cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ማራኪ ስነ-ፅሁፍ

በያላችሁበት ሰላማችሁ ይብዛ!!! ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ፡ በቻናላችን ማራኪ ፣ አዝናኝና ቁም ነገር የሚያስጨብጡ ስነ -ፅሁፎችን ፡ ከተለያዩ የስነ-ፅሁፍ ባለሙያዎች ወደ እናንተ ይዘን እንቀርባለን። https://t.me/+n3xAcsHqjJNlNDg0 ሀሳብና አስተያየት በ @Muke_ye ያድርሱን

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
657
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Repost from ከእኔ ጋር...
እስከመጨረሻው ይነበብ❗❗❗ ምንም ቃላት የማይገልፀው ጀግንነት ፣ የሀቂቃ ወንድማማችነትና መተሰሳብ በዚህ ታሪክ ላይ ይንፀባረቃል !!!! ----------------------- በካሊድ (ረዲየሏሁ ዓንሁ) የሚመራው እና በሰሀባዎች የተዋቀረው የጦር ሰራዊት በአውላላ ሜዳ ላይ በሮማውያን ወታደሮች ተከቧል። በዚህ ተስፋ አስቆራጭ ቅፅበት ላይ በመካ በረሃዎች ያደገው ዒክሪማ አስደንጋጭ ውሳኔ ወስኖ ሰይፉን ከወገቡ እየታጠቀ፦ «ለሞት ቃል ኪዳን ሚገባ ካለ ይከተለኝ» 400 የነብዬ ሙሐመድﷺ ጀግኖች 500,000 ሮማውያንን ሊፋለሙ ከዒክሪማ ጎን ተሰለፉ። የሙስሊሞቹ የጦር መሪ ካሊድ ዒክሪማን ሊከለክለው ጠጋ አለ። የጀግንነት ግርማው ከፊቱ የሚታየው ዒክሪማ፦ «ካሊድ ዞር በልልኝ ብዬኻለሁ! አንተ ለራስህ ከነቢ ጋ የብዙ ዘመቻ እድል ገጥሞኻል። በቀደመው ዘመን እኔ እና አባቴ ነቢን ﷺ ብዙ ተዋግተናቸዋል፤ ዛሬ ነፍሴን ሰውቼ ያጠፋሁትን ላካክስ። እኔ ከነቢ ﷺ ለመጋፈጥ ብዙ ዘመቻዎችን ተሳትፊያለሁ። ታድያ ዛሬ ሮም ከፊቴ ብትቆም እምፈራ ይመስልሃልን? ወላሂ አይሆንም» ወንድ ልጅ ወሰነ። 400 የሞት ባለሟሎች ከሜዳው የተሰለፉትን እልፍ አእላፍ ሮማውያንን ሊገጥሙ ተንደረደሩ። ኩነቱን ከዙፋኑ ላይ ሁኖ የሚከታተለው የሮሙ ጦር መሪ ተምዘግዛጊውን ዒክሪማ በቀስት እንዲመታ ትዕዛዝ አስተላለፈ። በጦር አዛዡ ትዕዛዝ በርካታ የቀስት ፍላፃዎች ወደ ዒክሪማ ይዘንቡ ጀመር። ከላይ ሚወነጨፉ ፍላፃዎች የዒክሪማን ፈረስ አደካክመው ጣሉት። ዒክሪማ ከወደቀው ፈረሱ ላይ ዘሎ ወረደ። በመጣበት ሞራላዊ ፍጥነት ለቅፅበት ሳያንገራግር ከፊቱ የተሰለፉትን ሮማውያን ሰልፍ እያተራመሰ ከመሀከላቸው ተከሰተ። በአላህ መንገድ የመዘዛትን ሰይፍ እየለካ የከሀዲያኑን አንገት እና ወገብ ይሰፍር ጀመር። ይህን ጀግንነት ከዳር ሁነው የሚመለከቱት ባለሟሎቹ የሞራል ስሜት ቢገፋቸው የአላህን ልቅና ከጦር ሜዳው እያስተጋቡ ትርምሱን ተቀላቀሉ። የአላህ ሰንደቅ ከፍ ብላ እንድትውለበለብ ዒክሪማ ገደለ፣ ተጋደለ...በመጨረሻም ለኩፋሮች ያቀመሳትን የሞት ፅዋ ቀምሶ ሸሂድ ሊሆን ከሜዳው ላይ ወደቀ። የወደቀው በወደቀበት ሲየቃስት፣ የሞተው ሬሳው በአቧራ ሲላወስ በፈረሶች ጩኸት የሚተራመሰው ጦር ሜዳ ገበያውን አድምቆታል። በዚህ መሀል የነቢ ﷺ መድረሳ ምሩቃኖች የጦር ሜዳውን በተክቢራት እያናወጡ የሮማውያኑን ሰራዊቶች ቁልቁል ያሳድዷቸው ጀመር። የነቢ ﷺ ሙሪዶች ድል ቀናቸው። ጦርነቱን አሸንፈው ሮምን በሀፍረት ካሳደዱ በኋላ የሸሂዶችን አፀደ ስጋ ለመሰብሰብ ከሜዳው ተበተኑ። ካሊድ በሜዳው ከተዘረሩት የሙታን ገላዎች የዒክሪማን እያፈላለገ ሲዘዋወር ድንገት ከሁለት የጀነት ሙሽሮች መሀል ተጋድሞ ሲጣጣር ደረሰ። ሀሪስ፣ ዒክሪማ እና ዐያሽ ከገላቸው ደም እየፈሰሰ የጀነት ማረፍያዎቻቸውን እየተጠባበቁ ነበር። የበረሀው ሀሩር ላንቃውን ያደረቀው ሀሪስ ከአሸዋ ላይ ተኝቶ እያጣጣረ ውሀ እንዲሰጠው ጠየቀ። ውሀውም ተቀድቶ ቀረበለት። ሀሪስ ውሀውን ሊጠጣ ከከንፈሩ ሲያስጠጋ ከጎኑ የተጋደመውን ዒክሪማን ተመለከተ፦«ውሀውን ለዒክሪማ ስጡት መጀመርያ» የወንድምነት ፋንታ ውሀው ወደ ዒክሪማ ተወሰደ። ዒክሪማ ውሀውን ሊጠጣ ቀና ሲል ከጎኑ የተጋደመውን ዐያሽን ተመለከተው። «ቀድማችሁ ዐያሽ ጋ ውሰዱ» ብሎ ውሀውን ሳይቀምስ መለሰው። ውሀው በመጨረሻም ከዐያሽ ዘንድ ደርሶ ሲሰጠው፦ «ውሀውን ቀድሞ ለጠየቃችሁ ወንድሜ ስጡት» ብሎ መለሰላቸው። ውሀዋ ተመልሳ ከሀሪስ ዘንድ ተወሰደች፤ ሀሪስ ሙቷል። ዳግም ከዒክሪማ ዘንድ መጣችለት ግና ሩሑ የለችም። ከዐያሽ ዘንድም ውሀዋ ስትወሰድ ዐያሽም ጓደኞቹን ተከትሎ ገላው ቀዝቅዟል። ረዲየላሁ ዐንሁም አጅመዒን _ ምንጭ፦ صور من حياة الصحاب -------------------- 👑 @mengeshaye 👑 👑 @mengeshaye 👑
Mostrar todo...
Repost from ከእኔ ጋር...
Photo unavailableShow in Telegram
አዝናኝ የሆኑ ወጎች
አነቃቂ ምክሮች
አስተማሪ ልቦለዶች
ግጥም
ታሪክ : ጨዋታ : ወጎች
👆 ይቀላቀሉን...👆
Repost from ከእኔ ጋር...
ያቺ ስስ ልቤ... አሁን አገኘች የ'ውነት ነፃነት! --------------------------------------- (ሙከረም ሙስጦፋ✍) ... ሰልቦብኝ ልቤን ፍጥኝ ጠፍንጎ አስሮ እንደ ፈቺ ጣፋጣ አስምጎ አስርቆ ወስዶ መስሎ አደላዳይ ለነብሴም ችሯት ነፃነት መሳይ አስወተወታት አልቻላት ሸምጋይ ዋለለች ያች ልብ ሆና ተላላ ካጥፊዋ ጎጆ ታየች ተዱላ ያቺ ስስ ልቤ ርቃ ብትጠልምም ውስጥ ውስጡን ሰርጋ ሰምጣ አልቀረችም ፈንቅላው ወጣች ጠልፎ አሳሪዋን ካ'ውሬ አስበርግጋ ወድቃ አልቀረችም አልነካት ክስረት ያች ስስ ልቤ አሁን አገኘች የ'ውነት ነፃነት ባንድ ስም ሰበብ ዳነች ከጥፋት ወዳጁን አይጥልም ፡ ሆኖ የልብ ወዳጅ ከሀይለኛው ጭንቁ ፡ ስቦ ቢያወጣ እንጅ እኔም ከስስ ልቤ ፡ ስሙን የነቀስሁት በምላሴም ስሙን ፡ ከወግ ያላመድሁት ካስቀረኝ አግቶ ፡ በውር ስደናበር ካጥፊዬ ሰወረኝ ፡ ጠበቀኝ ከአሽራር እዝነትን አላብሶ ሸለመን ጀሊሉ ብሎም ደነገገ ከስሙ ጋር ዋሉ ነውና ያ ስሙ...ﷺ ለጀነት ሁር የሚያጭ ክብረትን ሸላልሞ። ____ Like & share እያረጋቹ! 👑 @mengeshaye 👑 👑 @mengeshaye 👑
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
አይንህ ያየውን ሳይሆን ልብህ የወደደውን አፍቅር ...ሰዎች ምን ይሉኛል ብለህ ማሰብ የለብህም። ምክንያቱም ይህ ያንተ ፍቅር እንጂ የነሱ አይደለም። @maraki_lyrics @maraki_lyrics
Mostrar todo...
ስለሚጠቅሞ ያንብቡት አንድ ሴት በጣም የምትወደው የቤት እንስሳ አርጋ የምትንከባከበው አንድ እባብ ነበራት እርዝመቱ ወደ ሁለት መትርከግማሽ ይሆናል ከተወሰኑ ቀናቶች ጀምሮ ግን እባቡ ምግብ መመገብ ስላቆመ እንዲመገብ ብዙ ጥረት ብታደርግም ስላልተሳካላት ትጨነቅ እና ወደ እንስሳት ሃኪም ይዘው ትሄዳለች ከዛም የእንስሳት ሃኪሙ የተወሰነ ጥያቄዎችን መጠየቅ ጀመረ ከቅርብ ጊዜ ወዲ እባቡ እንዴት ነው የሚተኛው ሴቲቱም መለሰች ከመኝታዬ ስነቃ አንድ ቀን ከጎኔ ሙሉ በሙሉ ተዘርግቶ ተኝቶ አገኘውት ሌላ ቀን ደግሞ እራሱን በግርጌ እግሩን በራስጌ አድርጎ ዝርግት አድርጎ ተኝቶ አገኘውት ምኑም ስላልገባኝ ልረዳው አልቻልኩም ትላለች ሃኪሙም በጣም ከተገረመ በዋላ እሷ አደጋ ላይ እንደሆነች እና እባቡን ለእንስሳት ማረሚያ ጣቢያ እንድትሰጠው መከራት እባቡ መመገብ ያቆመው ሆዱን ባዶ ለማረግ እና ሆዱ ውስጥ ሰፊ ቦታ እንዲኖረው ለማድረግ ነው ከጎንሽ በተለያዩ አቅጣጫዎች ተኝቶ የምታገኚው አንቺን እንዴት አድርጎ እንደሚውጥሽ ልክሽን እየለካ ነው አላት ሁሉም ፍቅር ፍቅር አይደለም ሁሉም ጓደኝነት ጓደኝነት አይደለም ልዩነቱን እናስተውል ጠላት ወዳጅ መስሎ ሊቀርበን ይችላል ትህትና እርራሄ ሊያሳየን ይችላል ግን በጥንቃቄ እንመርምር ምክንያቱም ወዳጅ መስሎ ደካማ ጎናችንን እያየ እያጠና ወይም እንዴት አድርጎ ሊያጠፋን እንደሚችል በፍቅር ስም ጉርጓዳችንን እያመሠልን ሊሆን ይችላል እና የሚቀርባቹን ሰው መርምሩ በህይወት ትምህርት ውሰዱ አስደንጋጭ ቢሆንም አስተማሪ ታሪክ ስለሆነ ነው ያጋረዋቹ። ቀላል ይሆናል
Mostrar todo...
ተዋት አትለምኗት ትሂድ ካመረረች ካንተ መለየቱ ይሻለኛል ካለች ያሳለፍነዉ ፍቅር ትርጉሙ ካልገባት ስነግራት ካልሰማች እኔ እንደ ምወዳት መንገዱን በሙሉ ጨርቅ ያርግልሽ በሏት..... ዘከርያ✍
Mostrar todo...
እንደ አደይ አበባ ወራቷን ጠብቃ ለምትለዉ ብቅ ወራቶ ሲያበቃ ልጠፋኝ ልትርቅ ይገርማል ይቀንቃል የኔ መናፈቅ ልቤም የዋህ ነዉ የለዉም ክፋት ስትመጣ መቀበል ስትሄድ መሸኘት
Mostrar todo...
ክፍል አስራ አምስት (15) "ጤዛዉ ፍቅሬ" የመጨረሻዉ መጨረሻ (ኑዕማን ኢድሪስ) . .... ሆስፒታሉ በትራፊክ ፖሊሶችና ቆመዉ ክስተቱን በሚመለከቱ ሰዎች ተሞልቷል። ሁሉም ጭንቅላታቸዉን በሁለት እጃቸዉ ይዘዉ የተጎጂዉን መትረፉን ይሁን መሞቱን በጉጉት ይጠባበቃሉ። ... ከሰዎቹ መካከል ግን የፎዚያ የተለየ ነበር። ከዚያ ሁሉ ሰዎች ጉልበቷ ሀይሎ የድገተኛ ክፍሉን በር ገንጥላ ለመግባት ትታገላለች። እሷን ለመያዝና ለማረጋጋት የተወሰኑ ሰዎች እየታገሏት ነዉ። ከነዚያ ሰዎች መካከል ግን መኪያ የለችም። ለባሏ ጓደኛዉ ምን እንደሆነ ለመንገር ሀምዛ ወደተኛበት ጠባቧ ክፍል ሩጫ በቀረዉ ሶምሶማ ደረጃዉን ሽቅብ እየወጣች ነዉ። ባሏ ያለበት ክፍል ገብታ ጉዱን ልታረዳዉ ተቻኩላለች። ስትሮጥ እንኳ ምንም አልደከማትም። ክፍሏ ጋር እንደደረሰች የበሩን እጀታ ይዛ በሀይል ከፈተችዉ። ትንሽ እንቅልፍ ቢጤ ሸለብ አድርጎት በሰሰመን ዉስጥ የነበረዉ ሀምዛ የበሩን በሀይል አከፋፈት ሰምቶ ተዘግተዉ የነበሩ አይኖቹን ወደ በሩ በለጠጣቸዉ ። በሩን በሃይል ገፍታ ፤ ከፍታ የገባችዉ መኪያ ነበረች። ነገር ግን ስትለየዉ በሰላም የወጣችዉ መኪያ ሳትሆን ሁሉ ነገሯ ተቀያይሮ ፤ ድንጋጤና ፍራሃት ግንባሯ ላይ ሸንተር ሰርተዋል። ልቧ በአፏ ልትቀጣ ደርሳ ድዉ ድዉ ትላለች። በአይኗቿ እንባ እያዘነበች ነበር። .. " እህ እህ..." እያለች ልትናገር የፈለገችዉን ትንፍሿ ይዉጥባታል። ሀምዛ ጋደም ካለበት አልጋ ከወገቡ ቀና አለና ተቀምጦ... "መኪ ምን ሆነሽ ነዉ?" ብሎ የድንጋጤዉን ጮኸ። መኪያ እየተከታተለ የሚወጣዉን ትንፋሿን ገታ አድርጋ... "ሀቢብ ... ሀቢብ..." ስትለዉ የሀምዛ ፊት ባንዴ ተቀያየረ ፊቱን ቅጭም አድርጎ ..." ሀቢብ ምን ሆነ?" አላት። .... "የመኪና አደጋ ደርሶበት ... እዚህ" እያለች ጣቷን ወደኃላዋ እንደመቀሰር ስታደርግ ሀምዛ ከተኛበት አልጋ ላይ ምንጥቅ ብሎ ተነሳ። መኪያ ባለችበት እንደቆመች ክፍሉን ለቆ ወደ ድንገተኛ ክፍል በቸርኬዉ ተፈተለከ። መኪያም የባሏን በእግሩ መራመድ ሳታስተዉል ከኃላዉ ተከታትላዉ ሀቢብ ወደተኛበት ድንገተኛ ክፍል ተሯሯጡ። የሆስፒታሉን ደረጃ ተንደርድረዉ ወረዱት ከማለት ይልቅ ዘለዉ ባ'ንዴ ከሰዎቹ አጠገብ ደረሱ ማለት ይቀላል። ሀምዛ የእግሩን መጎዳት ረስቶት በሩጫ ከድንገተኛ ክፍል ሲደርስ የተሰበሰቡት ሰዎች የጸጥታ አዋጅ የታወጀ ይመስል ጸጥ ብለዋል። ከሰዎቹ መካከል ግን በሴቶች ተከባ ማልቀስ የምትችልበት ሀይል አጥታ አይኗ እንደፈጠጠ በደረቁ የምትንሰቀሰቅ ፤ ከናፍሮቿ ዉሃ ካገኙ ሳምንታት ያስቆጠሩ ይመስል ዝናብ ጥሎበት እንደደረቀ ዋልካ መሬን የተሰነጣጠቀባት ሴት ተመለከተ - ፎዚያ ነበረች። ... ሀምዛ ሰዉነቱን በሞላ ከዚህ በፊት ተሰምቶት የማያዉቅ የሀዘን ስሜት መላ አካላቱን ሲያዳርሰዉ ተሰማዉ። ፎዚን በተቀመጠችበት አለፍ አለና ወደ ድንገተኛ ክፍሉ ተጠግቶ በመስተዋት የተገጠመዉን በር ወደ ዉስጥ ያሳየዉ ዘንድ አይኖቹን ቀረብ አድርጎ ሲመለከት በነጭ ጨርቅ መላ አካላቱ የተሸፈነ አስክሬን ተመለከተ። - ሀቢብ ስለመሆኑ አልተጠራጠረም። ምንም እንኳ ሁሉም አካሉ የተሸፈነ ቢሆንም ቁመቱ ሀቢብ መሆኑን ይናገራል። "ሞቷል?" ሲል ከአንደበቱ ቃል አወጣ። አጠገቡ ቆሞ የነበረ አንድ ሰዉ እሱን የጠየቀዉ መስሎት "አዎ ሞቷል" ብሎ መለሰለት። ሰማይ ፤ ምድሩ የተቀላቀሉበት መሰለዉ። አይኑ ፍጥጥ ፤ ደሙ ቀጥ አለበት። የስንት ጊዜ ጓደኛዉ ፤ ክፉ ደጉን አብረዉ ያሳለፉ ፤ ደስታንና ሀዘንን በጋራ አብረዉ የወጡት ፤ እንደ'ራሱ የሚወደዉ ጓደኛዉ እሱን ለመጠየቅ ወደ ሆስፒታል ሲመጣ መንገድ ላይ ቀረ። ላይመለስ ምድርን ተሰናበተ። . .... ፎዚያ ትእግስት አሳጥቷታል። የህይወት አጋሯ ፤ ከራሷ አስበልጣ የምትወደዉ ሀቢብ ሞቷል። ሳትወድ በግዷ አምና ተቀብላለች። ከዚህ በኃላ ሀቢብን በድጋሜ አታገኘዉም። ፍቅሯ እንደ ጧት ጤዛ ሆኖ ቀረ። ያ እንክብካቤና ደስታ በጅምር ቀረ። ዉስጧ ተብሰከሰከ ፤ ያ የዉበት ጸዳል የሆነዉ ፊቷ ሀዘን የሚባል መጥሮ ነገር ፤ ሞት የሚባል የማይለመድ ክስተት ጥላዉን አጥልተዉበት ከጥቀርሻም በላይ ጠቆረ። እንደ ማለዳ ወፍ ዜማዎች የሚያምረዉ ድምጿ ተኩረፈረፈ ፤ ልሳኗ ተዘጋ። ሀቢብን በስስት የምታይበት አይኖቿ .. በርበሬ የተቦካበት ሙሃቻ ይመስል ቀይ ሆነ። ... ... በዚህ ምድር እጅግ ከባዱ ነገር የሚወዱትን ሰዉ መለየት ነዉ። ፎዚያ ግን ያን ሁሉ የችግር ወቅት ከሀቢብ ላለመለየት ታግሳና ችላ ኖራ ነበር። የሰቆቃዉ ህይወት አልፎ የደስታዉ ዘመን ሲመጣ ደስታዋን የሚያጠፋ ፤ ፍቅሯን የሚያከስም ነገር ተፈጠረ።... ሀቢብ ሞተ!!! . . . ... የሀቢብ የቀብር ስነ ስርአት ከተፈጸመ ዛሬ ሦስተኛ ቀኑን አስቆጠረ። ፎዚያ ሊያስተዛዝኗት በሚመጡ ሰዎች ተከባለች። ሁሉም 'አብሽሪ' ይሏታል። ሞት በሁሉም ሰዉ ላይ ያለ ነዉ። እኛም ተራችንን ጠባቂዎች እንጂ ይህችን ምድር ለዝንታለም አንኖርባትም። አድርን የማንዉልባት ፤ ዉለን የማናድርበት ጠፊ አለም ናት!። እያሉ ይመክሯታል። እሷ እንደሆነ ሀቢብን ብቻ ሳይሆን ፍቅሯንም ከባሏ ጋር አብራ ቀብረዋለች። አንድ ቀን በትክክል ያጣጣመችዉን ፍቅር በድጋሜ ሳታገኘዉ መንገድ ላይ ቀርቶባል። የሚደፈያስተዛዝኗት ሰዎች ያወራሉ እንጂ እሷ ሀሳቧ ሁሉ ከሟች ባሏ ጋር ነዉ። . . ... ሀምዛና መኪያ ከአንድ ጥግ ተቀምጠዉ ፎዚያን አሻግረዉ ይመለከቷታል። ዉበቷ ሀያ አራት በሙሉ እንደ ጨረቃ ሲያበራ የነበረችዉ ፎዚ ሳትሆን ሀዘን እንዳይሆኑ አድርጓታል። ሀምዛ ወደ ፎዚያ ተጠግቶ ሊያስተዛዝናት ፤ ሊያጽናናት ድፍረቱን አጣ። እሷ ዘንድ ሂዶ ስለ ሀቢብ አንስቶ 'አብሽሪ' ቢላት ሁለታቸዉም አይኖቻቸዉ በእንባ እንደሚሞሉና ትዕግስት እንደሚያጡ ዉስጡ ነግሮታል። በተቀመጠበት ሆኖ አሻግሮ እያያት ስለ'ሷ የወደፊት ህይወት 'ብቸኝነትና ሀዘን' እንደሚበረታባት ሲያስብ እንዴት አድርጎ ሊረዳት እንደሚችል ማስተንተን ጀመረ። ... የሱ ህይወት አያስጨንቀዉም። ምክንያቱም ቤቱ በደስታና በፍቅር የተሞላ ነዉ። እግሩም ቢሆን ደህና ነዉ። ለተወሰነ ጊዜ ክራንች ተጠቅሞ ይበልጥ ደህና ሲሆን የእስከዛሬዉን ሙሉዉን ሀምዛ እንደሚሆን ተነግሮታል ~ አልሐምዱሊላህ!!። አሁን የሚያስጨንቀዉ ጉዳይ የፎዚያ ነዉ። ስለሷ ያስባል... ያስባል.... 'ብቸኝነቷን እንዴት እንደሚያስወግድላት ፤ ከዚህ በኃላ እንዴት ደስተኛ እንደምትሆን እያሰላሰለ በሃሳብ ነጉዷል።... ጭል.....ጥ ብሏል።.....። በዚህ መሃል መኪያ ዘወር ብላ ስታየዉ ትካዜ ዉስጥ እንደሆነ አስተዋለች። ... "ሀምዚ .. ሀምዚ የነሰ..." ብላ ጠራችዉ። ... "ወይዬ መኪዬ.." ሲል መለሰላት። ... "ምን እያሰብክ ነዉ?" ብላ ከአይኖቹ ስለምን እንደሚያስብ ታዉቅ ይመስል ትክ ብላ አየችዉ። ... "መኪዬ የፎዚ የወደፊት ሁኔታ ግን አላሰሳሰበሽም?" ብሎ መልሶ እሷኑ ጠየቃት። መኪያም ስለፎዚያ ሁኔታ እያሰበች ነበር። ነገር ግን መፍትሄ ሳታገኝ ቀርታ ዝምታን መርጣ ነበር። ... "እኔምኮ አስቤዉ ነበር ሀቢቢ?" አለችዉ። ... "ብቸኝነት እንዳይሰማትና ደስታ እንዳይርቃት ምን እናድርግ የኔ ቆንጆ?" እያለ መፍትሄ ትነገረዉ ዘንድ በአይኖቹም ጭምር ተማጸናት። መኪያ ዝም አለች። ሀምዛም የሚስቱን አይን አይኗን እያየ ዝም ብሎ ከሷ መልስ ይጠባበቅ ጀመር።... በመካከላቸዉ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ዝምታ ከሰፈነ በኃላ መኪያ በሷና በሀምዛ አጠገብ የሚያወሩትን ፤ የሚነጋገሩትን የሚሰማቸዉ ሰዉ አለመኖሩን ካረጋገጠች በኃላ
Mostrar todo...
ወደ'ሱ ጠጋ አለች። ... "ሀምዚ... ፎዚን ግን ለምን አታገባትም?" ስትለዉ ሀምዛ ጆሮዉን ማመን አቅቶት በመቅጽበት ወደ'ሷ ዘወር ብሎ..."ምንንን?" አላት። ... በዚህ መካከል አንድ የሰፈሩ ሽማግሌ ጮኽ ብለዉ መናገር ጀመሩ። ... ".... ልጆቼ ነገ በአኼራ ሰዉ ከሚወደዉ ሰዉ ጋር ነዉ የሚቀሰቀሰዉ። እናም ፎዚያ ልጄ! ... አላህ እናንተን ለዘላለም ላትለያዩ በጀነት ሊያኖራችሁ ይችላል። ለሱም ቢሆን ዱዓ ብታደርጊለት እንጂ ለቅሶና ሀዘን አይበጀዉም። ..." እያሉ ብዙ ከመከሯቸዉ በኃላ ንግግራቸዉን ጨረሱ የፎዚያ ፍቅርም ልክ እንደ ጧት ጤዛ በጅምር ቀረ ... የኔ ጽሁፍም በዚሁ ተቋጨ..... ሼር♻️ ላይክ👍 ያድርጉ ❤️ @maraki_lyrics ❤️ ❤️ @maraki_lyrics ❤️
Mostrar todo...
ወደ'ሱ ጠጋ አለች። ... "ሀምዚ... ፎዚን ግን ለምን አታገባትም?" ስትለዉ ሀምዛ ጆሮዉን ማመን አቅቶት በመቅጽበት ወደ'ሷ ዘወር ብሎ..."ምንንን?" አላት። ... በዚህ መካከል አንድ የሰፈሩ ሽማግሌ ጮኽ ብለዉ መናገር ጀመሩ። ... ".... ልጆቼ ነገ በአኼራ ሰዉ ከሚወደዉ ሰዉ ጋር ነዉ የሚቀሰቀሰዉ። እናም ፎዚያ ልጄ! ... አላህ እናንተን ለዘላለም ላትለያዩ በጀነት ሊያኖራችሁ ይችላል። ለሱም ቢሆን ዱዓ ብታደርጊለት እንጂ ለቅሶና ሀዘን አይበጀዉም። ..." እያሉ ብዙ ከመከሯቸዉ በኃላ ንግግራቸዉን ጨረሱ የፎዚያ ፍቅርም ልክ እንደ ጧት ጤዛ በጅምር ቀረ ... የኔ ጽሁፍም በዚሁ ተቋጨ..... ሼር♻️ ላይክ👍 ያድርጉ ❤️ @Yefkrtarik ❤️ ❤️ @Yefkrtarik ❤️
Mostrar todo...