cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ፍኖተ ጥበብ ሰንበት ት/ቤት

ይህ የሲኤምሲ አቡነ ተክለሐይማኖትና ቅድስት ልደታ ለማርያም የፍኖተ ጥበብ ሰንበት ት/ቤት በሰንበት ት/ቤቱ ግንኙነት ክፍል የተከፈተ የቴሌግራም ቻናላችን ነው።ለማንኛውም ሃሳብ አስተያየትና ጥያቄ @FinoteTebebBot የሚለውን ቦት ተጠቀሙ። የአቡነ ተክለሐይማኖት አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ከኛ ጋር ይሁን!!!

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
211
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días
Archivo de publicaciones
25|06|16 ፎቶዎች
Mostrar todo...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
የካቲት ፳፫ እንኳን ለሊቀ ሰማዕቱ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳቹ🙏 ረዳትነቱ ፣ ምልጃዉ እናጥበቃዉ አይለየን አሜን🙏 የዓድዋ ጦርነት በእመብርሃን  አማላጅነት በቅዱስ ጊዮርጊስ ረዳትነት እና በኢትዮጵያ ሕዝብ መስዋትነት ድል ነስተናል🙏 እና የምንኮራበት የድል በዓላችን ነዉ 🙏 እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን🙏 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 @Finotetebebbb
Mostrar todo...
👍 1
21.73 MB
የልደተ ፍኖተ ጥበብ የጸሎት መርሐ ግብር ማጠቃለያ መዝሙር ።
Mostrar todo...
24.01 MB
በዚ መሠረት ለአርብ ጸሎት እንዘጋጅ
Mostrar todo...
4_5938287964600668477.mp311.96 MB
🙏 1
መሐረነ አብ ጸሎት.pdf4.87 KB
Photo unavailableShow in Telegram
💫06 ቀን ቀረው💫 ““የጥበብን መንገድ አስተማርሁህ፤ በቀናች ጎዳና መራሁህ።”   — ምሳሌ 4፥11 እንኳን ለፍኖተ ጥበብ ሰንበት ት/ቤት ፲፱ነኛ የምሥረታ ዓመት በዓል በሰላም  አደረሰን አደረሳቹሁ።       🌟ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ 🌟 የፍኖተ ጥበብ ሰ/ት/ቤት19ነኛ የምስረታ በዓል ከየካቲት 22_24 /2016 ዓ/ም ያከብራል ተጋባዥ መምህራን እና ዘማሪያን ይገኛሉ በመሆኑም እርሶም በእዚህ ጉባኤ ላይ ወዳጅ ዘመዶን በመጋበዝ  ቃለ እግዚአብሔርን እንዲማሩ  በእግዚአብሔር ስም ጠርተኖታል! 👉አርብ 10:30 ጀምሮ የመሃረነ አብ ጸሎት በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ 👉ቅዳሜ እና እሁድ 10:00-ጀምሮ የአውደ ምህረት ጉባኤ 👉 እሁድ 3:00 የደምልገሳ መርሐ ግብር በሰንበት ት/ት ቤት አዳራሽ ማስታወሻ መያዞን አይዘንጉ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን በመቀላቀለ ቤተሰብ ይሁኑ! የ telegram ገፅ✅ https://t.me/Finotetebebbb
Mostrar todo...
👍 2
Repost from N/a
✍️✍️ኑ ስለኛዋ ነነዌ እናልቅስ✍️✍️✍️ ህዝብ እንደ ፈረስ ጀሮ እንደ ጦር ጉሮሮ ተስተካክሎ የሚበድልባት ስለእኛዋ ነነዌ እናለቅስ ዘንድ ኑ አብረን እናልቅስ።ነነዌ ምን እድለኛ ሀገር ናት፤እግዚአብሔርን ከመጥፋቷ በፊት በልቅሶ የጠየቀች።ከንጉሥ እስከ ህፃናት፤ከሰው እስከ እንስሳት ለአንድነት የተባበሩላት ነነዌ እውነትም እደለኛ ናት።ይህ በጨለማው ዘመን ሆነ በብርሃኑ ዘመን ስላለን ስለእኛ የነነዌ ሰዎች ኑ አብረን እናልቅስ።ባሕር አስጥሞ ስላስቀራቸው ዮናሶችም አብረን እናልቅስላቸው የዋጣቸው አሳ ድንገት ቢተፋቸው።ከፍ ብለን ትችቱን ዝቅ ብለን ቁጣውን እንተወውና በሰውነታችን ላይ የተንጠባጠበውን የራሳችንን ቆሻሻ ኑ እናራግፍ፤እኔን ከምታማ አቅርበህ ንገረኝ፤እኔንም ታድነኛለህ አንተም ትባረክበታለህ።ኑ ዮናስን እንሁን አንድነቱ፤መተሳሰቡ፤ቢሮው፣ዘመዱ ጓደኝነቱ፣አገልግሎቱ የታወከው በእኔ አስመሳይነት፣ውሸት፣ጎጠኝነት፣አልጠግብ ባይነት፣እራስወዳድነት፣ክብር ፈላጊነት ነው ብለን እራሳችንን ወደ ጥልቁ እውነት ወርውረን ህዝብን፣ወገንን፣ሀገርን ፤ሃይማኖትን ከጥፋት እንታደግ።ዮናስ እኔ ነኝ፣ዮናስ አንተ ነህ፣ዮናስ አንቺ ነሽ፤ለምስጋና ተፈጥረን ለትችት፥ለስድብ ያደርነው እኛው ነን ኑ አሁንም ስለእኛዋ ነነዌ እናልቅስ።የሌሎች ጉድፍ ከማየታችን በፊት የእኛውን ምሰሶ እናንሳ ለሆድ ከማደር ወጥተን ለእውነት እንደር፤ለምድራዊ ዝናና ክብር ሳይሆን ለሰማያዊ መንግስቱ ቀንተን እንሩት።ሰማእታት የዚቺን ዓለም ጣዕም ናቁ ደማቸውንም ስለእግዚአብሔር አፈሰሱ፤እንደለ ቅዱስ ኤፍሬም ኑ ክፋትን፣ስንፍናንን፣ጥላቻን ጠልተን ስለሰው ልጅ ክብር አብረን እንባን እናፍስ።ነነዌ ሀገራችን፤ነነዌ ቤተ እምነታችን፤ነነዌ ቤተሰባችን፤ነነዌ ጉባኤችን ከሆነ ቆይቷልና ኑ ስለእኛዋ ነነዌ አብረን እናልቅስ አምላካችን ይቅር ይለን ዘንድ የታመነ ነው።
Mostrar todo...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
🙏ከግል ጸሎት በኋላ ስለ ሰንበት ትምህርት ቤታችን እንጸልይ 📖 ከመዝሙረ ዳዊት የሚከተሉትን ምዕራፎች book 📖 24 50(51) 90(91) 101(102 135(136) ማጠቃለያ አቡነ ዘበሰማያት ብለን እፈጽማለን።
Mostrar todo...
🙏 2
Photo unavailableShow in Telegram
ቅድስት ኪዳነ ምህረት🙏 “በከመ ልማድኪ በሊ ኀበ ወልድኪ ከሃሊ   ኦ ርኅሩኅ ኢተበቃሊ   ያጠፍኦኑ ለሥዕሉ ሠዓሊ   ኪነተከ ዘትካት ኀሊ” (እንደ ልማድሽ ኹሉን የሚችል ወደሚኾን ልጅሽ የማትበቀል ቸር ሆይ፤ ሠዓሊ ሥዕሉን ያጠፋዋልን፤ የቀድሞ ፍጥረትኽን ዐስብ በዪ) አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ምልጃዋ አይለየን እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን🙏🙏🙏 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 @Finotetebebbb
Mostrar todo...
🙏 2👍 1
"ማርያም ቅድስት ድንግልተ አፍአ ወውስጥ፤ ቤዛ ይኩነኒ ኪዳንኪ በገጸ ፈጣሪ ሥሉጥ፤" {መልክአ ኪዳነ ምሕረት} ድንግል ማርያም በቃል ኪዳኗ ትከልለን🙏🙏🙏 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 @Finotetebebbb
Mostrar todo...
መዝሙር 44 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²² ስለ አንተ ሁልጊዜም ተገድለናል፥ እንደሚታረዱም በጎች ሆነናል። ²³ አቤቱ፥ ንቃ፤ ለምንስ ትተኛለህ? ተነሥ፥ ለዘወትርም አትጣለን። ²⁴ ለምንስ ፊትህን ትሰውራለህ? መከራችንንና ችግራችንንስ ለምን ትረሳለህ? ²⁵ ነፍሳችን በመሬት ላይ ተጐሳቍላለችና፥ ሆዳችንም ወደ ምድር ተጣብቃለችና። ²⁶ አቤቱ፥ ተነሥና እርዳን፥ ስለ ስምህም ተቤዠን። 🙏🙏🙏 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 @Finotetebebbb
Mostrar todo...
🙏 2
Photo unavailableShow in Telegram
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የተላለፈ ወቅታዊ መልዕክት። ጥንታዊት፣ ታሪካዊት፣ ብሔራዊትና ዓለም አቀፋዊት በሆነችው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥር ከሚገኙት ጥንታዊያን ገዳማት መካከል ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አንዱና ዋነኛው መሆኑ ይታወቃል። ይህ ጥንታዊና ታሪካዊ ገዳም በርካታ ቅርሶችና መናንያን የሚገኙበት ገዳም ሲሆን በተለያዩ ጊዜያት በተከሰተበት ዘረፋና ቃጠሎ ከባድ ጉዳቶችን ያስተናገደ መሆኑም ይታወሳል። በዛሬው ዕለት ከሀገረ ስብከቱ በደረሰን መረጃ መሰረትም፦ 1.  የገዳሙ መጋቢ አባተክለማርያም ዐሥራት 2.  የገዳሙ ጸሐፊ አባ ኪዳነ ማርያም ጥላሁን 3.  የገዳሙ የመጽሐፍ መምህርና ቀዳሽ አባ ገ/ማርያም አበበ 4.  በአመክሮ የሚኖሩ መናኝ ኃይለማርያም ወልደሰንበት የካቲት 12 ቀን "ኦነግ ሸኔ" በተባለው ታጣቂ ቡድን ከተወሰዱ በኋላ አራቱም በትላንትናው አለት የተገደሉ ሲሆን አባ ኪዳነማርያም ገ/ሰንበት የተባሉት አባት ቆስለው በገዳሙ እንደሚገኙ ታውቋል። በአሁኑ ሰዓትም ታጣቂዎቹ ወደ ገዳሙ ለመግባት እንቅስቃሴ የሚያደርጉበት መንገድ እንዳይኖርና መናንያኑና የገዳሙ ቅርስ አደጋ ላይ እንዳይወድቁ  የፌዴራልና የክልሉ የጸጥታ አካላት ገዳማዊያኑንና ገዳሙን የመታደግ ሥራ እንዲሠሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከአደራ ጭምር መልዕክቷን ታስተላልፋለች። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን    መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት            የካቲት ፲፬ቀኝ ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም                   አዲስ አበባ -ኢትዮጵያ 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 @Finotetebebbb
Mostrar todo...
💔 1
Photo unavailableShow in Telegram
19ነኛ ዓመት የምስረታ በዓል
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
💫10 ቀን ቀረው💫 ““የጥበብን መንገድ አስተማርሁህ፤ በቀናች ጎዳና መራሁህ።”   — ምሳሌ 4፥11 እንኳን ለፍኖተ ጥበብ ሰንበት ት/ቤት ፲፱ነኛ የምሥረታ ዓመት በዓል በሰላም  አደረሰን አደረሳቹሁ።       🌟ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ 🌟 የፍኖተ ጥበብ ሰ/ት/ቤት19ነኛ የምስረታ በዓል ከየካቲት 22_24 /2016 ዓ/ም ያከብራል ተጋባዥ መምህራን እና ዘማሪያን ይገኛሉ በመሆኑም እርሶም በእዚህ ጉባኤ ላይ ወዳጅ ዘመዶን በመጋበዝ  ቃለ እግዚአብሔርን እንዲማሩ  በእግዚአብሔር ስም ጠርተኖታል! 👉አርብ 10:30 ጀምሮ የመሃረነ አብ ጸሎት በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ 👉ቅዳሜ እና እሁድ 10:00-ጀምሮ የአውደ ምህረት ጉባኤ 👉 እሁድ 3:00 የደምልገሳ መርሐ ግብር በሰንበት ት/ት ቤት አዳራሽ ማስታወሻ መያዞን አይዘንጉ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን በመቀላቀለ ቤተሰብ ይሁኑ! የ telegram ገፅ✅ https://t.me/Finotetebebbb
Mostrar todo...
👍 1 1
💦🌟🌟እናታችን - ፍኖተ  ጥበብ     -🌟⭐️💦 የሕይወትን ቃል የሰማንባት - የተማርንባት፣ የመላእክትን ዝማሬ የቀመስንባት፣ ቅዱሳንን ያየንባት፣ እግዚአብሔር አምላካችንን ያወቅንባት፣ የእመቤታችንን ፍቅር የቀመስንባት፣ በድኅነት ጎዳና ላይ የተጓዝንባት፣ ኹላችን በአንድ የተሰባሰብንባት፣ ካደረግንላት በላይ እልፍ ያደረገችልን፣ መጠሪያ ስማችንና ክብራችን፣ ለማንነታችን ትርጉም የሰጠችልን፣ ሕጻናት በምስጋና የሚያድጉባት፣ ወጣንያን በትኅትና የሚያገለግሉባት፣ ጎልማሶች በኅብረት የሚመላለሱባት፣ ኹሉን በፍቅር ያስተሣሠረች፣ መሠረታችን፣ የማንደራደርባት ቤታችን፣ በዓለም እንዳንጠፋ መሸሸጊያችን፣ ከምንም በላይ በውብ እና ክቡር መጠሪያ “አገልጋይ” የተባልንባት፣ ብድራቷን ያልከፈልናት - ፍኖተ ጥበብ ! ስለሰንበት ትምህርት ቤቴ ያገባኛል የምትል ኹሉ ጥር 26  በሚደረገው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንድትታደም እናም እንድትመክር ተጠርተኻል!
Mostrar todo...
6.62 KB
👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
"ለነገዋ የቤተክርስቲያን ገጽታ የምትጨነቁ ከኾነ፤ ዛሬ የሰንበት ትምህርት ቤትን አገልግሎት በልባችኹ አኑሩ" ብፁዕ አቡነ ጎርጎሪዮስ ካልዕ "ወንድሜ ኾይ ሰንበት ትምህርት ቤታችንን ትወዳታለኽን? አንቺስ እህቴ ከምንም ከማንም በላይ ታስቢላታለሽን? ምላሻችኹ "አዎን" እንደኾነ ጥርጥር አይገባንም። 🙏🙏🙏 እንግዲያውስ ሰለ አገልግሎቷ መስፋት እና መሳካት ስለ አገልጋዩ ትጋት እና ሕይወት የምንመክርበት - ያለፈውን የምንከልስበት - ስለመጪው የምናቅድበት የሰንበት ትምህርት ቤታችን ጠቅላላ ጉባኤ የፊታችን እሑድ ጥር 26 ቀን 2016 ዓም ከጠዋቱ ሰዓት ጀምሮ ይከናወናልና የፍኖተ ጥበብ ጉዳይ የኔ ጉዳይ ነው የምትሉ ልጆቿ ኹሉ በሰንበት ትምህርት ቤቱ አዳራሽ እንድትገኙ ይኹን!
Mostrar todo...
👍 1
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.