cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

#ጥበብ

'የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሄርን መፍራት ነው'

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
158
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ፍልስፍና በፈላስፎች እይታ (፩) 📖📜📜📜📖 "ፍልስፍና ምንድነው?" የሚለው ጥያቄ በርካታ ፈላስፋዎችን በልዩነት ያፈላሰፈ ጉዳይ ነው። ይሁን እንጂ ሁሉም ፈላስፋዎች በፍልስፍና ባህሪ ላይ የሰጡት ትርጉም ሰፊ ልዩነት ያለው ነው። ፧ ለምሳሌ ፦ ❇️ ለሶቅራጥስ ፍልስፍና የነፍስ ማንነትን ለመኖር ስጋን መግደል ማለት ነው። በሶቅራጥስ ሌላ ትርጉም አለማወቅን ማወቅ ፍልስፍና ነው። ❇️ የፕሌቶ ፍልስፍና ትርጉም ከስሜት ደረጃ የዘለለ የነፍስ እውነታ ለመረዳት የሚያስችል የሁለተኛ ደረጃ ግንዛቤ ነው። ❇️ ለአርስቶትል ፍልስፍና የሁሉም ጥናቶች አባት የሆነ ጥቅል ሳይንስ ነው። በሌላኛው ትርጉሙ አርስቶትል ፍልስፍናን ሲገልፀው የመገረም ወይም የመደነቅ ስሜት የሚፈጥረው የማወቅ ጉጉት ማለት ነው። ❇️ ፍልስፍና ለካርል ማርክስ የለውጥ ሂደት ነው። ፧ በአጠቃላይ በፍስፍና ባህሪ ላይ የተሰጡት ትርጉሞች በስፋትም በልዩነትም ሊታዩ የሚችሉ ቢሆንም በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል ። አንደኛው የትርጉም አማራጭ ፍልስፍናን በራሱ እውቅት አድርጎ የሚወሰድ ሲሆን፤ ሁለተኛው ትርጉም አማራጭ ፍልስፍናን እውቀት ሳይሆን የእውቀት መንገድ አድርጎ የሚወሰድው ነው። 📜📜📜 📖 የመጀመሪያው የትርጉም አማራጭ በማንኛውም ጉዳይ ላይ በማንኛውም መልኩ የሚፈጠር አስተሳሰብ በራሱ ፍልስፍና አድርጎ የሚወሰድ ነው። ይህ ትርጉም አጠቃላይ የአለማትን እውነት አሳብና ስሜት አዋቅሮ በማንኛውም የአስተሳሰብ ቅርፅ መፍጠርን መሰረት የሚያደርግ ስነ ኑባራያዊ ውክልና (Metaphysical make up) ግንባታ ላይ የሚያተኩር ነው። ፧ ለምሳሌ ፦ መሬት ክብ ናት ወይም መሬት ጠፍጣፋ ናት የሚለው የመሬትን እውነታ በአስተሳሰብ የመወከል ጉዳይ በመሆኑ ይህ በራሱ ፍልስፍና እንደሆነ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። 📜📜📜 📖 በሁለተኛው የትርጉም አማራጭ ፍልስፍና በራሱ አስተሳሰብ ሳይሆን አስተሳሰብ የመፍጠር ሂደት ነው። በዚህ መሰረት መሬት ክብ ናት የሚለው አሳብ በራሱ አስተሳሰብ ሳይሆን የማሰብ ሂደት ነው። በዚህ መልኩ የሚወሰደው የፍልስፍና ትርጉም ፍልስፍና ማለት ማወቅ ሳይሆን የማወቅ ሂደት፣ አስተሳሰብ ሳይሆን የማሰብ ሂደት፣ ጥበብ ሳይሆን የጥበብ መንገድ እና የመሳሰሉትን የመጠየቅና ምላሽ የመፈለግ፣ የመጠራጠር ወዘተ ሂደቶችን የሚያመላክት እንደሆነ ሊወሰድ ይችላል። ... ይቀጥላል... ምንጭ ፦ ኢትዮጵያዊው ኦሾ ፌስቡክ ገጽ እንዲሁም " የፍልስፍና አጽናፍ " መጽሐፍ @abrhott @abrhott @abrhott
Mostrar todo...
#ሳይኮሎጂ እንደሚለው ሴቶች በተሻለ መንገድ ያጭበረብራሉ እንዲሁም ምክንያቶች አላቸው (ወንዶች ዝም ብለው ያደርጉታል እና ሲያዙ ሊያብራሩት አይችሉም)
Mostrar todo...
ሁለት እግርም እያለህ ; ሚዛንህንም የሚጠብቅልህ ሰረሰርጌ አንጎልህም ጤነኛ ሆኖ እያለ መሬትም የተሰራችበትን ቅርፅ ሳትለውጥ ተንበርክከህ የምትሄድበት ግዜ ይመጣልና ክፉ አታስብ ክፉ አትዝራ ክፉም አታድርግ ።ሰርቶ ዘርቶ ለበለጠህ አድንቅ እንጅ አትመቅኘው የዋህነትን ገዝተህም ቢሆን የአንተ አድርግው ።ተኝተህ እንኳን እንቅልፍ ካጣህ ፀልይ ከህሊናህ የበታችነትን ስሜት አርቅ ምቀኛ ህሊናም ካለህ ተው ራስህን ግዛ ።ገንዘብህ እና አልጋህ ሳይሆን እረፍት የሚሰጥህ የሰራህ ፈጣሪ መሆኑን እመን ለተደረገልህ ሁሉ አመስጋኝ ሁን ባትሰጥ እንኳን የተቸገረ ሰው ስታይ የሚያዝን ልብ ይኑርህ።ስንፍናና ምቀኝነት ካለብህ ራስህ የራስህን መቃብር እየቆፈርክ መሆኑን እመን የደስታ ዘመንህን በንሰሃ ግዛ ደስታህን በራስህ ፊት ላይ ሳይሆን ሰዎች በሆነላቸው ስኬት ላይ ፈልገው። በቀጭኑ መንገድ ተንበርክከህ ካለፍክ በሰፊው ጎዳና ቆመህም ጨፍነህም ማለፍህ አይቀርም።ዳር የሚያደርስህ መንገዱ ሳይሆን ከቅዠት በላይ ያለምከው ህልምህ ነው። Make your self very Optimistic person in you lifetime through!!! Super star karate Dojo & Gym...
Mostrar todo...
Mostrar todo...
Mostrar todo...
The best you try The best you get #Joel..
Mostrar todo...
#Morning_Motivation! መልካም ጓደኛ! ▸ የጓደኛህን ስሜት ለመራዳት ሞክር፣ ▸ መልካም የሆነውን ነገሩን አውጣለት፣ ▸ አበረታታው፣ ▸ እንደማይጠቅም አትንገረው፣ ▸ ለሀዘኑ ሳይሆን ለደስታው ምክንያት ሁን፣ ▸ ለስኬቱ እንጂ ለውድቀቱ መንስኤ አትሁን፣ ▸ መልካም ጓደኛ፦ የማይቀና አሳቢና መካሪ፣ ከእኔ ይልቅ ለአንተ የሚል ካለህ አንተ ታድለሃል። ከሌለህ ደግሞ አንተ ራስህ መልካም በመሆን ጀምር፣ ባህሪህንና ስራህን አይተው ይመጣሉ። 🔹''ዙሪያህን አዎንታዊ ነገሮችን በሚያስቡ፣ በሚናገሩ እና በሚያደርጉ እልፎም በሚደግፉህ እና መልካም አስተዋጽዖን በሚያበረክቱልህ ሰዎች ክበበው፡፡ አንተም ለእነሱ ተመሳሳይ ነገር ማድረግ እንዳትዘነጋ፡፡'' በመልካም ሀሳብ የምንሞላበት ብሩህ ቀን ይሁንልን!🙏 ❤️Join our channel and share kindly👇👇👇 @r15b5l @r15b5l @r15b5l! @r15b5l @r15b5l @r15b5l
Mostrar todo...
ከሰነፍ ደስታ የጠቢብ ሀዘን ይበልጣል <<...አንድ ቀን ከአንዲት አሮጊት ጋር ወግ ስንቀልስ ነፍሷ ከምና ከማን እንደተሰራ አለማወቃ ያስጨንቃት እንደሆነ ጠየኳት። አሮጊቷ ግን በጥያቄዬ ፍፁም ግራ ተጋባች>> ይላል መልካሙ ሕንዳዊ። ቮልቴር ሲነግረን መልካሙ ሕንዳዊ እድሜ ዘመኑን የተጨነቀለትን የነፍስ ጥያቄ ይኸቺ አሮጊት ግን በረዥም የእድሜ ዘመኗ ውስጥ ለአፍታ አስባው አታውቅም። ለአሮጊቷ ነፍሷ በእግዚያብሄር የተፈጠረችና በማለዳው የምትጠጣው ውሃም መባረክን እያገኘች በእድሜ ዘመኗ መጨረሻ ደግሞ የገነትም ወራሽ ሆና እንደምትገባ በማሰብ ደስተኛ ነበረች። ቮልቴር መልካሙን ሕንዳዊ ይጠይቀዋል። <<ታዲያ ከመኖሪያ ብዙም ያልራቀች አሮጊት አንተ የእድሜህ ዘመንህን የተጨነቅህለትን ጥያቄ ለአፍታም አስባው አለማወቋና ነገር ግን በዘመኗ ሁሉ ደስተኛ መሆኗ አላናደደህም?>>¶ አለው። መልካሙን ሕንዳዊም፦ <<ትክክል ነህ! ለራሴ ደጋግሜ የነገርኩት ነገር እንደዚህች አሮጊት ደስተኛ መሆን አለብኝ በማለት ነበር። ነገር ግን የምሻው ደስተኛነቷን እንጂ አላዋቂነቷን አልነበረም። ስለዚህም ከሰነፍ ደስታ፣ የጠቢብ ሐዘን ይበልጣል በማለት ተጽናናሁ ሲል መለሰለት።...>> ✍️ጥበብ_ከጲላጦስ /ገፅ 454 መልካም የሆነው ሁሉ ተመኘን🙏 ❤️Join our channel and share kindly👇👇👇 @r15b5l @r15b5l @r15b5l! @r15b5l @r15b5l @r15b5l
Mostrar todo...
በመጽሐፉ የውስጥ ገጽ እንዲህ ይለናል! “እኛ ሰዎች ድንቅ ሆነን የተፈጠርነው፣ ድንቅ ሆነን በመገኘት፣ ድንቅ ሕይወት ለመኖር ነው። ታድያ ለምንድን ነው ብዙ ሰው ድንቅ ማንነቱን ትቶ፣ ተራ ሆኖ በመገኘት ተራ ሕይወት የሚኖረው? ምክንያቱም ተራ መሆን በጣም ቀላል ስለሆነ ነው። ድንቅ መሆን ቀላል ነገር አይደለም፤ በነጻም አይገኝም፤ ዋጋ ያስከፍላል፤ መሥዋትነትም ይጠይቃል። ተራ ሰው ልክ እንደ ድንቅ ሰው ሁሉ ድንቅ ሕይወት መኖር ይፈልጋል። ነገር ግን ለድንቅነት የሚከፈለውን ዋጋ መክፈል አይፈልግም። ተራ ሰው፣ ድንቅ መሆን ይጀምራል፤ ከዚያም ትንሽ ከበድ ሲለው፣ ተስፋ ይቆርጣል፤ ወደ ተራ ሕይወቱም ይመለሳል። “እንዴት አድርገህ ነው ሙሉ በሙሉ ራስህን ልትቀይር የምትችለው? ''ራሴን መቀየር አለብኝ” ብለህ ስታስብ፣ “ምንህ እንዲቀየር ነው የምትጠብቀው? ምንህስ ነው መቀየር ያለበት? የሰው ልጅ ማን ነው? ምንድንስ ነው? በምንና እንዴት ነው የሚሠራው? ራስን ለመቀየር መቀየር የሚያስፈልገው ነገር ምንድን ነው?” ⬆️እነዚህን ጥያቄዎች በትክክል መመለስ ስትችል፣ ራስህን እንዴት አድርገህ መቀየር እንደምትችል በቀላሉ መረዳት ትችላለህ።“ የዳዊት ድሪምስ “ ትልቅ ሕልም አለኝ “ መፅሐፍ ላይ የተቀነጨበ... ውብ አዳር ተመኘን🙏 ይቀላቀሉ👇👇 @r15b5l @r15b5l @r15b5l
Mostrar todo...
ኃይል (ስልጣን) እና ራስን መግዛት “የመጨረሻው ሰው ለማግኘት ሊጣጣር የሚገባው ኃይል (ስልጣን) ራስን የመግዛት ኃይል (ስልጣን) ሊሆን ይገባዋል” - Elie Weisel “ሌሎችን መግዛት ጥንካሬ ነው፣ ራስን መግዛት ግን እውነተኛ ኃይል ነው” ይላል የሰነበተ የሩቅ ምስራቆች አባባል፡፡ ሰው ሰፊ ቤተሰብ፣ ግዙፍ ድርጅት፣ ከዚያም አልፎ አገር እያስተዳደረ ራሱን በቅጡ ላያስተዳድር ይችላል፡፡ ቤተሰብ ለማስተዳደር ምናልባት በቂ ገንዘብን ማቅረብ ሊጠይቅ ይችላል (ሁኔታውን በዚያ ጎኑ ብቻ ለማየት ከወሰንን)፡፡ ድርጅትና ሃገርን ማስተዳደር ምናልባት እውቀትንና ሹመትን ይጠይቅ ይሆናል፡፡ ራስን ለማስተዳደር ግን ይህ ነው የማይባል ዲሲፕሊን ይጠይቃል፡፡ ባለህ ገንዘብ ሰዎችን ስታስተዳድር በአንተ ላይ የተደገፉትን ሰዎች ለተወሰነ ጊዜ ታኖራቸዋለህ፡፡ በጨዋነትህና በዲሲፕሊንህ ራስህን ስታስተዳድር ግን ለራስህም ሆነ ለእነሱ ለረጅም ጊዜ ትኖራለህ፡፡ ባካበትከው ገንዘብ፣ በቀሰምከው እውቀትም ሆነ በሌሎች ነገሮች አማካኝነት በእጅህ በገባው ኃይልና ስልጣን ተጠቅመህ ትክክለኛውን ነገር ማድረግ የምትችለው፣ በአካባቢህ የሚገኙትን ሰዎችን ባለህ ኃይለኛነት ተጠቅመህ አንቀጥቅጠህ ስለገዛሃቸው ሳይሆን ራስህን በመግዛት ለእውነት ስትኖር ነው፡፡ የአንድ ሕብረተሰብ ውድቀት የሚጀምረው ኃይልና ስልጣንን ከዚህ ከዚያ ብለው እጃቸው ካስገቡ በኋላ የራስን አጀንዳና ለማራመድና ሰውን ለመጨፍለቅ የሚጠቀሙ ሰዎች ሲበራከቱ ነው፡፡ እደ እውነቱ ከሆነ፣ “ኃይል የሚያስፈልግህ ሰዎችን የሚጎዳ ነገር ለማድረግ ስትፈልግ ብቻ ነው፡፡ አለዚያ፣ ማንኛውንም ነገር ለማከናወን ፍቅር በቂ ነው” – Charles Chaplin 📓🙏 ❤️Join our channel and share kindly👇👇👇 @r15b5l @r15b5l @r15b5l!!!!
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.