ ፎቶ መነሳት ነው። እንዲህ የሚያደርጉ ማንበባቸውን ፎቶው እንዲናገርላቸው ነው። ታዱያ በንግግራቸው ወይም በጽሁፋቸው ውስጥ የመጽሀፉ ቁምነገር የለም። ልብ በሉ! ቁምነገሩ ማንበብ ነው እንጂ ማንበብን ማሳወቅ አይደለም። አያችሁ መጻህፍት ማንበብ ልክ እንደ ወሲብ ነው። ወሲብ በአደባባይ አታደርጉም ወይም እያደረጋችሁ ፎቶ አትነሱም። ከተዘጋ በር ጀርባ በጥልቅ ስሜት የሚከወን ተግባር ነው። ውጤቱስ? ውጤቱ እርግዝና ነው። በአደባባይ ለሁሉም ይታያል። የንባባችሁ ውጤትም በንግግራችሁ፣ በአስተሳሰባችሁ በግልጽ ለሁሉም ይታያል! መልካም የአለም የመጻህፍት ቀን!!! © Tewodros Shewangizaw
Mostrar todo...
👍 27 7👎 3
👉 🌿Ethiopian digital library🌿 A library in which you can get many ✅reference books 📚 ✅Textbooks ✅Freshman course ✅Amharic fictions ✅Premium applications ✅Extreme serious books 📚 ✅TOP BOOKS SERIOUS 📚 Join and share 👇👇 https://t.me/ethiolibrary1 https://t.me/Ethiolibrary1Bot #Share Ethiopian digital library Highschool library Pro bot
Mostrar todo...
ETHIOPIAN DIGITAL LIBRARY

✔️ መጽሀፍት በPDF ያገኛሉ ✓Top books ✓Extreme books ✅ ለትምህርታዊ መፅሀፍቶች ✅ ቴክኖሎጂ መፃሀፍቶች ✅ የሳይንስ መጽሀፍቶ ✅ የመደበኛ ተማሪዎችን መጽሀፍትን፣ ✅ የሶሻልና የናቹራል መጽሀፎች Email: [email protected]

https://t.me/ethiolibrary1

https://t.me/Ethiolibrary1Bot

👍 1💯 1
በቃላትኛ: ብልሀት: በጉልህ: "እመት: ደስታ" ብዬ: ጽፌ: ከፊት: ለፊቴ: አኖርኩት: ጽሑፉን: አንብበው፤ ድንገት: መልስ: ቢሰጡኝ።እንዳላየ: እየለዩ: መጽሐፍ: ፍለጋቸውን: ቀጠሉ። እንደ: ድብብቆሽ፣ ሳውቅዮሽ: እየተጨዋወትን: ሰአቱ: ገፋ። ፊቴን: ወደመስኮቱ: መለስ: ባደርግ፤ አንዲት: ዘለግ: ያለች፣ ፀጉረ: ረዥም: ወጣት: መጣችና፣ "እማማ: ደስታ: የት: ጠፍተው: ኖረዋል! እኛ: ላይ: ታች: ስንፈልግዎ። ይኸንን: ሎሚ: ለምን: ለሰው: ሰጡት?" በማለት: በአለንጋ: ጣቶቿ: ወደ: እኔ: ጠቆመች። አተኩረው: አዩኝና: "የእኔ: ሎሚ: አይደለም" አሏት። እንግሊዘኛቸው: የሀገሬው: ነዋሪ: ቃናና: ጥራት: አለው። አይ: ተመሳስሎ: ነው። ምን: እንዴት: ቢሆን፤ የቀበና: ወንዝ: ባልቴት፤ እመት-ደስታ: እንግሊዝ: ምድር: ደርሰው?! አይ: የማይመስል: ነገር: ነው። " የእኔ: ወንድም: ሀበሻ: ነህ?" ብለው: ሲያናግሩኝ፤ እግሮቼ: ተሳሰሩ፣ ከንፈሬም: ቆረፈዱ። እንዴት፣ ምን፣ እንደምመልስ: ጠፋኝ። ጥቂት: አምጬ፣ "አዎን" የሚል: ቃል: ከውስጤ: ወጣ። ፈጠን: ብለው: ሄደው: ወንበር: አመጡና: ከአጠገቤ: ተቀመጡ። "እዚህ: ሰፈር: መሬት: ይመራሉ: ንግስቲቱ: የሚል: ጭምጭምታ: ሰምቼ: የመጣሁ: ሀገር: ጎብኚ: ነኝ። ምትረዳኝ ነገር: ቢኖር?" ከተጎናፀፉት: ወርቃማ: በፍታ: ስር: ከደረታቸው: ላይ: የተጎበጎበ የመሬት: መልከአ-ምድር: ንቅሳት: ነገር: ታየኝ። "እማማ: ደስታ: አይደሉም: እንዴ!" ስል: ብጮህ፤ "እኔስ: መሆኑን: ነኝ። አንተ: ማን: ትሰኛለህ?" አሉ: "እኔንማ: ሊያስታውሱኝ: አይችሉም። ዘመኑ: እሩቅ: ነው። በርስት: የተነሳ..." ብዬ: ሳልጨርስ፤ እጃቸውን: አንስተው:- " በቃ! በቃ! በቃ!÷ የመሬት: የርስትን: ነገር: አታንሳብኝ": አሉና: ጉንጬን: በስሱ: ዳሰስ: አድርገው: ሲሄዱ፤ ተከትዬ፣ "እንዴ! ምንድነው: ነገሩ!፤ ምን: የተባለ: ንፋስ: ነው: እዚህ: ያደረስዎት?" ስል: ጮህኩኝ። መሀረባቸውን: አውጥተው: ገፃቸውን: እየደባበሱ፣ "ርስት: ፍለጋ: ነው: ንፋስ: አይደለም" አሉና: በፈገግታ: "ደሞስ: ቢሆን: ሠማህ: ወይ: ወገኔ: ንፋስ: አበቦችን: ከማሳመም: ሌላ: ምን: ተግባር: አለው: ብለህ!" ብለውኝ: ተሰወሩ። ያንን: ምሽት፤ በቴሌቭዥንም፣ በራዲዮም፣ ከምስራቅ: የመጣ: ሀይለኛ: አብሎ: ንፋስ፤ እጅግ: ብዙ: የእንግሊዝ: ገጠሮችን: እንዳወከ፤ ከየአቅጣጫው: ተነገረ፣ ተሰማ።" ገፅ 104-105 ጃርሶ ሞትባይኖር ኪሩቤል፣ ከኪነታዊ ሕይወቱ ውጪ ፖለቲከኛም ነበር። ከ19 60ዎቹ መጀመሪያ እስከ 70 ዎቹ አጋማሽ የኢሕአፓ አባል ሆኖ ከፍተኛ እንቅስቃሴ አድርጓል። እንደምታውቁት ጠልሰም ምትሃታዊ የደብተራ ስዓል ክህሎት ቢሆን ጃርሶ ደግሞ አዲስ ጠልሰማዊ የስነፅሁፍ ዘርፍ አስጀምሯል። ይዘቱ ብቻ ሳይሆን የተፃፈበት ቋንቋ እና ክህሎት ራሱ ምትሃታዊ በመሆኑ አዲስ ዘርፍ ቢሆን ማጋነን አይሆንም። የተራቀቁ የአውሮፓ ከተሞችን የኑሮ ዘይቤ እና ታሪክ በዱሮ አማርኛ መተረክ መቻል በራሱ ምትሃትን ይጠይቃል። እስቲ ከምትሃት ነክ ታሪኮቹ ሁለቱን ጀባ እንበላችሁ አንደኛ ". . .በማግስቱ ከየብርሌው የሚዋኘው የየኔታ ጭራ ንቃይ ለደንበኛው ሁሉ ሲታይ ጉድ እየተባለ ይወራ ጀመረ ። ከጉሮሮአቸው ተጣብቆ በትንታ የሚረብሹ ደንበኞች ጩኸት ማሰማት ጀመሩ ። <<እንዴ! ወለላ ምንድነው ነገሩ ? በሰንበሌጥ ይሁን ቃጫ አለቅን'ኮ! . . . ወለላ ሁለት ጠላ ጠማቂዎች በሽልንግ ቀጥረው ጋኑን ፣ ደንበጃኑን ፣ ማጣሪያውን ፣ ነጠላውን ጥድት አስደረጉት ። የየኔታ ጥሩነህ ጭራ ብናኝ ከወዴት እንደሚመጣ አልታወቀም ። ከብርሌ ሁሉ ተሰግስጎ ይታይ ጀመር ። . . . አቶ ታመነ ጠጋ ብሎ <<ወለላዬ ፣ የእኛ ሰው ለምን አይን ተፈጠረብህ ብሎ ነው የሚቀና ። ለምን እርስዎ?>> አላቸው ። << የእጀ-ሰብ ፀላኢ የሚያውቁ ወዳጅ አሉኝ ። ነገ ምሽት . . . ጠጅ-ሣርና አሪቲ ከቤቱ ነስንሰው የእጁን መደጎሚያ ቋጥረው ይጠብቁኝ>> ብሏቸው ወጣ ። . . . በማግስቱ ይማሩ ጉንዶ እና ስልቻ ዙሪያውን እንደ ሲባጎ የየኔታ ጭራ ቋጥሮት ተገኘ ። " የየኔታ ጥሩነህ ጭራ ( ከገጽ 28 - 29) ፦ ሁለተኛ " እትዬ: ማሚቴ: ገብሬ ፤ ዛር: ስላለባት: ሽቱ: ትጠጣለች። እትዬ: ማሚቴን: የሚያውቃት: ሁሉ: በሽቱ: ጠጪነትዋ: ያውቋታል። ጠረኗ: የባህር: ዕጣን: እና: ሉባንጃ: ነው። ሽቱ: ተቀብታ: አታውቅም። << የሰው: እንኳን: ሲሸተኝ: ትንፋሼ: ያበረክትብኛል>> ትላለች። <<ትንፋሼ>> የምትለው: በቀን: የምትቆጥረው ፥ ሃያ: አንድ: ሺህ: አንድ ፥ : የማይጨምር፣ የማይቀንስ: እስትንፋሷ: ነው። እንደ: መጥፎ: ዐመል: አብሯት: የአረጀ: ልማድ: በመሆኑ: ስትቆጥረው: እንኳ: አያስታውቅባትም። ሁለት: አንጎል: የአላት: ይመስል: በአንደኛው: ሃሳብና: ንግግር: ስታካሂድ: በሌላኛው: ትንፋሿን: ትቆጥራለች። እትዬ: ማሚቴ: የሠፈራችን: ትዕንግርት: ነበረች።" የሊባኖስ ሽቱ (ገጽ 87) በተረፈ ጃርሶ ከሸገሯ የወግ እመቤት መዓዛ ብሩ ጋር ያደረገው ቃለምልልስ እጅግ ጠቃሚ ስለሆነ You tube ውስጥ ገብታችሁ እንድትሰሙት እንመክራለን። ይህን መጽሐፍ ለሕትመት እንዲበቃ ያደረጉትን ጋሽ ክብሩንም እጅግ እናመሰግናለን። በዚህ መጽሐፍ መግቢያ ላይ ደራሲው የጨረሳቸው እና በቅርቡ ለሕትመት የሚበቁ የረጅም ልቦለድ መጻሕፍት እንዳሉት ቢጠቅስም ይኸው ዓመታቱ እየነጎዱ ስለሆነ ቢፈጥን ይበጀዋል። ክብረት ይስጥልን የቀበናው ጃርሶ ሞት ባይኖር! The Reviewer is the managing editor of Think Ethiopia © Think Ethiopia
Mostrar todo...
👍 2👎 1
ስለጃርሶ (9.4) ርእስ፦ ከደመና በላይ ጸሐፊ፦ ጃርሶ ሞት ባይኖር ኪሩቤል ይዘት፦ አጫጭር ልቦለድ Rating : 9.4 ጃርሶ ሞትባይኖር ኪሩቤል ተወልዶ ያደገው እዚሁ አዲስ አበባ ቀበና አካባቢ ነው። በተለይም "አስኮ ጌታሁን" የተሰኘችው ስምንት አጫጭር ልብ ወለዶችን የያዘችው መፅሐፉ እጅግ ታዋቂ ናት ። በቀድሞው አጠራሩ "የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ" በአሁኑ "ዶቼ ቨለ ራዲዮ" ደግሞ፣ ከ1973 እስከ 1992 ድረስ 44 የ የአጫጭር ልብ ወለድ ታሪኮቹ በራሱ ተራኪነት ለአድማጮች ተላልፈዋል። ከነዚህ ውስጥ ስምንቱ እዚሁ መፅሐፉ ውስጥ ተካተዋል።"የአዲሳባ ልጆች"፣ "ስምንተኛ ዲ"፣ "ጆርዳን" እና የመሳሰሉት ናቸው። በነገራችን ላይ ምትሃታዊ ስነፅሁፍ እና የአፃፃፍ ስልት የምናውቅ አይመስለኝም።ስለምትሃት በደረቁ መፃፍ እንደ ሃሪ ፖተር እና ናርኒያ መሰል ድርሳናት ተምኔታዊ ዓለም በመገንባት ሊከወን ቢችል እንኳ የአፃፃፍ ስልቱን ራሱን ምትሃታዊ ማድረግ ግን የተለየ ክህሎት ይጠይቃል። የጃርሶን አዲሱን ድርሳን ሲያነቡ ቃላቱ ራሳቸው ከወረቀቱ ላይ እየበረሩ ወደ ዓይንዎ ሲሰርፁ ሊታዘቡ ይችላሉ። የጃርሶ አጫጭር ተረኮች ውስጥ ያለው ገፀ ባህርይ በአውሮፓ የሚኖር ሰዓሊ እና ደራሲ ነው። የራሱን ስም በየታሪኮቹ ስንቅር ስለሚዶላቸው እውን ታሪክ ይሁን የልቡናው ውልደት ግራ ያጋባል፣ ምትሃትም አይደል? ለምሳሌ ከሳላሳ ዓመት በፊት ቀበና ወንዝ ስለሚያውቃቸው ሴት ሲያወራ አብረውት አንዱ አውሮፓ ቤተመጻሕፍት የተቀመጡ ይመስላሉ። " በወጣትነት ዘመኔ፤ የስነ-ጽሑፍን አድማስ: እየቃኘሁ፤ በለጋ አዕምሮ፤ በጉጉ: መንፈስ፤ ህይወትን፣ "ልወቅሽ-ታውቂኝ"፤ እያልኩኝ: ስፍጨረጨር፤ ዙሪያዬ: ሁሉ፤ በግጥም: ውበት፣ በቃላት: ኃይል፤ ሊገለፅ: እንዲችል: ብዬ፤ ከሃሳብ፣ ከፊደል: ጋር: ስሟገት: ሳለሁ፤ እቤታችን: ከሚመጡት: የእናቴ: ወዳጆች: አንደኛዋ፤ ስሙኒም፣ ሽልንግም፣ የእህል: ዱቄቱንም፤ እንጀራውንም፤ አስቋጥራ: ከምትሸኛቸው: መሳኪን: አንደኛዋ: "እመት: ደስታ" ይሰኙ: ነበር። "እመት: ደስታን" አይቶ፤ ለሥዕል: የማይመኝ፣ ድም፣ ሰምቶ: "ምን: ይሆን: የህይወታቸው: አይነትና: ጠረን?" ብሎ: የማይመሰጥ: ከያኒ: አይገኝም። እንዲሁ: ሲያዩዋቸው፤ ተመራመሩኝ፣ ፈልጉኝ፣ እሹኝ: የሚል: አይነት: ፊደል: ከላህያቸው: ይነበባል። እኔም: ሆዬ፤ እንኳን: ደርሰውብኝ፤ ፈልጌ፣ አስሼ፣ የምመራመር: አይነት: በለስ: በመሆኔ፤ "እመት-ደስታ" ብዬ: በመሰየም÷ ከግጥም: ወደ: ስድ: ጽሑፍ: ዓምድ: የተሻገርኩበትን፤ የመጀመሪያዬን: ተረክ በአፍላው: እድሜዬ: ጻፍኩኝ። ከረዥሙ: በአጭሩ፤ ቀበና: ወንዝ: ዳር፤ ሀኪም: ሜዳ: ከሚሰኘው: መንደር: በታች፤ ጭቃ: ምርግ፤ አንዲት: ክፍል: ቤት: ተዘግተው: የሚኖሩ፤ አፅመ-ርስታቸውን: ፍርደ-ገምድል: ዳኛ፣ በግፍና: በውሸት: ምስክሮች: ተነጥቀው፣ ራሳቸውን: የሳቱ፤ የተረፈች: ህይወታቸውን፤ ከጨለማ: ክፍላቸው፤ እሳቸው: እራሳቸው፣ አንዴ: ዳኛ፣ አንዴ: ጠበቃ፣ አንዴ: ከሳሽ፣ አንዴ: ተከሳሽ: በመምሰል: ተውኔት፤ የገዛ: ድምፃቸውን ሲያዳምጡ፤ ወፍ: ጪጪ: ጪጪ: የሚልላቸው:ሴት: ነበሩ።" ገፅ 102 ዋናው ገፀባህሪይ ጠልሰም ቢጤ የሆኑትን እና የመሀከለኛው ዘመን የቤተስኪያን ስዕሎችን በየአውሮፓ ከተማ የጥናት ጉባኤ እየተገኘ የሚመረምር ደብተራ ወይ ያፈረሰ ቄስ ይመስላል። ከእነዚህ ከተሞች ሆኖ በናፍቆት ወለድ ቁጭት ስለሀገሩ (ቀበና) ሲፅፍልን ግን ምታት ነገር በየመሃሉ እየከተተ ስልቱን ያለማምደናል። ቃላቶቹ ፍልስፍና ወለድ ስለሆኑም ጭምር ብዙ ያመራምራሉ። " የእመት: ደስታን: ሕይወት: መርምሬ፤ ፅፌ: ያስነበብኳቸው ሁሉ፤ ለጊዜው: በጥልቁ: ነበር: መንፈሳቸው: የተነካው። የመሬትን፣ የርስትን: ነገር፤ ቁጣና: መከራ፣ ጣጣ፣ ግፍን: በደልን: አስታወሳቸው። ይህ: የሆነው፣ ሳይጋነን÷ ከ33፣ከ34: ዓመታት: በፊት ነበር። ጊዜ ተተክቶ፣ ሰባት: ባህር፣ ሦስት: ውቂያኖስ፣ 60ወንዞች: አቋርጩ፤ ብዙ: የብስ: እግሬ: ረግጦ፣ ብዙ: ብዙ: ነገር፤ ሰው: እንደሆነው: ሆኜ፣ አይሆነው: ሆኜ፤ ዛሬ: እዚህ: አካል: ሰውነቴ: ካለበት: እንግሊዝ: ምድር፣ ሎንዶን፤ እንደገና: እመት: ደስታን: አገኘኋቸው። አብሮኝ: የኖረን፤ የልማድ፣ የአመል: ሙያ፤ እንደወትሮው: ሁሉ: ከአንድ: ቤተ-መጻሕፍት: ጥግ: ይዤ፤ ስቸከችክ፤ እመት: ደስታ፤ በቀጥታ: ወደተቀመጥኩበት: መጥተው፤ ካልጠፋ: መቀመጫ፣ ካልጠበበ: ቦታ፤ እየገፋፉኝ፤ ከመደርደሪያው: መጽሐፍ: ለማውጣት: ይታገላሉ። የጸሀፊ: አንጎል: አንዳንዴ፤ ያለፈ: ትውስታውን፤ የሌሊት: ህልሙንና የቀን: የእውኑን: ትእይንት: ስለሚያጠናግር፤ እራሴውኑ: መላልሼ: በመጠየቅ: "እውን: የማየውን: እመት: ደስታን: ነውን? ከሆነስ: እንዴት: ሳያረጁ? ደሞስ: ምንስ፣ ነፋስ: ቢነፍስ: ነው፤ ከቀበና: ወንዝ፣ ከስንት: ባህር: ባሻገር: ከሎንዶን: ምድር: ያሳረፋቸው? ደሞስ: ከ30: ዓመታት: በኋላ: እንደገና፤ ቦታ: እርስት: ብለው፤ ከእኔ: ጋር: መጋፋት: ምን: አመጣው?" እያልኩ: ስጠይቅ፤ እንኳን: የዘንድሮ: አቅለቢስ: ሰው፤ ድሮም: ቢሆን: ሰው: ይመሳሰላል: እና፤ "ድንገት: ተመሳስለውስ: ቢሆን? አማርኛ: ተናጋሪ: በግንባሩ: አይለይም። ፈረንጁም፣ አፍሪካውም፣ ጃማይካውም: የሚናገረው: ነው: ዛሬ....." እንዲህ: እንዲህ: እያልኩኝ: ሳሰለስል፤ ድንገት: ነጠቅ: ብለው: ከአጠገቤ: ሄዱ። አስቤ: ሳልጨርስ፤ ደሞ: ተመልሰው: መጡ፤ እና: ያልጠፋቸውን: መጽሐፍ: ፍለጋ፤ ከንቱ: ይባዝኑ: ጀመር። " ገፅ 103 ጃርሶ ያለ ማብራሪያ የሚጥላቸው አባባሎች አሉት። ለአብነት "ዓለም የወደዳትን ጥሬ ከብስል ታላምን " የሚለውን ፈሊጥ እስካሁን እየተመራመርኩበት ነው፣ በብቃት ላብራራልኝ ወሮታውን እከፍላለሁ። ጃርሶ ከደራሲነቱ ባሻገርም ሠዓሊና የሙዚቃ ባለሙያ ነው። በልጅነቱ የካቶሊክ ኃይማኖት ተከታይ፣ በወጣትነቱ ኢ–ዓማኒ፣ ከ19 76 ዓም ጀምሮ እስካሁን ደግሞ የአይሁድ (Judaism) እምነትን የሚከተለው ጃርሶ፣ የሙዚቃ ሥራውን በአብዛኛው ለመንፈሳዊ ዓላማ እንደሚጠቀምበት ይናገራል። "ከቶ: ምንድነው: ነገሩ? "ፈደለ:ፈጠረ: ነው:: ፊደል:ፍጥረት:ነው። እና: አንድ: ናቸው" ብለው÷ መምህራችን: ጥንት: ያስተማሩኝ: ከአንጎሌ: ደወለ። የሰላሳ: አራት: አመቱ: ፊደል፤ ቀንና: ኮከብ: ቆጥረው: ተመልሰው: ወደእኔው: መጡብኝ: ይሆን?÷ ተነስቼ: ወደ: ውጭ: ወጣ ብዬ: አየር: ተቀብዬ: ስመለስ፤ የሉም። ከተቀመጥኩበት: ወንበር: : ሎሚ: አኑረዋል። ምንድነው: ብልሀቱ? ሎሚዋንም: የሀገርቤት: ሎሚ: እንደሆነች: ጠረኗ: ነገረኝ። እመት: ደስታ: እራሳቸው: ናቸው፣ ሎሚ: ከመዳፋቸው: አይጠፋም: ነበር፤ ትዝ: ይለኛል። እሳቸው: ናቸው! ደንቃራ: እንዳይሆን: ጠረጠርኩኝ። ሎሚዋን: እያሻሸሁ: ሳሸታት: ተመልሰው: መጡ። ይግረምህ: ብለው፤ የባሰውን: ከጉልበቴ: ጋር: ይታሸሹ: ያዙ። ምኞታቸው: ግን: ያሮጊት: አልመስልህ: አለኝ። ከአካሄዳቸውም: የልጃገረድም: አይነት: ነገር: ይመስላል።
Mostrar todo...
👍 2
⨳አዲስ ነገር ነገረ ማቲን የተመለከተ የስነ ጥበብ ስራችን ውስጥ በተለይ በፊልም እና መፅሀፋችን ብዙ ስራዎች ቢኖሩም የተላበሱት ወንዳዊውን አለም እንጂ ሴታዊነት የለበትም። ወይም ሴት ልጅ ስትተርክ የሚያሳይ ስራ እምብዛም ነው። ጥቂት ከሚባሉት ውስጥ በአሪፍ ጅማሮ ነገረ ማቲን በሴት አለም ውስጥ ያየሁት በዚህ የልቦለድ መፅሀፍ ነው። ለዚህም ከሁሉ ከሁሉ ደራሲዋ ብትመሰገን አይበዛባትም። ⨳ገፀባህሪያት => ኮብላይ ናቸው - የረጋ መቼትና ሰፈር የላቸውም በሚያካልባቸው የህይወት ግፊት ልክ እንደ ጥንት የኢትዮጵያ ነገስታት ቋሚ ከተማ እንዳይኖራቸው አድርጓል። mobile capital city የሆነ መገለጫ የተላበሱ ናቸው። ለምሳሌ ከመፅሀፉ አንድ ቦታ የጎሹ ሚስት « እኔም ስደተኛ ሆንኩ። ጎጆ የማይወጣላት። ተባልኩ። » ትላለች። ሌላው አከላቴ ስትዳር ወደ ማታውቀው ሀገር መሰደዷ እና በተለይ በተለይ የሰር ከኖረችበት ቀየ ኮብልላ ወደነ አኬ መንደር መምጣቷ አመላካች ነው። => ጭምትና ህይወት በክፉ ክርኗ የደቆሰቻቸው ናቸው - በሀዘን ተሰብረው የሚቀሩ ሳይሆኑ ከገቡበት ችግር ለመውጣት በህይወታቸው የያዝዋትን አንድ አማራጭ እንኳን የሚሰዉ ናቸው ለምሳሌ። በ « ጣሪያ » ውስጥ መውለድ ያቃታት እናት በጠበልና በሌሎች ሀይማኖታዊ ስርዓት ነገሯ አልቀና ቢል በምሽት ወደ አዋቂ ቤት እስከመሄድ የተገደደችና በእሴት ደረጃ እምነት የሚባለውን dogmatic principal አፈር የሚ ያደርግ ውሳኔን ስትወስን እንመለከታለን። በሌላም ቦታ በገፅ ላይ አካላቴ ታማ በጠበሉ አልሻላት ሲል እምነት ብትቀይርና ቸርች ቢፀለይላት እንደምትድን የሚመክር ጠያቂ እንደመጣባት ተመልክተናል። እነዚህ የህይወትን መከራ ፣ አሜን ብሎ ከመቀበል ይልቅ በእምቢተኝነት ድጋሚ ከዜሮ በመነሳት ለመጀመር መጣራቸው ከላይ ካየነው ሲሲፈሳዊ የሰው ልጅ ጠባይ ጋር የሰመረ ቁርኝት እንዳለው የሚያመላክቱ ናቸው። በቦታ ወሰን ተገድበው አይታዩ እንጂ ይህ አይነት የአኗኗር መንገድ በብዙሃኑ ጋር የሚታይ ቢሆንም በአንፃሩ ከቀሪው የማህበረሰብ ክፍል ጋር የሚያቃርንና መገፋትን የሚፈጥር ፈርጅ መሆኑም እሙን ነው። ሌላው ማህበራዊ መልክ ሰዎች በባህል ተገፍተውም ይሁን ውስጣቸው ባለው የጥርጣሬ ስሜት የሚቀሰቅስ ( skeptic affecting ) ሌላውን የማህበረሰብ ክፍል መገለል እንዲደርስበት ሊያደርጉ ይችላሉ። ቡዳ ነው። በሚል የጥርጣሬ ስም ለብሰው የተገለሉ ገፀ ባህሪያት በዚህም መፅሀፍ ውስጥ ተገኝተዋል። አንዷ አከላቴ እንዳትሄድባት የሚነገራት የላይ ቤቷ ሴት ስትሆን ሁለተኛው ያኚ ፂማም ሽማግሌ ናቸው። ታዲያ ለሁለቱም የግዞታቸውን አርነት ያገኙ ያህል ነፃነታቸውን ስታውጅ የነበረችው አከላቴ ናት። ረጅም ዘመን አብሮ የኖረ አዋቂ ያልተረዳውን እውነት ፣ ትህትና እና ፍቅር በአንድ ጀምበር ከአንዲት የዋህ ህፃን ያገኙ ሽማግሌ ስሜታቸው ሌላ ሆኖ እንመለከታለን « ልንካዎት? » ነጭ የሚያምር ጢም አላቸው። ጠይም ሆነው ተአባቴም በጣም የሚያረጁ ይመስላሉ። ዓይን ለዓይን ተያየን። እምባ አቅርሯል አይናቸው። « የማነሽ መልዓክ ልጀ? ማነው ነጣ አውጭው ብሎ የላከሽ?» እምባቸው ወረደ። « አባቴ እንደርሶ ቆንጆ ነበረ።» አልኳቸው። «እሱ ሰው ሰውን አይበላም ብሎኛል። እላይ ቤት ያለችዋ ጎረቤታችንም ሰው እንደማትበላ አውቃለሁ።» እኔም እምባዬ መጣ። ሩጬ እቅፋቸው ውስጥ ገባሁ። « አልቴት አልቴት የምትሸች የኔ መልዓክ...» « ቡዳ እንዳይበላኝ ነውኮ።» « መች ጠፋኝ ? ስም ይወጣል ተቤት ይከተላል ጎረቤት ሆኖ። እንግዲ ማን እንዳወጣልኝ ያላወቅኩት ስም አብሮኝ አረጀ ልጄ። መግቢያ መውጫ ባጣ 'አዋጅ' እል ጀመራ ቡድነቴ...» / ገፅ 67 / ከመንጋው እሳቦት የወጣች ብቸኛ የነፃነት ብርሃን..! ስለማህበራዊ መልክ ካነሳን አይቀር እንደማህበረሰብ የምናውቃቸው አዘቦታዊ ብልጭታዎች ስር የሚመላለሱ የገፀ ባህሪያት ቅንበባ ከሁሉም ከሁሉ ለልቦለዱ የቋንቋና የስልት ጉዳይ ጥሩ ፍሰት እንዲኖረው የረዳው ያህል ይሰማኛል። እዚህ ጋ አንባቢ ልብ ሊለው የሚገባው አንድ ነገር የገፀ ባህሪያቱ ግንባታ አዘቦታዊ ዘውግ ይልበስ እንጂ ለታሪክ መዋቅሩ የሚቀርቡት ተረኮች ማህበረሰቡን በወከሉት ነፍስ ውስጥ እንደትልቅ ገጠመኝ የሚታዩና ተቦክተው የተሰሩበት ቁም ነገር ነው። ይህም ከፍሰቱ ውጪ ለሰንሰለታዊ የልቦለዱ ቅርፅ ይህ ነው የማይባል ጉጉትን ፈጥሯል። እንደማጠቃለያ የይፍቱ ስራ ምትኩ በተለይ አስራ አንደኛው ኖቮሌት ቅርፅ የልቦለድ መፅሀፍ በውስጡ ብዙ ደሳስ የሚሉ ያልተከላለሱ ያልተበራረዙ የትረካ ንጋቶችን ያሳየን ይመስለኛል። ብዙ ለሚባለው የአንባቢ ክፍል የጎላ አረዳድን የማይጠይቅ ቀለል ያለ የሀረግና የአረፍተ ነገር ምስረታን ያቀፈም ነው። መነሻና መድረሻውን በሰሜኑ የኢትዮጵያ ገጠራዊ ክፍል ያደረገ መቼት ቢኖረውም ደራሲዋ የተጠቀመቻቸው ወጎች ለታሪኩ ቀጥ ብሎ መጓዝ ውለታ ውሎላታል ብዬ አስባለሁ። በአጠቃላይ በቆንጆ ፍሰት ውስጥ የተወለደ ቆንጆ ስራ ነው። .... የመፅሀፉ ዳሰሳ አቅራቢ ሲራክ ወንድሙ በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ልዩ ልዩ መጣጥፍ በማቅረብ ይታወቃል። በቅርቡ ለረዥም ጊዜ የለፋበትን ስራ ለማሳትም እየተጋ ይገኛል። © Think Ethiopia
Mostrar todo...
በተለይ በተለይ(9.1) የመጽሐፉ ርዕስ፦ በተለይ አስራ አንደኛው ጸሐፊ፦ ይፍቱሥራ ምትኩ የመጽሐፍ ዘውግ፦ ልቦለድ የገጽ ብዛት፦ 106 Rating፦ 9.1 በ 106 ገፆችና በስምንት ርዕሶች የተከፋፈለ ኖቭሌት ቅርፅ ያለው መፅሀፍ ቢሆንም በውስጡ በያዘው ቀለማም መልከ ብዙ የህይወት ፈርጅ ድንቅ መፅሀፍ ያደርገዋል። በሰው ልጆች የእጣ ፈንታ ዳረጎት ላይ የተቋጠረች ህልውናን ባስመለከተ በሰፊው ለመዳሰስ የተነሳው ይህ የመፅሀፍ ጭብጥ በኢትዮጵያ ስነ ፅሁፍ ውስጥ ሁሌም እንግዳ ሆኖ ከሚታየው lower class የማህበረሰብ ደረጃ ላይ ቆሞ ታንቲራ ይገጥማል። በሌላ መልኩ የገጠሪቱን ኢትዮጵያ ማህበረሰባዊ እሳቦት ፣ የስነ ልቦና ዳር ፣ የልቦና ውቅርና መሰል የተዘነጉ የሚመስሉ ግን መጋረጃው ቢገለጥ አፍጥጠው የሚገኙ እሴቶች ላይ ትኩረት አድርጓል። ገፀባህሪያቱ በተረካቸው የሚነኩት ነጥብና ቀዝቃዛ ስሜት አኗኗራቸው ካደረሰባቸው ጉስቁልና ጋር ተዳምሮ የመፅሀፉን መዳረሻ በቀዝቃዛ የስስ ስሜቶች ሙሌት እንዲታጀብ ሆኗል። እስኪ ለአመል መንሳፈፋችንን እናቁምና ከላይ የጠቀስኳቸውን ነጥቦች በጥልቀት ለመረዳት እያንዳንዱን ገፅ እንግለጥ.... ተራኪያችን ማቲ ናት። ህፃን። በኖረችበት ቀዬ የረባ ስም የላትም። እናቷ ጥላት ስትሄድ ያገኘቻት አኬ የምትባል አሳዳጊዋ በምትጠራት ስም እንቀጥል..! አካላቴ ትላታለች አሳዳጊዋ። ካለ ህይወት መደላድል በወጣትነት የስሜት ትኩሳት ዘላ የገባች አንድ ሴት እንዳይሆን ሆነና አረገዘች። ያን ሲያውቅ ባሏ ጥሏት ጠፋ። እሷም ፈለጉን በመከተልና ራሷን ነፃ አድርጋ ከህይወት ጋር ለመታገል ስትል የሶስት ዓመት ሞሳ ልጇን የትም ጥላ ጠፋች። ተራኪያችን ከአሳዳጊዋ ጋር የምትገናኘው እንደዚህ ነው። መንደሯ ብዙ በሚናፈቁ አለላዎች የተሰራች ሌማት ትመስላለች። እድገቷንም በባይተዋርነት ጎዳና ላይ እየተረማመደች የሰፋችው ከዚሁ ዳርቻ ነበር። አንድ ቀን ከአቻዎቿ ጋር ሱዚ እየተጫወተች እያለ ያቺ የምትወዳት የሰር በሰዎች ተደግፋ ወደ ቀየዋ ስትገባ አየች። በአይኗ ያየችው ነገር ልቧን ብቻ ሳይሆን እሷንም በምህዋሩ ላይ ሰቅሎ ዝም አለ። ድንጋጤ ሲፈጠር የምድር ህግጋት ውላቸውን ይስታሉ መሰለኝ የመሬት ስበት ቀረ። ሽቅብ ሰማይ ጉና አየሩ ላይ ቀረች።... ጀበና! በመፅሀፉ የመጀመሪያ ርዕስ ስር የምንመለከተው ታሪክ መልከ ብዙ ነው ለእኔ ጠቅላላ ታሪኮችን በአንድ እሽም አድርጎ ከመያዙም ባለፈ ለቀጣይ የጭብጥና የታሪክ ነገራ መንገድ ትንቢት የሚሆን ይመስለኛል። ህይወትን በአንዲት ጀበና የመሰራትና የማለቅ አፅናፍ የያዘ ስሁት ልቦለዳዊ እውነታ ነው። ይህ ጀበና በሚል ርዕስ ስም የነቃው ታሪክ በመኖር ቀለም ዳር Relative context የሚቃርመው የመሳሳብ ህጎችን እንዳፀና የሚገልፅ ጎሕ አለው። ቀደምት ሊቃውንቱ ሞት ሙትን ይስባል እንደሚሉት ደሀ ከደሀ ይሳሳባል። ሀብታም ከሀብታም ይዋደዳል። ይባላል። ገና በውልደት ጅማሮ ማህበረሰብ የውበት መለኪያውን የሰቀለበት ቆጥ ስር መልከ ጥፉነት active ሊያደርግ ከሚችልበት ውሎ ገፍቶ ያወጣል። ‑ « .... እናቴን አልመስል አባቴን .... ኬት ወጥቼ እንደሁ ፥ አባቴም ሁለት ሶስት'ዜ ማን ጎበኘሽ እያለ ታንቲራ ሲገጥማት ትዚ'ለኛል በልጅነቴ። ... » . ይህ ከባድ የስነ ልቦና ልምሻ ከመሆንም ባለፈ በ scientific wey of biological knowledge ብንሄድ ሌላ ትርጉም ያለው የ Gene ግኝትና ስነ ተዋልዷዊ ጥያቄዎችን በብዙ ቤተሰቦች ላይ የሚፈጠር ጥያቄ ነው። በተለይ ልጄ እከሌን መስላለች በእከሌ ትወጣለች አይነት እምነት ላለው ማህበረሰብ... የሆነው ሆነና የሰር በመልከ ጥፉነቷ የተገፋች ሆነች። ፈላጊም ጠያቂም ጠፋ። አባቷ ቆማ ከምትቀር አለና ከአንድ ሽፍታ ጋር ሊድራት ተስማማ። ዳስ ተጣለ። ሰርጉ ተደገሰ። ቀየው ሞቅ ደመቅ እንዳለ መሸ። ሙሽራው ቢጠበቅ የውሃ ሽታ ሆነ። የሰዓቱ መግፋት ና የሙሽራው መዘግየት ያሳሰባቸው ቢጠይቁ ተጋቢው በመንገድ ላይ እያለ ከሽፍታ ጋር ተታኩሶ መሞቱን ይሰማሉ። ደስታ ነው ያሉት በሀዘን ተቀየጠ። የነገ ተስፋዋ ከሰባራ እድል ጋር ተሰብሮ ቀረ።... በኋላ ላይ በሆነ አጋጣሚ የሰር ከነ አካላቴ ጋር ትገናኝና ጓሯቸው ጀበና መስራት ትጀምራለች። ለጀበና የሚሆን አፈር ለማምጣት አካላቴን አስከትላ ተራራ ትወጣለች።ትወርዳለች። እዚህ ጋ የተራራ ትርጉሙ ምንድነው ? በዚህ ድርሰት ውል ውስጥ የተገለፀው መልከ ሰብዓዊ ህፀፆች የሰርንም ሆነ አኬን ከግሪኩ የአፈታሪክ ንግርት ጋር የሚያመሳስለው ነገር የለም? ስብሐት ሲሲፈስ የሚወክለው የሰውን ልጅ እንጂ ሌላ አይደለም ያለውስ እንዲሁ ዘበት ነው? ወደ የሰር ስንመለስ ሲሲፈስ ድንጋዩን እየገፋ ጫፍ አደረስኩ ሲል ይመለስበታል። ድንጋዩን ተከትሎ ወደ ንቃቃቱ ይሮጣል። ከዚያ ሽቅብ ወደ ላይ እየገፋ ይወጣል። አሁንም ይመለስበታል። ሲሲፈስ ተመላሹን ድንጋይ እየተከተለ ወደ ታች - እየገፋ ወደ ላይ የሚኖር የዘላለም ፍርደኛ ነው።የሰርን በዚህ የህይወት እሽክርክሪት ውስጥ ከተን ብንዳስሳት ይኸው ነች።የእምባ አለቷን በመግፋት ፈገግታ የሚናፍቃት ፍርደኛ። ከላይ እንደጠቀስኩት የእሷ የህይወት ዝቅታ የሚጀምረው ገና ከፍጥረቷ አንስቶ ነው። ማህበረሰብ የደነገገው የውበት ትርጉም መዝገብ ውስጥ ተፈልጋ ስትታጣ የእድሜ ዘመኗን እኩሌታ ለደስታ የራቀች ለሀዘን ወዳጅ የነበረች ሆና ለመቆየት ተገደደች። ያ ያመጣው መዘዝ የባል ችግር እንደየሎስ እንዲያንዣብብባት ሆነ። በስተመጨረሻም : « ኋላ ሳድግ ' ይህቺ ልጅ ቆማ ቀረች ' ሲባል አባቴ ታንድ ሽፍታ ጋር ልጅህን ለልጀ ተባብሎልሁ መጣ። ሁለት የቸገራቸው ሲገናኙ....የሽፍታንስ ልጅ ተመልከ ጥፉ ውጭ ማን ያገባል? » መላ አካሌ ጆሮ ሆኖ ይሰማል።.. / ገፅ 18 / ዳስ ተጥሎ ሰርጉ ተደገሰ። ግን አልተሰረገም። የቤታቸው ከባቢ ደመቅ መቅ ብሎ ሙሽራውን ይናፍቅ ገባ። ከዚያም ! « ... እኩለ ሌት ሆነ ሲጠበቅ። ሙሽራው የውሃ ሽታ። ' እስቲ ወጣ በሉና 'እዩ' ተባለ ጨፋሪው...ግማሽ መንገድ እንደኸዱ ነዋሉ ' አከባቢው ሰላም አደለም' ..... 'ምንድነው? ' ቢሉ ' ሽፍታ ሰው ገሎ' ....እህ ቢሉ ሟቹ ሙሽራው። » / ገፅ 19 / : ተገፍቶ ላይ ወጥቶ የነበረው ድንጋይ ወደ ንቃቃቱ ተመለሰ። ሽፍታው ተስፋዋን ይዞባት የሄደ መሰለ። አኬ በአንድ ቦታ ተራኪያችንን አምሮትሽን በላሁ እንዳለቻት ሁሉ በሞቱ መርዶ የተስፋዋን ብስራት ቀበረ። ሁሉም በዜሮ ተባዛ። «እሜቴ የት ልደር... እካብ ላይ ብሰራ እባቡ መከራ .. » ሆነ። ወጣ ወጣና እንደሸንበቆ ተንከባለለ እንደሙቀጫ። ታሪከኛችን የሰር በተለምዶ ቀደምት የማህበረሰብ አተያይ ቡዳ እየተባለ የውርደት ስም በሚሰጠው ጫፍ የቆመ የሸክላ ስራ ባለሙያ ነች። ሊያውም ጀበና ሰሪ... በእድሏ ጥመት ሰርክ የምትብከነከነው የሰር የአምላኳን የእጅ ስራ ተምሳሌት ለምን ተከተለች? ሸክላ ሰሪስ ትሁን ሰርክ ከመቃጠል የማይድን ጀበናን ከመስራት የአበባ ማስቀመጫ ወይም ውሃ መቅጃ እንሰራ ለምን ምርጫዋ አልሆነም?
Mostrar todo...
👍 3