cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ትምህርታዊ እና የፀሎት ጥቅሶች😊

ይህ ቻናል የተከፈተው ለሁሉም እምነት ተከታዮች ስለሆነ ለመቀላቀል አትፍሩ በመሆኑም የተለያዩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጥቅሶች እና ትምህርታዊ ፅሁፎች ይለቀቃሉ።

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
158
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ከመሬት የተገኘች ሰማይ ከሰማይ የሰፋች አለም። እግዚአብሔር ለእግዚአብሔርነቱ በራሱ ለራሱ ያበጃት መቅደስ፤ ኮሬብ ያልቻለችውን፣ ሲና የተንቀጠቀጠችለትን፣ ታቦር የራደችለት፣ ዮርዳኖስ የሸሸችለትን፣ ግሩምና ታላቅ ኃይል በማህፀኗ የተሸከመች ደብር ነባቢት፤ ቃል የማይገልጣት ንፁህ፣ ለቅድሱ አምላክ ፍፁምና ቅዱስ ማደሪያ የሆነች፣ ከሰው ተገኝታ ከመላዕክት የበለጠች፤ የፍቅር እናት የጌታ እናት የቤተ ክርስትያን እናት የአለም እናት የእኛ እናት የፍጥረት ሁሉ ጌጥ ወላዲተ አምላክ #ዛሬ_ተወለደች እንኳን ደስ አለን። #አቡኑ_ማሞ
Mostrar todo...
እግዚአብሔር ዓሣን ሲፈጥር "ሕይወት ያላቸውን አስገኝ" ብሎ ባሕርን ተናገረው እግዚአብሔር ዛፎችን ሲፈጥር ደግሞ ዛፍ እንድታበቅል መሬትን ተናገራት ሰውን ሲፈጥር ግን የተናገረው ለራሱ ነበር እግዚአብሔርም አለ "ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር" ልብ አድርጉ :- ዓሣ ከባሕር ከወጣ ወዲያውኑ ይሞታል ዛፍም ከምድር ላይ ከተነቀለም ይሞታል ሰውም ከእግዚአብሔር ከተለየ ይሞታል:: ባሕር ለዓሣ መሬት ለዛፍ ተፈጥሮአዊ መጠለያቸው እንደሆነ የሰው ልጆች ተፈጥሮአዊ መጠጊያችንም እግዚአብሔር ነው:: የተፈጠርነው ከእርሱ ጋር ልንኖር ነው:: ሕይወት ያለን ከእርሱ ጋር ነውና መኖር የምንችለው በእርሱ ብቻ ነው:: ይህንንም እናስታውስ ዓሣ ያለ ባሕር ምንም ነው:: ባሕር ግን ያለ ዓሣ ያው ባሕር ነው:: ዛፍ ያለ መሬት ምንም ነው መሬት ግን ያለ ዛፍ ያው መሬት ነው:: ሰው ያለ እግዚአብሔር ምንም ነው:: እግዚአብሔር ግን ያለ ሰው ያው እግዚአብሔር ነው:: ቅዱስ ባስልዮስ እንዲህ እንዳለ :- "ጌታ ሆይ የአንተ አምላክነት ለእኔ ያስፈልገኛል እንጂ የእኔ ፍጡርነት ለአንተ አያስፈልግህም" ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ኅዳር 23 2013 ዓ ም Translated from Mighty arrows publications                                         @Eftah_bemaleda @orthodoxchristian3
Mostrar todo...
ማቴዎስ 28 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁵ መልአኩም መልሶ ሴቶቹን አላቸው። እናንተስ አትፍሩ የተሰቀለውን ኢየሱስን እንድትሹ አውቃለሁና፤ ⁶ እንደ ተናገረ ተነሥቶአልና በዚህ የለም፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ። ክርስቶስ ተንስዓ እም ሙታን በአብይ ሀይል ወስልጣን አሰሮ ለሰይጣን አጋዞ ለአዳም ሰላም_እምይእዜሰ ኮነ ፍስሀ ወሰላም እንኳን አደረሳችሁ
Mostrar todo...
tafach enkilf.mp32.33 MB
መቼስ ማሕበረ ቅዱሳን በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ያለውን ቦታ ለእናንተ አላስታውስም። በሉ ይኸው የራሳቸው ማስታወቂያ ሰብስክራይብ እንድታደርጉ https://www.youtube.com/user/EOTCMK
Mostrar todo...
ማሕበረ ቅዱሳን.mp46.46 MB
ያሳዝናል ማርያምን.. በሉ እናፍጥነው። በዳታ የምትጠቀሙ ራሱ ገብታቹ ቪድዮ ባታዩም ሰብስክራይብ አድርጉና ውጡ.. ይሄ በቃ ሃላፊነት እናድርገው። አሁን ይሄንን እያየን አንለፍ.. በእርግጥም አናልፍምም እንደውም ሼር ሼር እያደረግን እስቲ ሁሉም ሰብስክራይብ አድርጎ ምን ያህል እንደምንደርስ እንይ.. ከታች የማስቀምጠውን ሊንክ በመጫን "subscribe" የሚለውን ተጫኑ 👇👇👇 https://www.youtube.com/user/EOTCMK
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.