cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Christ Exalting Channel

We exalt the exalted Christ. "Wherefore God also hath highly exalted him, and given him a name which is above every name:" (Philippians 2:9) Contact us @Amwaitingrupture

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
189
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

እውነተኛ ነጻነት። True Liberty በማን?
Mostrar todo...
9.51 KB
Mostrar todo...
Hojiin Harka Waaqayyoo... - Gospel Singer Solomon Adugna | By Gospel...

60K views, 5.6K likes, 367 loves, 275 comments, 708 shares, Facebook Watch Videos from Gospel Singer Solomon Adugna: Hojiin Harka Waaqayyoo Dinqiidha! የእግዚአብሔር እጅ ስራ ድንቅ ነው።

ታላቁ ሃይል🎇
Mostrar todo...
1.26 MB
Repost from Artios Media
💎💎💎 💎 ⒶⓇⓉⒾⓄⓈ 💎 💎💎💎 💎💎💎 💎 ⒶⓇⓉⒾⓄⓈ 💎 💎💎💎 Artios Devotion ⒺⓅⒽⒺⓈⒾⒶⓃⓈ ⒹⒶⓎ #2 አስቀድሞ መርጦናል የኤፌሶን መልዕክት 1:4-6 =================================== "በፊቱ ቅዱሳንና ነውር አልባ እንድንሆን ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ በእርሱ መርጦናልና። በፍቅር፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ልጆቹ እንሆን ዘንድ፣ እንደ በጎ ፈቃዱ አስቀድሞ ወሰነን፤ ይኸውም፣ በሚወደው በእርሱ በኩል በነጻ የተሰጠን ክቡር የሆነው ጸጋው እንዲመሰገን ነው።" =================================== ሐዋርያው ጳውሎስ በእነዚህ ቁጥሮች ላይ በቁ.3 ላይ የተናገረውን መንፈሳዊ በረከት መነሻና ዓላማ ያሳያል። የበረከቱ እቅድና ዝግጅት ጅማሬው ምድር ሳይሆን ሰማይ እንደሆ ጊዜውንም ደግሞ አሁን ሳይሆን ከፍጥረት በፊት እንደነበር ይናገራል። እግዚአብሔር በራሱ ሉዐላዊነት በክርስቶስ በማመን ብቻ የሚገኘውን ድነት የሚቀበሉ ቅዱሳንን አስቀድሞ መወሰኑንና መምረጡን፣ ጊዜው ሲደርስ ደግሞ አስቦት የነበረውን እቅድ መተግበሩን ያሳያል። አስቀድሞ ወስኖ መረጠን የሚሉ ቃላት ድነታችን በእግዚአብሔር ሉዓላዊ ምርጫና ቸርነት ላይ የተጠነሰሰና የቤዛነት ፕሮግራም ጀማሪና ተቆጣጣሪ እርሱ ራሱ መሆኑንን አጉልቶ የሚያሳይ ነው። ይህ ሲባል ከሰው የሚጠበቅ አንዳች ነገር የለም ማለታችን ግን አይደለም። ሰው ይህንን ትልቅ ግብዣ አውቆ፣ ፍቃዱን ተጠቅሞ በእምነት ተቀብሎ እያመሰገነ መኖር አለበት። ድነት ሰው ነጻ ፍቃዱን ተጠቅሞ በክርስቶስ ሥራ ሲያምን የሚያገኘው ሕይወት ነው ወይስ የእግዚአብሔር ሉዓላዊ ምርጫ አካል ተደርጎ አስቀድሞ የተመረጡ ሰዎች ብቻ የሚታደሉት ሲሳይ ነው? የሚለው ጥያቄ የሥነ መለኮት አጥኚዎች በየዘመናቱ የተለያየ ጎራ ፈጥረው የሚከራከሩበት ጉዳይ ነው። ክቡር የሆነው ፀጋ እንዲመሰገን ታስቦ የተሠጠውን የዘላለም ሕይወት አውርደው ቋሚ የመከራከሪያ ርዕስ በማድረግ በተገናኙ ቁጥር በዚያ የሚበሻሸቁ አማኞችን ሳይ አዝናለሁ። በእኔ እምነት ቃሉም የሚለው ድነቱ በትክክል የገባው ሰው ጎራ ፈጥሮ፤ የሙግትና የክርክር ችሎት ሰይሞ የሚቧቀስበት ጊዜ አይኖረውም። ስለ መዳን ሲታሰብ ክርክርና ሙግት ሳይሆን ምስጋናና አምልኮ ነው ከአማኙ ሕይወት ውስጥ የሚፍለቀለቀው። እግዚአብሔር ድነትን ሲሰጠኝ ምርምር የምሰራበትን ርዕስ ሳይሆን መቼም ተዋኝቶ በማያልቅ የምስጋና ባህር ውስጥ እንዳስገባኝ ነው የማስበው። 🛃 ዛሬ የማሰላስለው የቃሉ እውነት፦ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት የድነቴ ፕሮግራም ተነድፎ ነበር! 🅿️ የዛሬው ፀሎቴ፦ "ጌታ ሆይ መመረጤንና መዳኔን እያሰብኩ ሁሌም በአምልኮና በውዳሴ በፊትህ የምሆን አመስጋኝ ሰው አድርገኝ" ነገ እስከምንገናኝ ደህና ሁኑ!! 🖋 ባይሣ ገመቹ ሰኔ 11, 2014 💎💎💎💎 ⒶⓇⓉⒾⓄⓈ 💎💎💎💎 💎💎💎💎 ⒶⓇⓉⒾⓄⓈ 💎💎💎💎 🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔻 @artios_media @artios_media @artios_media
Mostrar todo...
Repost from Artios Media
💎💎💎 💎 ⒶⓇⓉⒾⓄⓈ 💎 💎💎💎 💎💎💎 💎 ⒶⓇⓉⒾⓄⓈ 💎 💎💎💎 Artios Devotion ⒺⓅⒽⒺⓈⒾⒶⓃⓈ ⒹⒶⓎ #1 የባረከን ይባረክ የኤፌሶን መልዕክት 1:1-3 ==================================== "በእግዚአብሔር ፈቃድ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስ፤ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉ፣ ለታመኑ፣ በኤፌሶን ለሚገኙ ቅዱሳን፤ ከእግዚአብሔር ከአባታችን፣ ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ በክርስቶስ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ"። ==================================== የደብዳቤው መግቢያ እንደ መሆኑ መጠን በእነዚህ የመጀመሪያዎቹ ቁጥሮች ውስጥ የጻፊውን ማንነት፣ ተደራሲያኑንና የመልዕክቱን ቁልፍ ሃሳብ እናገኛለን። የዚህ መልዕክት ጸሐፊ ሐዋርያው ጳውሎስ መሆኑን እራሱ በቁ.1 ላይ በግልጽ አስቀምጦታል። ከጥንት ጀምሮ በደብዳቤው ደራሲ ማንነት ላይ ጥያቄ ባይነሳም ሁሉን ነገር ካልተቃወማችሁ የተባሉ ይመስል መቧጨር ልማዳቸው የሆነ አንዳንድ ዘመነኛ የሥነ መለኮት ምሁራን እንደ ለመዱት እርሱ አይደለም ቢሉም ውሃ የሚቋጥር ምክንያት ግን ማቅረብ አልቻሉም። ጳውሎስ በሌሎች ደብዳቤዎች ሁሉ እንደሚያደርገው እራሱን ሐዋርያ ብሎ ይጠራል። ሐዋሪያ ማለት ቀጥተኛ ትርጉሙ የተላከ ማለት ሲሆን ጳውሎስ ይህን ስያሜ የሚጠቀመው የራሱን ሹመት ለማጉላት ሳይሆን የመልዕክቱን እውነተኛነት፣ ተዓማኒነትና ከጌታ የተቀበለው መሆኑን ለመግጽ ነው። የመልዕክቱ ተደራሲያን በኤፌሶን የሚገኙ ቅዱሳ፣ በዚያች ከተማ ዙሪያ ለሚኖሩ ወገኖች፣ ደግሞም እስከ ንጥቀት ድረስ በዚህ ምድር ላይ ላሉት ቅዱሳን ሁሉ እንደሆነ የደብዳቤው ይዘት ያመላክታል። እዚህ ላይ ሳልጠቅሰው ማለፍ የማልፈልገው ጉዳይ ቀደም ብለው በነበሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች ላይ "በኤፌሶን ለሚገኙ ቅዱሳን" የሚል ሐረግ ስለሌለ ይህ መልዕክት በትንሿ ኤስያ አከባቢ ላሉት ቅዱሳን ሁሉ የተላከና እየተዘዋወረ የሚነበብ መልዕክት ነው የሚሉ ወገኖች ብዙ ናቸው። በእኔ ምልከታ ለኤፌሶን የሚል ቀጥተኛ አድራሻ ቢኖረውም ባይኖረውም በመልዕክቱ አስፈላጊነትና ተደራሽነት ላይ አንዳች ተጽዕኖ ይኖረዋል የሚል ግምት የለኝም። ሐዋሪያው ጳውሎስ ተደራሲያኑን ቅዱሳን ብሎ ነው የሚጠራቸው። ቅዱስ መባል እኛ የሰራነው ገድል ተመዝኖ የሚሰጠን የማዕረግ ደረጃ ሳይሆን በክርስቶስ የቤዛነት ሥራ አምነው በመንፈሱ ታትመው በእውነተኛ ጎዳና ላይ በፀጋው እየተጓዙ የጌታቸውን መመለስ ለሚናፍቁ ሁሉ የተቸረ ስምና የማንነት መገለጫ ሥም መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። በመጨረሻም ለእነዚህ ቅዱሳን ፀጋና ሰላም ይብዛላችሁ ካለ በኋላ የደብዳቤው ማዕከላዊ እውነት ወደ ሆነው በሰማያዊ ስፍራ የተባረክንበትን መንፈሳዊ በረከት በመግለጽ ይቀጥላል። መንፈሳዊ በረከት ሁሉ ስንል እግዚአብሔር አብ በልጁ ሞት በኩል ለአማኞች ሁሉ የሰጠውን የቤዛነት ሥራ የሚያጠቃልል ንግግር ነው። ሐዋርያው በሚቀጥሉት ቁጥሮችና ምዕራፎች ላይ በድነቱ ፕሮግራም ውስጥ የሥላሴን ድርሻ በሚገባ ይተርካል። እግዚአብሔር አብ የድነት እቅድ ጠንሳሽ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ የእቅዱ ፈጻሚ፣ መንፈስ ቅዱስ የድነቱ ሥራ በአማኞች ሕይወት ውስጥ በማተም የበረከቱ ተካፋዮች እያደረጉን እንዳለ መገንዘብ ይቻላል። ጌታች ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ካልመጣ በሚቀጥሉት ቀናት ይህ በረከት እንዴት በዝርዝር እንደ ተገለፀ፤ እንዲሁም በሕይወት እስካለን ድረስ ይህንን በረከት እንዴት በምድር ላይ መግለጽ እንደሚገባን እናያለን። 🛃 ዛሬ የማሰላስለው የቃሉ እውነት፦ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የተባረኩ ሰው ነኝ! 🅿️ የዛሬው ፀሎቴ፦ "እግዚአብሔር ሆይ በልጅህ በክርስቶስ በኩል በሰማያዊው ስፍራ እኔን የባረክበትን መንፈሳዊ በረከት መረዳት እንድችል አእምሮዬን ክፈትልኝ" ነገ እስከምንገናኝ ደህና ሁኑ!! 🖋 ባይሣ ገመቹ ሰኔ 10, 2014 💎💎💎💎 ⒶⓇⓉⒾⓄⓈ 💎💎💎💎 💎💎💎💎 ⒶⓇⓉⒾⓄⓈ 💎💎💎💎 🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔻 @artios_media @artios_media @artios_media
Mostrar todo...
➪#በውስጤ_ያለው ኧረ! ይሔ መዝሙር መንፈስ ቅዱስን በሌላ መጠን እንድወደው እያደረገኝ ነው ሰምታቹ ተባረኩበት 😭😭😭እኔን የሚወደኝ መንፈስ ቅዱስ ነው😭😭❤️❤️ 👉#ዘማሪት_ዘርፌ
Mostrar todo...
08_track_Bewste_yalew_zerfie_kebede_official_Amharic_Iyrics_song128k.m4a4.64 MB
👉ሐዋርያት የተሰደዱበት እውነት 👉መንፈስ ቅዱስ በሰዎች አልፎ የሚመሰክረው ሃቅ 👉ከእግዚአብሔር የተወለድንበት መሠረት 👉አለምኔ ያሸነፍንበት ምስጢር
Mostrar todo...
ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው
Mostrar todo...
እውነት ነው የጸደቅነው በደሙም ነው በትንሳኤውም ነው። ታዲያ እንዴት እናስታርቃቸዋለን ካልን መልስ የሚሆነው ኢየሱስ እኛን ለማጽደቅ ሲል በመስቀል ላይ ያፈሰሰውን ደም ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ይዞ መግባት ነበረበት ፤ ሊቀካህን በአደባባይ ላይ የተሰዋውን የኮርማ ደም ይዞ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ባይገባ ስለ ሕዝቁ እንዴት ስርየት ሊያስገኝ ይችላል? ደሙስ በስርየት መክደኛው ላይ ካልተረጨ የሕዝቁ ሐጢአት እንዴት ይከደናል? ለዚህ ነው በመስቀል ላይ የኢየሱስ ደም መፍሰሱ አይደለም ያጸደቀን ያልኩት በመስቀል ላይ ስለ ሐጢአታችን ዕዳ መስዋዕት በመሆን ደሙን አፍስሶልናል ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ያጸድቀን ዘንድ የአዲስ ኪዳን ሊቀካህን የሆነው ኢየሱስ በእጅ ወዳልተሰራችው እውነተኛ ድንኳን በመስቀል ያፈሰሰውን የእራሱን ደም ይዞ በመግባት ደሙን በአብ ፊት ሲያሳይ እግዚአብሔር ጻድቅ መሆናችንን አወጀልን ስለዚህም በእርሱ በኩል የሚመጡትን በፈሰሰው በበጉ ደም የሚታመኑትን ፈጽሞ እንደሚያድናቸው ቃሉ ይነግረናል። ነገር ግን ኢየሱስ ደሙን ወደ ሰማያዊቷ ድንኳን ይዞ እነንዲገባ ከሙታን መነሳት ነበረበት ስለዚህ በትንሳኤው ወደ አብ የእራሱን ደም ይዞ በመግባቱ አጽድቆናል። ስለዚህ ጽድቃችነ በደሙ እና በትንሳኤው ሆኖልናል።
Mostrar todo...
🎁ጽድቃችን በምን?🎁 ✍በሮሜ 4:25 ላይ ኢየሱስ እኛን ስለ ማጽደቅ ከሞት እንደተነሳ የእግዚአብሔር ቃል ይናገራል። " ስለ በደላችን አልፎ የተሰጠውን እኛን ስለ ማጽደቅም የተነሣውን ጌታንችንን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው ለምናምን ለእኛ ይቈጠርልን ዘንድ አለው። (ወደ ሮሜ ሰዎች 4:24-25) ✍ሮሜ 5:9 ላይ እኛ የጸደቅነው በኢየሱስ ክርስቶስ ደም እንደ ሆነ የእግዚአብሔር ቃል ይነግረናል። " ይልቁንስ እንግዲህ አሁን በደሙ ከጸደቅን በእርሱ ከቍጣው እንድናለን።" (ወደ ሮሜ ሰዎች 5:9) 👉 ታዲያ የጸደቅነው ኢየሱስ ከሞት በመነሳቱ ነው ወይስ በደሙ ነው? 👉በእርግጥ ይሄ ሁለቱ ሀሳብ ይጋጫሉን? 👉የማይጋጩ ገለጻዎች ከሆኑ እንዴት እናስታርቃቸዋለን?
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.